Tuesday, February 7, 2023

 

ታሪክህን አገላብጥ[1]

እረ የህገሬ  ስው ታሪክህን አገላብጥ አትሁን ተላላ፣

በጠብ በክርክር በጦርነት  ጉልበት አይላላ፣

አንድነትህን ጠብቅ  እንዳትሆን ቅራሬና አተላ።

የዘመኑ ትውልድ  ተነሳ ታሪክህን አንብብ፣

ሆነህ አንዳትቀር ሳይሞቅ ፈላ ነገረ ቅልብልብ።

ስከን ረጋ በል ዙሪያህን ተመልከት፣

ሥልጣን ለማግኘት ብልህ እንዲሁ አትዋትት።

ልምከርህ ሩጫህ አላማ ይኑረው፣

የአባቶችህ ታሪክ የሚደግፈው፣

አልያማ አስተውል  አላማ ቢስ ሩጫህ ምን ፋይዳ አለው።

አንዲሁ ከቀጠልክ ሌላውን አጥፍተህ አንተም ትጠፋለህ፣

አላማህ ሳይሳካ ዋትህ መንገድ ተቀራለህ።

ቂምና በቀልን ዘረኝነትን ወደህዋላ ትተህ፣

የፍቅርና የአንድነትን ስንደቅህን አንስተህ፣

ተነሳ ወጣቱ ስላምን ፍጠር በአንድነት ተነስተህ።

እኔ የምለው፣

እንደው ለመሆኑ ሳይገባህ ቅርቶ ነው፣

ሀገር ከፈረስ ወዴት ልትገባ ነው፣

ሀገርን መጠበቅ ያለብህ ለራስህ ብለህ ነው።

 

 

 



[1] በዶ/ር አመለወርቅ ሥዩም 2023

0 comments:

Post a Comment