እራስ ወዳድ[1]
የራስ ወዳዱ የይቀኑ ትልሙ፣
እራሱን ማደስት ሆኖ ቀረ ሕልሙ።
እራሱን ለማስደስት ሆነና ሙከራው፣
ወዳጆቹን ማሳዘን ሆኖ ቀረ አላማው።
በአስመሳይነቱ እራሱን ሽፍኖ፣
ለባህሪው ሽፋን ቃላትን ተክኖ፣
የጓደኛውን ፍላጉት ሳይረዳ ቀርቶ፣
እራስ ወዳድ ተግባሩን አራመደ አብዝቶ፣
ተራው ደረስና ማንም ሳይረዳው ቀረ ተንከራቶ።
እኔ የምለው!
ወንድሜ ልምከርህ እራስ ወዳድ መሆን አያዋጣምና፣
ለሌሎች በማስብ ነፍስ ዘርተህ ኑሮ ጀመር እንደገና።
0 comments:
Post a Comment