Monday, August 1, 2022

 

ምርኩዜ[1]

የስውን ምርኩዝ ፈልጌ፣

ቁጭ ብድግ ማለት ጀመርኩ አደግድጌ።

ምርኩዝ ፍለጋ ላይ ታች አልኩ፣

ወጣሁ ወርደኩ እንጂ ምንም አልተጠቀምኩ።

አማራጭ ምርኩዝ ተመለከትኩ፣

ግንዝብን ምርጫዬ አድርጌ ወስድኩ፣

ያም አልጠቀመኝ እንዲያው ተብክነክንኩ፣

ይህም ሆኖብኝ ተስፋ አልቆረጥኩ።

ፍቱን ምርኩዝ ለማግኘት ተነሳሁ አስልሼ፣

በውሳኔዬ ለመጽናት እንዳላስብ ቀልብሼ።

ቀልብሶ ማስብ አስፈርቶኝ፣

መሥራት ጀመርኩኝ ምርኩዝ አጥቼ አንዳልገኝ፣

ፈጣሪዬ ግን እራርቶልኝ ምርኩዜ እንደሆነ ገለጠልኝ።

ፈጣሪዬ አንተ ለኔ ምርኩዜ ከሆንክማ፣

ልኑር በምድር ላይ ሳላቅማማ።

አንተ ለኔ ጽኑ ምክኩዝ ባንትሆን ኑሮ፣

ባዶዬን ቀርቼ ነበር አምናና ዘንድሮ።

ካሁን በኋላ ምርኩዜ አንተ ነህ፣

ቀልብሼ አንዳላስብ እርዳኝ እባክህ።

እኔ የምልህ!

የስው ምክኩዝ ካላገኘህ፣

የገንዘብ ምርኩዝ ካበከንህ፣

ወደ እውነተኛው ምርኩዝ ተመለስ  ተነቃቅተህ።

 



[1] በዶ/ር አመለወርቅ ተገጠመ 2022

0 comments:

Post a Comment