በዶ/ር አመለወርቅ ሥዩም ተገጠመ 2021
ፍቅር ወዴት ነህ?
ፍቅርን መፈለግ ከጀመርኩ ከረምረም ብዬአለሁ፣
ወጣሁ ወረድኩ እንጂ ምንም አላገኘሁ።
ተስፋ አልቆርጥ ብዬ ፍለጋ ተነሳሁ እንደገና፣
ግራ ቀኝ ተመልክቼ ፍቅርን ፈልጌ አጣሁት፣
ተስፋ ሳልቆርጥ መላልሼ ፍቅርን ጠራሁት።
አረ! ፍቅር ወዴት ነህ ብዬ ስጣራ፣
ምንም በሌለበት በቀነ ጠራራ፣
ሀሩሩና ሞቃት ውሽንፍሩ ሲነፍስ ለስው ሳይራራ፣
ፍቅር ድምጽ አውጥቶ ተናገረ በቀነ መከራ።
እንደው ተፈልጊኛለሽ እኔን አታገኚኝም፣
እኔ የነበርኩት በድንጋይ ዳቦ ጊዜ ፣
አንቺ የምትጣሪው ዛሬ፣
ለምን ጠርተሽ ታስቸግሪኛለሽ በዘመነ ኩነኔ።
አታውቂም እንዴ እኔ እኮ ሕያው ነኝ፣
በስው ልብ አልኖርም ካልተፈቀደልኝ።
ከመጤዎች ማህበር ከራቅሁ ከርሜአለሁ፣
ቀረ በነያእቆብ ጊዜ በድርጊት ከመጣሁ ፣
ስው ፈቅዶ ከልቡ አስወጣኝ፣
ወደመጣሁበት ጉዞዬን ጀመርኩኝ፣
ስትጠሪኝ ጊዜ አሳዘንኝሽና መጣሁ ተመለስኩኝ።
እስቲ ልጠይቀስ ለምንስ ጠራሽኝ?
አንቺም ፍቅር ርቆሽ ተቸግረሽ ይሆን?
እኔም አይ! ፍቅር ከኔ አልራከኝም፣
አንተ ግን ፍቅር ከስው ርቀህ ስላየሁ፣
ከፍቅር እርቆ የሚኖረውን ሕዝብ ጉዳቱን ስላየሁ፣
ይኸው ችግር በኔ እንዳይደገም አጥብቄ ተጣራሁ፣
አሁን መልሴን ካንተ አግኝቼአለሁ ምን እፈልጋለሁ።
ከአሁን በህዋላ ፍቅር እንዳትርቀኝ፣
በልቤ ጽላት ውስጥ ሥፍራ እስጥሃለሁ፣
አዎን! የልቤ ማህተብ አድርጌ በውስጤ አኖርሃለሁ፣
ቅዱስ ያዕቆብ እንዳለው በተግባር እገልጽሃለሁ፣
ያን ጊዜም ሕይወት ከኔ ጋር እንዳለ አረጋግጣለሁ።
ፍቅር አንዴ ላስቸግርህ?
በመጤዎች የልብ ደጃፍ ያለፍክ ለታ፣
መጤ ነኝ ብላችሁ ተው አትኩራሩ አትታለሉ፣
"ፍቅር የሌለው ክርስቶስ የለውም" እንዲል እወቁ።
ያለፍቅር ጎዞ አያዋጣምና፣
መጤዎች ግቡ ወደ ፍቅር ጎዳና፣
የስበካችሁትን ኑሩበት ቁሙ እንደገና።






0 comments:
Post a Comment