አትዘናጋ[1]
ስዎች ዝም አትበሉ ዘመኑ እየከፋ መጣ፣
ስውም ሆነ ፈጣጣ ቅጥ ያጣ፣
ይባስ ብሎ እርስ በርሱም ሆነ ባላንጣ።
ዘመን ተጠቅልሎ ፍርድ ከመምጣቱ በፊት፣
በእግዚአብሄር ዙፋን ፊት ከመቅረብህ በፊት፣
ስላም ፈጠር አድርገህ በራስህ ላይ ግፊት።
በህሊናህ ተዳኝተህ አድርግ ከራስህ ጋር እርቅ፣
እድሉን ቸል ብለህ በችግር ሕይወትህን አታድቅ።
በችግር መድቀቅን ማን ይፈልገዋል፣
በበሽታ መመታትን ማንስ ይመርጠዋል።
ባመጣኸው መዝዝ አንዳትጠላለፍ፣
ትንሽ ባሃሳብህ ካለህበት እለፍ።
እደግ በረታ ስው ሁን አትሁን ተላላ፣
ሆነህ እንዳትቀር ሃሳበ ቀውላላ፡፡
ወገኔ እደግ እንጂ ጫጭትህ ትቀራላህ፣
ከክፉ መልካምን መምረጥ ካስኘህ።
መልካም ተግባራትን ሽማህ አድርጋቸው፣
በመከራ ዘመን ከሞት እንድትድንባቸው።
የፈተና ወቅት ማቆም የሚቻለው፣
ጌታ ለስው ልጆች አዝኖ ፈውሱን የሚያስፍነው፣
በተግባር ወደ ፈጣሪህ ከተመለስክ ነው።
አባክህ ወዳጄ ቀኖች እየቀጠርክ አትዘናጋ፣
ወደ ፈጣሪህ ተመለስ ዘመን ሳይዘጋ።
______________________________
0 comments:
Post a Comment