ዶ/ር አመለወርቅ ከተጻፈው
የአአምሮ ጤና
ክፍል 1፡ ስደትና የአዕምሮ ጤንነት
ስደተኛ/መጻተኛ መሆን ጥናታዊነት አለው ለዚህም እንደ አይነተኛ ምሳሌ የሚሆነው ከመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ዘፍጥረት 23፡4, 28፡4,
ኦሪት ዘጽዓት 22፡21,
23፡9, ኦሪት ዘዳግም 10፡18-19, 27፡7 መጽሐፈ ሳሙ. ካልዕ 15፡19,
መዝ. 94፡6 ናቸው።
ከላይ የተጠቀሱት የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ስደተኛ/መጻተኛ መሆን በጥንቱም ህብረተስብ መታወቁንና መኖሩን ያመለክታሉ።
ስለጥንታዊው ስደተኛ/መጻተኛ ስለመሆን ዝርዝር ውስጥ ባልገባም ስደተኛ መሆን በጥንት ጊዜ በኢትዮጵያ የታወቀ ነበር። ምናልባትም ስደቱ ከቦታ ወደቦታ በሃገር ውስጥ እንጂ ከሀገር ውጪ አይደልም ብዬ አስባለሁ። በየትኛውም ዘመን ስደትኛ/መጻተኛ መሆን እየታወቀ የመጣው መንግስታት ሃይላቸውን አጠንከረው ህብረተስቡ ላይ ጫና ያበዙ ጊዜ እንደሆነ የተኛውም ህብረተስብ ምርጫ ስለሌለው ማንኛውም ዕድል ተጠቅሞ የሚኖርበትን ሥፍራ ይለቃል። የትኛውም እውነተኛ ስደተኛ ከሀገር የመውጣቱም ሆነ የመጻተኛነት ኑሮ እንዲመርጥ ያደረገው ከነበረበት ጫና ለመገላገልና የእፎይታ ኑሮ ከተስደደበት ሀገር ለመኖር እንደሆነ ይታወቃል። በኢትዮጵያም ሆነ በአለም ላይ የስደተኛው ቁጥር እየጨመረ የሄደው በኮሚኒስቱ ዘመነ መንግስት እንደሆነ ታሪክ ያስታውስዋል። በዚያን ዘመን በኮሚኒስት አገዛዝ ሥር የነበረው ህብረተስብ ታላቅ ችግር ላይ በድሀነት ወይም በአጦትና በስላም ማጣት ህይወቱን ለማዳን የሚያድርገው እውነተኛ ስደት ነበር በዚያን ዘመን የሚስደደው ስደተኛ የሞትና የሽረት ጉዳይ ስለሆነበት እራሱን ለማዳን ያደረገው ወይም የሚወስደው እርምጃ እንደሆነ ታሪክ መዝግቦታል። በኢትዩጵያና በመሳስሉት ሀገሮች በዚያን ዘመን የመንግሥት የአስተዳደር ጉድለት ብቻ ሳይሆን የተፈጥሮ ችግሮችም እንደድርቅ አይነት በመላው አህጉራት የተከስተበት ወቅት ነበር። ህዝቡ ከችግሩ ለመላቀቅ ይልዳስው ነገር አልነበረም አልበቃ ብሎት ህዝቡ ከሚያውቀውና ከባህሉ የወጣበትና ከእግዚአብሄር ይልቅ ቁሳዊ የአልም ፍልስፍና ለመከተል ጥረት አደረገ ይኽውም በሃገሩ ውስጥ በስፈነው ፍልስፍና የተነሳ እግዚአብሔርን ክዶ የሞራል ውደቀት የደርስበትና በአባገነኑ መንግስት ጨካኝነት መንገዱን ሳተ ይሁን እንጂ ለችግሩ መፍትሄ አላመጣለትም ስለሆነም በሃገሩ ላይ የመኖር ተስፋው የመነመነ ስደተኛ/መጻተኛ መሆንን መረጠ። ስደተኛው ከሞትና ክጭንቀት ለመዳን ቁስሉን ይዞ ስደተኛ ሆኖ በተስደደበት በስሜኑ አሜሪካ በአውሮፓ በተለያዩ ሥፍራዎች ነበር ከተስደደበት ቦታ ሲኖር ሌላ ችግር በስደቱ ሥፍራ በተለይየ መልኩ ይገጥመዋል ለአገሩ እንግዳ ለስው ባዳ ከመሆኑ የተነሳ ሆድ ይብስዋል።
ስደተኛው በሚስደድበት ጊዜ ወደ ተስደደበት ቦታ ከደረስ በኋላ እርፍ ብሎ ሥራ ስርቶ እራሱን ችሎ ልጅ ወልዶ ከብዶ ልመኖርና ጥሪትም አፍርቶ የተስደደበትን ምድር እንደራሱ ህገር አድርጎ ለመኖር ይመጣል ወደተስደደበት ቦታ ከገባ በኋላ የሚጠብቀው ድሮ ከነበረበት ቤተስቡና ህብረተስቡ ባህሉ አኗኗሩ ሁሉ አዲስ ሆኖ ያገኘዋል ከዚህም የተነሳ ሌላ ውጣ ውረድ ውስጥ ይገባል ይህም የተስደደበትን ሀገር ባህል ማጥናት ቋንቋ መማር ከዚም በኋላ ሥራ ስርቶ መኖር ግዴታ ይሆንበታል ይህንን ሁሉ ጥረት ሲያደርግ የሚያልፍበት ጊዜ በየለቱ ኑሮው ጫና ይገጥመዋል ለምሳሌ ሥራ እንደፈለገው ያለማግኘቱ ችግር ካገኘም በኋላ አቀጣጠጠሩ ላይ የሚገጥመው ልዩነት ወይም ደግሞ ለተቀጠረበት ሥራ ብቁ ያለመሆን የመሳስሉት ይገጥሙታል።
ይህንኑ የስደተኛውን ችግር በተመለከተ በካናዳ በኮሚኒቲ ደርጃ ከከፍተኛ የትምህርት ተቅዋም የተደረገው ከተጠናው ጥናትና ከተስበስበው ዳታ በተለይም በ 1980 ዎቹ የተስደዱት ስደተኞች የሥራ ማጣት የልጆች ቡሊያንግ በግዋደኞቻቸው መጠቃት የመሳስሉት ችግሮች ከተስደደበት ህብረተስብ ተዋህዶ የመኖር ችግር እንደገጠመው ያመለክታል። ይህም ሌላው የስደተኛው ችግር ስለሆነ በስሜቱ ወይም በሕይወቱ ላይ የሚያመጣው ሥነልቡናዊ ጫና እንዳለ ያመለከታል ይህም ሥራ ለመፈለግ ወይም እንደህገሩ ነዋሪዎች ጋር ተወዳደሮ ለማሽነፍ ለመሥራት የሚያሽችለውን አቅም ያሳጣዋል ከዚህም የተነሳ ከጥቂቱ በተቀር በመንግሥት እርዳት መኖርን ወይም ኑሮውን ለማሽነፍ አልባሌ ቦታ ገብቶ ለሌላ ችግር እራሱን መስጠትን ይመርጣል ይህም መርጫው የማይስራ ሆኖ ሲያገኘው ወደ በለጠው ጭንቀትና ዲፕሬስን ውስጥ ይገባል።
ከዚህም የተነሳ ይህ ስደተኛ የስሜት ጫና መሽከም የየለቱ ባህሉና አኗኗሩ አድርጎ ይወስደዋል ከዚህም የተነሳ ደስታውን ከርሱ ይረቃል በሥራውም ሥራ ደስተኛ አይሆንም ምናልባትም የስለጠነ ባለሙያ ካለመሆኑ የተነሳ የሚከፈለው ደሞዝ ከእጅ ወደ አፍ ይሆናል ከዚህም የተነሳ በሀገሩ ደርጃ መኖር ያቀተዋል-ያለመደስቱ ምክንያት ከዚህ ይጀምራል። ብቸኝነት ሌላው ችግሩ ስለሚሆን ሚስት ማግባት ስላለበት ያገባል ይህም ሌላ ሃላፊነት ነው ስለሆነም በዚህ ላይ ደግሞ ከሚስቱ ጋር ተሳስቦ ያልኖሩ እንደሆነ ሌላ ችግር ያመጣበታል የተገባቸውም ሴት እንደዚሁ የሚገጥማት ውጣ ውረድ ይኖራል ስለዚህ በስደተኛነት የሚኖረው ኢትዮጵያዊ/ት የሚደርስበት የኑሮ ጫናው ለማቃለል ሲፈልግና ሲጥር መውጫው መንገድ የጠበበው እንደሆነ አጣብቂኝ መሃል የገባ ይመስለውና ከዚህ ማን ያውጣኝ በማለት ለማረፍ በፊቱ ያገኘውን ሁሉ ሲዳሥስ ይገኛል እንዲህም ሆኖ ያልተሳካለት እንደሆነ መጨንቅ ይጀምራል እንግዲህ የጭንቀት መጠን ከስው ስው ይለያያል አንዱ በመጠኑ ሲጨነቅ ሌላው ጭንቀቱ የከፋ ሆኖበት እንቅልፍ ያሳጣዋል ከዚህም ሌላ እንቅልፍ ማጣቱ ሌላው የጭንቀቱ ከባድ ገጽታ ይሆናል። እዚህ ላይ ነው ስደተኛው እራሱን የሚረዳበት ሌላ ዘዴ መፈለግ ይጀምራል ከነዚህም መሃከል የአልኮል መጠጥ አዳንዛዥ እጾችን በመልመድና መጠቀም ችግሩን ለመርሳት አይነተኛ መውጫ መንገድ አድርጎ ይወስደዋል ስለሆነም በየማታው በየቡና ቤቱ መገኘትና መጠጣት ይጀምራል ምናልባትም በዚህ ጊዜ ልጅ ተወልዶ ይሆናል።
ሚስት ከልጅ ጋር ቀንም ማታም ትቆያለች ይህም ይስለቻታል ውጪ አምሽቶ ስለሚመጣ አንድ ቀን ሁለት ቀን ታልፍና እየበዛ ሲሄድ በዚህ የተነሳ ጭቅጭቅ ይጀምራሉ ባልም በስደት ምድር ችግሩን ለማቃለል የመረጠው ምርጫ ወደሌላ ጫና ይመራዋል ከዚህ በኋላ ያለበት ኑሮ ህመሙ የበለጠ እየከበደው ስለመጣ የበለጠ በአልኮል መጠጥ መደንዘዙን ይቀጥላል። ይህ አመሉ እየባሳበት ይሄድና በስካሩ ማግስት ወደሥራ መሄድ ያቀተውና ከሥራ ይቀራል ሥራው ብዙ ውድድር ያለበት ስለሆነ አለቃው ላንድ ቀን ይፈቅድለታል ስደተኛው ግን የመጠጥ አመሉ እየባስ ለሄድ መቅረቱን እየደጋገመ ስለሆነ ይህም ስው ከሥራ መውጣቱ የማይቀር ነው። ከዚህ በኋላ ደግሞ በመጠጥ መዳንዘዝ ስላልቻለ ያለበት ኑሮ ስለተስማው ሌላ ማደንዘዣ ይፈልጋል ይህም ማደንዘዣ እጽ ሆኖ ይገኘዋል በስደት አለም የስሜት ጫናቸውን ለማቃለል ወደማይፈልጉት አመል የሚገቡት ወንዶች ብቻ ሳይሆኑ ሴቶችም ናቸው።
ክፍል 2፡ የአአምሮ ጤንነትና ሕመም (መጓደል)
የአአምሮ ጤንነት ስንል የሃሳብ የስሜትና የባህሪ ጤንነት ማለታችን ነው። የማስብ (thinking) ጤንነት የማመዛዘን የማቀደን የማስላስልን የመረዳትን ሊከስት የሚችልን አደጋም ሆነ መልካም ነገር መገመትን ተለዋዋጭ ከሆነ ነባራዊ ሁኔታ ጋር ራስን አስተካክሎ መኖርን ነገሮች ከአወንታ ጋር ያላቸውን ግንኙነት ለይትቶ ማስተዋልንና የመሳስሉትን ያጠቃልላል። የስሜት (emotion, feeling) ጤንነት ሚዛኑን በጠበቀ መልኩ ድስታን ሃዘንን ብስጭትን ቁጣን ፍርሃትን ድፍረተን ወዘተ ማስተናገድ መቻልን ያመለክታል።
የባህሪ (behavior) ጤንነት በድርጊት የሚፈጸሙ ማንኛውንም አይነት ተግባራት የራስንና የሌሎችን ሕይወት በሚጠቅም ወይም በማይጎዳ መልክ ማከናወን መቻልን ያጠቃልላል። ባህሪ ማለት ሃስብና ስሜት በድርጊት ሲገለጥ ማለት ነው። የሃስብና ስሜት የማይዳስ ሱና (የማይጨበጡ) የማይታዩ የረቀቁና የጠለቁ የስው ማንነት ክፍል ሲሆኑ ለሌላው በሚታወቅ መልክ የሚገለጡት በባህሪ አማካኝነት ነው። ለምሳሌ አንድ ስው ምን አይነት የሃስብ ይዘት እንዳለውና ወድ አንድ ግብ የሚያደርስ ትክክለኛ ሃስብ በቅደም ተከተል እያስበ መሆኑን የሚታወቅበት አንደኛው መንገድ በንግግሩ ነው ንግግር ከስው ልጅ ባህሪዎች አንዱ ነው። የአንድ ስው ሃስብ የሚመነጨው ከሚያየው ከሚስማውና ከተማረው ከተለማመደው ከሚያጋጥመው ወዘተ ጋር በተያያዘ ሁኔታ ነው።
በየቀኑ የሚያጋጥሙ ክስተቶች ግንኙነቶች የምንፈጽማቸው ድርጊቶች በአአምሮ ውስጥ ሃሳብ ይጭራሉ ሃስብ ደግሞ ተብላልቶና ተደማምሮ ለሁኔታዎች ምላሽ በመስጠት ወደ ድርጊት ይቀየራል። የሃስብ ይዘትና (content) ሂደት (process) አለው። ይዘት የሚባለው የሚታስበው እርዕስ ጉዳይ ማለት ነው። የአንድን ስው ሃሳብ ይዘት ስውዬው ያለበት የኑሮና የትምህርት ደረጃ የአካባቢው ባህልና እምነት ይወስነዋል ስለሆነም በነዚህ ነገሮች ተመሳሳይነት ያላቸው ስዎች የሃሳብ ይዘት( አስተሳስብ) ተመሳሳይነት አለው እንዲኖረውም ይጠበቃል። ይህ ካልሆነ በአንድ አካባቢ ባለ ህብረተስብ ጋር ተግባብቶና ተረጋግቶ መኖር አስቸጋሪ ይሆናል። ስለሆንም የአንድ ስው የሃስብ ይዘት (አስተሳስብ) ለስው ልጅ አጂግ አስፈላጊ ክፍሉ እንደሆነ ያመለክታል።
በእርግጥ አንዳንድ ጊዜ ከአካባቢው ማህበረስብ ወጣ ያሉ አስተሳስቦች ጠቃሚነት ሊኖራቸው ይችላል። አዳዲስ ግኝት ያስገኙ ለስው ልጅ እድገት ትልቅ እገዛ ያደረጉ አስተሳስቦች በሳይንቲስቶች በማህበራዊ ኑሮ ሊቃውንት በኩል በመከስታቸው ጠቃሚ ውጤቶች ታይተውባቸዋል። ስለዚህ ለጤናማ ኑሮና ሕይወት ከማህበረስብ ጋር ተመሳሳይ የሃሳብ ይዘት መኖሩ በጣም አስፈላጊ መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ ሁሉም ሁልጊዜም ጠቃሚ ነው ባይባልም አንዳንድ ጊዜ ወጣ ያሉ አዳዲስ ሃስቦችም ጠቃሚ የሚሆኑበት ጊዜ አለ ማለት ነው። ሆኖም እንደዚህ የወጣ አስተሳስብ ያላቸው ስዎች ጤንነታቸው በማህበራዊና በግል የኑሮ ሁኔታዎች እንዲሁም ባህሪዎች መመዘን ይኖርበታል።
የሃስብ ሂደት አንዱን ሃስብ ከሌላው ጋር ወጤት ያለው ወይም ወደ አንድ ግብ የሚያደርስ ቅንብር (logical connection) እንዲኖረው አድርጎ ማያያዝ ማለት ነው። ሃሳብን በትክክል ማቀናበር ውጤት ለስው ተግባር የሚያንደረድር ሂደት ነው ምንም አይነት ተግባር ለመፈጽም ቅደም ተከተሉና ስልቱ ተስርቶ የሚያልቀው በአአምሮ ውስጥ ነው ይህም የሃሳብ ሂደት ጤንነትን ነው። ከሃሳብ ጋር የጠበቀ ግንኙነት ያለው አአምሮ ጤንነት ወይም የአአምሮ ክፍል ደግሞ ስሜት ነው። የሚያሳዝን ሁኔታ ባለ ጊዜ ማዘን የሚያስደስት ሁኔታ ሲከስት መደስት መፍራት በሚያስፈልግ ጊዜ መፍራት መቆጣት በሚያፈልግበት ጊዜ መቆጣት እነዚህንም ስሜቶች በሚዛን ጠብቆ ለማስኬድ አቅም ማግኘት የአአምሮ ጤንነት አንዱ ክፍል ነው። አንድን ነገር ለማከናውን ፍላጎት ወይም ተነሳሽኒትም መኖር የአአምሮ ጤንነት ይሳያል።
የሃስብና የስሜት አግባብ የሆነ ቅንብር በግፊት (ፍላጎት) አማካኝነት ወደ ተጨባጭ ተግባር ሲለወጥባህሪ ይባላል። ይህም ንግግር በጽሑፍና በልዩ ልዩ ተግባራት ይገለጣል። አገላለጹም በአሉታዊና በአወንታዊ መልክ ሊሆን ይችላል። ባህሪ የሚታይና የሚስማ የሚዳስስ ተጨባጭ ድርጊት በመሆኑ የሃሳብና የስሜት ጤንነትና ሕመም የሚገለጠው በአብዛኛው በባህሪ አማካኝነት ነው። ባህሪ በማድረግ ወይም በድርጊት ብቻ ሳይሆን ባለማድረግም ይገለጣል። ለምሳሌ መናገር አንድ ባህሪ ሲሆን ዝምታም ሌላው ባህሪ ነው። ወደ መሥሪያ ቤት መሄድ አንድ ባህሪ ሲሆን አለመሄድ ሌላው ባህሪ ነው። ማድረግና አለማድረግ በተፈራራቂ መልክ አሉታዊና በአወንዊታ ባህሪያት ሊሆኑ ይችላሉ። ለምሳሌ ምግብ መብላት አዎንታዊ ባህሪ ሲሆን ምግብ አለመብላት ደግሞ አሉታዊ ነው። በአንጻሩ ሲጋር ማጤስ አሉታዊ ባህሪ ነው አለማጨስ ወይም ማጤስን ማቆም ደግሞ አዎንታዊ ባህሪ ነው።ስለዚህ መደረግ ያለበትን ነገር ማድረግ አዎንታዊ እንደሆነ ሁሉ መደረግ የሌለበትን ነገር ማድረግ አሉታዊ ይሆናል። መደረግ ያለበትንና የሌለበትን ነገር የሚወስኑት የተፈጥሮ ሞራልና የባህል ግዴታዎች ናቸው። ለምሳሌ መብላት የተፈጥሮ ግዴታ ነው በሌላው ስው ላይ ክፉ ነገር አለማድረግ ወይም ሌላውን ስው መርዳት የሞራል ግዴታ ሲሆን የተወስነ አለባበስን መከተል የባህል ግዴታ ነው። ስናጠቃልለው የሃስብ የስሜትና የባህሪ ቅንብሮች ውጤታማነትን የአአምሮ ጤንነት ልንለው እንችላለን።
የአአምሮ ሕመምን ደግሞ ለመረዳት በምንሞክርበት ጊዜ የሃስብ የስሜትና የባህሪ መዛባት እንደሆነ እንገነዘባለን። የአአምሮ ሕመምን በተሻለ መንገድ ለመረዳት በሃስብ ይዘትና ሂደት በስሜት እንዲሁም በባህሪ ላይ የሚታዩ ለውጦችን ከፋፍሎ ማየት መልካም ይሆናል። የሃሳብ ይዘትን ችግር የምንመለከተው የአንድ ስው አስተሳስብ (ሃሳብ) ከተጨባጭ እወንታ ጋር ባለው ግንኙነት ይሆናል። ይህም ማለት አንድ ስው እውነት ነው ብሎ የያዘው አአምሮውን የሞላው ሃስብ ወይም እምነት በእድሜ በሃይማኖት በባህልና በትምህርት ደረጃ ተመሳሳይነት ያላቸው ስዎች የማይጋሩት ከተጨባጭ ሁኔታ ጋር ግንኙነት የሌለው በዚያ ስው ብቻ በጽናት የሚታመን የተያዘው እምነት ውሽት መሆኑን የሚያስረዳ በቂ መረጃ ቢቀርብም ለመለወጥ የማይቻል ሲሆን ያ
ስው የሃሳብ ይዘት ችግር (delusion) አለበት ይባላል። እንደዚህ አይነት ችግር የገጠማቸው ስዎች ሌላው ስው ሊያየው ወይም ሊጋራው ወደማይችል የተለየ የተዛባና የራሳቸው የሆነ አወንታ ውስጥ ገብተዋል ማለት ነው። ለምሳሌ አንድ የሀገራችን ገበሬ በአካባቢው ቀበሌ ውጪ ሊያሳውቀው የሚችል ድርጊት ፈጽሞ የማያውቅ ሆኖ ሳለ የአለም መሪዎች እኔን ለመግደል ተስማምተዋል ብሎ ቢያምን የሃሳብ ይዘት ችግር አለበት ብሎ መገመት ይቻላል። ሌላው ደግሞ በአለም ውስጥ ለሚመጣው የተፈጥሮ አደጋ ሁሉ ተጠያቂ እኔ ነኝ ብሎ ቢያምን ይህንንም እንደመጀመሪያው ማስብ ይችላል። የሃስብ ሂደት ችግር ቀደም ተብሎ እንደተገለጠው ሃሳብን ማቀናበር ያለመቻል የተለያዩ ወደ አንድ ግብ በቅደም ተከተል መደርደር ፍስት እንዲኖራቸው የማድረግ ችግር ነው። ይህም ከይዘት ችግር ጋር የተገናኘ ሊሆን ይችላል። በዚህ አይነት ችግር ውስጥ ያሉ ስዎች ውጤት ያለው ተግባር ለማከናወን ይቸገራሉ ምክንያቱም ነገሮች ሁሉ ወደተግባር ከመቀየራቸው በፊት በአአምሮ ውስጥ መሳል አለባቸው። ቅደም ተከተላቸው ግልጽ መሆን አለበት። አንድ ስው ይህን ማድረግ ከቃጣው ሃሳቦች ሳይገናኙ ፈንጠር ፈንጠር ብለው እንደተቀመጡ የስንስለት ቀለበቶች ናቸው ማለት ይቻል። የስንስለት ቀለበቶች በአንድ ላይ ካልተያያዙ ወጤት ያለው ሥራ ሊስሩ አይችሉም። የሃሳብ ይዘትና ሂደት (ፍስት?) ችግሮች የአአምሮ ሕመም በሌላቸው ስዎችም በተለያዩ አይነት ሁኔታዎች ውስጥ ሲያልፉ በጊዚያዊነት ሊከስቱ ይችላሉ። ነገር ግን ሁኔታዎች ሲለወጡ ወይም ይዘቱን የሚያፈርስ ማስረጃ ሲቀርብላቸው የመለወጥ ባህሪ አላቸው ለምሳሌ በአንድ መስሪያ ቤት ውስጥ ሃላፊው አንድ ቀን ሰራተኞችን በአስቸኳይ ቢሮዬ ድረስ እንድትመጡ ብሎ ጠርቶ ከሥራ የማስናበቻ ደብዳቤ ስጥቶ ባስናበታቸው በሳምንቱ በተመሳሳይ ክፍል የሚስራውን ሌላ ስው እድገት ሲስጠው በአስቸኳይ ተፈለጋለህ ብሎ ቢያስጠራው ከሥራ እንደሚስናበት እርግጠኛ ሆኖ የግል እቃውን ሁሉ በቦርሳው ከቶ የቅርብ የሥራ ባልደረቦቹን ተስናብቶ በፍርሃት ወደሃላፊው ቢሮ ሲሄድ የእድገት ደብዳቤ ቢጠብቀው የነበረው የሃሳብ ይዘት ይቀየራል። በተመሳሳይ መልኩ ዝግጂት ያላደረገበት ድንገተኛ ወይም አስደንጋጭ ወይም መፈናፈኛ የሚያሳጣ አጣብቂኝ ውስጥ ስንገባ የሃሳብ ፍስታችን ወይም ሂደታችን ሊዘበራረቅ ወይም ለቅጽበት ሊቆም ይችላል ነገር ግን ሁኔታው ሲያልፍ ወደመስመር እንገባለን። ወደ ስሜት የጤና መጓደል ስንመጣ ይህም በልዩ ልዩ አይነት መልክ ሊገለጥ ይችላል። ለምሳሌ በቂ ምክንያት በሌለበት ከልክ ያልፈ ሃዘን ወይም የድባቴ ስሜት (depression) የደስታ ወይም የሽቅለት (manic) ስሜት የፍርሃት (fear) ስሜት የጭንቀት (anxiety) ስሜት ትዕግስት የማጣት ወይም በቀላሉ የመቆጣት የመነጫነጭ (irritability) ስሜት ወዘተ ሊሆን ይችላል። ከዚህም በተጨማሪ የስሜት ድንዛዜ ወይም በሚያሳዝን ሁኔታ የሃዘን በሚያስደስት ሁኔታ የደስታ ስሜት አለመኖር የስሜት የጤና ክፍሉ መዛባቱን ያመለክታሉ። በሚያስቅ ነገር ማልቀስ ወይም በሚስለቅስ ነገር ነገር መሳቅ ሃስብና ስሜት የማይታዩና የማይዳስሱ (abstracts) እንደሆኑ ሁሉ የሃሳብና የስሜት መዛባቶችም እንዲሁ ናቸው። የነርሱ መዛባት በአብዛኛው የሚገለጠው በውጫዊ ባህሪ ነው የአአምሮ ሕመም የሚገለጥባቸው መንገዶች በንግግር በአለባበስ በራስ እንክብካቤ በማህበራዊ ግንኙነቶች በሥራ ውጤታማነትና በመሳስሉት ነው። ለምሳሌ ቀደም ተብሎ የተጠቀስው የሀገራችን ገበሬ የአለም መሪዎች ያሴሩብኛል ብሎ በማመን ከቤት አለመውጣቱን ከላይ በተዘረዘሩት ባህሪዎች ስንቃኘው በአንዱ ወይም በሁለቱ ውስጥ እናገኘዋለን። ይህም ማለት ከቤት ባለመውጣቱ የማህበራዊ ግንኙነቱን ይጎዳል በሌላ በኩል ደግሞ ስርቶ ማግኘት ያለበትን ውጤት ሊያገኝ አያስችለውም። የሃስብና የስሜት መረበሽ ማንኛውም ስው በተለያየ ሁኔታ ውስጥ ሲያልፍ በመጠኑም የሚያጋጥመው ጉዳይ ነው። ነገር ግን የአአምሮ ሕመም ነው የሚባለው ለረዢም ጊዜ ሲቆይና በስውዬው ሕይወት ላይ አሉታዊ ለውጦች ሲያመጣበት ነው። ስለዚህ አንድ ስው የአአምሮ ሕመም አለበት የሚያስኘው ግለስቡ በውስጡ የሚስማው መረበሽ መደናገር መጨነቅ መጠበብ ወይም የውስጥ ስቃይ (psychic pain) ነው። የአአምሮ ሕመም ዋናው ችግር ከላይ እንደተጠቀስው እንደማንኛውም የሕመም ስሜት የማይታይና የማይዳስስ አሉታዊ ስሜት ነው። ነገር ግን በሌላው ስው ዘንድ የሚታወቀው ችግር ባለበት ስው በንግግር ወይም በሌላ መንገድ ሲገለጽ ነው። አብዛኛው የአአምሮ ሕመም ስሜት ሕመምተኛው ራሱ ገልጦ ለሌላው ለማስረዳት የሚችለው ሲሆን አንዳንዱ የአአምሮ ሕመም ግን ስውዬው የመታመሙን ግንዛቤና እርዳታ የመፈለጉን አቅም ስለሚያጠፋበት ሕመምተኛው ለሌላው ስው ችግሩን ለማካፈልም ሆነ እርዳታ ለመጠየቅ አይገፋፋም። በሌሎች የሚስጠውንም ምክር ወይም እርዳታ ለመቀበል አያስችለውም። በሀገራችን ወይም በብዙ ስዎች ዘንድ የአአምሮ ሕመም ተብሎ የሚጠራው በአብዛኛው እነደዚህ አይነቱ ነው። ነገር ግን ይህ አይነቱ የአአምሮ ሕመም በአንጻራዊ መልኩ ሲታይ ብዙ የማይከስት ነገር ሲከስት ትኩረትን በሚስብ መልኩ የሚመጣ ስለሆነ በሁሉም ስው ዘንድ እንዲታወቅ አድርጎታል እንጂ በብዙ ስው ላይ የሚከስቱ ከቀላል እስከ ከባድ የአአምሮ ሕመም አይነቶች ብዙ ናቸው። ይህ መጽሐፍ የተዘጋጀበት ዋናው አላማ በገራችን በማህበረስብ ጠቅለል ያለ ግንዛቤ ለመስጠት ስለሆነ ስለ እያንዳንዱ የሕመም አይነት ዝርዝር ማብራሪያ አይገባም። የአአምሮ ሕመም የውስጥና ስውር የሆነ ሕመም ቢሆንም በግለስቡ ላይ በሚከስቱት የባህሪያት ለውጦች አማካኝነት አንድ ስው መታመሙንና አለመታመሙን እንዲሁም ምን አይነት ህመም እደታመመ የሚጠቁሙ ምልክቶች አሉ ወደ ምልክቶቹ በዝርዝር ሳይገባ ጠቅለል ባለ መልኩ ሊዳስሱ የሚገባቸው የባህሪ ለውጦች አሉ እነርሱም
1. በግል እንክብካቤ ዙሪያ
2.በማህበራዊ ሕይወት ዙሪያ
3. በሥራ ውጤታማነት ዙሪያ
4. በንግግርና በልዩ ልዩ ባህሪያት ዙሪያ
በግል እንክብካቤ ዙሪያ መታየት የሚገባቸው የባህሪ ለውጦች የልብስ የገላና የጸጉር ወዘተ ንጽህና የቤትና የእቃ አያያዝ የአመጋገብና የእንቅልፍና የመሳስሉት ሁኔታዎች ናቸው።
በማህበራዊ ሕይወት (ኑሮ) ዙሪያ በቤተስብና በማህበረስብ ውስጥ ባሉ ግንኙነቶች የመጡ ለውጦችን ማየት ማለት ነው። በቤተስብ ጋር ባለ ግንኙነት ላይ ለውጦችን በቅርብ ማየት ጠቃሚ ይሆናል ከዚያም በተጨማሪ ከጓደኞች ከሥራ ባልደረቦች ከጎረቤት ከሌሎችም ማህበራዊ ግንኙነቶች አኳያ ያለውን ለውጥ መመልከት ጠቃሚ ይሆናል። አንዳንድ ስው የአአምሮ ሕመም በሚከስትበት ጊዜ ራሱን ያገላል ወይም ስው አይለየኝ ይላል ወይም ቁጡ ይሆናል ወይም በሌላው ስው ጉዳይ ላይ ያለአግባብ ለመግባት ይሞክራል ወይም ሌላውን ስው ያላግባብ ይከሳል ይፈራል።
ስለሥራ ውጤታማነት ስንመለከት ቀደም ሲል የተመስገነ ውጤታማ የነበረ ስው በሕመሙ ምክንያት የነበረውን ያህል ምርታማ አይሆንም በጊዜ ስርቶ አይጨርስም ከሥራ ይቀራል አርፍዶ ይገባል ማስጠንቀቂያ ሊደርስውም ይችላል። በንግግሩ ደግሞ ዝም ማለት ወይም ብዙ መናገር ሌላው ስው ሊረዳው በማይቻለው ፍጥነትና የማይገናኙ ሃሳቦችን አገናኝቶ መናገር የሚናገሩት ማጣትና የመሳስሉት ሊከስቱ ይችላሉ። አንዳንድ ጊዜ ደግሞ ህብረተስቡ የማይጠብቀው አይነት ወይም ቀድሞ ያልነበሩ የተለያዩ ባህሪዎችን ማሳየት ይሆናል።
“በሁሉም የዓለም ክፍል የሚኖሩ በብዙ መቶ ሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች በአእምሮ ሕመም ይሠቃያሉ፤ እንዲሁም ችግሩ በቤተሰቦቻቸውና በወዳጆቻቸው ሕይወት ላይ ጫና ይፈጥራል። ከአራት ሰዎች መካከል አንዱ በሕይወቱ ውስጥ በሆነ ወቅት ላይ የአእምሮ ሕመም ያጋጥመዋል። ለዚህ ዓለም አቀፍ ችግር ዋነኛው መንስኤ የመንፈስ ጭንቀት ነው። በጣም ከባድ ከሆኑትና በሰዎች ላይ ተጽዕኖ ከሚያሳድሩት የአእምሮ ሕመሞች መካከል ስኪትሰፍሪኒያ እና ባይፖላር ዲስኦርደር ይገኙበታል።
በጣም ብዙ ሰዎች በአእምሮ ሕመም የሚጠቁ ቢሆንም ችግሩ አሁንም በድብቅ የሚያዝ ከመሆኑም ሌላ ችላ ይባላል፤ በተጨማሪም እንዲህ ዓይነት በሽታ ያለባቸው ሰዎች መድሎ ይፈጸምባቸዋል።”የዓለም የጤና ድርጅት
የዓለም የጤና ድርጅት እንደገለጸው በአእምሮ ሕመም የተያዙ ብዙ ሰዎች ከኅብረተሰቡ መገለል ስለሚያስፈራቸው ሕክምና ከማግኘት ወደኋላ ይላሉ።
አብዛኞቹ የአእምሮ ሕመሞች በሕክምና መዳን ይችላሉ፤ ያም ቢሆን በዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ባለፈው ዓመት ብቻ የአእምሮ ሕመም ያለባቸው 60 በመቶ ገደማ የሚሆኑ አዋቂዎችና 50 በመቶ የሚሆኑ ከ8 እስከ 15 ባለው የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ወጣቶች ሕክምና እንዳላገኙ በአእምሮ ሕመም ለተያዙ ሰዎች እርዳታ የሚሰጥ አንድ ተቋም ዘግቧል።
በአሁኑ ዘመን በአለም ላይ በጣም ጉልቶ የሚታየው የስው ልጆች ጭንቀትና መታረዝ ጦርነት በተለያየ በሽታዎች መጠቃት ከዚያም ባለፈ ከብዙ ውጣ ውረድና ጭንቀት የተነሳ ለተለያዩ የጤና እክሎችና ብሎም ለአእምሮ ህመም መጋለጥ በስው ልጆች ላይ እንደተከስተ በግልጥ የሚታ የሚታይ ነገር ነው። ታዲያ በዚህ አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ለሚያልፉት ግለስቦችና ቤተስቦች ቤተክርስቲያን የምታደርገው እርዳታ ይኖር ይሆን?
መቼም በአሁኑ ዘመን ከመቼውም ይልቅ አለም በተለያዩ ቸግሮች በውጥረት የተያዘበት ቢሆንም በአለም ያሉ የጤና ደርጅቶች በተቻላቸው መጠን የሚያደርጉት ህክምና እንዳለ በግልጽ ይስተዋላል ይህም ሆኖ ችግሩ በጉዳቱ ከተጠቂት ግለስቦች ላይ ሲቀርፍ አልታየም ችግሩ ምን ይሆን? ይህ ችግር ከጊዜ ወደጊዜ እየጎላና እየተስፋፋ በመሄዱ መፍተሄ አምጪዎቹ የህክምና ተቅዋማት ብቻ ስይሆኑ የሃይማኖት ድርጂቶች በተለይም የክርስቲያን እምነት ተከታዮች በዚህ ጉዳይ ላይ ችግሩን ለመቅረፍ መረባርብ አለባቸው ብዬ አስባለሁ። በዚሁ በሽታ ለተጠቁት ሁሉ እርዳታ ለማበርከት የአዕምሮ ህመም መኖሩን የሚጠቁሙ አንዳንድ ማስጠንቀቂያ ምልክቶችን ማወቅ ይረዳል። እነዚህም በበሽተኛው ላይ የሚታዩት የሚከተሉት ምልክቶች በተለያዩ የአእምሮ ጤንነት ተቋም የተጠኑና የተረጋገጡ በህክምና ጽሑፍ ላይ የተጠቀሱ ናቸው:
የአእምሮ ሕመም መኖሩን የሚጠቁሙ አንዳንድ የማስጠንቀቂያ ምልክቶች የሚደርግላቸው እርዳታ
የቤተሰብ አባል ወይም በቅርብ የምታውቀው ሰው የሚከተሉት ምልክቶች የሚታዩበት ከሆነ ሐኪም ወይም የአእምሮ ጤና ባለሙያ ማማከር ሊያስፈልገው ይችላል:-
• ለረጅም ጊዜ የሚዘልቅ ሐዘን ወይም ብስጭት
• ተደጋጋሚ የሆነ ቅዠት
• አጥርቶ ማሰብ አለመቻል
• ከእውነታው የራቀ አስተሳሰብ ወይም የቁም ቅዠት
• ስለሞት ወይም የራስን ሕይወት ስለማጥፋት ማሰብ
• ችግሮችን መቋቋምና የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴዎችን በሚገባ ማከናወን አለመቻል
• በግልጽ የሚታዩ ችግሮችን አምኖ አለመቀበል
• ራስን ከሌሎች ማግለል
• ጎልቶ የሚታይ የስሜት መለዋወጥ
• ከልክ ያለፈ ቁጣ
• ግልፍተኛ መሆን
• ሱስ የሚያስይዙ ንጥረ ነገሮችን አላግባብ መጠቀም
• ከልክ ያለፈ ፍርሃትና ጭንቀት
• ክብደት እጨምራለሁ የሚል ከፍተኛ ስጋት
• በአመጋገብ ወይም በእንቅልፍ ልማድ ላይ የሚታይ ከፍተኛ ለውጥ
• መንስኤያቸው የማይታወቅ በርካታ አካላዊ ሕመሞች
የምትናገረው ነገር ምንም ውጤት እንደማያመጣ ሆኖ ሲሰማህ ዝም ብለህ ሕመምተኛውን አዳምጠው
በጭንቀት ምክንያት የሚመጣ የስሜት ቀውስ ያለባቸውን ሰዎች መርዳት
“ብዙውን ጊዜ ልቤ በኃይል ይመታል፣ ላብ ያጠምቀኛል እንዲሁም ትንፋሽ ያጥረኛል። በፍርሃትና በስጋት ስሜት እዋጣለሁ፤ አእምሮዬም ይረበሻል።”፣
በ40ዎቹ ዕድሜ የምትገኝና ከመጠን ባለፈ የፍርሃት ስሜት* የምትሠቃይ ጭንቀት “የፍርሃት ወይም የስጋት ስሜት” ተብሎ ሊገለጽ ይችላል። ለምሳሌ ኃይለኛ ውሻ ሲመጣብህ ፍርሃት ተሰምቶህ ያውቃል? ውሻው ትቶህ ቢሄድስ? ፍርሃቱና ስጋቱ እንደሚለቅህ ግልጽ ነው። ይሁንና ጭንቀት የጤና እክል የሚሆነው መቼ ነው?
አንድ ሰው እንዲፈራ ያደረገው ነገር ከተወገደም በኋላ ስጋት የሚሰማውና በጣም የሚረበሽ ከሆነ ግለሰቡ በጭንቀት ምክንያት የሚመጣ የስሜት ቀውስ (አንግዛይቲ ዲስኦርደር) አለበት ማለት ነው። የዩናይትድ ስቴትስ ብሔራዊየአእምሮ ጤንነት ተቋም እንደሚገልጸው ከሆነ “በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ . . . ዕድሜያቸው 18 ዓመትና ከዚያም በላይ የሆኑ 40 ሚሊዮን አሜሪካውያን በጭንቀት ምክንያት በሚመጣ የስሜት ቀውስ ይታወካሉ።” በካናዳም እንደዚሁ።
ፋታ የማይሰጥ የጭንቀት ስሜት ከባድ ችግር ሊያስከትል ይችላል።
ይህ ችግር በግለሰቡ ላይ ብቻ ሳይሆን በቤተሰቡ አባላት ላይም ጫና ሊያሳድር ይችላል። ይሁንና እንዲህ ያሉት ሰዎች ምንም ተስፋ የላቸውም ማለት አይደለም። የዩናይትድ ስቴትስ ብሔራዊ የአእምሮ ጤንነት ተቋም ያሳተመው አንድ ጽሑፍ እንዲህ ይላል፦ “በጭንቀት ምክንያት የሚመጣ የስሜት ቀውስን ለመቋቋም የሚረዱ ውጤታማ የሆኑ ሕክምናዎች አሉ፤ ሳይንሳዊ ምርምሮች እንዲህ ዓይነት ችግር ያላቸው ሰዎች በሥራቸው ውጤታማ እንዲሆኑና እርካታ የሚያስገኝ ሕይወት እንዲመሩ የሚያግዟቸውን አዳዲስ ሕክምናዎች እያስገኙ ነው።”
የቤተሰብ አባላትና ጓደኞችም እንዲህ ዓይነት ችግር ያለባቸውን ሰዎች ክርስቲያኖች መርዳት ይችላሉ። እንዴት?
እርዳታ መስጠት የሚቻልበት መንገድ
ደግፏቸው፦ ያለ ምክንያት ከልክ በላይ የመጨነቅ ችግር ያለባትና ከአሰቃቂ ገጠመኝ በኋላ በሚከሰት ጭንቀት የምትሠቃየው አንዲት ልጅ “አብዛኞቹ ሰዎች ያሉብኝን ስሜታዊ ችግሮች መረዳት አዳጋች ይሆንባቸዋል” በማለት የሚያጋጥማትን አስቸጋሪ ሁኔታ ገልጻለች። በዚህም የተነሳ በጭንቀት ምክንያት በሚመጣ የስሜት ቀውስ የሚሠቃዩ ሰዎች፣ ሌሎች በተሳሳተ መንገድ እንዳይረዷቸው ስለሚሰጉ ችግራቸውን ለመደበቅ ይሞክራሉ። ይህ ደግሞ የጥፋተኝነት ስሜት እንዲያድርባቸው በማድረግ ችግሩን ያባብሰዋል። ስለዚህ ከቤተሰባቸው አባላትና ከጓደኞቻቸው ድጋፍ ማግኘታቸው በእጅጉ አስፈላጊ ነው።
ስለ ችግሩ ያላችሁን ግንዛቤ አሳድጉ፦ በተለይ ከላይ የተገለጸው ዓይነት የስሜት ቀውስ ያለባቸውን ሰዎች የሚቀርቧቸው ግለሰቦች ስለ ጉዳዩ ግንዛቤያቸውን ማስፋታቸው ተገቢ ነው። ይህም የቤተሰባቸውን አባላትና የቅርብ ጓደኞቻቸውን ይጨምራል።
እርስ በርሳችሁ መጽናናታችሁን ቀጥሉ፦ በመጀመሪያው መቶ ዘመን የነበረው ቅዱስ ጳውሎስ የተባለ ሚስዮናዊ በግሪክ በምትገኘው በተሰሎንቄ የነበሩ ወዳጆቹን “እርስ በርሳችሁ መጽናናታችሁንና እርስ በርስ መተናነጻችሁን ቀጥሉ” በማለት መክሯቸዋል። (1 ተሰሎንቄ 5:11) ይህንን ማድረግ የምንችለው በምንናገራቸው ቃላት ብቻ ሳይሆን በድምፃችን ቃናም ጭምር ነው። ለወዳጆቻችን በጥልቅ እንደምናስብ ማሳየት የሚያስፈልገን ሲሆን ስሜት የሚጎዳና ጥፋተኛ እንደሆኑ እንዲሰማቸው የሚያደርግ አስተያየት ከመሰንዘር መቆጠብ ያስፈልገናል።
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጠቀሰውን ኢዮብን ለማጽናናት የመጡትን ሦስት ወዳጆቹን እንደ ምሳሌ እንውሰድ። ታሪኩ እንደሚገልጸው እነዚህ ወዳጅ ተብዬዎች፣ ኢዮብ በድብቅ የሠራቸውን ኃጢአቶች እንደሸፋፈነና የደረሰበት መከራ መንስኤም ይኸው እንደሆነ በመናገር በስህተት ወነጀሉት።
ስለዚህ እናንተም የግለሰቡን ስሜት ለመረዳት ሞክሩ። ሲናገር በጥሞና አዳምጡት። ራሳችሁን በግለሰቡ ቦታ ለማስቀመጥ ሞክሩ። የሚናገረውን ነገር ሳይጨርስ ቸኩላችሁ ያልሆነ መደምደሚያ ላይ ከመድረስ ተቆጠቡ። የኢዮብ ወዳጅ ነን ብለው የመጡት ሰዎች እንዲህ በማድረጋቸው ኢዮብ “የምታስጨንቁ አጽናኞች ናችሁ” ብሏቸዋል። እነዚህ ሰዎች ኢዮብን ከማጽናናት ይልቅ ይባስ መጥፎ ስሜት እንዲሰማው አድርገውታል! ኢዮብ 16:2
እንግዲያው እንዲህ ያለ ችግር ያለባቸውን ሰዎች በጥሞና ማዳመጥ እንዳለባችሁ አትዘንጉ። የልባቸውን አውጥተው እንዲናገሩ ዕድል ስጧቸው። ይህም ስሜታቸውን በተሻለ ሁኔታ ለመረዳት ያስችላችኋል። ደግሞም እንዲህ ማድረግ የሚያስገኘውን ጥቅም አስቡ! በጭንቀት ምክንያት የሚመጣ የስሜት ቀውስ ያለባቸውን ሰዎች፣ ትርጉም ያለውና የሚያረካ ሕይወት እንዲመሩ ልትረዷቸው ትችሉ ይሆናል።
በጭንቀት ምክንያት የሚመጡ የጤና እክሎች
በጭንቀት ምክንያት የሚመጡ የስሜት ቀውስ ዓይነቶችን መረዳት በጣም አስፈላጊ ነው፤ በተለይም ይህ ዓይነት ችግር ያለባቸው ሰዎች የቤተሰባችን አባላት ወይም የቅርብ ወዳጆቻችን ከሆኑ በቂ ግንዛቤ ማግኘታችን ጠቃሚ ነው። ከእነዚህ የጤና እክሎች መካከል አምስቱ ከዚህ በታች ቀርበዋል።
አንዲት ልጅ ከመጠን ያለፈ የፍርሃት ስሜት (ፓኒክ ዲስኦርደር)፦ ሁኔታ እንመልከት። የሚረብሻት በጭንቀት ምክንያት የሚያጋጥማት የስሜት ቀውስ ብቻ አይደለም። “በተረጋጋሁበት ሰዓት እንኳ ‘ጭንቀቱ እንደገና ይነሳብኝ ይሆን?’ የሚለው ስጋት በጣም ይረብሸኛል” በማለት ትናገራለች። በዚህም የተነሳ እንዲህ ዓይነት ችግር ያለባቸው ሰዎች ከዚህ በፊት የስሜት ቀውስ ያጋጠማቸው ቦታ ዳግመኛ ድርሽ አለማለትን ይመርጣሉ። አንዳንዶቹ የትም መሄድ ስለሚፈሩ ከቤታቸው አይወጡም፤ ከወጡ ደግሞ የሚፈሩት ሁኔታ ወዳለበት ቦታ የሚሄዱት ከሚተማመኑበት ሰው ጋር ብቻ ነው። ኢዛቤላ እንዲህ በማለት ተናግራለች፦ “ብቻዬን መሆኔ በራሱ እንኳ የስሜት ቀውስ ሊፈጥርብኝ ይችላል። ከእናቴ ጋር ስሆን እረጋጋለሁ፤ እሷ አጠገቤ ከሌለች ግን በጣም እረበሻለሁ።”
ጭንቀትን ለመቀነስ ሲሉ አንድን ነገር ደጋግሞ የማድረግ አባዜ (ኦብሰሲቭ ኮምፐሊስቭ ዲስኦርደር)፦ ቆሻሻ ወይም ጀርሞች የሚያስከትሉት ጉዳት ከልክ በላይ የሚያስጨንቀው ሰው አሁንም አሁንም እጁን እንዲታጠብ የሚያስገድደው ኃይለኛ ስሜት አለው። ሬናን እንዲህ ያለውን ስሜት በተመለከተ እንዲህ ይላል፦ “ቀደም ሲል የሠራኋቸውን ስህተቶች እየመላለስኩ ስለማውጠነጥናቸውና ከተለያዩ አቅጣጫዎች ለማየት ስለምሞክር አእምሮዬ ሁልጊዜ እንደተበጠበጠ ነው።” እንዲህ ዓይነት ችግር ያለበት ሰው የቀድሞ ስህተቶቹን ነጋ ጠባ ለሌሎች እንዲናዘዝ የሚገፋፋ አባዜ ይኖረዋል። ሬናን ዘወትር ማበረታቻ ያስፈልገዋል። መድኃኒት መውሰዱም ችግሩን ለመቋቋም ረድቶታል።*
ከአሰቃቂ ገጠመኝ በኋላ የሚከሰት ጭንቀት (ፖስት ትራውማቲክ ስትረስ ዲስኦርደር)፦
ይህ አገላለጽ፣ ሰዎች አካላዊ ጉዳት የሚያደርስ በጣም አሰቃቂ ሁኔታ ስላጋጠማቸው፣ ስለተመለከቱ አሊያም እንዲህ ባለው ሁኔታ ውስጥ ስላለፉ የሚፈጠሩባቸውን የተለያዩ ሥነ ልቦናዊ ችግሮች ያመለክታል። እንዲህ ያለ ችግር ያለባቸው ሰዎች በቀላሉ ሊደነብሩ፣ ሊነጫነጩ፣ ስሜታቸው ሊደነዝዝ፣ ይወዷቸው በነበሩ ነገሮች ላይደሰቱ እንዲሁም ለሌሎች፣ በተለይም በጣም ይቀርቧቸው ለነበሩት ሰዎች ፍቅር ለማሳየት ሊቸገሩ ይችላሉ። አንዳንዶቹ ቁጡዎች አልፎ ተርፎም ጠበኞች ይሆናሉ፤ እንዲሁም የደረሰባቸውን አሰቃቂ ገጠመኝ ከሚያስታውሷቸው ሁኔታዎች መራቅን ይመርጣሉ።
ሰዎችንና ማኅበራዊ ግንኙነቶችን ያለ ምክንያት መፍራት (ሶሻል ፎብያ)፦ እንዲህ ዓይነት ችግር ያለባቸው ሰዎች ከሌሎች ጋር የሚያገናኟቸውን የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴዎች ሲያከናውኑ ሰዎች ምን ይሉኛል የሚለው ስሜት ከልክ በላይ ያስጨንቃቸዋል። አንዳንዶቹ፣ ሰዎች ሁልጊዜ እንደሚከታተሏቸውና እንደሚታዘቧቸው በማሰብ በስጋት ይዋጣሉ። በአንድ ዝግጅት ላይ ከመገኘታቸው በፊት ለቀናት ወይም ለሳምንታት ሲጨነቁ ሊሰነብቱ ይችላሉ። የሚሰማቸው ፍርሃት በጣም ከፍተኛ ከመሆኑ የተነሳ ሥራቸውን፣ ትምህርታቸውን ወይም ሌሎች የተለመዱ እንቅስቃሴዎቻቸውን ሊያስተጓጉልባቸው ይችላል፤ እንዲሁም ጓደኛ ማፍራትና በጓደኝነት መቀጠል አዳጋች ይሆንባቸዋል።
ያለ ምክንያት ከልክ በላይ መጨነቅ (ክሮኒክ አንዛይቲ ዲስኦርደር)፦ እንዲህ ዓይነት ችግር ያለባቸው ሰዎች መጥፎ ነገር ቢደርስስ ብለው ይሰጋሉ፤ እንዲሁም ስለ ጤንነታቸው፣ ስለ ገንዘብ፣ ስለ ቤተሰብ ችግሮች ወይም በሥራ ቦታ ስለሚያጋጥማቸው ችግር ከልክ በላይ ይጨነቃሉ። ‘ቀኑ እንዴት ያልፍ ይሆን?’ የሚለው ሐሳብ ብቻ እንኳ ጭንቀት ውስጥ ሊከታቸው ይችላል።*
ክፍል 3፡ ጭንቀት የእምነት ማነስን ያመለክታል? የመጽሐፍ ቅዱስ አመለካከት
“መጨነቅ ተገቢ አይደለም።” በ20ኛው መቶ ዘመን መጀመሪያ ላይ አንድ ቄስ በዚህ ርዕስ ባቀረቡት ጽሑፍ ለቁሳዊ ነገሮች መጨነቅ ስህተት ብቻ ሳይሆን “ከባድ ኃጢአት” እንደሆነም ተናግረዋል። በቅርቡ ደግሞ አንድ ዘጋቢ ስጋትንና ጭንቀትን ስለመቋቋም ሲጽፍ “ጭንቀት በአምላክ እንደማንታመን ያሳያል” ብሏል።
ከላይ የተጠቀሱት ሁለቱ ጸሐፊዎች ከዚህ ድምዳሜ ላይ የደረሱት ኢየሱስ በተራራ ስብከቱ ላይ “አትጨነቁ” በማለት የተናገረውን ተንተርሰው ነው። (ማቴዎስ 6:25) በዛሬው ጊዜ ብዙ ሰዎች በጭንቀት ስለሚጠቁ አንድ ክርስቲያን በጭንቀት ከተዋጠ የጥፋተኝነት ስሜት ሊያድርበት ይገባል? ብለን እንጠይቅ ይሆናል። መጨነቅ የእምነት ማነስን ያመለክታል?
እግዚአብሄር አምላክ ፍጽም ያለመሆናችንን ይረዳልናል
መጽሐፍ ቅዱስ የጭንቀት መንስኤ ምንጊዜም የእምነት ማነስ ነው ብሎ አያስተምርም። የምንኖረው ‘በሚያስጨንቅ ጊዜ’ ውስጥ ስለሆነ ይብዛም ይነስ እንጂ ጭንቀት ማጋጠሙ አይቀርም። (2 ጢሞቴዎስ 3:1) ታማኝ ክርስቲያኖች በጤና ዕጦት፣ በእርጅና፣ በገንዘብ ችግር፣ በቤተሰብ ግጭት፣ በወንጀልና በሌሎችም ችግሮች የተነሳ በየዕለቱ የሚያጋጥሟቸውን ጭንቀቶች ተቋቁመው ለመኖር ይገደዳሉ። በጥንት ጊዜም የአምላክ አገልጋዮች ፍርሃትና ስጋት ያጋጥማቸው ነበር።
መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ሎጥ የሚናገረውን ታሪክ ስንመለከት ሰዶምና ገሞራ ሲጠፉ ሕይወቱን እንዳያጣ ወደ ተራራ ሸሽቶ እንዲያመልጥ እግዚአብሄር አምላክ አዝዞት ነበር። ይሁን እንጂ ሎጥ ከባድ ጭንቀት አደረበት። ‘እግዚአብሄር ሆይ፣ እባክህ እንደዚህስ አይሁን’ አለ። በመቀጠልም ፈራ ተባ እያለ “እኔ እንደሆንሁ ወደ ተራሮቹ ሸሽቼ ማምለጥ ስለማልችል የሚወርደው መዓት ደርሶ ያጠፋኛል” አለ። ሎጥ ወደ ተራሮቹ መሸሽ የፈራው ለምንድን ነው? መጽሐፍ ቅዱስ ምክንያቱን አይነግረንም። ምክንያቱ ምንም ይሁን ምን፣ ብቻ ሎጥ በጣም ፈርቷል። እግዚአብሄር አምላክ ምን ምላሽ ሰጠው? ሎጥ እምነት አንሶሃል ወይም በአምላክ አልታመንክም ተብሎ ተወቅሶአል? ከዚህ በተቃራኒ እግዚአብሄር ለሎጥ አሳቢነት በማሳየት በአቅራቢያው ወዳለች ከተማ ሸሽቶ እንዲያመልጥ ፈቅዶለታል። ዘፍጥረት 19:18-22
የእግዚአብሄር ታማኝ አምላኪዎች በጣም የተጨነቁባቸው ጊዜያት እንደነበሩ የሚያሳዩ ሌሎች የመጽሐፍ ቅዱስ ምሳሌዎች አሉ። ነቢዩ ኤልያስ የግድያ ዛቻ ሲደርስበት ፈርቶ ሸሽቶአል። (1 ነገሥት 19:1-4) ሙሴ፣ ሃና፣ ዳዊት፣ ዕንባቆም፣ ጳውሎስና ሌሎች ጠንካራ እምነት የነበራቸው ወንዶችና ሴቶች የተሰማቸውን ጭንቀት ገልጸዋል። (ዘፀአት 4:10፤
1 ሳሙኤል 1:6፤ መዝሙር 55:5፤ ዕንባቆም 1:2, 3፤
2 ቆሮንቶስ 11:28) ሆኖም አምላክ ርኅራኄ በማሳየትና በእነሱ መጠቀሙን በመቀጠል ፍጹማን ያልሆኑ ሰዎች ችግር የሚገባው መሆኑን አሳይቷል።
‘በቀላሉ ተብትቦ የሚይዘን ኀጢአት’
ይሁን እንጂ የማያቋርጥ ጭንቀት እምነታችንን ሊያዳክምና በእግዚአብሄር አምላክ ላይ ያለንን ትምክህት ሊያጠፋብን ይችላል። ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ እምነት ማጣትን ‘በቀላሉ ተብትቦ የሚይዘን ኀጢአት’ ሲል ገልጾታል። (ዕብራውያን 12:1) ጳውሎስ ራሱን ጨምሮ መናገሩ አልፎ አልፎ የእምነት መዳከም ሲያጋጥመው ‘በቀላሉ ተተብትቦ’ የመያዝ አዝማሚያ እንዳለው ማመኑ ሊሆን ይችላል።
በአንድ ወቅት የኢየሱስ ሐዋርያት ‘እምነታቸው በማነሱ’ ምክንያት ተአምራዊ ፈውስ ማድረግ አቅቷቸው ነበር። ይሁን እንጂ ሐዋርያቱ በአምላክ ዘንድ የነበራቸውን ተቀባይነት አላጡም።ማ ቴዎስ 17:18–20፤
ሉቃስ 1:18, 20, 67፤ ዮሐንስ 17:26
በሌላ በኩል ደግሞ መጽሐፍ ቅዱስ በእግዚአብሄር ላይ ያላቸውን ትምክህት አጥተው አስከፊ መዘዝ የደረሰባቸውን ሰዎች ምሳሌም ይዟል። ለምሳሌ ያህል ከግብፅ የወጡ ብዙ እሥራኤላውያን እምነት በማጣታቸው ወደ ተስፋይቱ ምድር እንዳይገቡ ተከልክለዋል። በአንድ ወቅት እነዚያ ሰዎች “በምድረ በዳ እንድንሞት ከግብፅ ያወጣችሁን ለምንድነው? ምግብ የለ! ውሃ የለ!” በማለት በአምላክ ላይ ጭምር እስከማጉረምረም ደርሰዋል። አምላክ ደስ እንዳልተሰኘባቸው ለመግለጽ መርዛማ እባቦችን በመስደድ ቀጣቸው። ዘኍልቁ 21:5, 6
ጌታ ኢየሱስ ያደገባት የናዝሬት ከተማ ነዋሪዎች እምነት ስላልነበራቸው ብዙ ተአምር የማየት መብት ተነፍጓቸዋል። ከዚህም በላይ በዚያ ዘመን የነበረው ክፉ ትውልድ እምነት በማጣቱ የተነሳ ኢየሱስ ክፉኛ ነቅፎታል። (ማቴዎስ 13:58፤
17:17፤ ዕብራውያን 3:19) ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ “ወንድሞች ሆይ፤ ከእናንተ ማንም ከሕያው እግዚአብሔር የሚያስኰበልል፣ ኀጢአተኛና የማያምን ልብ እንዳይኖረው ተጠንቀቁ” ማለቱ የተገባ ነበር።ዕብራውያን 3:12።
አዎን፣ በአንዳንድ ሁኔታዎች የእምነት ማጣት ከክፉ ልብ ሊመነጭ ይችላል። ይሁን እንጂ ከላይ በተጠቀሱት ምሳሌዎች እንዳየነው በዘካርያስና በኢየሱስ ሐዋርያት ላይ የደረሰው ሁኔታ ይህ አልነበረም። የእነሱ የእምነት ማነስ መንስኤ ድንገተኛ ድካም ነበር። አኗኗራቸውን በአጠቃላይ ካየን “ልባቸው ንጹሕ” እንደሆነ እንገነዘባለን። ማቴዎስ 5:8
እግዚአብሄር አምላክ የሚያስፈልገንን ያውቃል
ቅዱሳን ጽሑፎች በዕለታዊ ሕይወታችን በሚያጋጥመን ጭንቀትና እንደ ኃጢአት በሚቆጠረው እምነት ማጣት መካከል ያለውን ልዩነት እንድናስተውል ይረዱናል። ዕለታዊ ጭንቀት ወይም በሰብአዊ ድካም የተነሳ የሚያጋጥም ድንገተኛ የእምነት ማጣት ከክፉና ደንዳና ልብ ከሚመነጨው በአምላክ ላይ ፈጽሞ እምነት ከማጣት ጋር አንድ ተደርጎ መታየት አይኖርበትም። በመሆኑም ክርስቲያኖች አልፎ አልፎ ጭንቀት ቢያጋጥማቸው በጥፋተኝነት ስሜት መዋጥ የለባቸውም። ይሁንና ሕይወታችንን እስኪቆጣጠረው ድረስ ከልክ በላይ በጭንቀት ላለመዋጥ መጠንቀቅ ያስፈልገናል። በመሆኑም ኢየሱስ “ስለ ኑሮአችሁ ምን እንበላለን? ምን እንጠጣለን? ምንስ እንለብሳለን? በማለት አትጨነቁ” ሲል ጥበብ የተሞላበት ሐሳብ ተናግሯል። ኢየሱስ ከዚህ በማስከተል የሚከተሉትን የሚያጽናኑ ቃላት ተናግሯል:-
“የሰማዩ አባታችሁም እነዚህ ሁሉ ለእናንተ እንደሚያስፈልጓችሁ ያውቃል። ከሁሉ አስቀድማችሁ ግን የእግዚአብሔርን መንግሥትና ጽድቁን እሹ፤ እነዚህ ሁሉ ይጨመሩላችኋል።”ማቴዎስ 6:25-33






0 comments:
Post a Comment