Thursday, February 16, 2023

 

ተራራዬ[1]

የወይን ሐረግ ፍሬ ሳያፈራ፣

ችግሬ ቆሞ አየሁት እንደተራራ፣

ተራራዬን መግፋት ተነሳሁ ሳልፈራ።

ተራራዬን የምገፋበት ስሌት፣

ተግቼ ስራሁ ቀን ከሌት፣

ጀመርኩ ተራራዬን ልገፋ፣

ያለ የሌለ ሃይሌን ተጠቅሜ ልለፋ፣

ተራራዬ ከፊቴ ቆሞ ኑሮ አይገፋ።

የችግሬን ተራራ ዳር ዳሩን ዞሬ፣

መፍትሄ ሳላገኝ እንደዚሁ ቆየሁ እስከዛሬ።

ድምጽ አወጣሁ ተራራዬን ተናገርኩት መዞሬን አቆሜ፣

ድምጽ ማስማት ስለሆነ አቅሜ።

ተራራዬን  ከፈጣሪ አቅም አግኝቼ ከገፋሁ፣

ከአሽናፊዎች መካከል እሆናልሁ እንጂ  ምንም አልተረታሁ።

 



[1] በዶ/ር አመለወርቅ ሥዩም 2023

0 comments:

Post a Comment