ቀኞቹ ክፎዎች ናቸውና ዘመኑን ዋጁት (ኤፌ. 5:16)
መጽሐፍ ቅዱስ ‘የመጨረሻ ቀኖች’ የሚለውን ሐረግ የሚጠቀምበት የአንድ የነገሮች ሥርዓት ማክተሚያ ወደሚሆን መለኮታዊ ጥፋት ወደሚፈጸምበት ጊዜ የሚያደርሰውን የመደምደሚያ ዘመን ለማመልከት ነው። መጽሐፍ ቅዱስ የመጨረሻው ቀን መለያ ምልክት የሆኑትን ድርጊቶችና ሁኔታዎች ይገልጻል “ምልክቱ” ብዙ ማስረጃዎችን አጣምሮ የያዘ ነው። ስለዚህ የመጨረሻው ቀኖች ምልክቶች በአንድ ትውልድ ዘመን ውስጥ በግልጽ መታየት አለባቸው። የምልክቱ የተለያዩ ገጽታዎች በማቴዎስ ምዕራፍ 24, 25፣ ማርቆስ 13 እና ሉቃስ 21 ላይ ተመዝግበው ይገኛሉ። ተጨማሪ ዝርዝር መረጃዎች በ2 ጢሞቴዎስ 3:1–5፤ 2 ጴጥሮስ 3:3, 4 እና ራእይ 6:1–8 ላይ ይገኛሉ። የዚህን ምልክት ዋና ዋና ክፍል የሆኑ ጥቂት ምሳሌዎችን እንመለከታለን።
መጽሐፍ ቅዱስ በዛሬው ጊዜ የሚታየውን የሥነ ምግባር ውድቀት በተመለከተ ከረጅም ጊዜ በፊት እንዲህ በማለት ትንቢት ተናግሯል:- “በመጨረሻው ዘመን የሚያስጨንቅ ጊዜ እንደሚመጣ ይህን ዕወቅ። ሰዎች ራሳቸውን የሚወዱ ይሆናሉ፤ ገንዘብን የሚወዱ፣ . . . ለወላጆቻቸው የማይታዘዙ፣ የማያመሰግኑ፣ ቅድስና የሌላቸው፣ ፍቅር የሌላቸው፣ . . . ጨካኞች፣ መልካም የሆነውን የማይወዱ፣ ከዳተኞች፣ ችኩሎች፣ በከንቱ በትዕቢት የተወጠሩ፣ ከእግዚአብሔር ይልቅ ተድላን የሚወዱ ይሆናሉና።ሃይማኖታዊ መልክ አላቸው፤ኀይሉን ግን ክደዋል።” 2 ጢሞቴዎስ 3:1-5
ይህ የመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢት አሁን ያለንበትን ዓለም ጥሩ አድርጎ ይገልጸዋል ቢባል እንደምትስማማ ምንም ጥርጥር የለውም። የሚገርመው ግን ትንቢቱ የተጻፈው የዛሬ 2,000 ዓመት ገደማ ነው! ይህ ትንቢት የሚጀምረው “በመጨረሻው ዘመን” በማለት ነው። ታዲያ ‘የመጨረሻው ዘመን’ የሚሉት ቃላት ምን ያመለክታሉ?
‘የመጨረሻው ዘመን’ ተብሎ የተተረጎመው ዘ ላስት ዴይስ የሚለው የእንግሊዝኛ አገላለጽ በጣም የተለመደ ሆኗል። በእንግሊዝኛ ቋንቋ ብቻ እንኳ በመቶዎች በሚቆጠሩ መጻሕፍት ርዕሶች ውስጥ እነዚህ ቃላት ይገኛሉ። ለምሳሌ ያህል፣ በቅርቡ ለንባብ የበቃውን ዘ ላስት ዴይስ ኦቭ ኢኖሰንስ—አሜሪካ አት ዋር 1917-1918 የተባለውን መጽሐፍ እንመልከት። መጽሐፉ በመቅድሙ ላይ እንደገለጸው “ዘ ላስት ዴይስ” (የመጨረሻው ዘመን) የሚለውን አገላለጽ የሚጠቀምበት ከፍተኛ የሥነ ምግባር ዝቅጠት የታየበትን የተወሰነ ጊዜ ለማመልከት ነው።
የመጽሐፉ መቅድም በመቀጠል “በ1914 አገሪቱ ዩናይትድ ስቴትስ በታሪኳ ታይቶ በማይታወቅ ፍጥነት ለውጥ ማድረግ ጀመረች” ብሏል። እርግጥ ነው፣ 1914 ከዚያ በፊት ታይቶ የማይታወቅ ዓለም አቀፍ ጦርነት የጀመረበት ዓመት ነው። መጽሐፉ “ይህ በሁለት ሠራዊቶች መካከል የተደረገ ተራ ግጭት ሳይሆን የዓለም መንግሥታት እርስ በርስ የተፋለሙበት አጠቃላይ ጦርነት ነበር” ብሏል።
መጽሐፍ ቅዱስ ይህ ዓለም ከመጥፋቱ በፊት ‘የመጨረሻው ዘመን’ የተባለ አንድ የተወሰነ ጊዜ እንደሚኖር ያስተምራል። እንዲያውም መጽሐፍ ቅዱስ “በዚያን ጊዜ የነበረው ዓለም በውሃ ተጥለቅልቆ ጠፋ” በማለት ከዚህ ቀደም የጠፋ ዓለም እንደነበር ይገልጻል። በዚያን ጊዜ የተባለው ዘመን የትኛው ነው? የጠፋውስ ዓለም ምንድን ነው? ጥንት በኖኅ ዘመን የነበረው ‘የኃጢአተኞች ዓለም’ ነው። በተመሳሳይም በዛሬው ጊዜ ያለው ዓለም ይጠፋል። ይሁን እንጂ ኖኅና ቤተሰቡ እንደተረፉ ሁሉ እግዚአብሄርን የሚያገለግሉ ሰዎች ከፊታችን ካለው ጥፋት ይድናሉ። 2 ጴጥሮስ 2:5 3:6፤ ዘፍጥረት 7:21-24፤ 1 ዮሐንስ 2:17
ኢየሱስ ክርስቶስ ሰዎች ‘በጥፋት ውሃ ስለተጥለቀለቁበት’ ስለ ‘ኖኅ ዘመንም’ ተናግሯል። ከጥፋት ውኃው ቀደም ብሎ ማለትም በዚያን ጊዜ የነበረው ዓለም ከመጥፋቱ በፊት የነበረውን ሁኔታ “የዓለም መጨረሻ” ብሎ በጠራው ጊዜ ውስጥ ከሚታዩት ነገሮች ጋር አመሳስሎታል። (ማቴዎስ 24:3, 37-39) “የዓለም መጨረሻ” የሚለውን አባባል አንዳንድ መጽሐፍ ቅዱሶች “የዘመኑ መጨረሻ” በማለት ተርጉመውታል። ዘ ኒው ኢንግሊሽ ባይብል እና ኒው ኢንተርናሽናል ቨርሽን።
ኢየሱስ ትንቢቱን በመቀጠል እንዲህ ብሏል:- “በተለያየ ስፍራም ራብና የመሬት መንቀጥቀጥ ይሆናል፤ ይህ ሁሉ ግን የምጡ መጀመሪያ ነው።” አክሎም ‘ክፋት እየገነነ’ እንደሚሄድ ተናግሯል። (ማቴዎስ 24:7-14) በእርግጥም በዘመናችን ይህ ሁኔታ ሲፈጸም ተመልክተናል። በዛሬው ጊዜ የሥነ ምግባር ውድቀት እየጨመረ መሄዱ የመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢት ፍጻሜ ነው!
በሥነ ምግባር በዘቀጠው በዚህ ዓለም ውስጥ አኗኗራችን ምን ዓይነት ሊሆን ይገባል? ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በሮም ለሚገኙ ክርስቲያኖች በጻፈው ደብዳቤ ላይ የሥነ ምግባር ዝቅጠትንና ‘አሳፋሪ ምኞት’ የነበራቸውን ሰዎች አስመልክቶ እንዲህ በማለት ተናግሯል:- “ሴቶቻቸውም እንኳ ለባሕርያቸው የሚገባውን ግንኙነት ባሕርያቸው ላልሆነው ግንኙነት ለወጡ። እንደዚሁም ወንዶች ለባሕርያቸው የሚገባውን ሴቶችን መገናኘት ትተው እርስ በርሳቸው በፍትወት ተቃጠሉ፤ ወንዶች ከወንዶች ጋር ነውር ፈጸሙ።” ሮሜ 1:26, 27
ታሪክ ጸሐፊዎች እንደተናገሩት በመጀመሪያው መቶ ዘመን የነበረው ማኅበረሰብ በሥነ ምግባር ከጊዜ ወደ ጊዜ እያዘቀጠ በመሄዱ “በቁጥር አነስተኛ የነበረው የክርስቲያኖች ቡድን ተድላ ያሳበደውን አረማዊ ዓለም በመንፈሳዊ አቋሙና በመልካም ምግባሩ ይኮንነው ነበር።” ይህ ሁኔታ እኛም እንዲህ እያልን ራሳችንን እንድንጠይቅ ሊያደርገን ይገባል:- ‘ስለ ራሴም ሆነ በጓደኝነት ስለምመርጣቸው ሰዎች ምን ማለት ይቻላል? በሥነ ምግባር በዘቀጠው በዚህ ዓለም ውስጥ ስኖር በአኗኗሬ ከሌሎች የተለየሁ ሆኜ እታያለሁ?’ 1 ጴጥሮስ 4:3, 4
በዙሪያችን ያለው ዓለም በሥነ ምግባር የተበላሸ ቢሆንም እንኳ መጽሐፍ ቅዱስ ‘በጠማማና በክፉ ትውልድ መካከል ንጹሓንና ያለ ነቀፋ፣ ነውርም የሌለብን’ ሆነን እንድንገኝ ያስተምረናል። ይህን ለማድረግ ምንጊዜም “የሕይወትን ቃል” አጥብቀን መያዝ ይኖርብናል። (ፊልጵስዩስ 2:15, 16) ይህ የመጽሐፍ ቅዱስ ሐሳብ ክርስቲያኖች በሥነ ምግባር ብልግና ሳይበከሉ መኖር የሚችሉት እንዴት እንደሆነ ይጠቁመናል። ክርስቲያኖች በሥነ ምግባር ንጹሕ ሆነው መኖር ከፈለጉ በእግዚአብሄር ቃል ውስጥ የሚገኘውን ትምህርት በጥብቅ መከተልና ቃሉ የያዘው የሥነ ምግባር መሥፈርት ከሁሉ የተሻለ የሕይወት መመሪያ መሆኑን አምነው መቀበል ይኖርባቸዋል።
“የዚህ ዓለም አምላክ” የሆነው ሰይጣን ዲያብሎስ ሰዎች ከእርሱ ወገን እንዲሰለፉ ለማድረግ ይጥራል። (2 ቆሮንቶስ 4:4) መጽሐፍ ቅዱስ፣ ሰይጣን ‘የብርሃን መልአክ ለመምሰል ራሱን እንደሚለውጥ’ ይናገራል። እርሱ የሚያደርገውን በማድረግ የሚያገለግሉት ሰዎችም ቢሆኑ ከእርሱ የተለዩ አይደሉም። (2 ቆሮንቶስ 11:14, 15) እነዚህ አገልጋዮች፣ ሰዎች ነጻነትና ደስታ እንደሚያገኙ ቃል ይገባሉ፤ ነገር ግን መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚናገረው “እነርሱ ራሳቸው የጥፋት ባሪያዎች” ናቸው። 2 ጴጥሮስ 2:19። እንዲህ ዓይነቱ ማባበያ ሊያታልልህ አይገባም። የእግዚአብሄርን የሥነ ምግባር መሥፈርቶች ችላ የሚሉ ሰዎች አሳዛኝ ውጤት ይገጥማቸዋል። የመጽሐፍ ቅዱሱ መዝሙራዊ “ሥርዐትህን ስለማይሹ፣ ድነት ከክፉዎች የራቀ ነው” በማለት ጽፏል። (መዝሙር 119:155፤ ምሳሌ 5:22, 23)። ይሁን እንጂ ብዙዎች ‘የማደርገው ነገር በሕግ የሚያስጠይቅ እስካልሆነ ድረስ ምንም ችግር የለውም’ የሚል የተሳሳተ አመለካከት አላቸው። ሆኖም እንዲህ ያለው አመለካከት ትክክል አይደለም። በሰማይ የሚኖረው አባታችን በፍቅር ተነሳስቶ የሥነ ምግባር ደንቦችን ሰጥቶናል። ይህን ያደረገው እኛን ለመጠበቅ እንጂ ሕይወት አሰልቺ እንዲሆንብንና ነጻነት እንድናጣ ብሎ አይደለም። እኛን ‘የሚበጀንን ያስተምርሃል።’ በተጨማሪም ክፉ ነገር እንዳይደርስብን እንዲሁም በሕይወታችን ደስተኛ እንድንሆን ይፈልጋል። በእርግጥም መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚያስተምረው እግዚአብሄርን ማገልገል “ለአሁኑም ሆነ ለሚመጣው ሕይወት ተስፋ” እንዲኖረን ያደርጋል። የመጽሐፍ ቅዱስን ትምህርቶች በሥራ ላይ ማዋል የሚያስገኛቸውን ጥቅሞች የተማርነውን ተግባራዊ አለማድረጉ ውሎ አድሮ ከሚያስከትለው ጉዳት ጋር እናወዳድረው። እግዚአብሄርን በመስማት የእርሱን ሞገስ ማግኘት በእርግጥም ከሁሉ የተሻለ የሕይወት መንገድ ነው! እግዚአብሄርን “የሚያዳምጠኝ ሁሉ ግን በሰላም ይኖራል፤ ክፉን ሳይፈራ ያለ ሥጋት ይቀመጣል” በማለት ቃል ገብቷል። ምሳሌ 1:33
መጽሐፍ ቅዱስ፣ የእግዚዝብሄር መንግሥት በምድር ላይ ዘላቂ ሰላምና ደስታ እንደሚያመጣ ይተነብያል። (ዳንኤል 2:44) አቡነ ዘበሰማያት ወይም አባታችን ሆይ በሚለው ጸሎት ላይ ኢየሱስ ተከታዮቹን “መንግሥትህ ትምጣ፤ ፈቃድህ በሰማይ እንደ ሆነች፣ እንዲሁ በምድር ትሁን” ብለው እንዲጸልዩ አስተምሯቸዋል። (ማቴዎስ 6:10) ኢየሱስ በደብረ ዘይት ተራራ ላይ ሆኖ ለደቀ መዛሙርቱ በነገራቸው በሰፊው የሚታወቅ ትንቢት ላይ ከመንግሥቱ መምጣት ጋር የተያያዙ ክንውኖችን በዝርዝር ተናግሯል። እነዚህ ክንውኖች አንድ ላይ ተጣምረው የመጨረሻው ቀን ምልክት ሆነዋል፤ ልበ ቅን የሆኑ ሰዎችም ይህን ምልክት በግልጽ ሊያስተውሉት ይችላሉ። የዚህ ምልክት ገጽታ ከሆኑት ከሚከተሉት ክንውኖች መካከል የትኞቹ ሲፈጸሙ ተመልክተናል?
ፈውስ ያልተገኘላቸው በሽታዎች። የዓለም የጤና ድርጅት “አንድ ሦስተኛ የሚሆነው የዓለም ሕዝብ በሳንባ ነቀርሳ ባክቴሪያ ተይዟል” በማለት ዘግቧል። ድርጅቱ አክሎም፣ የሳንባ ነቀርሳ በሽታ በበርካታ አገሮች እንዲስፋፋ አስተዋጽኦ ካደረጉት ነገሮች መካከል አንዱ ኤች አይ ቪ መሆኑን ገልጿል። በእያንዳንዱ ሴኮንድ አንድ ሰው በሳንባ ነቀርሳ የሚያዝ ሲሆን በሽታው መድኃኒት የማይበግረው እየሆነም መጥቷል። በአውሮፓ የሚገኝ አንድ የሳንባ ነቀርሳ ሕመምተኛ “ምንም ዓይነት መድኃኒት ቢሰጠውም ከያዘው በሽታ መዳን እንዳልቻለ” ኒው ሳይንቲስት የተባለ መጽሔት በ2007 ዘግቧል፣ በአሁንም ጊዜ በተመራማሪዎች አዳዲስ ዘገባዎችና ጥናቶች ይቀርባሉ።
ነባርም ሆኑ አዳዲስ በሽታዎች በዓለም ዙሪያ በርካታ ሰዎችን እያጠቁ ሲሆን ለእነዚህ በሽታዎችም መድኃኒት ማግኘት አስቸጋሪ እየሆነ መጥቷል። ለምሳሌ ያህል፣ የወባ በሽታ ከቁጥጥር ውጭ እየሆነ በመሄዱ በሽታውን ለማጥፋት ታስበው በተነደፉ ዓለም አቀፋዊ መርሐ ግብሮች ላይ በተደጋጋሚ ጊዜ ማስተካከያዎችን ማድረግ አስፈልጓል። ከዚህም በተጨማሪ ሳንባ ነቀርሳን ጨምሮ ሌሎች ነባር በሽታዎች ኤድስን ከመሳሰሉ አዳዲስ በሽታዎች ጋር ተዳምረው በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን ሕይወት እየቀጠፉ ይገኛሉ። በአንደኛው የዓለም ጦርነት ማብቂያ ላይ ስፓኒሽ ፍሉ (በኢትዮጵያ የኅዳር በሽታ የሚባለው) በዓለም ላይ በመሰራጨት በበሽታ ታሪክ ውስጥ አቻ በማይገኝለት ፍጥነት ከ20 ሚልዮን የሚበልጡ ሰዎችን ሕይወት አጥፍቷል። የሕክምና ሳይንስ ትልቅ እድገት ቢያደርግም በየዓመቱ በነቀርሳ፣ በልብ ሕመም፣ ዓይነታቸው በርካታ በሆኑት የአባለዘር በሽታዎች፣ የሰውነት ክፍሎችን በሚያደርቁ በሽታዎች፣ በወባ፣ በሪቨር ብላይንድነስ እና በቻጋስ በሽታ የሚሞቱት ሰዎች ቁጥር ከፍተኛ ነው። አሁን ደግሞ ባለንበት ዘመን ሳርስ ከሳርስ የበሳው ደግሞ ኮሮናቫይረስ የተባለው ከመቼውም ይልቅ አለም በሙሉ ያስፈራውና ያሰደንገጠ ሆኖ ይገኛል፣ መድሃኒት የሌለው በመሆኑ የሚያስከትለው ኮምፕሌክስ የስውን ህይወት የሚቀጥፍ አድርጎታል፣ የአለም የጤና ድርጅት ሐኪሞችም ሆኑ ተመራማሪዎች መልስ ያጡለት ሆንዋል፣ በዚህ አስፈሪ ወቅት ወደ ታላቁ አምላካችንና ፈዋሻችን በሆነው እንድንታመን ያደርገናል። በ ዘጽ. 15:26 “እኔ ፈዋሽን አምላክህ እግዚአብሄር ነኝ” ብሎ የተነገረውን ቃል ማመን የሚበጅ ነው። የስው ልጅ/ አለም በሙሉ በፍጹም ልብና ሃሳብ ወደ እግዚአብሔር መመለስና ማመን በዚህ ቃል ጥላ ሥር ያደርገዋል ማምለጫና መሽሽጋያ እንዲሆንለትና እግዚአብሔር ለፈጠረው የስው ልጅ ከለላ ሆኖ ከመጣው የበሽታ መቅስፍት ይታደገዋል።
ዓለም አቀፍ ጦርነቶች። “ሕዝብ በሕዝብ ላይ፣ መንግሥትም በመንግሥት ላይ ይነሣል” (ማቴ. 24:7) ኢየሱስ “ሕዝብ በሕዝብ ላይ፣ መንግሥትም በመንግሥት ላይ ይነሣል” ሲል አስቀድሞ ተናግሯል። (ማቴዎስ 24:7) ከአንደኛው የዓለም ጦርነት በፊት በነበሩት ጊዜያት ጦርነቶች የሚደረጉት በተወሰኑ አካባቢዎች ብቻ ነበር። አንደኛው የዓለም ጦርነት፣ የምድራችንን አብዛኛውን ክፍል ያካለለ ብቻ ሳይሆን ከዚያ በፊት ታይቶ በማያውቅ ሁኔታ ይበልጥ አውዳሚ የሆኑ የጦር መሣሪያዎች መመረት የጀመሩበት ወቅት ነበር። ለምሳሌ ያህል፣ በወቅቱ የተፈለሰፉት አዳዲስ አውሮፕላኖች በሰላማዊ ሰዎች ላይ ቦምብ ለመጣል አገልግለዋል። የጦር መሣሪያዎች በገፍ መመረታቸው በጦርነት የሚሞቱትን ሰዎች ቁጥር ከዚያ ቀደም ፈጽሞ ሊታሰብ በማይችል ሁኔታ እጅግ ከፍተኛ እንዲሆን አድርጎታል። በወቅቱ በውጊያ ከተሰለፉት 65 ሚሊዮን የሚያህሉ ወታደሮች መካከል ግማሽ የሚሆኑት ሕይወታቸውን አጥተዋል አሊያም ጉዳት ደርሶባቸዋል። የሰው ልጆች ወደ 20ኛው መቶ ዘመን ዘልቀው ሲገቡ ደግሞ በጦርነት የሚሞቱት ሰዎች ቁጥር የዚያኑ ያህል ጨምሮ ነበር። አንድ የታሪክ ጸሐፊ እንዳሉት ከሆነ በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት የሞቱት ወታደሮችና ሰላማዊ ሰዎች “ቁጥር ይህ ነው ሊባል አይችልም።” ጦርነቶች አሁንም ድረስ ቀጥለዋል።
ለአያሌ ሺህ ዓመታት ጦርነቶች የዚችን ምድር ሕይወት አጨልመውት ኖረዋል። አንዱ አገር ከሌላው አገር ጋር፤ እንዲሁም በአንዱ አገር ውስጥ ባሉ በተቀናቃኝ ወገኖች መካከል ጦርነት ተካሂዷል። አንደኛው የዓለም ጦርነት ጀመረ። ይህ ጦርነት በሁለት ሠራዊቶች መካከል የተደረገ ተራ ጦርነት አልነበረም። የዓለም ዋና ዋና ኃይሎች በሙሉ የተሳተፉበት ጦርነት ነበር። የየአገሩ ሕዝቦች በሙሉ፣ ሲቪሎችም ጭምር ለጦርነቱ ድጋፍ እንዲሰጡ ተደርጎ ነበር። ጦርነቱ ባከተመበት ጊዜ ከዓለም ሕዝቦች በሙሉ 93 በመቶ የሚያክሉት በጦርነቱ ተካፍለው እንደነበረ ተገምቷል።
በራእይ 6:4 ላይ አስቀድሞ እንደተነገረው ‘ሰላም ከምድር ላይ ተወስዷል።’ ከ1914 ጀምሮ ዓለም በብጥብጥ ስትናወጥ ቆይታለች። ሁለተኛው የዓለም ጦርነት ከ1939 እስከ 1945 ተደረገ። ከ1945 ጀምሮ እስከ 1982 ድረስ ሌሎች 270 ጦርነቶች ተደርገዋል። በዚህ መቶ ዘመን ከ100 ሚልዮን በላይ የሚሆኑ ሰዎች በጦርነት አልቀዋል። በ1982 ታትሞ የወጣው ወርልድ ሚሊተሪ ኤንድ ሶሻል ኤክስፔንዲቸርስ እንደገለጸው በዚሁ ዓመት በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ 100 ሚልዮን ሰዎች በውትድርና ሥራዎች ተካፍለዋል።
ይህ የትንቢት ክፍል በትክክል ተፈጽሟል ለማለት ከዚህ የበለጠ ነገር መፈጸም ይኖርበታልን? በቅጽበት ሥራ ላይ ሊውሉ የሚችሉ በአሥር ሺህ የሚቆጠሩ የኑክሌር ጦር መሣሪያዎች አሉ። መንግሥታት ከኑክሌር የጦር መሣሪያዎቻቸው ጥቂቱን እንኳን ቢጠቀሙ ሥልጣኔና መላው የሰው ዘር ይጠፋል በማለት የታወቁ ሳይንቲስቶች ተናገረዋል። ይሁን እንጂ የመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢት እንዲህ ዓይነት እልቂት እንደማይደርስ ያመለክተናል።
በየቦታው የሚከሰት ረሃብ። ኢየሱስ ‘በተለያየ ስፍራ ረሃብ እንደሚሆን’ አስቀድሞ ተናግሯል። (ማቴዎስ 24:7) በ2005 ሳይንስ የተባለው መጽሔት “በዓለም ላይ 854 ሚሊዮን (ከዓለም ሕዝብ 14 በመቶ) የሚሆኑ ሰዎች ዘላቂ ወይም ጊዜያዊ በሆነ የምግብ እጥረት ይሠቃያሉ” በማለት ገልጿል። በረሃም ከሚስቅዩትም ሀገር አንድዋ ኢትዮጵያ ናት በአሁኑ ጊዜ ገበሬውም ህዝቡ በልማት ሥራ ላይ ደፋ ቀና እያለ ምግቡን ለማምረት ቢሞክረም በአየር ቀውስ የተነሳ ለህዝቡ የሚበቃውን ምግብ አቅርቦት ስለቀነስ ወደ ስምንት ሚሊዮን ህዝብ እንደተራበ በአሁኑ ስአት ይነገራል። በ2007 ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የተገኘ አንድ ምንጭ፣ 33 አገሮች ሕዝቦቻቸውን ለመመገብ የሚያስችል በቂ ምግብ እንደሌላቸው ሪፖርት አድርጓል። በዓለም ላይ የሚመረተው እህል እየጨመረ ባለበት በአሁኑ ጊዜ ይህ ሁኔታ ሊከሰት የቻለው እንዴት ነው? አንዱ ምክንያት ሕዝቡን ለመመገብ ጥቅም ላይ ይውል የነበረው መሬትና እህል ኤታኖል የተባለ ነዳጅ ለማምረት መዋሉ ነው። ዘ ዊትነስ የተባለው የደቡብ አፍሪካ ጋዜጣ እንዲህ ብሏል፦ “አንድ የመስክ መኪናን ለአንድ ጊዜ ያህል ብቻ ለመሙላት የሚያገለግል ኤታኖል ለማምረት የሚውለው እህል ለአንድ ሰው የዓመት ቀለብ ሊሆን ይችላል።” የምግብ ዋጋ መናር በበለጸጉ አገሮች የሚኖሩ በርካታ ሰዎችን ሳይቀር ከዕለት ጉርሳቸው አሊያም እንደ መድኃኒትና የቤት ማሞቂያ ከመሳሰሉት አስፈላጊ ነገሮች መካከል አንዱን እንዲመርጡ አስገድዷቸዋል።
“ራብም . . . በልዩ ልዩ ስፍራ ይሆናል” (ማቴ. 24:7)
በሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ ብዙ ጊዜ ረሀብ ደርሷል። ይሁን እንጂ በ20ኛው መቶ ዘመን ረሀብ ምን ያህል ተስፋፍቷል? የዓለም ጦርነት በአውሮፓና በእስያ ረሀብ እንዲስፋፋ አድርጓል። አፍሪካ በአስከፊ ድርቅ በመመታቷ ምክንያት ተርባለች። በ1980 መጨረሻ ላይ 450 ሚልዮን ሰዎች ለሞት በሚያደርስ ረሀብ ተጐድተው እንደነበርና እስከ አንድ ቢልዮን የሚደርሱ ሰዎች ደግሞ በቂ ምግብ እንዳልነበራቸው የምግብና የእርሻ ድርጅት ገምቷል። ከእነዚህ ውስጥ በአንድ ዓመት ውስጥ 40 ሚልዮን (በአንዳንድ ዓመታት እስከ 50 ሚልዮን ይደርሳል) የሚያክሉት ይሞታሉ።
“በልዩ ልዩ ሥፍራ ቸነፈር . . . ይሆናል” (ሉቃስ 21:11)
ይህ በዚህ ዘመን የሚታየው የምግብ እጥረት የተለየ ባሕርይ አለውን? አዎ፤ አለው። የምግብ እጥረት ያለው እህል ሳይጠፋ ነው። አንዳንድ አገሮች እጅግ የተትረፈረፈ እህል አላቸው፤ እህሉን ለተቸገሩት በአጭር ጊዜ ውስጥ ለማድረስም ዘመናዊ መጓጓዣ አላቸው። ይሁን እንጂ ብሔራዊ ፖሊሲና የንግድ ጥቅም ጋሬጣ ሆነዋል። እንዲያውም በሚልዮን የሚቆጠሩ ዜጎቻቸው ተርበው እያሉ ምርጥ እህላቸውን የተትረፈረፈ እህል ላላቸው አገሮች ይሸጣሉ። ይህ ዓይነቱ ሁኔታ በአንድ አካባቢ ብቻ የተወሰነ ሳይሆን ዓለም አቀፋዊ ስፋት ያለው ነው። ዘ ኒው ዮርክ ታይምስ በ1981 እንዲህ በማለት ገልጾ ነበር:- “የኑሮ ደረጃ መሻሻሉና በዓለም ዙሪያ የምግብ ተፈላጊነት እየጨመረ መሄዱ የምግብ ዋጋ ከፍ እንዲል ተጽዕኖ በማድረጉ ድሀ አገሮች የምግብ ፍላጎታቸውን ከውጪ አገሮች በማስመጣት ለማሟላት ከብዶባቸዋል።” በብዙ አገሮች በዘመናዊ ሳይንስ የሚታገዘው የምግብ ምርት በየጊዜው ከሚጨምረው የሕዝብ ቁጥር ጋር በሚተካከል መጠን ሊያድግ አልቻለም። ዘመናዊ የምግብ ኤክስፐርቶች ለችግሩ ምንም ዓይነት ትክክለኛ መፍትሔ አላገኙም።
ከባድ የመሬት መናወጦች። ኢየሱስ “ታላቅ የመሬት መናወጥ” እንደሚሆን ተናግሯል። (ሉቃስ 21:11) በዛሬው ጊዜ፣ ሰዎች ከመቼውም ጊዜ ይበልጥ በመሬት መናወጥ ምክንያት ጉዳት እየደረሰባቸው እንዳለ የሚሰማን ከሆነ አልተሳሳትንም። በ2007 ረጀንደር ቻዳ የተባሉ የምድርን ነውጥ የሚያጠኑ ሕንዳዊ፣ “ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የመሬት መንቀጥቀጥ በዓለም ዙሪያ በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩን ማስተዋል ችለናል” በማለት ተናግረዋል። አክለውም “ይህ ለምን እንደሆነ ግን ማንም አያውቅም” ብለዋል። ከዚህም በላይ ለመሬት መንቀጥቀጥ በተጋለጡ አካባቢዎች ላይ የሚኖሩ ሰዎች ቁጥር በፍጥነት ማደጉ በእነዚህ አደጋዎች የሚሞቱት ሰዎች ቁጥር እንዲጨምር አድርጓል። የዩናይትድ ስቴትስ የጂኦሎጂ ጥናት ተቋም እንዳለው ከሆነ፣ በ2004 የሕንድ ውቅያኖስን የመታው የመሬት መንቀጥቀጥና ከዚያ ጋር ተያይዞ የተነሳው ሱናሚ “ባለፉት 500 ዓመታት ውስጥ ከደረሱት የመሬት መናወጦች ሁሉ እጅግ አስከፊ ጉዳት የደረሰበት” ዓመት እንዲሆን አድርጎታል።
“ታላቅም የምድር መናወጥ . . . ይሆናል” (ሉቃስ 21:11) ባለፉት መቶ ዘመናት ትልልቅ የመሬት መንቀጥቀጦች ደርሰው እንደነበር እውነት ነው። በተጨማሪም ሳይንቲስቶች በመሣሪያዎች አማካይነት በየዓመቱ ከአንድ ሚልዮን የሚበልጡ የመሬት መንቀጥቀጦችን ይመዘግባሉ። ታላላቅ የምድር መናወጦች መድረሳቸውን ለማወቅ ግን ልዩ መሣሪያ አያስፈልገም።
በኮሎራዶ ቦልደር ከሚገኘው ብሔራዊ የጂኦፊዚካል የመረጃ ማዕከልና ከሌሎች የመረጃ ምንጮች የተገኙትን ተጨማሪ መረጃዎች በመውሰድ በሬክተር መለኪያ 7.5 ወይም ከዚያ በላይ የሆኑ ወይም አምስት ሚልዮን ዶላር ወይም ከዚያ በላይ የሚገመት የንብረት ጥፋት ያደረሱ ወይም ለ100 ሰዎች ወይም ከዚያ በላይ ለሚሆኑ ሰዎች ሕልፈት ምክንያት የሆኑ የመሬት መንቀጥቀጦች ብቻ በሰንጠረዥ ተዘርዝረው በ1984 ቀርበው ነበር። ከ1914 በፊት በነበሩት የ2,000 ዓመታት ጊዜ ውስጥ እንዲህ የመሰሉ የመሬት መንቀጥቀጦች 856 ጊዜ ደርሰው ነበር። ከ1914 ወዲህ ባሉት 69 ዓመታት ውስጥ ብቻ 605 ተመሳሳይ የመሬት መንቀጥቀጦች እንደደረሱ ይኸው ሰንጠረዥ ያሳያል። ይህም ማለት ከ1914 ወዲህ በአንድ ዓመት ውስጥ በአማካይ የደረሱት የመሬት መንቀጥቀጦች ከ1914 በፊት ከነበሩት 2,000 ዓመታት ጋር ሲወዳደሩ 20 ጊዜ ይበልጣሉ ማለት ነው።
‘የዓመፃ መብዛት፤ እንዲሁም የብዙ ሰዎች ፍቅር መቀዝቀዝ’ (ማቴ. 24:11, 12) ስለ ወንጀል ምርምር የሚያደርጉ አንድ ባለሙያ “በዓለም ደረጃ የሚፈጸመውን ወንጀል ስትመለከቱ የሚያስደነግጣችሁ ነገር በየቦታው የሚፈጸመው ወንጀል እየተስፋፋ መሄዱና ከቁጥጥር ውጭ መሆኑ ነው። ወንጀል ያልተስፋፋባቸው ገለልተኛ አካባቢዎች በጣት የሚቆጠሩ ናቸው። እነርሱም ቢሆኑ እየጨመረ በሚሄደው የወንጀል ጎርፍ መጥለቅለቃቸው አይቀርም” ብለዋል። (ዘ ግሮውዝ ኦቭ ክራይም (የወንጀል መብዛት)፣ ኒው ዮርክ፣ 1977፣ ሰር ሊዎን ራድዚኖቪች እና ጆአን ኪንግ፣ ገጽ 4, 5) ያለማጋነን ወንጀል ጨምሯል። ጭማሪው ወንጀሎች ከቀድሞው በተሻለ ሁኔታ ሪፖርት የሚደረጉ በመሆናቸው የመጣ አይደለም። ባለፉት ትወልዶችም ቢሆን ወንጀለኞች እንደነበሩ አይካድም። ይሁን እንጂ እንደ አሁኑ ወንጀል በየቦታው የተስፋፋበት ጊዜ አልነበረም። በዕድሜ የገፉት ሰዎች ይህንን ከግል ተሞክሯቸው አረጋግጠዋል።
በትንቢቱ ውስጥ የተጠቀሰው ዓመፅ ሰዎች ለታወቁት የእግዚአብሄር ሕጎች ንቀት ማሳየታቸውንና በሕይወታቸው ቀዳሚውን ቦታ የሚሰጡት ለእግዚአብሄር ሳይሆን ለራሳቸው መሆኑን ይጨምራል። እንዲህ ዓይነት አቋም በመስፋፋቱ የተነሣ ፍቺ በጣም እየጨመረ ሄዷል። ከጋብቻ ውጪ የሚደረግ ሩካቤ ሥጋና ግብረ ሰዶም በሰፊው ተቀባይነት አግኝተዋል። በየዓመቱ በብዙ ሚልዮን የሚቆጠር ውርጃ ይፈጸማል። ይህ ዓመፅ (በማቴዎስ 24:11, 12 ላይ የተጠቀሰው) የራሳቸውን ትምህርት ከእግዚአብሄር ቃል አስበልጠው የእግዚአብሄርን ቃል ወደ ጎን ገሸሽ ካደረጉት የሐሰተኛ ነቢያት ተጽዕኖ ጋር ይዛመዳል። ሰዎች ከመጽሐፍ ቅዱስ ይልቅ የእነርሱን ፍልስፍና መከተላቸው ፍቅር የለሽነት በዓለም በሙሉ እንዲስፋፋ አስተዋፅኦ አድርጓል። (1 ዮሐ. 4:8) ስለዚህ ጉዳይ በ2 ጢሞቴዎስ 3:1–5 ላይ የሚገኘውን መግለጫ አንብብ።
“የሚያስፈራም ምልክት ይሆናል” (ሉቃስ 21:11)
ዩኤስ ኒውስ ኤንድ ወርልድ ሪፖርት “ዛሬ በሕይወታችን ላይ የሰለጠነው ትልቅ ስሜት ፍርሃት ነው” ብሏል። (ጥቅምት 11, 1965፣ ገጽ 144) ሆርሱ የተባለው የጀርመን መጽሔት ደግሞ “ሰዎች እንደ ዛሬው በፍርሃት የተዋጡበት ጊዜ የለም” ብሏል። ቁጥር 25፣ ሰኔ 20, 1980፣ ገጽ 22
ለዚህ ዓለም አቀፍ የሆነ የፍርሃት አየር አስተዋጽኦ ያደረጉ ብዙ ነገሮች አሉ። ከምክንያቶቹ መካከል ኃይል የታከለበት ወንጀል፣ ሥራ አጥነት፣ ብዙ አገሮች ሊወጡ በማይችሉት ዕዳ ውስጥ በመዘፈቃቸው ምክንያት የመጣው የኢኮኖሚ አለመረጋጋት፣ ዓለም አቀፍ የአካባቢ መበከል፣ ጠንካራ መተሳሰርና ፍቅር የሰፈነበት ቤተሰብ አለመኖሩ፣ በሰው ልጅ ላይ ያንዣበበው የኑክሌር እልቂት ይገኙባቸዋል።
‘የክርስቶስ እውነተኛ ተከታዮች በስሙ ምክንያት በሁሉም ሕዝቦች ዘንድ የተጠሉ ይሆናሉ’ (ማቴ. 24:9) የኢየሱስ ክርስቶስ ተከታዮች ስደት የሚደርስባቸው በፖለቲካ ጉዳዮች ውስጥ ጣልቃ ገብተው ስለሚዘባርቁ ሳይሆን ‘ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ስም’ ነው። ተከታዮቹ የእግዚአብሄርን ስለሚከተሉ፣ ከማንኛውም ምድራዊ ገዥ አስበልጠው ክርስቶስን ስለሚታዘዙ፣ለመንግሥቲቱ በታማኝነት ስለሚቆሙና በሰብዓዊ መንግሥታት ጉዳዮች ጣልቃ ስለማይገቡ ይሰደዳሉ። የዘመናችን ታሪክ እንደሚያረጋግጠው ክርስቲያኖች በሁሉም የምድር ክፍሎች ስደት ደርሶባቸዋል። ‘ይህ የመንግሥት ወንጌል ምሥክር እንዲሆን በዓለም ሁሉ ይሰበካል (ማቴ. 24:14)
ሉቃስ 21:31, 32:- “ይህ ሁሉ መሆኑን ስታዩ የእግዚአብሔር መንግሥት እንደ ቀረበች [ማለትም መንግሥቲቱ የአሁኑን ክፉ ዓለም የምታጠፋበትና የምድርን ጉዳዮች ሙሉ በሙሉ የምትቆጣጠርበት ጊዜ እንደደረሰ] እወቁ። እውነት እላችኋለሁ፣ ይህ ሁሉ እስኪሆን ድረስ ይህ ትውልድ አያልፍም።”
“የሁለተኛው የዓለም ጦርነት ይህ ጦርነት ለአዲስ የታሪክ ምዕራፍ መክፈቻ እንደሆነ አድርጎ ይታስባል። . . . የራሳችንን ከንቱነት፣ ይኸውም ከታሪክ ጋር ፊት ለፊት የመጋጠማችንን ሐቅ መቀበል ይገባናል። ይሁን እንጂ በማኅበራዊ ኑሮ ረገድ ይበልጥ ወሳኝ የሆነ ለውጥ የተደረገው ከአንደኛው ዓለም ጦርነት በኋላ መሆኑን ማወቅ ይኖርብናል። ለበርካታ መቶ ዘመናት ሲገነቡ የቆዩት ፖለቲካዊና ማኅበራዊ ሥርዓቶች በጥቂት ሳምንታት ውስጥ የፈራረሱት በዚህ ጊዜ ነበር። አንዳንዶቹ ሁኔታዎች ቀድሞ ወደነበሩበት ሁኔታ ሊመለሱ በማይችሉበት መልክ ተለውጠዋል። ለብዙ ዘመናት የቆዩት የተረጋጉ ሁኔታዎች የተናጉት በአንደኛው የዓለም ጦርነት ነበር። . . . ሁለተኛው የዓለም ጦርነት ደግሞ ይህንን ለውጥ ገፋበት፣ አረጋገጠው፣ አጠናከረው። ከማኅበራዊ ኑሮ አንፃር ከታየ ሁለተኛው የዓለም ጦርነት የአንደኛው ዓለም ጦርነት መጠናቀቂያ ነበር።” ዘ ኤጅ ኦቭ አንሰርቴኒቲ (መተማመን የጠፋበት ዘመን)፣ (ቦስተን፣ 1977) ጆን ኬ ጋልብሬዝ፣ ገጽ 133
“አሁን ግማሽ መቶ ዘመን የሚያክል ጊዜ አልፎአል፣ ይሁን እንጂ የትልቁ ጦርነት [ የፈነዳው አንደኛው ዓለም ጦርነት] አሳዛኝ ሁኔታ በሕዝቦች አካልና ነፍስ ላይ የተወው ጠባሳ ገና አልጠፋም። . . . ይህ መዓት በአካልና በሥነ ምግባር ላይ ያስከተለው ጉዳት ከፍተኛ በመሆኑ ምንም ነገር እንደ ድሮው ሊሆን አልተቻለም። መላው ኅብረተሰብ፣ የመስተዳድር ሥርዓቶች፣ ብሔራዊ ወሰኖች፣ ሕጎች፣ የጦር ኃይሎች፣ በብሔራት መካከል ያሉት ግንኙነቶች፣ ርዕዮተ ዓለም፣ የቤተሰብ ኑሮ፣ ሀብት፣ ሥልጣን፣ ሰብዓዊ ግንኙነቶች፣ ማንኛውም ነገር ከላይ እስከታች ተለውጧል። . . . የሰው ልጅ ሚዛኑን ሳተ፤ እስከ ዛሬም የድሮው ቦታው አልተመለሰም።” ጄነራል ቻርለስ ደ ጎል፣ በ1968 የተናገሩት (ለ ሞንድ፣ ኅዳር 12, 1968፣ ገጽ 9)
ማቴ. 24:21, 22:- “በዚያን ጊዜ ከዓለም መጀመሪያ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ያልሆነ እንግዲህም ከቶ የማይሆን ታላቅ መከራ ይሆናልና። እነዚያ ቀኖችስ ባያጥሩ ሥጋ የለበሰ ሁሉ ባልዳነም ነበር፤ ነገር ግን እነዚያ ቀኖች ስለ ተመረጡት ሰዎች ያጥራሉ።” (ስለዚህ ከጥፋቱ የሚተርፍ ጥቂት ‘ሥጋ ለባሽ’ ይኖራል ማለት ነው)።
ምሳሌ 2:21, 22:- “ቅኖች በምድር ላይ ይቀመጣሉና፣ ፍጹማንም በእርስዋ ይኖራሉና፤ ኃጥኣን ግን ከምድር ይጠፋሉ፣ ዓመፀኞችም ከእርስዋ ይነጠቃሉ።”
መዝ. 37:29, 34:- “ጻድቃን ምድርን ይወርሳሉ፣ በእርስዋም ለዘላለም ይኖራሉ። እግዚአብሔርን ደጅ ጥና፣ መንገዱንም ጠብቅ፣ ምድርን ትወርስ ዘንድ ከፍ ከፍ ያደርግሃል፤ ኃጢአተኞችም ሲጠፉ ታያለህ።”
እግዚአብሄር ክፉዎችን ሳያጠፋ ይህን ያህል ጊዜ የቆየው ለምንድን ነው? 2 ጴጥ. 3:9:- “ለአንዳንዶች የሚዘገይ እንደሚመስላቸው ጌታ [“የእግዚአብሄር” ስዓት] ስለ ተስፋ ቃሉ አይዘገይም፣ ነገር ግን ሁሉ ወደ ንስሐ እንዲደርሱ እንጂ ማንም እንዳይጠፋ ወዶ ስለ እናንተ ይታገሣል።”
ማር. 13:10:- “አስቀድሞም ወንጌል ለአሕዛብ ሁሉ ይሰበክ ዘንድ ይገባል”። ማቴ. 25:31, 32, 46:- “የሰው ልጅ [ኢየሱስ ክርስቶስ] በክብሩ በሚመጣበት ጊዜ ከእርሱም ጋር ቅዱሳን መላእክቱ ሁሉ፣ በዚያን ጊዜ በክብሩ ዙፋን ይቀመጣል አሕዛብም ሁሉ በፊቱ ይሰበሰባሉ፤እረኛ በጎቹን ከፍየሎች እንደሚለይ እርስ በርሳቸው ይለያቸዋል፣እነዚያም[የክርስቶስ መንፈሳዊ ወንድሞች የሆኑትን የንጉሡ ወኪሎች እንደሆኑ አድርገው ያልተቀበሉት] ወደ ዘላለም ቅጣት [“ጥፋት” ስዓት]፣ ጻድቃን ግን ወደ ዘላለም ሕይወት ይሄዳሉ።”
ዛሬ ያሉት ሁኔታዎች ከቀድሞው የተለዩ አይደሉም። ጦርነት፣ ረሀብ፣ የመሬት መንቀጥቀጥ፣ ወንጀል ጠፍቶ አያውቅም’ የተወለድነው እነዚህ ነገሮች ዕለታዊ ዜና በሆኑበት ዓለም ውስጥ ነው። ይሁን እንጂ 20ኛው መቶ ዘመን ልዩ የሚሆንበት የራሱ ባሕርይ እንዳለው ታሪክ ጸሐፊዎች ይናገራሉ። ‘ነገሩን ልዩ የሚያደርገው ጦርነት፣ ረሀብ፣ የመሬት መንቀጥቀጥና ወንጀል መኖራቸው አይደለም። ኢየሱስ የሰጠው ምልክት ብዙ ነገሮችን አጣምሮ የያዘ ነበር ‘ኢየሱስ አንድ ድርጊት ብቻውን “በመጨረሻው ቀን” ውስጥ እንደምንገኝ ያረጋግጣል ብሎ አልተናገረም። ልዩ ትርጉም የሚኖረው ምልክቶቹ በሙሉ መታየታቸው ነው። በተለይ ምልክቶቹ በመጽሐፍ ቅዱስ የዘመን አቆጣጠር ተለይቶ በሚታወቅ ዓመት ጀምሮ በመላው ዓለም መታየቱ ልዩ ትርጉም የሚያሰጠው ነው።”
‘ማን ያውቃል፤ ትንቢቱ የበለጠ የሚፈጸምበት ሌላ ትውልድ ቢመጣስ?’ እንዲህ በማለት ልትመልስ ትችላለህ:- መልሱም ‘በመጨረሻ ቀኖች’ ውስጥ የምንኖር መሆናችንን ጐላ አድርጎ ያሳያል። እንዴት? ኢየሱስ የሰጠው ምልክት በሕዝቦችና በመንግሥታት መካከል ጦርነት እንደሚኖር ይናገራል። ይህ ምልክት የሚፈጸመው በኃያላን መንግሥታት መካከል በሚደረግ ሌላ አጠቃላይ ጦርነት ነው ብንል ምን ይሆን ነበር? እንዲህ የመሰለ ጦርነት ቢነሣ በሕይወት የሚተርፍ ሰው አይኖርም። ስለዚህ ከእልቂት የሚተርፉ ሰዎች እንዲኖሩ የእግዚአብሄር ዓላማ መሆኑ ወደዚህ ሥርዓት ፍጻሜ በጣም መቅረባችንን ያሳያል።’ ወይም እንዲህ ማለት ትችላለህ:- ‘የዓለምን ሁኔታዎች ከዚህ ትንቢት ጋር ማዛመድ የጣት አሻራን ከአሻራው ባለቤት ጋር እንደማዛመድ ነው።
ይህን ዓይነት አሻራ የሚኖረው ሌላ ሰው ሊኖር አይችልም። በተመሳሳይም በ1914 የጀመሩት ሁኔታዎች ወደፊት በሚመጣ ትውልድ ውስጥ አይደገሙም።’ ከዚያም ምናልባት እንዲህ በማለት ልትቀጥል ትችላለህ:- (1) ‘የዚህ ምልክት ክፍል የሆኑት ነገሮች ሁሉ በግልጽ እየታዩ ነው።’ (2) ‘መቼም በኖኅ ዘመን እንደነበሩት ሰዎች መሆን እንደማንፈልግ የተረጋገጠ ነው። (ማቴ. 24:37–39)’
‘መጨረሻው በእኛ የሕይወት ዘመን አይመጣም’ ‘ይሁን እንጂ አንድ ወቅት ላይ እግዚአብሄር ጣልቃ ገብቶ እርምጃ እንደሚወስድ ያምናሉ፤ አይደለም?’ ከዚያም ምናልባት እንዲህ በማለት ልትቀጥል ትችላለህ:- (1) ቀኑን ወይም ሰዓቱን ማንም ማወቅ እንደማይችል ኢየሱስ በግልጽ አስረድቷል። ቢሆንም ይህ ጥፋት በሚመጣበት ጊዜ በሚኖረው ትውልድ ዘመን ስለሚሆኑት ነገሮች በዝርዝር ገልጿል።’ (2) ‘ኢየሱስ ስለዚህ ጉዳይ የሰጠው መግለጫ እርስዎ በግል የሚያውቋቸውን ነገሮች ይጨምራል። ‘ስለ እነዚህ ነገሮች አልጨነቅም፤ እኔ የማስበው ስለዛሬው ቀን ብቻ ነው’ እንዲህ በማለት ልትመልስ ትችላለህ:- ‘ስለወደፊቱ ጊዜ ከመጠን በላይ አለመጨነቅ ጥሩ ነው። ሆኖም ግን ሁላችንም በራሳችንም ሆነ በምንወዳቸው ሰዎች ላይ ጉዳት በማያደርስ ሁኔታ ለመኖር ዕቅድ ለማውጣት እንሞክራለን። ተግባራዊ ሊሆን የሚችል ዕቅድ ማውጣት ተገቢ ነው።
መጽሐፍ ቅዱስ ከፊታችን አስደናቂ ነገሮች እንደሚጠብቁን ይናገራል። በእነዚህ አስደናቂ ነገሮች ለመጠቀም የሚያስችለንን ዕቅድ ብናወጣ ጥበበኞች እንሆናለን። (ምሳሌ 1:33፤ 2 ጴጥ. 3:13)
‘ስለ እነዚህ መጥፎ ሁኔታዎች ማሰብ አልፈልግም። ስለወደፊቱ ሁኔታ ብሩህ አመለካከት እንዲኖረኝ እፈልጋለሁ’ ማለት ትችላለህ:- ‘እንዲያውም ባይገርምዎ፤ ኢየሱስ በዘመናችን የሚኖሩት ተከታዮቹ ስለወደፊቱ ጊዜ ብሩህ ተስፋ እንዲኖራቸው የሚያስችል ምክንያት እንደሚኖራቸው ተናግሯል። (ሉቃስ 21:31)’ ከዚያም ምናልባት እንዲህ በማለት ልትቀጥል ትችላለህ:- ‘ይሁን እንጂ በዓለም የሚሆኑትን ነገሮች እንዳያዩ ዓይናቸውን ጨፍነው እንዲደሰቱ እንዳልነገራቸው ልብ ይበሉ። በጥሩ ምክንያት ላይ የተመሠረተ ተስፋ እንደሚኖራቸው ተናግሯል። የዓለምን ሁኔታዎች ትርጉም ስለሚረዱና ውጤታቸውም ምን እንደሚሆን ስለሚያውቁ ተስፋቸው ጽኑ መሠረት አለው።’
ሥነ ምግባራዊ ውድቀትና ማኅበራዊ ቀውስ። “የመጨረሻው ቀን” ያለውን እውነታ በሥነ ምግባር ጉዳዮች ረገድ ለብዙ መቶ ዘመናት ዋነኛ መመሪያ ሆኖ በስፋት ሲሠራበት ከቆየው መጽሐፍ ማለትም የእግዚዝብሄር ቃል ከሆነው ከመጽሐፍ ቅዱስ አኳያ እንመልከተው። በዛሬው ጊዜ ያለውን ዓለም መጽሐፍ ቅዱስ በሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ እጅግ ወሳኝ የሆነውን ዘመን አስመልክቶ ከሚሰጠው ትንቢታዊ መግለጫ ጋር ማነጻጸሩ ሁኔታውን በጥልቀት ለማስተዋል ይረዳል። መጽሐፍ ቅዱስ ይህን እጅግ ወሳኝ የሆነ ዘመን የ“መጨረሻው ቀን” ወይም “የነገሮች ሥርዓት መደምደሚያ” በማለት ይጠራዋል። (2 ጢሞቴዎስ 3:1፤ ማቴዎስ 24:3) እነዚህ መግለጫዎች እንደሚያሳዩት ይህ ጊዜ የአንድን ዘመን ማብቂያና የአዲስ ዘመን መባቻን የሚያመለክት ነው። የእግዚዝብሄር ቃል የመጨረሻው ቀን “የሚያስጨንቅ ዘመን” እንደሚሆን ይናገራል። መጽሐፍ ቅዱስ በንቃት የሚከታተሉ ሰዎች የመጨረሻውን ቀን ለይተው ማወቅ እንዲችሉ የዚህ በዓይነቱ ልዩ የሆነ ወቅት ግልጽ መግለጫ ወይም ጥምር ምልክት ሆነው የሚያገለግሉ በርካታ ዝርዝር ሁኔታዎች ይገልጻል።
ኢየሱስ “ክፋት ስለሚገን የብዙ ሰዎች ፍቅር ይቀዘቅዛል” ብሏል። (ማቴዎስ 24:12) ኢየሱስ ከተናገረው ትንቢት በተጨማሪ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ማኅበራዊና ሥነ ምግባራዊ እሴቶች እያሽቆለቆሉ እንደሚሄዱ ጠቁሟል። ቅዱስ ጳውሎስ፣ የእግዚአብሄር መንግሥት ይህን ሥርዓት ከማጥፋቱ በፊት ባለው ‘የመጨረሻ ዘመን’ ውስጥ ስለሚኖሩት አስጨናቂ ሁኔታዎች ሲገልጽ እንዲህ ብሏል፦ “ሰዎች ራሳቸውን የሚወዱ ይሆናሉ፤ ገንዘብን የሚወዱ፣ ትምክሕተኞች፣ ትዕቢተኞች፣ ተሳዳቢዎች፣ ለወላጆቻቸው የማይታዘዙ፣ የማያመሰግኑ፣ ቅድስና የሌላቸው፣ ፍቅር የሌላቸው፣ ለዕርቅ የማይሸነፉ፣ ሐሜተኞች፣ ራሳቸውን የማይገዙ፣ ጨካኞች፣ መልካም የሆነውን የማይወዱ፣ ከዳተኞች፣ ችኩሎች፣ በከንቱ በትዕቢት የተወጠሩ፣ ከእግዚአብሔር ይልቅ ተድላን የሚወዱ ይሆናሉና። ሃይማኖታዊ መልክ አላቸው፤ ኀይሉን ግን ክደዋል።” (2 ጢሞቴዎስ 3:1-5) በአሁኑ ጊዜ ሰዎች እንዲህ ያሉ መጥፎ ባሕርያትን ከመቼውም ጊዜ ይበልጥ ሲያሳዩ አልተመለከትክም?
ጌታ ኢየሱስና ቅዱስ ጳውሎስ አሁን ላለው የዓለም ሁኔታ ምክንያት የሆኑትን ታሪካዊ፣ ማኅበራዊና ፖለቲካዊ ሁኔታዎች በሙሉ አልዘረዘሩም። ይሁንና የተናገሯቸው ትንቢቶች በዛሬው ጊዜ የምናያቸውን ክስተቶችና የሰዎችን ባሕርይ በትክክል የሚገልጹ ናቸው። ስለ ወደፊቱ ጊዜስ ምን ማለት ይቻላል? ስለ መሲሑ መምጣት በትክክል የተነበየው የኢሳይያስ መጽሐፍ የእግዚአብሄር መንግሥት በምድር ላይ ስለሚያመጣቸው በረከቶችም ይገልጻል።
ቅዱስ ጳውሎስ በመጀመሪያው መቶ ዘመን በኤፌሶን የነበሩትን ክርስቲያኖች እንዲህ ሲል መክሯቸዋል:- “እንግዲህ እንደ ጥበበኞች እንጂ ጥበብ እንደሌላቸው ሳይሆን እንዴት እንድትመላለሱ በጥንቃቄ ተጠበቁ፤ ቀኖቹ ክፉዎች ናቸውና ዘመኑን ዋጁ።” (ኤፌሶን 5:15, 16) ይህ ምክር አስፈላጊ የነበረው ለምንድን ነው? ይህንን ጥያቄ ለመመለስ አሁን በቶሮንቶ በሌሎችም ትላልቅ የአለም ታዋቂ ከተሞች እንደሚታዩት ፈተናዎች ሁሉ በዚያች ጥንታዊ ከተማ ይኖሩ የነበሩት ክርስቲያኖች ስለተጋፈጧቸው ፈተናዎች በቂ ግንዛቤ ማግኘቱ አስፈላጊ ስለሆነ ነበር።
ኤፌሶን በከፍተኛ ብልጽግናዋ፣ ጸያፍ በሆነው ሥነ ምግባሯ፣ በተስፋፉት የወንጀል ድርጊቶቿና በተለያዩ አጋንንታዊ ተግባሮቿ በሰፊው የምትታወቅ ከተማ ነበረች። ከዚህም በተጨማሪ እዚያ የነበሩት ክርስቲያኖች ጊዜን አስመልክቶ ከሰፈነው ፍልስፍና ጋር መታገል ነበረባቸው። በኤፌሶን የሚኖሩት ክርስቲያን ያልሆኑ ግሪካውያን ጊዜ በአንድ አቅጣጫ ይጓዛል ብለው አያምኑም ነበር። የግሪክ ፍልስፍና ሕይወት ማቆሚያ የሌለው የዑደት ድግግሞሽ እንደሆነ አስተምሯቸው ነበር። ጊዜውን በአንድ ዓይነት የሕይወት ዑደት ውስጥ ያባከነ ሰው ያንኑ ጊዜውን በሌላ ዑደት መልሶ ሊያገኘው ይችላል። እንዲህ ያለው አስተሳሰብ የኤፌሶን ክርስቲያኖች በእግዚአብሄር መለኮታዊ ፍርድ የሚያስፈጽምበትን ጊዜ ጨምሮ ለነገሮች ያወጣውን የጊዜ ሠሌዳ በተመለከተ የግድየለሽነት ዝንባሌ እንዲያዳብሩ ሊያደርጋቸው ይችል ነበር። ስለዚህ ቅዱስ ጳውሎስ “ዘመኑን ዋጁ” የሚል ምክር መስጠቱ ተገቢ ነበር።
እዚህ ላይ ቅዱስ ጳውሎስ እንዲሁ ስለ ጊዜ መናገሩ አልነበረም። የተጠቀመበት የግሪክኛ ቃል ለአንድ ለተለየ ዓላማ አመቺ የሆነን ወይም የተወሰነን ጊዜ ያመለክታል። ቅዱስ ጳውሎስ የመጀመሪያው መቶ ዘመን ክርስቲያኖች መለኮታዊ ምህረት ማግኘትና ከተዘረጋላቸው የመዳን ዝግጅት መጠቀም የሚችሉበት ጊዜ ከማለቁ በፊት ያገኙትን ምቹ ጊዜ ወይም የሞገስ ዘመን በጥበብ እንዲጠቀሙበት መምከሩ ነበር። ሮሜ 13:11-13፤ 1 ተሰሎንቄ 5:6-11
እኛም በተመሳሳይ ምቹ በሆነ ጊዜ ውስጥ እንገኛለን። ክርስቲያኖች ዓለም የሚያቀርባቸውን ጊዜያዊ ደስታ የሚያስገኙ ነገሮች በመከታተል ይህንን ፈጽሞ የማይደገም የሞገስ ዘመን ከማባከን ይልቅ ጊዜያቸውን ‘ለእግዚአብሄር ማደራቸውን የሚያሳዩ ሥራዎች’ ለመሥራትና ፈጣሪ ከሆነው ከእግዚአብሄር አምላክ ጋር ያለንን የልጂና የአባት ግንኙነት ለማጠንከር ከተጠቀሙበት ጥበበኞች ናቸው።2 ጴጥሮስ 3:11፤ መዝሙር 73:28፤ ፊልጵስዩስ 1:9, 1
0 comments:
Post a Comment