ጤና በመጽሐፍ ቅዱስ አመለካከት
helth
(ሻሎም yeshu`ah,
'arukhah; riph'uth,' arukhah; soteria, hugiaino): ሻሎም በፍልስጤም
ሆነ በእስራኤል ውስጥ
አሁንም የተለመደ መደበኛ
የሰላምታ ክፍል ነው።
በዚህ መልኩ በዘፍጥረት
43:28፡ 2 ሳሙኤል 20 ላይ
ጥቅም ላይ ውሏል፤ ግንዱ
ቃል "ሰላም" ማለት
ነው እና ደህንነት,
ስኬት እና ጥሩ
የሰውነት ጤንነት ጋር
በተያያዘ አገላለጽን በተመለከተ
ብዙ ልዩ ልዩ
ጥቅም ላይ ይውላል
በተለይም ነፃ ወይም
እርዳታ መዝሙር
42:11 ላይ መዝሙር
43: 5 ላይ Yeshu`ah
እንዲሁም በመዝሙር 67:2 ውስጥ አሜሪካን
ስታንዳርድ ሪቫይዝድ ቨርዥን
ውስጥ "እርዳታ" ተብሎ
ተተርጉሟል።
Riph'uth "ፈውስ" ምሳሌ
3:8 ላይ ይገኛል።
Marpe 'ደግሞ
ሥጋ ፈውስ ማለት
ነው፤ ነገር ግን
ምሳሌ 4:22 ውስጥ አእምሮ
እና ሥነ ምግባር
ያለው ጤናማ አስተሳሰብ
ለማስፋፋት እንደ ምሳሌያዊ
በሆነ መንገድ ጥቅም
ላይ ውሏል ምሳሌ
12:18; ምሳሌ 13:17 ደግሞ የተሻሻለው
(ብሪታንያና አሜሪካ) ቨርዥን
እንዳስቀመጠው
በኤርምያስ 8:15 በምሳሌ 16:24 "ፈውስ" 'Arukhah ደግሞ
ኢሳይያስ 58:8 ውስጥ ተመሳሳይ
ምሳሌያዊ በሆነ መንገድ
ጥቅም ላይ ውሏል ኤርምያስ
8:22፤ ኤርምያስ 30:17 ትንቢተ ኤርምያስ
33: 6 ቃል በቃል "ጥገና
ወይም ወደ ነበረበት
መመለስ" ማለት ነው
ይህ ነህምያ (ምዕራፍ
4) የኢየሩሳሌም
ቅጥር ጥገና ላይ
የዋለው ቃል ነው።
"ጤና" የሚለው
ቃል በአዲስ
ኪዳን ውስጥ ሁለት
ጊዜ የሐዋርያት
ሥራ 27:34) ምግብ
መውሰድ ለሚጓዙት ቅዱስ
ጳውሎስ ይግባኝ ውስጥ
ተጠቅሶል ይህ ትምህርት
ቃል በቃል ሲተረጎም
"ደህንነት" ያላቸውን soteria ነው
ይላል ስለዚህ አሜሪካን
ስታንዳርድ ኪንግ ጄምስ
ቨርዥን "ጤና" ሐዋርያው
ሰላምታ ውስጥ
hugianino የሚለው
ቃል በ2ዮሐንስ 1:3 ጥቅም
ላይ ውሏል።
የስው ልጆችን መታመም በተመለከተ መጽሐፍ ቅዱስ መንስዔው ምንድነው ይላል?
“በአንድ ሰው በአዳም የተነሳ ኃጢአት ወደ ዓለም ገባ፤ በኃጢአትም ምክንያት ሞት መጣ” ሮም 5:12። ብዙዎች ስዎች በሽታ ሰው በዝግመተ ለውጥ ሲገኝ በአጋጣሚ የተከሰተ ችግር ነው ብለው ሲያምኑ፣ ሌሎች ደግሞ እንደ ክፉ መናፍስት ያሉ ሚስጥራዊ ኃይሎች የጤና መቃወስ እንደሚያስከትሉብን አድርገው ያስባሉ።
መጽሐፍ ቅዱስ፣ የምንታመመው የመጀመሪያዎቹ ባልና ሚስት አዳምና ሔዋን በእግዚአብሄር ላይ በማመፃቸው የተነሳ እንደሆነ ይናገራል (ሮም 5:12)። የመጀመሪያዎቹ ወላጆቻችን አዳምና ሔዋን በእግዚአብሄር ላይ ከማመፃቸው በፊት ፍጹም ጤንነት ነበራቸው። አፍቃሪ የሆነውን አምላክ እንክብካቤ ካጡ እንደሚሞቱ ያውቁ ነበር። (ዘፍጥረት 2:16, 17) ይሁንና ከእግዚአብሄር ጋር እንዲቆራረጡ የሚያደርጋቸው ሃጢያትን ፈጸሙ፤ በመሆኑም እግዚአብሄር ካስቀመጠላቸው ደረጃ ወይም መመሪያ ዝቅ አሉ ስለሆነም ችግር ውስጥ ገቡ ። ፍጽምናቸውን ያጡት የመጀመሪያዎቹ ወላጆቻችን ለእኛም ሃጢያትን አወረሱን። በመሆኑም የጤና እክሎችን ለማስወገድ የቱንም ያህል ጥረት ቢደረግ መታመማችን አይቀርም። እግዚአብሄር ያወጣቸውን ጥበብ የሚንጸባረቅባቸው መመሪያዎች በመታዘዝ ከእሱ ጋር እርቅ አንድ ስው ከመስረተ ወደፊት በኢሳይያስ 33:24፤ ራእይ 21:3- 4 እግዚአብሄር ሕመምን፣ በሽታንና ሞትን ለማስወገድ ቃል ገብቷል ጤንነትም ተገኝቶ መኖር እንደሚቻል መጽሐፍ ቅዱስ ያስተምራል።
ከላይ እንዳነሳሁት
በሽታ ወደ አለም
የገባው በሐጢያት የተነሳ
ሲሆን እተባባስ የሄደው
በሞራል ወድቀትና በድሎትና
በምቾት የተነሳ ነው።
የበሽታ ከተፈጥሮ መነሻዎቹ
ደግሞ
በእብራውያን
መካከል በክፉ መናፍስት
የተነሳ በሽታዎች በኢዮብ
2፡7 ማርቆ. 9፡17
ሉቃስ 13፡16 1 ቆር.
12፡7 ተጠቅስዋል። ሃይማኖተኛ
የሆኑት አይሆዳውያን ደግሞ
በሽታ በእግዚአብሔር እጅ
የሚላክ መሆኑን በመዝ.
39፡9-11 መዝ. 90፡3-12
ተጽፎል በነርሱ አስተሳስብ
በሁሉም ሁኔታ የተለዩ
በሽታዎች ወደ ስው
የሚላኩት ለቅጣት እንደሆነ
በአቤሜሌክ ግያዝ እዮብ
ኡዚያ ሚሪያም ሄሮድና
ፍልስጤማያን
ወዘተ ታሪካቸው
ያመለክታል።
በመጽሐፍ ቅዱስ
ጊዜ የታወቁት ህዝቦች
ፍልስጤምና ግብጻውያን ኢትዮጵያውያን
ወዘተ ነበሩ። የፍልስጤም
ሕብረተስብ በጥንት ጊዜ
ከግብጽም በበለጠ ጤነኛ
ሕብረተስብ የሚገኝበት ተብሎ
ይወስድ ነበር። የግብጽ
ሕብረተስብ ጤንነት በምን
አይነት ደርጃ ላይ
እንደነበረ (ዘዳግም 7፡15
ዘዳግም 28፡60 አሞጽ
4፡10) የተመለከቱት ጥቅሶች
ያመለክታሉ።
በእብራውያን
ህብረተስብ መካከል የጽዳቱ
ሥርዕትና በቀሳውስቱ የሚደረገው
ቁጥጥር የህዝቡ የጤና
ጥበቃው ወደ ክፍተኛ
ደርጃ አድርሶታል፤ ነገር
ግን ይኸው የጽዳቱ
ሥርዕትና ቁጥጥር በስፋት
የተራመደ አልነበረም፤ በመጽሐፍ
ቅዱስ ጊዜ
የነበሩት በሽታዎች ለጉዳት
የሚዳርጉ የስውነት ትኩሳቶች
የጠነከሩ የቆዳ በሽታዎች
ሽባነት ተቅማጥ የተለያዩ
የአይን በሽታዎች ሲሆኑ
እነዚህም በሽታዎች በበሽተኛው
ላይ መንፈሳዊና ሥነ-ልቡናዊ ጫና
ላይ ያስከትላሉ። በመጽሐፍ
ቅዱስ ጊዜ የነበሩት
በሽታዎች እየተባባሱ የሄዱበት
ወቅት ነበር ከነዚህም
መሃከል የተለያዩ የስውነት
ትኩሳቶች ተቅማጥ የቆዳ
ላይ ለምጽ ወይም
ቁምጥና የአንጀት ውስጥ
ትላትል መቅስፍት የነርቭ
በሽታዎች (እንደሽባነት) የተለያዩ
የአይን በሽታዎች እነዚህም
በተለያዩ ስሞች ተስጥቷቸዋል።
እነዚህም ስሞች ሕመም
ወይም ደዌ በሽታ
ሥቃይ ሲሆኑ እነዚህም
2 ነገስት 1፡2
2 ነገሥት
8፡8 ማቴ. 9፡35
ማቴ. 8፡17 ዮሐ.
5፡4 ሉቃ. 7፡21
መዝ. 38፡7 ተመልክተዋል።
በአሁንም ዘመን ስድስት ተላላፊ በሽታዎች የተነሳ ከሚሞቱ ሰዎች መካከል 90% ምክንያት ኤች አይ ቪ / ኤድስ የተቅማጥ በሽታ ሳንባ ነቀርሳ ወባ እና ኩፍኝ አጣዳፊ የመተንፈሻ ኢንፌክሽን (ሞት ሊያስከትል ይችላል)ተላላፊ በሽታዎች በአብዛኛው እነዚህ በሽታ-አምጪ ጀርሞች ባክቴሪያዎች ቫይረሶች ፈንገሶች protozoans, እና ጥገኛ ትሎች ውስጥ የተለያዩ ያካትታሉ።
ከተባሉትም ሌላ ጥንትም
ሆነ አሁን የሰውን
ዘር የሚያጠቁ አብዛኞቹ
በሽታዎች እንደ ፍርሃት፣
ሐዘን፣ ቅናት፣ ብስጭት፣
ጥላቻና የጥፋተኝነት ስሜት
ከመሳሰሉ ስሜታዊ ውጥረቶች
እንደሚመነጩ ይታመናል። ከዚህ
አንፃር ‘እግዚአብሄርን መፍራት’
“ለሥጋህ ፈውስ ለአጥንትህም ጠገን” ነው
የሚለው የመጽሐፍ ቅዱስ
አነጋገር ያጽናናል ምሳሌ 3:7, 8። አጥንት የሰውነት ምሰሶ
ነው። በመሆኑም መጽሐፍ
ቅዱስ አንድን ሰው
በተለይም ጥልቅ በሆኑ
ስሜቶች የሚነካውን የአንድን
ሰው ውስጣዊ ማንነት
ለማመልከት “አጥንት” የሚለውን
ቃል በምሳሌያዊ አነጋገር
ይጠቀምበታል። ሆኖም እግዚአብሄርን
መፍራት “ለስውነትህ ፈውስ”
የሚሆነው እንዴት ነው? እግዚአብሄርን መፍራት
የጥበብ መንገድ ነው።
ከእግዚአብሄር የአቋም ደረጃዎች
ጋር ተስማምቶ መኖር
አሁንም ቢሆን በአካል
ጤነኞች እንድንሆን ሊረዳን
ይችላል። ከዚህም በላይ
የእግዚአብሄር ሞገስ ያስገኝልናል።
ይህ ደግሞ እግዚአብሄር
በአካልም በስሜትም ፍጹም
ጤንነት ወደምናገኝበት ፍጻሜ
ወደሌለው ሕይወት ይመራናል
ኢሳይያስ 33:24፤
ራእይ 21:4፤ 22:2።
አንዳንዶች የሕክምና እርዳታ ከማግኘት ይልቅ ሃይማኖታዊ ፈውስ (ወይም የእምነት ፈውስ) ማግኘት የተሻለ እንደሆነ ይናገራሉ። በጥንት ዘመን በነበሩ የእግዚአብሄር ሕዝቦች መካከል የጤና እርዳታ የሚሰጡ ሰዎች የነበሩ ሲሆን እግዚአብሄር ይህን ሙያቸውን አልተቃወመም። (ዘፍጥረት 38:28፤ ቆላስይስ 4:14) እነዚህ ሰዎች ለመድኃኒትነት የሚውሉ ተክሎችንና* ቅባቶችን በመጠቀም እንዲሁም ለሕመምተኞቹ አንድ ዓይነት የአመጋገብ ሥርዓት በማዘዝ ወይም በሌሎች የሕክምና ዘዴዎች ተጠቅመው ሕክምና በመስጠታቸው አምላክ እንዳልተደሰተ የሚገልጽ ሐሳብ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አናገኝም። ይሁን እንጂ መጽሐፍ ቅዱስ ጤነኛ ለመሆን ማንኛውም ዓይነት መሥዋዕት መከፈል አለበት የሚለውን አመለካከት አይደግፍም ማለትም በመናፍስታዊ ድርጊቶች አማካኝነት ፈውስ ለማግኘት መሞከር በእግዚአብሄር ዘንድ ተቀባይነት የለውም። (ገላትያ 5:19-21) የጤና እክል በሚያጋጥመን ጊዜ መጽሐፍ ቅዱስ በሚያወግዛቸው መንገዶች መጠቀም ተገቢ ያለመሆኑን የተረዳ ስው ለፈውስ መጸለይ ወይም የሚችል ከሆነ ወዲያውኑ ጥሩ ሕክምና ለማግኘት መሞከር የጥበብ እርምጃ ነው።
በመጽሐፍ ቅዱስ
ጊዜ የተለያዮ በሽታዎች
የሚታከሙት በባለመድሐኒቶች ምናልባትም
ከተክሎች በሚገኙ መድሐኒቶች
ነው ተብሎ ይታመናል
ለዚህም ምሳሌ ንጉስ
አሳ 2 ዜና መዋዕል
16፡12 እንደተጠቀስው “በነገስ
በስላሳ ዘጠነኛው አመት
አሳ እግሩን ታመመ
ደዌውም ጽናበት ነገር
ግን በታመመ ጊዜ
ባለ መድሐኒቶችን እንጂ
እግዚአብሄርን
አልፈለገም“ ፈውስንም አላገኘም።
መድኃኒትነት ያላቸው እጽዋት
ለሕክምና ተግባር ማገልገል
ከጀመሩ በጣም ረጅም
ዘመን አልፏል። በ16ኛው መቶ ዘመን
ከክርስቶስ ልደት በፊት
በግብጽ በተዘጋጀው ኤበርስ
ፓፒረስ የተባለ ጽሑፍ
ውስጥ ለተለያዩ በሽታዎች
የሚያገለግሉ በመቶዎች የሚቆጠሩ
የተፈጥሮ መድኃኒቶች ተመዝግበው
ተገኝተዋል። ይሁን እንጂ
አብዛኛውን ጊዜ መድኃኒትነት
ያላቸው እጽዋት በጽሑፍ
ሰፍረው የሚገኙ ሳይሆን
በአፍ ከትውልድ ወደ
ትውልድ ሲተላለፉ የቆዩ
ናቸው።
በጥንቱ የብሉይ
ኪዳን ህብረተስብ የአይን
ሕመምም ሌላው ችግራቸው
ነበር ይህም በአያሌ
ሥፍራዎች በመጽሐፍ ቅዱስ
ውስጥ ተጠቅሷል የተጠቀስውም
ከሌሎቹ በሽታዎች ጋር
ሲሆን የበለጠ የተያያዘው
በአይሁዶች ከግብጾችና ከፍልስፍጤም
ስዎች ጋር ነበር።
በዘፍጥረት 27፡1 የተጠቀስው
“ይስሐቅም ሽምግሎ አይኖቹ
ከማየት በፈዘዙ ጊዜ ችግሩ
የካታራክት ወይም የሬቲና
ዲጀነሬሽን ችግር ነው
ያዕቆብ ደሞ ዘፍ.
48፡10 ዔሊ 1 ሳሙ.
4፡15 ተመሳሳይ የአይን
ችግሮች አሏቸው። ሙሴና
በዘዳግም 34፡7 ሙሴ
በመቶ ጊዜ 120 አመቱ
ነበር አይኑም አልፈዘዘም።
ይህም በሽታ የሚይዘው
በማንኛውም እድሜ ያሉትን
ስዎች ሲሆን በከባድ
ሁኔታ የሚተላለፍና በዚያን
ጊዜ ከንጽሕና ጉድለትና ልጆች
ላይ በዝንቦች ከታመሙ
ስዎች አይን ወደ
ሌሎች ስዎች በዝንብም
ሆነ በንክኪ ይህ
አይነት ተላላፊ የአይን
በሽታ ያጠቃቸው ነበር።
በአሁድም ሕብረተስብ
ውስጥ ይኸው የአይን
በሽታ ተባብሶ እውርነትን
ስለሚያስከተል
በዚህ የአይነስውር የሆኑ
ቀሳውስት ማገልገል አይመረጡም
(ዘለዋ. 21፡16፥18)
የአይን መሞጭሞችም እንኳ
ለአገልግሎች
እንዳይመረጥ
ያደርገዋል (ዘለዋ. 21፡20)። በአዲስ
ኪዳን ደሞ ከመወለዱ
ጀመሮ እውር የነበር
(ዮሐ. 9፡1) ይኸኛውም
ሌላ የአይን መታወር
ችግር ነው። በማርቆስ
8፡22 ላይ የተጠቀስውን
ጌታ የፈውስው መታወሩ
ከልጅነቱ ጀመሮ እንደሆነ
ያመለክታል።
ቅዱስ
ጳውሎስም በደማስቆ መንገድ
ላይ ከታላቅ ብርሃን
የተነሳ አይኑ እንደታወረ
ያመለክታል በዚህ ሥፍራ
የቅዱስ ጳውሎስ አይን
የታወረው በአይኑ ውስጥ
ከገባው ከታላቅ ብርሃን
የተነሳ ነበር በሐዋሪያት
ሥራ 9፡18 ሐናንያ
በጸለየለት ጊዜ ከአይኑ
ላይ ቅርፊት ወደቀ
ይሁን እንጂ የግራ
አይኑ ምን ያህል
ደካማ እንደሆነ አይታወቀም።
በሮሜ 16፡22
የሮሜ መልክቱን የጻፈው
እርሱ እራሱ ሳይሆን
በቃል እየተናገረ የጻፈለት
ሌላ እንደሆነ ያመለክታል
ምናልባትም ቅዱስ ጳውሎስ
የአይን ችግር ስለላው
ነበር ተብሎ ይገመታል።
በገላትያ 6፡11 እንዴት
ባሉ ትላልቅ ፈደላት
በእጄ እንደጻፉላችሁ እዩ
ብሎ ለገላትያ ስዎች
ይጽፍላቸዋል
ምናልባትም ከዚህ አባባሉ
የአይን ጤና ችግሮች
አሉት ይህም 2 ቆሮ.
12፡7 የተጠቀስው ከዚህ
የተነሳ ነው ተብሎ
ይታመናል።
እግዚአብሄር አምላክ
ሰብዓዊ ፍጡሮቹ ሲፈጥር
እንዲታመሙና
እንዲሞቱ ዓላማው አልነበረም።
አዳምንና ሔዋንን በዔድን
የአትክልት ቦታ ማለትም
በደስታ ገነት ውስጥ
ያስቀመጣቸው
ለ70 ወይም ለ80
ዓመታት ብቻ ሳይሆን
ለዘላለም ‘እንዲያለሟትና እየተንከባከቡ
እንዲጠብቋት’
ነበር። (ዘፍ. 2:8, 15፤ መዝ.
90:10) እነዚህ የመጀመሪያዎቹ ባልና
ሚስት ለእግዚአብሄር ታማኝ
ሆነው ቢዘልቁና ለሉዓላዊነቱ
በፍቅር ቢገዙ ኖሮ
ጤና ማጣትንም ሆነ
እርጅና የሚያስከትለውን ጉስቁልና
እንዲሁም ሞትን ባላዩ
ለኛም ባላስተላለፉት ነበር።
መክብብ ምዕራፍ
12 ፍጹማን ባልሆኑ ሰዎች
ላይ ከእርጅና ጋር
ተያይዞ ስለሚመጣው “የጭንቀት
ጊዜ” ቁልጭ አድርጎ
ይገልጻል። (መክብብ 12:1-7)
ሽበት ‘ከለውዝ ዛፍ’
አበባ ጋር ተመሳስሏል።
እግሮች፣ እየጎበጡና እየተብረከረኩ
ከመጡ ‘ብርቱ’ ሰዎች
ጋር ተመሳስለዋል። የዓይን
መዳከም፣ ብርሃን እናያለን
ብለው ወደ መስኮት
ሲመጡ ከጨለማ ሌላ
ምንም ነገር ባላገኙ
ወይዛዝርት መመሰሉ ትክክለኛ
መግለጫ ነው። የረገፉ
ጥርሶች ‘ጥቂት በመሆናቸው
ምክንያት መፍጨት ባቆሙ’
ሴቶች ተመስለዋል። የሚብረከረኩ
እግሮች፣ የደከሙ ዓይኖችና
ጥርስ አልባ የሆኑ
ድዶች አምላክ ለሰው
ዘር የነበረው የመጀመሪያ
ዓላማ ክፍል አይደሉም።
ከዚህ በተጨማሪ ከአዳም
የወረስነው ሞት ‘ከዲያብሎስ
ሥራዎች’ አንዱ ሲሆን
የእግዚአብሄር
ልጅ በመስቀል ላይ
በከፈለው ዋጋ አስወግዶታል ለዚህ
ነው ሐዋርያው
ዮሐንስ “የእግዚአብሔር ልጅ
የተገለጠውም
የዲያብሎስን
ሥራ ያፈርስ ዘንድ
ነው” ብሎ በድፍረት
የጻፈው። 1 ዮሐ. 3:8
መጽሐፍ ቅዱስ
የሕክምና መጽሐፍ አይደለም፤
ደግሞም ሰዎች የሚያደርጉትን
እያንዳንዱን
ነገር የሚቆጣጠር መመሪያ
አልያዘም። ያም ቢሆን
እግዚአብሄር
ጤንነትን ስለ መጠበቅ
ያለውን አመለካከት የሚጠቁሙ
በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ
የሚገኙ ሐሳቦችን ያሳውቃል።
መጽሐፍ ቅዱስ ለሰውነታችን
የምናደርገው
እንክብካቤ እግዚአብሄርን እንደሚያሳስበው
የሚጠቁሙ በርካታ ሐሳቦች
ይዟል። ለምሳሌ ያህል
መጽሐፍ ቅዱስ ሆዳምነትንና
ሰካራምነትን
ጨምሮ ከልክ በላይ
የሚደረጉ ጎጂ ነገሮችን
ያወግዛል። (ምሳሌ 23:20) እግዚአብሄር
ለጥንቶቹ እስራኤላውያን በሰጠው
ሕግ ላይ በሽታዎች
እንዳይስፋፉ
ለመቆጣጠር ከተቻለም እንዳይከሰቱ
ለመከላከል መደረግ ያለባቸው
ነገሮች ተካትተዋል። በተጨማሪም
ሕጉ በሰው ላይ
ጉዳት የሚያደርሱ አደጋዎችን
ለማስወገድ የሚረዱ የደህንነት
መመሪያዎችን
ይዟል። (ዘዳግም 22:8) ከዚህ
በግልጽ ለማየት እንደሚቻለው
መጽሐፍ ቅዱስ፣ ሰውነታችንን
እንድንንከባከብና
ጤንነታችንን
ለመጠበቅ አስፈላጊውን ነገር
እንድናደርግ
ያበረታታል።
በመጽሐፍ ቅዱስ
ውስጥ ብዙ ተስፋዎች
ለነፍስም ሆነ ሥጋ
ፈውስ ማግኛ መንገድ
ተስጥተዋል፤
ሆኖም በመጸሐፍ
ቅዱስ ውስጥ የተጠቀሱትን
ተስፋዎችና መመሪያዎችን አውቆ
ከመጠቀም ይልቅ ባለማወቅ
ብዙ ስዎች
በአካልና በነፍስ በሽታ
ይስቃያሉ። በአሁኑ ጊዜ
ፈውስ በመጽሐፍ ቅዱስ
ውስጥ የሚገለጸው በምን
መንገድ ነው? ለሚለው
መልሱ መጽሐፍ ቅዱስ
በዚህ አስፈላጊ በሆነ
ትምህርት ላይ በደፈናው
አያልፈውም ይልቁንም እግዚአብሔር
የፈውስን መንገዶች
እንደተከናውኑ
ለትምህርታችን
ተጽፈው ይገኛሉ።
·
እግዚአብሔር በሽታን
እንደሚፈወስና
ጤናን እንደሚያድስ (ዘዳግም
8፡4) ያመለክታል ይህም
እውነት ለብዙዎች ያስፈልጋል
·
መጽሐፍ
ቅዱስ ስለጤናማ ኒዩትሪሽን
(ኦሪት ዘጽአት15፡16፤ ኦሪት
ዘለዋውያን 11 ተጽፎ ይገኛል
ጤናማ ያልሆኑ ምግቦች
ለተለያዩ በሽታዎች ተመጋቢውን
ያጋልጣሉ
·
መጽሐፍ
ቅዱስ ጤናማ አኗኗርን
ማለትም ተከታታይ የስውነት
እንቅስቃሴዎችንና
ከተፈጥሮ ውጪ የሆኑ
ጭናዎችን ማስወገድ (ኦሪት
ዘለዋውያን 12-14) ተጽፎ ይገኛል
ጫና የተለያዩ በሽታዎች
መነሻ መሆኑን ያመለክታል
·
እግዚአብሔር
ደግሞ ለጤና ፈውስን
በመድሐኒት አዘጋጅቷል (ያዕቆብ
5፡14)
ከሃጢያት የተነሳ
የሚመጣውን በሽታ እግዚአብሔር
በሽተኛውን ይቀርታ በመስጠትና
በማንጻት ፈውስን ይስጣል
(ኦሪት ዘሁልቁ 12፡13)
·
እግዚአብሔር
በእምነት በጽሎት በሽታን
ይፈውሳል (ያዕቆብ 5፡15)
·
እግዚአብሔር
ፈውስን በተአምር (በእግዚአብሄር
ምርጫ) ወይም በመድሕኒት ይፈውሳል
የታመመው አማኝ እንዲፈወስ
ምን ማድረግ አለበት?
በሌላ ጊዜም ደግሞ
ስዎች ታመው እንደሐዋሪያው
ጳውሎስ 2 ቆሮ. 12፡7,10
ያልተፈውሱበት
ጊዜ እንዳለ ማወቅ
ይስፈልጋል
·
አማኙ በአካል
የታመመ እንደሆነ የበሽታው
መነሻ ምን እንደሆነ
ለይቶ ማወቅ ይኖርበታል፤
በሽታው መነሻው ከኒዩትሪሽን
የተነሳ ከሆነ ኒዩትሪሽንን
በማስተካከል
እራስን መርዳት ነው።
መታወስ ያለበት በሆስዔ
4፡6 ከውቀት ማጣት
የተነሳ የሚመጣ ጉዳት
እንዳለም ነው።
·
በሽታው በሀጢያት
የተነሳ ከመጣ (ያዕቆብ
5፡14,15) እንደተጠቀስው ፈውሱን
መፈለግ ይኖርበታል
·
የአማኙ መታመም ምናልባትም
የእግዚአብሔር
ፈቃድ ያለበት
2 ሳሙ.
4:4; እና
2 ቆሮ.12:7,10 ላይ እንደተጠቀስው
አይነት ከሆነ ደግሞ
ሌላ ገጽታ አለው።
·
በጣም
አስፈላጊ የሆነው የእምነት
ጸሎት በሐዋሪያው ያዕቆብ
የተጠቀስው የእምነት ጸሎት
የተኮተኮተውና
ጥንቃቄ የተደረገለት ትምህርቱ
የሚያተኩረው
በዮሐንስ ወንገል 16፡13
የተመስረተ የመንፈስ ቅዱስ
ማደሪያ ስለመሆን የተመለከተው
ነው። የእምነት ጽሎት
ያዕቆብ መንፈሳዊ መለየትንና
መረዳትን በመለማመድ
እምነት ጸሎት ውጤቱ
ምንም ይሁን መጸለየና
መቆምን ያመለክታል።
·
ጸሎት
እግዚአብሔር
የሚፈውስበት
መንገድ የቱንም
ይምረጥ ታማኝነቱን ያረጋግጣል
ስለሆነም የእምነት ጽሎት
ጸላዮ የሚቀበለው እግዚአብሔር
አማኙ የተያዘበትን በሽታ
በመዝ 23፡4 ይቀበለዋል።
የስውን ደካማነት የእግዚአብሔርን
ጉልበት ይገልጣል (2 ቆሮ. 12፡7,10)።
ኢየሱስ በሽተኞችን የፈወሰው በዘመናችን ፈውስ ከሚያከናውኑ ሰዎች ፍጹም በተለየ መንገድ ነበር። ለምሳሌ ያህል፣ ኢየሱስ እርዳታ ፈልገው ወደ እሱ የመጡትን ሕመምተኞች በሙሉ ፈውሷል። ከታመሙ ሰዎች መካከል የተወሰኑትን ፈውሶ የተቀሩትን እንዲሁ አልተዋቸውም። ከዚህም በተጨማሪ ሰዎችን የፈወሰው ሙሉ በሙሉ ከመሆኑም ሌላ ሁልጊዜ ማለት ይቻላል ሰዎቹ ከበሽታቸው የሚድኑት ወዲያውኑ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ “ኀይል ከእርሱ እየወጣ ሁሉንም ይፈውስ ስለ ነበር፣ ሰዎቹ ሁሉ እርሱን ለመንካት ይፈልጉ ነበር” በማለት ይናገራል ሉቃስ 6:19። ‘ኢየሱስ ሰዎችን የሚፈውሰው እምነታቸውን መሠረት አድርጎ ካልሆነ የፈወሳቸውን ሰዎች ብዙውን ጊዜ “እምነትህ አድኖሃል” ይላቸው የነበረው ለምንድን ነው?’ ተብሎ ቢጠየቅ (ሉቃስ 8:48፤ 17:19፤ 18:42) ኢየሱስ እንዲህ ብሎ ሲናገር እንደሚፈወሱ አምነው ወደ እሱ የመጡት ሰዎች እንደተፈወሱና ይህን ያላደረጉት ግን አጋጣሚውን ሳይጠቀሙበት እንደቀሩ መግለጹ ነበር። ከበሽታቸው የዳኑት ሰዎችም ቢሆኑ የተፈወሱት በእምነታቸው ሳይሆን በእግዚአብሄር ኃይል ነው። መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ኢየሱስ ሲናገር እንዲህ ይላል፦ “እግዚአብሔር . . . በመንፈስ ቅዱስና በኀይል ቀባው፤ እርሱም እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ስለ ነበረ በደረሰበት ሁሉ መልካም እያደረገ በዲያብሎስ ሥልጣን ሥር የነበሩትን ሁሉ ፈወሰ።” የሐዋርያት ሥራ 10:38።
ወደ ህክምና የተመጣ
እንደሆነ ሁሉንም ዓይነት
ሕመምና በመጨረሻም ሞትን
ሊያስቀር የሚችል አንድም
የሰው ልጅ ሕክምና
የለም። ይህ የሆነበት
ምክንያት እነዚህ ከመጀመሪያው
አባታችን ከአዳም የተወረሱ በመሆናቸው ነው።
(ኢዮብ 14:4፤ መዝሙር
51:5፤ ሮሜ 5:12) ብዙ
የሕክምና ዓይነቶች ጠቃሚ
ሆነው ሊገኙ ይችላሉ።
ይሁንና ሕይወትን ከማራዘምና
ለተወሰነ ጊዜ ብቻ
ደህና ኑሮ እንዲኖር
በማድረግ ለጊዜው እንደ
ማስታገሻ ከማገልገል አያልፉም።
ይሁን እንጂ ለጤና
ችግሮች አስተማማኝ ፈውስ
የሚገኝበት መንገድ አለ
ዛሬም ቢሆን በሚልዮን
የሚቆጠሩ ሰዎች ይህን
መንገዱን አውቀው እየተጠቅሙበት
ይገኛሉ። ይህን ፈውስ ያዘጋጀው
ታላቁ ሐኪም ፈጣሪያችን
እግዚአብሄር አምላክ ነው።
በእርሱ በማመንና ኃጢአትን
በደሙ በእምነት በሚያነጻው
በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ
በማመን ከሕመም ነፃ
በሆነ ዓለም ውስጥ
ፍጹም ጤናና የዘላለም
ሕይወት አምኖ የተቀበለው
ማገኘት ያስችለዋል (ማቴዎስ
20:28) ኢሳይያስ 33:24።
ውስጥ “እንደተጠቀስው ታምሜአለሁ
አይልም” የሚል ተስፋ
ይሰጣል። እግዚአብሄር በቃሉ
የስጠውን ተስፋ መቀበል
ለነፍስ ብቻ ሳይሆን
በዚህ አለምም ስንኖር
ይበጃናል ስለዚህ አምንነን
እንቀበለው። ጌታ ይረዳን!
ለፈውስ ጸሎት
በስደት ምድር በአለም ዙሪያ የሚኖሩትን ክርስቲያኖችንም ሆነ ያልሆኑትን ይህንን የጻፍኩትን ያነበቡትን ሁሉ ማንኛውም የጤና ችግር ያለባቸውን ሐኪም እንክዋን ሊረዳቸው ያልቻለውን ሁሉ ይዤ በፊትህ እቀርባለው “እኔ ፈዋሽህ አምላክህ ነኝ” ያልክ አንተ እግዚአብሄር አንተ ጂሆቫ ኒሲ አዶናይ የምድራና የስማይ የስውም ልጆች ፈጣሪ የሆንክ የነፍስ አዳኝ ብቻ ሳትሆን የሥጋንም ፈውስ ታደርጋለህና ምድርና ስማይን ባጸናው በታላቁ ስምህ “በጌታ በየሱስ ስም” በፊታቸው ተራራ ሆኖ የቆመውን የበሽታን ሃይል እንድታነሳና እንድተፈውሳቸው እለምንሃለሁ ስለስማኸኝም አመስግንሃለሁ፤ ከሥጋቸውም ፈውስ የበለጠ ነፍሳቸውን አድነህ የራስህ እንድታደርጋቸው እለምንሃለሁ በጌታ በየሱስ ስም አሜን!
ይቀጥላል...
0 comments:
Post a Comment