የፍቅር አርጪሜ[1]
ባል ሆይ! ሴትን ቀላል ፍጥረት አረካት፣
የለበጣ ፍቅር ስጠሃት፣
ሳትረዳት ቀርተህ ፍቅር አሳጣሃት፣
ባሌ! አይወደኝም ብላ ውስጥዋ ተበሳጨ፣
ላንተ ያላት ፍቅር ሄደ እየቀጨጨ።
ጥልና ንትርክ ውስጥዋ አበቀለ፣
ያንተን ፍቅር ለማግኘት ንትርክዋ ቀጠለ።
መፍተሄ አድርግ እንጂ እንዲሁ አታለም።
ፍቅርህ ደብዛው ጠፍቶ እንዳይልብህ እልም።
የስላም ኑሮ ለመኖር ከሆነ ህልምህ፣
አረሙን ለመንቀል ብዙ ሥራ አለብህ።
የደባል ኑሮና ጭቅጭቅዋ ከስለቸህ፣
የሚስትህን ልብ በፍቅር አርጪሜ አቅልጠህ፣
ፍቅርህን ተግባራዊ አድርገህ፣
ከቁጣዋ ፈረስ ላይ አውርደህ፣
ያኔ ስላም ታገኛለህ ለመኖር እርግተህ።






0 comments:
Post a Comment