ሕልም አልሜ[1]
በጨለማው ለሊት ሕልም አልሜ፣
የራሴን ሃሳብ ጨምሬበት አቅልሜ፣
በመንገድ ላይ ቀረሁ ተልሜ።
ሕልሜን አልሜ ሳልጨርስ፣
ነገር ተነሳብኝ የሚወስውስ፣
ሕልሜን ካለበት የሚያቃውስ።
ሕልሜ ህልም ብቻ ሆኖ እንዲቀር፣
እኔ እራሴ በህልሜ ላይ እያወጣሁ አቃቂር፣
ለነገሩ ምንም ባደርግ ህልሜ እንደሆነ አይቀየር።
አንድ ቀን ተስፋ ሳልቆርጥ ተነሳሁ አስልሼ፣
ሕልሜን ከግብ ለማድረስ ሃይል ተላብሼ።
ሕልሜ በቦታው እንደሆነ አረጋግጬ፣
ተነሳሁ እንደገና በብሩህ ተስፋ አጊጬ።
ተስፋ መቁረጤ ከውስጤ ተነነ፣
ሕልሜ በፈጣሪዬ እርዳታ ተከናወነ፣
ውስጤ በንቃት ተሞላ ከእንቅልፍ እንደባነነ።
ሕልሜን ላሳካልኝ ፈጣሪዬ ምስጋና ይድረስው፣
ሕልሜ ህልም ብቻ ሆኖ እንዳይቀር ለኔ ለደረስው፣
እኔ የምልህ!
ሕልምህ መሳካቱ ላይቀር፣
ሕልምህን አታደብዘዘው እያወጣህለት አቃቂር።
0 comments:
Post a Comment