የምዬን ላብዬ
አይ የኔ ነገር መደነባበሬ፣
የማይወደድ አመል ላይጠቅመኝ አዳብሬ፣
በባዶ ቀረሁ እንደው ተደናግሬ
የሚያስከልብኝን ሳልረዳ ቀረቼ፣
በሃሳብ እንደወጣሁ ቀረሁ ተንከራትቼ።
የምዬን ባብዬ ላይ ባላላክክ ኖሮ፣
አይገጥመኝም ነበረ መላ ያጣ ኑሮ፣
ካፌ አይወጣም ነበር የሃዘን እንጉርጉሮ፣
የምዬን ባብዬ ላይ ማላከኩን ትቼ፣
አሽሙርና ቧልትን እረስቼ፣
ከተጠናወተኝ አመል አንስራርቼ፣
በጥሞና ልኑር አመሌን ስርቼ።
እኔ የምልህ!
አይበጅህምና  የምዬን ባባዬ ላይ ማላከኩን ትትህ፣
በቀደሞውን ስህተትህን እረስትህ፣
በጥሞና ለመኖር ሞክር ያለፈውን እረስተህ።






0 comments:
Post a Comment