ሲሮጡ የታጠቁት ሲሮጡ ይፈታል[1]
የሕይወት ሩጫ ስንቱን አካለበ፣
ሳይሞላ የሃሳቡ እንደው ኮበለለ፣
ሮጦ ሮጦ እንደው መና ሊቀር ምነው ተዋከበ።
መሮጥ ብቻ ሆነ የየለት ቀልቡ፣
እንዲያው ይሮጣል እንጂ አይደለ ከቀልቡ፣
እንደው ብቻ መሮጥ ሆነ ሳይሞላ የልቡ።
ባሉበት ከመቀመጥ ሩጫ ያዋጣል፣
በደፈናው ሩጭ ግን ዋጋ ይስከፍላል፣
ከመንገድ አውጥቶ ያደናግርሃል።
በጭፍን ሩጫህ ጀመርህ ከሆነ፣
የትም ሳያደርስህ ጊዜህን እንደው አባከነ።
የህይወት ሩጫን ስትሮጥ አላማ ይኑርህ፣
ከግብ ትደርሳለሁ ማንም አያቆምህ።
አትሩጥ ብቻ ወደላይ አንጋጥ የተባለውን ዘንግቶ፣
ሩጫ ብቻ የሚያወጣው እንደሆነ በሃሳቡ አጉልቶ፣
የቸኮለ አፍሳሶ ለቀመ የተባለው እርስቶ፣
እረ ስንቱ ከመንገድ ላይ ቀረ እንደው ተንገላቶ።
ሲሮጡ የታጠቁት ሲሮጡ ይፈታል፣
ሩጫ ያለቦታው እረ ያንግላታል፣
በርጋታ የተሮጠው ሩጫ ከአላማው ያደርሳል።
እኔ የምለው!
ሲሮጡ የታጠቁት ሲሮጡ ይፈታል የሚለው አባባል የገባህ ከሆነ፣
የሩጫህን ስሌት ቀይር ምን ይቸግርሃል ጊዜህ አልባከነ?
0 comments:
Post a Comment