Friday, January 29, 2021

 

 የፓስተሩ ሚስት

አቤት! የፓስተር ሚስት መሆን እንዴት ያስደስታል፣

ከሽለቆ አውጥቶ በከፍታ ሥፍራ ያስቀምጣል፣

በከፍታ ሥፍራ የተቀመጠችው፣

አርአያ ለመሆን የተመረጠቸው፣

በምዕመኖችዋ የተከበረችው፣

በቤተስብዋ የተወደደቸው፣

በፓስተሩ ባልዋ የተደነቀችው፣

ከድባቴ ውስጥ ገብታ እራስዋን ለምን አገኘችው?

አይ ስው! ያላወቀላት በቸኛይቱ፣

ብቻዋን መሆንን ባዘወተረች ጊዜ፣

አቤት! ተጋለጠች  ለሃዘን ለትካዜ፣

ፓስተሩ ቀን ከሌት በአግልግሎቱ ተጠመድኩ እያለ፣

ክስልክ ላይ ተጥዶ ውሎ ስላደረ፣

ሚስቲቱ ብቸኝነት ተጫናትና፣

ወደ ውጪ  ወጣ አለች አራስዋን ልታጽናና፣

የጉድ ሀገር ግንፎ እያደር ይሞቃል እንድተባለው፣

ፓስተሩ ባስበት ባህሪው ተለወጠ ከቀድሞው፣

ንግግርም የለ ፍቅር ቀዝቀዝ ከመካከላቸው፣

አንድ ነብስ መሆን ቀርቶ ተለየ አልጋቸው፣

ባንድ ጣራ ይኖራሉ እንጂ ልዩ ነው ልባቸው፣

ለየቅሉ ሄዱ ክፍተት ስለመጣ በየመንገዳቸው፣

አይ! ብቸኛይቱ የሃሳብ ስመመን የሚያስቸግራት፣

በመንፈሳዊነት ታስራ ችግር የሚያንገላታት፣

ችግርዋ አይሎ ወደ ታች ተጫናት፣

ታዲያ በዚህ ወቅት ማን ይድረስላት?

አወይ! የስው ነገር  ከምዕመኖችዋ ማንም አልተረዳት፣

አባክህ ፈጣሪ አንተ ድርስና ከችግርዋ አውጣት።



በዶ/ር አመለወቅ ሥዩም ተገጠመ 2021

 

0 comments:

Post a Comment