Tuesday, December 4, 2018

የሕብረተስብ ጤንነት




ሕብረተስብ ጤንነት

ክፍል  1

በዶ/ አመለወርቅ

 

በመጽሐፍ ቅዱስ ጊዜ የታወቁት ህዝቦች ፍልስጤምና ግብጻውያን ኢትዮጵያውያን ወዘተ ነበሩ። የፍልስጤም ሕብረተስብ በጥንት ጊዜ ከግብጽም በበለጠ ጤነኛ ሕብረተስብ የሚገኝበት ተብሎ ይወስድ ነበር። የግብጽ ሕብረተስብ ጤንነት በምን አይነት ደርጃ ላይ እንደነበረ (ዘዳግም 715 ዘዳግም 2860 አሞጽ 410) የተመለከቱት ጥቅሶች ያመለክታሉ። በእብራውያን ህብረተስብ መካከል የጽዳቱ ሥርዕትና በቀሳውስቱ የሚደረገው ቁጥጥር የህዝቡ የጤና ጥበቃው ወደ ክፍተኛ ደርጃ አድርሶታል፤ ነገር ግን ይኸው የጽዳቱ ሥርዕትና ቁጥጥር በስፋት የተራመደ አልነበረም፤ በመጽሐፍ ቅዱስ ጊዜ  የነበሩት በሽታዎች ለጉዳት የሚዳርጉ የስውነት ትኩሳቶች የጠነከሩ የቆዳ በሽታዎች ሽባነት ተቅማጥ የተለያዩ የአይን በሽታዎች ሲሆኑ እነዚህም በሽታዎች በበሽተኛው ላይ መንፈሳዊና ሥነ-ልቡናዊ ጫና ላይ ያስከትላሉ። በመጽሐፍ ቅዱስ ጊዜ የነበሩት በሽታዎች እየተባባሱ የሄዱበት ወቅት ነበር ከነዚህም መሃከል የተለያዩ የስውነት ትኩሳቶች ተቅማጥ የቆዳ ላይ ለምጽ ወይም ቁምጥና የአንጀት ውስጥ ትላትል መቅስፍት የነርቭ በሽታዎች (እንደሽባነት) የተለያዩ የአይን በሽታዎች እነዚህም በተለያዩ ስሞች ተስጥቷቸዋል። እነዚህም ስሞች ሕመም ወይም ደዌ በሽታ ሥቃይ ሲሆኑ እነዚህም 2 ነገስት 12:  2 ነገሥት 88 ማቴ. 935 ማቴ. 817 ዮሐ. 54 ሉቃ. 721 መዝ. 387 ተመልክተዋል።   በአሁንም ዘመን ስድስት ተላላፊ በሽታዎች የተነሳ ከሚሞቱ ሰዎች መካከል 90% ምክንያት ኤች አይ / ኤድስ የተቅማጥ በሽታ ሳንባ ነቀርሳ ወባ እና ኩፍኝ  አጣዳፊ የመተንፈሻ ኢንፌክሽን (ሞት ሊያስከትል ይችላል)ተላላፊ በሽታዎች በአብዛኛው  እነዚህ በሽታ-አምጪ ጀርሞች ባክቴሪያዎች  ቫይረሶች ፈንገሶች protozoans, እና ጥገኛ ትሎች ውስጥ የተለያዩ ያካትታሉ።

የመጀመሪያው ስለፓራሳይቶች ጽሑፍ 3000 እስከ 400 BC በግብጾች በፓፓይረሳቸው ላይ ተጽፎ የተገኘው ነው።

በጽሁፉም ውስጥ ራውንድዎርምስ ጊኒዎርምስ ትሬድዎርምስ ቴፕዎርመስ እንደነበሩ ያመለክታል።

እንደ ግብጻውያንም የጥንቶቹ ግሪኮች ሂፓክራተስና አሪስቶትል አያሌ ፓራሳይቶችን አጥንተው መዝገበዋል። ከተመዘገቡትም መሃከል በሄፓክራተስና በአሪስቶትል በወቅቱ የነበሩትን Corpus Hippocraticus በተባለው መጽሐፋቸው ውስጥ የመዘገቧቸው ነበሩ። በዚህ መጽሐፍ ውስጥ አያሌ ፓራሳይቶች በአሳዎችና በቤት እንስሳትና በስዎች ወስጥም እንደሚገኙ አስቀምጧል። ፓራሳይቶችም በሽታዎችንም እንደሚያመጡ ጠቀስዋል ከነዚህም መሃከል በጊኒዎርም የተነሳ የሚመጣው በሽታ dracunculiasis የተባለው ነበር።

በዚያን ጊዜ በተለያየ ባህል ውስጥ የነበሩት ሕዝቦች እንደ አረቦችና ባቢሎናውያን እንደዚሁ

ስለፓራሳይቶች ጽሑፍ ነበራቸው። በጥንቱ ግሪክና ሮማውያን ጽሑፍ ውስጥ ብዙ ፓራሳይቶች የተለዩ አይደሉም ምክንያቱም የበሽታዎቹ ምልክቶች ከሌሎቹ በሽታዎች ይመሳስላሉ ከሚመሳስሉትም መሃከል ፍሉ የብርድ በሽታ ተቅማጥ ናቸው። እንደ እለፋንታያሲስ (Elephantiasis) ሲስቶሶማያሲስ (Schistosomiasis) ወባ (Malaria) እና አሜባ (Amebiasis) ያሉት በሽታዎች መነሻቸው ከፓራሳይቶች የተነሳ ቢሆንም የተለየ የበሽታ ምልክቶች እንደሚያስከተሉም የሕክምና ጽሑፋቸው ያመለክታል። በጊኒዎርም የሚነሱት በሽታዎች በጥንቃቄ ተጽፈው የተገኙት ሴቷ የጊኒዎርም የምተፈላው በቆዳ ላይ ስለሆነ ይህም የሚያምና የማቃጠል ምልክቶችን ስለሚያመጣ የሚታለፍ አልነበረም። ይህም የተለየ በሽታ በመጽሐፍ ቅዱስ በብሉይ ኪዳን በስፋት “fiery serpents” ተብሎ ተወስዷል።

ስሜን አፍሪካ መከከለኛው ምስራቅና ሞሶፓታሚያ

የጥንቱ የፓርሺያው ዶክተር Avicenna አያሌ ፓራሳይቶች በእንስሶችም ሆነ በበሽተኞቹ ውስጥ እንዳሉ መዝግቧል ከመዘገባቸውም መሃከል የጊኒዎርም የትሬድዎርምስ ቴፕዎርምስና አስካሪስ ዎርምስ ይገኙበታል። ይህም የአረቦች ባህላዊ ህክምና ከሺ አመታት በላይ የሚያመላክተው በቀይ ባህር አካባቢ ይሁን እንጂ የህክምናው ጽሑፍ በበሽታዎችንና በፓራሳይቶች መካከል ግንኙነቶች እንዳላቸው አያስረግጥም። የመካከለኛው ምሥራቅ የህክምና እንደግሪኮቹና ሮማውያን ጽሑፍ የጊኒዎርም የበሽታ መነሻ እንደሆነ ጽፏል። በአያሌዎች የአሲሪያን ጽሁፎች ውስጥ በተለይም በንጉስ Ashurbanipal ቤተመጻሕፍት ውስጥ የሚገኙት የጊኒዎርምስ የበሽታ መነሻ እንደሆኑ ያመለክታሉ። በግብጽ ውስጥ Ebers በተባለው በጥንቱ ፓፓይረስ ጽሑፍ ውስጥ የተገኙት ጥቂቶች አመላካቾች ሁክዎርምስ በሽታን እንደሚያመጡ ቢጠቀስም ያስቀመጠው በደፈናው ነበር በሌላው የግብጽ የሕክምና ጽሁፍ ውስጥ ደግሞ ኢለፋንታያሲስ ስለተባለው በሽታ የተጻፈው ምልክቶቹ በእግሮችና በእጆች በጡቶችም በሴትና በወንድ ብልቶች ላይ እብጠትን እንደሚያስከትል ነበር። በኢለፋንታያሲስ ከታመሙትም መሃከል

የግብጽ ፈርኦንን  Mentuhotep II የተባለው ሲሆን በዚሁ በሽታ ከተስቃየ በኋላ እንዳገገመ ተጽፎ ይገኛል።  ኢለፈንታያሲስ የተባለው በሽታ በአረቦች ሃኪሞች Avicenna ጨምሮ ስለበሽታው ከማወቃቸውም ባለፈ በቁምጥናና በኢለፈንታያሲስ መካከል ያለውን ልዩነትም ጥንቀቀው አውቀውት ነበር። በጥንቱም ግብጽ ህብረተስብ ውስጥ ሲስቶሶማያሲስ ይታወታል ሌላው ስሙ ቢላርዚያ ይባላል።

ከላይ ከተጠቀሱት ታሪኮች አንባቢው ፓራስይቶች በተመለከተ በጥንት ጊዜም የነበሩና በአሁኑ ጊዜ የበለጠ እየተባዙ እንዳሉና ለተለያዩ በሽታዎች መነሻዎች እንደሆኑ ከተጻፈው ይረዳል።

በባክቴሪያዎችንና በቫይረሶች የተነሳ የሚመጡ በሽታዎች

1. ባክቴሪያዎች በሽታዎችን ያመጣሉ

አያሌ ጥናቶች አብዛኛውን የስው በሽታ የሚመጣው በባክቴሪያ ወይም በቫይረስ በሚመረዝበት ጊዜ እንደሆነ ያመለክታሉ። እነዚህም ጥናቶች የሚደገፉትና የሚካሄዱት በአሜሪካን በሚገኘው የዲፓርትሜንት ኦፍ ሄልዝ የተላላፈ ሕመሞች መቆጣጠሪያ ክፍል ነው። በካናዳም እንደዚሁ የጥናት ዲፓርትሜንት አለው።

ባክቴሪያዎች እያንዳንዳቸው በተፈጥሮ ነጠላ ሴል ያላቸው ፍጥረቶች ሲሆኑ የሚመሳስሉት ከተክሎች ጋር ነው።  ባክቴሪያዎች በአለም ላይ በየትም ሥፍራ የሚገኙ ሲሆኑ ሁሉም ባክቴሪያዎች መጥፎ አይደሉም ለምሳሌ ያህል በሆድ ውስጥ የሚገኙት ባክቴሪያዎች የቃሚዎች ናቸው። አንዳንዶቹ ባክቴሪያዎች ደግሞ በመመረዝና በሽታዎችን በማምጣት ይታወቃሉ። ባክቴሪያዎች ከመረዙ በኋላ  በሽታዎችን ማምጣት የሚችሉት ፓቶጀኒክ ባክቴሪያዎች ተብለው ይጠራሉ። በባክቴሪያዎች መመረዝ የተነሱ በሽታዎች ሁሉ በአንቲባዮቲክ መድሀኒቶች ይታከማሉ። ይሁን እንጂ አንቲባዮቲክን መጠቀም ደግሞ አስፈላጊ የሆኑትን ባክቴሪያዎች ያጠፋሉ። አንቲባዮቲክን የሚቋቋሙ በክቴሪያዎች ደግሞ ይነሳሉ። ይህንንና የመሳስሉትን በባክቴሪያ የተነሳ የሚመጡትን በሽታዎች ለመከላከል ኮንቬንሽናል ሜዲስን የሚጠቀመው ለዚሁ የተስሩ መድሐኒቶችንና ክትባትን መስጠት ነው።

  2. ቫይረሶች በሽታዎችን ያመጣሉ

ቫይረሶች በስውነት ውስጥ ከገቡ በኋላ በመደበቅ የሚቋቋሙት የግለስቡን የስውነትን ኢሚውን ሲስተም ነው። ቫይረሶች በጣም አነስተኛ ማክሮኦርጋኒዝም ስለሆኑ የሚባዙትም በገቡበት ስውነት ውስጥ  ስለሚሆን በጣም ጠንካራ የሆኑ ተላላፊ በሽታዎች በህክምናው አለም ለማጥፋትም አስቸጋሪ ያደርገዋል።

(ፓቶጀኒክ ባክቴሪያበሽታን አስተላላፊዎቹ ወደ ስው ስውነት የሚገቡበት መንገድ ከዚህ እንደሚከተለው ነው። በአካል ላይ የተቆረጠ ወይም ክፍት በሆነ የስውነት ክፍል በኩል፣ በተበላሽ ምግብ ወይም ውሃ፣  በባክቴሪያዎች ከተመረዘው ግለስብ ጋር በመነካካት፣ በባክቴሪያዎች ከተመረዘው ግለስብ የሚወጡትን እንደ ስገራና ሽንት ሌሎችንም ፈሳሽ በመንካት፣ በባክቴሪያዎች ከተመረዘው ግለስብ ጋር በሚስልበት ወይም በሚያነጥስበት ጊዜ ከውስጡ የሚወጣውን ፈሳሽ ወይም አየር በአጠገቡ ሆኖ በመተንፈስ፣  በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ በባክቴሪያዎች የተመረዘው ግለስብ የተጠቀመባቸውን ዕቃዎችም የፈት መታጠቢያዎች ላይ ያሉትን ቧንቧዎችን የሽንት ቤት ውሃ መለቂያዎች ወዘተ. በመንካት መራዦቹ ባክቴሪያዎች ከተመረዘው ስው ወደጤነኛው የማለፊያ መንገዶች ይሆናሉ።

በቫይረስ የተነሳ  የሚመጡ የጉበት በሽታዎች

ጉበት ከደም ውስጥ መርዛማ ነገሮችን የሚያጣራ ከመሆኑም ባሻገር ቢያንስ ቢያንስ 500 የሚሆኑ ሌሎች አስፈላጊ ተግባራትን ያከናውናል። ሄፕታይተስ ወይም የጉበት ብግነት የአንድን ሰው ጤንነት በእጅጉ ሊጎዳ የሚችለው በዚህ ምክንያት ነው። ሄፕታይተስ አልኮል አብዝቶ በመጠጣት ወይም መርዛማ ለሆኑ ነገሮች በመጋለጥ ሳቢያ ሊመጣ ይችላል። ይሁን እንጂ አብዛኛውን ጊዜ ለሄፕታይተስ መንስኤ የሚሆኑት ቫይረሶች ናቸው። ሳይንቲስቶች ሄፕታይተስ አምጪ የሆኑ አምስት ቫይረሶችን መለየት የቻሉ ሲሆን ቢያንስ ሌሎች ሦስት ዓይነት ቫይረሶችም ሊኖሩ እንደሚችሉ ያምናሉ።

ከአምስቱ ቫይረሶች አንዱ የሆነው ሄፕታይተስ ቫይረስ በየዓመቱ ቢያንስ 600,000 ሰዎችን ይገድላል፤ ይህም በወባ ምክንያት ከሚሞቱ ሰዎች ጋር ይተካከላል። ከሁለት ቢሊዮን የሚበልጡ ሰዎች ማለትም ከዓለም ሕዝብ አንድ ሦስተኛ ገደማ የሚሆኑት በሄፕታይተስ ቫይረስ የተጠቁ ሲሆን አብዛኞቹ በወራት ጊዜ ውስጥ ከበሽታው ድነዋል። ይሁን እንጂ 350 ሚሊዮን በሚሆኑት ሰዎች ላይ በሽታው ሥር ሰዶባቸዋል። እነዚህ ሰዎች በቀሪ ሕይወት ዘመናቸው የበሽታው ምልክት ይኑራቸውም አይኑራቸው በሽታውን ወደ ሌሎች ሊያስተላልፉ ይችላሉ።*

ሥር የሰደደ የሄፕታይተስ ቫይረስ ያለባቸው ሰዎች ገና ከጅምሩ ተገቢውን ሕክምና ካገኙ በጉበታቸው ላይ የሚደርሰውን ከባድ ጉዳት ማስቀረት ይችላሉ። ይሁን እንጂ ሄፕታይተስ ቫይረስ ለዚሁ ተብሎ በሚደረግ ልዩ የደም ምርመራ ካልሆነ በስተቀር ሊታወቅ ስለማይችል አብዛኞቹ ሰዎች በበሽታው እንደተያዙ እንኳ አያውቁም። በተለምዶ የሚደረገው የጉበት ምርመራ እንኳ የበሽታውን ምልክት ላያሳይ ይችላል። በመሆኑም ሄፕታይተስ ቫይረስ አለምንም ማስጠንቀቂያ ለከፋ ጉዳት የሚዳርግ ድምጽ አልባ ገዳይ በሽታ ሊሆን ይችላል። በአንድ ሰው ላይ ግልጽ የሆኑ የሕመም ምልክቶች የሚታዩት በቫይረሱ ከተያዘ ከአሥርተ ዓመታት በኋላ ሊሆን ይችላል። በዚህ ወቅት ግን ሕመሙ ተባብሶ ስሮሲስ የተባለ የጉበት በሽታ ወይም ካንሰር ወደ መሆን ደረጃ ሊደርስ ይችላል። እነዚህ በሽታዎች የሄፕታይተስ ቫይረስ በደማቸው ውስጥ ከሚገኝባቸው አራት ሰዎች መካከል የአንዱን ሕይወት ያጠፋሉ።

በሄፕታይተስ ቫይረስ መመረዝ

የሄፕታይተስ ቫይረስ አንድ ስው ከተመረዘ በህዋላ የበሽታዎቹ ምልክቶች በተመረዘው ስው ላይ ይታያሉ።ለመጀመሪያ ጊዜ የሕመም ምልክት ይታያሉ በወቅቱ ተቅማጥ የያዘውን በሽተኛ  የምዕራባውያን ሕክምና ከሄደ የሚስጡት ህክምና  ሕክምና የሕመሙን ምልክት ለጊዜው የሚያስወግድ ብቻ ሊሆን ይችላል።  የባሕል ሐኪም ዘንድ ከተሄደ ደግሞ እሱም ለአንጀትና ለሆድ የሚሆን መድኃኒት ይስጥህ ይሆናል። ሁለቱም ሐኪሞች ሄፕታይተስ በተመረዘው ስው  እንዳለበት ለማረጋገጥ  ምርመራ አያደርጉም ይሆናል። አንዳንድ ጊዜም ደግሞ ተቅማጡ ሊቆምልኝ ካልቻለ የምዕራባውያን ሕክምና ወደሚሰጠው ሐኪም ተመልሶ መሄድ ያስፈልግ ይሆናል።  የሚያደርገውም ምርመራ የበሽተኛውን ሆድ  በስተቀኝ በኩል ቀስ ብሎ መታ መታ ሲያደርግ ሕመም ሊስማው ይችላል። የደም ምርመራውም  ከተደረገ ደግሞ ጥርጣሬው ትክክል መሆኑን ያረጋግጣል፤ በደም ውስጥ የሄፕታይተስ ቫይረስ ይታያል። በዚህ ጊዜ በሽተኛው እጅግ  ሊደናገጥ ይችላል በሽተኛው ምናልባትም በህክምናው ወቅጥ ደም ወስዶ ሆነ የፆታ ብልግና አልፈጸመም ይሆናል።

በሽተኛው ሄፕታይተስ ቫይረስ የተያዘው ከሌላ  ተጋብቶበት ሊሆን ይችላል ወይስ ሁሉም በበሽታው ለመያዛቸው ምክንያት የሆነው ነገር አንድ ይሆን? ይህን በእርግጠኝነት ማወቅ አይቻልም። እንዲያውም 35 በመቶ የሚሆኑት ሰዎች በቫይረሱ የተያዙት እንዴት እንደሆነ በውል አይታወቅም። ሆኖም ሄፕታይተስ በዘር፣ ተራ በሆነ ንክኪም ሆነ ምግብ አብሮ በመብላት እንደማይተላለፍ በእርግጠኝነት መናገር ይቻላል። ከዚህ ይልቅ ሄፕታይተስ ቫይረስ የሚጋባው በቫይረሱ ከተያዘው ሰው የወጣው ደም አሊያም ሌላ ፈሳሽ (ለምሳሌ ከወንድ ወይም ከሴት ብልት የሚወጣ ፈሳሽ) ወይም ደግሞ ምራቅ በቆሰለ ሰውነት ወይም የአካል ሽፋን በኩል ወደ ሌላ ግለሰብ የደም ሥር በሚገባበት ጊዜ ነው።

በተለይ የሄፕታይተስ ቫይረስ ምርመራ በብዛት በሌለባቸው አሊያም ጨርሶ በማይደረግባቸው አገሮች ቫይረሱ ያለበትን ደም በመውሰዳቸው ምክንያት ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሰዎች ለበሽታው ይዳረጋሉ። ሄፕታይተስ ቫይረስ ከአንዱ ወደ ሌላ የመተላለፍ አቅሙ ኤድስ አምጪ ከሆነው ከኤች አይ ቫይረስ 100 እጥፍ ይበልጣል። በምላጭ ጫፍ ላይ ያለ የደም ቅንጣት እንኳ ሄፕታይተስ ቫይረስ ሊያስተላልፍ የሚችል ሲሆን የደረቀ የደም ጠብታ ለአንድ ሳምንት ወይም ከዚያ ለሚበልጥ ጊዜ ቫይረሱን የማስተላለፍ አቅም ይኖረዋል።

ሁኔታውን በሚገባ መረዳት

ቫይረሱ ስለሚተላለፍበት መንገድ ትክክለኛ ግንዛቤ  ማግኘት ከችግሩ ለማዳን አይነተኛ መንገድ መሆን ያስችላል በቂ እውቀት አላቸው የሚባሉ ሰዎች እንኳ ሄፕታይተስ ቢን ከሄፕታይተስ ጋር ሊያማቱት ይችላሉ። ሄፕታይተስ በቀላሉ የሚተላለፍ ሲሆን ለሞት የመዳረግ አቅሙ ግን አነስተኛ ነው። ከዚህም በተጨማሪ ሄፕታይተስ ቫይረስ በፆታ ግንኙነት የሚተላለፍ በመሆኑ ጨዋ የሆኑ ሰዎች እንኳ በጥርጣሬ ዓይን ሊታዩ ይችላሉ።  ስለ ሁኔታው ትክክለኛ ግንዛቤ አለማግኘትና ጥርጣሬ ከባድ ችግሮች ሊያስከትሉ ይችላሉ። ለምሳሌ በብዙ አካባቢዎች ሰዎች በደማቸው ውስጥ የሄፕታይተስ ቫይረስ ያለባቸውን ሕሙማን ትንሽ ትልቅ ሳይሉ ሁሉንም ያገላሉ። ጎረቤቶች ልጆቻቸው አብረዋቸው እንዲጫወቱ አይፈቅዱም፣ ትምህርት ቤቶች አይቀበሏቸውም፣ አሠሪዎችም ሊቀጥሯቸው ፈቃደኛ አይሆኑም። ሰዎች እንዲህ ያለውን መገለል ስለሚፈሩ የሄፕታይተስ ቫይረስ ምርመራ ከማድረግ ወይም ሕመሙ እንዳለባቸው ከመናገር ወደኋላ ይላሉ። እንዲያውም አንዳንዶቹ እውነታውን ከማሳወቅ ይልቅ የራሳቸውንም ሆነ የቤተሰባቸውን ጤንነት አደጋ ይጥላሉ። በዚህ ምክንያት ይህ ቀሳፊ በሽታ ከትውልድ ወደ ትውልድ ይተላለፋል። በተኛውም ህብረተስብ ውስጥ ያሉ በዚህ በሽታ የተጠቁ ስዎች እራሳቸውን ከመደበቅ ይልቅ ማሳወቅና ለሌሎችም እንዳያስተላለፉ የሞራል ግዴታ አለባቸው። ልክ በኤድስ የተያዘው በሽተኛ እራሱን ኤድስ እንደሌለበት ወስዶ ለሌላው ማስተላለፍ የሞራልና በህግም የሚያስጠይቀው መሆኑን አወቆ ወንደም ሆነ ሴት  ከጤነኛ ግለስብ ጋር የጾታ ግንኙነት ማደርግ እንደሌለባችው ማለት ነው።

እንደዚህ አይነቱ የጤና ችግር በተለይም በቤት እምነት ውስጥ ስለበሽታው አጥፊነት ግንዛቤና እውቀት ባለመኖሩ የተነሳ ትኩረት የሚደረገው በሃይማኖት ትምህረት ላይ ብቻ በመሆኑ ይህ የጤና ችግር እንደሚገባ ትኩረት ሳይስጥበት ቀርቶ በቤተ እምነት ውስጥ ያሉትን ግለስቦች በሃይማኖት ሽፋን ለችግር ሊዳርግ ይቸላል። ይህንንም ሲል አንዳንድ ቤተ እምነቶች በተለይም የኤድስ በሽተኛው በሐኪም ተመርምሮ የኤድስ መድሐኒት እንዲወስድ ሃኪሙ ካዘዘው በህዋላ ተፈውስሃል ተብሎ መድሂኒቱን ከተወ በህዋላ ለበለጠ ችግር የሚዳርግ ህመምተኛ  አለ። ይህም ብቻ አይደለም አንዳንዱ ደግሞ በራሱ ምርጫ የመድሐኒቱን ሳይድ ኢፊክት ስለሚያስቸግራቸው የታዘዘላቸውን መድሐኒት ከመውስድ ይልቅ ሞታቸውን የሚመርጡ ግለስቦች ይኖራሉ።

የእረፍት አስፈላጊነት

ለሁለትም አይነት በሽተኞች የሚያስፈልጋቸው አሉታዊ አስተሳስብና በአ ዕምሮኦም በአካልም ማረፍ ነው። ከዚህም አልፎ ባለፈው እንደጠቀስኩት  ተመጣጣኝ ምግቦችን መመገብ አስፈላጊ ነው። ሐኪም ሙሉ በሙሉ እረፍት ከውጥረት ነጻ የሆነ ኑሮ መኖር እንዳለበት  ለሽተኛው  ሃኪሙ መክሮታል።  በደም ምርመራም ሆነ በሲቲ ስካን ምንም ዓይነት የስሮሲስ ምልክት ላይታይና ደህና ደህንነት መስማት ይቻል ይሆናል። በዚህ ህመም የተያዘ በሽተኛ ውጥረት የበዛበት ከሆነ ለምሳሌ ውጥረት የበዛበት  ያለዕራፍት የስራ እንደሆነ  ደም ውስጥ ያለው የቫይረስ መጠን በጣም ከፍ ስላለ ከፍተኛ ድካም ሊስማው ይችላል። በሽተኛውን ከድካሙና ከህመሙ ጥንካሬ የተነሳ ሥራው ለመተው ይገደዳል።

 ከሄፕታይተስ ጋር መኖር

በሽታው ከባሰበት የሚኖሩት አማራጮች በጣም ውስን ናቸው። ፀረ-ቫይረስ መድኃኒቶች ቫይረሱን ሙሉ በሙሉ ሊያስወግዱለት አይችሉም። ከዚህም ሌላ መድኃኒቶቹ አስከፊ የሆነ የጎንዮሽ ጉዳት ሊያስከትሉ ይችላሉ። የመጨረሻው አማራጭ ጉበቱን ማስቀየር ቢሆንም ጉበት የሚለግሳቸው ሰው ለማግኘት እየተጠባበቁ ያሉት ሕመምተኞች ቁጥር ከለጋሾቹ ቁጥር በእጅጉ ይበልጣል። ይሁን እንጂ ይህን እያሰቡ መቆዘም የሚፈይደው ነገር የለም።

የአንድ ሰው በሽታ ተከላካይ ሕዋሳት ቫይረሱን በስድስት ወር ጊዜ ውስጥ ከሰውነት ማስወገድ ካልቻሉ በሽታው ሥር እንደ ሰደደ ይቆጠራል። በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ደም በሚፈስበት ጊዜ አንድ እጅ በረኪናን 10 እጅ ውኃ በመበጥበጥ ጓንት አድርጎ የፈሰሰውን ደም ወዲያውኑ በሚገባ ማጽዳት ያስፈልጋል። ሌሎችም ጠንካራ አኒቲ ቫይረስ ፈሳሽ ኬሚካሎችን በመጠቀም አካባቤውን መጽዳት አስፈላጊ ነው።  ይህም ቫይረሱ እንዳያገገምና በተለያየ መንገድ ወደ ሌሎች እንዳይተላለፍ ለማድረግ ይረዳል።

መጽሐፍ ቅዱስ በሽታ ስለማይኖርበት ዓለም የሚሰጠውን ተስፋ በሚመለከት ራእይ 21:3, 4 እንዲሁም ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው? የተባለውን መጽሐፍ ተመልከት። ይህም ቢሆን እንክዋን በምድር ላይ በሽተኛው ስለሚኖር ቶሎ ሕክምና መውሰድ ጉዳቱ እንዳይባባስ ሊረዳ ይችላል። ሰዎች ያገሉኛል የሚለው ፍራቻ ብዙዎች የሄፕታይተስ ቫይረስ ምርመራ ከማድረግም ሆነ ቫይረሱ እንዳለባቸው ከመናገር ወደኋላ እንዲሉ ያደርጋቸዋል።

ሄፕታይተስ የሚያመጡ አምስት ዓይነት ቫይረሶች እንዳሉ የሚታወቅ ሲሆን በስፋት የታወቁት ሄፕታይተስ ኤ፣ እና የሚባሉት ሦስቱ የቫይረስ ዓይነቶች ናቸው። ሌሎች ቫይረሶችም ሊኖሩ እንደሚችሉ ይገመታል። ሁሉም ዓይነት የሄፕታይተስ በሽታዎች እንደ ኢንፍሉዌንዛ ያለ የሕመም ምልክቶችን የሚያስከትሉ ሲሆኑ ዓይንን ቢጫ ሊያደርጉ ወይም ላያደርጉ ይችላሉ። ብዙ ሰዎች በተለይም ደግሞ ትናንሽ ልጆች ምንም ዓይነት የሕመም ምልክት አይታይባቸውም። በሽታው ሄፕታይተስ ወይም ሄፕታይተስ በሚሆንበት ጊዜ የሕመም ምልክቶች መታየት የሚጀምሩት ጉበት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ከደረሰ በኋላ ሊሆን ይችላል።

ሄፕታይተስ ቫይረስ

ሄፕታይተስ ቫይረስ በበሽታው በተያዘ ሰው ዓይነ ምድር ውስጥ ይገኛል። ቫይረሱ በጨዋማም ሆነ ጨዋማ ባልሆነ ውኃ እንዲሁም በበረዶ ውስጥ ሳይሞት ሊቆይ ይችላል። አንድ ሰው በሚከተሉት መንገዶች ለሄፕታይተስ ቫይረስ ሊጋለጥ ይችላል፦

መጸዳጃ ቤት ከገቡ በኋላ፣ በበሽታው የተያዘ ሕፃን ሽንት ጨርቅ ከለወጡ በኋላ ወይም ምግብ ከማዘጋጀት በፊት እጅን በደንብ አለመታጠብ

በሰው ዓይነ ምድር ከተበከለ የውኃ አካል የተገኘን ዓሣና ሌሎች የባሕር ምግቦች ሳያበስሉ መብላት ወይም የተበከለ ውኃ መጠጣት

በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር የሚደረግ አካላዊ ንክኪ ወይም አብሮ መብላትና መጠጣት አሊያም የመመገቢያ ዕቃዎችን በጋራ መጠቀም

ሄፕታይተስ

አጣዳፊ ሕመም የሚያስከትል ይሁን እንጂ አብዛኛውን ጊዜ ሥር አይሰድም። አብዛኛውን ጊዜ ሰውነታችን በራሱ በሳምንታት ወይም በወራት ጊዜ ውስጥ ቫይረሱን ያስወግደዋል። እረፍት ከማድረግና ጥሩ ምግብ ከመመገብ ሌላ ይህ ነው የሚባል የተለየ ሕክምና የለውም። ጉበት ሙሉ በሙሉ እንደዳነ በሐኪም ከመረጋገጡ በፊት አልኮል መጠጣትና ጉበት ላይ ጫና ያመጣሉ የሚባሉ እንደ አሲታሚኖፊን ያሉ መድኃኒቶችን መውሰድ ተገቢ አይደለም። ሄፕታይተስ ቫይረስ አንድ ጊዜ የያዘው ሰው ተመልሶ በዚሁ ቫይረስ አይያዝ ይሆናል እንጂ ሌላ ዓይነት የሄፕታይተስ በሽታዎች ሊይዙት ይችላሉ። ሄፕታይተስ ኤን በክትባት መከላከል ይቻላል።

ሄፕታይተስ ቫይረስ

ሄፕታይተስ ቫይረስ በበሽታው በተያዙ ሰዎች ደም እንዲሁም ከብልታቸው በሚወጡ ፈሳሾች ውስጥ ይገኛል። እንደነዚህ ያሉት ፈሳሾች ቫይረሱን የመከላከል አቅም በሌለው ሰው ሰውነት ውስጥ በሚገቡበት ጊዜ ቫይረሱ ይዛመታል። ቫይረሱ በሚከተሉት መንገዶች ሊተላለፍ ይችላል፦

በወሊድ ወቅት (በቫይረሱ ከተያዘች እናት ወደ ልጅ)

በተገቢው መንገድ ከጀርም ያልጸዳ የሕክምና፣ የጥርስ፣ የንቅሳት ወይም ሰውነትን ለመብሳት የሚያገለግል ሌላ መሣሪያ

መድኃኒት ለመስጠት የሚያገለግል መርፌን፣ ምላጭን፣ የጥፍር መሞረጃን ወይም መቁረጫን፣ የጥርስ ብሩሽን ወይም በቆሰለ የአካል ክፍል በኩል የደም ቅንጣትን ሊያስተላልፍ የሚችል ማንኛውንም ሌላ መሣሪያ በጋራ መጠቀም

የፆታ ግንኙነት

ሄፕታይተስ ቫይረስ በትናንሽ ነፍሳት ወይም በሳል፣ እጅ በመጨባበጥ፣ በመተቃቀፍ፣ ጉንጭ ላይ በመሳሳም፣ ጡት በማጥባት ወይም አብሮ በመብላትና በመጠጣት እንዲሁም እንደ ሹካ ያሉ ሌሎች የመመገቢያ መሣሪያዎችን በጋራ በመጠቀም እንደማይተላለፍ የጤና ባለሙያዎች ያምናሉ። አብዛኛውን ጊዜ አዋቂ የሆኑ ሰዎች ሄፕታይተስ ቫይረስ ተይዘው ከዳኑ በኋላ ሰውነታቸው ዳግመኛ በዚህ በሽታ እንዳይያዙ የሚያደርግ የመከላከያ አቅም ያዳብራል። ትናንሽ ልጆች ሥር በሰደደ ኢንፌክሽን የመያዛቸው አጋጣሚ ከፍተኛ ነው። ተገቢው ሕክምና ካልተደረገ በስተቀር ሥር የሰደደ የሄፕታይተስ በሽታ ጉበት ሥራውን እንዲያቆም በማድረግ ለሞት ሊዳርግ ይችላል። ሄፕታይተስ ቢን በክትባት መከላከል ይቻላል።

ሄፕታይተስ ቫይረስ

ሄፕታይተስ ቫይረስ የሚተላለፍበት መንገድ ከሄፕታይተስ ቫይረስ ብዙም ያልተለየ ቢሆንም አብዛኛውን ጊዜ የሚተላለፈው በተበከለ መርፌ ዕፆችን በመውሰድ ነው። ሄፕታይተስ ምንም ዓይነት መከላከያ ክትባት የለውም።

የሄፕታይተስ ቫይረስን ዑደት ማቆም

ሄፕታይተስ በመላው ዓለም የሚኖሩ ሰዎችን የሚያጠቃ ቫይረስ ቢሆንም ሥር የሰደደ የሄፕታይተስ በሽታ ካለባቸው ሰዎች 78 በመቶ የሚሆኑት የሚኖሩት በእስያና በፓስፊክ ደሴቶች ነው። በእነዚህ አገሮች ውስጥ ከሚኖሩት 10 ሰዎች መካከል አንዱ በደሙ ውስጥ ይህ ቫይረስ ይገኛል። በዚያ የሚገኙ አብዛኞቹ ሕሙማን በቫይረሱ የሚያዙት በወሊድ ጊዜ ከእናታቸው ስለሚተላለፍባቸው አሊያም ሕፃናት ሳሉ በበሽታው ከተያዙ ሌሎች ሕፃናት ደም ጋር ንክኪ ስለሚኖራቸው ነው። ለአራስ ልጆችና ለቫይረሱ ተጋላጭ ለሆኑ ሌሎች ሰዎች የሚሰጠው ክትባት ይህን ዑደት ለማስቆም በሚደረገው ጥረት ከፍተኛ አስተዋጽኦ በማድረግ ላይ ነው።* ክትባት በሚሰጥባቸው አገሮች የበሽታው ስርጭት በእጅጉ ቀንሷል።

 

 3. ፓራሳይቶች የተለያዩ በሽታዎችን ያመጣሉ

ፓራሳይቶች ለተለያዩ በሽታዎች መነሻ ናቸው። ፓራሳይቶች ሕይወት ያላቸውና በስውነት ውስጥ ከገቡ በኋላ በገቡበት ስውነት ውስጥ የሚኖሩና የሚመገቡት የገቡበትን ስውነት ሴሎችና ግለስቡ የሚመገበውን ምግብ ወይም እንደተጨማሪ የሚውስዳቸውን ሁሉ በመጋራት ነው። ፓራሳይቶች ብዙ አይነት አላቸው እነዚህም በሁለት ይከፈላሉ ወርምስና ፕሮቶዞዋ ይባላሉ። ፕሮቶዝዋን የሚባሉት ነጠላ ሴሎች ያሏቸው የሚመገቡትም ኦርጋኒክ ኮምፓውንድ እንደ ናይትሮጂንና ካርቦንን ነው ለዚህም ጥሩ ምሳሌ የሚሆኑት አሜባዎች አሜባ ናቸው። አሜባዎች ትናንሽ ከሚሆናቸው የተነሳ የሚታዩት በማክሮስኮፓ ነው። ሌሎቹ ክፍሎች ደግሞ ዎርምስ ናቸው ዎርሞች ብዙ ሴሎች ያላቸው ሲሆን በመጠናቸውም የተለያዩ ናቸው። ዎርሞች ወደ ስው ስውነት ውስጥ

ከገቡ የገቡበትን ሥፍራ በመባዛት ይቆጣጠሩታል። ለምሳሌ ከዎርሞች መሃከል እንደ ፒንዎርምስና ቴፕዎርምስ ወደ ስው ስውነት ውስጥ ከገቡ በኋላ አንጀትንም ሆነ የገቡበትን ስውነት ይቆጣጠሩታል። ቴፕዎርምስ (የኮሶ ትሎች) በኢትዮጵያ ውስጥ የታወቁ ናቸው። በተለይም የመተላለፊያው መንገድ በኮሶ ትል የተመረዘ የከብት ጥሬ ሥጋ የበላ ስው በዚሁ በኮሶ ትሎች ይመረዛል። ስለሆነም ጥሬ ሥጋ ያለመብላት ከዚሁ ችግር ለመዳን ይረዳል። ባለንበት ዘመን ውስጥ ፓራሳያቶች በሽታዎችን እንደሚያመጡ ሐኪሞችም እንኳ እምብዛም ትኩረት የስጡበት በተለይም በምዕራቡ አለም አይመስልም። ይሁን እንጂ አንድ ስው በፓራሳይቶች ከተመረዘ ለተለያዩ በሽታዎች የተጋለጠ እንደሆነ ጥናቶች ያመለክታሉ።

በፓራሳይቶች የመመርዝ ምልክቶች

የሕክምና ጽሑፎች ስለፓራሳይት የጻፉት ተቅማጥ ከማምጣታቸውን ከዳይት የሚገኙት ንጥረ-

ነገሮች ወደ የስውነት በሚገባ እንዳይዳረስ የሚያደርጉት ፓራሳይቶች ናቸው ከሚለው ግኝታቸው ሌላ ለበሽታዎች መነሻዎች እንደሆኑ አጠንክረው አልጠቀሱም።  ይሁን እንጂ ፓራሳይቶች ከስው ስውነት ውስጥ ከገቡ በኋላ  በሽታዎችንና ምልክቶቻቸውም ያስከትላሉ። ከሚያስከትሏቸው ምልክቶችንም ማሃከል በእንቅልፍ ልብ (በአልጋ ላይ መሽናት)ያልታወቀ የምግብ አለርጂዎች በአይኖች ሥር በክቡ ጥቁረቶች  (መበለዝ) የሚገማ ሽታ ያለው ተቅማጥ በተለይም በቀኑ መጨረሻ ይብሳል፣ የሆድ ድርቀት ወይም የተቅማጥ መቀያየር፣ የሆድ ውስጥ ጩኸት ከረሃብ ወይም ከመብላት ጋር ያለተገናኘ ቃር ወይም የደረት ላይ ሕመም፣  የጉንፋን አይነት ምልክቶች ካሉ (እንደሳል ተኩሳት የአፍንጫ መዘጋት፣ በአፍንጫ  በጆሮዎችና በፊንጣጣ አካባቢ ማታ ማታ ማሳከክ፣ እራብን ያስከተለ የክብደት መቀነስ፣ የደም ማነስ፣  በስገራ ውስጥ ደም ካለ፣ የሆድ ውስጥ አየር መብዛት መነፋት፣ የምግብ ፍላጎት ማጣት፣ ማቅለሽለሽ፣ ማስታወክ፣ የአፍና የድድ ቁስለት፣ የማያቋርጥ የአፍንጫ ማሳከክ፣ የጥርስ ማፏጨት በተለይም ማታ ወይም በእንቅልፍ ልብ፣ ከባድ ድካም፣ የራስ ምታት፣ የጡንቻ  ላይ ሕመም፣ የትንፋሽ ማጠር፣ በቆዳ ላይ ሽፍታ፣ ድባቴና ማስታወስ ያለመቻል ናቸው።        

      ፓራሳይቶች የሴንትራል ነርቭስ ሲስተም (የአንጎል ክፍል) ይመርዛሉ

1. የሴንትራል ነርቭስ ሲስተምን (የአንጎልን ክፍል) በመመረዙ የታወቀው ፓራሳይት Toxoplasma gondii ነው። ስዎች በዚህ ፓራሳይት የሚመረዙት ያልተቀቀለ ሥጋ ወይም በድንብ ያልበስለ ሥጋ የበሉ እንደሆነ ነው።  በፓራሳይቱ ከተመረዙ የቤት እንስሶች ጋር ከስገራቸው ወይም ከሽንታቸው ጋር ንከኪ

(cat litter) ያለ እንደሆነ ከፓራሳይቱ እንቁላሎች የተነሳ ወደ ስው ይተላለፋል። እርጉዝ ሴት Toxoplasma gondii ከተመረዘች ጽንሱ ይጨነግፋል ወይም ከፓራሳይቱ የተነሳ ጽንሱ ሞቶ ይወለዳል ወይም የተወለደው ሕጻን congenital toxoplasmosis ያለው ከመሆኑ የተነሳ የአይን የማቃጠል ችግር መታወር የጉበት በሽታ (ጆንዲስ) የሚጥል በሽታ ከመጠን በላይ ትንሽ ወይም ትልቅ እራስ ያለው ዘገምተኛ አዕምሮ (mental retardation) ያለው ይሆናል። ደካማ የኢሚውን ሲስተም ያላቸው ስዎች ማለትም እንደ ዔድስ በሽተኞች ያሉት toxoplasmosis የተጋለጡ ናቸው ስውነታቸውን ከመመረዙ የተነሳ በስውነታቸው ላይ ማቃጠል የራስ ምታት መንቀጥቀጥ የሃሳብ መደበላለቅ በከፊል ስውነታቸው ላይ ሽባነት ወይም ኮማ ያስከትልባቸዋል።

2. ፓራሳይቶች ሚክሮ ኒትርየንቶችን ያቀንሳሉ

ፓራሳይቶች ወደ ስው አካል ውስጥ ከገቡ በኋላ ለጤናማ እድገትና አስራር የሚያስፈልጉትን ቪታሚኖችና ሚኒራሎች ስለሚጋሩ ስውነት ለመኖርም ሆነ በሚገባ ለመሥራት ስለሚቸገር ጉድለቱ ለተለያዩ በሽታዎች የተጋለጠ ያደርገዋል።

3. ፓራሳይቶች የሆድ ውስጥ ጤናን ያወካሉ

MeSH የተደረገው ጥናት እንደሚያመለክተው Protozoan   helminthes የተባሉት ፓራሳይቶች የሆድ ሕመምና የምግብ ፍላጎት መዘጋትን ያስከትላሉ። MeSH የተደረገው ጥናት የአንጀት ውስጥ የሆድ ህመም ባለባቸው በሽተኞች የፓራሳይቶች ምርመራ ማድረግ እንደሚኖርባቸው ያመለክታል። ጥናቱም የደመደመው የሆድ ህመም ያለባቸው በሽተኞች በሙሉ መመርመር ያለባቸው የአንጀት ውስጥ ፓራሳይቶችንና በተጨማሪም Microsporidium ያለበት ግለስብ አዘውትሮ የአሲድ ኢንዳጀሽንና ድካም ስለሚታይበት ምርመራው Microsporidium ይጨምራል። ይሁን እንጂ አንድ ስው ምግብ መብላት ካቃተውና የአሲድ ኢንዳይጀሽን ችግር ካለው ምርመራው በዚሁ ላይ ትኩርት ይስጣል።

4. ፓራሳይቶች በጡንቻዎች ላይ ሕመም ያስከትላሉ

MeSH የተደረገው ጥናት በአምሳ አንድ አመት እድሜ ያለው የጤና ችግሮች ማለትም የልብ ምት ፍጥነቱ ክፍተኛና ጉበቱ የተጎዳና የደም መርጋት ችግር ያለበት ወንድ ስው ጥሬ የፍየል ሥጋ ከበላ በኋላ fasciculations የጡንቻ ላይ ቁርጥማት በታችኛው የእጆችና የእግሮቹ ክፍሎች ህመምና አቅም ማጣትና በጡንቻዎች ላይ በማስከተሉ የተነሳ ጥናት ተደረገ። የምርመራው ውጤት ያመለከተው positive antibodies የተገኙበት ሲሆን በተቃራኒው Toxocaracanis የተባለው ፓራሳይት በስውዬው ደም ውስጥና cerebrospinal ፈሳሹ ውስጥ እንዳለ ምርመራው አመለከተ። ጥናቱ የሚያመለክተው Toxocaracanis በተባለው ፓራሳይት የተነሳ የጡንቻና የእግሮችና የእጆቹ ሕመም የመጣው ከዚሁ ፓራሳይት የተነሳ እንደሆነ ነው። በህክምና ማለትም albendazole and riluzole በተባሉት በመድሐኒቶችም ቢረዳም እንኳ ጡንቻዎቹ ማለቃቸው አላቆሙም ይልቁንም ወደ መተንፈሻ ክፍሉ ጡንቻዎች ላይ መተላለፉ ቀጠለ።

 5. ፓራሳይቶች የደም ማነስ ያስከትላሉ

የኢትዮጵያ በገጠሩም ሆነ በከተማው (hookworm infection) በሁክዎርም ይመረዛል። በሁክዎርም መመረዝ የሚካሄደው በተረሱት ከባድ ሙቀት ቦታዎች ከመሆኑም ሌላ ድህነትን የሚያራመድ ወይም ለድህነት መነሻ የሚሆን በሽታ ነው። ጥናቶችም እንዳመለከቱት በሁክዎርምስ የተመረዙት በአለም ዙሪያ የሕዝብ ብዛት 576 እስከ 740 ሚሊዮን ሲሆኑ አብዛኞዎቹ ሕዝቦች የሚኖሩት በሞቃቱ የአለም ክፍሎች በትሮፒክስና በሳፕትሮፕክስ አካባቢዎች ነው። በኢትዮጵያ ውስጥ በዚሁ ሁክዎርም መመረዝ እንዳለ የታወቀው በምሥራቅ ወለጋ በሚገነኘው Fenan Medical Centre  2007 . መጋቢት እስክ ሚያዚያ የተደረገው የደም ምርመራ በደጋው የወለጋ ክፍል የሁክዎርም ፓራሳይት እንዳለ ምርመራው አመልክቷል። በተመርማሪዎቹ በአንጀት ውስጥ የሚገኙት 64% ሌሎች ፓራሳይቶች መሃከል 49.7% የሁክዎርም ፓራስይት እንደሆኑ ጥናቱ አመልክቷል።

በጥናቱ ከተሳተፉት ስዎች መሃከል 83.9% በሁክዎርምስ የተመረዙት በደም ማነስ የተጠቁ ናቸው። .

የሁክዎርም መጠኑ ትንሽ የሆነ ፓራሳይት nematodes  የተባለው ወደ ስው ስውነት ውስጥ ከገባ በኋላ የገባበትን ስው ደም እየተመገበ የሚኖር ፕራሳይት ነው።  በሁክዎርም ፓራሳይት የተመረዘው ስው የደም ማነስ የሚኖረው ፓርሳይቱ ደሙን  እየተመገበ በስውነቱ ውስጥ ስለሚኖር ነው።

አንድ ስው ለደም ማነስ ከሚያገልጡት ተመጣጣኝ ዳይት ያለመመገብና የውስጥ መድማት ችግር ሌላ የሁክዎርም ፓራሳይትም ለደም ማነስ (አኒሚያ) ድርሻ አለው። የደም ማነሱ ችግሩ መንስዔው የትኛው እንደሆነ ለማወቅና በሽተኛውን ለመረዳት የደምና የስገራ ምርመራ ቢደርግ ይመረጣል። በሀገር ውስጥም ሆነ ከውጪ ወደ ኢትዮጵያ ተጉዘው ለሚመጡ ግለስቦች የደም ማነስ ችግራቸው ካልታወቀላቸው ሐኪማቸውን የፓራሳይት መርመራ እንዲደርግላቸው ማሳስብ ይኖርባቸዋል።

ከዚህ በታች የተጻፉት ሃሳቦች ለትምህርት እንጂ አንባቢው እራሱን በራሱ በቦታኒካል ሜዲስንም ሆነ በፈርማሲዩቲካል መድሐኒቶች እንዲያክም እይደለም፤ አንባቢው እራሱን በራሱ ከዚህ በታች ከተጠቀሱት ቦቦታኒካል ሚዲስንም ሆነ የፈርማሲዩቲካል መድሐኒቶች ወስዶ እራሱን አክሞ ጉዳት ቢደርስበት

እኔ / አመለወርቅ ተጠያቂ እንዳልሆንኩ አንባቢው ሁሉ ይወቅ።  አንባቢው ለማንኛውም ህክምና የግል ሐኪሙን ማየትና ምክር መጠየቅ ያስፈልገዋል።

1.ኒዩትሪሽናል ቲራፒ

የሚከተሉት የአመጋገብ ለውጦችን ማድረግ በፓራሳይት መመረዝን ይከላከላል።

ተመጣጣኝ ምግቦችን መመገብ  በብዛትም ከምግብ ውስጥ ፍይበርን ማብዛት አታክልቶችን ፍራፍሬዎችን ሆልግሬን ምግቦችን ነትስ በተለይም ፋይበር ውርሞችን ከአንጀት ውስጥ የማስወገድ ጉልበት አለው።

ተመጣጣኝ ምግብ መመገብ ኢሚውን ሲስተም እንዲጠናከርና ስውነትን ከውጪ ወራሪ ባክቴሪያም ሆነ ቫይረስ ፓራሳይቶችን አንዳያጠቃው ጠንክሮ እንዲስራ ያደርገዋል።

ከምግብ ውስጥ መቀነስ ያለበት ዲሪ ፕሮዳክቶችንና (ከወተት የሚገኙ ምግቦችን) ስክዋርንና  ስብነት ያላቸውን ምግቦች ነው። በተለይም ያልተቀቀሉ የአሳ የፓርክና የከብት ሥጋዎችን ያለመብላት ይመረጣል።

በየቀኑ ደግሞ ማልቲቪታሚን/ ሚኒራል ስፕሊመንቶችን መውስድ ከማልኒዩትሪሽን ከመከላከሉም ሊላ ኢሚውን ሲስተም እንደሻሻል ወይም እንዲጠናከር ይረዳል።

እንደተጨማሪ ምግብ ደግሞ ፕሮፓዮቲክን እንደ  Lactobacillus acidophilus,

Bifidobacteria, ሌሎችንም ጠቃሚ  አንጀትን የሚረዱ ፕሮፓዮቲክ ምግቦች ጤናማ ባክቴሪይዎች

በአንጀት ውስጥ የሚገኘውን ጤናማውን ኢንተስቲናል ፍሎራ በማሻሻል ፓራሳይት በአንጀት  ውስጥ እንዳይበዛና እንዳይስራጭ ያደርጋሉ።

     2. ቦታኒካል ሜዲስን ቲራፒ

ቦታኒካል ሜዲስን ከምግቦች ጋር የተወስዱ እንደሆነ ወርሞች ከሆድ ውስጥ እንዲጠፉ ይረዳል። የሚከተሉት ፓራሳይቶችን ከሆድ ውስጥ እንዳይረቡ በማስወገድ የታወቁ ናቸው።

• Melaleuca alternifolia (tea tree)

oil ብዙ ጥቅሞችን ያስገኛል  ከነዚህም መሃከል የአንጀት ውስጥ ፓራሳይቶችን ቅማል  ሌሎችንም የማስወገድ ጉልበት አለው።

• Artemisia annua (wormwood herb) እና citrus seed

extract እነዚህ ሁለቱ በአንድ ላይ የተወስዱ እንደሆነ Giardia

lamblia የተባለውን ፓራሳይት ከአንጀት ውስጥ ያስወግዳል።

• Berberine- ያለባቸው ቦታኒካል ሜዲስኖች  ቤርቤሪን የታወቀው አንቲማይክሮቢያል አልክሎይድ የተባለውን

ንጥረ- ነገሩን በመያዙ በአንጀት ግድግዳ ላይ  የተጣበቁትን ፓራሳይቶች የመከላከል ጉልበት አለው።   እንደውም አንድ ጥናት ያሳየው  amoebal Giardia የተባለውን ፓራሳይት የማጥፋት ጉልበት እንዳለው ጥናቱ አሳይትዋል። lamblia እንደ  metronidazole ደረጃውን የጠበቀ ትሪትመንት ነው።

ፓታኒካል ሚዲስን  berberine ከያዙት መሀከል፡

(1) goldenseal (Hydrastis canadensis),

(2) barberry (Berberis vulgaris)

(3)  Oregon grape (Berberis aquifolium)

(4)  goldthread (Coptis chinensis) ናቸው።

3. ፈርማኮቲራፒ በአንጀት ውስጥ ለሚገኙ ፓራሳይቶች

የፓራሳይቶች ትሪትመንት የሚደረገው antiparasitic

drugs በተባሉት መድሐኒቶች ነው።  እንደጥንካሬው መጠን እንደፓራሳይቱ አይነት መድሐኒቶቹ  በሐኪሙ ይመረጣሉ።

እነዚህም መድሐኒቶች የሚከተሉት ናቸው።

       (1 )Albendazole (2)  furazolidone, (3)  iodoquinol, (4) mebendazole,

(5) metronidazole, (6) niclosamide,  (7) paromomycin, (8) pyrantel pamoate,(9) pyrimethamine, (10)  quinacrine,

(11)  sulfadiazine ወይም thiabendazole.

እንደገና በፓራሳይት ታማሚው ደግሞ እንዳይመረዝ ወደ ሌላው እንዳይተላለፍ  እጅን መታጠብ  ልብሶችን መጠብ አንሶላዎችንም ሆነ የአልጋልብሶችን ልጆች የሚጫወቱበትን አሻንጉሊቶች ማጠብ ሌላው ፓራሳይቶች ወደ ሌላው ስው እንዳይተላለፉ

ይረዳል። ይህ እርምጃ ቤተስቡን ሁሉ ይጨምራል።

ሴንትራል ነርቭስ ሲስተማቸው toxoplasmosis በተባለው ፓራስይት የተመረዘ ስዎች ደግሞ

 spiramycin ወይም  sulfadiazine አብሮም  pyrimethamine የተባሉት መድሒኒቶች በሐኪም

ይስጣቸዋል። የተመረዙት ስዎች በተለይም ለኤድስ በሽተኞች  ከሆኑ ላለተወስነ ጊዜ መድሐኒቱን እንዲወስድ ይደረጋል።

ፓራሳይቲክ ኢንፊክሽንን በምርመራ ማወቅ አስቸጋሪ ነው  ቢሆንም እንክዋን ፓራሳይቶቹ እንዳይባዙ ቦታኒካል ሜዲስን ወይም  antiparasitic drugs ችግሩ ይቃለላል።

የመከላከያ ህክምና

ከዚህ በታች የተቀመጡት እርምጃዎች ግለስቡን በፓርሳይት ከመመረዝ ይከላከሉ

ምግብን ከመብላትም በፊት ሆነ በህዋላ እጆችን መታጠብ

የመጸዳጃ ቤቶን ከተጠቀሙ በህዋላ እድን በውሃና በሳሙና በሚገብ መታጠብ

አታክልት በሚተከልበት ጊዜም ሆነ አፈር በእጅ እንዳይነካ ግሎቭስ መልበስ  ምክንያቱም አፈርም ሆነ አሽዋ በፓራሳይቶች እንቁላሎች መመርዝ ስለሚችሉ ነው

•  እርጉዝ ሴት የድመት ኩስ መንካት የለለባትም

ልጆች የቤት እንስ ሳትን መሳም እንስ ሳውም ልጆቹን በምላሱ መላስ የለበትም

ቪጂቲብሎችንም ሆነ ፍራፍሬዎችን ከመበላታቸው በፊት በሚገባ መጠብ  ምክንያቱም ብዙ ስዎች ያልታጠቡ የአታክልት

ምግቦችንም ሆነ ፍራፍሬዎችን የተመገቡ እንደሆነ  ከጥሪ ፍራፍሬዎች  ላይ Entamoeba histolytica የተባለው ፓራሳይት አብረው ካልታጠበው ፍራፍሬ ጋር  ወደሆዳቸው የመግባት እድል ይኖረዋል።

ጥሬ ሥጋ  Giardia lamblia የተባለው ፓርሳይት ስለሚገኝበት አለመብላት ይመረጣል።

በተቻለ መጠን የሚለበስው ልብስ እጅጌ ያለው ሽሚዝ እርጂም ሱሪና ቡትስ በጫካው ውስጥ የተሄደ እንደሆነ  ቢሆን ይመረጣል ከዚህም በተጨማሪ ነፍሳትን የሚያባርር ስፕሬ በልብስ ላይ ነፍቶ መውጣት ሌላው እምጃ ነው።

የበለጠ ለማወቅ  Burton Goldberg Group. “Parasitic Infections.” in Alternative Medicine: The Definitive Guide. Tiburon, CA: Future Medicine Publishing, Inc., 1999. ያንብቡ።

 ክፍል 2

 ከኤችአይ ቫይረስ ጋር መኖር

ከኤችአይ ጋር መኖር ቫይረስ ጋር መኖር ማለት ቫይረሱ በደሙ ውስጥ እንዳለ የተረዳ ሰው ራሱን አረጋግቶና ችግሩን እንደማንኛዉም የጤና ችግር በማየት ቫይረሱ የሚያስከትለውን ጉዳት ለመቀነሰ እና ለመከላከል በሕክምና፣ በአመጋገብ፣ እንዲሁም በባህርይ ላይ አስፈላጊ የሆኑ ለውጦችን በማምጣት ጥሩ ሕይወት መኖር ማለት ነው። አንድ ሰው ኤችአይ አለበት ማለት አሁኑኑ ታሞ ይተኛል ወይም በቅርቡ ሕይወቱ ያልፋል ማለት አለመሆኑን ማወቅ ተገቢ ነው። ከኤች.አይ. ጋር የሚኖሩ ሰዎች የእድሜ ማራዘሚያ መድሀኒቶችን ፀረ-ኤችአይቪ መዳኒቶች  በመጠቀም ለረጅም ዓመታት ጤናማ ሆነው ለመኖር ይችላሉ። አንዳንድ ሰዎች የበሽታዉ ምልክት ጨርሶ ሳይታይባቸው 15 ዓመት በላይ ከቫይረሱ ጋር መኖር እንደሚችሉ አንዳንድ ጥናቶችም ያመለክታሉ። ኤችአይ ቫይረስ በደም ውስጥ በመኖሩ ምክንያት ሊሰማ የሚችለዉን ስሜት አውነታውን መቀበል መቻል በጣም አስፈላጊ ነው። ጥሩ ያልሆኑትን ስሜቶች ለማስወገድ የሚከተሉትን ምክሮች መቀበልና መተግበርም ተገቢ ነው።

ሁኔታዎች እያደር የተሻሉ እንደሚሆኑ ተስፋ ማድረግ፦ ፈታኝ የሆነ ሰሜት ሲሰማ ሁኔታዎች ሁሉ ከጊዜ ጋር እየተሻሻሉ እንደሚሄዱ ማመን በጣም ጠቃሚ ነው። የተሻለ ሁኔታ እንደሚኖር ተስፋ የሚሰጡ ብዙ መንገዶች አሉ። ለምሳሌ የራስን ጤንነት መጠበቅና የቀድሞውን የተረጋጋ ህይወት እንደገና መጀመር አንዱ መንገድ ነው።

ከኤችአይ ጋር ከሚኖሩ ሰዎች ጋር መመካከር፦ ማንኛውንም የሚሰማን ስሜት ወይም የህመም ምልክት፤ ሌሎችም ምናልባት ተመሳሳይ ስሜት እና ምልክት ሊኖራቸው ስለሚችል ከቫይረሱ ጋር ከሚኖሩ ሰዎች ጋር መመካከር ወይንም ከቫይረሱ ጋር የሚኖሩ ሰዎች ወደመሠረቷቸው ማህበራት በመሄድ የምክር እርዳታ ማግኘት አስፈላጊ ነው።

ሁሌም የሚያስደስቱን ነገሮች ከማድረግ አለመቆጠብ፦ አንድ ሰው ኤች.አይ. ቫይረስ በደሙ ውስጥ መኖሩን ካወቀ በኋላ የደረሰበትን ድንጋጤ ለማስወገድ ቀደም ሲል ያደርጋቸው የነበሩትን አስደሳች ስራዎችን በመቀጠል አሁን የተፈጠሩበትን የኀዘንና የብስጭት ሰሜቶችን መርሳት መቻል ይገባዋል። ዘወትር ሲያደርገው ያስደስቱት የነበሩትን ሥራዎች በቀጣይነት ማድረግ ኀዘን ወይም ጭንቀት ላይ ብቻ እንዳያተኩር ይረዳል።

አካላዊ እንቅስቃሴ ማድረግ፦ ከኤች.አይ. ጋር የሚኖር ሰው ድካም ሊሰማዉና ሊጫጫነው ይችላል። በዚህ ጊዜ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ ብርታትና ጥንካሬ ይሰጣል። ከፍተኛ የሰውነት እንቅስቃሴ ባይሆንም እንኳን ቀላል እርምጃዎችን ማዘውተር ለአእምሮና ለሰውነት ጤንነት በጣም አስፈላጊ ነው።

ጎጂ የሆኑ ቅፅበታዊ ለውጦችን በህይወት ላይ አለማድረግ፦ ሥራን አለመተው፣ ዘመድ ወዳጆችን አለመራቅ፣ ንብረቶችን አለመሸጥ። በእርግጥ አንድ ከኤችአይ ቫይረስ ጋር የሚኖር ሰው የወደፊት እቅዱን ሊለውጥ ይችላል፤ ይህ ለውጥ ጫና ያልበዛበትና ውጤቱም ጠቃሚ መሆኑን አስቀድሞ መለየት ያስፈልጋል።

ባለሞያን ማማከር፦ ስለ ኤችአይ/ኤድስ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ በመኖሪያ አካባቢያችን እንቅስቃሴ የሚያደርጉ ማህበራትን ወይም ድርጅቶችን ማወቅ ጠቃሚ ነው። አንድ ከኤች.አይ. ጋር የሚኖር ሰዉ የጭንቀት እና የመከፋት ስሜት ካለቀቀው የህክምና ባለሞያዎች ወይንም አማካሪዎችን በስልክም ሆነ በአካል ማግኘትና ማማከር ያስፈልገዋል።

ያስታውሱ! ብቻዎን አይደሉም ፦ኢትዮጵያ ውስጥ ከኤችአይ ቫይረስ ጋር የሚኖሩ ከአንድ ሚሊዮን ተኩል በላይ ሰዎች አሉ። በአሁኑ ጊዜ 12 በመቶ ገደማ የሚሆኑ ከኤችአይ ጋር የሚኖሩ ሰዎች አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ይኖራሉ። በመላው ኢትዮጵያ ውስጥ ዕድሜያቸው 15 እና 49 መካከል የሚገኙ 4 ከመቶ በላይ የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን ከኤችአይ ቫይረስ ጋር ይኖራሉ። አንድ ኤችአይ ቫይረስ በደሙ ውስጥ ያለበት ሰው በቫይረሱ ለመያዝ ሆን ብሎ የሰራው ስህተት ስለሌለ ራሱን መውቀስ እና መጨነቅ የለበትም። ማድረግ ያለበት ነገር ቢኖር ለሌሎች ተጓዳኝ በሽታዎች እንዳይጋለጥ ራሱን እንዲጠብቅ ትምህርት ማግኘት እና ከኤች.አይ. ነፃ የሆኑ ሰዎች ለቫይረሱ እንዳይጋለጡ ስብዓአዊነት ተስምቶት ቅድመ ጥንቃቄዎችን ማድረግና፣ ከተቻለም ማስተማር።

ከኤችአይ ቫይረስ ጋር የሚኖሩ ሰዎች ቫይረሱ እንዳለባቸዉ አውቀው ከጥቂት ጊዜ በኋላ ያሉበትን የጤና ሁኔታ ተቀብለው ራሳቸውን በማረጋጋት ወደፊት በተሻለ መንገድ ለመኖር ምን ማድረግ እንዳለባቸው ማሰብ ይጀምራሉ። እራሰን አረጋግቶ ለመኖር ከዚ በታች የተጠቀሱት ጠቃሚ መመሪያዎች በዝርዝር ጠንቅቆ ማወቅ አጥጋቢ የሆነ የፀባይ እና የአኗኗር ለውጥ ለማምጣት ይረዳል፦ ኤችአይ ቫይረስ በደም ዉስጥ መኖሩን በታወቀበት ጊዜ ሊገጥም የሚችለውን የጭንቀት እና የፍርሃት ስሜት እንዴት ማስወገድ እንደሚቻል፤

•         አጋጣሚን ጠብቀው የሚመጡ የበሽታ ስሜት/ምልክቶች በሰውነት ላይ ሲታዩ መወሰድ ያለባቸውን ህክምና እና ጥንቃቄ፤

•         የተመጣጠነ ምግብ መመገብ፣ የራስን ንፅህና መጠበቅ እና የሰውነት እንቅስቃሴ የማድረግ አስፈላጊነትን፤

•         ጥንቃቄ ስለተሞላበት የግብረ ሥጋ ግንኙነት እና ስለወሊድ።

ተስፋ እና የወደፊት ህይወት

ከኤች.አይ. ጋር ኑሮን በሠላም ለረጅም እድሜ መምራት እንደሚቻል መገንዘብ አስፈላጊ ነው። እንዲሁም ከኤች.አይ. ጋር የሚኖሩ ሰዎች ህጋዊ መብታቸውን የሚያከብሩ ህግጋት እንዲደነግጉ ድጋፍን በመስጠት የራስን አስተዋፅኦ በማድረግ ተስፋን እውን ማድረግ። በተጨማሪም የዕለት ዜናዎችን በመከታተል፣ባለሞያዎችን ወይንም አማካሪዎችን በመጠየቅ በኤች.አይ. ላይ ያሉ አዳዲስ የህክምና እና የመድሀኒት ግኝቶችን መከታተልና ማወቅ ተስፋን ይሰጣል። ስለ ከኤችአይ  ዕውቀትን ማዳበርና ይበልጥ ማወቅ ራስን በደንብ ለመንከባከብ ይረዳል። አንድ ከኤች.አይ. ጋር የሚኖር ሰው ልጆች ካሉት ህመም ሲጠና ልጆችን የሚንከባከብ ሰው ቀድሞ ማዘጋጀት ያስፈልጋል።

ህክምና

ኤች.አይ./ኤድስ ክትባት ወይም ፈዋሽ መድኀኒት ባይገኝለትም ምርምሩና ሙከራዉ እንደቀጠለ ነው። የዕድሜ ማራዘሚያ መድሃኒቶች ፀረ-ኤችአይቪ መዳኒቶች  ቫይረሱ በደም ውስጥ የሚያደርገውን የስርጭት ፍጥነት ለመግታትና ለማስቆም የሚወሰዱ መድሃኒቶች ናቸው። በሰውነት ዉስጥ የሚገኘውን የኤች.አይ. ቁጥር መቀነስ ይችላሉ፤ መድሃኒቶቹ ቫይረሱን ከናካቴው ማጥፋት አይችሉም። መድሃኒቶቹን ያለ ህኪም ትዕዛዘና ፍቃድ መውሰድ በጤንነት ላይ ትልቅ ችግር ያስከትላል። የመድሃኒቶቹ ተጠቃሚ ሰው አንድ በቅርብ ሆኖ የሚከታተለው ብቃት ያለው የህክምና ባለሙያ ያስፈልገዋል።

አመጋገብ

የተመጣጠነ ምግብ መመገብ ሰውነታችንን እና የሰውነት የመከላከያ አቅማችንን እንደሚያጠነክር ሁሉ በቀላሉ ለበሽታ እንዳንጋለጥም ይጠቅመናል። ከኤችአይ ጋር የሚኖሩ ስዎች በምግብ እና ውኀ ውስጥ ለሚገኙ በሽታን ወይም ህመምን ሊያስከትሉ ለሚችሉ ጀርሞች በቀላሉ የተጋለጡ በመሆናቸዉ፤ በቤት ውስጥም ሆነ ከቤት ውጭ ሲመግቡ ንጽህናውን የጠበቀ የአመጋገብ ሥርዓት መከተልና የሚጠጣው ውሃ ንጹሀ መሆኑን ማረጋግጥም በጣም ጠቃሚ ነው። ከኤችአይ ጋር የሚኖሩ ስዎች የተለያዩ ዓይነት ምግቦችን በመመገብ ያልተፈለገ የሰውነት ክብደት መቀነሰን ለመከላከል እና ጡንቻዎቻቸዉ እንደጠነከሩ እንዲቆዩ የሰውነት እንቅስቃሴ ማድረግ አለባቸው። ሁሉም የምግብ ዓይነቶች የተለያዩ ጥቅሞች አላቸዉ። የተለያዩ የምግብ ዓይነቶች በሚከተለው መሰረታዊ ምድቦች ተከፋፍለው ሊታዩ ይችላሉ።

•         ገንቢ ምግቦች፦ ባቄላ፤ አተር፣ ምስር፣ እንቁላል፣ ሥጋ፣ አሣ፣ ዶሮ፣ ወተት፣ አይብ እና ለውዝ ሰውነትን ለመገንባት የሚያስችሉ የምግብ ንጥረ ነገሮችን ይዘዋል።

•         ኃይል ሰጪ ምግቦች፦ ለሰውነት የሚያስፈልገውን ኃይል ሁሉ የምናገኝባቸው የምግብ አይነቶች እንደ በቆሎ፣ እንጀራ፣ ዳቦ፣ ድንች፣ ፓስታ፣ ሩዝ፣ ስንዴ፣ አጃ፣ ዳጉሳ፣ ማሽላ፣ ስኳር፣ ማርማላት፣ ማርጋሪን፣ ዘይት፣ ሲሆኑ በተጨማሪም እንደ ለውዝ እና አቮካዶ የመሳሰሉ የቅባት ምግቦችንም ያጠቃልላል።

•         የሰውነትን የመከላከል አቅም የሚያጎለብቱ ምግቦች፦ አትክልትና ፍራፍሬ መመገብ የሰውነታችንን አቅም በማጎልበት በሽታን በሚገባ ለመቋቋም ያስችላል፤ እንዲሁም እንደ ካሮት፣ ሰላጣ እና ጎመን የመሳሰሉ ምግቦችንም መመገብ ቫይታሚን ለማግኘት ይረዳናል።

የሰዉነትን የመከላከል አቅም ለማጎልበት፦

•         የምግብን የመፍጨት ሂደት ሊያውኩ የሚችሉ እንደ ቃሪያ፣ በርበሬ ወይም ሚጥሚጣ የመሳሰሉ እና ሌሎች ቅመማ ቅመም የበዛባቸውን ምግቦች በብዛት አለመመገብ፣ ለስለስ ያሉ እንደ አልጫ ወጥ ያሉ ምግቦችን መመገብ፣ ከህይለኛ ቅመሞች ይልቅ የጥብስ ቅጠልን የመሳሰሉ የምግብ ማጣፈጫዎች መጠቀም ያስፈልጋል።

ፍራፍሬ እና የአትክልት አመጋገባችንን መጨመር፣ እነዚህን የሰውነት የመከላከል አቅም የሚያጎለብቱ ምግቦች በቫይታሚንና በማዕድን የበለፀጉ በመሆናቸው ሰውነታችንን ከበሽታ ይከላከላሉ። በመሆኑም እንደ ቆስጣ እና ጎመን የመሳሰሉ በጣም አረንጓዴ የሆኑ የቅጠላቅጠል ምግቦችን፣ እንደ ዱባ፣ ብርቱካን፣ ሎሚ፣ ማንጎ እና የመሳሰሉ ፍራፍሬዎችን በየቀኑ መመገብ ያስፈልጋል። በተጨማሪም ከጤፍ፣ ከጥቁር ስንዴ፣ ገብስ የተዘጋጁ ዳቦዎችን እና ሌሎች ምግቦችን መመገብ።

•    ዉኃ ለሰውነታቻን ከሚያሰፈልጉን ነገሮች አንዱ ነው። በየቀኑ ቢያንስ 8 ብርጭቆ ዉሃ መጠጣት ጠቃሚ ነው። የምንጠጣው ዉሃ ንፁህ መሆን አለበት። ከኤች. አይ. ጋር የሚኖር ሰው እንደ ተስቦ፣ ኮሌራ፣ ቢልሀርዚያ እና ጃርዲያ ለመሳሰሉት በተበከለ ውኃ አማካኝነት በሚተላለፉ በሽታዎች የተጋለጠ ስለሆነ በቀጥታ የህይቅ ወይም የምንጭ ውኃ ከመጠጣት ፈልቶ የቀዘቀዘ ውኃ መጠጣት በጣም አስፈላጊ ነው።

ሰዉነታችንን በጤንነት ለማቆየትና ቫይረሱ በጤና ላይ ሊያስከትል የሚችለውን ጉዳት ለመቀነስ ቫይታሚን ኤ፣ 6 12 ሲ፣ ዚንክ፣ አይረን፣ ኮፐር፣ ማንጋኒዝ፣ ማግኒዥየም እና ሴሊኒየም ጨዉ የመሳሰሉትን ሁሉ መመገብ ይጠቅማል። የሰዉነትን የተፈጥሮ በሽታን የመከላከል አቅም በማጎልበት ረገድ ቫይታሚን ኤ፣ ሲ፣ ኢ፣ እና ከማዕድናትም ዚንክ በጣም ጠቃሚዎች ናቸው። እነዚህ የምግብ ንጥረ-ነገሮች በተፈጥሮ ከተለያዪ ምግቦች ዉስጥ ይገኛሉ።

 የቫይታሚኖች እና የማዕድናት መገኛ:

ቫይታሚን ''

ጉበት፣ ቅቤ፣ አይብ፣ እንቁላል፣ ቆሰጣ፣ ቢጫና አረንጓዴ አትክልቶች ' ቫይታሚን 12 ' ጉበት፣ ኩላሊት፣ አሳ፣ ሥጋ፣ ዕንቁላል፣ ወተት ቫይታሚን '' ቲማቲም፣ ድንች፣ማንጐ

ቫይታሚን ''የአትክልት ዘይት ' አይረን ' የበሰለ ጉበት፣ ኩላሊት፣ እንጀራ፣ ቀይስጋ እና ዕንቁላል፣ ' ኮፐር ' ጉበት፣ ለውዞች፣ ባቄላ፣ ስጋ፣ አሳ፣ ዶሮ፣ እና የስንዴ ዳቦ፤

ቫይታሚን '6' ከስንዴ የተዛመዱ ምግቦች፣ ጉበት፣ ሙዝ፣ ስጋ፣ ድንች፣ አትክልት፣ ዕንቁላል እና ለውዞች፤ ' ዚንክ ' የስንዴ ዳቦ፣ እንቁላል፣ ባቄላ፣ ሩዝ፣ አረንጓዴ ቅጠላማ አትክልቶች፣ ድንች ጉበት ስጋና ለዉዝ፤ ' ሴሊኒየም ' ጉበት፣ ኩላሊት፣ ልብ፣ ቀይ ስጋ፣ የወተት ምርቶች፣ አትክልት እና ፍራፍሬ

' ማግኒዥየም ' አደንጓሬ፣ ለውዞች፣ የስንዴ ዱቄት፣ ቡናማ ሩዝ፣ ደረቅ አተር፣ አትክልቶች፣ ሰጋ፣ ሙዝ፣ አረንጓዴ ቅጠላማ አትክልቶች፤ ' ማንጋኒዝ ' የስንዴ ዳቦ፣ ለውዝ፣ ፍራፍሬ አረንጓዴ ቅጠላማ አትክልቶች፣ ጉበት፣ የስራስር አትክልቶች፣ ስጋ እና አሳ

አንዳንድ ጊዜ የተመጣጠነ ምግብ ባለመመገባችን ምክንያት የሚከተለውን ክፍተት ለማካካስ በፋብሪካ የተዘጋጁ ቫይታሚኖችን እንወስድ ይሆናል። ቅድሚያ መስጠት የሚገባን የተመጣጠነ ምግብ በመመገብ ተፈላጊ የሆኑትን የምግብ ንጥረ ነገሮች ማግኘት ቢሆንም የቫይታሚን እንክብሎችን መውሰድ አስፈላጊ የሚሆንባቸው ጊዜያት አሉ። በግምት ብዙ ቫይታሚኖችን መውሰድ ጤንነትን ስለሚያቃውስ የቫይታሚን እንክብ በሚወሰድበት ጊዜ በህክምና ባለሞያ ትዕዛዝ መሰረት መሆን አለበት።

 በምግብ አዘገጃጀት እና አመጋገብ ምክንያት ሊከሰቱ ከሚችሉ በሽታዎች ራስን መከላከል

ከኤችአይ ጋር የሚኖሩ ሰዎች በምግብ ምክንያት ለሚመጡ በሽታዎች የተጋለጡ ናቸዉ። አንዳንድ ጎጂ የሆኑ ጀርሞች ከጥሬ ስጋ፣ ምግቡን ከሚያዘጋጁ ሰዎች ወይም አብረዉ እንጀራ ከሚበሉ ሰዎች አፍና እጅ ንክኪ ሊሸጋገሩና የምንመገበውም ሊበከል ይችላል። ከኤችአይ ቫይረስ ጋር የሚኖር ሰው በምግብ መመረዝ ሲታመም ለማዳን በጣም ከባድ ከመሆኑ ሌላ በሽታው በተደጋጋሚ ሊመላለስበት ይችላል። እንደ ኮሶ፣ ወስፋት እና አሜባ የመሳሰሉት በሽታዎች ከፍተኛ የጤና ችግርን እንዲሁም ሞትን ሊያስከትሉ ይችላሉ። ከነዚ በሽታዎች አብዛኛዎቹ በቀጥታ በበሽታዎቹ ከተያዘ ሰው የሚተላለፉ ቢሆንም ባልበሰለ ወይም ንጽህናው ባልተጠበቀ ምግብ፣ በነፍሳት (ተባዮች) በተበከለ ምግብ፣ የምግብ አያያዝ ሥርዓትና ደንብን ባልተከተለ ሰው ተዘጋጅቶ በሚቀርብ ምግብ አማካይነት ሊተላለፉ ይችላሉ። ምግብን በደምብ ማብሰል ባክቴርያና ጀርሞች እንዲሞቱ ይረዳል። ከኤችአይ ጋር የሚኖሩ ሰዎች ጥሬ ሥጋ ወይም ጥሬ ክትፎም ሆነ ለብለብ ክትፎ ባይመገቡ ይመረጣል። በተጨማሪም ከቤት ውጭ በሆቴሎችና ቡና ቤቶች ውስጥ መመገብ ምግቡ እንዴት እንደተዘጋጀ ስለማይታወቅ ለህመም ሊያጋልጥ ይችላል። ከተቻለ ከቤት ውጭ አለመመገብ፤ ካልሆነም ምግቡ እንዴት እንደተዘጋጀ እና ጥሬ የሆኑ የምግብ ውህዶች ማለትም ያልበሰለ ሥጋ፣ እንቁላል ወይም አትክልት የሌለበት መሆኑን ጠይቆ ማረጋገጥ ያስፈልጋል።

ዕፅ እና አልኮል

ዕፅም ሆነ አልኮል በብዛት መውሰድ የሰውነትን የተፈጥሮ በሽታን የመከላከል አቅም ያዳክማል። ጤናማ ሆኖ ለመኖርም ሆነ ጤንነትን ለመንከባከብ አልኮልንም ሆነ ዕፅን መጠቀምን እስከመጨረሻው መተው አማራጭ መንገድ ቢሆንም ይህንን ሁሉም ሰው በቀላሉ ሊያደርገው አይችልም። የሚወሰደው የሲጋራ፣ የዕፅ ወይም የአልኮል መጠንን በተቻለ መጠን መቀነስ ጤንነትን በተሻለ ሁኔታ ለመጠበቅም ይረዳል።

የአካል ብቃት እንቅስቃሴ

የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ የተሻለ ጢና እንዲኖር ከመርዳቱ ሌላ የመጨነቅ፣ እና የድካም ስሜትን ይቀንሳል። የአካል ብቃት እንቅስቃሴው ራስን ዘና የሚያደርግና የልብን ምት እንዲጪምር ተደርጎ መሠራት አለበት እንጂ እስኪደክሙ መሆን የለበትም። ተገቢውን የየአካል ብቃት እንቅስቃሴ መጠን ለማወቅ ቢቻል የስፖርት ባለሞያዎችን አስቀድሞ ማማከር የተሻለ ነው። በየቀኑ 30 እስከ 60 ደቂቃ ያህል በእግር መጓዝ የተሻለ ጤና እንዲኖረን ከሚረዱት የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎች አንዱ ነው።

 ወሲብና ፍቅር

አንድ ከኤችአይ ጋር የሚኖር ሰው ስለራሱ ጤና በተመለከተ መብቱ የተሰጠዉ ለራሱ በመሆኑ ለፈለገው ሰው መንገር፣ ካልፈለገ ደግሞ ያለመናገርም ውሳኔው በእጁ ነው። ነገር ግን ከዚህ ጋር በተያያዘ መዘንጋት የሌለበት ጉዳይ አለ። በወንጀለኛ መቅጫ ሕግ ላይ የሰፈረ ድንጋጌ አንድ ሰው የሌላውን ሰው ጤንነት በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ ሆን ብሎ ይሁን በቸልተኝነት የሚጎዳ ተግባር ከፈጸመ እንደሚቀጣ ያስረዳል። ስለዚህ ከወሲብ ጓደኛ ጋር በሚኖር ግንኙነት ቫይረሱ ወደዛ ጓደኛ እንዳይተላለፍ ኮንዶም መጠቀም ያስፈልጋል ይህ ከሆነ ከኤችአይ ነፃ የሆነውን ወዳጅ ከቫይረሱ ለመጠበቅ ይረዳል። ከኤችአይ ጋር ነዋሪ መሆንን ለወሲብ/ፍቅር ጓደኛዎ አንዳንድ ጊዜ በቀጥታ ሌላ ጊዜ ደግሞ በተዘዋዋሪ መናገር ይቻላል። ለምሳሌ ስለቅድመ ወሲብ ጥንቃቄ ወይም ስለ ኤችአይ እና መተላለፊያ መንገዶች በማንሳት መነጋገር ይቻላል።

ወሊድ ( ከኤችአይ ያለባት እናት

አንዲት ሴት ኤችአይ በደሟ ውስጥ ቢኖርም እንኳን ልጆች ማፍራት ትችላለች። ተገቢውን ጥንቃቄ እና የህክምና ክትትል ካደረገች ከኤችአይ ነፃ የሆነ ጤነኛ ልጅ ሊኖራት ይችላል። ይሁን እንጂ ለኤችአይ የሚጋለጥም ልጅ ሊኖር ይችላል። ልጅ ለመውለድ እቅድ ካለ የሚከተሉትን ነጥቦች ልብ ማለት እና የህክምና ባለሞያን ማማከር ያስፈልጋል

የጤንነት ሁኔታ- በእርግዝና ወቅት በብዛትም ሆነ በጥራት የተሻለ የምግብ አቅርቦት መኖር አለበት። ከኤችአይ ጋር የሚኖር ሰው ደግሞ ከፍ ያለ የምግብ መጠንና የተለያዩ የምግብ ዓይነቶች ማግኘት ያስፈልገዋል።

ፅንሱን ከቫይረሱ መከላከል- ኤችአይ በደም ውስጥ መኖሩን አውቆ ልጅን ከኤችአይ ለመታደግ አስፈላጊውን እቅድ ማዉጣትና ተገቢውን ህክምና መከታተል የልጅን በቫይረሱ የመያዝ አጋጣሚ ለመቀነስ ይረዳል።

•    በደም ዉስጥ የኤችአይ መኖር- ወደፊት አንድ ወቅት ላይ የኤድስ ታማሚ ሊሆኑ እና አልጋ ላይ የመዋል አጋጣሚ ሊመጣ ይችላል። ስለዚህ ልጅዎ ያለ ተንከባካቢ እንዳይቀር ቀደም ብሎ ሁኔታዎችን ማመቻቸትም ያስፈልጋል።

ኤችአይ እና ሰብአዊ መብት

ከኤችአይ ጋር መኖር ከማንኛውም ሰብአዊ ፍጡር አያሳንሰም። ኤችአይ በደም ውስጥ በመኖሩ በሰብአዊ ፍጡርነት ሊኖር የሚገባውን መብት ሊያጓድል የሚችል አንድም ምክንያት የለም። ይህም ማለት ከኤችአይ ጋር የሚኖር ማንኛውም ሰው እንደሌሎ

. እንደማንኛውም ሰው ቫይረሱ በደሙ ያለበት ሰው የጤና አጠባበቅ አገልግሎት፣ ሥራ እና የትምህርት ዕድል የማግኘትና፣ በማህበራዊ ክንውኖች፣ ለምሳሌ፣ ዕድር፣ በዕምነት፣ በማህበራት ወይም የስፖርት ቡድን በመሳሰሉ ማህበራዊ ተቋማት አባል የመሆን መብት አለው።

ከኤችአይ ጋር የሚኖር ሰው ቤት የመከራየት ወይም ባለንብረት ለመሆን፣ የጤና፣ የህይወት ወይም የንብረት መድን የመግባት መብት አለው።

ከኤችአይ ጋር በሚኖሩ ሰዎች ላይ የሚደረግ መድልዎ ዋና ዋና መንስኤዎች አሉት፦ እነዚህም

•  ስለ ኤችአይ ቫይረስ መተላለፊያ መንገዶች ዝቅተኛ ወይም የተሳሳተ መረጃ መኖር፤

•  በቂ ግንዛቤ ካለማግኘት ወይም ከተሳሳተ መረጃ ላይ በመመርኮዝ የሚመጣ ፍርሃት፤

•  ስለግብረ ስጋ ግንኙነት በግልጽ መነጋገር እንደ ነውር ስለሚቆጠር፤

በሥራ ቦታ ላይ ስለሚደርስ መድልዎ ማወቅ፦ አንድ ሰው ከኤችአይ ጋር በመኖሩ ምክንያት መገለል ወይም አድልዎ ከደረሰበት ከቀጣሪው ጋር በመነጋገር ወይም በፍርድ ቤት በመክሰስ ፍትህ የማግኘት መብት አለው። ሕግም ከለላና ጥበቃ ያደርግለታል።

ኤድስን መግታት ይቻል ይሆን? ከሆነስ እንዴት?

በብዙዎቹ የአፍሪካ አገሮች የሚኖሩ አብዛኞቹ ሰዎች እስከ ቅርብ ጊዜያት ድረስ የኤድስን መኖር አያምኑምነበር። እንዲያውም አንዳንዶች ስለ ኤድስ አንስተው መወያየት እንኳን አይፈልጉም ነበር። ይሁን እንጂከቅርብ ዓመታት ወዲህ በተለይ ወጣቶችን ለማስተማርና በጉዳዩ ላይ ግልጽ የሆነ ውይይት የማድረግባሕል እንዲሰፍን ለማበረታታት ጥረት ሲደረግ ቆይቷል። እነዚህ ጥረቶች በተወሰነ ደረጃ ውጤት ያስገኙቢሆንም እንኳ የሰዎች የአኗኗር ዘይቤና ልማድ በጣም ሥር የሰደደ ከመሆኑ የተነሳ የሚፈለገውን ያህልለውጥ ማምጣት አስቸጋሪ ሆኗል።

በሕክምናው መስክ የታየ ለውጥ

በሕክምናው መስክ ሳይንቲስቶች ስለ ኤች አይ ብዙ ግንዛቤ ያገኙ ከመሆኑም ሌላ የብዙዎችን ሕይወትማራዘም የቻሉ መድኃኒቶችን መፈልሰፍ ችለዋል። ቢያንስ ሦስት ዓይነት የዕድሜ ማራዘሚያመድኃኒቶችን በማቀናጀት የሚሰጠው ሕክምና ጥሩ ውጤት አስገኝቷል።

እነዚህ መድኃኒቶች ፈውስ ማስገኘት ባይችሉም እንኳ በተለይ በበለጸጉ አገሮች በኤች አይ የሚሞቱሰዎችን ቁጥር መቀነስ ችለዋል። ብዙ ሰዎች እነዚህ መድኃኒቶች በማደግ ላይ ወደሚገኙ አገሮችምመግባት እንዳለባቸው ይናገራሉ። ይሁን እንጂ መድኃኒቶቹ ውድ በመሆናቸው በእነዚህ አገሮች ውስጥየሚኖሩት አብዛኞቹ ሰዎች እነዚህን መድኃኒቶች የመግዛት አቅም የላቸውም።

ይህ ሁኔታ፣ ገንዘብ ከሰው ሕይወት ይበልጣል? የሚል አከራካሪ ጉዳይ አስነስቷል። የብራዚል የኤች አይቪ/ኤድስ ፕሮግራም ዲሬክተር የሆኑት ዶክተር ፓውሎ ቴሼይራ ሁኔታውን እንዲህ ሲሉ ገልጸውታል:- “መድኃኒቶቹን የሚያመርቱት ኩባንያዎች ከልክ ያለፈ ትርፍ እንዲያጋብሱ ሲባል ብቻ በሺህዎችየሚቆጠሩ ሰዎች ሕይወታቸውን ለማቆየት የሚያስችሏቸውን መድኃኒቶች ማግኘት ተስኗቸው ሲቸገሩዝም ብለን ማየት አንችልም።አክለውምግብረገብንና ሰብዓዊ ርኅራኄን ወደ ጎን ገሸሽ አድርጎ ለንግድጥቅም ብቻ መሯሯጥ አይገባምብለዋል።

አንዳንድ አገሮች የመድኃኒት አምራች የሆኑ ትልልቅ ኩባንያዎችን የባለቤትነት መብት ባለማክበር የንግድምልክት የሌላቸውን ተመሳሳይ መድኃኒቶች በዝቅተኛ ዋጋ ለማስገባት ወይም ለመሥራት ወስነዋል።*አንድ ጥናት እንዳመለከተው ከሆነ “[የንግድ ምልክት የሌላቸው መድኃኒቶች] ዝቅተኛ ዋጋ ከዩናይትድስቴትስ መነሻ ዋጋ 82 በመቶ ዝቅ ብሎ ተገኝቷልሲል ሳውዝ አፍሪካን ሜዲካል ጆርናል ዘግቧል።

ሕክምናው ያጋጠሙት እንቅፋቶች

ይሁንና ውሎ አድሮ ትልልቆቹ የመድኃኒት አምራች ኩባንያዎች የኤድስ መድኃኒቶችን ለታዳጊ አገሮችዝቅ ባለ ዋጋ ማቅረብ ጀምረዋል። በዚህ መንገድ ብዙ ተጨማሪ ሰዎች መድኃኒቶቹን ማግኘት ይችላሉተብሎ ተስፋ ተደርጓል። ይሁን እንጂ እንዲህ ያሉ መድኃኒቶች በታዳጊ አገሮች ውስጥ በስፋት ጥቅም ላይእንዳይውሉ ከባድ እንቅፋት የሆኑ ነገሮች አሉ። ከእነዚህ እንቅፋቶች መካከል አንዱ የዋጋው ጉዳይ ነው።ዋጋው በእጅጉ እንዲቀንስ ቢደረግም መድኃኒቶቹ የሚያስፈልጓቸው ብዙዎቹ ሰዎች አሁንም የመግዛትአቅም የላቸውም።

ሌላው ችግር ደግሞ የመድኃኒቶቹ አወሳሰድ ነው። በየዕለቱ ሰዓቱን በትክክል እየጠበቁ ብዙ ኪኒኖችመውሰድ ይጠይቃል። ታካሚው መድኃኒቶቹን በአግባቡ የማይወስድ ወይም በየመሃሉ የሚያቋርጥ ከሆነመድኃኒቱን መቋቋም የሚችሉ የኤች አይ ዝርያዎች ሊፈጠሩ ይችላሉ። ምግብ፣ ንጹሕ የመጠጥውኃም ሆነ የሕክምና ተቋማት በበቂ ሁኔታ በማይገኙባቸው የአፍሪካ አገሮች ታካሚዎች መድኃኒቶቹንበትክክል እንዲወስዱ ማድረግ አስቸጋሪ ነው።

በተጨማሪም መድኃኒቶቹን የሚወስዱ ሰዎች ክትትል ያስፈልጋቸዋል። ቫይረሱ መድኃኒቶቹን መቋቋምከጀመረ የመድኃኒቶቹ ዓይነት መለወጥ አለበት። ይህ ደግሞ ልምድ ያላቸው የህክምና ባለሙያዎችማግኘት የሚጠይቅ ከመሆኑም ሌላ ምርመራው የሚጠይቀው ወጪም ቀላል አይደለም። ከዚህምበተጨማሪ መድኃኒቶቹ የራሳቸው የሆነ ጉዳት ያላቸው ሲሆን መድኃኒት መቋቋም የሚችሉ ቫይረሶችምእየተፈጠሩ ይሄዳሉ።

የተባበሩት መንግሥታት ጠቅላላ ጉባኤ ሰኔ 2001 ኤድስን አስመልክቶ ባካሄደው ልዩ ስብሰባ ላይ ታዳጊአገሮችን ለመርዳት ለጤና አገልግሎት የሚውል የእርዳታ ገንዘብ በዓለም አቀፍ ደረጃ እንዲሰባሰብ ሐሳብቀርቦ ነበር። ለዚህ እርዳታ 7 ቢልዮን እስከ 10 ቢልዮን የሚደርስ የአሜሪካ ዶላር እንደሚያስፈልግተገምቷል። ይሁን እንጂ እስካሁን ድረስ ቃል የተገባው ገንዘብ ከሚፈለገው ገንዘብ ጋር ሲነጻጸር አነስተኛነው።

ሳይንቲስቶች በሽታውን የሚከላከል ክትባት እናገኛለን የሚል ጠንካራ እምነት ያላቸው ሲሆን የተለያዩክትባቶችም በተለያዩ አገሮች እየተሞከሩ ነው። ይሁን እንጂ እነዚህ ጥረቶች ቢሳኩ እንኳን ክትባቱእስኪዘጋጅ፣ እስኪሞከርና አስተማማኝነቱ ተረጋግጦ በስፋት ጥቅም ላይ እስኪውል በርከት ያሉ ዓመታትይወስዳል።

እንደ ብራዚል፣ ታይላንድና ኡጋንዳ ያሉ አንዳንድ አገሮች በዘረጉት የሕክምና ፕሮግራም ጥሩ ውጤትአግኝተዋል። ብራዚል በአገር ውስጥ የሚመረቱ መድኃኒቶችን ጥቅም ላይ በማዋል በኤድስ የሚሞቱሰዎችን ቁጥር በግማሽ መቀነስ ችላለች። የገንዘብ አቅሙ ያላት ትንሿ አገር ቦትስዋና በአገሪቱ ውስጥበኤች አይ ለተጠቁ ሰዎች የዕድሜ ማራዘሚያ መድኃኒቶች ለማዳረስና አስፈላጊ የሆኑትን የጤናአገልግሎት መስጫ ተቋማት ለማሟላት ጥረት እያደረገች ነው።

ኤድስ ድል የሚደረግበት መንገድ

ኤድስን መከላከል የሚቻል መሆኑ ከሌሎች ወረርሽኞች የተለየ ያደርገዋል። ሰዎች የመጽሐፍ ቅዱስንመሠረታዊ ሥርዓቶች ካከበሩ ከኤድስ ራሳቸውን መጠበቅ ይችላሉ።

የመጽሐፍ ቅዱስ የሥነ ምግባር ደንቦች የማያሻሙ ናቸው። ያልተጋቡ ሰዎች ከጾታ ግንኙነት መታቀብአለባቸው። (1 ቆሮንቶስ 6:18) የተጋቡ ሰዎችም ለትዳር ጓደኛቸው ታማኝ መሆንና ከምንዝር መራቅአለባቸው። (ዕብራውያን 13:4) በተጨማሪም አንድ ሰው ከደም እንድንርቅ የሚያዝዘውን የመጽሐፍቅዱስ ማስጠንቀቂያ መከተሉ በበሽታው ከመያዝ ይጠብቀዋል። ሐዋ.ሥራ 15:28, 29

በበሽታው የተያዙ ሰዎች አምላክ በቅርቡ ስለሚያመጣው ከበሽታ ነፃ የሆነ ዓለም በመማርና አምላክያወጣቸውን ብቃቶች በማሟላት ከፍተኛ ደስታና መጽናኛ ማግኘት ይችላሉ።

መጽሐፍ ቅዱስ በሽታን ጨምሮ በሰው ልጆች ላይ እየደረሱ ያሉት ችግሮች በሙሉ እንደሚወገዱያረጋግጥልናል። ይህ ተስፋ በራእይ መጽሐፍ ውስጥ ተገልጾአል:- “ታላቅም ድምፅ ከሰማይ:- እነሆ፣የእግዚአብሔር ድንኳን በሰዎች መካከል ነው ከእነርሱም ጋር ያድራል፣ እነርሱም ሕዝቡ ይሆናሉእግዚአብሔርም እርሱ ራሱ ከእነርሱ ጋር ሆኖ አምላካቸው ይሆናል፤ እንባዎችንም ሁሉ ከዓይኖቻቸውያብሳል፣ ሞትም ከእንግዲህ ወዲህ አይሆንም፣ ኀዘንም ቢሆን ወይም ጩኸት ወይም ሥቃይ ከእንግዲህወዲህ አይሆንም፣ የቀደመው ሥርዓት አልፎአልና ብሎ ሲናገር ሰማሁ።ራእይ 21:3, 4

ይህ ዋስትና የተሰጠው ውድ መድኃኒቶችን የመግዛት አቅም ላላቸው ብቻ አይደለም። ኢሳይያስ 33:24 “በዚያም የሚቀመጥ:- ታምሜአለሁ አይልምበማለት በራእይ ምዕራፍ 21 ላይ የተገለጸውን ትንቢታዊቃል ያጠናክርልናል። በዚያ ዘመን በምድር ላይ የሚኖሩ ሁሉ የአምላክን ሕግ የሚጠብቁ ከመሆናቸውምበላይ ፍጹም የሆነ ጤና ያገኛሉ። በዚህ መንገድ የብዙዎችን ሕይወት እየቀጠፈ ያለው ኤድስም ሆነሌሎች በሽታዎች በሙሉ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ይወገዳሉ።

የንግድ ምልክት የሌላቸው መድኃኒቶች በሌሎች የመድኃኒት አምራች ኩባንያዎች የተፈበረኩመድኃኒቶችን በማስመሰል የሚሠሩ ናቸው። የዓለም የንግድ ድርጅት አባል የሆኑ አገሮች ድንገተኛናአጣዳፊ ሁኔታዎች በሚያጋጥሙበት ጊዜ የመድኃኒቶችን የባለቤትነት መብት ያለማክበር ህጋዊ ፈቃድአላቸው።

ስፈልገው የነበረው እውነተኛ ፈውስ ይህ ነው

በኤች አይ መያዜን ያወቅኩበት ቀን አሁንም ድረስ ትዝ ይለኛል ትላለች አንድ ወጣት

በሕክምና ክፍሉ ውስጥ ከእናቴ ጋር ቁጭ ብዬ ሳለ ነበር ዶክተሩ መርዶዬን የነገረኝ። በሕይወቴእንደዚያን ዕለት ያዘንኩበት ቀን አልነበረም። ሁሉ ነገር ተመሰቃቀለብኝ። ጆሮዬን ማመን አልቻልኩም።ምርመራው ላይ ስህተት ተሠርቶ ሊሆን ይችላል ብዬ አሰብኩ። የምናገረውና የማደርገው ነገር ሁሉጠፋኝ። አልቅሽ አልቅሽ ቢለኝም የማለቅስበት እንባ እንኳ አልነበረኝም። ዶክተሩ ስለ ዕድሜ ማራዘሚያመድኃኒቶችና ስለ ሌሎች ጉዳዮች ከእናቴ ጋር እየተነጋገረ የነበረ ቢሆንም በጣም ከመደንገጤ የተነሳ ምንእንደሚል እንኳ ሊገባኝ አልቻለም ነበር።

እማርበት በነበረው ዩኒቨርሲቲ ውስጥ አንድ ሰው አስይዞኝ ሊሆን እንደሚችል ገመትኩ። ያለሁበትንሁኔታ ሊረዳልኝ ለሚችል ሰው ስሜቴን ለማካፈል ብፈልግም ማንም ሰው ወደ አእምሮዬ ሊመጣልኝአልቻለም። የከንቱነትና የዋጋቢስነት ስሜት ተሰማኝ። ቤተሰቦቼ አስፈላጊውን ድጋፍ ቢያደርጉልኝምየተስፋ መቁረጥና የፍርሃት ስሜት አደረብኝ። እንደ ሌላ ማንኛውም ወጣት እኔም ብዙ የምመኛቸውነገሮች ነበሩ። በሳይንስ የመጀመሪያ ዲግሪዬን ለማግኘት ሁለት ዓመት ብቻ ቀርቶኝ የነበረ ቢሆንም ያሁሉ ተስፋ እንዳልነበረ ሆነ።

የታዘዙልኝን የዕድሜ ማራዘሚያ መድኃኒቶች መውሰድና ወደ ኤድስ ሕሙማን አማካሪዎች መሄድብጀምርም ያደረብኝ ጭንቀት ሊለቀኝ አልቻለም። ከመሞቴ በፊት እውነተኛውን ክርስትናእንዲያሳውቀኝ ወደ አምላክ ጸለይኩ።  ሁለቱ ሴቶች   በሬን አንኳኩ። ያን ቀን በጣም አሞኝ የነበረቢሆንም ሳሎን ውስጥ እንደ ምንም ብዬ ቁጭ አልኩ። ሁለቱ ሴቶች ራሳቸውን ካስተዋወቁኝ በኋላ ሰዎችመጽሐፍ ቅዱስን እንዲያጠኑ በመርዳት ላይ መሆናቸውን ነገሩኝ። ጸሎቴ በመጨረሻ መልስ በማግኘቱትልቅ እፎይታ ተሰማኝ። ሆኖም አቅም አንሶኝ ስለነበር ረዘም ላለ ጊዜ ማንበብም ሆነ በትኩረትመከታተል አልቻልኩም። ሆኖም መጽሐፍ ቅዱስ ማጥናት እንደምፈልግ ነገርኳቸውና ቀጠሮ ይዘንተለያየን። ይሁንና የቀጠሮው ጊዜ ከመድረሱ በፊት ባደረብኝ የመንፈስ ጭንቀት ሳቢያ የአእምሮሕሙማን ወደሚታከሙበት ሆስፒታል ገባሁ። ከሦስት ሳምንታት በኋላ ከሆስፒታል ስወጣ ሁለቱ ሴቶችእንዳልረሱኝ በማወቄ በጣም ደስ አለኝ።  ሁለቱ ሴቶች አንዷ ዘወትር እየመጣች ትጠይቀኝ እንደነበርአስታውሳለሁ። በተወሰነ ደረጃ አገገምኩና ዓመቱ መገባደጃ ላይ መጽሐፍ ቅዱስ ማጥናት ጀመርኩ።ይሁን እንጂ የጤንነቴ ሁኔታ በየጊዜው ይለዋወጥ ስለነበረ ይህን ማድረጉ ቀላል አልነበረም። ሆኖምየምታስጠናኝ ሴት ችግሬን ትረዳልኝ የነበረ ከመሆኑም በላይ ታጋሽ ነበረች።

ስለ እግዚአብሔርና ስለ ባሕርያቱ ከመጽሐፍ ቅዱስ ስማርና እግዚአብሔርን ማወቅና የዘላለም ሕይወትተስፋን መጠባበቅ ምን ማለት እንደሆነ ስገነዘብ ልቤ በጣም ተነካ። በተጨማሪም በሰው ልጆች ላይመከራ የሚደርሰው ለምን እንደሆነ ለመጀመሪያ ጊዜ በግልጽ ተረዳሁ። በቅርቡ ሰብዓዊ መንግሥታትንሁሉ ስለሚተካው የእግዚአብሔር  መንግሥት ያገኘሁት እውቀትም እጅግ ያስደሰተኝ ከመሆኑም በላይአኗኗሬን ሙሉ በሙሉ እንድለውጥ አነሳሳኝ።

ስፈልገው የነበረው እውነተኛ ፈውስ ይህ ነው። እግዚአብሔር  አሁንም እንደሚወደኝና እንደሚያስብልኝማወቄ በጣም አጽናናኝ። ቀደም ሲል  እግዚአብሔር  እንደጠላኝና ይህ በሽታ የያዘኝም በዚሁ ምክንያትእንደሆነ አድርጌ አስብ ነበር። ይሁን እንጂ እግዚአብሔር  በፍቅር ተነሳስቶ በኢየሱስ ክርስቶስ ቤዛዊመሥዋዕት አማካኝነት የኃጢአት ይቅርታ ማግኘት የምንችልበትን ዝግጅት እንዳደረገ ሳውቅእርሱ ስለእናንተ ያስባልና የሚያስጨንቃችሁን ሁሉ በእርሱ ላይ ጣሉትየሚለው 1 ጴጥሮስ 5:7 ጥቅስበሚገልጸው መሠረት በእርግጥም እግዚአብሔር  የሚያስብልን መሆኑን ተገነዘብኩ።

መጽሐፍ ቅዱስን በየዕለቱ በማጥናትና በሚካሄዱ ስብሰባዎች ላይ በመገኘት ወደ እግዚአብሔር ለመቅረብየተቻለኝን ሁሉ እያደረግኩ ነው። ይህን ማድረጉ ሁልጊዜ ቀላል ባይሆንም እንኳ የሚያስጨንቀኝን ሁሉለእግዚአብሔር በጸሎት በመግለጽ ብርታትና ማጽናኛ እንዲሰጠኝ እለምነዋለሁ። በተጨማሪምየጉባኤያችን አባላት ምንጊዜም ከጎኔ ስለሆኑ በጣም ደስተኛ ነኝ።

  ክፍል 3

 

ሁሉም ሰው አልፎ አልፎ ይታመማል። ሰዎች የሚታመሙት፣ የሚያረጁትና የሚሞቱት ለምን እንደሆነ ታውቃለህ? አንድ ቀን ሰዎች መራመድ የማይችል ሰው ወደ ኢየሱስ አምጥተው ነበር፤ በዚህ ጊዜ ኢየሱስ ሰዎች የሚታመሙትና የሚሞቱት ለምን እንደሆነ ጠቁሞ ነበር። እስቲ በዚያ ወቅት የተፈጸመውን ነገር ልንገርህ።

ኢየሱስ በገሊላ ባሕር አቅራቢያ በሚገኝ አንድ ቤት ውስጥ ተቀምጦ ነበር። በዚህ ጊዜ ብዙ ሰዎች ወደ እሱ መጡ። በጣም ብዙ ሰዎች መጥተው ስለነበር ሌሎች ተጨማሪ ሰዎች ወደ ቤት መግባት አልቻሉም። ከሕዝቡ ብዛት የተነሳ ወደ በሩ ለመጠጋት የሚያስችል ቦታ እንኳ አልነበረም። ያም ሆኖ ሰዎቹ መምጣታቸውን አላቋረጡም ነበር። በዚህ ጊዜ ሰዎች መራመድ የማይችል ሽባ የሆነ ሰው አመጡ። ሰውየውን በትንሽ አልጋ ወይም በቃሬዛ ላይ አድርገው የተሸከሙት አራት ሰዎች ነበሩ።

ሰዎቹ ይህን የታመመ ሰው ወደ ኢየሱስ ማምጣት የፈለጉት ለምን እንደሆነ ታውቃለህ? ኢየሱስ ሊረዳውና ከበሽታው ሊፈውሰው እንደሚችል እርግጠኞች ስለነበሩ ነው። ታዲያ ሁሉ ሰው እያለ ሽባውን ሰው እንዴት ኢየሱስ ፊት እንዳቀረቡት ታውቃለህ?

በመጀመሪያ ሰውየውን ተሸክመው ጣሪያው ላይ ወጡ። ጣሪያው ለጥ ያለ ነበር። ከዚያም ጣሪያውን በስተው ሰውየውን ሊያሾልክ የሚችል ትልቅ ቀዳዳ ሠሩ። በመጨረሻም የታመመውን ሰው ከነአልጋው በቀዳዳው በኩል አሾልከው ወደ ውስጥ አወረዱት። በእርግጥም ጠንካራ እምነት ነበራቸው!

በቤቱ ውስጥ ያሉት ሰዎች በሙሉ ይህን ሲያዩ ተገረሙ። ሽባውን ሰው የተሸከሙት ሰዎች ከነአልጋው አውርደው በተሰበሰቡት ሰዎች መካከል አደረጉት። ኢየሱስ ሰዎቹ ያደረጉትን ሲያይ ተቆጣ? በጭራሽ! እንዲያውም ሰዎቹ ባሳዩት እምነት ተደስቶ ነበር። ሽባውንኃጢአትህ ይቅር ተብሎልሃልአለው።

በቦታው የነበሩት አንዳንድ ሰዎች ኢየሱስ እንዲህ ብሎ መናገሩ ትክክል አይደለም ብለው አሰቡ። ኢየሱስ ኃጢአትን ይቅር ማለት የሚችል አልመሰላቸውም ነበር። ስለዚህ ኢየሱስ ኃጢአትን ይቅር ማለት እንደሚችል ለማሳየት ሰውየውንተነስ፣ አልጋህን ተሸክመህ ወደ ቤትህ ሂድአለው።

ኢየሱስ ይህን ሲናገር ሰውየው ተፈወሰ። ሽባ መሆኑ ቀርቶ አሁን ያለማንም ድጋፍ ራሱ ቆሞ መሄድ ቻለ። ይህን ተአምር ያዩት ሰዎች በጣም ተገረሙ። በሕይወታቸው በሙሉ እንደዚህ ያለ አስገራሚ ነገር አይተው አያውቁም። ሰዎችን ከበሽታቸው መፈወስ የሚችል እንደዚህ ያለ ታላቅ አስተማሪ ስለሰጣቸውአምላክን አመሰገኑት።ማርቆስ 2:1-12

እኛ ከዚህ ተአምር ምን እንማራለን? ኢየሱስ ኃጢአትን ይቅር ለማለትና የታመሙ ሰዎችን ለማዳን የሚያስችል ኃይል እንዳለው እንማራለን። ይሁን እንጂ ሌላም የምንማረው በጣም አስፈላጊ ነገር አለ። ሰዎች የሚታመሙት በኃጢአት ምክንያት እንደሆነ እንማራለን።  ታዲያ ሁላችንም አንዳንድ ጊዜ የምንታመመው ኃጢአተኞች ስለሆንን ነው ማለት ነው? አዎ፣ መጽሐፍ ቅዱስ ሁላችንም ኃጢአተኞች ሆነን እንደተወለድን ይናገራል። ኃጢአተኛ ሆኖ መወለድ ምን ማለት እንደሆነ ታውቃለህ?ሁላችንም ፍጽምና የሌለን ወይም ጉድለት ያለብን ሆነን ተወልደናል ማለት ነው። አንዳንድ ጊዜ ሳንፈልግ ስህተት እንሠራለን። ሁላችንም ኃጢአተኞች ልንሆን የቻልነው ለምን እንደሆነ ታውቃለህ?

ሁላችንም ኃጢአተኞች ልንሆን የቻልነው የመጀመሪያው ሰው አዳም አምላክን ስላልታዘዘ ነው። አዳም የአምላክን ሕግ በጣሰ ጊዜ ኃጢአት ሠራ። እኛ ሁላችን ደግሞ ከአዳም ኃጢአትን ወረስን። ኃጢአት ከአዳም የተጋባብን እንዴት እንደሆነ ታውቃለህ? እስቲ ይህን ነገር ሊገባህ በሚችል መንገድ ላስረዳህ።

ዳቦ ሲጋገር አይተህ ታውቃለህ? የዳቦ መጋገሪያ ዕቃው የተሰረጎደ ከሆነ የሚጋገረው ዳቦ ሁሉ ምን እንደሚሆን ታውቃለህ? በዚህ ዕቃ የሚጋገረው ዳቦ ሁሉ ልክ እንደ ዕቃው የተሰረጎደ ይሆናል፣ አይደል?

አዳም እንደ ዳቦ መጋገሪያ ዕቃው ሲሆን እኛ ሁላችን ደግሞ እንደ ዳቦው ነን። አዳም የአምላክን ሕግ ሲጥስ ፍጽምና የጎደለው ሆነ። ልክ እንደ ዕቃው የተሰረጎደ ወይም መጥፎ ምልክት የወጣበት ያህል ነበር። ስለዚህ እሱ የሚወልዳቸው ልጆች እንዴት ያሉ ይሆናሉ? ልጆቹ በሙሉ ያንኑ የአለፍጽምና ምልክት ወይም ጉድለት ይዘው ይወለዳሉ።

አብዛኞቹ ልጆች ሲወለዱ በዓይን የሚታይ ትልቅ ጉድለት አይኖርባቸውም። እጅ ወይም እግር የሌላቸው ሆነው አይወለዱም። ሆኖም ያለባቸው አለፍጽምና ወይም ጉድለት ከባድ በመሆኑ ይታመሙና ከጊዜ በኋላ ይሞታሉ።

እርግጥ ነው፣ አንዳንድ ሰዎች ከሌሎች ይበልጥ ቶሎ ቶሎ ይታመማሉ። ይህ የሆነው ለምንድን ነው? ከሌሎች ሰዎች የበለጠ ኃጢአተኛ ሆነው ስለሚወለዱ ነው? አይደለም፤ ሁሉም ሰው ይዞት የሚወለደው ኃጢአት መጠን እኩል ነው። ሁላችንም ኃጢአተኞች ሆነን ተወልደናል። ስለዚህ ከጊዜ በኋላ ሁሉም ሰው በሆነ ዓይነት በሽታ መታመሙ አይቀርም። የአምላክን ሕግ በሙሉ ለመታዘዝ የሚጥሩና ምንም ዓይነት ክፉ ነገር የማይሠሩ ሰዎችም እንኳን ሊታመሙ ይችላሉ።

ታዲያ አንዳንዶቹ ሰዎች ከሌሎቹ ይበልጥ ቶሎ ቶሎ የሚታመሙት ለምንድን ነውይህ የሚሆንበት ብዙ ምክንያት አለ። ምናልባት የሚመገቡት በቂ ምግብ ላይኖራቸው ይችላል። ወይም ደግሞ ለጤንነታቸው ጠቃሚ የሆነ ምግብ አይመገቡ ይሆናል። እንደ ኬክና ከረሜላ ያሉ ብዙ ጣፋጭ ነገሮች ይበሉ ይሆናል። ሌላው ምክንያት ደግሞ ማታ ቶሎ ስለማይተኙና በቂ እንቅልፍ ስለማያገኙ ሊሆን ይችላል። ወይም ደግሞ በዝናብና በብርድ ሰዓት የሚሞቅ ልብስ አይለብሱ ይሆናል። አንዳንድ ሰዎች ደግሞ ራሳቸውን ለመንከባከብ ቢጥሩም ሰውነታቸው ከሌሎቹ ይበልጥ ደካማና በሽታን መከላከል የማይችል ነው።

ታዲያ ፈጽሞ የማንታመምበት ጊዜ ይመጣ ይሆን? ከኃጢአት ነፃ መሆን እንችል ይሆን? ኢየሱስ ለሽባው ሰው ያደረገለት ነገር ምን ነበር? ኢየሱስ ኃጢአቱን ይቅር ብሎታል፤ እንዲሁም ፈውሶታል። ኢየሱስ ይህን መፈጸሙ ትክክል የሆነውን ነገር ለማድረግ ለሚጥሩ ሰዎች ሁሉ አንድ ቀን ምን እንደሚያደርግላቸው ያሳያል።

እኛም ኃጢአት መሥራት እንደማንፈልግና መጥፎ የሆነውን ነገር እንደምንጠላ የምናሳይ ከሆነ ኢየሱስ ይፈውሰናል። ወደፊት አሁን ያለብንን አለፍጽምና ሁሉ ያስወግድልናል። ይህን የሚያደርገው የአምላክ መንግሥት ንጉሥ ሆኖ በሚገዛበት ጊዜ ነው። ኃጢአታችን የሚወገድልን በአንድ ጊዜ ሳይሆን ቀስ በቀስ ነው። ከዚያም ኃጢአታችን ሙሉ በሙሉ ሲወገድ ዳግመኛ አንታመምም። ሁላችንም ፍጹም ጤንነት ይኖረናል። ይህ በጣም የሚያስደስት ይሆናል!

ኃጢአት በሁላችንም ላይ ምን እንደሚያስከትል ይበልጥ ለመረዳት ኢዮብ 14:4 መዝሙር 51:5 ሮም 3:23 5:12 እና 6:23 አንብቡ።

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

 መጽሐፍ ቅዱስ የሕክምና መጽሐፍ አይደለም፤ ደግሞም ሰዎች የሚያደርጉትን እያንዳንዱን ነገር የሚቆጣጠር መመሪያ አልያዘም። ያም ቢሆን አምላክ፣ ጤንነትን ስለ መጠበቅ ያለውን አመለካከት የሚጠቁሙ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የሚገኙ ሐሳቦችን ማወቅህ ይጠቅምሃል።

መጽሐፍ ቅዱስ ለሰውነታችን የምናደርገው እንክብካቤ አምላክን እንደሚያሳስበው የሚጠቁሙ በርካታ ሐሳቦች ይዟል። ለምሳሌ ያህል፣ መጽሐፍ ቅዱስ ሆዳምነትንና ሰካራምነትን ጨምሮ ከልክ በላይ የሚደረጉ ጎጂ ነገሮችን ያወግዛል። (ምሳሌ 23:20) አምላክ ለጥንቶቹ እስራኤላውያን በሰጠው ሕግ ላይ በሽታዎች እንዳይስፋፉ ለመቆጣጠር ከተቻለም እንዳይከሰቱ ለመከላከል መደረግ ያለባቸው ነገሮች ተካትተዋል። በተጨማሪም ሕጉ በሰው ላይ ጉዳት የሚያደርሱ አደጋዎችን ለማስወገድ የሚረዱ የደህንነት መመሪያዎችን ይዟል። (ዘዳግም 22:8) ከዚህ በግልጽ ለማየት እንደሚቻለው መጽሐፍ ቅዱስ፣ ሰውነታችንን እንድንንከባከብና ጤንነታችንን ለመጠበቅ አስፈላጊውን ነገር እንድናደርግ ያበረታታል።

የምንታመምበትን ምክንያት በተመለከተ መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

በአንድ ሰው አማካኝነት ኃጢአት ወደ ዓለም ገባ፤ በኃጢአትም ምክንያት ሞት መጣ።ሮም 5:12

ሰዎች ምን ይላሉ?

ብዙዎች በሽታ ሰው በዝግመተ ለውጥ ሲገኝ በአጋጣሚ የተከሰተ ችግር እንደሆነ ያምናሉ። ሌሎች ደግሞ እንደ ክፉ መናፍስት ያሉ ሚስጥራዊ ኃይሎች የጤና መቃወስ እንደሚያስከትሉብን አድርገው ያስባሉ።

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

መጽሐፍ ቅዱስ፣ የምንታመመው የመጀመሪያዎቹ ባልና ሚስት በአምላክ ላይ በማመፃቸው ምክንያት እንደሆነ ይናገራል። (ሮም 5:12) የመጀመሪያዎቹ ወላጆቻችን አዳምና ሔዋን በአምላክ ላይ ከማመፃቸው በፊት ፍጹም ጤንነት ነበራቸው። አፍቃሪ የሆነውን አምላክ እንክብካቤ ካጡ እንደሚሞቱ ያውቁ ነበር። (ዘፍጥረት 2:16, 17) ይሁንና ሆን ብለው ከአምላክ ጋር እንዲቆራረጡ የሚያደርግ ነገር ፈጸሙ፤ በመሆኑም ፍጽምናቸውን አጡ።*

ፍጽምናቸውን ያጡት የመጀመሪያዎቹ ወላጆቻችን ለእኛም አለፍጽምናን አወረሱን። በመሆኑም የጤና እክሎችን ለማስወገድ የቱንም ያህል ጥረት ቢደረግ መታመማችን አይቀርም።

ምን ማድረግ ትችላለህ?

አምላክ ያወጣቸውን ጥበብ የሚንጸባረቅባቸው መመሪያዎች በመታዘዝ ከእሱ ጋር እርቅ ከፈጠርክወደፊት ምድር ገነት ስትሆን ፍጹም ጤንነት አግኝተህ መኖር እንደምትችል መጽሐፍ ቅዱስ ያስተምራል።(ኢሳይያስ 33:24) አምላክ ሕመምን፣ በሽታንና ሞትን ለማስወገድ ቃል ገብቷል። ራእይ 21:3, 4

መጽሐፍ ቅዱስ የሕክምና እርዳታ ማግኘትን ይቃወማል?

ሐኪም የሚያስፈልጋቸው ሕመምተኞች እንጂ ጤነኞች አይደሉም።ማቴዎስ 9:12

ሰዎች ምን ይላሉ?

አንዳንዶች የሕክምና እርዳታ ከማግኘት ይልቅ ሃይማኖታዊ ፈውስ (ወይም የእምነት ፈውስ) ማግኘትየተሻለ እንደሆነ ይናገራሉ።

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

በጥንት ዘመን በነበሩ የአምላክ ሕዝቦች መካከል የጤና እርዳታ የሚሰጡ ሰዎች የነበሩ ሲሆን አምላክይህን ሙያቸውን አልተቃወመም። (ዘፍጥረት 38:28 ቆላስይስ 4:14) እነዚህ ሰዎች ለመድኃኒትነትየሚውሉ ተክሎችንና ቅባቶችን በመጠቀም እንዲሁም ለሕመምተኞቹ አንድ ዓይነት የአመጋገብ ሥርዓትበማዘዝ ወይም በሌሎች የሕክምና ዘዴዎች ተጠቅመው ሕክምና በመስጠታቸው አምላክ እንዳልተደሰተየሚገልጽ ሐሳብ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አናገኝም። እንዲያውም ኢየሱስሐኪም የሚያስፈልጋቸውሕመምተኞች እንጂ ጤነኞች አይደሉምሲል ተናግሯል። ማቴዎስ 9:12

ይሁን እንጂ መጽሐፍ ቅዱስ ጤነኛ ለመሆን ማንኛውም ዓይነት መሥዋዕት መከፈል አለበት የሚለውንአመለካከት አይደግፍም። ለምሳሌ ያህል መጽሐፍ ቅዱስ፣ በዛሬው ጊዜ በሚከናወነው የእምነት ፈውስከተፈወሱ መልካም ነው   ከዚህም ሌላ በመናፍስታዊ ድርጊቶች አማካኝነት ፈውስ ለማግኘት መሞከርበአምላክ ዘንድ ተቀባይነት የለውም። (ገላትያ 5:19-21) የጤና እክል በሚያጋጥመን ጊዜ መጽሐፍ ቅዱስበሚያወግዛቸው መንገዶች መጠቀም ተገቢ ባይሆንም የሚቻል ከሆነ ወዲያውኑ ጥሩ ሕክምና ለማግኘትመሞከር የጥበብ እርምጃ ነው።

በዚህ ርዕስ ውስጥፍጹምእናፍጽምናየሚሉትን ቃላት የተጠቀምነው የመጀመሪያዎቹ ባልና ሚስትአምላክ ሲፈጥራቸው የነበራቸውን ጤንነት ለማመልከት ነው፤ የመጀመሪያዎቹ ወላጆቻችን በሕመም፣በበሽታና በሞት አይጠቁም ነበር።

 

 

በአንድ ሰው በአዳም የተነሳ ኃጢአት ወደ ዓለም ገባ፤ በኃጢአትም ምክንያት ሞት መጣሮም 5:12  ብዙዎች ስዎች በሽታ ሰው በዝግመተ ለውጥ ሲገኝ በአጋጣሚ የተከሰተ ችግር ነው ብለው ሲያምኑ፣ ሌሎች ደግሞ እንደ ክፉ መናፍስት ያሉ ሚስጥራዊ ኃይሎች የጤና መቃወስ እንደሚያስከትሉብን አድርገው ያስባሉ።

መጽሐፍ ቅዱስ፣ የምንታመመው የመጀመሪያዎቹ ባልና ሚስት አዳምና ሔዋን በእግዚአብሄር ላይ በማመፃቸው የተነሳ እንደሆነ ይናገራል (ሮም 5:12) የመጀመሪያዎቹ ወላጆቻችን አዳምና ሔዋን በእግዚአብሄር ላይ ከማመፃቸው በፊት ፍጹም ጤንነት ነበራቸው። አፍቃሪ የሆነውን አምላክ እንክብካቤ ካጡ እንደሚሞቱ ያውቁ ነበር። (ዘፍጥረት 2:16, 17) ይሁንና  ከእግዚአብሄር ጋር እንዲቆራረጡ የሚያደርጋቸው ሃጢያትን ፈጸሙ፤ በመሆኑም እግዚአብሄር ካስቀመጠላቸው ደረጃ ወይም መመሪያ ዝቅ አሉ ስለሆነም ችግር ውስጥ ገቡ ፍጽምናቸውን ያጡት የመጀመሪያዎቹ ወላጆቻችን ለእኛም ሃጢያትን አወረሱን። በመሆኑም የጤና እክሎችን ለማስወገድ የቱንም ያህል ጥረት ቢደረግ መታመማችን አይቀርም። እግዚአብሄር ያወጣቸውን ጥበብ የሚንጸባረቅባቸው መመሪያዎች በመታዘዝ ከእሱ ጋር እርቅ አንድ ስው ከመስረተ ወደፊት በኢሳይያስ 33:24 ራእይ 21:3- 4  እግዚአብሄር ሕመምን፣ በሽታንና ሞትን ለማስወገድ ቃል ገብቷል  ጤንነትም ተገኝቶ መኖር እንደሚቻል መጽሐፍ ቅዱስ ያስተምራል።

ከላይ እንዳነሳሁት በሽታ ወደ አለም የገባው በሐጢያት የተነሳ ሲሆን እተባባስ የሄደው በሞራል ወድቀትና በድሎትና በምቾት የተነሳ ነው። የበሽታ ከተፈጥሮ መነሻዎቹ  ደግሞ በእብራውያን መካከል በክፉ መናፍስት የተነሳ በሽታዎች በኢዮብ 27 ማርቆ. 917 ሉቃስ 1316 1 ቆር. 127 ተጠቅስዋል። ሃይማኖተኛ የሆኑት አይሆዳውያን ደግሞ በሽታ በእግዚአብሔር እጅ የሚላክ መሆኑን በመዝ. 399-11 መዝ. 903-12 ተጽፎል በነርሱ አስተሳስብ በሁሉም ሁኔታ የተለዩ በሽታዎች ወደ ስው የሚላኩት ለቅጣት እንደሆነ በአቤሜሌክ ግያዝ እዮብ ኡዚያ ሚሪያም ሄሮድና ፍልስጤማያን ወዘተ  ታሪካቸው ያመለክታል።

ከተባሉትም ሌላ ጥንትም ሆነ አሁን የሰውን ዘር የሚያጠቁ አብዛኞቹ በሽታዎች እንደ ፍርሃት፣ ሐዘን፣ ቅናት፣ ብስጭት፣ ጥላቻና የጥፋተኝነት ስሜት ከመሳሰሉ ስሜታዊ ውጥረቶች እንደሚመነጩ ይታመናል። ከዚህ አንፃርእግዚአብሄርን መፍራት’ “ለሥጋህ  ፈውስ  ለአጥንትህም ጠገንነው የሚለው የመጽሐፍ ቅዱስ አነጋገር ያጽናናል ምሳሌ 3:7, 8  አጥንት የሰውነት ምሰሶ ነው። በመሆኑም መጽሐፍ ቅዱስ አንድን ሰው በተለይም ጥልቅ በሆኑ ስሜቶች የሚነካውን የአንድን ሰው ውስጣዊ ማንነት ለማመልከትአጥንትየሚለውን ቃል በምሳሌያዊ አነጋገር ይጠቀምበታል። ሆኖም እግዚአብሄርን መፍራትለስውነትህ ፈውስየሚሆነው እንዴት ነውእግዚአብሄርን መፍራት የጥበብ መንገድ ነው። ከእግዚአብሄር የአቋም ደረጃዎች ጋር ተስማምቶ መኖር አሁንም ቢሆን በአካል ጤነኞች እንድንሆን ሊረዳን ይችላል። ከዚህም በላይ የእግዚአብሄር ሞገስ ያስገኝልናል። ይህ ደግሞ እግዚአብሄር በአካልም በስሜትም ፍጹም ጤንነት ወደምናገኝበት ፍጻሜ ወደሌለው ሕይወት ይመራናል ኢሳይያስ 33:24 ራእይ 21:4 22:2

አንዳንዶች የሕክምና እርዳታ ከማግኘት ይልቅ ሃይማኖታዊ ፈውስ (ወይም የእምነት ፈውስ) ማግኘት የተሻለ እንደሆነ ይናገራሉ።በጥንት ዘመን በነበሩ የእግዚአብሄር ሕዝቦች መካከል የጤና እርዳታ የሚሰጡ ሰዎች የነበሩ ሲሆን እግዚአብሄር ይህን ሙያቸውን አልተቃወመም። (ዘፍጥረት 38:28 ቆላስይስ 4:14) እነዚህ ሰዎች ለመድኃኒትነት የሚውሉ ተክሎችንና* ቅባቶችን በመጠቀም እንዲሁም ለሕመምተኞቹ አንድ ዓይነት የአመጋገብ ሥርዓት በማዘዝ ወይም በሌሎች የሕክምና ዘዴዎች ተጠቅመው ሕክምና በመስጠታቸው አምላክ እንዳልተደሰተ የሚገልጽ ሐሳብ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አናገኝም። ይሁን እንጂ መጽሐፍ ቅዱስ ጤነኛ ለመሆን ማንኛውም ዓይነት መሥዋዕት መከፈል አለበት የሚለውን አመለካከት አይደግፍም ማለትም በመናፍስታዊ ድርጊቶች አማካኝነት ፈውስ ለማግኘት መሞከር በእግዚአብሄር ዘንድ ተቀባይነት የለውም። (ገላትያ 5:19-21) የጤና እክል በሚያጋጥመን ጊዜ መጽሐፍ ቅዱስ በሚያወግዛቸው መንገዶች መጠቀም ተገቢ ያለመሆኑን የተረዳ ስው ለፈውስ መጸለይ ወይም የሚችል ከሆነ ወዲያውኑ ጥሩ ሕክምና ለማግኘት መሞከር የጥበብ እርምጃ ነው።

(med'-i-sin, med'-i-s'-n) የሐጢያት መድሐኒት ማለት ሲሆን (gehah, teruphah, rephu'ah) እነዚህ ቃላት በሥራ ላይ የዋሉት ለበሽታ በመድሐኒትነት ነው። በምሳሌ 17:22 በኪንግ ጄምስ ቨርሽን የተነሳውደስ የሚለው ልብእንደ ጥሩ መድሐኒት ነው ይለዋል።

በምሳሌአዊ አባባል ይሁዳንና እስራኤልን በተመለከተ ወደ ህዋላ ስለመመለስ (ኤርም. 30:13) የተመለከተ ነው።  ነብዮ እንዳለው rephu'ah የሚፈውስ መድሐኒት (ኤር. 30:13) ነብዮ እንዳለው የሚፈውስ መድሐኒት የለም ነው። በመጨረሻም በኤር. 46:11 ኤርሚያስ ግብጽን ካልተፈውስች ሴት ወደ ገላአድ በለሳን ለመግዛት  ከሄደችው ድንግልን ጋር ያወድድራታል። የነብዩ የህዝቅኤል ስለ ህይወት ዛፍና ቅጠሎቹ ያየው ራእይ (በኪንግ ጀምስ  ቨርቪን) መድሐኒት የሚለውን ሲሆን ዘሪቫይዝድ ቨርቪን የብሪቲሽን የአሜሪካን የሚያሳየውየሚፈውስ ወይም ፈውስይለዋል አባባሉም ራዕ. 22:2 ላይ የተጠቀስውንየዛፉ ቅጠሎችህዝቡን ሁሉ የሚፈውስከሚለው ከህዝቅኤል 47:12 አወዳድር።  

በጣም ጥቂት የተወሰኑ መፍትሄዎች በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጠቀሱ አሉ። እነዚህም (በኤርምያስ 8:22) "የገለዓድ በለሳን" አንድ anodyne እንደሆነ ይነገራል። "እንኮይ" (ዘፍጥረት 30:14) እና "caperberry" (መክብብ 12: 5 ከርቤ  ከእንስላል  ከአትክልትም  ከከሙንም  "ዘይትና የወይን ጠጅ" መልካም ሳምራዊ  ሳሙና እና sodic ካርቦኔት (cleansers በስህተት "nitre") የተባለ በናትሮን" እና "የበለስ ጥፍጥፍ" ናቸው።

 የግብጽ ፈርማኮፒያ ውስጥ ተለይተው ሊታወቁ የማይችሉ ብዙ ዕፅዋት ነበሩ ነገር ግን ጥቅም ላይ መድኃኒቶች አብዛኞቹ እንደ ማር ወተት ዱቄት ዘይት ኮምጣጤ, ወይን ጠጅ እንደ Dietetic ነበር።  የባቢሎናውያን መድሃኒቶ ተመሳሳይ  Mishna ውስጥ እሬት  የዱር አበባ  hemlock aconite እና ሌሎች መድኃኒቶች ነበሩ የኪንግ ጀምስ ቅጂ (ዘፀአት 30:25) በዚያን ጊዜ በአፓቲካሪ ጥበብ የተቀመመ የተቀደስ ዘይት እንደሆነ ነው  የተጠቀሰው የሽቶዎችና የመድሃኒቶች ሽቶዎች ሠሪ እንደነበረ ያመለክታል።

በመጽሐፍ ቅዱስ ጊዜ የተለያዮ በሽታዎች የሚታከሙት በባለመድሐኒቶች ምናልባትም ከተክሎች በሚገኙ መድሐኒቶች ነው ተብሎ ይታመናል ለዚህም ምሳሌ ንጉስ አሳ 2 ዜና መዋዕል 1612 እንደተጠቀስውበነገስ በስላሳ ዘጠነኛው አመት አሳ እግሩን ታመመ ደዌውም ጽናበት ነገር ግን በታመመ ጊዜ ባለ መድሐኒቶችን እንጂ እግዚአብሄርን አልፈለገምፈውስንም አላገኘም። መድኃኒትነት ያላቸው እጽዋት ለሕክምና ተግባር ማገልገል ከጀመሩ በጣም ረጅም ዘመን አልፏል። 16ኛው መቶ ዘመን ከክርስቶስ ልደት በፊት በግብጽ በተዘጋጀው ኤበርስ ፓፒረስ የተባለ ጽሑፍ ውስጥ ለተለያዩ በሽታዎች የሚያገለግሉ በመቶዎች የሚቆጠሩ የተፈጥሮ መድኃኒቶች ተመዝግበው ተገኝተዋል። ይሁን እንጂ አብዛኛውን ጊዜ መድኃኒትነት ያላቸው እጽዋት በጽሑፍ ሰፍረው የሚገኙ ሳይሆን በአፍ ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲተላለፉ የቆዩ ናቸው።

በጥንቱ የብሉይ ኪዳን ህብረተስብ የአይን ሕመምም ሌላው ችግራቸው ነበር ይህም በአያሌ ሥፍራዎች በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ተጠቅሷል የተጠቀስውም ከሌሎቹ በሽታዎች ጋር ሲሆን የበለጠ የተያያዘው በአይሁዶች ከግብጾችና ከፍልስፍጤም ስዎች ጋር ነበር። በዘፍጥረት 271 የተጠቀስውይስሐቅም ሽምግሎ አይኖቹ ከማየት በፈዘዙ ጊዜ  ችግሩ የካታራክት ወይም የሬቲና ዲጀነሬሽን ችግር ነው ያዕቆብ ደሞ ዘፍ. 4810 ዔሊ 1 ሳሙ. 415 ተመሳሳይ የአይን ችግሮች አሏቸው። ሙሴና በዘዳግም 347 ሙሴ በመቶ ጊዜ 120 አመቱ አይኑም አልፈዘዘም። ይህም በሽታ የሚይዘው በማንኛውም እድሜ ያሉትን ስዎች ሲሆን በከባድ ሁኔታ የሚተላለፍና በዚያን ጊዜ ከንጽሕና ጉድለትና  ልጆች ላይ በዝንቦች ከታመሙ ስዎች  አይን  ወደ ሌሎች ስዎች በዝንብም ሆነ በንክኪ ይህ አይነት ተላላፊ የአይን በሽታ ያጠቃቸው ነበር።

በአሁድም ሕብረተስብ ውስጥ ይኸው የአይን በሽታ ተባብሶ እውርነትን ስለሚያስከተል በዚህ የአይነስውር የሆኑ ቀሳውስት ማገልገል አይመረጡም (ዘለዋ. 211618) የአይን መሞጭሞችም እንኳ ለአገልግሎች እንዳይመረጥ ያደርገዋል (ዘለዋ. 2120)  በአዲስ ኪዳን ደሞ ከመወለዱ ጀመሮ እውር የነበር (ዮሐ. 91) ይኸኛውም ሌላ የአይን መታወር ችግር ነው። በማርቆስ 822 ላይ የተጠቀስውን ጌታ የፈውስው መታወሩ ከልጅነቱ ጀመሮ  እንደሆነ ያመለክታል። ቅዱስ ጳውሎስም በደማስቆ መንገድ ላይ ከታላቅ ብርሃን የተነሳ አይኑ እንደታወረ ያመለክታል በዚህ ሥፍራ የቅዱስ ጳውሎስ አይን የታወረው በአይኑ ውስጥ ከገባው ከታላቅ ብርሃን የተነሳ ነበር በሐዋሪያት ሥራ 918 ሐናንያ በጸለየለት ጊዜ ከአይኑ ላይ ቅርፊት ወደቀ ይሁን እንጂ የግራ አይኑ ምን ያህል ደካማ እንደሆነ አይታወቀም። በሮሜ 1622  የሮሜ መልክቱን የጻፈው እርሱ እራሱ ሳይሆን በቃል እየተናገረ የጻፈለት ሌላ እንደሆነ ያመለክታል ምናልባትም ቅዱስ ጳውሎስ የአይን ችግር ስለላው ነበር ተብሎ ይገመታል። በገላትያ 611 እንዴት ባሉ ትላልቅ ፈደላት በእጄ እንደጻፉላችሁ እዩ ብሎ ለገላትያ ስዎች ይጽፍላቸዋል ምናልባትም ከዚህ አባባሉ የአይን ጤና ችግሮች አሉት ይህም 2 ቆሮ. 127 የተጠቀስው ከዚህ የተነሳ ነው ተብሎ ይታመናል።

እግዚአብሄር አምላክ ሰብዓዊ ፍጡሮቹ ሲፈጥር እንዲታመሙና እንዲሞቱ ዓላማው አልነበረም። አዳምንና ሔዋንን በዔድን የአትክልት ቦታ ማለትም በደስታ ገነት ውስጥ ያስቀመጣቸው 70 ወይም 80 ዓመታት ብቻ ሳይሆን ለዘላለምእንዲያለሟትና እየተንከባከቡ እንዲጠብቋትነበር። (ዘፍ. 2:8, 15 መዝ. 90:10) እነዚህ የመጀመሪያዎቹ ባልና ሚስት ለእግዚአብሄር ታማኝ ሆነው ቢዘልቁና ለሉዓላዊነቱ በፍቅር ቢገዙ ኖሮ ጤና ማጣትንም ሆነ እርጅና የሚያስከትለውን ጉስቁልና እንዲሁም ሞትን ባላዩ ለኛም ባላስተላለፉት ነበር።  መክብብ ምዕራፍ 12 ፍጹማን ባልሆኑ ሰዎች ላይ ከእርጅና ጋር ተያይዞ ስለሚመጣውየጭንቀት ጊዜቁልጭ አድርጎ ይገልጻል። (መክብብ 12:1-7ሽበትከለውዝ ዛፍአበባ ጋር ተመሳስሏል። እግሮች፣ እየጎበጡና እየተብረከረኩ ከመጡብርቱሰዎች ጋር ተመሳስለዋል። የዓይን መዳከም፣ ብርሃን እናያለን ብለው ወደ መስኮት ሲመጡ ከጨለማ ሌላ ምንም ነገር ባላገኙ ወይዛዝርት መመሰሉ ትክክለኛ መግለጫ ነው። የረገፉ ጥርሶችጥቂት በመሆናቸው ምክንያት መፍጨት ባቆሙሴቶች ተመስለዋል። የሚብረከረኩ እግሮች፣ የደከሙ ዓይኖችና ጥርስ አልባ የሆኑ ድዶች አምላክ ለሰው ዘር የነበረው የመጀመሪያ ዓላማ ክፍል አይደሉም። ከዚህ በተጨማሪ ከአዳም የወረስነው ሞትከዲያብሎስ ሥራዎችአንዱ ሲሆን የእግዚአብሄር ልጅ በመስቀል ላይ በከፈለው ዋጋ አስወግዶታል  ለዚህ ነው  ሐዋርያው ዮሐንስየእግዚአብሔር ልጅ የተገለጠውም የዲያብሎስን ሥራ ያፈርስ ዘንድ ነውብሎ በድፍረት የጻፈው። 1 ዮሐ. 3:8::

መጽሐፍ ቅዱስ የሕክምና መጽሐፍ አይደለም፤ ደግሞም ሰዎች የሚያደርጉትን እያንዳንዱን ነገር የሚቆጣጠር መመሪያ አልያዘም። ያም ቢሆን እግዚአብሄር ጤንነትን ስለ መጠበቅ ያለውን አመለካከት የሚጠቁሙ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የሚገኙ ሐሳቦችን ያሳውቃል። መጽሐፍ ቅዱስ ለሰውነታችን የምናደርገው እንክብካቤ  እግዚአብሄርን እንደሚያሳስበው የሚጠቁሙ በርካታ ሐሳቦች ይዟል። ለምሳሌ ያህል መጽሐፍ ቅዱስ ሆዳምነትንና ሰካራምነትን ጨምሮ ከልክ በላይ የሚደረጉ ጎጂ ነገሮችን ያወግዛል። (ምሳሌ 23:20) እግዚአብሄር ለጥንቶቹ እስራኤላውያን በሰጠው ሕግ ላይ በሽታዎች እንዳይስፋፉ ለመቆጣጠር ከተቻለም እንዳይከሰቱ ለመከላከል መደረግ ያለባቸው ነገሮች ተካትተዋል። በተጨማሪም ሕጉ በሰው ላይ ጉዳት የሚያደርሱ አደጋዎችን ለማስወገድ የሚረዱ የደህንነት መመሪያዎችን ይዟል። (ዘዳግም 22:8) ከዚህ በግልጽ ለማየት እንደሚቻለው መጽሐፍ ቅዱስ፣ ሰውነታችንን እንድንንከባከብና ጤንነታችንን ለመጠበቅ አስፈላጊውን ነገር እንድናደርግ ያበረታታል።

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ብዙ ተስፋዎች ለነፍስም ሆነ ሥጋ ፈውስ ማግኛ መንገድ ተስጥተዋል፤ ሆኖም በመጸሐፍ  ቅዱስ ውስጥ የተጠቀሱትን ተስፋዎችና መመሪያዎችን አውቆ ከመጠቀም ይልቅ ባለማወቅ ብዙ ስዎች  በአካልና በነፍስ በሽታ ይስቃያሉ። በአሁኑ ጊዜ ፈውስ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገለጸው በምን መንገድ ነው? ለሚለው መልሱ መጽሐፍ ቅዱስ በዚህ አስፈላጊ በሆነ ትምህርት ላይ በደፈናው አያልፈውም ይልቁንም እግዚአብሔር  የፈውስን  መንገዶች እንደተከናውኑ ለትምህርታችን ተጽፈው ይገኛሉ።

•   እግዚአብሔር በሽታን እንደሚፈወስና ጤናን እንደሚያድስ (ዘዳግም 84) ያመለክታል ይህም እውነት ለብዙዎች ያስፈልጋል።

•   መጽሐፍ ቅዱስ ስለጤናማ ኒዩትሪሽን (ኦሪት ዘጽአት1516 ኦሪት ዘለዋውያን 11 ተጽፎ ይገኛል ጤናማ ያልሆኑ ምግቦች ለተለያዩ በሽታዎች ተመጋቢውን ያጋልጣሉ::  መጽሐፍ ቅዱስ ጤናማ አኗኗርን ማለትም ተከታታይ የስውነት እንቅስቃሴዎችንና ከተፈጥሮ ውጪ የሆኑ ጭናዎችን ማስወገድ (ኦሪት ዘለዋውያን 12-14) ተጽፎ ይገኛል ጫና የተለያዩ በሽታዎች መነሻ መሆኑን ያመለክታል   እግዚአብሔር ደግሞ ለጤና ፈውስን በመድሐኒት አዘጋጅቷል (ያዕቆብ 514)

ከሃጢያት የተነሳ የሚመጣውን በሽታ እግዚአብሔር በሽተኛውን ይቀርታ በመስጠትና በማንጻት ፈውስን ይስጣል (ኦሪት ዘሁልቁ 1213)

•  እግዚአብሔር በእምነት በጽሎት በሽታን ይፈውሳል (ያዕቆብ 515)

•    እግዚአብሔር ፈውስን በተአምር (በእግዚአብሄር ምርጫ) ወይም በመድሕኒት  ይፈውሳል የታመመው አማኝ  እንዲፈወስ ምን ማድረግ አለበት? በሌላ ጊዜም ደግሞ ስዎች ታመው እንደሐዋሪያው ጳውሎስ 2 ቆሮ. 127,10 ያልተፈውሱበት ጊዜ እንዳለ ማወቅ ይስፈልጋል   አማኙ በአካል የታመመ እንደሆነ የበሽታው መነሻ ምን እንደሆነ ለይቶ ማወቅ ይኖርበታል፤ በሽታው መነሻው ከኒዩትሪሽን የተነሳ ከሆነ ኒዩትሪሽንን በማስተካከል እራስን መርዳት ነው። መታወስ ያለበት በሆስዔ 46 ከውቀት ማጣት የተነሳ የሚመጣ ጉዳት እንዳለም ነው።

በሽታው በሀጢያት የተነሳ ከመጣ (ያዕቆብ 514,15) እንደተጠቀስው ፈውሱን መፈለግ ይኖርበታል    የአማኙ መታመም  ምናልባትም የእግዚአብሔር ፈቃድ ያለበት  2 ሳሙ. 4:4;  እና 2 ቆሮ.12:7,10 ላይ እንደተጠቀስው አይነት ከሆነ ደግሞ ሌላ ገጽታ አለው።

•     በጣም አስፈላጊ የሆነው የእምነት ጸሎት በሐዋሪያው ያዕቆብ የተጠቀስው የእምነት ጸሎት የተኮተኮተውና ጥንቃቄ የተደረገለት ትምህርቱ የሚያተኩረው በዮሐንስ ወንገል 1613 የተመስረተ የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያ ስለመሆን የተመለከተው ነው። የእምነት ጽሎት ያዕቆብ መንፈሳዊ መለየትንና መረዳትን በመለማመድ  እምነት ጸሎት ውጤቱ ምንም ይሁን መጸለየና መቆምን ያመለክታል።   ጸሎት እግዚአብሔር የሚፈውስበት መንገድ የቱንም  ይምረጥ ታማኝነቱን ያረጋግጣል ስለሆነም የእምነት ጽሎት ጸላዮ የሚቀበለው እግዚአብሔር አማኙ የተያዘበትን በሽታ በመዝ 234 ይቀበለዋል። የስውን ደካማነት የእግዚአብሔርን ጉልበት ይገልጣል (2 ቆሮ. 127,10)  ኢየሱስ በሽተኞችን የፈወሰው በዘመናችን ፈውስ ከሚያከናውኑ ሰዎች ፍጹም በተለየ መንገድ ነበር። ለምሳሌ ያህል፣ ኢየሱስ እርዳታ ፈልገው ወደ እሱ የመጡትን ሕመምተኞች በሙሉ ፈውሷል። ከታመሙ ሰዎች መካከል የተወሰኑትን ፈውሶ የተቀሩትን እንዲሁ አልተዋቸውም። ከዚህም በተጨማሪ ሰዎችን የፈወሰው ሙሉ በሙሉ ከመሆኑም ሌላ ሁልጊዜ ማለት ይቻላል ሰዎቹ ከበሽታቸው የሚድኑት ወዲያውኑ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስኀይል ከእርሱ እየወጣ ሁሉንም ይፈውስ ስለ ነበር፣ ሰዎቹ ሁሉ እርሱን ለመንካት ይፈልጉ ነበርበማለት ይናገራል ሉቃስ 6:19  ‘ኢየሱስ ሰዎችን የሚፈውሰው እምነታቸውን መሠረት አድርጎ ካልሆነ የፈወሳቸውን ሰዎች ብዙውን ጊዜእምነትህ አድኖሃልይላቸው የነበረው ለምንድን ነው?’ ተብሎ ቢጠየቅ (ሉቃስ 8:48 17:19 18:42) ኢየሱስ እንዲህ ብሎ ሲናገር እንደሚፈወሱ አምነው ወደ እሱ የመጡት ሰዎች እንደተፈወሱና ይህን ያላደረጉት ግን አጋጣሚውን ሳይጠቀሙበት እንደቀሩ መግለጹ ነበር።  እምነት አያስፈልግም እያልኩ አይደለም::  ከበሽታቸው የዳኑት ሰዎችም ቢሆኑ የተፈወሱት በእምነታቸው ብቻ ሳይሆን በእግዚአብሄር ኃይል ነው። መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ኢየሱስ ሲናገር እንዲህ ይላል፦   “እግዚአብሔር . . . በመንፈስ ቅዱስና በኀይል ቀባው፤ እርሱም እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ስለ ነበረ በደረሰበት ሁሉ መልካም እያደረገ በዲያብሎስ ሥልጣን ሥር የነበሩትን ሁሉ ፈወሰ።የሐዋርያት ሥራ 10:38

 "እግዚአብሔር ይፈውሳል ሐኪሙ ክፍያ ይጠይቃል" (ቤንጃሚን ፍራንክሊንሁሉንም ዓይነት ሕመምና በመጨረሻም ሞትን ሊያስቀር የሚችል አንድም የሰው ልጅ ሕክምና የለም። ይህ የሆነበት ምክንያት እነዚህ ከመጀመሪያው አባታችን ከአዳም የተወረሱ  በመሆናቸው ነው። (ኢዮብ 14:4 መዝሙር 51:5 ሮሜ 5:12) ብዙ የሕክምና ዓይነቶች ጠቃሚ ሆነው ሊገኙ ይችላሉ። ይሁንና ሕይወትን ከማራዘምና ለተወሰነ ጊዜ ብቻ ደህና ኑሮ እንዲኖር በማድረግ ለጊዜው እንደ ማስታገሻ ከማገልገል አያልፉም።

 

ክፍል 4

በዘመናችንተአምራዊ ፈውስየሚከናወነው በአምላክ ኃይል ነው?

ሁላችንም ስንታመም ከሥቃያችን እፎይ የምንልበትን ጊዜ እንናፍቃለን። ኢየሱስ ክርስቶስ ሁሉንም ዓይነት በሽታዎች በመፈወስ ለብዙ ሕሙማን እፎይታ አስገኝቶላቸው እንደነበር የሚገልጹ በርካታ ታሪኮችን ከመጽሐፍ ቅዱስ ላይ አንብበህ ይሆናል። እነዚህ ሰዎች ሊፈወሱ የቻሉት እንዴት ነበር? መጽሐፍ ቅዱስ በአምላክ ኃይል እንደሆነ ይገልጽልናል። (ሉቃስ 9:42, 43 የሐዋርያት ሥራ 19:11, 12) ስለሆነም ሰዎቹን እንዲፈወሱ ያስቻላቸው እምነታቸው ብቻ ሳይሆን የአምላክ ቅዱስ መንፈስ ነበር። (የሐዋርያት ሥራ 28:7-9) ኢየሱስ የታመሙ ሰዎች ከሕመማቸው ለመፈወስ በእርሱ ማመናቸውን እንዲናገሩ የማይጠብቅባቸው ለዚህ ነበር።

ተአምራዊ ፈውስ ጊዜ ያለፈበት ነገር ነው? ወይስ ኢየሱስ ያከናወናቸው ዓይነት ፈውሶች ወደፊትም ይኖራሉ? በሕመም የሚሰቃዩ ወይም ሊድን በማይችል በሽታ የተያዙ ሰዎች ምን ተስፋ አላቸው?’ ብለህ ትጠይቅ ይሆናል።

አምላክ ጽድቅ በሚሰፍንበት አዲስ ዓለም ውስጥ ኢየሱስ ምድር ሳለ ያከናወናቸውን ዓይነት ተአምራዊ ፈውሶች እንደገና እንደሚፈጽም መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል። በአካባቢህ የሚኖሩ ክርስቲያኖች አምላክ ሁሉንም ዓይነት በሽታዎች አልፎ ተርፎም ሞትን በማስቀረት ማንኛውም የእምነት ፈዋሽ ማከናወን የማይችለውን ፈውስ የሚፈጽመው እንዴትና መቼ እንደሆነ እንድታውቅ ሊረዱህ ፈቃደኞች ናቸው። አዎን፣ አምላክሞትንም ለዘላለም ሽሮአል።ኢሳይያስ 25:8

በአንዳንድ አገሮች፣ ሃይማኖተኛ የሆኑ ሰዎችበማይድንበሽታ የተያዙ ብዙዎች ፈውስ እንዳገኙባቸው ወደሚታሰቡ ቅዱስ ስፍራዎች ሲጓዙ ማየት የተለመደ ነው። በሌሎች አገሮችም፣ መለኮታዊ ኃይል በመጠቀም በሽተኞችን እንደሚፈውሱ የሚናገሩ ሰዎች አሉ። በሌሎች አካባቢዎች ደግሞ በአንዳንድ መንፈሳዊ ፕሮግራሞች ላይ፣ የታመሙ ሰዎች ፈውስ እንዳገኙ በመናገር ከተሽከርካሪ ወንበራቸው ላይ ተነስተው ሲዘሉ አሊያም ምርኩዛቸውን ሲወረውሩ ይታያሉ።

እንዲህ ያሉትን ፈውሶች የሚያከናውኑት ሰዎች በአብዛኛው ሃይማኖታቸው የተለያየ ነው፤ ብዙውን ጊዜም አንዳቸው ሌላውን ከሃዲ፣ ሐሰተኛና አረማዊ እንደሆነ አድርገው ይመለከታሉ። በመሆኑምአምላክ እርስ በርስ በሚቃረኑ ሃይማኖታዊ ድርጅቶች ተጠቅሞ ተአምር ይሠራል?’ የሚል ጥያቄ ይነሳ ይሆናል። ደግሞም መጽሐፍ ቅዱስ፣እግዚአብሔር የሰላም አምላክ እንጂ የሁከት አምላክ አይደለምይላል። (1 ቆሮንቶስ 14:33) ታዲያ እንዲህ ያሉትተአምራዊ ፈውሶችየሚከናወኑት በእርግጥ በአምላክ ኃይል ነው? ፈውስ የሚያከናውኑ አንዳንድ ሰዎች ይህን የሚያደርጉት በኢየሱስ ኃይል እንደሆነ ይናገራሉ። እስቲ ኢየሱስ ሰዎችን እንዴት እንደፈወሰ እንመልከት።

ኢየሱስ ሰዎችን የፈወሰው እንዴት ነበር?

ኢየሱስ በሽተኞችን የፈወሰው በዘመናችን ፈውስ ከሚያከናውኑ ሰዎች ፍጹም በተለየ መንገድ ነበር። ለምሳሌ ያህል፣ ኢየሱስ እርዳታ ፈልገው ወደ እሱ የመጡትን ሕመምተኞች በሙሉ ፈውሷል። ከታመሙ ሰዎች መካከል የተወሰኑትን ፈውሶ የተቀሩትን እንዲሁ አልተዋቸውም። ከዚህም በተጨማሪ ሰዎችን የፈወሰው ሙሉ በሙሉ ከመሆኑም ሌላ ሁልጊዜ ማለት ይቻላል ሰዎቹ ከበሽታቸው የሚድኑት ወዲያውኑ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስኀይል ከእርሱ እየወጣ ሁሉንም ይፈውስ ስለ ነበር፣ ሰዎቹ ሁሉ እርሱን ለመንካት ይፈልጉ ነበርበማለት ይናገራል። ሉቃስ 6:19

አንድ የታመመ ሰው ካልተፈወሰ ይህ የሆነው ግለሰቡ እምነት ስለሌለው እንደሆነ በመናገር ሰበብ ከሚደረድሩት በዘመናችን የሚገኙ ፈዋሾች በተቃራኒ ኢየሱስ በእሱ ላይ እምነት የሌላቸውን አንዳንድ ሰዎችን እንኳ ፈውሷል። ለአብነት ያህል፣ ማየት የተሳነው አንድ ሰው እንዲፈውሰው ባይጠይቀውም ኢየሱስ ግን ፈውሶት ነበር። በኋላም ኢየሱስበሰው ልጅ ታምናለህን?” ሲል ጠየቀው። ሰውየውም መልሶጌታዬ፤ አምንበት ዘንድ እርሱ ማን ነው?” አለው። በዚህ ጊዜ ኢየሱስከአንተ ጋር የሚነጋገረው እርሱ ነውበማለት መለሰለት። ዮሐንስ 9:1-7, 35-38

ኢየሱስ ሰዎችን የሚፈውሰው እምነታቸውን መሠረት አድርጎ ካልሆነ የፈወሳቸውን ሰዎች ብዙውን ጊዜእምነትህ አድኖሃልይላቸው የነበረው ለምንድን ነው?’ ብለህ ትጠይቅ ይሆናል። (ሉቃስ 8:48 17:19 18:42) ኢየሱስ እንዲህ ብሎ ሲናገር እንደሚፈወሱ አምነው ወደ እሱ የመጡት ሰዎች እንደተፈወሱና ይህን ያላደረጉት ግን አጋጣሚውን ሳይጠቀሙበት እንደቀሩ መግለጹ ነበር። ከበሽታቸው የዳኑት ሰዎችም ቢሆኑ የተፈወሱት በእምነታቸው ሳይሆን በአምላክ ኃይል ነው። መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ኢየሱስ ሲናገር እንዲህ ይላል፦እግዚአብሔር . . . በመንፈስ ቅዱስና በኀይል ቀባው፤ እርሱም እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ስለ ነበረ በደረሰበት ሁሉ መልካም እያደረገ በዲያብሎስ ሥልጣን ሥር የነበሩትን ሁሉ ፈወሰ።ሐዋርያት ሥራ 10:38

በዘመናችን፣ ያለ ገንዘብፈውስማግኘት የሚቻል አይመስልም። ፈውስ የሚያከናውኑ ሰዎች ገንዘብ በመሰብሰብ ረገድ የተዋጣላቸው ናቸው። ከእነዚህ ፈዋሾች መካከል አንዱ በዓለም አቀፍ ደረጃ ባከናወነው ሥራ በአንድ ዓመት ውስጥ 850 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ እንዳገኘ ተገልጿል። አብያተ ክርስቲያናትም ፈውስ እንደሚያገኙ ተስፋ በማድረግ ቅዱስ ወደሆኑ ስፍራዎች ከሚመጡ ሃይማኖተኛ ሰዎች ከፍተኛ ትርፍ ያጋብሳሉ። በአንጻሩ ግን ኢየሱስ ከፈወሳቸው ሰዎች ፈጽሞ ገንዘብ አልጠየቀም። እንዲያውም በአንድ ወቅት የፈወሳቸውን ሰዎች መግቧቸው ነበር። (ማቴዎስ 15:30-38) ደቀ መዛሙርቱን ለስብከት ሲልካቸው እንዲህ ብሏቸው ነበር፦በሽተኞችን ፈውሱ፤ ሙታንን አስነሡ፤ ለምጻሞችን አንጹ፤ አጋንንትን አስወጡ፤ በነጻ የተቀበላችሁትንም በነጻ ስጡ።” (ማቴዎስ 10:8) ታዲያ በዘመናችን ፈውስ የሚያከናውኑ ሰዎች የሚያደርጉት ነገር ከኢየሱስ የተለየ የሆነው ለምንድን ነው?

ፈውስየሚያከናውኑት በማን ኃይል ነው?

ባለፉት ዓመታት፣ በሕክምና መስክ የተሰማሩ አንዳንድ ሰዎች በአምላክ ኃይል ፈውስ እንዳከናወኑ የሚናገሩ ሰዎች አደረግን የሚሉት ነገር እውነት መሆኑን ለማረጋገጥ ሞክረዋል። ታዲያ ምን ውጤት አገኙ? በለንደን የሚታተም ዴይሊ ቴሌግራፍ የተባለ ጋዜጣ በዚህ ጉዳይ ላይ 20 ዓመታት ጥናት ያካሄዱ በእንግሊዝ የሚገኙ አንድ ሐኪም የሰጡትን ሐሳብ ጠቅሶ እንደዘገበው ከሆነተአምራዊ ፈውስ እናከናውናለን የሚሉ ሰዎች የሚናገሩት ነገር እውነት መሆኑን የሚያረጋግጥ በሕክምናው መስክ የተገኘ አንድም ማስረጃ የለም።ያም ሆኖ በርካታ ሰዎች እንደ ቅዱስ ተደርገው የሚታዩ ነገሮችን በመጠቀም፣ ቅዱስ ወደሆኑ ቦታዎች በመሄድ ወይም የአምላክ ኃይል እንዳላቸው በሚናገሩ ሰዎች አማካኝነት እንደተፈወሱ በቅንነት ያምናሉ። ታዲያ እነዚህ ሰዎች ተታልለው ይሆን?

ኢየሱስ ዝነኛ በሆነው የተራራ ስብከቱ ላይ፣ አስመሳይ የሆኑ የሃይማኖት ሰዎችጌታ ሆይ፤ ጌታ ሆይ፤ በስምህ . . . ብዙ ታምራት አላደረግንምን?” እንደሚሉት ተናግሯል። እሱ ግን መልሶከቶ አላወቅኋችሁም፤ እናንት ክፉዎች፤ ከእኔ ራቁ!” ይላቸዋል። (ማቴዎስ 7:22, 23) ሐዋርያው ጳውሎስ ተአምር እንደሚፈጽሙ የሚናገሩ ሰዎች ኃይል የሚያገኙት ከማን እንደሆነ ሲገልጽ እንዲህ ብሏል፦የዐመፀኛው አመጣጥ በሰይጣን አሠራር ላይ የተመሠረተ ሲሆን፣ ይህም በሐሰተኛ ታምራት በምልክቶችና በድንቅ ነገሮች ሁሉ ይሆናል፤ እንዲሁም . . . በሚያታልል በተለያየ የክፋት ሥራ ይመጣል።”2 ተሰሎንቄ 2:9, 10

በተጨማሪም እንደ ቅዱስ ተደርገው በሚታዩ ነገሮች፣ በጣዖታትና በምስሎች አማካኝነት የሚከናወኑትፈውሶችበአምላክ ዘንድ ተቀባይነት የላቸውም። እንደዚህ የሚባለው ለምንድን ነው? ምክንያቱም የአምላክ ቃልከጣዖት አምልኮ ሽሹእንዲሁምራሳችሁን ከጣዖቶች ጠብቁየሚል ግልጽ መመሪያ ይሰጣል። (1 ቆሮንቶስ 10:14 1 ዮሐንስ 5:21) እንዲህ ያሉትፈውሶችዲያብሎስ ሰዎችን ከእውነተኛው አምልኮ ለማራቅ ከሚጠቀምባቸው መሠሪ ዘዴዎች መካከል የሚመደቡ ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስሰይጣን ራሱ የብርሃን መልአክ ለመምሰል ራሱን ይለዋውጣልይላል። 2 ቆሮንቶስ 11:14

ኢየሱስና ሐዋርያቱ ሰዎችን የፈወሱት ለምን ነበር?

በክርስቲያን ግሪክኛ ቅዱሳን መጻሕፍት ውስጥ ተመዝግበው የሚገኙ እውነተኛ ተአምራዊ ፈውሶች ኢየሱስና ሐዋርያቱ የአምላክ መልእክተኞች እንደሆኑ በግልጽ የሚያሳዩ ናቸው። (ዮሐንስ 3:2 ዕብራውያን 2:3, 4) ኢየሱስ ያከናወነው ተአምራዊ ፈውስ ሲሰብክ የነበረውን መልእክት የሚደግፍ ነበር፤በምኩራቦቻቸው እያስተማረ፣ የእግዚአብሔርን መንግሥት የምሥራች ቃል እየሰበከ፣ በሕዝቡ መካከል ማንኛውንም ደዌና ሕመም እየፈወሰ በመላው ገሊላ ይዘዋወር ነበር።” (ማቴዎስ 4:23) ኢየሱስ የታመሙትን መፈወስን ብቻ ሳይሆን በርካታ ሰዎችን መመገብን፣ የተፈጥሮ ኃይላትን መቆጣጠርንና ሙታንን ማስነሳትን ጨምሮ ያከናወናቸው ሌሎች ታላላቅ ነገሮች ታዛዥ ለሆኑ የሰው ልጆች በመንግሥቱ አገዛዝ ሥር ምን እንደሚያደርግላቸው የሚያሳዩ ናቸው። በእርግጥም ይህ የምሥራች ነው!

 የሱስ ያከናወናቸው ተአምራዊ ፈውሶች ለእኛ ትልቅ ትርጉም አላቸው። ኢየሱስ ስለ አምላክ መንግሥት ላስተማራቸው ትምህርቶች ትኩረት የምንሰጥና በትምህርቶቹ ላይ እምነት የምናሳድር ከሆነበዚያ ተቀምጦታምሜአለሁየሚል አይኖርምየሚለው በመንፈስ መሪነት የተነገረ ተስፋ በመንፈሳዊም ሆነ በአካላዊ ፍጻሜውን የሚያገኝበትን ጊዜ በጉጉት መጠባበቅ እንችላለን። ኢሳይያስ 33:24 35:5, 6 ራእይ 21:4

0 comments:

Post a Comment