የላይኛይቱ ጥበብ[1]
ፈጣሪ አወጣ ጥበበኛ ስልቱን፣
ለስው ልጆች ስለሆነ ፍቱን።
ፈጣሪ ምድርን በጥበብ መስረተ፣
በስው ልጆች ክፋት ምነው አልታከተ።
በማስተዋሉም ስማያትን አጸና፣
በምድር የስው ልጅ ኑሮው እንዲቃና፣
በየዘመናቱ የሆነው ገናና።
በጥበብ ቀላያቱን ቀደደ፣
ፍጡር ሁሉ በቀላያቱ ቀረ እየተስተናገደ።
ደመናቱ ጥልን ያንጠባጥባሉ፣
የፈጣሪያቸውን ድንቅ ሥራ አብረው ያሳያሉ።
አንተም ጥበብን ሳትዘገይ ፈልጋት፣
አይንህ እንዲከፈት እንድታይ በጥራት።
በማስተዋልም ድምጽህን በታነሳ፣
ጥበብን ለመፈለግ ቆርጠህ ብትነሳ፣
ከሥራትህ ወጣህ እንዳትሆን አንካሳ።
ጥበብን እንደብር ፈልጋት፣
ያኔ ፊትህ ያበራል እንደ ጠዋት ንጋት።
ጥበብ ፈቅደህላት ወደ ልብህ የገባች ለታ፣
ትፈነድቃለህ ነፍስህ ደስ ተስኝታ።
0 comments:
Post a Comment