Friday, July 12, 2019


ስለአእምሮ ጤንነት አንዳንድ እውነቶች
በሁሉም የዓለም ክፍል የሚኖሩ በብዙ መቶ ሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች በአእምሮ ሕመም ይሠቃያሉ፤ እንዲሁም ችግሩ በቤተሰቦቻቸውና በወዳጆቻቸው ሕይወት ላይ ጫና ይፈጥራል። ከአራት ሰዎች መካከል አንዱ በሕይወቱ ውስጥ በሆነ ወቅት ላይ የአእምሮ ሕመም ያጋጥመዋል። ለዚህ ዓለም አቀፍ ችግር ዋነኛው መንስኤ የመንፈስ ጭንቀት ነው። በጣም ከባድ ከሆኑትና በሰዎች ላይ ተጽዕኖ ከሚያሳድሩት የአእምሮ ሕመሞች መካከል ስኪትሰፍሪኒያ እና ባይፖላር ዲስኦርደር ይገኙበታል። . . . በጣም ብዙ ሰዎች በአእምሮ ሕመም የሚጠቁ ቢሆንም ችግሩ አሁንም በድብቅ የሚያዝ ከመሆኑም ሌላ ችላ ይባላል፤ በተጨማሪም እንዲህ ዓይነት በሽታ ያለባቸው ሰዎች መድሎ ይፈጸምባቸዋል።” የዓለም የጤና ድርጅት
የዓለም የጤና ድርጅት እንደገለጸው በአእምሮ ሕመም የተያዙ ብዙ ሰዎች ከኅብረተሰቡ መገለል ስለሚያስፈራቸው ሕክምና ከማግኘት ወደኋላ ይላሉ።
አብዛኞቹ የአእምሮ ሕመሞች በሕክምና መዳን ይችላሉ፤ ያም ቢሆን በዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ባለፈው ዓመት ብቻ የአእምሮ ሕመም ያለባቸው 60 በመቶ ገደማ የሚሆኑ አዋቂዎችና 50 በመቶ የሚሆኑ 8 እስከ 15 ባለው የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ወጣቶች ሕክምና እንዳላገኙ በአእምሮ ሕመም ለተያዙ ሰዎች እርዳታ የሚሰጥ አንድ ተቋም ዘግቧል።
የአእምሮ ሕመምግንዛቤያችንን ማስፋት
የአእምሮ ሕመም ምንድን ነው? አንድ ሰው የአእምሮ ሕመም አለበት የሚባለው ከሚያስብበት መንገድ፣ ከስሜቱ እንዲሁም ከባሕርይው ጋር በተያያዘ ጉልህ የሆነ እክል ሲያጋጥመው እንደሆነ ባለሙያዎች ይናገራሉ። ይህ ችግር ያለበት ሰው ብዙውን ጊዜ የሌሎችን ስሜት መረዳትና የኑሮ ጫናዎችን መቋቋም ይከብደዋል።
የአእምሮ ሕመም የሚመጣው በግል ድክመት ወይም በባሕርይ ችግር አይደለም
የሕመሙ ምልክት ይኸውም ችግሩ የሚቆይበት የጊዜ ርዝመትም ሆነ የሥቃዩ መጠን ከሰው ሰው ይለያያል፤ ምልክቱ ግለሰቡን በያዘው የበሽታ ዓይነትና ግለሰቡ ባለበት ሁኔታ ላይ የተመካ ነው። ሕመሙ ፆታ፣ ዕድሜ፣ ባሕል፣ ዘር፣ ሃይማኖት ወይም የትምህርት ደረጃና የገቢ መጠን ሳይለይ ማንኛውንም ሰው ሊያጠቃ ይችላል። የአእምሮ ሕመም የሚመጣው በግል ድክመት ወይም በባሕርይ ችግር አይደለም። እንዲህ ዓይነት የጤና እክል ያለባቸው ሰዎች ተገቢውን የሕክምና ክትትል ካደረጉ ሊድኑ ብሎም ስኬታማና አርኪ ሕይወት ሊመሩ ይችላሉ።
የአእምሮ ሕመምሕክምና
የአእምሮ ጤና ባለሙያዎች የተለያዩ የአእምሮ ችግሮችን በተሳካ መንገድ ማከም ይችላሉ። በመሆኑም የመጀመሪያው ወሳኝ እርምጃ፣ የአእምሮ ሕመምን በማከም ረገድ ተሞክሮ ያካበተ ብቃት ያለው የጤና ባለሙያ ዘንድ ሄዶ የተሟላ ምርመራ ማድረግ ነው።

የአእምሮ ሕመምተኞች እንዲህ ካለው እርዳታ ተጠቃሚ ሊሆኑ የሚችሉት የሚሰጣቸውን ሕክምና ለመቀበል ፈቃደኞች ከሆኑ ብቻ ነው። ይህን ለማድረግ ደግሞ የአእምሮ ሕመምን በተመለከተ ከሌሎች ጋር ለመነጋገር የሚሰማቸውን ፍርሃት ማሸነፍ ሊያስፈልጋቸው ይችላል። ሕክምናው ከሠለጠኑ የአእምሮ ጤና ባለሙያዎች ጋር መነጋገርን ይጨምራል፤ እነዚህ ባለሙያዎች ታካሚው ስለ ሕመሙ ግንዛቤ እንዲያገኝ፣ በዕለት ተዕለት ሕይወቱ የሚያጋጥሙትን ችግሮች እንዲወጣና ሕክምናውን ሳያቋርጥ እንዲከታተል ሊረዱት ይችላሉ። ግለሰቡ እንዲህ ያለ ሕክምና በሚከታተልበት ጊዜ አንድ የቤተሰቡ አባል ወይም ወዳጁ ከጎኑ ሆኖ ሊያበረታታውና ድጋፍ ሊሰጠው ይችላል።
ብዙ ሰዎች ስለ ሕመማቸው የተሻለ ግንዛቤ በማግኘታቸውና በአእምሮ ጤና ባለሙያዎች የሚታዘዝላቸውን ሕክምና በመከታተላቸው ሕመሙን ተቋቁመው እየኖሩ ነው።  አንድ ስው ባለቤቴ የአእምሮ ሕመም እንዳለባት ከማወቃችን በፊት ስለዚህ ሕመም ምንም የምናውቀው ነገር አልነበረም ማለት ይቻላል። አሁን ግን ነገሮችን እንዳመጣጣቸው መቀበልና ከሁኔታው ጋር መላመድ ችለናል። በተጨማሪም እምነት ከሚጣልባቸው ባለሙያዎች እንዲሁም ከቤተሰቦቻችንና ከወዳጆቻችን የምናገኘው ድጋፍ ጠቅሞናል።
የመጀመሪያው ወሳኝ እርምጃ፣ የአእምሮ ሕመምን በማከም ረገድ ተሞክሮ ያካበተ ብቃት ያለው የጤና ባለሙያ ዘንድ ሄዶ የተሟላ ምርመራ ማድረግ ነው እንዲህ ብላለች አንድ ሴት፦መጀመሪያ ላይ የምርመራው ውጤት ሲነገረኝ እስር ቤት እንደገባሁ ሆኖ ተሰማኝ። ያለብኝ የጤና እክል በሁለታችንም ላይ የአቅም ገደብ ቢያስከትልም በጣም አስቸጋሪ የሚመስሉ መሰናክሎችንም መቋቋም እንደሚቻል ተገንዝቤያለሁ። በመሆኑም ከሕክምና ቡድኑ ጋር ተባብሬ በመሥራት፣ ከሌሎች ጋር ያለኝን ዝምድና በማጠናከርና ሕይወትን እንዳመጣጡ በመቀበል ያለብኝን ሕመም መቋቋም ችያለሁ።
መንፈሳዊ ጤንነት አስፈላጊ ነው
መጽሐስ ቅዱስ እኔ ፈዋሽህ አምላክህ እግዚአብሄር ነኝ ብሎት ስለእግዚአብሄር ፈዋሽነት ይናገራል፤  ያም ሆኖ በዓለም ዙሪያ የሚገኙ ብዙ ቤተሰቦች መጽሐፍ ቅዱስ ከሚያስተምረው ነገር ማጽናኛና ማበረታቻ አግኝተዋል። ለምሳሌ ያህል፣ መጽሐፍ ቅዱስ፣ አፍቃሪው ፈጣሪያችንልባቸውና መንፈሳቸው የተሰበረሰዎችን እንደሚያጽናና ያረጋግጥልናል። መዝሙር 34:18
መጽሐፍ ቅዱስ የሕክምና መጽሐፍ ባይሆንም ሥቃይ የሚያስከትሉ ስሜቶችንና አስጨናቂ ሁኔታዎችን ለመቋቋም የሚረዳ ሐሳብ ይዟል። በተጨማሪም መጽሐፍ ቅዱስ ወደፊት በምድር ላይ ከሕመምና ከሥቃይ ነፃ የሆነ ሕይወት የምንመራበት ጊዜ እንደሚመጣ ይናገራል። የአምላክ ቃል የሚከተለውን ተስፋ ይሰጣል፦በዚያን ጊዜም የዕውር ዐይኖች ይገለጣሉ፤ የደንቈሮም ጆሮዎች ይከፈታሉ። አንካሳ እንደ ሚዳቋ ይዘላል፤ የድዳውም አንደበት በደስታ ይዘምራል።”—ኢሳይያስ 35:5, 6
ለአጻጻፍ እንዲያመች ሲባል፣ በዚህ ርዕስ ውስጥየአእምሮ ሕመምየሚለው ስያሜ የአእምሮ በሽታዎችን እንዲሁም የባሕርይና የሥነ ልቦና መቃወስን ያካትታል።
ከአእምሮ ሕመም ጋር መታገል
ውስጤ እስከሚረብሽ ጊዜ እጨነቃለሁ አንዳንዴማ ከቤቴም መውጣት እራሱ ማስቡ ያስፈራኛል፣ የምፈራውም ብዙ ጊዜ “ፓኒክ አታክ”  ይይዘኛል፤ ያኔማ አዕምሮዬም ውስጤም ተረብሾ ላብ ያስመጠኛል፣ ያኔውኑ የምሞት ይመስለኛል፣ ይህ ስቃይ የሚቆይብኝ ለሁለት ደቂቃ ያህል ነው፤ ይህ የማይወደድ ልምድ ስላለኝ ከቤት መውጣት አይሆንልኝም። ስለራሴ የለኝ ህሳቤ ዘቀተኛ ነው፣  ስለምጨነቅ አንዳንድ ነገሮችን ማከናወን እንደማልችል ሆኖ የሚሰማኝ ጊዜ አለ፤ አንዳንድ ጊዜ ለማንበብ እንኳ ትኩረቴን መሰብሰብ አልችልም። በሌሎች ጊዜያት ደግሞ ከባድ የመንፈስ ጭንቀት ስለሚኖርብኝ ከሰዎች አልፎ ተርፎም ከጓደኞቼም ጭምር እሸሻለሁ። አንዳንድ ሰዎች ያለብኝ ችግር በቅርቡ መፍትሔ ማግኘቱ እንደማይቀር ወይም እኔን ያስጨነቀኝ ነገር የማስበውን ያህል የከፋ እንዳልሆነ በመናገር ሊያጽናኑኝ ይሞክራሉ። ሌሎች ደግሞ ሁልጊዜ ስለኑሮ አሉታዊ ህሳቤን በንግግሬም ሆነ በኑሮዬ እንደአስተዋሉ ይነግሩኛል እናም አዎንታዊ እንድሆን ይነግሩኛል። እኔም ይህን ለማድረግ ጥረት ባደርግም አልስራልኝም።  እርግጥ ነው፣ እንዲህ የሚሉኝ ለእኔ አስበው እንደሆነ ይገባኛል፤ ያም ቢሆን እንዲህ ያሉ አስተያየቶች ያለብኝ የጥፋተኝነትና የከንቱነት እንዲሁም አልረባም የሚል ስሜት እንዲባባስ ከማድረግ ውጭ የሚፈይዱት ነገር የለም።ትላለች አንድ ጭንቀት ያስቸገራት ሴት
የአእምሮ ሕመምን ተቋቁሞ መኖር
የአእምሮ ሕመምን ተቋቁሞ መኖር የአዕምሮ ሕመም ችግር አለባቸሁ የተባላችሁት ሁሉ ብቃት ባላቸው የአእምሮ ጤና ባለሙያዎች የታዘዘላችሁን ሕክምና  በትክክል ውስዱ ወይም ተከታተሉ።
በደረጃችሁ በየ ዕለቱ የምታከናውኑት ዕለታዊ ተግባሮቻችሁን የምታከናውኑበት ሚዛናዊና ቋሚ ፕሮግራም ይኑራችሁ። ለምሳሌ እንደሚከተሉት ያሉትን ተግባራት በትክክል አከናውኑ፦
  አካላዊ እንቅስቃሴ አድርጉ።
·        በቂ እንቅልፍ አግኙ።
·        በየዕለቱ ዘና የምትሉበት ጊዜ መድቡ።
·        ገንቢና የተመጣጠነ ምግብ ተመገቡ።
·        ከአልኮል መጠጥና በሐኪም ካልታዘዙላችሁ መድኃኒቶች ጋር በተያያዘ ገደብ አብጁ።
·        ብቻችሁን አትሁኑ፤ ከምታምኗቸውና ከሚያስቡላችሁ ሰዎች ጋር ጊዜ አሳልፉ።
·        ለመንፈሳዊ ፍላጎታችሁ ትኩረት ስጡ።
ክርስቲያኖች የሚያደርጉት የትኛውም ዓይነት ሕክምና ከመጽሐፍ ቅዱስ መመሪያዎች ጋር የሚጋጭ እንዳይሆን ጥንቃቄ ማድረግ አለባቸው።

0 comments:

Post a Comment