ቅንነት ከስመ[1]
ቅንነት ከስው ውስጥ ከጠፋ ቆይትዋል፣
በዘመናችንም ችግር አስከትልዋል።
ቅንነት ከስው ውስጥ በመጥፋቱ፣
ስው ተዳረገ ለህሳቤ
ከንቱ።
ስው እንደእባብ ብልህ እንደ እርግብ የዋህ የተባለውን ሳይረዳው ቀርቶ፣
ስንቱ ተዳረገ ያለማወቁ ሆኖበት ማነቆ።
ልበቅኖች ፈጣሪን ያዩታል የተባለውን ረስቶ፣
መዳከር ጀመረ ከችግር ውስጥ ገብቶ።
ሕሊናው ጨለመ ቅንነቱ ከሰመ፣
ችግሩን አገዘፈው እንጂ ምንም አልከተመ።
ሕሊናው ጨልሞ ሃሳቡን አዛባው፣
ከቅን ሃሳብ ይልቅ ክፉን አስለቀመው።
ክፋት አይሎ ቅንነት ደብዝዞ፣
ሰው አሳልፎ ስጠ እራሱን እንዲኖር በሃጢያት ደንዝዞ።
እኔ የምለው!
ስው ክፋት ተንኮል አያዋጣም ብሎ፣
ምናለ! የስው ልጅ ይህን ችግር ባያየው አቅሎ፣
እንዳይቀረ በሃሳብ እንደው ተቀዋሎ።
0 comments:
Post a Comment