Wednesday, August 10, 2022

 

የሞት ጎዳና እንዳልጀምር[1]

በወጣትነቴ አስተዋይ የሆንኩ መስሎኝ፣

ልጅ በልጅነት ነው ብዬ ጸነስኩኝ፣

አይ! የኔ ነገር የሚያስከተለውን አላወኩኝ፣

ልጅ መውለዴ በማር የተለወስ እሬት ሆነብኝ።

አልገባኝም እንጂ ችግሬ የጀመረው ገና ሲረገዝ  ነው፣

ምጥ ሲጀምረኝ መጥፊያዬ ሊሆን ነው።

ችግሬን ያዩ ሐኪሞች ተስበስቡና፣

ለገዋን ወጣት በወሊድ ስትሞት አናይም አሉና፣

ተነሱ ሊያክሙኝ አንዳልጀምር የሞትን ጎዳና፣

ትዕይንቱን ጀመሩ ሐኪሞች ተዋናዮች ሆኑና።

በአልጋ ላይ አጋደሙኝ፣

አፌን በአንስቲዚያ ልጉዋም አስሩኝ፣

አዚያው እዳለሁ ደነዘዝኩኝ፣

እነርሱም ሥራቸውን ቀጠሉና፣

ልጁ ተወለደ በጥገና።

እኔም የሆነብኝን አልተረዳሁ፣

ለካስ በሞት ታናሽ ወንድም ተይዤአለሁ።

ለቀናት የት እንዳለሁ አላወቅሁ፣

ስነቃ ግን በህመሜ ተስቃየሁ።

ከቀን ወደ ቀን ሕመሜ ሄደ እየጠነከረ፣

ጨንቀኝ የት ልግባ ነገሬ ከረረ።

የአልጋ ቁራኛ እንዳልሆን ፈራሁና፣

ወደ ፈጣሪዬ አንባዬን አፈስስኩ እንደገና፣

ጌታም ፈወስኝ እራራልኝና።

እኔ የምልሽ!

የፈጣሪ እርዳታ ካስፈለገሽ፣

በስው የማይፈታ ችግር ካለሽ፣

ወደ ፈጣሪ ጸልይ እንዲረዳሽ።

 

 

 



[1] በዶ/ር አመለወርቅ ሥዩም 2022

0 comments:

Post a Comment