Tuesday, July 12, 2022

 የቸገረው እርጉዝ ያገባል[1]

የቸገረው እርጉዝ ያገባል ተምሳሌቱ፣

የተባለ  ይመስላል ለተቸገሩቱ።

የተምሳሌቱን አባባል ሳጠና፣

የችግሩን መንስ ላቃና።

ብዙ ሞከርኩ ተምሳሌቱን ላስላ፣

 የተባለው ለሚጉላሉት እንደሆነ በአበሳ።

ችግረኛው ከችግሩ ለመወጣት ተነሳና

በችግር ላይ ሌላ ችግር ጨመረና፣

መቃኘት ጀመረ ህይወቱ እንዲቃና።

ከችግሩ ለመውጣት አስልቶ ተነሳ፣

ታዲያ ምን ያደርጋል መፍትሄ  ያለው ገምቶ አነሳ።

እርጉዝ ማግባት ችግሩን ያቃለለ መስሎት፣

በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ መሆኑን አረስቶት፣

መፍትሄ ያለው ምርጫ ተስፋውን አሟጦት፣

ድብርትና ሀዘን ብቻ ሆኖ ቀረ የርሱ ቅንጦት።

ተመከር ወንድሜ እንደው በጭፍንህ አትፍጠር ግርግር

መለስ ታገኛለህ አጥርተህ ማየት ስትጀመር።

የችግርህ መፍትሄ   ከፊትህ ላይ አለ፣

ካላነሳኸው ግን  በመጣበት እግሩ ሄደ ኮበለለ።

እኔ የምለው!

የችግርህን መፍትሄ አውቀህ፣

አጥረተህ ማየት መፍትሄ ካስገኘህ፣

እረ! ልጠይቅህ መፍትሄ ነው ብለው ለምን እርጉዝ ታገባለህ?

በችግር ላይ ችግር መጨመር መሆኑን ታውቃለህ?




[1][1] በዶ/ር አመለወርቅ ሥዩም ተገጠመ 2022

0 comments:

Post a Comment