Wednesday, May 16, 2018

ከመሪዎች ሁሉ የላቀ መሪ

ከመሪዎች ሁሉ የላቀ መሪ

አንድ ስው ደራሲና ገጣሚ ነበር፤ በሚኖርበትም ሀገር የታወቀ ነው፤ የወደፊቱ ጊዜ ለሁሉም ሰው ጥሩ ነገር እንደሚያመጣ ብሩህ ተስፋ ነበረው። ከ90 ዓመት ገደማ በፊት “አእምሮ ከፍርሃት የሚላቀቅበትንና ሰዎች አንገታቸውን ቀና አድርገው የሚሄዱበትን፣ እውቀት በነፃ የሚገኝበትን፣ ዓለም በብሔራዊ ድንበሮች የማትከፋፈልበትን፣ እውነት የሚነገርበትን [እና] ሰዎች ያላሰለሰ ጥረት በማድረግ በሚሠሯቸው ነገሮች ከጊዜ ወደ ጊዜ ይበልጥ ወደ ፍጽምና መቅረብ የሚችሉበትን” ዓለም በዓይነ ህሊናው ተመልክቶ ነበር።

ከዚያም ደራሲው የአገሩም ሆነ የተቀረው የዓለም ሕዝብ አንድ ቀን ይህን በመሰለ ቦታ እንደሚኖሩ ያለውን ተስፋ ገለጸ። የኖቤል ተሸላሚ የሆነው ይህ ገጣሚ ዛሬ በሕይወት ቢኖር ኖሮ ከፍተኛ ሐዘን እንደሚሰማው ምንም አያጠራጥርም። ዓለም ከፍተኛ እድገትና መሻሻል ብታሳይም ከመቼውም ጊዜ ይበልጥ ተከፋፍላለች። እንዲሁም የሰው ልጅ የወደፊት ተስፋ በአጠቃላይ ጨልሟል።

አንድ ገበሬ በሚኖርበት አገር ውስጥ በተወሰኑ አንጃዎች መካከል በድንገት ግጭት ሊፈጠር የቻለው ለምን እንደሆነ ሲጠየቅ መንስኤ ይሆናል ብሎ ያሰበውን አንድ ምክንያት ጠቅሷል።ችሎታ ያላቸው መሪዎች በመጥፋታቸው ነውሲል ተናግሯል። የታሪክ ምሁር የሆኑት  ሁሉ የሚስነዝሩት ሃሳብ የተካሄደው የዘር ማጥፋት ወንጀል ሳይታሰብ የፈነዳ የጎሳ ጥላቻ አይደለም። ከዚህ ይልቅ ሥልጣን ላይ መቆየት የፈለጉ ሰዎች ያቀነባበሩት ሴራ ነውሲሉ ተመሳሳይ አስተያየት ሰጥተዋል።

በአንዳንድ አገሮች መሪዎች በሙስና በመከሰሳቸው ምክንያት ሥልጣናቸውን በገዛ ፈቃዳቸው ለመልቀቅ ተገድደዋል። እንግዲያው ዓለም በተለያዩ ምክንያቶች የተነሳ የአመራር ቀውስ እንደደረሰበት በግልጽ ማየት ይቻላል። 2, 600 ዓመታት ገደማ በፊት የኖረ አንድ ነቢይ የተናገራቸው ቃላት እውነት መሆናቸውን ሁኔታዎች ይመሰክራሉ። ነቢዩየሰው መንገድ ከራሱ እንዳይደለ አውቃለሁ፣ አካሄዱንም ለማቅናት ከሚራመድ ሰው አይደለምሲል ተናግሯል።ኤርምያስ 10:23

በአሁኑ ጊዜ በዓለም ላይ የሚታየው ችግር መፍትሔ ይኖረዋል? ሰብዓዊ ኅብረተሰብ በግጭት መከፋፈሉ ወደሚያቆምበት እና ከፍርሃት ወደሚላቀቅበት፣ እውነተኛ እውቀት በነፃና እንደ ልብ ወደሚገኝበት እንዲሁም ሰዎች ፍጹም ወደሚሆኑበት ዓለም የሰው ልጆችን ሊያስገባ የሚችለው ማን ነው?

አንድ የህብረተስብ ጥናት ያጠኑ ስው የሰጡት ሐሳብ ሕዝቡ ነገሮችን ለማስተካከል ከልባቸው የሚጥሩና ችሎታ ያላቸው መሪዎች እንደሚፈልግ ቁልጭ አድርጎ ያሳያል። ከምርጫ ዘመቻ ጋር የተያያዘ ሥራ የሚሠሩ አንዲት ሴት ሁኔታውን እንዲህ ሲሉ ገልጸውታል፦ሰዎች ፕሬዚዳንት ሲመርጡ ሕይወታቸውን፣ የወደፊት ተስፋቸውንና ልጆቻቸውን በአደራ የሚሰጡት ሰው እየመረጡ ነው።እንደዚህ ያለውን አደራ መወጣት ደግሞ ከባድ ኃላፊነት ነው። እንዲህ የምንለው ለምንድን ነው?

ዓለማችን መፍትሔ የሚገኝላቸው በማይመስሉ ችግሮች የተሞላ ነው። ወንጀልንና ጦርነትን ለማስወገድ የሚያስችል ብልሃትም ሆነ ኃይል ያለው የትኛው መሪ ነው? በዛሬው ጊዜ ካሉት መሪዎች መካከል ሁሉም ሰው ምግብ፣ ንጹሕ ውኃና ሕክምና እንዲያገኝ ለማድረግ የሚያስፈልገው አቅምም ሆነ ርኅራኄ ያለው ማን ነው? አካባቢያችንን ለመንከባከብና ወደ ቀድሞ ሁኔታው ለመመለስ የሚያስፈልገው እውቀትም ሆነ ቁርጠኝነት ያለው ማን ነው? የሰው ዘር በሙሉ ደስተኛ ሆኖ ለረዥም ዘመን እንዲኖር ለማድረግ ብቃቱም ሆነ ኃይሉ ያለው የትኛው ገዢ ነው?

1940 በብሪታንያ ፓርላማ ውስጥ አመራርን በተመለከተ ውዝግብ ተነስቶ ነበር። በስብሰባው ላይ ከነበሩት ሰዎች መካከል ብሪታንያ በአንደኛው የዓለም ጦርነት ወቅት ድል እንድትቀዳጅ ያስቻሏት የሰባ ሰባት ዓመቱ አረጋዊ ዴቪድ ሎይድ ጆርጅ ይገኙበታል። እኚህ ሰው ለረዥም ዓመታት ከፖለቲካዊ ጉዳዮች ጋር የተያያዘ ሥራ በማከናወናቸው የባለ ሥልጣናቱን ሥራ ለመገምገም ብቃት ነበራቸው። ግንቦት 8 በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ውስጥ ባቀረቡት ንግግር እንዲህ ብለዋል፦ሕዝቡ ጥሩ መሪ እስካገኘ፣ ብሔሩን የሚመሩት ሰዎች አቅማቸው የፈቀደውን ሁሉ እያደረጉ እንደሆነ እርግጠኛ መሆን እስከቻለና መንግሥት ዓላማውን በግልጽ እስካስቀመጠ ድረስ ማንኛውንም መሥዋዕትነት ለመክፈል ዝግጁ ነው።

እርግጥ ነው፣ አንዳንድ መሪዎች በተወሰነ መጠን እንደተሳካላቸው አይካድም። ሆኖም የሥልጣን ዘመናቸው በዛ ቢባል ከጥቂት አሥር ዓመታት የማያልፍ ከመሆኑም በላይ በእነርሱ እግር የሚተካው መሪ ማን እንደሚሆን አይታወቅም። በምድር ላይ ከኖሩት መሪዎች ሁሉ በችሎታው ተወዳዳሪ የሌለው የጥንቷ እስራኤል ንጉሥ ሰሎሞን ይህ ጉዳይ አሳስቦት ነበር። እንዲህ ብሏል፦ከፀሓይ በታች የደከምሁበትን ነገር ሁሉ ጠላሁት፣ ከኋላዬ ለሚመጣው የግድ እተውለታለሁና። እርሱ ጠቢብ ወይም ሞኝ ይሆን እንደ ሆነ ማን ያውቃል? ሆኖም ከፀሓይ በታች ድካሜንና ችሎታዬን ባፈሰስሁበት ሥራ ሁሉ ላይ ባለቤት ይሆንበታል፤ ይህም ደግሞ ከንቱ ነው።” መክብብ 2:18 19

ሰሎሞን ቀጣዩ ንጉሥ እርሱ ሲያከናውን የኖረውን መልካም ሥራ ይግፋበት ወይም ያበላሸው ማወቅ አይችልም ነበር። በእርሱ አመለካከት የቀድሞ መሪዎችን በአዲሶች እየተኩ የማለፉ ሂደትከንቱነበር። ሌሎች የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞች ይህንን ሁኔታእርባና ቢስወይምትርጉም የለሽብለውታል።

ከፍተኛ ግምት የሚሰጣቸው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት የነበሩት አብርሃም ሊንከን በአንድ ወቅት እንዲህ ብለው ነበር፦ለአጭር ጊዜም ቢሆን አስፈላጊ የሆነ ሥራ እንዳከናውን መርጣችሁኛል፤ አሁን በእናንተ ዘንድ ከፍተኛ ተሰሚነት ያለኝ ቢሆንም ብዙም ሳይቆይ እንደማጣው የታወቀ ነው።እውነትም ደግሞ የሥልጣን ዘመናቸው አጭር ነበር። ፕሬዚዳንት ሊንከን ሕዝቡን ለማገልገል ብዙ ከመድከማቸውም በላይ ሊያከናውኗቸው የሚፈልጓቸው በርካታ ነገሮች ቢኖሩም አገራቸውን መምራት የቻሉት ለአራት ዓመታት ብቻ ነው። ለሁለተኛ ጊዜ ተመርጠው ሥራቸውን እንደጀመሩ የአመራር ለውጥ በፈለገ አንድ ሰው ተገደሉ።

የተዋጣላቸው የተባሉት ሰብዓዊ መሪዎችም እንኳ ስለ ራሳቸው ሕይወት እርግጠኞች መሆን አይችሉም። ታዲያ ለእነዚህ መሪዎች ሕይወትን ያህል ነገር በአደራ ሊስጣቸው ይገባልን? መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል፦በገዦች አትታመኑ፤ ማዳን በማይችሉ ሥጋ ለባሾችም አትመኩ። መንፈሳቸው ትወጣለች፤ ወደ መሬታቸውም ይመለሳሉ፤ ያን ጊዜም ዕቅዳቸው እንዳልነበር ይሆናል።መዝሙር 146:3 4

በሰብዓዊ መሪዎች እንዳንታመን የተሰጠንን ምክር መቀበል ይከብደን ይሆናል። ሆኖም መጽሐፍ ቅዱስ የሰው ዘር ብቃት ያለውና አስተማማኝ መሪ ጨርሶ አያገኝም አይልም። ኢሳይያስ 32:1 “እነሆ፤ ንጉሥ በጽድቅ ይነግሣልይላል። የሰው ዘር ፈጣሪ የሆነው ይሖዋ አምላክ በቅርቡ ምድርን ሙሉ በሙሉ የሚቆጣጠራትንጉሥወይም መሪ አዘጋጅቷል። ይህ መሪ ማን ነው? የመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢት መልሱን ይሰጠናል።

ከሁለት ሺህ ዓመታት በፊት አንድ መልአክ ማርያም ለተባለች አንዲት አይሁዳዊት ወጣት እንዲህ ብሏት ነበር፦ትፀንሻለሽ፤ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ፤ ስሙንም ኢየሱስ ትዪዋለሽ። እርሱም ታላቅ ይሆናል፤ የልዑል ልጅም ይባላል፤ ጌታ አምላክ የአባቱን የዳዊትን ዙፋን ይሰጠዋል፤ በያዕቆብም ቤት ላይ ለዘላለም ይነግሣል፤ ለመንግሥቱም ፍጻሜ የለውም።” (ሉቃስ 1:31-33) ይህ ትንቢት የተነገረለት ንጉሥ የናዝሬቱ ኢየሱስ ነው።

ሃይማኖታዊ ሥዕሎች በአብዛኛው ኢየሱስን እንደ ሕፃን፣ ደካማና ኮስማና እንደሆነ ሰው ወይም ምንም ነገር ቢያጋጥመው በቀላሉ እጁን እንደሚሰጥ ባሕታዊ አድርገው ያቀርቡታል። እነዚህ ምስሎች በኢየሱስ መሪነት እንድንተማመን አያደርጉም። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተገለጸው እውነተኛው ኢየሱስ ክርስቶስ ብርቱና ኃያል አምላክ ነው። ለመሪነት ብቁ የሚያደርጉት ሌሎች ባሕርያትም አሉት። (ሉቃስ 2:52) ግሩም ከሆኑት ባሕርያቱ መካከል ጥቂቶቹ ከዚህ ቀጥሎ ቀርበዋል፦

ሕይወቱን ሙሉ በሙሉ የተስጠ ነበር። ከእግዚአብሄር የተሰጠውን ሥራ ለማከናወን ቆርጦ ስለነበር የሰዎችም ሆነ የአጋንንት ተቃውሞ ወደኋላ እንዲል አላደረገውም። የኃይል ጥቃት ቢሰነዘርበትም አልፈራም። (ሉቃስ 4:28-30) ድካምና ረሃብ ተስፋ አላስቆረጡትም። (ዮሐንስ 4:5-16 31-34) ወዳጆቹ ጥለውት ቢሸሹም ከዓላማው ፈጽሞ ወደኋላ አላለም። ማቴዎስ 26:55 56 ዮሐንስ 18:3-9
ፈጽሞ ነቀፋ የሌለበት ሰው ነበር። ሐቀኛና መልካም ምግባር ያለው ሰው ስለነበር ጠላቶቹ በማስረጃ ሊከሱት ይችሉ እንደሆነ በሕዝብ ፊት ቢጠይቃቸውም አንዳች እንከን አላገኙበትም። (ዮሐንስ 8:46) ትምህርቶቹ ከግብዝነት የራቁ በመሆናቸው ቅን ልብ ያላቸው ብዙ ሰዎች ተከታዮቹ ሆነዋል። ዮሐንስ 7:46 8:28-30 12:19

ለሰዎች በጥልቅ ስለሚያስብላቸው የተራቡ ሰዎችን መግቧል። (ዮሐንስ 6:10 11) የተጨነቁትን አጽናንቷል። (ሉቃስ 7:11-15) ማየትና መስማት የተሳናቸውን እንዲሁም ሌሎች የጤና እክሎች ያሉባቸውን ሰዎች ፈውሷል። (ማቴዎስ 12:22 ሉቃስ 8:43-48 ዮሐንስ 9:1-6) ጠንክረው ይሠሩ የነበሩትን ሐዋርያቱን አበረታቷቸዋል። (ዮሐንስ ምዕራፍ 13 እስከ 17) በጎቹን የሚንከባከብመልካም እረኛነበር።ዮሐንስ 10:11-14

ለሥራ አይለግምም። ኢየሱስ ለሐዋርያቱ አንድ አስፈላጊ ትምህርት ለመስጠት ሲል እግራቸውን አጥቧቸዋል። (ዮሐንስ 13:4-15) አቧራማ በሆኑት የእስራኤል መንገዶች እየተዘዋወረ ይሰብክ ነበር። (ሉቃስ 8:1) “ወደ አንድ ገለልተኛ ስፍራሄዶ ለማረፍ ባሰበበትም ጊዜ እንኳ ሕዝቡ እንዲያስተምራቸው ፈልገው ወደ እርሱ ሲመጡ ተቀብሏቸዋል። (ማርቆስ 6:30-34) ስለዚህ በትጋት ረገድ ለሁሉም ክርስቲያኖች የሚሆን አርዓያ ትቷል። 1 ዮሐንስ 2:6

ኢየሱስ አገልግሎቱን ፈጽሞ ወደ ሰማይ ሄዷል። እግዚአብሄር አምላክ ለዚህ የታማኝነት አቋሙ በሰማይ ንጉሥ ያደረገው ከመሆኑም በላይ ያለመሞትን ባሕርይ አላብሶታል። መጽሐፍ ቅዱስ ከትንሣኤው በኋላ ኢየሱስ ስላገኘው ሕይወት ሲናገርክርስቶስ ከሙታን ተነሥቶአልና፣ ዳግመኛ እንደማይሞት እናውቃለንና፤ ሞት ከእንግዲህ በእርሱ ላይ ጉልበት አይኖረውምይላል። (ሮሜ 6:9) ኢየሱስ የሰው ዘር ሊያገኛቸው ከሚችላቸው ከመሪዎች ሁሉ የላቀ መሪ መሆኑን እርግጠኛ መሆን ችለናል። ኢየሱስ ክርስቶስ አንድ ጊዜ ምድርን ሙሉ በሙሉ ከተቆጣጠራት በኋላ ሌላ ሰው መሾምም ሆነ የአመራር ለውጥ ማድረግ አያስፈልግም። ማንም እርሱን በመግደል ከሥልጣኑ ሊያፈናቅለው አይችልም፤ እንዲሁም ችሎታ የጎደለው መሪ በእርሱ እግር ተተክቶ ያከናወነውን መልካም ሥራ ሊያበላሽበት አይችልም።
መዝሙር 72 ፍጹም የሆነውና ያለመሞትን ባሕርይ የተላበሰው ይህ መሪ እንዴት እንደሚገዛ የሚገልጽ ትንቢታዊ ዘገባ ይዟል። በቁጥር 7 እና 8 ላይ እንዲህ ይላል፦በዘመኑ ጽድቅ ይሰፍናል፤ ጨረቃ ከስፍራዋ እስከምትታጣ ድረስም ሰላም ይበዛል። ከባሕር እስከ ባሕር ድረስ፣ ከታላቁም ወንዝ እስከ ምድር ዳርቻ ይገዛል።ለሰው ልጆች ጥቅም በሚያስገኘው የግዛት ዘመኑ ወቅት የምድር ነዋሪዎች ሕይወት ዘላለማዊና የተረጋጋ ሁኔታ የሰፈነበት ይሆናል። በምድር ላይ የሚገኙ መሣሪያዎችን በሙሉ የሚያጠፋ ከመሆኑም በላይ ሰዎች ግጭት የመፍጠር ፍላጎት እንኳ እንዳይኖራቸው ያደርጋል። ዛሬ እንደተራበ አንበሳ ወይም እንደተቆጣ ድብ ሌሎችን የሚያጠቁ ሰዎች አመለካከታቸው ሙሉ በሙሉ ይለወጣል። (ኢሳይያስ 11:1-9) በምድር ሁሉ ላይ ሰላም ይሰፍናል።

መዝሙር 72 ከቁጥር 12 እስከ 14 አክሎ እንዲህ ይላል፦ችግረኛው በጮኸ ጊዜ፣ ምስኪኑንና ረዳት የሌለውን ይታደገዋል። ለድኾችና ለችግረኞች ይራራል፤ ምስኪኖችንም ከሞት ያድናል። ሕይወታቸውን ከጭቈናና ከግፍ ያድናል፤ ደማቸውም በእርሱ ፊት ክቡር ነው።በንጉሡ በኢየሱስ ክርስቶስ ግዛት ሥር ችግረኞች፣ ድኾችና ምስኪኖች የአንድ ደስተኛ ሰብዓዊ ቤተሰብ አባላት ሆነው በኅብረት ይኖራሉ። ሕይወታቸው በሥቃይና በተስፋ መቁረጥ የተሞላ መሆኑ ይቀርና ደስተኞች ይሆናሉ። ኢሳይያስ 35:10

ቁጥር 16 ደግሞበምድሪቱ ላይ እህል ይትረፍረፍ፤ በተራሮችም አናት ላይ ይወዛወዝይላል። ዛሬ በምድር ላይ የሚኖሩ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ይራባሉ። አብዛኛውን ጊዜ በፖለቲካና በስግብግብነት ምክንያት ምግብ በተገቢው መንገድ ለሁሉም አይዳረስም። በዚህም የተነሳ ሥፍር ቁጥር የሌላቸው ሰዎች በተለይም ልጆች በረሃብ ይሞታሉ። በኢየሱስ ክርስቶስ አገዛዝ ሥር ግን ይህ ችግር ይወገዳል። ምድር ጣፋጭ የሆኑ ምግቦችን አትረፍርፋ ስለምትሰጥ የሰው ዘር በሙሉ ጠግቦ ያድራል።

ችሎታ ያለው መሪ የሚያመጣቸውን እነዚህን በረከቶች ማግኘት እንፈልጋለን፤ ከሆነ በቅርቡ ምድርን ሙሉ በሙሉ ስለሚቆጣጠረው መሪ እንድትማሩ አብረታታችህዋለሁ።

አብዛኛውን ጊዜ አንድ መሪ በአገሩ ውስጥ በተወሰነ መጠንም ቢሆን ሰላምና አስተማማኝ የኑሮ ሁኔታ እንዲሰፍን ካደረገ ዜጎቹ እንደሚያከብሩትና እንደሚደግፉት ሊጠብቅ ይችላል። ይሁን እንጂ በሆነ ምክንያት ሕዝቡ በእርሱ ላይ እምነት ካጣ ብዙም ሳይቆይ ሥልጣኑን ለሌላ ያስረክባል። አንዳንድ ጠንካራ መሪዎች በድንገት ሥልጣናቸውን እንዲያጡ ካደረጓቸው ምክንያቶች ጥቂቶቹ ለአብነት ያህል ከዚህ ቀጥሎ ቀርበዋል።

ሕዝቡ በኑሮው አለመርካቱ። 18ተኛው መቶ ዘመን መገባደጃ አካባቢ አብዛኞቹ የፈረንሳይ ዜጎች ከፍተኛ ቀረጥ እንዲከፍሉ ይገደዱ የነበረ ከመሆኑም በላይ በአገሪቱ የምግብ እጥረት ነበር። እነዚህ ችግሮች ለፈረንሳዩ አብዮት መፈንዳት ምክንያት ሆኑና ንጉሥ ሉዊ 16ተኛ 1793 አንገታቸው በጊሎቲን ተቀንጥሶ ተገደሉ።

ጦርነት። አንደኛው የዓለም ጦርነት በታሪክ ውስጥ ኃያል ለሚባሉ አንዳንድ ንጉሠ ነገሥታት ከሥልጣን መፈናቀል ምክንያት ሆኗል። ለምሳሌ ያህል በቅዱስ ፒተርስበርግ፣ ሩስያ በጦርነት ሳቢያ በተከሰተው ረሃብ የተነሳ 1917 የየካቲቱ አብዮት ፈነዳ። ይህ ዓመጽ የሩስያው ዛር ዳግማዊ ኒኮላስ ከዙፋናቸው እንዲወርዱ ያደረገ ሲሆን በምትኩ ኮሚኒስቶች ሥልጣን ያዙ። በኅዳር ወር፣ 1918 ጀርመን ሰላም እንዲወርድ ትፈልግ የነበረ ቢሆንም የሕብረ ብሔሩ ጦር ግን የአመራር ለውጥ እስኪደረግ ድረስ ውጊያውን አላቆመም። በውጤቱም የጀርመኑ ንጉሠ ነገሥት ዳግማዊ ቪልኸልም ወደ ኔዘርላንድ ለመሰደድ ተገደዱ።  የፖለቲካው ሥርዓት እንዲለወጥ መፈለግ። 1989 የምዕራቡንና የምሥራቁን ዓለም ከፍሎ የነበረው የብረት መጋረጃ ሲገለጥ እንደ ዓለት የጠነከሩ የሚመስሉ መንግሥታት ዜጎቻቸው ኮሚኒዝምን ትተው ለየት ያሉ ሥርዓቶችን በማቋቋማቸው ፈራረሱ።

መንበሩን ልቀቅና ውረድ፤ የአንተ ነገር በቅቶናል። በፈጣሪ ስም እለምንሃለሁ፣ ሂድልን!”—የብሪታንያ ፓርላማ አባል የነበሩት ሊየፖልድ አሜሪ የኦሊቨር ክሮምዌልን አባባል ጠቅሰው የተናገሩት

ሁለተኛው የዓለም ጦርነት ከተጀመረ ስምንት ወራት ያስቆጠረ ሲሆን በዚህ ጊዜ ውስጥ ከፍተኛ ውድመት አድርሷል። አዝማሚያው ሲታይ ብሪታንያና ተባባሪዎቿ በጦርነቱ ድል ማድረግ የሚችሉ አይመስልም። ሊየፖልድ አሜሪና በሥልጣን ላይ የሚገኙ ሌሎችም የአመራር ለውጥ እንደሚያስፈልግ ተሰምቷቸዋል። በዚህም ምክንያት ግንቦት 7, 1940 ሚስተር አሜሪ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ኔቭል ቼምበርሊን በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ውስጥ ከላይ ያሉትን ቃላት ተናገሩ። ከሦስት ቀናት በኋላ ሚስተር ቼምበርሊን ሥልጣናቸውን የለቀቁ ሲሆን ዊንስተን ቸርችል በእርሳቸው እግር ተተኩ።

ከሰው ልጅ መሠረታዊ ፍላጎቶች አንዱ ጥሩ አመራር ማግኘት ቢሆንም ብቃቱን የሚያሟሉት ግን ሁሉም መሪዎች አይደሉም። በቤተሰብ ክልል ውስጥም እንኳ አንድ አባት ሚስቱና ልጆቹ ደስተኞች እንዲሆኑ ጥሩ መሪ መሆን አለበት። ከዚህ አንጻር የአንድ አገር ወይም የዓለም መሪ መሆን ምን ያህል ከፍተኛ ብቃት እንደሚጠይቅ መገመት ይቻላል! በመሆኑም ችሎታና አቅም ያላቸው መሪዎች ማግኘት በጣም አስቸጋሪ መሆኑ ምንም አያስገርምም። በዚህም ምክንያት በሺዎች ለሚቆጠሩ ዓመታትና ቁጥር ሥፍር ለሌላቸው ጊዜያት ነገሥታት ዘውድ ሲጭኑ፣ አብዮታዊ እንቅስቃሴና የመንግሥት ግልበጣ ሲካሄድ፣ መሪዎች ሲሾሙ፣ ምርጫ ሲደረግ፣ በሥልጣን ላይ ያሉ ሰዎች ሲገደሉ እንዲሁም የአገዛዝ ለውጥ ሲደረግ ቆይቷል። ነገሥታት፣ ጠቅላይ ሚኒስትሮች፣ ልዑላን፣ ፕሬዚዳንቶች፣ ዋና ጸሐፊዎች እንዲሁም አምባገነን መሪዎች የሥልጣን እርካብ ላይ ሲፈናጠጡና ሲወርዱ ኖረዋል። ኃያል የሚባሉት መሪዎችም እንኳ ባልተጠበቁ ለውጦች ሳቢያ ከሥልጣናቸው ተፈናቅለዋል።

ችሎታ  ያለው መሪ የማግኘቱ ጉዳይ ለብዙዎች ተስፋ አስቆራጭ መሆኑ አያስገርምም። በአንዳንድ አገሮች ሕዝቡ በተለይ በምርጫ ወቅት የግዴለሽነትና የተስፋ መቁረጥ ስሜት ይታይበታል። በአፍሪካ የሚገኝ ጄፍ ሂል የተባለ አንድ ጋዜጠኛ እንዲህ ብሏል፦ሰዎች በሥቃይ የተሞላ ሕይወታቸውን ለመለወጥ ምንም ማድረግ እንደማይችሉ ሲሰማቸው ቸልተኛ ይሆናሉ ወይም [በምርጫ ከመሳተፍ] ይታቀባሉ። . . . በአፍሪካ ውስጥ ሕዝቡ በምርጫ የማይካፈለው ባለው አገዛዝ ስለረካ ብቻ ላይሆን ይችላል። አብዛኛውን ጊዜ ችግራቸውን የሚረዳላቸው ወገን እንደሌለ የሚሰማቸው ሰዎች እርዳታ እንደሚፈልጉ የሚገልጹበት መንገድ ነው።

ሰብዓዊ መሪዎች የዜጎቻቸውን ፍላጎቶች ማሟላት አለመቻላቸው ችሎታ ያለው አመራር ፈጽሞ ማግኘት እንደማይቻል የሚጠቁም ነው? አይደለም። ከሁሉ የላቀ ብቃት ያለው አመራር አለ። የሚቀጥለው ርዕስ ለሰው ዘር ብቃት ያለው መሪ ማን እንደሆነና የዚህ መሪ አገዛዝ አንተን ጨምሮ በሚሊዮን የሚቆጠሩ የተለያዩ ሰዎችን የሚጠቅመው እንዴት እንደሆነ ያብራራል።


0 comments:

Post a Comment