Sunday, February 25, 2018

የወላጅነት ጥሪ


የወላጅነት ጥሪ
መላኩ ለእናቱ ምን መሆን እደሚገባት ልጁ  ከመወለዱ በፊት ነው ናዝራዊ የሆነ ልጅ የምታስፈልገው እናት ናዝራዊ የሆነች እንደሆነ ያመለክታል ማለትም ይህች ናዝራዊ እናት የሚያስክር ወይንም ሆነ ንጹህ ያልሆነ ነገር የምትመገብ አይደለችም ከአለም ከመለየትም ቀጥሎ ለእግዚአብሄር በንጽህና በቅድስና የተለየች መሆነ አለባት ይህም ለክርስቲያን ወላጆች የተስጠ የእግዚአብሄር ሚስጢር ነው።
ትምህርት ወይም እውቀት ብዙውም ጊዜ የሚያሳየን የምናደርገውን ወይም የምንስራውን የምንናገረውን ብቻ  ስይሆን ማንነታችንንም አጉልቶ የሚያሳይ ሆኖ ተገኝትዋል። ይህ ሃሳብ ወይም እውነት ልጆች አድገው ክፉን ወይም ደጉን በለዩበት ወቅት ብቻ ሳይሆን ከመወለዳቸውም በፊት መኖር ወይም መታወቅ ያለበት ሀቅ ነው። ታላቅ እንዲሁም ሚስጥራዊ በሆነው የእናት የልጅ አንድነት ወይም ህብረት የእናት መንፈስ በልጁ ላይ ሃይል እንዳለው መገንዘብ አስቸጋሪ አይሆንም። የእግዚአብሄር መላክ ለማኑሄ እንዲህ አለ “ሴቲቱ ከነገርክዋት ሁሉ ትጠንቀቅ ከወይንም ከሚወጣው ሁሉ አትብላ የወይን ጠጅንም የሚያስክርንም ነገር አትጠጣ ርኩስም ነገር ሁሉ አትብላ ያዘዝክዋትንም ሁሉ ትጠብቀው” አለው። ይህን ቃል ተቀብሎ በሥራ ላይ ለማዋል እራሱን መካድ በአለም ያለው ነገር ሁሉ እጂግ የሚያስደስት ሆኖ ቢገኝም እንክዋ በፈቃደኛነት ለዚህ  መመሪያ መገዛትና መኖር በፈቃደኛነት ለዚህ መመሪያ መገዛትና መኖር ለእናትየዋ መተኪያ የሌለው በመላኩ የተስጣት መመሪያ መሆኑን መገንዘብ እጅግ አስፈላጊ ነው። ይህ እንደወላጅነት መታዘዝና መቀበል እናትና አባት ለተጠሩበት አገልግሎት ማለትም ልጃቸውን ለማስልጠን መስረታዊ ሃሳብ ሆኖ የተስጠ ስለሆነ ለወላጆች ቢኖሩበትም የሚጠቀምባቸው የበረከት ምንጭ ይሆንላቸዋል። እግዚአብሄር ጸሎትን ይስማል እንዴት ልጆችን እንደምታዙ እንዲሁም በህይወት እስካላችሁ ድረስ ልጆቻችሁን ታስለጥናላችሁ ይኸውም ውጤት ያለው የሚሆነው እናተ እንደናዝራዊ ስትኖሩ ማለትም ለእግዚአብሄር የተቀደሳችሁ ስትሆኑ ልጃችሁም የናንተን ፈለግ በመከተል ለእግዚአብሄር የተለየ ናዝራዊ ይሆናል።
የወላጅ/አሳዳጊ/ መጠራት በሁለት ወገን ነው። በእምነት የተሞላና እንዲሁም ታማኝነቱን የሚጠብቅ ሆኖ ነው። እንደዚህ አይነቱ ወላጅ የእምነቱ መለኪያው ልኬታው የእግዚአብሄር ቃል ነው። ስለዚህ አንድ ወላጅ የእግዚአብሄር ቃል የእምነቱ ልኬታ እንዲሁም የቤተስቡና የህይወቱ መለኪያ አድርጎ  መውስድ ይገባዋል በተለይም ይህ የእግዚአብሄር ቃል በመለኪያነት የሚጠቀምበት በቤተስቡ ውስጥ ነው። አንድ ወላጅ እራሱ እንደሚፈልገው ሳይሆን እግዚአብሄር እንደሚፈግበት መሆን ይገባዋል በተለይም የአማኝ ቤተስብ በእለታዊ ኑሮው ወይም ፍላጎቱን መሻቱ የተቀደስ ኑሮ ለመኖር ጥረቱ መሆን አለበት ይህም በይበልጥ ጠቃሚ ሆኖ የሚገኘው  ለስማያዊ ቤት ብቻ ሳይሆን ቤተስብን ለመግዛት (ለማስተዳደር) በቤተስብ ውስጥ ትእዛዝ ለመስጠት ልጆችንም ለማስተዳደር ይህ የእግዚአብሄር ጎዳና ጠቃሚና አይነተኛ ነው። ይህ የቅድስና ኑሮ በአንድ ወላጅ/አሳዳጊ/ ህይወት ውስጥ በታየ ጊዜ እግዚአብሄር በተናገረው መሰረት ለዚያ ቤተስብ ያደርጋል። ወላጅም  በረከቱ በቤቱ ብቻ ሳይሆን በክርስትና ህይወቱም ላይ በረከትን እንዲሁም በልጆቹ ላይ  በረከተን ያመጣል። በዚህን ጊዜ አብረሃም ሃይል እንደተቀበለ በዚህ ልምምድ ውስጥ  ያለ ወላጅ እንደዚሁ ሃያልን ይቀበላል ይህም የእምነት ሚስጢር አብረሃም በውስጡ አድጎ ለስዶም ህዝብ የምልጃ ጸሎት እንዳቀረበ  አንድ ወላጅም/አሳዳጊ/ ወደዚህ እድገት ሲደርስ ለራሱ ከመጸለይ አልፎ ለጠፉት ነፍሳት በጸሎት የሚማልድ ህይወት ይስጠዋል። እግዚአብሄርም እምነትና እንዲሁም የወላጅ ታማኝነት ከእግዚአብሄር በጣም የተወደዱ ስዎች የተስጠ መሆኑን ስው አብኖ መቀበል እንዳለበት የአብረሃምን እምነትና እንዲሁም በወላጅነቱ ታማኝነቱን ማረጋገጫ አድርጎ በቃሉ ላይ ለትምህርታችን እንዲሆን አስፈረው።
የወላጅ አገልግሎት
አንድ አማኝ ወላጅ በእግዚአብሄር ተቀባይነትን አግኝቶና ተጠርቶ ልጁን ወደ ጌታ ለማምጣት የተዘጋጀ መሆን ይገባዋል። በብሉይ ሥርዓት የቤተስቡ ሃላፊ አባት በቤቱና በቤተስቡ ላይ የደሙን የመርጨት ሥር ዓት ማከናወኑ ቤተስቡን እንዲሁም ልጆቹን የሚመታው መላዕክ እንዲያልፍ በእግዚአብሄር ጥበቃ ሥር እንዲሆኑ አድርግዋቸዋል። እርሱም የእግዚአብሄር አላማ መፈጸሚያ ከመሆኑም በላይ በእግዚአብሄር ፊት የተከበረ እንዲሆን አድርጎታል። ይህንን ሲያከናውን በልጁ ቦታ ሆኖ ነው። ወላጅ ልጁ ማድረግ የማይችለውን በርሱ ሥፍራ ሆኖ ሲያከናውን ይታያል ይህም ተግባር በእግዚአብሄር ዘንድ ተቀባይነትን አስጥቶታል። በመጀመሪያ በበጉ ደም መረጨት ሥርአት ላይ እርሱም የበረከቱ ተካፋይ እንዲሆን አድርጎታል በህዋላም እያደገ ሲሄ ለርሱ በግሉ እንደዚሁ እምነቱንና ሥርዓቱን ያደርገዋል በዚህ መንገድ ከትውልድ ወደ ትውልድ ይተላለፋል።
አንድ ወላጅ ወደ ልጁ በሚመልከትበት ጊዜ መሽጋገሪያ ብርሃን በሆነው በእግዚአብሄር ውስጥ ነው ይህም ብርሃን የሚገኘው በእርሱና በእግዚአብሄር መካከል ነው። ልጅን እንደ አንድ እቃ ብንቆጥረው በብርሃኑ መካከል ያለ ሆኖ ልንመልከተው አስፈላጊ ነው ስለዚህ ይህ አማኝ ወላጅ ልጁን እንደእንግዳ ሊቆጥረው አይገባም ምክንያቱም ይህ የተወልደው ልጅ በጸጋ ተስፋ ውስጥ ያለ መበሆኑ ነው ሁልጊዜ ወላጆች ይህንን ሃሳብ በመረዳት ልጃቸውን እግዚአብሄር እንዲስራው ገና በህጻንነቱ አሳልፈው መስጠት አስፈላጊያቸው ነው። እርሱም የቃልኪዳኑን እውነትነት በእርሱና በእግዚአብሄር መካከል የተደረገውን ይህንን ቃል ኪዳን ደግሞ በክርስቶስ ኢየሱስ ደም ከሃጢያት መንጻትን በመረዳት ላይ የተመስረተው እምነት ነው። አንድ አማኝ ወላጅ ለልጁ እግዚአብሄር ለእስራኤል ለቤተስብ አላማ እንዳለው ማስረዳትና እግዚአብሄር እንዴት ከስራት እንዳወጣቸውና እንዳዳናቸው ማስተማር ያስፈልጋል። ልጅም ከዚህ ተነስቶ እንዴት እንደሚያምንና እንደሚጸልይም ማስተማር ተገቢ ነው። በዚህ ላይ ማንኛውም የቤተስብ አባል የእግዚአብሄርን መንገድ መከተል አስፈላጊ እንደሆነም አጥንክሮ ማመልከት ነው። ልጅ ምርጫ አይስጠውም ማለት ነው። ይህም ማለት ልጁን ወደዚህ እምነት ካደረስ በህዋል ስለልጁ በእግዚአብሄር ፊት ልመና ወይም ጸሎት አያደርግለትም ነጻ ያደርገዋል ማለት አይደለም ስለዚህ አማኝ ወላጅ የቃል ኪዳን አምላክ ለሆነው በጸሎት ስለልጁ ልመናውን ያቀርባል በጸሎትም ውስጥ የእግዚአብሄር የማዳን ሃይል ለርሱና ለልጁ እንዲሁም ለቤተስቡ እንደሆነ በእምነት የርሱ እንደሆነ ይቆጥረዋል።
የወላጅ ተፈጥሮአዊ ሕብረት
እግዚአብሄር ቤተስብን ለአላማው የሚጠቀምበት ሌላ መንገድ አለው። ይህም በወላጅና በልጅ መካከል ባለው ተፈጥሮአዊ ህብረት  ላይ ነው። በተፈጥሮ ወላጅና ልጅ አንድ ናቸው ሊለያይ በማይችል ቀርበት ባለው ክብር በሆነው ህብረት ላይ የተመስረተ ነው። ልጅ ሕይወት ያገኘው ከወላጅ አባቱ ነው አባት ልጁን እንደራሱ አካል ይመለከተዋል። አጥንቱ ከአጥንቱ ሥጋው ከሥጋው ነው  ልጁን አባት ይወዳል እንዲሁም ደስ የሚያስኘውን ለልጁ ያደርጋል። እናትም እንደዚሁ። የአባት ፍቅር በተፈጥሮውም እንክዋን ልጁ ደስተኛ እንዲሆን ይፈልጋል በዚህም ምክንያት ዘወትር ልጁን ደስ ለማስኘት መስዋዕትነት ያደርጋል። እግዚአብሄር በዚህ ፍቅር ውስጥ ነው ከወላጅ ጋር ቃል ኪዳን የሚያደርገው ይህም የወላጅነት ቃል ኪዳን በወላጅነት ፍቅር ላይ የተመስረተ ስለሆነ አንድን አማኝ ወላጅ ለልጁ ስለእግዚአብሄር ጸጋ መስካሪ እንዲሆን ብቁ ያደርገዋል። በወላጅ ፍቅር ውስጥ ደግሞ ወላጅ ወደራሱ ሃሳብ ለማምጣት የሚያስችለው ነው። በዚህም ደግሞ እንደወላጅ የልጁ ደካማ ባህሪው እራሱን ያለመቻሉ ይበልጡኑ በቤተስብ ወይም በወላጅ ላይ ጥገኛ ያደርገዋል። የራሱን ሃሳብ ብቻ ማከናወን ሳይሆን ይበልጡኑ እንደወላጁ ሃሳብና ፈቃድ ይሆናል።
የልጅነት ባህሪያት የሚቀረጸው በልጆች ህይወት ውስጥ ተመስጦአዊ ነገር ሲከናወን ባዩ ጊዜ ነው ይህ ተመስጦ (መሳብ) ሊመጣ የሚችለው ወላጆች ከልጆቻቸው ጋር የማያቅዋርጥ የግዋደኝነት ግንኙነት ሲኖራቸው ነው። ይህም እየቀጠለ ሲሄድ ጥልቀት ያለውና የማያቅዋርጥ ይሆናል በዚህ ጊዜ የልጁ ፍቅር በወላጁ ህይወት ውስጥ ያደገ ይሆናል ስለዚህ የልጁና የወላጁ ፍቅር በተመጣጣኝ ደረጃ ላይ ያስቀምጠዋል።  ጥሩ ጓደኛ መሆንና እንደ ልብ መወያየት - ከልጆቻችሁ ጋር ጊዜ ማሳለፍ በመካከላችሁ የቀረበ ትስስር እንዲፈጠር ያስችላል። ከዚህም በላይ ሐሳባቸውን የመግለጽ ችሎታቸውን ያዳብርላቸዋል። ቅዱሳን ጽሑፎች በቤት ውስጥም ሆነ በሌሎች ቦታዎች አመቺ በሆኑ ጊዜያት እንዲህ ያለው ቅርርብ እንዲኖር ያበረታታሉ።ዘዳግም 6:6, 7፤ 11:18-21
የሕፃናት አስተዳደግ ባለሞያዎች ወላጆች ከልጆቻቸው ጋር የሚያሳልፉት ጊዜ ውድ ከሆኑ መጫወቻዎች ወይም ከማንኛውም ዓይነት እንቅስቃሴ የበለጠ አስፈላጊ እንደሆነ ይስማማሉ። ብዙ ወጪ የማይጠይቁ የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴዎች ከልጆቻችሁ ጋር አስደሳች ጊዜ እንድታሳልፉ ያስችሏችኋል። ለምሳሌ ወላጆች ከልጆቻቸው ጋር ሆነው ተፈጥሮን ለማየት ወደ መናፈሻዎች ቢሄዱ ልጆቻቸውን ትርጉም ያላቸው ጥያቄዎች ለመጠየቅና ሐሳባቸውን አውጥተው እንዲናገሩ ለማበረታታት ጥሩ አጋጣሚ ሊከፍትላቸው ይችላል።
መጽሐፍ ቅዱስ “ለጭፈራም ጊዜ አለው” ይላል። (መክብብ 3:1, 4) አዎን፣ አንድ ልጅ በአእምሮ፣ በስሜትና ከሌሎች ጋር ተግባብቶ በመኖር ረገድ የተሟላ እድገት እንዲያደርግ በነፃነት የሚጫወትበት ጊዜ ሊኖረው ይገባል። የልጆች አስተዳደግ በለሙያዎች የሚሉት ጨዋታ ጠቃሚ ብቻ ሳይሆን የግድ አስፈላጊም ነው። “ልጆች የአንጎላቸውን የነርቭ አውታሮች ለተለያዩ ተግባራት የሚያዘጋጁበት ዋናው መንገድ በሚጫወቷቸው ጨዋታዎች አማካኝነት ነው” ብለዋል። አንድ ልጅ ራሱ በሚፈጥራቸው ጨዋታዎች የሚጠቀምባቸው መጫወቻዎች እንደ ባዶ ካርቶን ያሉ ቀላል ነገሮች ሊሆኑ ይችላሉ። ጉዳት የማያስከትሉ ተራ የቤት ውስጥ ቁሳቁሶች በጣም ውድ የሆኑ መጫወቻዎችን ያህል ያስደስቱታል።*
ልጆችን ትላልቅ ሰዎች በሚያዘጋጁዋቸው በርካታ እንቅስቃሴዎች ማጨናነቅ የፈጠራ ችሎታቸውን ይገድብባቸዋል። ልከኝነት አስፈላጊ ነው። ልጃችሁ የራሱን ዓለም እንዲመረምርና አቅሙንና ችሎታውን እንዲፈትን ፍቀዱለት። አንድ ልጅ አብዛኛውን ጊዜ ራሱን የሚያዝናናበት እንቅስቃሴ አያጣም። እንዲህ ሲባል ግን ልጃችሁ በራሱ ላይ ጉዳት እንዳያደርስ ምን እንደሚያደርግና የት እንደሚጫወት የማወቅ ኃላፊነት የለባችሁም ማለት አይደለም።
እግዚአብሄር ከሚጠቀምባቸው መሳሪያዎች ናቸው ብለን ከምናስባቸው ሁሉ እግዚአብሄር የልጅና የወላጅን ተፈጥሮአዊ ህብረት ሲጠቀምበት በጣም ያማረና አስደናቂ ወጤት የሚያመጣ ሆኖ ተገኝትዋል። አማኝ ወላጅ የእግዚአብሄር ፍቅርና ጸጋ ተካፋይ ከመሆኑም  ሌላ በረከትና የተስፋው የመንፈስ ቅዱስ ቃልኪዳን ተካፋይ ስለሆነ ይህ በጎ የእግዚአብሄር ሃሳብ ለልጁም እንደሆነ በእምነት ይቀበላል። በዚህን ጊዜ አማኝ ወላጅ ውስጥ ባለው የፍቅር ሃይል ሳቢያ እግዚአብሄር የቤተስብን ህይወት ማጥመጃና ልጁን ወደ እግዚአብሄር ማምጫ ታላቅ ሥራ የሚከናውነበት አድርጎታል። ይህ ደግሞ በምድር ላይ እውነተኛና አስደናቂ ምሳሌ የተስጠበትና የእግዚአብሄር ጸጋ በምድር የተገለጠበት አድርጎታል።


0 comments:

Post a Comment