Tuesday, June 28, 2022

 

 የፍቅር ሃይል [1]

የፍቅር ሃይል ሕይወት ይለውጣል፣

ለተጠቀመበት ሁሉ ብርታትን ይስጣል።

የፍቅርን ሃይል ስዎች ሳይረዱ ቀርተው፣

የፍቅርን ውጤት ሳያዩት አርቀው፣

በሜዳ ላይ ቀሩ እንደው በሃሳባቸው ተንቀዋለው።

የፍቅር  ሃይል ከሞት ያድንሃል፣

ለፈጣሪ ቅርብ ሁን  ፍቅሩን ያልብስሃል።

ይኽኔ የፍቅር ጮራ በህይወትህ ፈንጥቆ፣

ጥላቻህ በፍቅር ተውጦ፣

አይንህን ታነሳለህ በፍቅር ተመስጦ።

ፍቅርን  ለስዎች ስጥ ያለመታከት፣

ያኔ  ታድናቸዋለሁ ከታስሩበት እክት።

እራስህን አበርታ ለመሆን የፍቅር ወገን፣

አንዲያው አትቀርም ታገኛለህ የህይወት መጠገን።

ፍቅር የሚያለመልም የህይወት መዳኛ፣

ስዎችን ታደገ ክሙታን መገኛ።

ተመተው እንዳይቀሩ በክፉ መጋኛ።

ወገኔ ትብያህን አራግፈህ ፍቅርን ተላበስ፣

ሆነህ እንዳትቀር እንደው በዋል ፈስስ።

በዘፈቀደ መኖርህ አብቅቶ፣ 

ተነሳ ወገብህን ታጠቅ በፍቅር ቀበቶ፣

እኔ የምለው!

የፍቅር ጉልበቱ ካየለ፣

ትሩፋቱም ህይወትን ከክለለ፣

ለምን ባንተ ዘንድ ትርፉ ተቃለለ።

 

 



[1] በዶ/ር አመለወርቅ ሥዩም ተገጠመ 2022

0 comments:

Post a Comment