ደግሞ እላችኋለሁ፥ ከእናንተ ሁለቱ በምድር በማናቸውም በሚለምኑት ነገር ሁሉ ቢስማሙ በሰማያት ካለው ከአባቴ ዘንድ ይደረግላቸዋል። ሁለት ወይም ሦስት በስሜ በሚሰበሰቡበት በዚያ በመካከላቸው እሆናለሁና። -
በብሉይና በሃዲስ ኪዳን የተጸለዩ ጽሎቶች
1. አብረሃም ስለ ሰዶም በዘፍጥረት 18:22-23
በዚያን ዘመን ልጅ መውለድ አለመቻል እንደ እርግማን ይታይ ነበር። አብርሃም ዕድሜው እየገፋ እንደሆነና ልጅም እንዳልወለደ ሲመለከት ስለ ጉዳዩ ወደ አምላክ ጸልዮአል። እግዚአብሄር የገባውን ቃል እንደሚፈጽምለት ማረጋገጫ ሰጠው። ውጤቱስ ምን ነበር? አብርሃም “በእግዚአብሔር አመነ።” እኛም ለእግዚአብሄር በጸሎት የልባችንን ከነገርነው፣ በመጽሐፍ ቅዱስ አማካኝነት የሚሰጠንን ማረጋገጫዎች የምንቀበልና የምንታዘዘው ከሆነ እምነታችን ይጠናከራል።
ሌላው የታወቀ ጸሎት በዘፍጥረት ውስጥ ተመዝግቦ ይኸውም ጸሎት አብርሃም የወንድሙ ልጅ ሎጥ የሚኖርበት ቦታ ከሰዶም ሰዎች ጋር እንዳይጠፋ ለማዳን ያደረገው ጸሎት ነው (በዘፍጥረት 18:22-23)።
መጽሐፍ ቅዱስ ሎጥ “ጻድቅ” እንደሆነ ይናገራል ባደረገው መርጫ ጉዳይ ላይ የአብራምን አስተያየት ለማወቅም ሆነ የአረጋዊውን ሰው ምክር ለማግኘት የፈለገ አይመስልም።
(2 ጴጥሮስ
2:7) “ሎጥም በዮርዳኖስ ዙሪያ ያለውን አገር ሁሉ መረጠ ሎጥም ወደ ምሥራቅ ተጓዘ፤ አንዱም ከሌላው እርስ በርሳቸው ተለያዩ። አብራም በከነዓን ምድር ተቀመጠ ሎጥም በአገሩ ሜዳ ባሉት ከተሞች ተቀመጠ፣ እስከ ሰዶምም ድረስ ድንኳኑን ተከለ።” (ዘፍጥረት 13:11, 12) ሰዶም የበለጸገችና በርካታ ቁሳዊ ጥቅም የሚገኝባት ከተማ ነበረች። (ሕዝቅኤል 16:49, 50) በሥጋዊ ዓይን ሲታይ ሎጥ ጥበብ ያለው ምርጫ ያደረገ ሊመስል ቢችልም በመንፈሳዊ ዓይን ሲታይ ግን ጥበብ የጎደለው ነበር። ምክንያቱም “የሰዶም ሰዎች . . . ክፉዎችና በእግዚአብሔር ፊት እጅግ ኃጢአተኞች ነበሩ” በማለት ዘፍጥረት 13:13 ይናገራል። ሎጥ እዚያ ሄዶ ለመኖር ያደረገው ምርጫ ውሎ አድሮ በቤተሰቡ ላይ ከባድ ሐዘን የሚያስከትል ነበር። በአረጋዊ በአምረሃም ጸሎት እግዚአብሄር ሎጥን ከጥፋት አዳነው። ሎጥ የተሰጠውን ግልጽና ቀላል የሆነ መመሪያ ታዞ እርምጃ ለመውሰድ አመንትቶ ነበር። በሰዶምና በገሞራ ሰዎች ያዘቀጠ የሥነ ምግባር አቋም የተነሳ በእጅጉ ይሳቀቅና “ነፍሱን ያስጨንቅ ነበር።” (2 ጴጥሮስ 2:8) እግዚአብሄር እነዚያን ክፉ ከተሞች ሊያጠፋ እንዳሰበ ተናገረ፤ እንዲሁም ለሎጥ ቤተሰቡን ይዞ በመውጣት በሕይወት መትረፍ የሚችልበት አጋጣሚ ሰጠው። ሎጥ በዚህ ወሳኝ ወቅት እርምጃ ለመውሰድ አመነታ። እሱንና ቤተሰቡን ለማዳን የተላኩት መላእክት ሎጥንና ቤተሰቡን እጃቸውን ይዘው ከከተማዋ ማውጣት አስፈልጓቸው ነበር። ዘፍጥረት 19:15, 16
አብረሃም በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በተለያየ ጊዜ በየሄደባቸው ቦታዎች ለእግዚአብሄር መስዋዕትን በሚያቀርብበት ጊዜ ወደ እግዚአብሄር ከጸሎት ጋር መስዋዕትን እንደሚያቀርብ የታወቀ ነው።
2. የአብረሃም አገልጋይ ለምሪት የጸለየው ጸሎት በዘፍጥረት ውስጥ የአብረሃም አገልጋይ የነበረው አብረሃም መልዕክት በላከው ጊዜ ወደ እግዚአብሄር ለምሪት ያደረገው ጸሎት ነው። ኤሊዔዘር ጸሎት ኃይል እንዳለው ያምናል። ፍጹም ቅንነት በተሞላበት አስደናቂ እምነት የሚከተለውን የትሕትና ልመና አቀረበ:- “የጌታዬ የአብርሃም አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፣ እለምንሃለሁ፤ መንገዴን ዛሬ በፊቴ አቅናልኝ፣ ለጌታዬም ለአብርሃም ምሕረትን አድርግ። እነሆ፣ በዚህ የውኃ ምንጭ አጠገብ እኔ ቆሜአለሁ፣ የዚህችም ከተማ ሴቶች ልጆች ውኃውን ሊቀዱ ይመጣሉ፤ ውኃ እጠጣ ዘንድ እንስራሽን አዘንብዪ የምላት እርስዋም:- አንተ ጠጣ፣ ግመሎችህን ደግሞ አጠጣለሁ የምትለኝ ቆንጆ፣ እርስዋ ለባሪያህ ለይስሐቅ ያዘጋጀሃት ትሁን፤ በዚህም ለጌታዬ ምሕረትን እንዳደረግህ አውቃለሁ።” ዘፍጥረት 24:12-14። ኤሊዔዘር ጸሎት ኃይል እንዳለው የነበረው ትምክህት መና አልቀረም። እንዲያውም ወደ ውኃ ጉድጓዱ የመጣችው የመጀመሪያዋ ሴት የአብርሃም የወንድሙ የልጅ ልጅ ሆና ተገኘች! ይህች ሴት ርብቃ የምትባል ስትሆን ያላገባች፣ በሥነ ምግባር ንጹሕና ውብ ነች። የሚያስገርመው ነገር ለኤሊዔዘር የሚጠጣው ውኃ መስጠት ብቻ ሳይሆን ግመሎቹ ሁሉ ጥማቸው እስኪረካ ለማጠጣት በደግነት ጥያቄ አቀረበች። ትንሽ ቆየት ብሎ ቤተሰቡ በጉዳዩ ላይ ከመከረ በኋላ ርብቃ የአብርሃም ልጅ የይስሐቅ ሚስት ለመሆን ከኤሊዔዘር ጋር ወደ ሩቅ አገር ለመሄድ ሳታቅማማ ተስማማች። አምላክ በአንዳንድ ክስተቶች ላይ ተአምራዊ በሆነ መንገድ አልፎ አልፎ ጣልቃ ይገባ በነበረበት ዘመን ኤሊዔዘር ያቀረበው ጸሎት ምንኛ አስደናቂና ግልጽ ምላሽ አግኝቷል!በዘዳግም ውስጥ መጽሐፍ ቅዱስ መሠረታዊ ሃይማኖታዊ መመሪያዎችን ጨምሮ የተደራጀ ጸሎት የሚሆን መሠረት ይጥላል እና የመጽሐፍ ቅዱስ ከጊዜ በኋላ መጻሕፍት አማካኝነት ጸሎት ይበልጥ ደረጃውን የጠበቀ አድግዋል።
3. የያዕቆብ በረከት በዘፍጥረት
27 ያዕቆብ ለአብርሃም ለተገባለት የተስፋ ቃል ኪዳን ትልቅ ቦታ ይሰጥ ነበር። በመሆኑም እግዚአብሄር “ወደደው።” ኤሳው ስለመንፈሳዊ ውርሻው እምብዛም ደንታ የሌለውና ይህንኑ ውርሻውን ለወንድሙ ለያዕቆብ በምስር ወጥ ብኩርናውን የሸጠ ሰው ነበር። ያዕቆብ የታላቅ ወንዱሙን የኤሳውን የብኩርና መብት ሲወስድና ለወንድሙ ታስቦ የነበረውን ምርቃት ሲቀበል ዔሳው በቀል በተሞላበት ቁጣ ነደደ። በዚህ ጊዜ ያዕቆብ የሚወዳቸውን ቤተሰቦቹን ትቶ ለመሰደድ ተገደደ። በጉዞው ላይ ያጋጠመው ሁኔታ ሆኖ ጽሎት አድርግዋል በተላይም የምበላውን እንጀራ ብትስጠኝ...በትጠብቀኝም...በሽሽት ላይ እያለ ከጸለያቸው ጸሎቶች መካከል ናቸው። በዚህም ጸሎት ከ እግዚአብሄር የተስጠው ተስፋ እንዳለ ግልጽ ነው ስለሆነም የተደቆሰ መንፈሱን እንዳደሰለት ምንም ጥርጥር የለውም። ሚልክያስ
1:2, 3፤ ዘፍጥረት
25:27–34፤ 27:1-45:: እግዚአብሄር ለያዕቆብ መላእክት በሰማይና በምድር መካከል በቆመ መሰላል ወይም ደረጃ መሰል ነገር ላይ ሲወጡና ሲወርዱ በሕልም ካሳየው በኋላ እርሱንና ዘሩን እንደሚጠብቀው ነገረው። “የምድርም አሕዛብ ሁሉ በአንተ በዘርህም ይባረካሉ። እነሆም እኔ ከአንተ ጋር ነኝ፣ በምትሄድባትም መንገድ ሁሉ እጠብቅሃለሁ፣ ወደዚችም ምድር እመልስሃለሁ፤ የነገርሁህን ሁሉ እስካደርግልህ ድረስ አልተውህምና” አለው። ዘፍጥረት 28:10-15 ያዕቆብ ከእግዚአብሄር ጋር የሚያደርገውን የጽሎት ግንኙነቱን ቀጥልዋል ይህም ያዕቆብ በቤቴል ያደረገው ቃል ኪዳን ዘፍጥረት 28 ተጽፎ ይገኛል። ሌላው ደግሞ ያዕቆብ በጰንኤል የችግሩ ጊዜ የጸለየው ጸሎት ዘፍጥረት 32 የተጻፈ ሲሆን ልጆቹንም የባረከበት ጸሎት ዘፍጥረት
40-49 ተጽፎአል።
4. ሙሴ ያደረገው የምልጃ ጸሎት
· በሙሴ መሪነት እርሱና ወገኖቹ ከግብጽ በወጡ ጊዜ ያደረገው የጸሎትና የምስጋና መዝሙር ኦሪት ዘጽአት 15
· የሙሴ ለቅሶና ጸሎት ለወገኖቹ ከእግዚአብሄር ዞር ብለው የጥጃውን ምስል ባመለኩ ጊዜ (ኦሪት ዘጽአት
32፤ ኦሪት ዘለዋውያን. 9)
· ሙሴ የእግዚአብሄርን ክብር እንዲያየ ጸለየ/ጠየቀ (ኦሪት ዘጽአት 33)
· የአሮን የበረከት ጸሎት (ኦሪት ዘሁልቁ
6)
· ሙሴ ስለአመጸኞች ወገኖቹ ከእግዚአብሄር ምህረትን ለመነ (ኦሪት ዘሁልቁ 14)
· የሙሴ የጸሎት ዝማሪ-እግዚአብሄርና ህዝቡ (ኦሪት ዘለዋውያን
32)
· ሙሴ የእስራኤልን ህዝብ የባረከበት ጸሎት (ኦሪት ዘለዋውያን
33)
ጽሎት አስደናቂ ከሙሴ ጋር አብሮ የተፈጠረ ወይም ያደገ የባህርይ ነበር። በመስጠት ከእግዚአብሔር ጋር በጸሎት ውስጥ አርባ ቀን ሲጸልይ ያለመታከት ተአምራዊ ለውጥ ስርቶዋል ይኸውም ከረጅም የጸሎት ትግል በወረደ ጊዜ ፊቱን በአስደናቂ ብሩህነት ጸሎቱ በህዋላ አብርትዋል። የሙሴ መምራትና ጸሎት ከእግዚአብሄር የተስጡት ስጦታዎች ነበሩ። የእርሱ ተልዕኮ ጸሎት ስለሆነ አብሮት የተፈጠረ ፍጥረቱ ይመስላል ይህም በመጽሐፍ ቅዱስ ውስት ተመዝግቦ ይገኛል።
"የእግዚአብሄር ህዝብ ወደ ግብፅ በገባ ጊዜ እና አባቶቻችሁም ወደ እግዚአብሔር ጮኹ: ከዚያም ጌታ ከግብፅ አባቶቻችሁንም አመጡ ሙሴንና አሮንን ላከ: እንዲሁም በዚህ ቦታ አኖሩአቸው."
ይህ ከግብፅ ባርነት ከዕብራውያን መዳን ታላቅ እንቅስቃሴ ዘፍጥረት የተጠቀስ ነው ሙሴም ሥራውን የጀመረው ከዚህ በህዋላ የተጠራበትን የመምራትና የምልጃ የጸሎት አገልግሎቱን ጀመረ።
የእግዚአብሄር ስዎች የእግዚአብሔርን ታላቅ ሥራ እንቅስቃሴ ውስጥ ምንጫቸው ጉልበታቸው ጸሎት የማድረግ ቅርጽ ጎልቶ መታየት ጀመረ። ጸሎት ከእግዚአብሔር ጋር ችግሮችንና ፈተናዎችን ለመቋቋም አስተዋኦ አለው። ጸሎት በአምነት ይጸለያል በቅዱሳን ጸሎት እግዚዓብሄር ይደሰታል፤ ጸሎት እጅግ አምላክ ተጽዕኖ ያሳድራል። የአምላክንም-ተልዕኮ ለማከናወን ጸሎት ትልቅ ሥፍራ አለው ለዚህ ነበር ሙሴ አምላክ ታላቅ ሥራ መሥራት የቻለው፤ ሙሴ የአምላክ ሕዝቦች ያስተዳድራል ያለ የእግዚአብሄርን መለኮታዊ እቅድ ያለጸሎት ማከናውን ባልቻለም ነበር። ትክክለኛ ጸሎት ልክ ጥናው ዕጣን ተሞልቶ ወደ እግዚአብሄር እንደማአዛ ሽታ ሆኖ የሚቀርበው አይነት ነው የእግዚአብሔር ሥር አንዲስራ እሳት እና መዓዛ (እጣን) ሁልጊዜ እየነደደ እንደመልካም ሽቶ መቅረብ ይኖርበታል።
የሙሴ ጸሎት ብዙውን ጊዜ የእግዚአብሔር ቍጣ አስከፊ ቍስል ማስታገሻ ሆኖ ህዝቡ ተገልግሎበታል። አራት ጊዜ የእግዚአብሔር ቍጣ የሚያስፈራ ደም በመፍሰሱ ምክንያት እሱን ለማስታገስ ወደ ፈርዖን ሙሴ ጸሎዮ ነበር። በጣም አጥብቆ ሙሴ ፈርዖን ለመነው እና "ሙሴ እግዚአብሔር ከግብፅ ምድር ላይ ስላመጣቸው ጓጕንቸሮች ወደ እግዚአብሔር ጮኸ: እግዚአብሔርም እንደ ሙሴ ቃልም አደረገ።
"ዝንቦች ላይ ከባድ መቅሰፍት ምድር ሁሉ አበላሽቶ ነበርና ፈርዖን እንደገና አዝኖ" ለመናቸው" ሙሴም ከፈርዖን ዘንድ ወጣ: ወደ ጌታን ለመነ እግዚአብሔርም ሙሴን ዳግመኛ ቃል መሠረት አደረገ። ይህ ክፉ ንጉሥ አስከፈላቸው አስደንጋጭ እና ጥፋት ቍጣ ውስጥ ብርቱም ነጐድጓድ እና በረዶ ሆነ "ጌታ ሆይ እለምንሃለሁ" ሙሴም ሁሉን ቻይ አምላክ "ወደ ጌታ እጁን ዘረጋ እንዲሁም ነጐድጓድ በረዶ ተወ። ሙሴ ጸሎተኛ ቢሆንም የሕግ ሰውም ነበር ከእርሱ ጋር ጸሎት ያለውን ታላቅ ኃይል ህዝቡ አይትዋል ከእርሱ ጋር ይበልጥ መንፈሳዊ መጋቢነት መሪነት ተስጣኦ ያለው መሪ መሆን የቻለው በጸሎት ጉልበት እንደሆነ ከታሪኩ መገንዘብ ይስችላል።
ሙሴ ሙሉ በሙሉ ጸሎት ከእግዚአብሄር ጋር የተያያዘ መሆኑን ስለተረዳ በመጸለይ መሠረት መርህ ይቀበላል። በእግዚአብሔር ፊት በጸሎት መቅረብ በእርሱ ባሕርይ ውስጥ ተጽዕኖ አሳድርዋል ጸሎት የአምላክ ተጽዕኖ መሆኑን አወጀ። ሙሴ 'ተልዕኮ መለኮታዊ ነበር ይህ ትእዛዝ መመሪያ እና በእግዚአብሔር የታቀደ ነበር። የሙሴን ጸሎት አገዛዝ ጸሎት ድፍረት ጽናት አስፈላጊነት ያሳያል።
እንደገና ሙሴ እርምጃ እርከን ላይ ከባድ ጊዜ ውስጥ እፎይታ ለማግኘት ወደ ማን መጸለይ እንዳለበት ያውቅ ነበር። እግዚአብሔር ቍጣውን ለመቆየት እና እስራኤል እንዲራራላችሁ ጸለየ።
"እኔ ሁሉን በቅጽበት አጠፋቸው ዘንድ ከዚህ ማኅበር መካከል ፈቀቅ ራሳችሁን ለዩ። "እነርሱም በፊታቸው ወደቁ: እንዲህም አለ: አምላክ ሆይ: የሥጋ ሁሉ መናፍስት ጌታ አምላክ: አንድ ሰው ኃጢአት ቢሠራ አንተ በማኅበሩ ሁሉ ላይ ከጉባኤው ጋር ትቈጣለህን?"
ሙሴ ግን ለእህቱ ሲል ጥልቅ እና ልባዊ ምልጃ አድርጎ ጸሎት የሚያስፈራ እና የማይድን ሕመም ስለሚሰቃይ አድኗቸዋል።
"ሕዝቡም: ምን እንጠጣለን ብለው በሙሴ ላይ አንጐራጐሩ? በዚያም በዚያም ከእነርሱ አንድ ደንብ እና ሥርዓት አደረገ፤ ሙሴም ወደ እግዚአብሔር ጮኸ እግዚአብሔርም ከእርሱ ውኃን ጣፋጭ አደረገ። ሙሴ የጠየቀውን ነገር አግኝቷል የእርሱ የተወሰነ ነበር ሲጸልይ አምላክ የሰጠው መልስ እንዲሁ የተወሰነ ነበር. የጸለየው ጸሎት ሁልጊዜ እርሱ ሁሉን ቻይ አምላክ ተሰማ እና ሁልጊዜ በእግዚአብሔር መልስ ነበር።
በፀሎትና በምልጃ
“በጸሎት ረገድ ንቁዎች ሁኑ”
“ጤናማ አስተሳሰብ ይኑራችሁ፤ እንዲሁም በጸሎት ረገድ ንቁዎች ሁኑ።” 1 ጴጥ. 4:7
አሁን የምንገኘው የሰይጣን ክፉ ሥርዓት ማብቂያ በተቃረበበት ወቅት ላይ ነው። ይህ ሥርዓት በታሪክ ዘመን በሙሉ ታይቶ በማያውቅ ሁኔታ በከፍተኛ ጨለማ ተውጧል፤ በመሆኑም በዛሬው ጊዜ ያሉ ክርስቲያኖች በመንፈሳዊ ህይወታቸው ንቁ ሆነው ለመኖር ከፍተኛ ትግል ማድረግ ያስፈልጋቸዋል። (ሮም
13:12) በዚህ የመጨረሻ ሰዓት ላይ በእንቅልፍ ብንሸነፍ የሚደርስብን አደጋ ምንኛ አስከፊ ይሆናል! “ጤናማ አስተሳሰብ” መያዛችንና “በጸሎት ረገድ ንቁዎች ሁኑ” የሚለውን ቅዱስ ጽሑፋዊ ማሳሰቢያ ተግባራዊ ማድረጋችን ወሳኝ ነገር ነው። 1 ጴጥ.
4:7 በጊዜ ሂደት የት ቦታ ላይ እንደምንገኝ ስለምንገነዘብ እንዲህ እያልን ራሳችንን መጠየቃችን ተገቢ ነው፦ ‘በጸሎት ረገድ ምን ያህል ንቁ ነኝ? በሁሉም የጸሎት ዓይነቶች እጠቀማለሁ? በተደጋጋሚስ እጸልያለሁ? ስለ ሌሎች የመጸለይ ልማድ አለኝ? ወይስ አብዛኛውን ጊዜ የምጸልየው ስለሚያስፈልጉኝና ስለምፈልጋቸው ነገሮች ብቻ ነው? ደግሞስ ለመዳን ካለኝ ተስፋ ጋር በተያያዘ ጸሎት ምን ያህል አስፈላጊ ነው?’
ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ለኤፌሶን ክርስቲያኖች በጻፈው ደብዳቤ ላይ “በሁሉም ዓይነት ጸሎት” የመጸለይን አስፈላጊነት ጠቅሷል። (ኤፌ. 6:18) ወደ እግዚዝብሄር ስንጸልይ የሚያስፈልጉንን ነገሮች እንዲያሟላልንና የሚያጋጥሙንን እንቅፋቶች ለመወጣት እንዲረዳን በተደጋጋሚ ልመና እናቀርብ ይሆናል። ‘ጸሎት ሰሚ’ የሆነው አምላክ እርዳታ እንዲያደርግልን የምናቀርበውን ልመና በደስታ ያዳምጣል። (መዝ.
65:2) ይሁን እንጂ ለሌሎች የጸሎት ዓይነቶችም ትኩረት ለመስጠት ጥረት ማድረግ ይኖርብናል። እነዚህም ውዳሴን፣ ምስጋናንና ምልጃን ያካትታሉ።
ወደ እግዚዝብሄር ስንጸልይ ለእሱ ውዳሴ ማቅረባችን ተገቢ የሚሆንባቸው አያሌ ምክንያቶች አሉ። ለምሳሌ ያህል፣ “ስለ ብርቱ ሥራው” እና ‘ስለ ታላቅነቱ’ በምናስብበት ጊዜ እሱን ለማወደስ እንገፋፋለን። (መዝሙር 150:1-6ን) አንብብ። መዝሙር 150 ላይ የሚገኙት ስድስት ቁጥሮች ብቻ እንኳ 13 ጊዜ ያህል፣ እግዚአብሄርን እንድናወድስ ያበረታቱናል! ሌላ መዝሙረኛው ንጉሥ ዳዊት ደግሞ ለእግዚአብሄር ካለው ጥልቅ አክብሮታዊ ፍርሃት በመነሳት “ጻድቅ ስለ ሆነው ሕግህ፤ በቀን ሰባት ጊዜ አመሰግንሃለሁ” ወይም አወድስሃለሁ ሲል ዘምሯል። (መዝ.
119:164) በእርግጥም እግዚዝብሄርን ሊወደስ ይገባዋል። ታዲያ ወደ እሱ ስንጸልይ “በቀን ሰባት ጊዜ” ይኸውም ደግመን ደጋግመን ልናወድሰው አይገባም?
ሌላው አስፈላጊ የጸሎት ዓይነት ደግሞ ምስጋና ነው። ቅዱስ ጳውሎስ በፊልጵስዩስ ከተማ ለሚኖሩ ክርስቲያኖች የሚከተለውን ማበረታቻ ሰጥቷቸዋል፦ “ስለ ምንም ነገር አትጨነቁ፤ ከዚህ ይልቅ ስለ ሁሉም ነገር በጸሎትና በምልጃ ከምስጋና ጋር ልመናችሁን ለአምላክ አቅርቡ።”
(ፊልጵ. 4:6) ስንጸልይ ለእግዚዝብሄር ከልብ የመነጨ ምስጋና ማቅረባችን በራሱ የሚያስገኝልን ጥቅም አለ። ሰዎች “የማያመሰግኑ” በሆኑበት በመጨረሻዎቹ ቀኖች ውስጥ የምንኖር በመሆኑ ይህ ጉዳይ ልዩ ትኩረት ያሻዋል።
(2 ጢሞ. 3:1, 2) በእርግጥም ዓለም ምስጋና ቢስ የመሆን መንፈስ ተጠናውቶታል። ጠንቃቃ ካልሆንን ይህ መንፈስ በቀላሉ ሊጋባብን ይችላል። በጸሎት ለእግዚዝብሄር ምስጋና ማቅረባችን ባለን ረክተን እንድንኖር የሚያስችለን ከመሆኑም ሌላ ‘አጉረምራሚና በኑሯችን የምናማርር’ እንዳንሆን ይረዳናል። (ይሁዳ
16) በተጨማሪም የቤተሰብ ራሶች ከቤተሰባቸው ጋር በሚጸልዩበት ጊዜ ምስጋና ማቅረባቸው ሚስቶቻቸውና ልጆቻቸው የአመስጋኝነት መንፈስ እንዲያዳብሩ ይረዳቸዋል።
ምልጃ ውስጣዊ ስሜታችንን የምናፈስበት ከልብ የመነጨ ጸሎት ነው። ለእግዚዝብሄር ምልጃ ስናቀርብ የትኞቹን ጉዳዮች ማካተት እንችላለን? ስደት በሚያጋጥመን ጊዜ ወይም ለሕይወት አስጊ የሆነ በሽታ ሲይዘን ምልጃ ማቅረብ እንችላለን። በእንደዚህ ዓይነት ወቅቶች አምላክ እንዲረዳን የምናቀርበው ጸሎት የምልጃ ይዘት እንደሚኖረው የታወቀ ነው። ይሁንና ለይሖዋ ምልጃ ማቅረብ የምንችለው በእነዚህ ወቅቶች ብቻ ነው?
ጌታ እየሱስ የጸለየውን አንብብና ስለ እግዚዝብሄር ስም እንዲሁም ስለ እግዚዝብሄር መንግሥትና ፈቃድ ምን ሐሳብ እንደጠቀሰ ለማስተዋል እንሞክር። (ማቴዎስ 6:9, 10ን አንብብ።) ይህ ዓለም በክፋት ተሞልቷል፤ ሰብዓዊ መንግሥታት ደግሞ የዜጎቻቸውን መሠረታዊ ፍላጎቶች እንኳ ማሟላት እየተሳናቸው መጥቷል። ከዚህ አንጻር በሰማይ የሚኖረው አባታችን ስም እንዲቀደስና መንግሥቱ ከምድር ላይ የሰይጣንን አገዛዝ እንዲያስወግድ መጸለያችን በእርግጥ ተገቢ ነው። በተጨማሪም ይህ ወቅት የእግዚዝብሄር ፈቃድ በሰማይ እንደሆነ ሁሉ በምድርም ላይ እንዲፈጸም ለእግዚዝብሄር ምልጃ የምናቀርብበት ጊዜ ነው። በመሆኑም በሁሉም የጸሎት ዓይነቶች በመጠቀም ንቁ ሆነን እንኑር።
‘ሳታሰልሱ ጸልዩ’
ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ ለክርስቲያኖች “በጸሎት ረገድ ንቁዎች/ትጉዎች ሁኑ” የሚል ማበረታቻ ቢሰጥም ቢያንስ በአንድ ወቅት እሱ ራሱ ይህን ሳያደርግ ቀርቷል። በጌቴሴማኒ የአትክልት ስፍራ ኢየሱስ ይጸልይ በነበረበት ወቅት እንቅልፍ ከወሰዳቸው ደቀ መዛሙርት አንዱ ጴጥሮስ ነበር። ኢየሱስ “ነቅታችሁ ጠብቁ፤ ሳታሰልሱም ጸልዩ” ካላቸው በኋላ እንኳ የተባሉትን ማድረግ አልቻሉም። ማቴዎስ
26:40-45ን አንብብ። ይሁን እንጂ መንቃት ባለመቻላቸው በቅዱስ ጴጥሮስና በሌሎቹ ሐዋርያት ላይ ከመፍረድ ይልቅ የዕለቱ ውሏቸው በደካማ ሥጋቸው ላይ ከባድ ተጽዕኖ ማሳደሩን መዘንጋት አይኖርብንም። ለፋሲካ በዓል አስፈላጊውን ዝግጅት ሲያደርጉ ውለዋል፤ ምሽት ላይ ደግሞ በዓሉን አክብረዋል። ከዚያም ኢየሱስ የጌታን ራት በዓል አዘጋጀ፤ እንዲህ ማድረጉ ወደፊት የሞቱ መታሰቢያ በተመሳሳይ መንገድ እንዲከበር የሚያስችል ነበር። (1 ቆሮ.
11:23-25) “በመጨረሻ የውዳሴ መዝሙር ከዘመሩ በኋላ ወደ ደብረ ዘይት ተራራ ሄዱ”፤ ይህም ጠባብ የሆኑትን የኢየሩሳሌም ጎዳናዎች አቆራርጠው የተወሰነ ርቀት መጓዝ ነበረባቸው። (ማቴ. 26:30, 36) በዚህ ጊዜ እኩለ ሌሊት ሳያልፍ አይቀርም። በዚያ ሌሊት እኛም በጌቴሴማኒ የአትክልት ስፍራ ብንገኝ ኖሮ እንቅልፍ ሊጥለን ይችል ነበር። ኢየሱስ በድካም የዛሉትን ሐዋርያቱን ከመንቀፍ ይልቅ ያሉበትን ሁኔታ በመረዳት “መንፈስ ዝግጁ ነው፤ ሥጋ ግን ደካማ ነው” ብሏቸዋል።
ቅዱስ ጴጥሮስ በጌቴሴማኒ የአትክልት ስፍራ ያጋጠመውን ሁኔታ ፈጽሞ ሊረሳው አይችልም። በጸሎት ሳይተጋ በመቅረቱ ከፈጸመው አሳዛኝ ስህተት ትምህርት ቀስሟል። ቀደም ሲል ኢየሱስ “በዚህች ሌሊት ሁላችሁም በእኔ ምክንያት ትሰናከላላችሁ” ብሏቸው ነበር። በዚህ ጊዜ ቅዱስ ጴጥሮስ “ሌሎቹ ሁሉ በአንተ ምክንያት ቢሰናከሉ እንኳ እኔ ፈጽሞ አልሰናከልም!”
በማለት አስረግጦ ተናግሮ ነበር። ከዚያም ጌታ ኢየሱስ፣ ጴጥሮስ ሦስት ጊዜ እንደሚክደው ተናገረ። ቅዱስ ጴጥሮስ በዚህም ሳይበገር “አብሬህ መሞት ቢያስፈልገኝ እንኳ በምንም ዓይነት አልክድህም” አለ። (ማቴ.
26:31-35) ይሁንና ጌታ ኢየሱስ አስቀድሞ እንደተናገረው ጴጥሮስ መሰናከሉ አልቀረም። ቅዱስ ጴጥሮስ ኢየሱስን በመካዱ በጸጸት ስሜት ተውጦ “ምርር ብሎ አለቀሰ።” ሉቃስ
22:60-62።
ቅዱስ ጴጥሮስ ካጋጠመው ከዚህ ሁኔታ ትምህርት እንዳገኘ ምንም ጥያቄ የለውም፤ በራስ የመመካት ዝንባሌውንም አሸንፏል። በዚህ ረገድ ጸሎት ቅዱስ ጴጥሮስን እንደረዳው ግልጽ ነው። ደግሞም “በጸሎት ረገድ ንቁዎች/ትጉዎች ሁኑ” የሚለውን ምክር የሰጠው ቅዱስ ጴጥሮስ መሆኑ ልብ ሊባል ይገባል። በመንፈስ መሪነት የተሰጠውን ይህን ምክር በሥራ እያዋልን ነው? ደግሞስ ‘ሳናሰልስ በመጸለይ’ በእግዚዝብሄር ላይ እንደምንመካ እናሳያለን?
(መዝ. 78:7) በተጨማሪም “የቆመ የሚመስለው እንዳይወድቅ ይጠንቀቅ” በማለት ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ የሰጠውን ማሳሰቢያ መዘንጋት አይኖርብንም።1 ቆሮ. 10:12።
ነህምያ ያቀረባቸው ጸሎቶች
በአምስተኛው መቶ ዘመን ዓ.ዓ.
የፋርሱ ንጉሥ የአርጤክስስ ወይን ጠጅ አሳላፊ የነበረው ነህምያ ያጋጠመውን ሁኔታ እንመልከት። ነህምያ ልባዊ ጸሎት በማቅረብ ረገድ ጥሩ ምሳሌ ተደርጎ ሊጠቀስ የሚችል ሰው ነው። በኢየሩሳሌም የሚኖሩ አይሁዳውያን የደረሰባቸውን መከራ በተመለከተ ለብዙ ቀናት በእግዚአብሄር ፊት ‘ሲጾምና ሲጸልይ’ ቆይቷል። (ነህ.
1:4) አርጤክስስ ፊቱ ለምን እንዳዘነ ሲጠይቀው ነህምያ ወዲያውኑ ‘ወደ ሰማይ አምላክ ጸለየ።’
(ነህ. 2:2-4) ይህ ምን ውጤት አስገኘ? እግዚዝብሄር፣ ነህምያ ላቀረባቸው ጸሎቶች መልስ ሰጠ፤ ደግሞም ሕዝቡን የሚጠቅም ነገር እንዲከናወን አደረገ። (ነህ. 2:5, 6) ይህ ሁኔታ የነህምያን እምነት ምንኛ አጠናክሮት ይሆን!
ነህምያ እንዳደረገው ያለማሰለስ መጸለይ ጠንካራ እምነት እንዲኖረን ይረዳናል። ሰይጣን ምሕረት የሚባል ነገር አያውቅም፤ አብዛኛውን ጊዜ ደግሞ ጥቃት የሚሰነዝረው በደከምንበት ወቅት ነው። ለምሳሌ ያህል፣ ከሕመም ወይም ከመንፈስ ጭንቀት ጋር እየታገልን ከሆነ በየወሩ በአገልግሎት የምናሳልፈውን ጊዜ እግዚዝብሄር ሥፍራ የማይስጠው ወይም ከቁብ እንደማይቆጥረው ማሰብ እንጀምር ይሆናል። አንዳንዶቻችን የሚያስጨንቁ ሐሳቦች ይረብሹን ይሆናል፤ እንዲህ የሚሰማን ከዚህ ቀደም በሕይወታችን ባጋጠሙን ሁኔታዎች የተነሳ ሊሆን ይችላል። ጠላት/ሰይጣን አልረባም የሚል ስሜት እንዲያድርብን ይፈልጋል። በአብዛኛው የእሱ ጥቃት የሚያነጣጥረው በስሜታችን ላይ ነው፤ በዚህ መንገድ እምነታችንን ለማዳከም ይጥራል። ይሁን እንጂ “በጸሎት ረገድ ንቁዎችና የምንተጋ ከሆንን” መሆናችን እምነታችንን ሊያጠነክርልን ይችላል። በእርግጥም ‘ትልቁ የእምነት ጋሻ የሚንበለበሉትን የክፉውን ፍላጻዎች ሁሉ ለማምከን ያስችለናል።’ኤፌ. 6:16። “በጸሎት ረገድ ንቁዎች ወይም ትጉዎች” ከሆንን ተዘናግተን አንገኝም፤ ይህ ደግሞ ያልታሰበ የእምነት ፈተና ሲያጋጥመን አቋማችንን እንዳናላላ ይረዳናል። ፈተናዎችና መከራዎች ሲያጋጥሙን የነህምያን ምሳሌ በማስታወስ ምንም ጊዜ ሳናጠፋ ወደ እግዚአብሄር እንጸልይ። ተፈታታኝ ሁኔታዎችን በመቋቋም ረገድ ሊሳካልንና በእምነታችን ላይ የሚደርሰውን ፈተና በጽናት ልናልፍ የምንችለው በይሖዋ እርዳታ ብቻ ነው።
ለሌሎች ጸልዩ
ጌታ ኢየሱስ የቅዱስ ጴጥሮስ እምነት እንዳይጠፋ ምልጃ አቅርቧል። (ሉቃስ 22:32) በመጀመሪያው መቶ ዘመን የኖረው ታማኙ ክርስቲያን ኤጳፍራ የኢየሱስን ምሳሌ በመከተል በቆላስይስ ላሉት ወንድሞቹ በትጋት ይጸልይ ነበር። ቅዱስ ጳውሎስ “በእግዚአብሄር ፈቃድ ሁሉ የተሟላችሁና ጽኑ እምነት ያላችሁ ሆናችሁ እንድትቆሙ ዘወትር በጸሎቱ ስለ እናንተ እየተጋደለ ነው” በማለት ጽፎላቸው ነበር። (ቆላ.
4:12) ራሳችንን እንዲህ ብለን መጠየቃችን የተገባ ነው፦ ‘በዓለም ዙሪያ ላሉ ወንድሞቼ በትጋት እጸልያለሁ? በተፈጥሮ አደጋ ሳቢያ ጉዳት ለደረሰባቸው የእምነት ባልንጀሮቼ ምን ያህል እጸልያለሁ? በጉባኤ ውስጥ ለሚገኙ መከራ እየደረሰባቸው ላሉ ወንድሞች በቅርብ ጊዜ ውስጥ ጸልዬ አውቃለሁ?’
ለሌሎች ወደ እግዚዝብሄር አምላክ መጸለያችን በእጅጉ ሊረዳቸው ይችላል።
(2 ቆሮንቶስ 1:11ን
አንብብ።) እግዚዝብሄር ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው አገልጋዮቹ በጸሎት አንድን ጉዳይ ደጋግመው ስለጠየቁት የሆነ እርምጃ ለመውሰድ አይገደድም፤ ይሁንና አገልጋዮቹ በቡድን ደረጃ ያላቸውን ፍላጎት የሚመለከት ከመሆኑም ሌላ አንዳቸው ለሌላው የሚያሳዩትን ከልብ የመነጨ አሳቢነት ግምት ውስጥ በማስገባት ለጸሎታቸው ምላሽ ይሰጣል። በመሆኑም ስለ ሌሎች የመጸለይ መብታችንንም ሆነ ኃላፊነታችንን አክብደን ልናየው ይገባል። ኤጳፍራ እንዳደረገው ሁሉ እኛም ለክርስቲያን ወንድሞቻችንና እህቶቻችን በጸሎት በመጋደል ለእነሱ ያለንን ልባዊ ፍቅርና አሳቢነት ማሳየት ይኖርብናል። እንዲህ ማድረጋችን የላቀ ደስታ ያስገኝልናል፤ ምክንያቱም “ከመቀበል ይልቅ መስጠት የበለጠ ደስታ ያስገኛል” የሐዋ. ሥራ 20:35
‘መዳናችን ቀርቧል’
ቅዱስ ጳውሎስ “ሌሊቱ እየተገባደደ ነው፤ ቀኑም ቀርቧል” የሚለውን ሐሳብ ከመግለጹ በፊት “ዘመኑን ስለምታውቁም ይህን አድርጉ፤ አማኞች ከሆንበት ጊዜ ይልቅ አሁን መዳናችን ይበልጥ ስለቀረበ ከእንቅልፍ የምትነቁበት ሰዓት አሁን ነው” ሲል ጽፏል። (ሮም 13:11, 12) የእግዚዝብሄር ቃል የገባው መዳናችንም እኛ ከምናስበው በላይ በጣም ቀርቧል። በመሆኑም መንፈሳዊ እንቅልፍ ሊይዘን አይገባም፤ በዓለም ውስጥ ያሉት ትኩረት የሚከፋፍሉ ነገሮች ብቻችንን ሆነን ወደ እግዚአብሄር መጸለይ የምንችልበት ጊዜ እንዳያሳጡን መጠንቀቅ አለብን። ከዚህ ይልቅ “በጸሎት ረገድ ንቁዎች ወይም ትጉዎች” እንሁን። እንዲህ ማድረጋችን ‘ቅዱስ ሥነ ምግባር እየተከተልንና ለእግዚአብሄር ፈቃድ ያደርን መሆናችንን የሚያሳዩ ተግባሮች እየፈጸምን’ የእግዚዝብሄርን ቀን እንድንጠባበቅ ይረዳናል። (2 ጴጥ.
3:11, 12) ደግሞም አኗኗራችን በመንፈሳዊ ህይወታችን ንቁ እንደሆንና የዚህ ክፉ ሥርዓት ፍጻሜ በጣም መቅረቡን በእርግጥ እንደምናምን የሚያሳይ ይሆናል። እንግዲያው ‘ያለማቋረጥ እንጸልይ።’
(1 ተሰ. 5:17) በተጨማሪም የጌታችንን የኢየሱስን አርዓያ በመከተል ለብቻችን ሆነን ወደ እግዚዝብሄር መጸለይ የምንችልበት ምቹ ሁኔታ ለማግኘት እንጣር። ጊዜ ወስደን ወደ እግዚዝብሄር የምንጸልይ ከሆነ ይበልጥ ወደ እሱ እንቀርባለን። (ያዕ. 4:7, 8) እንዲህ ማድረጋችን ታላቅ በረከት ያስገኝልናል!
መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል፦ “ክርስቶስ በሥጋ በኖረበት ዘመን ከሞት ሊያድነው ለሚችለው በከፍተኛ ለቅሶና እንባ ምልጃና ልመና አቀረበ፤ አምላካዊ ፍርሃት በማሳየቱም ተሰሚነት አገኘ።”
(ዕብ. 5:7) የጌታ ኢየሱስ ምልጃና ልመና ያቀርብ የነበረ ሲሆን ምድራዊ ሕይወቱን እስካጠናቀቀበት ጊዜ ድረስ ለእግዚዝብሄር ታማኝ ሆኗል። ከዚህም የተነሳ እግዚዝብሄር የሚወደውን ልጁን ከሞት በማስነሳት በሰማይ የማይሞት ሕይወት በመስጠት ክሶታል። እኛም ወደፊት ምንም ዓይነት ፈተና ቢያጋጥመን በሰማይ ለሚኖረው አባታችን ታማኝ መሆን እንችላለን። “በጸሎት ረገድ ንቁዎች ወይም ትጉዎች” ከሆን የዘላለም ሕይወት ሽልማት እንደምናገኝ የተረጋገጠ ነው።
5. በለአም ከእግዚአብሄር ከተስጠው መመሪያ የተነሳ እስራኤኦን ባረከ (ኦሪት ዘሁልቁ 22-24)
6. የእያሱ ጸሎት በአይ ባደረገው ጦርነት እርሱና የእስራ ኤል ህዝብ ከተሽነፉ በህዋላ (እያሱ. 10)
7. የዲቦራ ዝማሬና ለእዚአብሄር ያቀረበቺው ምስጋና (መሳፍንት
5)
8. ጊዲዮን እግዚአብሄር ምልክትን እንዲስጠው የጸለየው ጸሎት (መሳፍንት
6)
9. የሃና ጸሎት ልጅ ለመውለድ (1ሳም.
1)፤
ያቀረበቺው ምስጋና (1 ሳም. 2)
10.
የነብዩ ሳሙኤል ጸሎት ለ
እስራ ኤል ህዝብ (1 ሳሙ.
7
11.
የዳዊት ጸሎት (2 ሳሙ. 7፤ 1
መጽሐፈ ዜና መዋዕል
17)
12.
ዳዊት ስለመዳኑ ያደረገው ጸሎትና ምስጋና (2 ሳሙ
22፤ መዝ.
18)
13.
የስለሞን ከእግዚአብሄር ጥበብን ለማግኘት የጸለየው ጸሎት (1ነገሥ.
3፤ 2 መጽሐፈ ዜና መዋዕል 1)
14.
ስለሞን የስራውን ቤተመቅደስ ለ
እግዚአሄር ባቀረበ ጊዜ የጸለየው ጸሎት (1 ነገሥ.8 ፤ 2
መጽሐፈ ዜና መዋዕል 6)
15.
ነብዩ ኢሳያስ በኮሬብ ተራራ ላይ ያደረገው ጸሎት (1 ነገሥ.
18)
16. ነብዩ ኢልያስ የስማው የ
እግዚአብሄር ድምጽ (1 ነገሥ.
19)
17.
ስናህሬ በ
እስራ ኤል ህዝብ ላይ በዛተ ጊዜ የተደረገው ጸሎት ( 2 ነገስ. 19፤ ኢሳ. 37)
18.
የእግዚአብሄር ታቦት ወደ እየሩሳሌም በገባ ጊዜ የተደረገው ምስጋና (2 መጽሐፈ ዜና መዋዕል 16)
19.
የዳዊት ጸሎት ለልጁ ለስለሞን (2 መጽሐፈ ዜና መዋዕል 29)
20.
እዝራ የ እስራ ኤልን ህዝብ ወክሎ ስለሃጢያቱ በእግዚአብሄር ፊት ያደረገው ጸሎት ( እዝራ.
9)
21.
የነህምያ ጽሎት ለወገኖቹ (ነህሚያ 1)
22.
በእዝራ የተመራ የእስራኤል ህዝብ በ እግዚአብሄር ፊት ያደረጉት የንስሃ ጽሎት (ነህሚያ
9)
23.
ኢዮብ ስለደረስበት ሥቃይና መከራ እግዚአብሄርን ምክንያቱን ለማወቅ ጸለየ (ኢዮብ
10)
24.
እግዚአብሄር ጉዳዩን በእግዚአብሄር ፊት እቀረበ (ኢዮብ 13-14)
25.
ኢዮብ ያደረገው ጸሎትና ንስሃ (ኢዮብ 42)
የምልጃ ጸሎት
ለምኑ ይስጣችህዋል መዝጊያንም አናክዋኩ ይከፈትላችህዋል ተብሎ እንደተጻፈ ዛሬ እንደቃልህ መስረት በተለያየ ጥያቄ ላይ ያሉትን ክርስቲያኖች ወንድሞቼንና እህቶቼን ይዤ በፊትህ እቀርባለሁ አንተን የሚወስንህ የለም ስለሆነም በአለም ዙሪያ በኢንተርኔት ላይ ይህንን የጻፍኩትን ለሚያነቡ ሁሉ እንድታስባቸው ለተቸገሩበት ነገር ሁሉ መልስ እንድትስጣቸው ጌታ እግዚአብሄርን ለመከተል ፈልገው ያቃታቸውን የጸጋ ሁሉ አምላክ ከላይ ከስማይ ጸጋህ እንዲለቀቅላቸው እስለያለሁ። በአለም ዙሪያ በስደት ላይ ላሉ ሁሉ እግዚአብሄር አምላክ ሆይ እንደቸርነትህና እንደባለጠግነትህ መጠን በክርስቶስ ኢየሱስ የሚያስፈልጋቸውን ሁሉ ሙላባቸው የቸገራቸውንና ጥያቄያቸውን ስለምታውቅ ለልባቸው ተናገር በመንፈስ ቅዱስ ደግፋቸው መልስም እንድተስጣቸው እማጸንሃለሁ ይህንን ጸሎቴን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም በፊትህ አቀርባለሁ ስለስማኸኝም አመስግንሃለሁ። አሜን!
በጸሎት አማካኝነት የሚገኝ ፈውስ
ስለ እኔ እና ስለ ሌሎች የጸሎት ልምዶች በአእምሮና በሰውነት ፈውስ ዘዴዎች መካከል ምስክርነት እሰጣለሁ፣ ጸሎት በሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ ሰርቷል፣ እና ሕይወትን ለመለወጥ እጅግ በጣም አስፈላጊው ስልት ሊሆን ይችላል። በጸሎት ምን ማለት ነው? ብዙዎቹ ክርስቲያኖች እንደሚሉት "ጸሎቶች ከእግዚአብሔር ነገሮች እየጠየቁ ማግኘት ነው።" ይሁን እንጂ "እግዚአብሔር ሥራችንን እንዲያከናውንልን ከመጠየቅ ያለፈ ነገር ነው ማለትም በሀብታሙ ሰው በር ላይ የፈለገው ፈላጊው ከፍ ያለ ነገር አለ ብሎ ነው።
“ጸሎት" የሚለው ቃል በእውነት "ወደ እግዚአብሔር የሚመጥን" ማለት ነው። ሁሉም እውነተኛ ጸሎት እግዚአብሔር ራሱ ነው፤ ምክንያቱም ከእርሱ ጋር የምንፈልገውን ሁሉ እናገኛለን፤ ጸሎት ማለት "ነፍስ ወደ እግዚአብሔር መዞር" ማለት ነው። ንጉሥ ዳዊት ሕያው ነፍስ ወደ ህያው እግዚአብሔር እንደሚለቀቅ ይገልጻል. "ነፍሴ ሆይ: ወደ አንተ እጸልያለሁ; ነፍሴንም (ነፍሴ) ትወድሳለች (መዝ 25 1) ጌታችን ኢየሱስ ነፍሳችንን እንዲመለከት ስንፈልግ፣ የቅድስና ውበት ለማግኘት እኛ ነፍሳችንን በጸሎት ወደ እግዚአብሔር ስንመልስ፣ እግዚአብሔር የሚፈልገውን ሁሉ ለማድረግ እንድንችል እድል ይሰጠናል፣ እግዚአብሔር ሁልጊዜ ከእኛ ጎን ነው።
የአይሁድ አረጋዊ አባቶች መንፈሳዊ ጸሎትን ሲገልሱት "ጸሎት፤ ሰማይና ምድር የሚሳሳሙበት ጊዜ ነው" ብለዋል። ስለዚህ ጸሎት ስንጸልይ እግዚአብሔር እንዲያደርግ የምንፈልገውን እንዲያደርግልን እየጠየቅነው ነው። እግዚአብሔር ሁልጊዜ ለታላላቅ ደስታችን ዓላማ ነው፣ምንም እንኳን በድንቁርና ያቀረበው ጸሎት እንኳን ቢኖር ያለማቋረጥ ስንጸልይ፣ የእኛ ፈቃደኛነት መልስ ሊያመጣ ይችላል።
አንድ ጸሐፊ እንዳሉት፣ ብቻችንን ስንሆን አዘውትረን ስሜታችን ለጸሎት ይነሳል፤ በውስጣችን "በቃላት በጥልቀት" የእኛን የጥፋተኝነት ስሜት፣ ጎዳታችንን፣ በአካባቢያችን ላይ እንጸልያለን፣ ጉባኤን ወይም ቤተክርስቲያንን እስክናገኝ ድረስ እስክንጸልይ እንጸልያለን። እነዚህ ጸሎቶች ወደ ሙሉ ብስለት እንዲጎለብት ከጸሎት ማህበረሰብ ጋር የተዋሐዱ መሆን አለባቸው። በአንዳንድ ሰዎች አእምሮ ውስጥ ጸሎት ለድንገተኛ አደጋ ብቻ ነው! አደገኛ ሥጋት ሲይፈጥራል፣ ሕመም ሲመጣል፣ እና ነገሮች ሲጎድላሉ - ከዚያም ይጸለያል፤ ይሁን እንጂ ጸሎት አንድ ነገር ለእግዚአብሔር ብቻ መሰጠትን እንድናስታውስ ስለሚረዳን በጣም አስፈላጊ ነገር ቢሆንም ጸሎት ግን አንድ ነገር ነው። ከእግዚአብሔር ጋር መነጋገር ማለት ነው። ከእነርሱ ጋር በመነጋገር ሰዎችን ማወቅ እንችላለን፣ እኛም በተመሳሳይ አምላክን በጸሎት እናውቀዋለን፣ የጸሎት ከፍተኛ ውጤት ከክፉ ነገር መከለል ወይም የተሸፈነ ነገርን መያዙ ሳይሆን፣ ስለ እግዚአብሔር እውቀት ነው። "(ዮሐ 17 3) አዎን፤ ጸሎት ተጨማሪ ስለ እግዚአብሔር ማግኘት፣ እናም ይህ ላንድ ስው ነፍስ እጅግ ግዙፍ ግኝት ነው።" አሁንም ቢሆን ሰዎች እንዲህ ብለው ጮኹ: - " ምን እንዳገኘው አውቅ ነበር፣ወደ መኖሪያ ቤቴ እኼዳለኹን? "(ኢዮ 23: 3)።
ጸሎት የእግዚአብሔር መገኘት ብቻ ነው፤ የእግዚአብሔር መገኘት በሕይወታችን ውስጥ ትልቅ ለውጥ ያመጣል። በመጀመሪያ፣ እግዚአብሔርን ያለማወቅ ምን ያህል እውቀት ማጣት እንዳለበት ማወቅ አለብን፤ እራሳችንን ለመለካት ሳይሆን ስለ እግዚአብሔር ባለን እውቀት በቤተክርስቲያናችን ውስጥ በስጦታ እና ኃላፊነት ስንቀመጥ እኛ በምንጸልይበት ጊዜ በልባችን ውስጥ ምን እንደሚክሰት መገንዘብ አለብን። ጌታ እንዲያሳየን እንጠይቅ።
ሁለተኛ፣ ጸሎት አዳኝን መፈለግ ነው። ጌታ በምድር ላይ በነበረበት ጊዜም ሰዎችን ከእሱ ጋር እንዲተባበሩ ይጋብዛል፤ ስለዚህም እርሱን እና አባቱን እንዲያውቁ ለማድረግ ነው። የብሉይ ኪዳን ጌታ የኢየሱስን መገለጦች ቅድመ-ፅንሰ-ሃሳቦች የዳንኤል መጽሐፍ እነዚህ ሁለት ምሳሌዎች እንደነበሩ ይነግረናል-በአራቱ የዳንኤል ከሦስት ጓደኞች ጋር 'እንደ አማልክት ወንድ ልጅ' (3:25 RSV) እሳቱ ውስጥ ማን ነበር? አምላክ ዳንኤልና ጓደኞች በችሮቻቸው ውስጥ በነበሩበት ጊዜና ዳን ዔል በአንበሾች ጉድግዋድ በተጣለ ጊዜ አንበሶችን አፎች እንዲደፍኑ የላከው መልአክ ማን ነበር? (6 22)። ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ስው እንደግል አዳኙ አድርጎ በተቀበለው ጊዚእ በመንፈሱ በስው ውስጥ ይኖራል፤ በአካል ውስጥ አለ፤ አሁንም እግዚአብሔርን በጸሎት ፈልገን እንደነዳንዔልና ግዋደኞቹ ማግኘቱን እናገኛለን። ጌታ እስኪያገኙ ድረስ ፈልገውት ያገኙታል፤ ምክንያቱም ቃሉ በሙሉ ልባችን ስንፈልገው እርሱን እናገኛለን በቃሉ ስለተጻፈ። ፈልጉን ታገኙኛላችሁ መንዝጊያን አንክዋኩ ይከፈትላችህዋል (ማቴ. 7፡7)
አማኞች/ ክርስቲያኖች ጸሎት ልክ እንደ እስትንፋስ አየር ስለሆነ ያለሱ መኖር አንችልም። ከእግዚብሔር ጋር ያለንን መንፈሳዊ ሕይወት በተመሳሳይ መንገድ እንደ እምነታችን እኛን ከእግዚአብሔር ጋር የሚያገናኘን የእምነታችን በጣም መሠረታዊ እና አስፈላጊ ነው። ጸሎት እንደ ሃይማኖታዊ እንቅስቃሴ እና ክስተት እንዲሆን አስፈላጊ አይደለም፤ ነገር ግን ለክርስቲያናዊ አኗኗራችን ብልጽግና እውነት የሆነ እንደሆነ አስፈላጊ ነው። በተጨማሪም ከፈጣሪያችን ጋር ያለን ግንኙነት ፍላጎታችንን ለማሟላት የእርሱን ታላቅነትን፣ ሀይልን እና ችሎታን በመቀበል ሙሉነታችንን ከፍ የሚያደርግ ነው። ሳናቋርጥ የእግዚአብሔርን ፊት በጸሎት ስንፈልግ፣ መንፈሳዊ ሕይወታችንን የሚያንፀባርቅ በሆነው መንፈሳዊ እድገታችን ውስጥ ፈጣንና ተጣጣፊ ለውጥ እንዲመጣ የሚያደርገውን ፈጣን ውጤት የሚያመጣውን በቃሉ ውስጥ ይሰጠናል።
ጸሎት በአስቸኳይ ጊዜ እንደ መሰረታዊ ግምት ብቻ ሳይሆን፣ ደስተኞች ስንሆን፣ አንዳንድ ጊዜ ግን በውጊያው እና በአስጨናቂ ጊዜ ውስጥ ወደ ጸሎት እንገፋፋለን። መጽሐፍ ቅዱሳችንን እና በብሉይ ኪዳን ውስጥ እና በቅዱስ ቅዱሳን የተጻፉ ጽሑፎችን ስንመለከት በእያንዳንዱ የሕይወት ጎዳና ውስጥ የጸሎትን ኃይል አረጋግጠዋል። ህይወታችንን ትርጉም ባለው መልኩ ለመምራት እንዲረዳን በተረጋጋ እና ጠንካራ መያዣን ለማንበብ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ወሳኝ ነጥቦች ያስፈልጉናል፤ በዚህ ታሪክ ላይ በመታመን በጸሎታቸው ምክንያት ህያው የሆኑ የሰዎች ምስክሮች አለን። ለእርሱ ስንጸልይና በእሱ ላይ ስንታመን፣ ይህንን ሁኔታ ለማሸነፍ እና ድፍረትን እና የድል ህይወትን ለመምራት ለእኛ ያለውን ችሎታ እና ጥበብ እናውቃለን።
እግዚአብሔር የኃይልና የፍቅር ራስንም የመግዛት መንፈስ እንጂ የፍርሃት መንፈስ አልሰጠንምና። እርሱም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። እግዚአብሔር ሙላቱ ሁሉ በእርሱ እንዲኖር በእርሱም በኩል በመስቀሉና በደም ሰላም አድርጎ በምድር ወይም በሰማያት ያሉትን ሁሉ ለራሱ እንዲያስታርቅ ፈቅዶአልና። እርሱ ያስተማረው ቃል ኢየሱስ የመጣበት ምክንያት ስለዚህ ክርስቶስ ያቀደው ጸሎት በሦስት ክፍሎች የተዋቀረ ነው። በንግግሩ የተነገረው በጸሎት በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት በእርሱ ደቀመዛሙርቱ እንዲፀልዩ ዮሐንስ አስተምሯቸዋል፤ ነገር ግን የጆን ተግባሮች ሁሉ በክርስቶስ መሠረት ላይ ተመስርተው ነበር እስከ "አድጋለሁ" ዮሐንስ ራሱ "መሻት" እና "ራሱን መጎነዝ" እንደሚመጣ አስቀድሞ ያውጃል - ከመንፈሱ ጋር ለጌታ ይሄድ ነበር፣ ስለዚህ ዮሐንስ ፀሎትን ያስተማረው ከምን አይነት ጸሎቶች ውጭ ሊሆን እንደማይችል ነው፤ ምክንያቱም ምድራዊ ነገሮች ለሰማያዊ ስፍራዎች ሰጥተዋል. ከዚህም በላይ, ጥበብ በተከታይ ደረጃ ስኬታማ ስለሆነ በእምነቱ ትሁትነት፣ እግዚአብሔር ጌታን በቃላት መቅረብ እንዳለበት እናስገነዝባለን። ጸሎት በሙሉው ወንጌል ተጠቃሎ የቀረበ ነው።
መፈወስን መቀበል
እንደምሳሌ፣ የታመሙ ሰዎችን ለመፈወስ የጸሎት መቀበሉን አስፈላጊነት በተመለከተ የምስክርነት ቃሌን እሰጣለሁ። በጸሎት ቡዴን ሲሳተፍም በግልሞ በጸልቴ ህይወቴ ውስጥ እጅግ ግልጽ የሆኑ ክስተቶች ነበሩኝ። ይህም አርብ ስብሰባ በቤተ ክርስቲያናችን ውስጥ ተከናውኗል። አምላክ በስሜታዊ ሁኔታው እና በአልኮል ስለታወቀው ግለሰብ እና ባህሪው በየትኛውም ቦታ ተቀባይነት ስለሌለው ግለሰብ ገለጸልኝ። የማይታወቅ ፕሮግራሞችን ቢወስድም ከዚህ ህክምና ምርጡን ለማግኘት አልሞከረም፣ የተስፋ መቁረጥ ስሜቱንና በመቆጣጠር እና በመርማሪነት ጊዜ በሰዎች ውስጥ በመዋጋት እና በህግ ፊት ሲገጥም ነበር። ይህ ችግር (በቃላት እና በአካል ጋር መዋጋት) ከተለያዩ ግለሰቦች በተደጋጋሚ አልተገለጠም፤ ምክንያቱም ማንም ሰው በቁም ነገር ቢወስድም ሁሉም ሰው ቤተ ክርስቲያን እንዳይሳተፍ ሊያደርገው ስለሚችልና በቤተክርስቲያን ውስጥ እንደጠጪ አድርገው ይቆጥሩ ስለነበር ነው። በእዚያ አርብ ምሽት፣ ልክ አንድ ሰባኪ ቡድኑን ለጸሎት ያዘጋጀውን የእግዚአብሔርን ቃል አቀረበ፤ በእዚያም ምሽት ክጸሎቱ ክፍል ወጥቶ ከሄደ በኋላ የትስበከውን ስብከት ቃል በቃል መዋጋት ጀመረ፤ በዚህ ሁኔታ ላይ እግዚአብሔር ጥልቅ ማስተዋል ሰጠኝ እና ወደ ኮሪደሩ በመሄድ ተመልሶ እንዲመጣ ጠየኩት፤ ከራሱ ጋር ማውራቱን ሲቀጥል በልቡ ውስጥ ቁጣና እርግማንን መያዙን ተረዳሁ፣ መንፈስ ቅዱስ ወደእኔ አመጣ፣ ለካስ ይህ ስው "እርሱ የአጋንንት መንፈስ ይዞት ነበር።" ተመልሶ ሲመጣ የጥላቻን መንፈስ በኢየሱስ ስም ገስጽኩት እናም ቀዝቅዞ ወደ ኮሪደር መጣ ሆኖም ግን፣ እግዚአብሔር ስለዚህ ስው በልቤ ውስጥ በአጋንንት ሥር እንደሆነ በልቤ አስቀመጠ፤ እኔም ይህንን ስው ክፉ የሚያስሩት እርኩስ መናፍስት ከእሱ እየወጡ እንደሚመጡ ስለማምን በቀጣይነት መጸለይ ቀጠልኩ። "ከሁሉም ሰው በጣም አስገራሚ የሆነው እርሱ ሁልጊዜ አንድም ስብሰባ አያመልጠውም ይሁን እንጂ በየትኛውም ስብስባ አልተፈወስም። መጸለዬን ቀጠልኩኝ። ይህም ስው በተከታታይ ከጸሎት ፕሮግራሞች አይቀርም አንድ ቀን ግን የርሱ ቀን መጣ። በመፈስ ቅዱስ ምሪት ከመጽሐፍ ቅዱስ አውጥቼ ድምጼን ከፍ አድርጌ ማንበብ ጀመርኩ፤ ይህም ስው ቃሉን ሲስማ ዘፍ ብሎ ወደቀ። የእግዚአብሔርን ቃል በማሰላሰል እና በመንፈስ ቅዱስ በልሳኖች እየጸለየኝ እያለ በዚያው ምሽት የፀሎቴ ገጠመኝ ሆነ።
የእግዚአብሔርን ቃል በተነበበ ጊዜ እርሱ መሬት ላይ ወድቆ እና ሰውነቶቹን መንቀጥቀጥ ጀመረ፤ በዚያው ምሽት መናፍስት ወጡ መንፈስ ቅዱስ በዚያ ተገኝቶ ከእግዚአብሔር በጸሎት ሃይል ተፈወስ። ይህ ግለሰብ ፈውስ እውነተኛ ሆነ፤ በቤተክርስቲያን በሚደረገው ጸሎት በቶሮንቶ ይህ የመፈወስ ሂደት ተካሄደ። ከዚያን ቀን ጀምሮ፣ ይህ ሰው ተለወጠ እና በክርስቶስ ውስጥ የተትረፈረፈ ህይወት አለው፤ አሁን ይህ ሰው ትዳር መስርቶ እና ሁለት ልጆችን ያቀፈ ነው። ይህ የእኔ የጸሎት ተሞክሮ ነው። ብዙውን ጊዜ ስዎች እጃቸውን ለመሰጠት በቀላሉ ሊቋቋሙት በማይቻላቸው ህመሞች እና በእራሱ ቁጥጥር ወደ እግዚአብሄር የሚደረጉ ስሜቶችን ለማቅረብ ይረዳል።
ሌላው በጣም አስደናቂ መጻሕፍት ላሪ DosKey, MD በነፍስ በማገገም ላይ በጸሎት ውጤቶች እና በነፍሳችን ሕልውና ላይ ምርምርን የሚያካሂድበት ነው። ተመራማሪዎች በሳን ፍራንሲስኮ ውስጥ በሚገኙ ሆስፒታል በሽተኞች ላይ መጸለይ የሚያስከትለውን ውጤት ዘመናዊ ጥናት አደረጉ፣ ታካሚዎች ዶክተሮች እና የሆስፒታል ሰራተኞች ስለ ጥናቱ አያውቁም ነበር - የሆስፒታሉ አስተዳዳሪ ብቻ ነው የተሳተፈው፣ ተመራማሪው በሆስፒታሉ ውስጥ ለሕመምተኞች ሆስፒታል የገቡ ታካሚዎች ዝርዝርን በግማሽ ተከታትለዋል፤ ከህመምተኞቹ ውስጥ ከግማሽ በላይ የሚሆኑት ከክልል ውጭ በሚገኙ የሰዎች ቡድኖች ተጸጽተው እና ሌላኛው ግማሽ ጸሎት አልተጸለየላቸውም። ውጤቱም አስገራሚ ነበር፣ የተጸለየላቸው ቡድኖች አነስተኛ ችግሮች ኖሮአቸው የሚወስዱት መድሐኒት እንደቀነስ ግኝቱ ያመለክታል። ያልተጸለየላቸው ሌሎች ቡድኖች ደግሞ ያሉበት ሁኔታ አልተሻሳለም ምናልባትም በጸሎት የማያምኑ ቡድኖች ይሆናሉ ብዬ አምናለሁ። ይህ ጥናት እና ሌሎች ጸሎት ፀጋ ሊለወጥ የሚችል መሆኑን ያመለክታሉ።
በእርግጥ፣ እነዚህ ሁሉ ልምዶች ሁልጊዜም በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል የእግዚአብሔርን ታማኝነት ያስታውሰኛል። የእርሱ ታማኝነት አሁንም ለእኛ ተመሳሳይ ነው፣ የሞተው: ይልቁንም ከሙታን የተነሣው: በእግዚአብሔር ቀኝ ያለው: ደግሞ ስለ እኛ የሚማልደው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው። "ሌላው ምልጃ የሚያተኩረው ስለ ምልጃ 1Ti 2: 1 በዚህ የቅዱሳት መጻሕፍት ክፍል ውስጥ ነው። "እንግዲህ፣ ከሁሉ አስቀድማችሁ (ምልጃ)፣ ጸልዩ፣ ጣልቃ መግባት፣ ምስጋናም ለአምላካችን ይሁን" የሚል ትእዛዝ ሰጥቷል። እናም ዕብራውያን 7፡ 25 ስለኢየሱስ ክርስቶስ የማዳን ኃይል የሚዳሰሰው፣ "ስለዚህ, (ክርስቶስ) በእርሱ ወደ እግዚአብሄር የሚደርሳቸው ሊያድናቸው ይችላል። ይህም ለእነሱ መማለጃ ሆኖ ለዘላለም ይኖራል "(ኢሳያስ 58 6፣7) በምርጫዎች ላይ አፅንዖት ሰጥቷል። "ይህ እኔ የመረጥኩት ፈተና አይደለምን? እናንተ ክፋትን ትሰብሩ ዘንድ…ፍጹማን ያደርጋችኋል። ከላይ የተመለከቱት የምልጃ መሰረታዊ መርሆች ክርስቲያናዊውን ሸክም እርስበርስ ሸክም እንደሆኑና የክርስቶስን ህግ እንደሚፈፅሙ (ገላ .6: 2). በችግሮች፣ በበሽታዎች፣ በሰይጣን እንቅስቃሴዎች ወይም በማንኛውም ነገር ውስጥ መጓጓዣ ጸሎት መቅረብ አለበት፤ የእግዚአብሔር ቃል ለህዝቡ ማማለድ ነው (ኢሳያስ 59፡ 16)።
0 comments:
Post a Comment