ስለ ስው ጤና መጽሐፍ ቅዱስ የሚለው
እግዚአብሄር ለሰውነታችን የምናደርገው
እንክብካቤ ያሳስበዋል? “ብዙ የወይን ጠጅ ከሚጠጡ፣ ሥጋ ከሚሰለቅጡ ጋር አትወዳጅ።” ምሳሌ 23:20። ይህን ማወቅ ለምን አስፈለገ? መጽሐፍ ቅዱስ የሕክምና መጽሐፍ አይደለም፤ ደግሞም
ሰዎች የሚያደርጉትን እያንዳንዱን ነገር የሚቆጣጠር መመሪያ አልያዘም። ያም ቢሆን እግዚአብሄር፣ ጤንነትን ስለ መጠበቅ ያለውን አመለካከት
የሚጠቁሙ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የሚገኙ ሐሳቦችን ማወቅ ይጠቅማል። መጽሐፍ ቅዱስ ለሰውነታችን የምናደርገው እንክብካቤ እግዚአብሄርን እንደሚያሳስበው
የሚጠቁሙ በርካታ ሐሳቦች ይዟል። ለምሳሌ ያህል፣ መጽሐፍ ቅዱስ ሆዳምነትንና ሰካራምነትን ጨምሮ ከልክ በላይ የሚደረጉ ጎጂ ነገሮችን
ያወግዛል። (ምሳሌ 23:20) እግዚአብሄር
ለጥንቶቹ
እስራኤላውያን በሰጠው ሕግ ላይ በሽታዎች እንዳይስፋፉ ለመቆጣጠር ከተቻለም እንዳይከሰቱ ለመከላከል መደረግ ያለባቸው ነገሮች ተካትተዋል።
በተጨማሪም ሕጉ በሰው ላይ ጉዳት የሚያደርሱ አደጋዎችን ለማስወገድ የሚረዱ የደህንነት መመሪያዎችን ይዟል። (ዘዳግም 22:8) ከዚህ
በግልጽ ለማየት እንደሚቻለው መጽሐፍ ቅዱስ፣ ሰውነታችንን እንድንንከባከብና ጤንነታችንን ለመጠበቅ አስፈላጊውን ነገር እንድናደርግ
ያበረታታል።
“በአንድ ሰው
አማካኝነት ኃጢአት ወደ ዓለም ገባ፤ በኃጢአትም ምክንያት ሞት መጣ።” ሮም 5:12። ሰዎች ደግሞ ብዙዎች
በሽታ ሰው በዝግመተ ለውጥ ሲገኝ በአጋጣሚ የተከሰተ ችግር እንደሆነ ያምናሉ። ሌሎች ደግሞ እንደ ክፉ መናፍስት ያሉ ሚስጥራዊ ኃይሎች
የጤና መቃወክ እንደሚያስከትሉብን አድርገው ያስባሉ። መጽሐፍ ቅዱስ፣ የምንታመመው የመጀመሪያዎቹ ባልና ሚስት በአምላክ ላይ በማመፃቸው
ምክንያት እንደሆነ ይናገራል። (ሮም 5:12) የመጀመሪያዎቹ ወላጆቻችን አዳምና ሔዋን በእግዚአብሄር ላይ ከማመፃቸው በፊት ፍጹም ጤንነት ነበራቸው።
አፍቃሪ የሆነውን አምላክ እንክብካቤ ካጡ እንደሚሞቱ ያውቁ ነበር። (ዘፍጥረት 2:16, 17) ይሁንና ሆን ብለው ከእግዚአብሄር ጋር እንዲቆራረጡ የሚያደርግ ነገር ፈጸሙ፤
በመሆኑም ፍጽምናቸውን አጡ። ፍጽምናቸውን ያጡት
የመጀመሪያዎቹ ወላጆቻችን ለእኛም አለፍጽምናን አወረሱን። በመሆኑም የጤና እክሎችን ለማስወገድ የቱንም ያህል ጥረት ቢደረግ መታመማችን
አይቀርም።
እግዚአብሄር ያወጣቸውን ጥበብ የሚንጸባረቅባቸው መመሪያዎች
በመታዘዝ ከእሱ ጋር እርቅ ከፈጠርክ ወደፊት ምድር ገነት ስትሆን ፍጹም ጤንነት አግኝተህ መኖር እንደምትችል መጽሐፍ ቅዱስ ያስተምራል።
(ኢሳይያስ 33:24) አምላክ ሕመምን፣ በሽታንና ሞትን ለማስወገድ ቃል ገብቷል። ራእይ 21:3, 4። መጽሐፍ ቅዱስ
የሕክምና እርዳታ ማግኘትን ይቃወማል? “ሐኪም የሚያስፈልጋቸው
ሕመምተኞች እንጂ ጤነኞች አይደሉም።” ማቴዎስ
9:12። ሰዎች ምን ይላሉ? አንዳንዶች የሕክምና እርዳታ ከማግኘት ይልቅ ሃይማኖታዊ ፈውስ
(ወይም የእምነት ፈውስ) ማግኘት የተሻለ እንደሆነ ይናገራሉ።
መጽሐፍ ቅዱስ
ምን ይላል? በጥንት ዘመን በነበሩ የእግዚአብሄር
ሕዝቦች
መካከል የጤና እርዳታ የሚሰጡ ሰዎች የነበሩ ሲሆን እግዚአብሄር ይህን ሙያቸውን አልተቃወመም። (ዘፍጥረት 38:28፤ ቆላስይስ
4:14) እነዚህ ሰዎች ለመድኃኒትነት የሚውሉ ተክሎችንና ቅባቶችን በመጠቀም እንዲሁም ለሕመምተኞቹ አንድ ዓይነት የአመጋገብ ሥርዓት
በማዘዝ ወይም በሌሎች የሕክምና ዘዴዎች ተጠቅመው ሕክምና በመስጠታቸው እግዚዝብሄር እንዳልተደሰተ የሚገልጽ ሐሳብ በመጽሐፍ ቅዱስ
ውስጥ አናገኝም። እንዲያውም ኢየሱስ “ሐኪም የሚያስፈልጋቸው ሕመምተኞች እንጂ ጤነኞች አይደሉም” ሲል ተናግሯል። ማቴዎስ 9:12። ይሁን እንጂ መጽሐፍ ቅዱስ ጤነኛ ለመሆን ማንኛውም ዓይነት
መሥዋዕት መከፈል አለበት የሚለውን አመለካከት አይደግፍም። ከዚህም
ሌላ በመናፍስታዊ ድርጊቶች አማካኝነት ፈውስ ለማግኘት መሞከር በእግዚዝብሄር ዘንድ ተቀባይነት የለውም። (ገላትያ 5:19-21)
የጤና እክል በሚያጋጥመን ጊዜ መጽሐፍ ቅዱስ በሚያወግዛቸው መንገዶች መጠቀም ተገቢ ባይሆንም የሚቻል ከሆነ ወዲያውኑ ጥሩ ሕክምና
ለማግኘት መሞከር የጥበብ እርምጃ ነው።
ጤናን በመንከባከብ ረገድ ቅዱስ ጽሑፋዊ አመለካከት ፦ “አንተም ጌታ
አምላክህን . . . በፍጹም ሐሳብህና በፍጹም ኀይልህ ውደድ።” ማር.
12:30 እግዚዝብሄር ሰብዓዊ ፍጡሮቹ
እንዲታመሙና እንዲሞቱ ዓላማው አልነበረም። አዳምንና ሔዋንን በዔድን የአትክልት ቦታ ማለትም በደስታ ገነት ውስጥ ያስቀመጣቸው ለ70
ወይም ለ80 ዓመታት ብቻ ሳይሆን ለዘላለም ‘እንዲያለሟትና እየተንከባከቡ እንዲጠብቋት’ ነበር። (ዘፍ. 2:8, 15፤ መዝ.
90:10) እነዚህ የመጀመሪያዎቹ ባልና ሚስት ለእግዚአብሄር ታማኝ ሆነው ቢዘልቁና
ለሉዓላዊነቱ በፍቅር ቢገዙ ኖሮ ጤና ማጣትንም ሆነ እርጅና የሚያስከትለውን ጉስቁልና እንዲሁም ሞትን ባላዩ ነበር። መክብብ ምዕራፍ
12 ፍጹማን ባልሆኑ ሰዎች ላይ ከእርጅና ጋር ተያይዞ ስለሚመጣው “የጭንቀት ጊዜ” ቁልጭ አድርጎ ይገልጻል። (መክብብ
12:1-7 ሽበት ‘ከለውዝ ዛፍ’ አበባ ጋር ተመሳስሏል። እግሮች፣ እየጎበጡና እየተብረከረኩ ከመጡ ‘ብርቱ’ ሰዎች ጋር ተመሳስለዋል።
የዓይን መዳከም፣ ብርሃን እናያለን ብለው ወደ መስኮት ሲመጡ ከጨለማ ሌላ ምንም ነገር ባላገኙ ወይዛዝርት መመሰሉ ትክክለኛ መግለጫ
ነው። የረገፉ ጥርሶች ‘ጥቂት በመሆናቸው ምክንያት መፍጨት ባቆሙ’ ሴቶች ተመስለዋል። የሚብረከረኩ እግሮች፣ የደከሙ ዓይኖችና ጥርስ አልባ የሆኑ ድዶች እግዚዝብሄር ለሰው ዘር
የነበረው የመጀመሪያ ዓላማ ክፍል አይደሉም። ከዚህ በተጨማሪ ከአዳም የወረስነው ሞት ‘ከዲያብሎስ ሥራዎች’ አንዱ ሲሆን የእግዚዝብሄር ልጅ በመሲሐዊ
መንግሥቱ አማካኝነት ያስወግደዋል። ሐዋርያው ዮሐንስ “የእግዚአብሔር ልጅ የተገለጠውም የዲያብሎስን ሥራ ያፈርስ ዘንድ ነው” ሲል
ጽፏል። 1 ዮሐ. 3:8
በአሁኑ ጊዜ አንዳንድ የእግዚአብሄር አገልጋዮች ኃጢአተኛ
በሆኑት የሰው ልጆች ሁሉ ላይ የሚደርሰው ከጤና ማጣትና ከእርጅና ጋር ተያይዞ በሚመጣው ችግር ይሠቃያሉ። እንዲህ ያለ ሁኔታ ሲያጋጥመን
ስለ ጤንነታችን በተወሰነ ደረጃ መጨነቃችን የሚጠበቅ ነገር ከመሆኑም በላይ ጠቃሚም ነው። ምክንያቱም የእግዚአብሄርን ‘በፍጹም ኀይላችን’
ማገልገል እንፈልጋለን። (ማር. 12:30) ይሁንና መጠነኛ ጤንነት እንዲኖረን ለማድረግ መጣራችን ተገቢ ቢሆንም እውነታውን መቀበል
እንዲሁም የእርጅናን ሂደት ለማዘግየት ወይም ፈጽሞ በበሽታ ላለመያዝ ማድረግ የምንችለው ነገር በጣም ውስን መሆኑን መገንዘብ ይኖርብናል። ብዙ ታማኝ የእግዚዝብሄር አገልጋዮች ከጤና ማጣት ጋር መታገል ግድ ሆኖባቸዋል። አፍሮዲጡ ከእነዚህ አንዱ ነበር።
(ፊልጵ. 2:25-27) የሐዋርያው ጳውሎስ ታማኝ ባልደረባ የሆነው ጢሞቴዎስ በየጊዜው የሚነሳበት የሆድ ሕመም ስለነበረበት ጳውሎስ
“ጥቂት የወይን ጠጅ” እንዲጠጣ መክሮታል። (1 ጢሞ. 5:23) ጳውሎስ ራሱም ቢሆን ‘የሥጋ መውጊያውን’ ችሎ ለመኖር ተገድዶ ነበር፤
ይህም በወቅቱ ፈውስ ያልተገኘለት የዓይን ሕመም ወይም ሌላ ዓይነት በሽታ ሊሆን ይችላል። (2 ቆሮ. 12:7፤ ገላ. 4:15፤
6:11) ጳውሎስ ‘የሥጋ መውጊያውን’ በተመለከተ እግዚዝብሄር ተማጽኖ ነበር። (2 ቆሮንቶስ 12:8-10ን) እግዚአብሄር ጳውሎስን
‘ከሥጋ መውጊያው’ በተአምር አላዳነውም። ከዚህ ይልቅ በሽታውን መቋቋም የሚችልበት ብርታት ሰጥቶታል። በመሆኑም ጳውሎስ ከነበረበት
ድካም የተነሳ የእግዚዝብሄር ኃይል በግልጽ
ሊታይ ችሏል።
ስለ ጤና ጉዳይ
ከልክ በላይ አትጨነቁ
አንድን የሕክምና ዓይነት ለይተን በመጥቀስ የተሻለ ነው የሚል አስተያየት ባንሰጥም የሕክምና ባለሙያዎች የሚያደርጉልንን
እርዳታም ሆነ የሚያሳዩንን የትብብር መንፈስ እናደንቃለን። እርግጥ ነው፣ ፍጹም የሆነ ጤንነት የሚገኘው ገና ወደፊት እንደሆነ እንገነዘባለን።
ስለዚህ የጤንነታችን ጉዳይ ከልክ በላይ አእምሯችንን እንዲቆጣጠረው ወይም ነጋ ጠባ እንዲያስጨንቀን ከመፍቀድ መቆጠባችን ጥበብ መሆኑን
እናውቃለን። ሕይወት የአሁኑ ብቻ እንደሆነ ከሚያስቡትና በዚህም ምክንያት ከሕመማቸው ለመዳን ማንኛውንም ዓይነት ሕክምና ከመሞከር
ወደኋላ ከማይሉት እንዲሁም “ያለ ተስፋ” ከሚኖሩት የዓለም ሰዎች የተለየ አመለካከት ሊኖረን ይገባል። (ኤፌ. 2:2, 12) ለእግዚአብሄር ታማኝ ሆነን ከጸናን “እውነተኛ የሆነውን ሕይወት” ማለትም ቃል በገባልን የዘላለም ሕይወት
እንደምናገኝ እርግጠኛ ስለሆንን የአሁኑን ሕይወታችንን ለማዳን ስንል የእግዚአብሄር ሞገስ የሚያሳጣ አንዳች ነገር ላለማድረግ ቆርጠናል።1 ጢሞ. 6:12, 19፤ 2 ጴጥ.
3:13
ስለ ጤንነታችን ከልክ በላይ ከማሰብ የምንርቅበት ሌላም ምክንያት አለን። ስለ ጤንነታችን
ከሚገባው በላይ መጨነቃችን ራስ ወዳዶች እንድንሆን ሊያደርገን ይችላል። ሐዋርያው ጳውሎስ ይህን አደጋ በሚመለከት የፊልጵስዩስ ክርስቲያኖችን
ሲያስጠነቅቅ “እያንዳንዳችሁ ሌሎችን የሚጠቅመውንም እንጂ፣ ራሳችሁን የሚጠቅመውን ብቻ አትመልከቱ” ብሏል። (ፊልጵ. 2:4) ለራሳችን
ጤንነት አስፈላጊውን እንክብካቤ ማድረጋችን ተገቢ ቢሆንም ለወንድሞቻችንና ‘የመንግሥቱን ወንጌል’ ለምንሰብክላቸው ሰዎች ያለን ልባዊ
አሳቢነት ለአካላዊ ጤንነታችን ከልክ በላይ ከመጨነቅ እንድንቆጠብ ያስችለናል። ማቴ.
24:14
እያንዳንዱ በዕድሜ የጎለመሰ ክርስቲያን አንድ ዓይነት የጤና እክል ሲያጋጥመው ይሻለኛል
የሚለውን የሕክምና ዓይነት በመምረጥ ረገድ ‘የራሱን ሸክም መሸከም’ ይኖርበታል። (ገላ. 6:5) ይሁን እንጂ የምንመርጠው የሕክምና
ዓይነት ከእግዚአብሄር ጋር ያለንን ግንኙነግት ይነካዋል። ለመጽሐፍ ቅዱስ መሠረታዊ ሥርዓቶች ያለን አክብሮት ‘ከደም እንድንርቅ’ እንደሚያደርገን ሁሉ ለእግዚአብሄር ቃል የምንሰጠው ከፍ ያለ ግምትም መንፈሳዊ ጉዳት ሊያስከትልብን ወይም ከእግዚአብንሄር ጋር ያለንን ግንኙነት ሊያበላሽብን ከሚችል የሕክምና ዓይነት እንድንርቅ ይገፋፋናል።
(የሐዋ. ሥራ 15:20) አንዳንድ ምርመራዎችና ሕክምናዎች የሚከናወኑበት መንገድ ከምትሐታዊ ድርጊት ጋር ይመሳሰላል። እግዚአብሄር ወደ
“ምትሐታዊ ኃይል” ወይም ወደ መናፍስታዊ ድርጊቶች ዞር ያሉ ከሃዲ እስራኤላውያንን አውግዟል። “ከንቱውን መባ አታቅርቡ፤ ዕጣናችሁን
እጸየፋለሁ፤ የወር መባቻ በዓላችሁን፣ ሰንበቶቻችሁን፣ ጉባኤያችሁንና በክፋት [“በምትሐታዊ ኃይል፣”] የተሞላውን ስብሰባችሁን መታገሥ
አልቻልሁም”። (ኢሳ. 1:13) በምንታመምበት ጊዜ ጸሎታችን እንዲታገድ የሚያደርግ ወይም ከእግዚብሄር ጋር የመሠረትነውን ግንኙነት አደጋ ላይ የሚጥል አንዳች ነገር ላለማድረግ መጠንቀቅ እንዳለብን
የታወቀ ነው።ሰቆ. 3:44
‘ጤናማ አስተሳሰብ
መያዝ’ አስፈላጊ ነው
በምንታመምበት ጊዜ እግዚአብሄር በተአምር ይፈውሰናል ብለን መጠበቅ ባንችልም እንኳ የሕክምና
ዓይነት በምንመርጥበት ጊዜ ጥበብ እንዲሰጠን መጸለይ እንችላለን። በዚህ ረገድ ምርጫ ስናደርግ በቅዱስ ጽሑፋዊ መሠረታዊ ሥርዓቶችና
በጥሩ የማመዛዘን ችሎታ መመራት ይኖርብናል። ያጋጠመን የጤና እክል አሳሳቢ በሚሆንበት ጊዜ “ምክር ሲጓደል ዕቅድ ይፋለሳል፤ በብዙ
አማካሪዎች ግን ይሳካል” በሚለው የምሳሌ 15:22 ጥቅስ መሠረት የሚቻል ከሆነ ከአንድ በላይ የሕክምና ባለሙያዎችን ማማከራችን
ጥበብ ይሆናል። ሐዋርያው ጳውሎስ የእምነት ባልንጀሮቹን “አሁን ባለው በዚህ ሥርዓት ውስጥ ጤናማ አስተሳሰብ በመያዝ፣ በጽድቅና
ለአምላክ በማደር” እንዲኖሩ አሳስቧቸዋል።ቲቶ 2:12
ብዙ ሰዎች በኢየሱስ ዘመን የኖረችው በበሽታ ትሠቃይ የነበረችው ሴት የደረሰባት ዓይነት
ሁኔታ ያጋጥማቸዋል። በማርቆስ 5:25, 26 ላይ እንዲህ የሚል እናነባለን፦ “ዐሥራ ሁለት ዓመት ደም ሲፈሳት የኖረችም ሴት በዚያ
ነበረች፤ በብዙ ባለ መድኀኒቶች ዘንድ በመንከራተት ያላትን ሁሉ ብትጨርስም፣ ሕመሙ ባሰባት እንጂ አልተሻላትም ነበር።” ኢየሱስ
ይህችን ሴት የፈወሳት ከመሆኑም ሌላ ርኅራኄ አሳይቷታል። (ማር. 5:27-34) አንዳንድ ክርስቲያኖች ለመዳን ካላቸው ከፍተኛ ምኞት
የተነሳ ንጹሕ የሆነው አምልኮ ከሚመራባቸው መሠረታዊ ሥርዓቶች ጋር የሚቃረኑ የምርመራ ወይም የሕክምና ዓይነቶችን ለመምረጥ ተፈትነዋል። ሰይጣን እኛን ከእውነተኛው አምልኮ ለማራቅ የማይፈነቅለው ድንጋይ የለም። አንዳንዶችን
ለማሰናከል የጾታ ብልግናንና ፍቅረ ንዋይን እንደሚጠቀም ሁሉ በምትሐታዊና በመናፍስታዊ ኃይሎች ከሚከናወኑ ሕክምናዎች የማይለዩ አጠያያቂ
ሕክምናዎችን እንዲከታተሉ በማድረግም የአንዳንዶችን ንጹሕ አቋም ለማጉደፍ ይሞክራል። እግዚአብሄር “ከክፉው” እና ከማንኛውም
ዓይነት “ክፋት” እንዲያድነን እንጸልያለን። ከምትሐታዊና ከመናፍስታዊ ድርጊቶች ጋር ንክኪ ሊኖረው ለሚችል ማንኛውም ድርጊት ራሳችንን
በማጋለጥ በሰይጣን መዳፍ ውስጥ መውደቅ አይኖርብንም። ማቴ. 6:13፤ ቲቶ 2:14
እግዚአብሄር እስራኤላውያንን ከሟርትና ከአስማት እንዲርቁ ነግሯቸው ነበር። (ዘዳ. 18:10-12) ሐዋርያው
ጳውሎስ “የሥጋ ሥራዎች” ብሎ ከዘረዘራቸው ነገሮች መካከል “መናፍስታዊ ድርጊት” ይገኝበታል። (ገላ. 5:19, 20) ከዚህም በላይ
“አስማተኞች” ወይም መናፍስታዊ ድርጊቶችን የሚፈጽሙ ሰዎች በእግዚአብሄር አዲስ ሥርዓት ውስጥ ቦታ አይኖራቸውም። (ራእይ 21:8) ከመናፍስታዊ
ድርጊት ጋር ንክኪ ያለው ማንኛውም ነገር በእግዚአብሄር ዘንድ አስጸያፊ እንደሆነ ግልጽ ነው።
ከላይ ከተጠቀሰው አንጻር ሲታይ አንዳንድ የምርመራ ወይም የሕክምና ዓይነቶች የሚከናወኑበትን
መንገድ በተመለከተ አጠራጣሪ የሆነ ነገር ካለ ብንተወው ጥበብ ይሆናል። እርግጥ ነው፣ አንድ የሕክምና ዘዴ እንዴት እንደሚሠራ ማስረዳት
ስላልቻልን ብቻ ሕክምናው በሆነ መንገድ ከመናፍስታዊ ድርጊት ጋር ግንኙነት አለው ማለት አይደለም። ጤናን በመንከባከብ ረገድ ቅዱስ
ጽሑፋዊ አመለካከት ለመያዝ መለኮታዊ ጥበብና ጥሩ የማመዛዘን ችሎታ እንዲኖረን ያስፈልጋል። በምሳሌ ምዕራፍ 3 ላይ የሚከተለውን
ማሳሰቢያ እናገኛለን፦ ‘በፍጹም ልብህ በእግዚአብሔር ታመን፤ በራስህ
ማስተዋል አትደገፍ፤ በመንገድህ ሁሉ እርሱን ዕወቅ፤ እርሱም ጐዳናህን ቀና ያደርገዋል። ትክክለኛ ፍርድንና አስተውሎ መለየትን ጠብቅ፤
ለነፍስህም ሕይወት ይሆናሉ።’ ምሳሌ
3:5, 6, 21, 22። በተቻለ መጠን ጤነኛ ሆነን ለመኖር አቅማችን የሚፈቅደውን ሁሉ የምናደርግ ቢሆንም ሕመማችንን
ወይም እርጅና የሚያስከትለውን ጣጣ ለመቋቋም በምናደርገው ጥረት የእግዚአብሄር ሞገስ ላለማጣት ጥንቃቄ ማድረግ ይኖርብናል። በሌሎች ጉዳዮች እንደምናደርገው ሁሉ፣ ጤንነታችንን
በመንከባከብ ረገድም ከመጽሐፍ ቅዱስ መሠረታዊ ሥርዓቶች ጋር ተስማምተን በመኖር “ምክንያታዊነታችን በሰው ሁሉ ዘንድ የታወቀ” እንዲሆን
ማድረግ ይገባናል። (ፊልጵ. 4:5 ) በመጀመሪያው መቶ ዘመን የነበረው የበላይ አካል በጻፈው እጅግ አስፈላጊ የሆነ ደብዳቤ ላይ
ክርስቲያኖች ከጣዖት አምልኮ፣ ከደምና ከዝሙት እንዲርቁ መመሪያ አስተላልፎ ነበር። በደብዳቤው ላይ “ከእነዚህ ዐይነት ነገሮች ብትርቁ
ለእናንተ መልካም ነው” የሚል ዋስትናም ታክሎበታል (የሐዋ.ሥራ 15:28, 29)
ፍጹም ጤንነት
የምናገኝበትን ጊዜ በማሰብ ለራሳችን ሚዛናዊ እንክብካቤ ማድረግ
እያንዳንዳችን ‘መጽሐፍ ቅዱስ ዝሙትን በተመለከተ የያዘውን መሠረታዊ ሥርዓት በጥብቅ መከተሌ
መልካም እንደሆነልኝ እገነዘባለሁ?’ ብለን ራሳችንን ብንጠይቅ ጥሩ ነው። በተጨማሪም “ሥጋንና መንፈስን ከሚያረክስ ነገር ሁሉ ራሳችንን”
ለማንጻት ጥረት በማድረጋችን ያገኘናቸውን ጥቅሞች አስቡ። (2 ቆሮ. 7:1) መጽሐፍ ቅዱስ የግል ንጽሕና አጠባበቅን በሚመለከት
የያዘውን መመሪያ በጥብቅ በመከተላችን ከብዙ በሽታዎች መዳን ችለናል። መንፈሳችንንና አካላችንን ከሚያረክሱ ከትንባሆና ከዕፆች መራቃችን
መልካም ሆኖልናል። በተጨማሪም በመብልና በመጠጥ ረገድ ልከኞች በመሆናችን ከጤና አንጻር ያገኘነውን ጥቅም አስቡ። (ምሳሌ
23:20ንና ቲቶ 2:2, 3) ምንም እንኳ እንደ እረፍትና የአካል ብቃት እንቅስቃሴ የመሳሰሉ ነገሮች በጥቅሉ ለጤንነታችን የሚያበረክቱት
አስተዋጽኦ ሊኖር ቢችልም በመንፈሳዊም ሆነ በአካላዊ ጥሩ ሁኔታ ላይ ልንገኝ የቻልነው ቅዱስ ጽሑፋዊ መመሪያዎችን በማክበራችን ነው።
የእግዚአብሄር በግ የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ “ወደ ሕይወት ውሃ ምንጭ” ይመራናል፤ እንዲሁም አምላክ እንባን ሁሉ ከዓይናችን
ያብሳል። (ራእይ 7:14-17፤ 22:1, 2) በመቀጠል ደግሞ “በዚያም የሚቀመጥ፦ ታምሜአለሁ አይልም” የሚለው አስደሳች ትንቢት
ፍጻሜውን ያገኛል። ኢሳ.
33:24። መዳናችን መቅረቡን በእርግጠኝነት እናምናለን፤ እንዲሁም እግዚአብሄር በሰው ልጅ ላይ የሚደርሰውን ሕመምና ሞት የሚያስቆምበትን ቀን በናፍቆት እንጠባበቃለን።
እስከዚያው ድረስ ግን፣ አፍቃሪ አባታችን ‘ስለ እኛ ስለሚያስብ’ ሕመምና ሥቃይ የሚያደርስብንን መከራ ችለን እንድንኖር እንደሚረዳን
እርግጠኞች ነን። (1 ጴጥ. 5:7) ለጤናችን ተገቢውን እንክብካቤ ማድረግ አስፈላጊ ቢሆንም ይህን የምናደርገው ግን በመንፈስ መሪነት
የተጻፈው የአምላክ ቃል ከያዘው ግልጽ መመሪያ ጋር በሚስማማ መንገድ መሆን ይኖርበታል!
ዘመናዊ ሕክምና ምን ያህል ይሳካለት
ይሆን?
የሕክምና ተመራማሪዎች በጥንቶቹ
ዝነኛ የሕክምና ባለሙያዎች ትከሻ ላይ በመቆም የላቀ የእድገት ደረጃ ላይ ደርሰዋል። ከጥንቶቹ ሐኪሞች
መካከል እንደ ሂፖክራቲዝ እና ፓስተር ያሉ እውቅ ሰዎች እንዲሁም እንደ ቨሴሊየስ እና ዊልያም ሞርተን ያሉ ስማቸው ብዙም ያልገነነ
ሰዎች ይገኙበታል። እነዚህ ሰዎች ለዘመናዊው ሕክምና ያበረከቱት አስተዋጽዖ ምንድን ነው? በጥንት ዘመን
ሕክምና በአብዛኛው ከሳይንስ ጋር ሳይሆን ከአጉል እምነትና ከሃይማኖታዊ ልማዶች ጋር የተያያዘ ሥራ ነበር። በዶክተር ፌሊክስ ማርቲ-ኢባንዬስ
የታተመው ዚ ኤፒክ ኦቭ ሜድስን የተሰኘው መጽሐፍ “ሜሶጶጣሚያውያን በሽታ የአማልክት ቅጣት ነው ብለው ያምኑ ስለነበር በሽታን ለመከላከል
. . . ይጠቀሙበት የነበረው ሕክምና ሃይማኖታዊ ልማዶችን አጣምሮ የያዘ ነው” ይላል። ከዚያ ዘመን ብዙም ሳይቆይ ብቅ ያለው የግብፃውያን
ሕክምናም እንዲሁ ከሃይማኖት ጋር የተሳሰረ ነው። ስለዚህ ገና ከጅምሩ አንስቶ ሐኪሞች ሃይማኖታዊ ከበሬታ ያገኙ ነበር።
ዶክተር ቶማስ ኤ ፕሬስተን ዘ ክሌይ ፔድስታል በተባለው መጽሐፋቸው ላይ እንዲህ ብለዋል:-
“የጥንቶቹ ሰዎች ከነበሯቸው እምነቶች መካከል ብዙዎቹ በሕክምናው መስክ እስከ ዘመናችን ድረስ የዘለቀ የማይፋቅ አሻራ ጥለው አልፈዋል።
ከእነዚህ እምነቶች አንዱ በሽታ ከሕመምተኛው ቁጥጥር ውጪ የሆነ ነገር በመሆኑ ማገገም የመቻሉ ሁኔታ የተመካው በሐኪሙ ልዩ ተሰጥኦ
ላይ ብቻ ነው የሚለው ነው።”
መሠረቱን መጣል
ይሁንና እያደር የሕክምና ሥራ ሳይንሳዊ እየሆነ መጣ። ቀደም ባሉት ዘመናት በግንባር ቀደምትነት
ሳይንሳዊ ሐኪም ሆኖ ብቅ ያለው ሂፖክራቲዝ ነው። በ460 ከዘአበ ኮስ በተባለችው የግሪክ ደሴት የተወለደው ሂፖክራቲዝ በብዙዎች
ዘንድ የምዕራባውያን ሕክምና አባት ተደርጎ ይታያል። ሂፖክራቲዝ ሕክምናን ምክንያታዊ በሆነ መንገድ ለመመልከት የሚያስችል መሠረት
ጥሏል። በሽታ ተፈጥሯዊ የሆነ ምክንያት ያለው ነገር እንደሆነ በማስረዳት የአማልክት ቅጣት ነው የሚለውን ሐሳብ ውድቅ አድርጓል።
ለምሳሌ ያህል የሚጥል በሽታ ሊፈወስ የሚችለው በአማልክት ብቻ ነው የሚል እምነት ስለነበረ ከረጅም ጊዜ አንስቶ ቅዱስ በሽታ እንደሆነ
ተደርጎ ሲታይ ቆይቷል። ሆኖም ሂፖክራቲዝ “ቅዱስ የሚባለው በሽታ ከሌሎቹ በሽታዎች ይበልጥ መለኮታዊም ሆነ ቅዱስ ተደርጎ ሊታይ
የሚችልበት ምንም ምክንያት አይታየኝም። ተፈጥሯዊ መንስኤ ያለው በሽታ ነው” ሲል ጽፏል። በተጨማሪም የተለያዩ በሽታዎችን ምልክቶች
እየተከታተለ ለወደፊቱ ማመሳከሪያ ሆነው እንዲያገለግሉ በመዝገብ ያሰፍር የነበረው የመጀመሪያው መድኃኒተኛ ሂፖክራቲዝ እንደሆነ ይነገርለታል።
ከበርካታ መቶ ዘመናት የተወለደው ጌለን የተሰኘ ግሪካዊ ሐኪምም እንደዚሁ አዲስ ሳይንሳዊ
ምርምር አድርጓል። ጌለን በተበለቱ የሰውና የእንስሳ አካል ክፍሎች ላይ ጥናት በማድረግ ዶክተሮች ለብዙ መቶ ዘመናት የተጠቀሙበትን
የአናቶሚ መማሪያ መጽሐፍ አዘጋጅቷል! በ1514 ብራሰልስ ውስጥ የተወለደው አንድሬያስ ቨሴሊየስ ኦን ዘ ስትራክቸር ኦቭ ዘ ሂውማን
ቦዲ የተሰኘ መጽሐፍ ለንባብ አበቃ። መጽሐፉ ጌለን ከደረሰባቸው በርካታ ድምዳሜዎች ጋር የሚጋጭ በመሆኑ ተቃውሞ ቢገጥመውም ለዘመናዊ
የአናቶሚ ጥናት መሠረት ጥሏል። ዲ ግሮሰን (ታላላቅ ሰዎች) የተባለው መጽሐፍ እንደሚለው ከሆነ ቨሴሊየስ “በታሪክ ዘመናት ሁሉ
ከኖሩት እጅግ ታላላቅ የሕክምና ተመራማሪዎች አንዱ” ለመሆን በቅቷል።
ጌለን ልብንና የደም ዝውውርን በተመለከተ የነበሩት ጽንሰ ሐሳቦችም ከጊዜ በኋላ ተሽረዋል።*
እንግሊዛዊው ሐኪም ዊልያም ሃርቬይ እንስሳትንና አዕዋፍን እየበለተ ጥናት በማካሄድ በርካታ ዓመታት አሳልፏል። የልብ ክፍ ክዶችን
(valves) ተግባር ከማጥናቱም በላይ በእያንዳንዱ ከርሰ ልብ (ventricle) ውስጥ ያለውን የደም ይዘት በመለካት በሰውነት
ውስጥ የሚኖረውን የደም መጠን ለመገመት ሞክሯል። ሃርቬይ የደረሰባቸውን ግኝቶች በ1628 ኦን ዘ ሞሽን ኦቭ ዘ ሃርት ኤንድ ብለድ
ኢን አኒማልስ በተባለው መጽሐፍ አማካኝነት ለንባብ አብቅቷል። ትችት፣ ተቃውሞ፣ ጥቃትና ዘለፋ ተሰንዝሮበታል። ይሁን እንጂ የሃርቬይ
ምርምር የሰውነትን የደም ዝውውር ሥርዓት በማሳወቅ በሕክምናው መስክ አዲስ ምዕራፍ ከፍቷል!
ከፀጉር ማስተካከል
እስከ ቀዶ ሕክምና
በቀዶ ሕክምናውም መስክ ከፍተኛ እመርታዎች በመታየት ላይ ነበሩ። በመካከለኛው ዘመን ቀዶ
ሕክምና በአብዛኛው የፀጉር አስተካካዮች ሥራ ነበር። አንዳንዶች የዘመናዊው ቀዶ ሕክምና አባት በ16ኛው መቶ ዘመን ይኖር የነበረው
ፈረንሳዊው አንብሮዋዝ ፓሬ ነው ማለታቸው ምንም አያስደንቅም። ፓሬ አራት የፈረንሳይ ነገሥታትን ያገለገለ የቀዶ ሕክምና ፈር ቀዳጅ
ከመሆኑም በላይ በርከት ያሉ የቀዶ ሕክምና መሣሪያዎች ፈልስፏል። ይሁንና በ19ኛው
መቶ ዘመን ይኖር ለነበረ ቀዶ ሐኪም ትልቅ ጋሬጣ የሆነው ነገር ቀዶ ሕክምና የሚያስከትለውን ሥቃይ ማስቀረት አለመቻሉ ነበር። ሆኖም
በ1846 የጥርስ ቀዶ ሐኪም የሆነው ዊልያም ሞርተን በቀዶ ሕክምና ወቅት ሰመመን የመስጠት ልማድ በስፋት ጥቅም ላይ እንዲውል ጥርጊያውን
አመቻቸ።*
በ1895 ጀርመናዊው ፊዚከኛ ቪልሄልም ሬንትገን ኤሌክትሪክ በመጠቀም ሙከራ በማካሄድ ላይ
እንዳለ ጨረሮች በአጥንት ሳይሆን በሥጋ ውስጥ ሲያልፉ ተመለከተ። ጨረሮቹ ከየት እንደመጡ ስላልተገነዘበ ኤክስ ሬይስ ብሎ ሰየማቸው።
ይህ ስያሜ አሁንም ድረስ በእንግሊዝኛ ተናጋሪው ዓለም ይሠራበታል። (ጀርመኖች እነዚህን ጨረሮች ሬንትገንስትራለን በማለት ይጠሯቸዋል።)
ዲ ግሮሰን ዶይቸን (ታላላቅ ጀርመናውያን) የተሰኘው መጽሐፍ እንደሚለው ሬንትገን ሚስቱን “ሰዎች ይህን ሲሰሙ ‘ሬንትገን አበደ’
ማለታቸው አይቀርም” ብሏት ነበር። በእርግጥም አንዳንዶች አበደ ብለው ነበር። ሆኖም ሬንትገን የደረሰበት ግኝት በቀዶ ሕክምናው
ዘርፍ ታላቅ ለውጥ አስከትሏል። ቀዶ ሐኪሞች የሰውን አካል ሳይቀዱ ውስጣዊ የአካል ክፍሎችን መመልከት ቻሉ።
በሽታን ድል መንሳት
ባለፉት የታሪክ ዘመናት እንደ ፈንጣጣ ያሉ ተላላፊ በሽታዎች በተደጋጋሚ ጊዜያት በመከሰት
ወረርሽኝ፣ ሽብርና ሞት አስከትለዋል። በዘጠነኛው መቶ ዘመን የኖረውና በአንዳንዶች ዘንድ የዘመኑ ታላቅ የእስልምናው ዓለም ሐኪም
ተደርጎ ይታይ የነበረው የፋርሱ ተወላጅ አር-ራዚ የፈንጣጣ በሽታን በተመለከተ የመጀመሪያውን ትክክለኛ ትንተና በጽሑፍ አስፍሯል።
ሆኖም ኤድዋርድ ጄነር የተባለ ብሪታንያዊ ሐኪም ለበሽታው ፈውስ ያገኘው ከብዙ መቶ ዘመናት በኋላ ነበር። ጄነር አንድ ሰው ካውፖክስ
በተባለ ምንም ጉዳት የማያስከትል በሽታ አንዴ ከተያዘ ሰውነቱ የፈንጣጣ በሽታ መከላከያ እንደሚያዳብር ተገነዘበ። ጄነር በዚህ ግንዛቤ
ላይ በመመርኮዝ በካውፖክስ ሳቢያ ከተፈጠረ ቁስል ላይ የፈንጣጣ መከላከያ ክትባት ሠራ። ይህ የሆነው በ1796 ነበር። ከእሱ ቀደም
አዳዲስ ነገሮችን እንዳስተዋወቁት ሰዎች ሁሉ ጄነርም ትችትና ተቃውሞ ገጥሞት ነበር። ይሁን እንጂ ክትባት መፈልሰፉ ውሎ አድሮ በሽታው
ከነአካቴው እንዲጠፋ ከማድረጉም በላይ የሕክምናው ዓለም በሽታን የሚዋጋበት ውጤታማ የሆነ አዲስ ብልሃት ሊያገኝ ችሏል።
ፈረንሳዊው ሉዊ ፓስተር የእብድ ውሻ በሽታንና (anthrax) ለመከላከል ክትባት ተጠቅሟል።
በተጨማሪም ፓስተር ጀርሞች በሽታ በማምጣት ረገድ ትልቅ ሚና እንደሚጫወቱ አረጋግጧል። በ1882 ሮበርት ኮች “የአሥራ ዘጠነኛው
መቶ ዘመን ግንባር ቀደም ቀሳፊ በሽታ” ሲሉ አንድ ታሪክ ጸሐፊ የገለጹትን የሳንባ ነቀርሳን የሚያስከትለውን ጀርም ለይቶ አወቀ።
ከአንድ ዓመት ገደማ በኋላ ደግሞ ኮች ኮሌራ አማጭ የሆነውን ጀርም ለይቶ አወቀ። ላይፍ የተሰኘው መጽሔት እንዲህ ይላል:- “የፓስተርና
የኮች ሥራዎች የማይክሮባዮሎጂ ሳይንስን ለዓለም ያስተዋወቁ ከመሆናቸውም በላይ በሰውነት መድህን ጥናት፣ በስነ ጤናና በንጽሕና አጠባበቅ
ለታዩት መሻሻሎች በር ከፋች ሆነዋል። ይህም የሰውን ልጅ ዕድሜ በማራዘም ረገድ ባለፉት 1, 000 ዓመታት ከታዩት ሳይንሳዊ ዕድገቶች
ሁሉ በበለጠ ትልቅ አስተዋጽኦ አበርክቷል።”
የሃያኛው መቶ
ዘመን ሕክምና
በ20ኛው መቶ ዘመን መጀመሪያ ላይ የሕክምናው ዓለም በእነዚህና በሌሎች የተራቀቁ የሕክምና
ባለሙያዎች ትከሻ ላይ ቆሞ ነበር። ከዚያን ጊዜ አንስቶ በሕክምናው መስክ ፈጣን እድገት ታይቷል። ለስኳር በሽታ ኢንሱሊን፣ ለካንሰር
ኬሚፈውስ (chemotherapy)፣ ከእጢ ጋር ለተያያዙ በሽታዎች በሆርሞን አማካኝነት የሚሰጥ ሕክምና፣ ለሳንባ ነቀርሳ አንቲባዮቲክ
መድኃኒቶች፣ ለተወሰኑ ዓይነት የወባ በሽታዎች ክሎሮክዊንንና ለኩላሊት በሽተኞች ደም የማጣራት ሂደት መፈጠሩ እንዲሁም ልብ ለተወሰነ
ጊዜ ሥራውን እንዲያቆም በማድረግ ቀዶ ሕክምና ማካሄድና አባላካልን በቀዶ ሕክምና መተካት መቻሉ እንደ ምሳሌ የሚጠቀሱ ናቸው። ይሁንና በ21ኛው
መቶ ዘመን መጀመሪያ ላይ በምንገኝበት በአሁኑ ወቅት የሕክምና ሳይንስ “የዓለም ሕዝብ ሁሉ ጥሩ ጤና እንዲኖረው” ለማድረግ ወደታለመው
ግብ ምን ያህል ተቃርቦ ይሆን?
የሕክምና ሳይንስ ከአንዱ እመርታ ወደ ሌላው እየተሸጋገረ ሲሄድ ቆይቷል። ሆኖም ሁሉም ሰው
ጥሩ ጤና እንዲኖረው ለማድረግ የታለመው ከሁሉ የላቀ ግብ ሊደረስበት የሚችል ሆኖ አልተገኘም። በመሆኑም በ1998
የአውሮፓ ኮሚሽን “አውሮፓውያን የአሁኑን ያህል ረጅምና ጤናማ ሕይወት መምራት የቻሉበት ጊዜ የለም” የሚል ዘገባ ያወጣ ቢሆንም
እንኳ ዘገባው “ከአምስት ሰዎች አንዱ 65 ዓመት ሳይሞላው ሕይወቱ ይቀጫል። ከእነዚህም መካከል 40 በመቶ ገደማ የሚሆኑት የሚሞቱት
በካንሰር ሳቢያ ሲሆን 30 በመቶ የሚሆኑት ደግሞ ከልብና ከደም ቧንቧዎች ጋር በተያያዙ በሽታዎች የሚሞቱ ናቸው . . . ጤናን
ለአደጋ የሚያጋልጡ አዳዲስ ሁኔታዎችን ለመዋጋት የተሻለ መከላከያ ማዘጋጀት ያስፈልጋል” ሲል አክሎ ገልጿል።
በኅዳር ወር 1998 ጌዙንትሃይት የተሰኘው የጀርመን የጤና መጽሔት እንደ ኮሌራና ሳንባ
ነቀርሳ ያሉ ተላላፊ በሽታዎች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣ ስጋት በመፍጠር ላይ መሆናቸውን ዘግቧል። ይህ የሆነው ለምንድን ነው?
አንቲባዮቲክ መድኃኒቶች “የቀድሞውን ዓይነት ውጤት ማስገኘት እየተሳናቸው መጥቷል። ከጊዜ ወደ ጊዜ በርካታ ባክቴሪያዎች ቢያንስ
ቢያንስ አንድ የተለመደ ዓይነት መድኃኒት መቋቋም ወደሚችሉበት ደረጃ እየተሸጋገሩ ነው። ከአንድ በላይ መድኃኒቶችን መቋቋም የቻሉ
ብዙ ባክቴሪያዎችም አሉ።” የቀድሞዎቹ በሽታዎች ማገርሸታቸውም ብቻ ሳይሆን እንደ ኤድስ ያሉ አዳዲስ በሽታዎችም ተከስተዋል። ስታትስቲክስ
1997 የተሰኘው የጀርመን የመድኃኒት አምራቾች ማኅበር ጽሑፍ “እስከ አሁን ባለው ሁኔታ መሠረት ካሉት በሽታዎች መካከል ሁለት
ሦስተኛ ለሚሆኑት ማለትም ወደ 20, 000 ገደማ ለሚጠጉት በሽታዎች መንስኤ የሆኑትን ነገሮች ማከም የሚቻልበት ደረጃ ላይ አልተደረሰም”
ሲል ያሳስበናል።
በጂን አማካኝነት የሚሰጠው ሕክምና
እርግጥ ነው፣ አዳዲስ ሕክምናዎች መፈልሰፋቸውን አላቋረጡም። ለምሳሌ ያህል፣ ብዙዎች ለተሻለ
ጤና ቁልፉ ጀነቲካዊ ምህንድስና ሊሆን እንደሚችል ያምናሉ። በ1990ዎቹ በዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ እንደ ዶክተር ደብሊው ፍሬንች
አንደርሰን በመሳሰሉ ሐኪሞች ምርምር ከተካሄደ በኋላ በጂን አማካኝነት የሚሰጠው ሕክምና “በእጅጉ ቀልብ የሚስብ አዲስ የሕክምና
ምርምር መስክ” ተብሎ ተገልጿል። ሃይለን ሚት ጌነን (በጂኖች መፈወስ) የተባለው መጽሐፍ በጂን አማካኝነት የሚሰጠውን ሕክምና በመጠቀም
“የሕክምና ሳይንስ ወደ አዲስ ምዕራፍ የሚሸጋገርበት ደረጃ ላይ የደረሰ ይመስላል። በተለይ ደግሞ እስካሁን ድረስ ፈውስ ካልተገኘላቸው
በሽታዎች ጋር በተያያዘ ይህ ሁኔታ እውን የሚሆንበት ጊዜ ተቃርቧል ማለት ይቻላል” ሲል ገልጿል።
ሳይንቲስቶች ውሎ አድሮ ለታካሚዎች የተስተካከሉ ጂኖችን በመስጠት በዘር የሚተላለፉ ጀነቲካዊ
በሽታዎችን መፈወስ እንደሚቻል ተስፋ ያደርጋሉ። ሌላው ቀርቶ እንደ ካንሰር ሕዋሳት ያሉ ጎጂ ሕዋሶች ራሳቸውን በራሳቸው እንዲያጠፉ
ማድረግ ይቻል ይሆናል። በአሁኑ ጊዜ አንድ ሰው በተፈጥሮው ለአንዳንድ በሽታዎች የተጋለጠ መሆን አለመሆኑን ለማረጋገጥ የሚያስችል
ጀነቲካዊ ምርምር ማካሄድ የሚቻልበት ደረጃ ላይ ተደርሷል። አንዳንዶች ቀጣዩ ሥራ መድኃኒቶችን ከታካሚው ጀነቲካዊ ቅንብር ጋር በሚስማማ
መንገድ ማዘጋጀት መቻል ይሆናል ይላሉ። አንድ የታወቁ ተመራማሪ ዶክተሮች አንድ ቀን “የታካሚዎቻቸውን በሽታ ለይተው በማወቅና ተስማሚውን
የዲ ኤን ኤ ክፋይ በመስጠት መፈወስ” የሚችሉበት ደረጃ ላይ ይደርሳሉ በማለት አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። ይሁን እንጂ በጂን
አማካኝነት የሚሰጠው ሕክምና ወደፊት “ቅጽበታዊ ፈውስ” ያስገኛል ብለው የሚያምኑት ሁሉም ሰዎች አይደሉም። እንዲያውም አንዳንድ
የተካሄዱ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ሰዎች በጀነቲካዊ ቅንብራቸው ላይ ምርምር እንዲካሄድ እንኳ ላይፈልጉ ይችላሉ። በተጨማሪም ብዙዎች
በጂን አማካኝነት የሚሰጠው ሕክምና የተፈጥሮ ሥርዓትን ሊያዛባ የሚችል አደገኛ ጣልቃ ገብነት ነው የሚል ስጋት አለባቸው።
ጀነቲካዊ ምህንድስናም ሆነ ሌሎች እጅግ የረቀቁ የሕክምና ዘዴዎች የታለመውንና የተጓጓለትን
ውጤት ያስገኙ ይሆን የሚለው ጉዳይ ጊዜ የሚያሳየው ነገር ነው። ይሁንና ከልክ ያለፈ ተስፋ መጣሉ ተገቢ አይሆንም። ዘ ክሌይ ፔድስታል
የተባለው መጽሐፍ አንድ በጣም የተለመደ ዓይነት ዑደት ይጠቅሳል:- “አንድ አዲስ የሕክምና ዘዴ ብቅ ይልና ሕክምና ነክ በሆኑ ስብሰባዎችና
በትልልቅ መጽሔቶች ላይ ብዙ ይባልለታል። ሕክምናውን የፈለሰፉት ሰዎች በሙያው መስክ ስማቸው ይገንናል፤ መገናኛ ብዙሃንም የታየውን
መሻሻል በከፍተኛ የአድናቆት ስሜት ያስተጋባሉ። ለተወሰነ ጊዜ የደስታ ስሜት ይነግሥና ልቆ የተገኘውን የሕክምና ዘዴ በመደገፍ በጠንካራ
ማስረጃ ላይ የተመረኮዘ ምሥክርነት ሲሰጥ ከቆየ በኋላ ቀስ በቀስ ያልታሰቡ ነገሮች ብቅ ማለት ይጀምሩና ለወራት አልፎ ተርፎም ለአሥርተ
ዓመታት የሚዘልቅ ግራ መጋባት ይፈጠራል። ከዚያ አዲስ የሕክምና ዘዴ ብቅ ይልና በአንድ ጀንበር ማለት ይቻላል፣ የቀድሞውን ዋጋ
አሳጥቶት ቁጭ ይላል።” በእርግጥም፣ አብዛኞቹ ዶክተሮች ፋይዳ ቢስ እንደሆኑ አድርገው በመደምደም እርግፍ አድርገው የተዉአቸው ብዙዎቹ
የሕክምና ዘዴዎች ዋነኛ የሕክምና መስጫ ዘዴዎች ተደርገው ይሠራባቸው የነበረበት ጊዜ ብዙ ሩቅ አይደለም። ምንም እንኳ በዛሬው ጊዜ ያሉት ዶክተሮች ለጥንቶቹ ሐኪሞች ይሰጥ የነበረው ዓይነት ሃይማኖታዊ
ከበሬታ ባይሰጣቸውም የሕክምና ባለሙያዎችን መለኮታዊ ኃይል እንዳላቸው ያህል አድርገው የሚመለከቱና ሳይንስ የሰውን ልጅ ለሚያጠቁት
በሽታዎች ሁሉ ፈውስ ማስገኘቱ እንደማይቀር አድርገው የሚያስቡ ሰዎች አልጠፉም። ይሁን እንጂ እውነታው ይህ ሊሆን እንደማይችል ያሳያል።
ዶክተር ሌናርድ ሄይፍሊክ ሃው ኤንድ ዋይ ዊ ኤጅ በተሰኘው መጽሐፋቸው ላይ “በ1900 ከዩናይትድ ስቴትስ ሕዝብ መካከል 75 በመቶ
የሚሆነው የሞተው ስልሳ አምስት ዓመት ሳይሞላው ነው። ዛሬ ግን ሁኔታው የተገላቢጦሽ ሆኗል ማለት ይቻላል:- ከሕዝቡ መካከል ወደ
70 በመቶ የሚሆነው የሚሞተው ስልሳ አምስት ዓመት ከሆነው በኋላ ነው” ብለዋል። የሰው ልጅ ዕድሜ በእንዲህ ያለ አስደናቂ ሁኔታ
ሊጨምር የቻለው ለምንድን ነው? ለዚህ “ዋነኛው ምክንያት በጨቅላ ዕድሜያቸው የሚቀጩ ሕፃናት ቁጥር መቀነሱ ነው” ሲሉ ሄይፍሊክ
ገልጸዋል። ይሁንና የሕክምና ሳይንስ ለአረጋውያን ሞት ዋነኛ ምክንያት የሆኑትን የልብ በሽታን፣ ካንሰርንና በአንጎል ውስጥ የሚከሰትን
የደም መፍሰስ ችግር ማስወገድ ቻለ እንበል። ይህ ከሞት ነፃ ሊያደርግ ይችላልን? በፍጹም። ዶክተር ሄይፍሊክ ያን ጊዜም እንኳ ቢሆን
“አብዛኞቹ ሰዎች መኖር የሚችሉት መቶ ዓመት ገደማ ነው” ሲሉ ገልጸዋል። አክለውም “መቶ ዓመት ገደማ መኖር ቢችሉም እንኳ ከሞት
ነፃ አይሆኑም። ለሞት የሚዳርጋቸው ነገር ምንድን ነው? እስኪሞቱ ድረስ እየደከሙና እየመነመኑ ይሄዳሉ” ብለዋል።






0 comments:
Post a Comment