በልጆች ሕይወት የተረጋጋ ስሜት እንዲኖራቸው ስለመቅረጽ
የልጆች ስብዕና እና እድገት የተስተካከለና የተሟላ እንዲሆንና መልካም ስነ ምግባራቸውን ጠብቀው
እንያድጉ ከፍተኛውን ሚና የሚጫወቱት ወላጆች ናቸው። ወላጆች ለልጆቻቸው ከሚስጧቸው ምድራዊ ሃብት የበለጠ ስሜታቸው የተረጋጋና በራቸው የሚተማመኑ ልጆች እንዲሆኑ ማድረግ ከሁሉም ስጦታቸው የበለጠ ነው ብዬ አምናለሁ። ወላጆች በሚገባ የወላጅነት ሥራቸውን ካላከናወኑ ልጆቹ
የሚቀርጽዋቸው የራሳቸው የእድሜ የትምህርት ቤት ወይም የመንደር ግዋደኞቻቸው ይሆናሉ። የልጆችን መልካም አስተዳደግ
ለማረጋገጥ ቤተሰብ ወይም ወላጆች፣ አሳዳጊዎችና ህብረተሰቡ በቅድሚያ በቂ ግንዛቤና እውቀት ሊኖራቸው ይገባል ከጐጂ ለማዳዊ ድርጊቶችና የህዋላ ቀር ባህል የተጠበቁና ጤናማ ልጆችንን ለመፍጠር በሚደረገው ጥረት ውስጥ አስተዋፅኦ ከአሳዳጊዎችም
ሆነ ከህብረተስቡ ደጋፍ መስጠት ይጠበቅባቸዋል።በልጆች ላይ በትምህርት ቤቶች ውስጥ፣ በመኖሪያ አካባቢያቸው፣ በቤተሰባቸውና በቅርብ ዘመዶቻቸው የስነ ልቦናዊና አካላዊ ጉዳዮች ይደርሱባቸዋል። ከሁሉም የከፋው ጉዳት ደግሞ ስነ ልቦናዊ ጉዳት
ነው።ቁንጥጫ፣ በአለንጋ መግረፍ፣ በርበሬ ማጠን፣ በእሳት ማቃጠልና ሌሎች ጎጂ ቅጣቶች በልጆቹ አካል ላይ የሚታዩ ቢሆኑም የስነ ልቦናዊነታቸው ጠባሳ ከሁሉም የበለጠና እጅግ የከፋ ነው፤ በዚህም ምክንያት ልጆቹ ከቤተሰብ ሽሽት፣ ጐዳና ተዳዳሪነትን
መምረጥ እና ከሀገር መኮብለልን አማራጭ አድርገው ይወስዱታል። ልጆች የጎዳና ተዳዳሪ የሚሆኑት በድህነት አለንጋ የሚገረፉት ወይም ስብሳቤ የሌላቸው ልጆች ብቻ ወላጆች/ በአስዳጊዎቻቸው የተጎዱ ልጆችም ለዚሁ አደጋ የተጋለጡ ይሆናሉ። ወላጆች ለጆቻቸውን እነርሱ ባደጉበት አስከፊ መንገድ ለማሳደግ ሲሞክሩ ልጆቻቸውን ከጉዳት ከማትረፍ ይልቅ ለአደጋ ያጋልጥዋቸዋል እነርሱም በድርጊታቸው አተርፍ ባይ አጉዳይ ሆነው ይገኛሉ።ልጆቹ ለሚያቀርቡት ጥያቄ አዎንታዊ ምላሽ አለመስጠት ስነ ልቦናቸውን ክፉኛ ይጐዳዋል፤ ማንቋሸሽና ማዋረድም የልጆቹ አእምሮ እንዲረበሽና መልካም አመለካከት እንዲኖንቸው አያደርግም፤ ቸልተኛ
አያያዝም ቢሆን የልጆችን እንክብካቤ የሚቀንስ በመሆኑ ለአካላዊ ጉዳይ ሲዳረጉ ይስተዋላል።የወላጆች ቸልተኛ አያያዝ ልጆቹንን በትኩረት ካለመከታተል የሚመነጭ ሲሆን ልጆቹ በእሳት ሊቃጠሉ፣
ውሃ ውስጥ ሊገቡ፣ ጉዳት ሊደርስባቸውና ከከፋም አስከ ሞት ሊዳረጉ ይችላሉ። የልጆቹን ክብር ዝቅ ማድረግ ደግሞ ሌላው
ስነ ልቦናዊ ቅጣት ነው። ይህም በራሳቸው እንዲያፍሩና እንዲሸማቀቁ ያደርጋቸዋል።በአካላቸው ላይ በሚፈፀምባቸው ቅጣት
ሳቢያ ልጆቹ የመድማት፣ የመቁሰል፣ አካላዊ እብጠት፣ ለረጅም ጊዜ የሚቆይ ጠባሳና ምልክት፣ አዝጋሚ የሆነ አካላዊ እድገት፣
አካል ጉዳተኝነትና ሞትን ያስከትላሉ። የልጆች በስነ ልቦናቸው ላይ ጉዳት ሲደርስባቸው ጥሩ ያልሆኑ የባህሪ ለውጦች ይስተዋልባቸዋል ይህም የምግብ ፍላጐት መቀነስ መነጫነጭ፣ ተደጋጋሚ ህመሞችና በሌሎች ምልክቶች ሊገለፅ ይችላል፡፡በራሳቸው ላይ ያላቸው እምነትም ይሸረሸራል፡፡በቤተሰቦቻቸው ወይም በአሳዳጊዎቻቸው ላይም ማመፅ ይጀምራሉ።ልጆች ሌሎችን የመቅረብና የማመን ከፍተኛ ስሜት አላቸው፤ ስነ ልቦናቸው ከተነካ ግን ሰዎችን የመቅረብና የማመን ሁኔታ ፈፅሞ አይስተዋልባቸውም የድባቴ ስሜትም አላቸው። የትምህርት ውጤታቸውም እየቀነሰ ይሄዳል፡፡ባሉበት ሁኔታ ውስጥም ያለመረጋጋት ፀባይ የሚታይባቸው ከመሆኑም በላይ የአዕምሮ ዘገምተኝነትም ሊከሰትባቸው ይችላል፡፡ ልጆቹ በእነዚህ ችግሮቻቸው ሳቢያ ማህበራዊ ቀውስ ሲፈፅሙ ይታያሉ፡፡መገለል፣ ትምህርት ማቋረጥ፣ መኮብለል፣ የአልኮልና አደንዛዥ ዕፅ ተጠቃሚና ተጠቂ ይሆናሉ፡፡ወደ ጐዳና ህይወት የሚቀላቀሉትም ብዙዎች ናቸው። ከዚያም ወንጀል መፈፀም፣ ህግንና ህግ አስከባሪ አከላትን ያለመቀበልና ጥቃት ማድረስ የመሳሰሉት ፀረ ማህበራዊ ባህሪያትን ለማሳየት በህብረተሰቡ ላይ አሉታዊ ተፅእኖ እንዲደርስ ያደርጋሉ።ድህነት ጉዳት ሊያስከትሉ ከሚችሉ የልጆች ቅጣትና አያያዝ መንስኤዎች መካከል ቅድሚያውን ይይዛል።ልጆችንን የንዴት ማብረጃ መንገድ በማድረግ አላስፈላጊ ቅጣቶች ይቀጣሉ፡፡ማህበራዊ አገልግሎት ያለመኖሩም በልጆቹ ላይ አሉታዊ ተፅእኖ ያሳድራል፡፡
በህብረተሰቡ ዘንድ ተቀባይነት ያላቸው ተገቢ ያልሆኑ የልጆችን አስተዳደግና የስነ ምግባር መገንቢያ ናቸው ተብለው የታመነባቸው የተለያዩ ዘይቤዎች ይገኛሉ፡፡ከእነዚህ መካከል የህብረተሰቡን ኋላቀር የሆነ ባህል፣ ወግ፣ ልምድና የአኗኗር ዘዴዎች ይጠቀሳሉ፡፡አማራጭ የመልካም ስነ ምግባር መገንቢያ መንገዶች ላይ የሚስተዋለው የግንዛቤ እጥረትም ሌላው ችግር ሲሆን ከፍተኛ የቤተሰብ ቁጥር እና ያልተመጣጣነ የቤተሰብ ቁጥር ለችግሩ መፈጠር መንስኤ ነው፡፡ወላጆች ችግሮችን የመቋቋም ችሎታቸው የቀነስ ከሆነ በልጆቻቸው ላይ ተፅእኖ ይፈጥራሉ፡፡ተከታታይ የቤተሰብ ቀውስ ማለትም የትዳር መፍረስ ሊሆን ይችላል ልጆች እንዲጐዱ ያደርጋል ወላጆች በልጆች አስተዳደግ
ዙሪያ ያላቸው ግንዛቤ ከራሳቸው የአስተዳደግ ምንጭ የመነጨ በመሆኑ ልጆቻቸውን እነሱ ባለፉበት የአስተዳደግ መስመር እንዲየልፉ በሚጥሩበት ወቅት ህፃናቱ ላይ አሉታዊ ተፅእኖ እንዲፈጠርባቸው ያደርጋል። የወላጆች የግል ባህሪ ቁጡ ከሆነ ይህንኑ ባህሪያቸውን መቆጣጠር ሳይችሉ የሚቀሩ ከሆነ ብሶትና ብስጭታቸውን በልጆቹ ፊት ወይም በልጆቹ ላይ ይፈፀማሉ። ልቅ የሆነ አስተዳደግም ለቁጥጥር አመቺ ስላልሆነ የልጆቹ አስተዳደግና ባህሪያቸው ከመስመር አንዲስት ያደርጋል።የልጆች ስነ ምግባር አስተማማኝ ደረጃ ላይ እንዲደርስ የልጆችንና ወላጆች ግንኙነት በመከባበር ላይ የተመሰረተ ሊሆን እንደሚገባ ይመከራል፡፡በመነጋገር ማመን፣ የልጆቹን ተፈጥሮአዊ ራስን የመቆጣጠር ብቃት የሚያዳብር ችሎታ ማዳበር እንዱችሉ ማድረግም ከቤተሰብ ይጠበቃል፡፡ልጆች ያሏቸውን አማራጮች በማቅረብ እንዱወስኑ አሊያም እንዲመርጡ ማድረግ ውሳኔ ሰጪነታቸው
እንዲበለፅግ ያደርጋል፡፡ መልካም ስነ ምግባሮቻቸውን ማድነቅና ማበረታታትም ተገቢ ነው፡፡ሲሳሳቱ እንደማስተማሪያ እንጂ እንደውድቀት መለኪያ አድርጐ መመልከት አሉታዊ ተፅእኖ አለውና በስህተታቸው እንዲማሩበት ማድረግ ይገባል፡፡ ወላጆች ለልጆች የሚያስተምሯቸውን እሴቶች ማክበር አለባቸው፤ መካከላቸው ያለው ግንኙነቶች ነፃና ክፍት መስመርን የሚያበረታታ መሆን አለበት፡፡በምንም አይነት መልኩ አዋራጅና ህፃናቱን ዝቅ የሚያደርጉ አያያዞች መታየት የለባቸውም፡፡ልጆቹን ሆን ብሎ ማናደድና ማነፃፀርን በማስወገድ ግንኙነቱን ጤነኛ ማድረግ ይቻላል።ወላጆችና አሳዳጊዎች ለልጆቹ ከፍተኛ
ትኩረት መስጠት ይኖርባቸዋል። በቂ እረፍት እንዲየገኙ ማድረግ፣ ከልጆች ጋር አብሮ ጊዜን ማሳለፍ፣ በልጆች መካከል የሚፈጠሩ አለመግባባቶችን በጊዜው መፍታት፣ ልጆቹን በተለያዩ ድርጊቶች ውስጥ ማሳተፍና የተለያዩ የማበረታቻ ሽልማቶችን መስጠት የልጆቹን አእምሮ ብሩህ ያደርጋልና ተፈፃሚ መሆን አለባቸው።የስሜት ደህንነቱ የበለጠ የተጠበቀ እንዲሆንለት የማይፈልግ የስው ልጅ የለም። ስሜታዊ ድህንነት አንድ ስው ስለራሱ የሚስማው ስሜት ነው። ከሌሎች ጋር ባለው ግንኙነት ጥሩ ስሜት የሚስማው ከማን ጋር (ለምሳሌ ከቤተብ ጋር) ነገሮች መልካም በሆኑ ጊዜ የሚስማውንም ስሜት አመኔታውንም ያካትታል።
አንዳንድ ጊዜ መጥፎ ገጠመኞቻቸው የተነሳ ስዎች በእነዚህ አካባቢ የሚስማቸው ስሜት አመኔታ የጎደለው ሊሆን ይችላል።በቤተስብ ውስጥ ወላጆች አጥብቀው መስራት ያለባቸው የልጆቻቸው የስሜታቸው ድህንነት የተጠበቀ እንዲሆን መሆን ይገባዋል። በአብዛኛው በቀላሉ የሚረበሹና አሉታዊ ጠባዮች የሚያሳዩትን ልጆች ለመረዳትና ወደ ጤናማ ጠባይ ለማምጣት የሚቻለው የልጁን ስሜትዊ ድህንነት ተረድቶና ጠብቆ ወደ ተሻለ ደረጃ ማምጣት ነው። ይህ ዘዴ የሚስራ ሆኖ ሳለ በሥራ ይተርጎም ሲባል በሥራ ለሚተረጉመው ግን ቀላል ሆኖ አይገኝም።
1. የሚስራውና ስኬታማ ውጤት ያስመዘገበው ዘዴ እንዲህ ነው፤ በየማታው ከ3 እስከ 5 ደቂቃ ለልጁ ብቻ ጊዜ
መመደብ፣ ከዚያም ልጁ ወደ መኝታ እንደሄደ እናት ወይም አባት ተራ በተራ በተኛበት ቦታ ሄደው የልጁን መኝታ
ቤት መብራት ጠፍቶ እያለ በልጁ የአልጋ ጫፍ ላይ መቀመጥ። ልጁ አሁን በመኝታ ክፍሉ በአልጋው ላይ እያለ
የወላጁን እጅ ይዞ በአይን መታያየት ሳይኖር መብራቱ ከመጥፋቱ የተነሳ ሳይተያዩ ወላጁ ለልጁ ስላሳለፈው ቀንና
የሆነውን ነገር ይነግረዋል፤ ወላጅ ይህንን ሲያደርግ ልጁን ጥያቄዎች አያነሳበትም ወይም እንዲናገር አይጠይቀውም።
በዚህን ጊዜ ልጁ ወላጁ የደረስበት ለማንኛውም ስው እንደሚደርስ ሲረዳና ሲያውቅ ልጁ በትምህርት ቤት ስላሳለፈው ቀን
መናገር አይከብደውም እንደውም የስሜት ጫና ካለው ለወላጁ መናገር ይጀምራል።
2. ልጁ ለወላጁ የሚናገረው (ለምሳሌ ትምህርት ቤት መሄድ እጠላለሁ) የሚል ከሆነ ወላጅ
በችኮላ ልጁ የበለጠ እንዳይናገር መዝጋት ወይም መንቀፍ የለበትም። ወላጅ ነቀፋውን ማቆየትና ልጁ ለምን
ትምህርት ቤት መሄድ እንደጠላ ለመጥላቱም መነሻ የሆነው ነገር ማወጣጣት
ይኖርበታል ግልጽ እንዲያደርገው። አንደኛው ዘዴና የሚስራው ስለትምህርት ቤት መሄድ
የጠላበትን መነሻ ካልተናገረ ዘዴው ወላጅ ልጁ ስላመጣው ሃሳብ በጥያቄ መልክ እንደገና ወደ
ልጁ መመለስ ነው (ለምሳሌ. ትምህርት ቤት መሄድ ጠላህ እንዴ?) የጠላኸው ማንን ነው?
ትምህርት ወይስ አስተማሪዎቹን? አስተማሪዎቹን ሁሉ ነው የጠላኸው? አይመስለኝም
ምናልባትም መምህር ዘውዴቱን? ወዘተ. ብሎ መጠየቅ
3. ለትናንሽ ልጆች “ለምን” የሚለው ጥያቄ ቢነሳላቸው መልስ የሚስጡት መልስ ላይኖር
ይችላል። አንዳንድ ጊዜ ትናንሽ ልጆች የሚስጡት መልስ አጥጋቢ አይሆንም ወይም መልስ
የሚስጡት ያጣሉ። ስለሆነም ወላጆች “ለምን” የሚለውን ጥያቄ ባይነሱ ይመረጣል።
4. ወላጆች ማስወገድ ያለባቸው አሉታዊ ቃሎችን (ዓይደለም ወይም ስህተት ነው የሚለውን)
በተለይም ልጁ በሚያንብበት ጊዜ፣ ከዚህ የተሻለው ምርጫ “ወደ ትክክሉ ተቃርበሃል” ወደ ትክክሉ ተቃርበሃል
የመሳስሉት ቃላት ልጁ ለማንበብ ፍላጎቱ እንዳይከስምና ስሜቱ ለማንበብና ለመማር ፍላጎት እንዲነሳሳ ይረዳዋል፤ ያለበለዚያ ግን ልጁ የሚታየው ውድቀቱ ብቻ
ይሆናል።
5. ወላጆች ለልጆቻቸው መንገር ያለባቸው ልጆች ባንዳንድ ነገሮች ችሎታ እንዳላቸው ጥሩ
ልጆችም እንደሆኑና እንደሚወደዱም ከወላጆቻቸው መስማት ለስሜታቸው ድህንነት አስተዋጽኦ ያደርጋል። ወላጆች ልጆቻችንን ወድቀታቸው ላይ ብቻ አተኩረን ከነገርናቸው መልስው እኛኑ ያስቸግራሉ ወይም ይረብሻሉ። እኛም ወላጆች ልጆቻችን ሲረብሹን ስለነርሱ
መልካም ነገር መናገር ያቅተናል። ከዚህ የተነሳ ልጆች ሁልጊዜ ትክክል እንዳልሆኑ ከወላጆቻቸው ከስሙ ውሎ አድሮ ስለራሳቸው ያላቸው አመለካከት አነስተኛ ስለሆነ የስሜታቸው
ድህንነት ያንኑ ያህል ይነካል።
6. ቀኝእጃቸውን የሚጠቀሙ ልጆች በቀኝ ጎናቸው ወይም በሆዳቸው መተኛት አብረውም
ጭንቅላታቸውን ወደ ግራ ትከሻቸው ማዞር ይቀናቸዋል። ግራኝ ልጆች ደግሞ በጠቅላላው
ሲተኙ ጭንቅላታቸውን ወደ ተቃራኔው ወገን ያዞሩታል። ወላጆች የልጃቸውን አልጋ
አቀማመጥ ተፈጥሮአዊ ወደሆነው አቅጣጫ (እንደ እጃቸው አጠቃቀም ማለትም ግራኞች
ወይም ቀኞች) ፈታቸው ወደ ግድግዳው ትይዩ በማድረግ መዘርጋት ይኖርባቸዋል። እንደዚህ
አይነቱ አስተኛኘትት ለልጁ የደህንነት ስሜት እንዲስማው ከማድረጉም ሌላ ልጁ በለሌት
ሽንት በመኝታው ላይ እንዳይሽናና ከለሊት የቅዠት ስሜት እንዳይቸገር ይረዳል ተብሎ
ይታመናል።የልጁን አልጋ የተዘረጋው በቤቱ ውስጥ በቀኝ መአዘን ላይ ከሌላው ክፍል ጋር የተያያዘ
ሥፍራ ከሆነ በእንቅልፍ ጊዜ እረፍት የማይስማው ልጅ ከሆነ እንዲህ አይነቱን ሥፍራ አይፈልገውም ምክንያቱም
በመኝታው ጊዜ ደህንነት አይስማውም።
7. ልጁ በመኝታው ጊዜ መብራት ያስፈለገው እንደሆነ ስማያዊ ወይም አረንግዋዴ አቦል ከቀይ
አቦል የተሻለ ስለሆነ ወላጅ ይህንኑ ቀለም መምረጥ ይኖርበታል ምክንያቱም ስማያዊ አረንግዋዴው ስሜቱን የሚያረጋገው ቀለም ሲሆን ቀዩ ደግሞ ብርሃኑ ስሜቱን የሚቀስቅስ ስለሆነ እንቅልፍ የሚነሳው ይሆናል ማለት ነው።
8. ወላጆች ስለልጆቻቸው እውነት የሆነውን የስሜታቸውን ገጽታ መቀበል መቻል አለባቸው።
ልጃቸው በአንድ ነገር የሚደነግጥና የሚፈራ ፍርሃቱም በወላጁ ዘንድ ተቀባይነት ባይኖረውም እንክዋን የልጁ እውነተኛው ስሜት ይህ ስለሆነ ወላጁ የልጁን ስሜት መቀበል ይኖርበታል። የልጁን ስሜት ባለምቀበል ከመተችት ይልቅ የልጁን ስሜት በወቅቱ መጠየቅና ከዚህ ከሚስማው ስሜት የሚወጣበትን መንገድ ወላጆች የልጁን ጭንቀት ወይም ፍርሃት ለመቀነስ ለመርዳት ጥረት ማድረግ ይኖርባቸዋል።
9. ወልጆች በተከታታይ የተወስኑ ደቂቃዎች (10 ደቂቃዎች) በመውስድ ለልጆቻቸው ትኩረት
በመስጠት ስለልጆቻቸው ለማወቅም ሆነ ለመረዳት ህሳቤ እንዲኖራቸው ይረዳቸዋል።
10. ወላጆች ለልጆቻቸው ማንበብ ይጠበቅባችዋል። ጨቅላ ልጆች እድሜያቸው (2-6) ክልል ውስጥ የሆኑት ከሚወድዋቸው የልጆች መጻህፍት የተነበብላቸውን ታሪክ በመድገም መልስው ለራሳቸው ያነቡታል። ከፍ ያሉት ልጆች እድሜያቸው (7- 10) ክልል ያሉት ደግሞ ወላጆቻቸው ልጆቹ ከሚወዱት መጻህፍት መካከል ያነበቡላቸው
እንደሆነ ከወላጆቻቸው ጋር ልጆቹ አንድ አይነት ፍላጎት እንዳላቸው እንደሚጋሩ ሆኖ ይስማቸዋል የታሪክ መጻህፍትና ከኢንሳክሎፒዲያ ታሪኮች የመሳስሉትን ማለት ነው።
11. ከልጆች ጋር ጊዜ ወስዶ መጫወት ልጆቹም አዋቂዎች መጫወትና መሳቅ እንደሚችሉ
ለማሳየት ልጆችን ለማስተማር ይረዳል።
12. በወላጆች ዘንድ መመሪያን በመስጠት ተከታታይነት ወይም ያለመወላወል ዋነኛና አስፈላጊ
መሆን አለበት። ወላጆች መመሪያ በመስጠቱ በኩል ተከታታይና የማይወላውሉ ከሆኑ
ልጆችም ሥፍራቸው የት እንደሆነ ያውቃሉ። ወላጆች መመሪያን በመስጠት ተከታታይና
የሚወላውሉ ከሆነ ልጆች የሚከተሉት አቅጣጫ የትኛው እንደሆነ ስለማያውቁ ስለሚዘበራረቅባቸው ልጆቹም ስሜታቸውና ሃሳባቸው የማይቸበጥ ያደርገዋል። ከዚህ ሁኔታ ለመዳን
ወላጆች ያሉትን ማድረግ ይኖርባቸዋል ቅጣት ካሉ መቅጣት ሽለማት እንስጣለን ካሉ ያሉትን ማድረግ ማለት ነው። ያለበለዚያ ወላጆች በልጆቻቸው ዘንድ ያላቸው ተቀባይነት በጥያቄ ላይ ይሆናል። ይህ ሁኔታ በወላጆችና በልጆች መካከል መፈጠሩ ለወደፊቱ የልጆቻቸው አስተዳደግ ሥራ ለወላጆች አስቸጋሪ ያደርግባቸዋል።






0 comments:
Post a Comment