
የሕብረተስብ ጤንነት
ክፍል 1
በዶ/ር አመለወርቅ
በመጽሐፍ ቅዱስ ጊዜ የታወቁት ህዝቦች ፍልስጤምና ግብጻውያን ኢትዮጵያውያን ወዘተ ነበሩ። የፍልስጤም ሕብረተስብ በጥንት ጊዜ ከግብጽም በበለጠ ጤነኛ ሕብረተስብ የሚገኝበት ተብሎ ይወስድ ነበር። የግብጽ ሕብረተስብ ጤንነት በምን አይነት ደርጃ ላይ እንደነበረ (ዘዳግም 7፡15 ዘዳግም 28፡60 አሞጽ 4፡10) የተመለከቱት ጥቅሶች ያመለክታሉ። በእብራውያን ህብረተስብ መካከል የጽዳቱ ሥርዕትና በቀሳውስቱ የሚደረገው ቁጥጥር የህዝቡ የጤና ጥበቃው ወደ ክፍተኛ ደርጃ አድርሶታል፤ ነገር ግን ይኸው የጽዳቱ ሥርዕትና ቁጥጥር በስፋት የተራመደ አልነበረም፤ በመጽሐፍ ቅዱስ ጊዜ የነበሩት በሽታዎች ለጉዳት የሚዳርጉ የስውነት ትኩሳቶች የጠነከሩ የቆዳ በሽታዎች ሽባነት ተቅማጥ የተለያዩ የአይን በሽታዎች ሲሆኑ እነዚህም በሽታዎች በበሽተኛው ላይ መንፈሳዊና ሥነ-ልቡናዊ ጫና ላይ ያስከትላሉ። በመጽሐፍ ቅዱስ ጊዜ የነበሩት በሽታዎች እየተባባሱ የሄዱበት ወቅት ነበር ከነዚህም መሃከል የተለያዩ የስውነት ትኩሳቶች ተቅማጥ የቆዳ ላይ ለምጽ ወይም ቁምጥና የአንጀት ውስጥ ትላትል መቅስፍት የነርቭ በሽታዎች (እንደሽባነት) የተለያዩ የአይን በሽታዎች እነዚህም በተለያዩ ስሞች ተስጥቷቸዋል። እነዚህም ስሞች ሕመም ወይም ደዌ በሽታ ሥቃይ ሲሆኑ እነዚህም 2 ነገስት 1፡2: 2 ነገሥት 8፡8 ማቴ. 9፡35 ማቴ. 8፡17 ዮሐ. 5፡4 ሉቃ. 7፡21 መዝ. 38፡7 ተመልክተዋል። በአሁንም ዘመን ስድስት ተላላፊ በሽታዎች የተነሳ ከሚሞቱ ሰዎች መካከል 90% ምክንያት ኤች አይ ቪ / ኤድስ የተቅማጥ በሽታ ሳንባ ነቀርሳ ወባ እና ኩፍኝ አጣዳፊ የመተንፈሻ ኢንፌክሽን (ሞት ሊያስከትል ይችላል)ተላላፊ በሽታዎች በአብዛኛው እነዚህ በሽታ-አምጪ ጀርሞች ባክቴሪያዎች ቫይረሶች ፈንገሶች protozoans, እና ጥገኛ ትሎች ውስጥ የተለያዩ ያካትታሉ።
የመጀመሪያው ስለፓራሳይቶች ጽሑፍ በ 3000 እስከ 400 BC በግብጾች በፓፓይረሳቸው ላይ ተጽፎ የተገኘው ነው።
በጽሁፉም ውስጥ ራውንድዎርምስ ጊኒዎርምስ ትሬድዎርምስ ቴፕዎርመስ እንደነበሩ ያመለክታል።
እንደ ግብጻውያንም የጥንቶቹ ግሪኮች ሂፓክራተስና አሪስቶትል አያሌ ፓራሳይቶችን አጥንተው መዝገበዋል። ከተመዘገቡትም መሃከል በሄፓክራተስና በአሪስቶትል በወቅቱ የነበሩትን Corpus Hippocraticus በተባለው መጽሐፋቸው ውስጥ የመዘገቧቸው ነበሩ። በዚህ መጽሐፍ ውስጥ አያሌ ፓራሳይቶች በአሳዎችና በቤት እንስሳትና በስዎች ወስጥም እንደሚገኙ አስቀምጧል። ፓራሳይቶችም በሽታዎችንም እንደሚያመጡ ጠቀስዋል ከነዚህም መሃከል በጊኒዎርም የተነሳ የሚመጣው በሽታ dracunculiasis የተባለው ነበር።
በዚያን ጊዜ በተለያየ ባህል ውስጥ የነበሩት ሕዝቦች እንደ አረቦችና ባቢሎናውያን እንደዚሁ
ስለፓራሳይቶች ጽሑፍ ነበራቸው። በጥንቱ ግሪክና ሮማውያን ጽሑፍ ውስጥ ብዙ ፓራሳይቶች የተለዩ አይደሉም ምክንያቱም የበሽታዎቹ ምልክቶች ከሌሎቹ በሽታዎች ይመሳስላሉ ከሚመሳስሉትም መሃከል ፍሉ የብርድ በሽታ ተቅማጥ ናቸው። እንደ እለፋንታያሲስ (Elephantiasis) ሲስቶሶማያሲስ (Schistosomiasis) ወባ (Malaria) እና አሜባ (Amebiasis) ያሉት በሽታዎች መነሻቸው ከፓራሳይቶች የተነሳ ቢሆንም የተለየ የበሽታ ምልክቶች እንደሚያስከተሉም የሕክምና ጽሑፋቸው ያመለክታል። በጊኒዎርም የሚነሱት በሽታዎች በጥንቃቄ ተጽፈው የተገኙት ሴቷ የጊኒዎርም የምተፈላው በቆዳ ላይ ስለሆነ ይህም የሚያምና የማቃጠል ምልክቶችን ስለሚያመጣ የሚታለፍ አልነበረም። ይህም የተለየ በሽታ በመጽሐፍ ቅዱስ በብሉይ ኪዳን በስፋት “fiery serpents” ተብሎ ተወስዷል።
ስሜን አፍሪካ መከከለኛው ምስራቅና ሞሶፓታሚያ
የጥንቱ የፓርሺያው ዶክተር Avicenna አያሌ ፓራሳይቶች በእንስሶችም ሆነ በበሽተኞቹ ውስጥ እንዳሉ መዝግቧል ከመዘገባቸውም መሃከል የጊኒዎርም የትሬድዎርምስ ቴፕዎርምስና አስካሪስ ዎርምስ ይገኙበታል። ይህም የአረቦች ባህላዊ ህክምና ከሺ አመታት በላይ የሚያመላክተው በቀይ ባህር አካባቢ ይሁን እንጂ የህክምናው ጽሑፍ በበሽታዎችንና በፓራሳይቶች መካከል ግንኙነቶች እንዳላቸው አያስረግጥም። የመካከለኛው ምሥራቅ የህክምና እንደግሪኮቹና ሮማውያን ጽሑፍ የጊኒዎርም የበሽታ መነሻ እንደሆነ ጽፏል። በአያሌዎች የአሲሪያን ጽሁፎች ውስጥ በተለይም በንጉስ Ashurbanipal ቤተመጻሕፍት ውስጥ የሚገኙት የጊኒዎርምስ የበሽታ መነሻ እንደሆኑ ያመለክታሉ። በግብጽ ውስጥ Ebers በተባለው በጥንቱ ፓፓይረስ ጽሑፍ ውስጥ የተገኙት ጥቂቶች አመላካቾች ሁክዎርምስ በሽታን እንደሚያመጡ ቢጠቀስም ያስቀመጠው በደፈናው ነበር ። በሌላው የግብጽ የሕክምና ጽሁፍ ውስጥ ደግሞ ኢለፋንታያሲስ ስለተባለው በሽታ የተጻፈው ምልክቶቹ በእግሮችና በእጆች በጡቶችም በሴትና በወንድ ብልቶች ላይ እብጠትን እንደሚያስከትል ነበር። በኢለፋንታያሲስ ከታመሙትም መሃከል
የግብጽ ፈርኦንን Mentuhotep II የተባለው ሲሆን በዚሁ በሽታ ከተስቃየ በኋላ እንዳገገመ ተጽፎ ይገኛል። ኢለፈንታያሲስ የተባለው በሽታ በአረቦች ሃኪሞች Avicenna ጨምሮ ስለበሽታው ከማወቃቸውም ባለፈ በቁምጥናና በኢለፈንታያሲስ መካከል ያለውን ልዩነትም ጥንቀቀው አውቀውት ነበር። በጥንቱም ግብጽ ህብረተስብ ውስጥ ሲስቶሶማያሲስ ይታወታል ሌላው ስሙ ቢላርዚያ ይባላል።
ከላይ ከተጠቀሱት ታሪኮች አንባቢው ፓራስይቶች በተመለከተ በጥንት ጊዜም የነበሩና በአሁኑ ጊዜ የበለጠ እየተባዙ እንዳሉና ለተለያዩ በሽታዎች መነሻዎች እንደሆኑ ከተጻፈው ይረዳል።
በባክቴሪያዎችንና በቫይረሶች የተነሳ የሚመጡ በሽታዎች
1. ባክቴሪያዎች በሽታዎችን ያመጣሉ
አያሌ ጥናቶች አብዛኛውን የስው በሽታ የሚመጣው በባክቴሪያ ወይም በቫይረስ በሚመረዝበት ጊዜ እንደሆነ ያመለክታሉ። እነዚህም ጥናቶች የሚደገፉትና የሚካሄዱት በአሜሪካን በሚገኘው የዲፓርትሜንት ኦፍ ሄልዝ የተላላፈ ሕመሞች መቆጣጠሪያ ክፍል ነው። በካናዳም እንደዚሁ የጥናት ዲፓርትሜንት አለው።
ባክቴሪያዎች እያንዳንዳቸው በተፈጥሮ ነጠላ ሴል ያላቸው ፍጥረቶች ሲሆኑ የሚመሳስሉት ከተክሎች ጋር ነው። ባክቴሪያዎች በአለም ላይ በየትም ሥፍራ የሚገኙ ሲሆኑ ሁሉም ባክቴሪያዎች መጥፎ አይደሉም ለምሳሌ ያህል በሆድ ውስጥ የሚገኙት ባክቴሪያዎች የቃሚዎች ናቸው። አንዳንዶቹ ባክቴሪያዎች ደግሞ በመመረዝና በሽታዎችን በማምጣት ይታወቃሉ። ባክቴሪያዎች ከመረዙ በኋላ በሽታዎችን ማምጣት የሚችሉት ፓቶጀኒክ ባክቴሪያዎች ተብለው ይጠራሉ። በባክቴሪያዎች መመረዝ የተነሱ በሽታዎች ሁሉ በአንቲባዮቲክ መድሀኒቶች ይታከማሉ። ይሁን እንጂ አንቲባዮቲክን መጠቀም ደግሞ አስፈላጊ የሆኑትን ባክቴሪያዎች ያጠፋሉ። አንቲባዮቲክን የሚቋቋሙ በክቴሪያዎች ደግሞ ይነሳሉ። ይህንንና የመሳስሉትን በባክቴሪያ የተነሳ የሚመጡትን በሽታዎች ለመከላከል ኮንቬንሽናል ሜዲስን የሚጠቀመው ለዚሁ የተስሩ መድሐኒቶችንና ክትባትን መስጠት ነው።
2. ቫይረሶች በሽታዎችን ያመጣሉ
ቫይረሶች በስውነት ውስጥ ከገቡ በኋላ በመደበቅ የሚቋቋሙት የግለስቡን የስውነትን ኢሚውን ሲስተም ነው። ቫይረሶች በጣም አነስተኛ ማክሮኦርጋኒዝም ስለሆኑ የሚባዙትም በገቡበት ስውነት ውስጥ ስለሚሆን በጣም ጠንካራ የሆኑ ተላላፊ በሽታዎች በህክምናው አለም ለማጥፋትም አስቸጋሪ ያደርገዋል።
(ፓቶጀኒክ ባክቴሪያ) በሽታን አስተላላፊዎቹ ወደ ስው ስውነት የሚገቡበት መንገድ ከዚህ እንደሚከተለው ነው። በአካል ላይ የተቆረጠ ወይም ክፍት በሆነ የስውነት ክፍል በኩል፣ በተበላሽ ምግብ ወይም ውሃ፣ በባክቴሪያዎች ከተመረዘው ግለስብ ጋር በመነካካት፣ በባክቴሪያዎች ከተመረዘው ግለስብ የሚወጡትን እንደ ስገራና ሽንት ሌሎችንም ፈሳሽ በመንካት፣ በባክቴሪያዎች ከተመረዘው ግለስብ ጋር በሚስልበት ወይም በሚያነጥስበት ጊዜ ከውስጡ የሚወጣውን ፈሳሽ ወይም አየር በአጠገቡ ሆኖ በመተንፈስ፣ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ በባክቴሪያዎች የተመረዘው ግለስብ የተጠቀመባቸውን ዕቃዎችም የፈት መታጠቢያዎች ላይ ያሉትን ቧንቧዎችን የሽንት ቤት ውሃ መለቂያዎች ወዘተ. በመንካት መራዦቹ ባክቴሪያዎች ከተመረዘው ስው ወደጤነኛው የማለፊያ መንገዶች ይሆናሉ።
3. ፓራሳይቶች የተለያዩ በሽታዎችን ያመጣሉ
ፓራሳይቶች ለተለያዩ በሽታዎች መነሻ ናቸው። ፓራሳይቶች ሕይወት ያላቸውና በስውነት ውስጥ ከገቡ በኋላ በገቡበት ስውነት ውስጥ የሚኖሩና የሚመገቡት የገቡበትን ስውነት ሴሎችና ግለስቡ የሚመገበውን ምግብ ወይም እንደተጨማሪ የሚውስዳቸውን ሁሉ በመጋራት ነው። ፓራሳይቶች ብዙ አይነት አላቸው እነዚህም በሁለት ይከፈላሉ ወርምስና ፕሮቶዞዋ ይባላሉ። ፕሮቶዝዋን የሚባሉት ነጠላ ሴሎች ያሏቸው የሚመገቡትም ኦርጋኒክ ኮምፓውንድ እንደ ናይትሮጂንና ካርቦንን ነው ለዚህም ጥሩ ምሳሌ የሚሆኑት አሜባዎች አሜባ ናቸው። አሜባዎች ትናንሽ ከሚሆናቸው የተነሳ የሚታዩት በማክሮስኮፓ ነው። ሌሎቹ ክፍሎች ደግሞ ዎርምስ ናቸው ዎርሞች ብዙ ሴሎች ያላቸው ሲሆን በመጠናቸውም የተለያዩ ናቸው። ዎርሞች ወደ ስው ስውነት ውስጥ
ከገቡ የገቡበትን ሥፍራ በመባዛት ይቆጣጠሩታል። ለምሳሌ ከዎርሞች መሃከል እንደ ፒንዎርምስና ቴፕዎርምስ ወደ ስው ስውነት ውስጥ ከገቡ በኋላ አንጀትንም ሆነ የገቡበትን ስውነት ይቆጣጠሩታል። ቴፕዎርምስ (የኮሶ ትሎች) በኢትዮጵያ ውስጥ የታወቁ ናቸው። በተለይም የመተላለፊያው መንገድ በኮሶ ትል የተመረዘ የከብት ጥሬ ሥጋ የበላ ስው በዚሁ በኮሶ ትሎች ይመረዛል። ስለሆነም ጥሬ ሥጋ ያለመብላት ከዚሁ ችግር ለመዳን ይረዳል። ባለንበት ዘመን ውስጥ ፓራሳያቶች በሽታዎችን እንደሚያመጡ ሐኪሞችም እንኳ እምብዛም ትኩረት የስጡበት በተለይም በምዕራቡ አለም አይመስልም። ይሁን እንጂ አንድ ስው በፓራሳይቶች ከተመረዘ ለተለያዩ በሽታዎች የተጋለጠ እንደሆነ ጥናቶች ያመለክታሉ።
በፓራሳይቶች የመመርዝ ምልክቶች
የሕክምና ጽሑፎች ስለፓራሳይት የጻፉት ተቅማጥ ከማምጣታቸውን ከዳይት የሚገኙት ንጥረ-
ነገሮች ወደ የስውነት በሚገባ እንዳይዳረስ የሚያደርጉት ፓራሳይቶች ናቸው ከሚለው ግኝታቸው ሌላ ለበሽታዎች መነሻዎች እንደሆኑ አጠንክረው አልጠቀሱም። ይሁን እንጂ ፓራሳይቶች ከስው ስውነት ውስጥ ከገቡ በኋላ በሽታዎችንና ምልክቶቻቸውም ያስከትላሉ። ከሚያስከትሏቸው ምልክቶችንም ማሃከል በእንቅልፍ ልብ (በአልጋ ላይ መሽናት)ያልታወቀ የምግብ አለርጂዎች ፣ በአይኖች ሥር በክቡ ጥቁረቶች (መበለዝ) የሚገማ ሽታ ያለው ተቅማጥ በተለይም በቀኑ መጨረሻ ይብሳል፣ የሆድ ድርቀት ወይም የተቅማጥ መቀያየር፣ የሆድ ውስጥ ጩኸት ከረሃብ ወይም ከመብላት ጋር ያለተገናኘ ቃር ወይም የደረት ላይ ሕመም፣ የጉንፋን አይነት ምልክቶች ካሉ (እንደሳል ተኩሳት የአፍንጫ መዘጋት፣ በአፍንጫ በጆሮዎችና በፊንጣጣ አካባቢ ማታ ማታ ማሳከክ፣ እራብን ያስከተለ የክብደት መቀነስ፣ የደም ማነስ፣ በስገራ ውስጥ ደም ካለ፣ የሆድ ውስጥ አየር መብዛት መነፋት፣ የምግብ ፍላጎት ማጣት፣ ማቅለሽለሽ፣ ማስታወክ፣ የአፍና የድድ ቁስለት፣ የማያቋርጥ የአፍንጫ ማሳከክ፣ የጥርስ ማፏጨት በተለይም ማታ ወይም በእንቅልፍ ልብ፣ ከባድ ድካም፣ የራስ ምታት፣ የጡንቻ ላይ ሕመም፣ የትንፋሽ ማጠር፣ በቆዳ ላይ ሽፍታ፣ ድባቴና ማስታወስ ያለመቻል ናቸው።
ፓራሳይቶች የሴንትራል ነርቭስ ሲስተም (የአንጎል ክፍል) ይመርዛሉ
1. የሴንትራል ነርቭስ ሲስተምን (የአንጎልን ክፍል) በመመረዙ የታወቀው ፓራሳይት Toxoplasma gondii ነው። ስዎች በዚህ ፓራሳይት የሚመረዙት ያልተቀቀለ ሥጋ ወይም በድንብ ያልበስለ ሥጋ የበሉ እንደሆነ ነው። በፓራሳይቱ ከተመረዙ የቤት እንስሶች ጋር ከስገራቸው ወይም ከሽንታቸው ጋር ንከኪ
(cat litter) ያለ እንደሆነ ከፓራሳይቱ እንቁላሎች የተነሳ ወደ ስው ይተላለፋል። እርጉዝ ሴት በ Toxoplasma gondii ከተመረዘች ጽንሱ ይጨነግፋል ወይም ከፓራሳይቱ የተነሳ ጽንሱ ሞቶ ይወለዳል ወይም የተወለደው ሕጻን congenital toxoplasmosis ያለው ከመሆኑ የተነሳ የአይን የማቃጠል ችግር መታወር የጉበት በሽታ (ጆንዲስ) የሚጥል በሽታ ከመጠን በላይ ትንሽ ወይም ትልቅ እራስ ያለው ዘገምተኛ አዕምሮ (mental retardation) ያለው ይሆናል። ደካማ የኢሚውን ሲስተም ያላቸው ስዎች ማለትም እንደ ዔድስ በሽተኞች ያሉት ለ toxoplasmosis የተጋለጡ ናቸው ስውነታቸውን ከመመረዙ የተነሳ በስውነታቸው ላይ ማቃጠል የራስ ምታት መንቀጥቀጥ የሃሳብ መደበላለቅ በከፊል ስውነታቸው ላይ ሽባነት ወይም ኮማ ያስከትልባቸዋል።
2. ፓራሳይቶች ሚክሮ ኒትርየንቶችን ያቀንሳሉ
ፓራሳይቶች ወደ ስው አካል ውስጥ ከገቡ በኋላ ለጤናማ እድገትና አስራር የሚያስፈልጉትን ቪታሚኖችና ሚኒራሎች ስለሚጋሩ ስውነት ለመኖርም ሆነ በሚገባ ለመሥራት ስለሚቸገር ጉድለቱ ለተለያዩ በሽታዎች የተጋለጠ ያደርገዋል።
3. ፓራሳይቶች የሆድ ውስጥ ጤናን ያወካሉ
በMeSH የተደረገው ጥናት እንደሚያመለክተው Protozoan ና helminthes የተባሉት ፓራሳይቶች የሆድ ሕመምና የምግብ ፍላጎት መዘጋትን ያስከትላሉ። በ MeSH የተደረገው ጥናት የአንጀት ውስጥ የሆድ ህመም ባለባቸው በሽተኞች የፓራሳይቶች ምርመራ ማድረግ እንደሚኖርባቸው ያመለክታል። ጥናቱም የደመደመው የሆድ ህመም ያለባቸው በሽተኞች በሙሉ መመርመር ያለባቸው የአንጀት ውስጥ ፓራሳይቶችንና በተጨማሪም Microsporidium ያለበት ግለስብ አዘውትሮ የአሲድ ኢንዳጀሽንና ድካም ስለሚታይበት ምርመራው Microsporidium ይጨምራል። ይሁን እንጂ አንድ ስው ምግብ መብላት ካቃተውና የአሲድ ኢንዳይጀሽን ችግር ካለው ምርመራው በዚሁ ላይ ትኩርት ይስጣል።
4. ፓራሳይቶች በጡንቻዎች ላይ ሕመም ያስከትላሉ
በ MeSH የተደረገው ጥናት በአምሳ አንድ አመት እድሜ ያለው የጤና ችግሮች ማለትም የልብ ምት ፍጥነቱ ክፍተኛና ጉበቱ የተጎዳና የደም መርጋት ችግር ያለበት ወንድ ስው ጥሬ የፍየል ሥጋ ከበላ በኋላ fasciculations ና የጡንቻ ላይ ቁርጥማት በታችኛው የእጆችና የእግሮቹ ክፍሎች ህመምና አቅም ማጣትና በጡንቻዎች ላይ በማስከተሉ የተነሳ ጥናት ተደረገ። የምርመራው ውጤት ያመለከተው positive antibodies የተገኙበት ሲሆን በተቃራኒው Toxocaracanis የተባለው ፓራሳይት በስውዬው ደም ውስጥና በ cerebrospinal ፈሳሹ ውስጥ እንዳለ ምርመራው አመለከተ። ጥናቱ የሚያመለክተው Toxocaracanis በተባለው ፓራሳይት የተነሳ የጡንቻና የእግሮችና የእጆቹ ሕመም የመጣው ከዚሁ ፓራሳይት የተነሳ እንደሆነ ነው። በህክምና ማለትም albendazole and riluzole በተባሉት በመድሐኒቶችም ቢረዳም እንኳ ጡንቻዎቹ ማለቃቸው አላቆሙም ይልቁንም ወደ መተንፈሻ ክፍሉ ጡንቻዎች ላይ መተላለፉ ቀጠለ።
5. ፓራሳይቶች የደም ማነስ ያስከትላሉ
የኢትዮጵያ በገጠሩም ሆነ በከተማው (hookworm infection) በሁክዎርም ይመረዛል። በሁክዎርም መመረዝ የሚካሄደው በተረሱት ከባድ ሙቀት ቦታዎች ከመሆኑም ሌላ ድህነትን የሚያራመድ ወይም ለድህነት መነሻ የሚሆን በሽታ ነው። ጥናቶችም እንዳመለከቱት በሁክዎርምስ የተመረዙት በአለም ዙሪያ የሕዝብ ብዛት 576 እስከ 740 ሚሊዮን ሲሆኑ አብዛኞዎቹ ሕዝቦች የሚኖሩት በሞቃቱ የአለም ክፍሎች በትሮፒክስና በሳፕትሮፕክስ አካባቢዎች ነው። በኢትዮጵያ ውስጥ በዚሁ ሁክዎርም መመረዝ እንዳለ የታወቀው በምሥራቅ ወለጋ በሚገነኘው Fenan Medical Centre በ2007 ዓ.ም መጋቢት እስክ ሚያዚያ የተደረገው የደም ምርመራ በደጋው የወለጋ ክፍል የሁክዎርም ፓራሳይት እንዳለ ምርመራው አመልክቷል። በተመርማሪዎቹ በአንጀት ውስጥ የሚገኙት 64% ሌሎች ፓራሳይቶች መሃከል 49.7% የሁክዎርም ፓራስይት እንደሆኑ ጥናቱ አመልክቷል።
በጥናቱ ከተሳተፉት ስዎች መሃከል 83.9% በሁክዎርምስ የተመረዙት በደም ማነስ የተጠቁ ናቸው። .
የሁክዎርም መጠኑ ትንሽ የሆነ ፓራሳይት nematodes የተባለው ወደ ስው ስውነት ውስጥ ከገባ በኋላ የገባበትን ስው ደም እየተመገበ የሚኖር ፕራሳይት ነው። በሁክዎርም ፓራሳይት የተመረዘው ስው የደም ማነስ የሚኖረው ፓርሳይቱ ደሙን እየተመገበ በስውነቱ ውስጥ ስለሚኖር ነው።
አንድ ስው ለደም ማነስ ከሚያገልጡት ተመጣጣኝ ዳይት ያለመመገብና የውስጥ መድማት ችግር ሌላ የሁክዎርም ፓራሳይትም ለደም ማነስ (አኒሚያ) ድርሻ አለው። የደም ማነሱ ችግሩ መንስዔው የትኛው እንደሆነ ለማወቅና በሽተኛውን ለመረዳት የደምና የስገራ ምርመራ ቢደርግ ይመረጣል። በሀገር ውስጥም ሆነ ከውጪ ወደ ኢትዮጵያ ተጉዘው ለሚመጡ ግለስቦች የደም ማነስ ችግራቸው ካልታወቀላቸው ሐኪማቸውን የፓራሳይት መርመራ እንዲደርግላቸው ማሳስብ ይኖርባቸዋል።
ከዚህ በታች የተጻፉት ሃሳቦች ለትምህርት እንጂ አንባቢው እራሱን በራሱ በቦታኒካል ሜዲስንም ሆነ በፈርማሲዩቲካል መድሐኒቶች እንዲያክም እይደለም፤ አንባቢው እራሱን በራሱ ከዚህ በታች ከተጠቀሱት ቦቦታኒካል ሚዲስንም ሆነ የፈርማሲዩቲካል መድሐኒቶች ወስዶ እራሱን አክሞ ጉዳት ቢደርስበት
እኔ ዶ/ ር አመለወርቅ ተጠያቂ እንዳልሆንኩ አንባቢው ሁሉ ይወቅ። አንባቢው ለማንኛውም ህክምና የግል ሐኪሙን ማየትና ምክር መጠየቅ ያስፈልገዋል።
1.ኒዩትሪሽናል ቲራፒ
የሚከተሉት የአመጋገብ ለውጦችን ማድረግ በፓራሳይት መመረዝን ይከላከላል።
• ተመጣጣኝ ምግቦችን መመገብ በብዛትም ከምግብ ውስጥ ፍይበርን ማብዛት አታክልቶችን ፍራፍሬዎችን ሆልግሬን ምግቦችን ነትስ በተለይም ፋይበር ውርሞችን ከአንጀት ውስጥ የማስወገድ ጉልበት አለው።
ተመጣጣኝ ምግብ መመገብ ኢሚውን ሲስተም እንዲጠናከርና ስውነትን ከውጪ ወራሪ ባክቴሪያም ሆነ ቫይረስ ፓራሳይቶችን አንዳያጠቃው ጠንክሮ እንዲስራ ያደርገዋል።
• ከምግብ ውስጥ መቀነስ ያለበት ዲሪ ፕሮዳክቶችንና (ከወተት የሚገኙ ምግቦችን) ስክዋርንና ስብነት ያላቸውን ምግቦች ነው። በተለይም ያልተቀቀሉ የአሳ የፓርክና የከብት ሥጋዎችን ያለመብላት ይመረጣል።
• በየቀኑ ደግሞ ማልቲቪታሚን/ ሚኒራል ስፕሊመንቶችን መውስድ ከማልኒዩትሪሽን ከመከላከሉም ሊላ ኢሚውን ሲስተም እንደሻሻል ወይም እንዲጠናከር ይረዳል።
• እንደተጨማሪ ምግብ ደግሞ ፕሮፓዮቲክን እንደ Lactobacillus acidophilus,
Bifidobacteria, ሌሎችንም ጠቃሚ አንጀትን የሚረዱ ፕሮፓዮቲክ ምግቦች ጤናማ ባክቴሪይዎች
በአንጀት ውስጥ የሚገኘውን ጤናማውን ኢንተስቲናል ፍሎራ በማሻሻል ፓራሳይት በአንጀት ውስጥ እንዳይበዛና እንዳይስራጭ ያደርጋሉ።
2. ቦታኒካል ሜዲስን ቲራፒ
ቦታኒካል ሜዲስን ከምግቦች ጋር የተወስዱ እንደሆነ ወርሞች ከሆድ ውስጥ እንዲጠፉ ይረዳል። የሚከተሉት ፓራሳይቶችን ከሆድ ውስጥ እንዳይረቡ በማስወገድ የታወቁ ናቸው።
• Melaleuca alternifolia (tea tree)
oil ብዙ ጥቅሞችን ያስገኛል ከነዚህም መሃከል የአንጀት ውስጥ ፓራሳይቶችን ቅማል ሌሎችንም የማስወገድ ጉልበት አለው።
• Artemisia annua (wormwood herb) እና citrus seed
extract እነዚህ ሁለቱ በአንድ ላይ የተወስዱ እንደሆነ Giardia
lamblia የተባለውን ፓራሳይት ከአንጀት ውስጥ ያስወግዳል።
• Berberine- ያለባቸው ቦታኒካል ሜዲስኖች ቤርቤሪን የታወቀው አንቲማይክሮቢያል አልክሎይድ የተባለውን
ንጥረ- ነገሩን በመያዙ በአንጀት ግድግዳ ላይ የተጣበቁትን ፓራሳይቶች የመከላከል ጉልበት አለው። እንደውም አንድ ጥናት ያሳየው amoebal Giardia የተባለውን ፓራሳይት የማጥፋት ጉልበት እንዳለው ጥናቱ አሳይትዋል። lamblia እንደ metronidazole ደረጃውን የጠበቀ ትሪትመንት ነው።
ፓታኒካል ሚዲስን berberine ከያዙት መሀከል፡
(1) goldenseal (Hydrastis canadensis),
(2) barberry (Berberis vulgaris)
(3) Oregon grape (Berberis aquifolium)
(4) goldthread (Coptis chinensis) ናቸው።
3. ፈርማኮቲራፒ በአንጀት ውስጥ ለሚገኙ ፓራሳይቶች
የፓራሳይቶች ትሪትመንት የሚደረገው በantiparasitic
drugs በተባሉት መድሐኒቶች ነው። እንደጥንካሬው መጠን እንደፓራሳይቱ አይነት መድሐኒቶቹ በሐኪሙ ይመረጣሉ።
እነዚህም መድሐኒቶች የሚከተሉት ናቸው።
(1 )Albendazole (2) furazolidone, (3) iodoquinol, (4) mebendazole,
(5) metronidazole, (6) niclosamide, (7) paromomycin, (8) pyrantel pamoate,(9) pyrimethamine, (10) quinacrine,
(11) sulfadiazine ወይም thiabendazole.
እንደገና በፓራሳይት ታማሚው ደግሞ እንዳይመረዝ ወደ ሌላው እንዳይተላለፍ እጅን መታጠብ ልብሶችን መጠብ አንሶላዎችንም ሆነ የአልጋልብሶችን ልጆች የሚጫወቱበትን አሻንጉሊቶች ማጠብ ሌላው ፓራሳይቶች ወደ ሌላው ስው እንዳይተላለፉ
ይረዳል። ይህ እርምጃ ቤተስቡን ሁሉ ይጨምራል።
ሴንትራል ነርቭስ ሲስተማቸው toxoplasmosis በተባለው ፓራስይት የተመረዘ ስዎች ደግሞ
spiramycin ወይም sulfadiazine አብሮም pyrimethamine የተባሉት መድሒኒቶች በሐኪም
ይስጣቸዋል። የተመረዙት ስዎች በተለይም ለኤድስ በሽተኞች ከሆኑ ላለተወስነ ጊዜ መድሐኒቱን እንዲወስድ ይደረጋል።
ፓራሳይቲክ ኢንፊክሽንን በምርመራ ማወቅ አስቸጋሪ ነው ቢሆንም እንክዋን ፓራሳይቶቹ እንዳይባዙ ቦታኒካል ሜዲስን ወይም antiparasitic drugs ችግሩ ይቃለላል።
የመከላከያ ህክምና
ከዚህ በታች የተቀመጡት እርምጃዎች ግለስቡን በፓርሳይት ከመመረዝ ይከላከሉ
• ምግብን ከመብላትም በፊት ሆነ በህዋላ እጆችን መታጠብ
•የመጸዳጃ ቤቶን ከተጠቀሙ በህዋላ እድን በውሃና በሳሙና በሚገብ መታጠብ
• አታክልት በሚተከልበት ጊዜም ሆነ አፈር በእጅ እንዳይነካ ግሎቭስ መልበስ ምክንያቱም አፈርም ሆነ አሽዋ በፓራሳይቶች እንቁላሎች መመርዝ ስለሚችሉ ነው
• እርጉዝ ሴት የድመት ኩስ መንካት የለለባትም
• ልጆች የቤት እንስ ሳትን መሳም እንስ ሳውም ልጆቹን በምላሱ መላስ የለበትም
• ቪጂቲብሎችንም ሆነ ፍራፍሬዎችን ከመበላታቸው በፊት በሚገባ መጠብ ምክንያቱም ብዙ ስዎች ያልታጠቡ የአታክልት
ምግቦችንም ሆነ ፍራፍሬዎችን የተመገቡ እንደሆነ ከጥሪ ፍራፍሬዎች ላይ Entamoeba histolytica የተባለው ፓራሳይት አብረው ካልታጠበው ፍራፍሬ ጋር ወደሆዳቸው የመግባት እድል ይኖረዋል።
• ጥሬ ሥጋ Giardia lamblia የተባለው ፓርሳይት ስለሚገኝበት አለመብላት ይመረጣል።
•በተቻለ መጠን የሚለበስው ልብስ እጅጌ ያለው ሽሚዝ እርጂም ሱሪና ቡትስ በጫካው ውስጥ የተሄደ እንደሆነ ቢሆን ይመረጣል ከዚህም በተጨማሪ ነፍሳትን የሚያባርር ስፕሬ በልብስ ላይ ነፍቶ መውጣት ሌላው እምጃ ነው።
የበለጠ ለማወቅ Burton Goldberg Group. “Parasitic Infections.” in Alternative Medicine: The Definitive Guide. Tiburon, CA: Future Medicine Publishing, Inc., 1999. ያንብቡ።
ክፍል 2
ከኤች·አይ·ቪ ቫይረስ ጋር መኖር
ከኤች·አይ·ቪ ጋር መኖር ቫይረስ ጋር
መኖር ማለት ቫይረሱ በደሙ ውስጥ እንዳለ የተረዳ ሰው ራሱን አረጋግቶና ችግሩን እንደማንኛዉም የጤና
ችግር በማየት ቫይረሱ የሚያስከትለውን ጉዳት ለመቀነሰ እና ለመከላከል በሕክምና፣ በአመጋገብ፣ እንዲሁም በባህርይ ላይ አስፈላጊ
የሆኑ ለውጦችን በማምጣት ጥሩ ሕይወት መኖር ማለት ነው። አንድ ሰው ኤች·አይ·ቪ አለበት ማለት አሁኑኑ ታሞ ይተኛል ወይም
በቅርቡ ሕይወቱ ያልፋል ማለት አለመሆኑን ማወቅ ተገቢ ነው። ከኤች.አይ.ቪ ጋር የሚኖሩ ሰዎች የእድሜ ማራዘሚያ መድሀኒቶችን ፀረ-ኤችአይቪ
መዳኒቶች በመጠቀም ለረጅም ዓመታት ጤናማ ሆነው
ለመኖር ይችላሉ። አንዳንድ ሰዎች የበሽታዉ ምልክት ጨርሶ ሳይታይባቸው ከ15 ዓመት በላይ ከቫይረሱ ጋር መኖር እንደሚችሉ
አንዳንድ ጥናቶችም ያመለክታሉ። ኤች·አይ·ቪ ቫይረስ በደም ውስጥ በመኖሩ ምክንያት ሊሰማ የሚችለዉን ስሜት አውነታውን መቀበል
መቻል በጣም አስፈላጊ ነው። ጥሩ ያልሆኑትን ስሜቶች ለማስወገድ የሚከተሉትን ምክሮች መቀበልና መተግበርም ተገቢ ነው።
ሁኔታዎች እያደር የተሻሉ እንደሚሆኑ ተስፋ
ማድረግ፦ ፈታኝ የሆነ ሰሜት ሲሰማ ሁኔታዎች ሁሉ ከጊዜ ጋር እየተሻሻሉ እንደሚሄዱ ማመን በጣም ጠቃሚ ነው።
የተሻለ ሁኔታ እንደሚኖር ተስፋ የሚሰጡ ብዙ መንገዶች አሉ። ለምሳሌ የራስን ጤንነት መጠበቅና የቀድሞውን የተረጋጋ ህይወት
እንደገና መጀመር አንዱ መንገድ ነው።
ከኤች·አይ·ቪ ጋር ከሚኖሩ ሰዎች ጋር
መመካከር፦ ማንኛውንም የሚሰማን ስሜት ወይም የህመም ምልክት፤ ሌሎችም ምናልባት ተመሳሳይ ስሜት እና ምልክት
ሊኖራቸው ስለሚችል ከቫይረሱ ጋር ከሚኖሩ ሰዎች ጋር መመካከር ወይንም ከቫይረሱ ጋር የሚኖሩ ሰዎች ወደመሠረቷቸው ማህበራት
በመሄድ የምክር እርዳታ ማግኘት አስፈላጊ ነው።
ሁሌም የሚያስደስቱን ነገሮች ከማድረግ
አለመቆጠብ፦ አንድ ሰው ኤች.አይ.ቪ ቫይረስ በደሙ ውስጥ መኖሩን ካወቀ በኋላ የደረሰበትን ድንጋጤ
ለማስወገድ ቀደም ሲል ያደርጋቸው የነበሩትን አስደሳች ስራዎችን በመቀጠል አሁን የተፈጠሩበትን የኀዘንና የብስጭት ሰሜቶችን
መርሳት መቻል ይገባዋል። ዘወትር ሲያደርገው ያስደስቱት የነበሩትን ሥራዎች በቀጣይነት ማድረግ ኀዘን ወይም ጭንቀት ላይ ብቻ
እንዳያተኩር ይረዳል።
አካላዊ እንቅስቃሴ ማድረግ፦
ከኤች.አይ.ቪ ጋር የሚኖር ሰው ድካም ሊሰማዉና ሊጫጫነው ይችላል። በዚህ ጊዜ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ ብርታትና
ጥንካሬ ይሰጣል። ከፍተኛ የሰውነት እንቅስቃሴ ባይሆንም እንኳን ቀላል እርምጃዎችን ማዘውተር ለአእምሮና ለሰውነት ጤንነት በጣም
አስፈላጊ ነው።
ጎጂ የሆኑ ቅፅበታዊ ለውጦችን በህይወት
ላይ አለማድረግ፦ ሥራን አለመተው፣ ዘመድ ወዳጆችን አለመራቅ፣ ንብረቶችን አለመሸጥ። በእርግጥ አንድ ከኤች·አይ·ቪ
ቫይረስ ጋር የሚኖር ሰው የወደፊት እቅዱን ሊለውጥ ይችላል፤ ይህ ለውጥ ጫና ያልበዛበትና ውጤቱም ጠቃሚ መሆኑን አስቀድሞ
መለየት ያስፈልጋል።
ባለሞያን ማማከር፦ ስለ
ኤች·አይ·ቪ/ኤድስ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ በመኖሪያ አካባቢያችን እንቅስቃሴ የሚያደርጉ ማህበራትን ወይም ድርጅቶችን ማወቅ
ጠቃሚ ነው። አንድ ከኤች.አይ.ቪ ጋር የሚኖር ሰዉ የጭንቀት እና የመከፋት ስሜት ካለቀቀው የህክምና ባለሞያዎች ወይንም
አማካሪዎችን በስልክም ሆነ በአካል ማግኘትና ማማከር ያስፈልገዋል።
ያስታውሱ! ብቻዎን አይደሉም ፦ኢትዮጵያ
ውስጥ ከኤች·አይ·ቪ ቫይረስ ጋር የሚኖሩ ከአንድ ሚሊዮን ተኩል በላይ ሰዎች አሉ። በአሁኑ ጊዜ 12 በመቶ ገደማ የሚሆኑ
ከኤች·አይ·ቪ ጋር የሚኖሩ ሰዎች አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ይኖራሉ። በመላው ኢትዮጵያ ውስጥ ዕድሜያቸው በ15 እና በ49
መካከል የሚገኙ ከ4 ከመቶ በላይ የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን ከኤች·አይ·ቪ ቫይረስ ጋር ይኖራሉ። አንድ ኤች·አይ·ቪ ቫይረስ በደሙ
ውስጥ ያለበት ሰው በቫይረሱ ለመያዝ ሆን ብሎ የሰራው ስህተት ስለሌለ ራሱን መውቀስ እና መጨነቅ የለበትም። ማድረግ ያለበት
ነገር ቢኖር ለሌሎች ተጓዳኝ በሽታዎች እንዳይጋለጥ ራሱን እንዲጠብቅ ትምህርት ማግኘት እና ከኤች.አይ.ቪ ነፃ የሆኑ ሰዎች
ለቫይረሱ እንዳይጋለጡ ስብዓአዊነት ተስምቶት ቅድመ ጥንቃቄዎችን ማድረግና፣ ከተቻለም ማስተማር።
ከኤች·አይ·ቪ ቫይረስ ጋር የሚኖሩ ሰዎች
ቫይረሱ እንዳለባቸዉ አውቀው ከጥቂት ጊዜ በኋላ ያሉበትን የጤና ሁኔታ ተቀብለው ራሳቸውን በማረጋጋት ወደፊት በተሻለ መንገድ
ለመኖር ምን ማድረግ እንዳለባቸው ማሰብ ይጀምራሉ። እራሰን አረጋግቶ ለመኖር ከዚ በታች የተጠቀሱት ጠቃሚ መመሪያዎች በዝርዝር
ጠንቅቆ ማወቅ አጥጋቢ የሆነ የፀባይ እና የአኗኗር ለውጥ ለማምጣት ይረዳል፦ ኤች·አይ·ቪ ቫይረስ በደም ዉስጥ መኖሩን
በታወቀበት ጊዜ ሊገጥም የሚችለውን የጭንቀት እና የፍርሃት ስሜት እንዴት ማስወገድ እንደሚቻል፤
·
አጋጣሚን ጠብቀው የሚመጡ የበሽታ ስሜት/ምልክቶች በሰውነት ላይ ሲታዩ
መወሰድ ያለባቸውን ህክምና እና ጥንቃቄ፤
·
የተመጣጠነ ምግብ መመገብ፣ የራስን ንፅህና መጠበቅ እና የሰውነት እንቅስቃሴ
የማድረግ አስፈላጊነትን፤
·
ጥንቃቄ ስለተሞላበት የግብረ ሥጋ ግንኙነት እና ስለወሊድ።
ተስፋ እና የወደፊት ህይወት
ከኤች.አይ.ቪ
ጋር ኑሮን በሠላም ለረጅም እድሜ መምራት እንደሚቻል መገንዘብ አስፈላጊ ነው። እንዲሁም ከኤች.አይ.ቪ ጋር የሚኖሩ ሰዎች ህጋዊ
መብታቸውን የሚያከብሩ ህግጋት እንዲደነግጉ ድጋፍን በመስጠት የራስን አስተዋፅኦ በማድረግ ተስፋን እውን ማድረግ። በተጨማሪም
የዕለት ዜናዎችን በመከታተል፣ባለሞያዎችን ወይንም አማካሪዎችን በመጠየቅ በኤች.አይ.ቪ ላይ ያሉ አዳዲስ የህክምና እና
የመድሀኒት ግኝቶችን መከታተልና ማወቅ ተስፋን ይሰጣል። ስለ ከኤች·አይ·ቪ ዕውቀትን ማዳበርና
ይበልጥ ማወቅ ራስን በደንብ ለመንከባከብ ይረዳል። አንድ ከኤች.አይ.ቪ ጋር የሚኖር ሰው ልጆች ካሉት ህመም ሲጠና ልጆችን
የሚንከባከብ ሰው ቀድሞ ማዘጋጀት ያስፈልጋል።
ህክምና
ኤች.አይ.ቪ/ኤድስ
ክትባት ወይም ፈዋሽ መድኀኒት ባይገኝለትም ምርምሩና ሙከራዉ እንደቀጠለ ነው። የዕድሜ ማራዘሚያ መድሃኒቶች ፀረ-ኤችአይቪ
መዳኒቶች ቫይረሱ በደም ውስጥ የሚያደርገውን
የስርጭት ፍጥነት ለመግታትና ለማስቆም የሚወሰዱ መድሃኒቶች ናቸው። በሰውነት ዉስጥ የሚገኘውን የኤች.አይ.ቪ ቁጥር መቀነስ
ይችላሉ፤ መድሃኒቶቹ ቫይረሱን ከናካቴው ማጥፋት አይችሉም። መድሃኒቶቹን ያለ ህኪም ትዕዛዘና ፍቃድ መውሰድ በጤንነት ላይ ትልቅ
ችግር ያስከትላል። የመድሃኒቶቹ ተጠቃሚ ሰው አንድ በቅርብ ሆኖ የሚከታተለው ብቃት ያለው የህክምና ባለሙያ ያስፈልገዋል።
አመጋገብ
የተመጣጠነ ምግብ መመገብ ሰውነታችንን እና
የሰውነት የመከላከያ አቅማችንን እንደሚያጠነክር ሁሉ በቀላሉ ለበሽታ እንዳንጋለጥም ይጠቅመናል። ከኤች·አይ·ቪ ጋር የሚኖሩ
ስዎች በምግብ እና ውኀ ውስጥ ለሚገኙ በሽታን ወይም ህመምን ሊያስከትሉ ለሚችሉ ጀርሞች በቀላሉ የተጋለጡ በመሆናቸዉ፤ በቤት
ውስጥም ሆነ ከቤት ውጭ ሲመግቡ ንጽህናውን የጠበቀ የአመጋገብ ሥርዓት መከተልና የሚጠጣው ውሃ ንጹሀ መሆኑን ማረጋግጥም በጣም
ጠቃሚ ነው። ከኤች·አይ·ቪ ጋር የሚኖሩ ስዎች የተለያዩ ዓይነት ምግቦችን በመመገብ ያልተፈለገ የሰውነት ክብደት መቀነሰን
ለመከላከል እና ጡንቻዎቻቸዉ እንደጠነከሩ እንዲቆዩ የሰውነት እንቅስቃሴ ማድረግ አለባቸው። ሁሉም የምግብ ዓይነቶች የተለያዩ
ጥቅሞች አላቸዉ። የተለያዩ የምግብ ዓይነቶች በሚከተለው መሰረታዊ ምድቦች ተከፋፍለው ሊታዩ ይችላሉ።
·
ገንቢ ምግቦች፦ ባቄላ፤ አተር፣ ምስር፣ እንቁላል፣ ሥጋ፣ አሣ፣ ዶሮ፣
ወተት፣ አይብ እና ለውዝ ሰውነትን ለመገንባት የሚያስችሉ የምግብ ንጥረ ነገሮችን ይዘዋል።
·
ኃይል ሰጪ ምግቦች፦ ለሰውነት የሚያስፈልገውን ኃይል ሁሉ የምናገኝባቸው
የምግብ አይነቶች እንደ በቆሎ፣ እንጀራ፣ ዳቦ፣ ድንች፣ ፓስታ፣ ሩዝ፣ ስንዴ፣ አጃ፣ ዳጉሳ፣ ማሽላ፣ ስኳር፣ ማርማላት፣
ማርጋሪን፣ ዘይት፣ ሲሆኑ በተጨማሪም እንደ ለውዝ እና አቮካዶ የመሳሰሉ የቅባት ምግቦችንም ያጠቃልላል።
·
የሰውነትን የመከላከል አቅም የሚያጎለብቱ ምግቦች፦ አትክልትና ፍራፍሬ
መመገብ የሰውነታችንን አቅም በማጎልበት በሽታን በሚገባ ለመቋቋም ያስችላል፤ እንዲሁም እንደ ካሮት፣ ሰላጣ እና ጎመን የመሳሰሉ
ምግቦችንም መመገብ ቫይታሚን ለማግኘት ይረዳናል።
የሰዉነትን
የመከላከል አቅም ለማጎልበት፦
·
የምግብን የመፍጨት ሂደት ሊያውኩ የሚችሉ እንደ ቃሪያ፣ በርበሬ ወይም
ሚጥሚጣ የመሳሰሉ እና ሌሎች ቅመማ ቅመም የበዛባቸውን ምግቦች በብዛት አለመመገብ፣ ለስለስ ያሉ እንደ አልጫ ወጥ ያሉ ምግቦችን
መመገብ፣ ከህይለኛ ቅመሞች ይልቅ የጥብስ ቅጠልን የመሳሰሉ የምግብ ማጣፈጫዎች መጠቀም ያስፈልጋል።
· ፍራፍሬ እና የአትክልት አመጋገባችንን መጨመር፣ እነዚህን የሰውነት
የመከላከል አቅም የሚያጎለብቱ ምግቦች በቫይታሚንና በማዕድን የበለፀጉ በመሆናቸው ሰውነታችንን ከበሽታ ይከላከላሉ። በመሆኑም
እንደ ቆስጣ እና ጎመን የመሳሰሉ በጣም አረንጓዴ የሆኑ የቅጠላቅጠል ምግቦችን፣ እንደ ዱባ፣ ብርቱካን፣ ሎሚ፣ ማንጎ እና
የመሳሰሉ ፍራፍሬዎችን በየቀኑ መመገብ ያስፈልጋል። በተጨማሪም ከጤፍ፣ ከጥቁር ስንዴ፣ ገብስ የተዘጋጁ ዳቦዎችን እና ሌሎች
ምግቦችን መመገብ።
· ዉኃ ለሰውነታቻን ከሚያሰፈልጉን ነገሮች አንዱ ነው። በየቀኑ ቢያንስ 8
ብርጭቆ ዉሃ መጠጣት ጠቃሚ ነው። የምንጠጣው ዉሃ ንፁህ መሆን አለበት። ከኤች. አይ.ቪ ጋር የሚኖር ሰው እንደ ተስቦ፣ ኮሌራ፣
ቢልሀርዚያ እና ጃርዲያ ለመሳሰሉት በተበከለ ውኃ አማካኝነት በሚተላለፉ በሽታዎች የተጋለጠ ስለሆነ በቀጥታ የህይቅ ወይም
የምንጭ ውኃ ከመጠጣት ፈልቶ የቀዘቀዘ ውኃ መጠጣት በጣም አስፈላጊ ነው።
ሰዉነታችንን
በጤንነት ለማቆየትና ቫይረሱ በጤና ላይ ሊያስከትል የሚችለውን ጉዳት ለመቀነስ ቫይታሚን ኤ፣ ቢ6፣ ቢ12፣ ሲ፣ ዚንክ፣
አይረን፣ ኮፐር፣ ማንጋኒዝ፣ ማግኒዥየም እና ሴሊኒየም ጨዉ የመሳሰሉትን ሁሉ መመገብ ይጠቅማል። የሰዉነትን የተፈጥሮ በሽታን
የመከላከል አቅም በማጎልበት ረገድ ቫይታሚን ኤ፣ ሲ፣ ኢ፣ እና ከማዕድናትም ዚንክ በጣም ጠቃሚዎች ናቸው። እነዚህ የምግብ
ንጥረ-ነገሮች በተፈጥሮ ከተለያዪ ምግቦች ዉስጥ ይገኛሉ።
የቫይታሚኖች
እና የማዕድናት መገኛ:
ቫይታሚን 'ኤ'
ጉበት፣ ቅቤ፣ አይብ፣ እንቁላል፣ ቆሰጣ፣
ቢጫና አረንጓዴ አትክልቶች
|
' ቫይታሚን
ቢ12 ' ጉበት፣ ኩላሊት፣ አሳ፣
ሥጋ፣ ዕንቁላል፣ ወተት
|
ቫይታሚን
'ሲ' ቲማቲም፣ ድንች፣
ማንጐ
|
ቫይታሚን 'ኢ'የአትክልት
ዘይት
|
' አይረን '
የበሰለ ጉበት፣ ኩላሊት፣ እንጀራ፣ ቀይስጋ እና ዕንቁላል፣
|
' ኮፐር '
ጉበት፣ ለውዞች፣ ባቄላ፣ ስጋ፣ አሳ፣ ዶሮ፣ እና የስንዴ ዳቦ፤
|
ቫይታሚን 'ቢ6' ከስንዴ
የተዛመዱ ምግቦች፣ ጉበት፣ ሙዝ፣ ስጋ፣ ድንች፣ አትክልት፣ ዕንቁላል እና ለውዞች፤
|
' ዚንክ '
የስንዴ ዳቦ፣ እንቁላል፣ ባቄላ፣ ሩዝ፣ አረንጓዴ ቅጠላማ አትክልቶች፣ ድንች ጉበት ስጋና ለዉዝ፤
|
' ሴሊኒየም '
ጉበት፣ ኩላሊት፣ ልብ፣ ቀይ ስጋ፣ የወተት ምርቶች፣ አትክልት እና ፍራፍሬ
|
' ማግኒዥየም '
አደንጓሬ፣ ለውዞች፣ የስንዴ ዱቄት፣ ቡናማ ሩዝ፣ ደረቅ አተር፣ አትክልቶች፣ ሰጋ፣ ሙዝ፣ አረንጓዴ ቅጠላማ አትክልቶች፤
|
' ማንጋኒዝ '
የስንዴ ዳቦ፣ ለውዝ፣ ፍራፍሬ ፣ አረንጓዴ ቅጠላማ አትክልቶች፣ ጉበት፣ የስራስር አትክልቶች፣ ስጋ እና አሳ
|
አንዳንድ ጊዜ
የተመጣጠነ ምግብ ባለመመገባችን ምክንያት የሚከተለውን ክፍተት ለማካካስ በፋብሪካ የተዘጋጁ ቫይታሚኖችን እንወስድ ይሆናል።
ቅድሚያ መስጠት የሚገባን የተመጣጠነ ምግብ በመመገብ ተፈላጊ የሆኑትን የምግብ ንጥረ ነገሮች ማግኘት ቢሆንም የቫይታሚን
እንክብሎችን መውሰድ አስፈላጊ የሚሆንባቸው ጊዜያት አሉ። በግምት ብዙ ቫይታሚኖችን መውሰድ ጤንነትን ስለሚያቃውስ የቫይታሚን
እንክብ በሚወሰድበት ጊዜ በህክምና ባለሞያ ትዕዛዝ መሰረት መሆን አለበት።
በምግብ አዘገጃጀት እና አመጋገብ ምክንያት
ሊከሰቱ ከሚችሉ በሽታዎች ራስን መከላከል
ከኤች·አይ·ቪ
ጋር የሚኖሩ ሰዎች በምግብ ምክንያት ለሚመጡ በሽታዎች የተጋለጡ ናቸዉ። አንዳንድ ጎጂ የሆኑ ጀርሞች ከጥሬ ስጋ፣ ምግቡን
ከሚያዘጋጁ ሰዎች ወይም አብረዉ እንጀራ ከሚበሉ ሰዎች አፍና እጅ ንክኪ ሊሸጋገሩና የምንመገበውም ሊበከል ይችላል።
ከኤች·አይ·ቪ ቫይረስ ጋር የሚኖር ሰው በምግብ መመረዝ ሲታመም ለማዳን በጣም ከባድ ከመሆኑ ሌላ በሽታው በተደጋጋሚ
ሊመላለስበት ይችላል። እንደ ኮሶ፣ ወስፋት እና አሜባ የመሳሰሉት በሽታዎች ከፍተኛ የጤና ችግርን እንዲሁም ሞትን ሊያስከትሉ
ይችላሉ። ከነዚ በሽታዎች አብዛኛዎቹ በቀጥታ በበሽታዎቹ ከተያዘ ሰው የሚተላለፉ ቢሆንም ባልበሰለ ወይም ንጽህናው ባልተጠበቀ
ምግብ፣ በነፍሳት (ተባዮች) በተበከለ ምግብ፣ የምግብ አያያዝ ሥርዓትና ደንብን ባልተከተለ ሰው ተዘጋጅቶ በሚቀርብ ምግብ
አማካይነት ሊተላለፉ ይችላሉ። ምግብን በደምብ ማብሰል ባክቴርያና ጀርሞች እንዲሞቱ ይረዳል። ከኤች·አይ·ቪ ጋር የሚኖሩ ሰዎች
ጥሬ ሥጋ ወይም ጥሬ ክትፎም ሆነ ለብለብ ክትፎ ባይመገቡ ይመረጣል። በተጨማሪም ከቤት ውጭ በሆቴሎችና ቡና ቤቶች ውስጥ መመገብ
ምግቡ እንዴት እንደተዘጋጀ ስለማይታወቅ ለህመም ሊያጋልጥ ይችላል። ከተቻለ ከቤት ውጭ አለመመገብ፤ ካልሆነም ምግቡ እንዴት
እንደተዘጋጀ እና ጥሬ የሆኑ የምግብ ውህዶች ማለትም ያልበሰለ ሥጋ፣ እንቁላል ወይም አትክልት የሌለበት መሆኑን ጠይቆ ማረጋገጥ
ያስፈልጋል።
ዕፅ እና አልኮል
ዕፅም ሆነ አልኮል በብዛት መውሰድ
የሰውነትን የተፈጥሮ በሽታን የመከላከል አቅም ያዳክማል። ጤናማ ሆኖ ለመኖርም ሆነ ጤንነትን ለመንከባከብ አልኮልንም ሆነ ዕፅን
መጠቀምን እስከመጨረሻው መተው አማራጭ መንገድ ቢሆንም ይህንን ሁሉም ሰው በቀላሉ ሊያደርገው አይችልም። የሚወሰደው የሲጋራ፣
የዕፅ ወይም የአልኮል መጠንን በተቻለ መጠን መቀነስ ጤንነትን በተሻለ ሁኔታ ለመጠበቅም ይረዳል።
የአካል ብቃት እንቅስቃሴ
የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ የተሻለ
ጢና እንዲኖር ከመርዳቱ ሌላ የመጨነቅ፣ እና የድካም ስሜትን ይቀንሳል። የአካል ብቃት እንቅስቃሴው ራስን ዘና የሚያደርግና
የልብን ምት እንዲጪምር ተደርጎ መሠራት አለበት እንጂ እስኪደክሙ መሆን የለበትም። ተገቢውን የየአካል ብቃት እንቅስቃሴ መጠን
ለማወቅ ቢቻል የስፖርት ባለሞያዎችን አስቀድሞ ማማከር የተሻለ ነው። በየቀኑ ከ30 እስከ 60 ደቂቃ ያህል በእግር መጓዝ
የተሻለ ጤና እንዲኖረን ከሚረዱት የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎች አንዱ ነው።
ወሲብና ፍቅር
አንድ ከኤች·አይ·ቪ ጋር የሚኖር ሰው
ስለራሱ ጤና በተመለከተ መብቱ የተሰጠዉ ለራሱ በመሆኑ ለፈለገው ሰው መንገር፣ ካልፈለገ ደግሞ ያለመናገርም ውሳኔው በእጁ ነው።
ነገር ግን ከዚህ ጋር በተያያዘ መዘንጋት የሌለበት ጉዳይ አለ። በወንጀለኛ መቅጫ ሕግ ላይ የሰፈረ ድንጋጌ አንድ ሰው የሌላውን
ሰው ጤንነት በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ ሆን ብሎ ይሁን በቸልተኝነት የሚጎዳ ተግባር ከፈጸመ እንደሚቀጣ ያስረዳል።
ስለዚህ ከወሲብ ጓደኛ ጋር በሚኖር ግንኙነት ቫይረሱ ወደዛ ጓደኛ እንዳይተላለፍ ኮንዶም መጠቀም ያስፈልጋል ። ይህ ከሆነ
ከኤች·አይ·ቪ ነፃ የሆነውን ወዳጅ ከቫይረሱ ለመጠበቅ ይረዳል። ከኤች·አይ·ቪ ጋር ነዋሪ መሆንን ለወሲብ/ፍቅር ጓደኛዎ
አንዳንድ ጊዜ በቀጥታ ሌላ ጊዜ ደግሞ በተዘዋዋሪ መናገር ይቻላል። ለምሳሌ ስለቅድመ ወሲብ ጥንቃቄ ወይም ስለ ኤች·አይ·ቪ እና
መተላለፊያ መንገዶች በማንሳት መነጋገር ይቻላል።
ወሊድ ( ከኤች·አይ·ቪ
ያለባት እናት
አንዲት ሴት
ኤች·አይ·ቪ በደሟ ውስጥ ቢኖርም እንኳን ልጆች ማፍራት ትችላለች። ተገቢውን ጥንቃቄ እና የህክምና ክትትል ካደረገች
ከኤች·አይ·ቪ ነፃ የሆነ ጤነኛ ልጅ ሊኖራት ይችላል። ይሁን እንጂ ለኤች·አይ·ቪ የሚጋለጥም ልጅ ሊኖር ይችላል። ልጅ ለመውለድ
እቅድ ካለ የሚከተሉትን ነጥቦች ልብ ማለት እና የህክምና ባለሞያን ማማከር ያስፈልጋል
· የጤንነት ሁኔታ- በእርግዝና ወቅት በብዛትም ሆነ በጥራት የተሻለ የምግብ
አቅርቦት መኖር አለበት። ከኤች·አይ·ቪ ጋር የሚኖር ሰው ደግሞ ከፍ ያለ የምግብ መጠንና የተለያዩ የምግብ ዓይነቶች ማግኘት
ያስፈልገዋል።
·ፅንሱን ከቫይረሱ መከላከል- ኤች·አይ·ቪ በደም ውስጥ መኖሩን አውቆ ልጅን
ከኤች·አይ·ቪ ለመታደግ አስፈላጊውን እቅድ ማዉጣትና ተገቢውን ህክምና መከታተል የልጅን በቫይረሱ የመያዝ አጋጣሚ ለመቀነስ
ይረዳል።
· በደም ዉስጥ የኤች·አይ·ቪ መኖር- ወደፊት አንድ ወቅት ላይ የኤድስ ታማሚ
ሊሆኑ እና አልጋ ላይ የመዋል አጋጣሚ ሊመጣ ይችላል። ስለዚህ ልጅዎ ያለ ተንከባካቢ እንዳይቀር ቀደም ብሎ ሁኔታዎችን
ማመቻቸትም ያስፈልጋል።
ኤች·አይ·ቪ እና ሰብአዊ መብት
ኤች·አይ·ቪ እና ሰብአዊ መብት
ከኤች·አይ·ቪ
ጋር መኖር ከማንኛውም ሰብአዊ ፍጡር አያሳንሰም። ኤች·አይ·ቪ በደም ውስጥ በመኖሩ በሰብአዊ ፍጡርነት ሊኖር የሚገባውን መብት
ሊያጓድል የሚችል አንድም ምክንያት የለም። ይህም ማለት ከኤች·አይ·ቪ ጋር የሚኖር ማንኛውም ሰው እንደሌሎ
. እንደማንኛውም ሰው ቫይረሱ በደሙ ያለበት ሰው የጤና አጠባበቅ አገልግሎት፣
ሥራ እና የትምህርት ዕድል የማግኘትና፣ በማህበራዊ ክንውኖች፣ ለምሳሌ፣ ዕድር፣ በዕምነት፣ በማህበራት ወይም የስፖርት ቡድን
በመሳሰሉ ማህበራዊ ተቋማት አባል የመሆን መብት አለው።
·ከኤች·አይ·ቪ ጋር የሚኖር ሰው ቤት የመከራየት ወይም ባለንብረት ለመሆን፣
የጤና፣ የህይወት ወይም የንብረት መድን የመግባት መብት አለው።
ከኤች·አይ·ቪ
ጋር በሚኖሩ ሰዎች ላይ የሚደረግ መድልዎ ዋና ዋና መንስኤዎች አሉት፦ እነዚህም
· ስለ ኤች·አይ·ቪ ቫይረስ መተላለፊያ መንገዶች ዝቅተኛ ወይም የተሳሳተ መረጃ
መኖር፤
· በቂ ግንዛቤ ካለማግኘት ወይም ከተሳሳተ መረጃ ላይ በመመርኮዝ የሚመጣ
ፍርሃት፤
· ስለግብረ ስጋ ግንኙነት በግልጽ መነጋገር እንደ ነውር ስለሚቆጠር፤
በሥራ ቦታ
ላይ ስለሚደርስ መድልዎ ማወቅ፦ አንድ ሰው ከኤች·አይ·ቪ ጋር በመኖሩ ምክንያት መገለል ወይም አድልዎ ከደረሰበት ከቀጣሪው ጋር
በመነጋገር ወይም በፍርድ ቤት በመክሰስ ፍትህ የማግኘት መብት አለው። ሕግም ከለላና ጥበቃ ያደርግለታል።
ኤድስን መግታት ይቻል ይሆን? ከሆነስ እንዴት?
በብዙዎቹ የአፍሪካ አገሮች የሚኖሩ አብዛኞቹ ሰዎች እስከ ቅርብ ጊዜያት ድረስ የኤድስን መኖር አያምኑም ነበር። እንዲያውም አንዳንዶች ስለ ኤድስ አንስተው መወያየት እንኳን አይፈልጉም ነበር። ይሁን እንጂ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በተለይ ወጣቶችን ለማስተማርና በጉዳዩ ላይ ግልጽ የሆነ ውይይት የማድረግ ባሕል እንዲሰፍን ለማበረታታት ጥረት ሲደረግ ቆይቷል። እነዚህ ጥረቶች በተወሰነ ደረጃ ውጤት ያስገኙ ቢሆንም እንኳ የሰዎች የአኗኗር ዘይቤና ልማድ በጣም ሥር የሰደደ ከመሆኑ የተነሳ የሚፈለገውን ያህል ለውጥ ማምጣት አስቸጋሪ ሆኗል።
በሕክምናው መስክ የታየ ለውጥ
በሕክምናው መስክ ሳይንቲስቶች ስለ ኤች አይ ቪ ብዙ ግንዛቤ ያገኙ ከመሆኑም ሌላ የብዙዎችን ሕይወት ማራዘም የቻሉ መድኃኒቶችን መፈልሰፍ ችለዋል። ቢያንስ ሦስት ዓይነት የዕድሜ ማራዘሚያ መድኃኒቶችን በማቀናጀት የሚሰጠው ሕክምና ጥሩ ውጤት አስገኝቷል።
እነዚህ መድኃኒቶች ፈውስ ማስገኘት ባይችሉም እንኳ በተለይ በበለጸጉ አገሮች በኤች አይ ቪ የሚሞቱ ሰዎችን ቁጥር መቀነስ ችለዋል። ብዙ ሰዎች እነዚህ መድኃኒቶች በማደግ ላይ ወደሚገኙ አገሮችም መግባት እንዳለባቸው ይናገራሉ። ይሁን እንጂ መድኃኒቶቹ ውድ በመሆናቸው በእነዚህ አገሮች ውስጥ የሚኖሩት አብዛኞቹ ሰዎች እነዚህን መድኃኒቶች የመግዛት አቅም የላቸውም።
ይህ ሁኔታ፣ ገንዘብ ከሰው ሕይወት ይበልጣል? የሚል አከራካሪ ጉዳይ አስነስቷል። የብራዚል የኤች አይ ቪ/ኤድስ ፕሮግራም ዲሬክተር የሆኑት ዶክተር ፓውሎ ቴሼይራ ሁኔታውን እንዲህ ሲሉ ገልጸውታል:- “መድኃኒቶቹን የሚያመርቱት ኩባንያዎች ከልክ ያለፈ ትርፍ እንዲያጋብሱ ሲባል ብቻ በሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ሕይወታቸውን ለማቆየት የሚያስችሏቸውን መድኃኒቶች ማግኘት ተስኗቸው ሲቸገሩ ዝም ብለን ማየት አንችልም።” አክለውም “ግብረገብንና ሰብዓዊ ርኅራኄን ወደ ጎን ገሸሽ አድርጎ ለንግድ ጥቅም ብቻ መሯሯጥ አይገባም” ብለዋል።
አንዳንድ አገሮች የመድኃኒት አምራች የሆኑ ትልልቅ ኩባንያዎችን የባለቤትነት መብት ባለማክበር የንግድ ምልክት የሌላቸውን ተመሳሳይ መድኃኒቶች በዝቅተኛ ዋጋ ለማስገባት ወይም ለመሥራት ወስነዋል።* አንድ ጥናት እንዳመለከተው ከሆነ “[የንግድ ምልክት የሌላቸው መድኃኒቶች] ዝቅተኛ ዋጋ ከዩናይትድ ስቴትስ መነሻ ዋጋ 82 በመቶ ዝቅ ብሎ ተገኝቷል” ሲል ሳውዝ አፍሪካን ሜዲካል ጆርናል ዘግቧል።
ሕክምናው ያጋጠሙት እንቅፋቶች
ይሁንና ውሎ አድሮ ትልልቆቹ የመድኃኒት አምራች ኩባንያዎች የኤድስ መድኃኒቶችን ለታዳጊ አገሮች ዝቅ ባለ ዋጋ ማቅረብ ጀምረዋል። በዚህ መንገድ ብዙ ተጨማሪ ሰዎች መድኃኒቶቹን ማግኘት ይችላሉ ተብሎ ተስፋ ተደርጓል። ይሁን እንጂ እንዲህ ያሉ መድኃኒቶች በታዳጊ አገሮች ውስጥ በስፋት ጥቅም ላይ እንዳይውሉ ከባድ እንቅፋት የሆኑ ነገሮች አሉ። ከእነዚህ እንቅፋቶች መካከል አንዱ የዋጋው ጉዳይ ነው። ዋጋው በእጅጉ እንዲቀንስ ቢደረግም መድኃኒቶቹ የሚያስፈልጓቸው ብዙዎቹ ሰዎች አሁንም የመግዛት አቅም የላቸውም።
ሌላው ችግር ደግሞ የመድኃኒቶቹ አወሳሰድ ነው። በየዕለቱ ሰዓቱን በትክክል እየጠበቁ ብዙ ኪኒኖች መውሰድ ይጠይቃል። ታካሚው መድኃኒቶቹን በአግባቡ የማይወስድ ወይም በየመሃሉ የሚያቋርጥ ከሆነ መድኃኒቱን መቋቋም የሚችሉ የኤች አይ ቪ ዝርያዎች ሊፈጠሩ ይችላሉ። ምግብ፣ ንጹሕ የመጠጥ ውኃም ሆነ የሕክምና ተቋማት በበቂ ሁኔታ በማይገኙባቸው የአፍሪካ አገሮች ታካሚዎች መድኃኒቶቹን በትክክል እንዲወስዱ ማድረግ አስቸጋሪ ነው።
በተጨማሪም መድኃኒቶቹን የሚወስዱ ሰዎች ክትትል ያስፈልጋቸዋል። ቫይረሱ መድኃኒቶቹን መቋቋም ከጀመረ የመድኃኒቶቹ ዓይነት መለወጥ አለበት። ይህ ደግሞ ልምድ ያላቸው የህክምና ባለሙያዎች ማግኘት የሚጠይቅ ከመሆኑም ሌላ ምርመራው የሚጠይቀው ወጪም ቀላል አይደለም። ከዚህም በተጨማሪ መድኃኒቶቹ የራሳቸው የሆነ ጉዳት ያላቸው ሲሆን መድኃኒት መቋቋም የሚችሉ ቫይረሶችም እየተፈጠሩ ይሄዳሉ።
የተባበሩት መንግሥታት ጠቅላላ ጉባኤ ሰኔ 2001 ኤድስን አስመልክቶ ባካሄደው ልዩ ስብሰባ ላይ ታዳጊ አገሮችን ለመርዳት ለጤና አገልግሎት የሚውል የእርዳታ ገንዘብ በዓለም አቀፍ ደረጃ እንዲሰባሰብ ሐሳብ ቀርቦ ነበር። ለዚህ እርዳታ ከ7 ቢልዮን እስከ 10 ቢልዮን የሚደርስ የአሜሪካ ዶላር እንደሚያስፈልግ ተገምቷል። ይሁን እንጂ እስካሁን ድረስ ቃል የተገባው ገንዘብ ከሚፈለገው ገንዘብ ጋር ሲነጻጸር አነስተኛ ነው።
ሳይንቲስቶች በሽታውን የሚከላከል ክትባት እናገኛለን የሚል ጠንካራ እምነት ያላቸው ሲሆን የተለያዩ ክትባቶችም በተለያዩ አገሮች እየተሞከሩ ነው። ይሁን እንጂ እነዚህ ጥረቶች ቢሳኩ እንኳን ክትባቱ እስኪዘጋጅ፣ እስኪሞከርና አስተማማኝነቱ ተረጋግጦ በስፋት ጥቅም ላይ እስኪውል በርከት ያሉ ዓመታት ይወስዳል።
እንደ ብራዚል፣ ታይላንድና ኡጋንዳ ያሉ አንዳንድ አገሮች በዘረጉት የሕክምና ፕሮግራም ጥሩ ውጤት አግኝተዋል። ብራዚል በአገር ውስጥ የሚመረቱ መድኃኒቶችን ጥቅም ላይ በማዋል በኤድስ የሚሞቱ ሰዎችን ቁጥር በግማሽ መቀነስ ችላለች። የገንዘብ አቅሙ ያላት ትንሿ አገር ቦትስዋና በአገሪቱ ውስጥ በኤች አይ ቪ ለተጠቁ ሰዎች የዕድሜ ማራዘሚያ መድኃኒቶች ለማዳረስና አስፈላጊ የሆኑትን የጤና አገልግሎት መስጫ ተቋማት ለማሟላት ጥረት እያደረገች ነው።
ኤድስ ድል የሚደረግበት መንገድ
ኤድስን መከላከል የሚቻል መሆኑ ከሌሎች ወረርሽኞች የተለየ ያደርገዋል። ሰዎች የመጽሐፍ ቅዱስን መሠረታዊ ሥርዓቶች ካከበሩ ከኤድስ ራሳቸውን መጠበቅ ይችላሉ።
የመጽሐፍ ቅዱስ የሥነ ምግባር ደንቦች የማያሻሙ ናቸው። ያልተጋቡ ሰዎች ከጾታ ግንኙነት መታቀብ አለባቸው። (1 ቆሮንቶስ 6:18) የተጋቡ ሰዎችም ለትዳር ጓደኛቸው ታማኝ መሆንና ከምንዝር መራቅ አለባቸው። (ዕብራውያን 13:4) በተጨማሪም አንድ ሰው ከደም እንድንርቅ የሚያዝዘውን የመጽሐፍ ቅዱስ ማስጠንቀቂያ መከተሉ በበሽታው ከመያዝ ይጠብቀዋል። ሐዋ.ሥራ 15:28, 29
በበሽታው የተያዙ ሰዎች አምላክ በቅርቡ ስለሚያመጣው ከበሽታ ነፃ የሆነ ዓለም በመማርና አምላክ ያወጣቸውን ብቃቶች በማሟላት ከፍተኛ ደስታና መጽናኛ ማግኘት ይችላሉ።
መጽሐፍ ቅዱስ በሽታን ጨምሮ በሰው ልጆች ላይ እየደረሱ ያሉት ችግሮች በሙሉ እንደሚወገዱ ያረጋግጥልናል። ይህ ተስፋ በራእይ መጽሐፍ ውስጥ ተገልጾአል:- “ታላቅም ድምፅ ከሰማይ:- እነሆ፣ የእግዚአብሔር ድንኳን በሰዎች መካከል ነው ከእነርሱም ጋር ያድራል፣ እነርሱም ሕዝቡ ይሆናሉ እግዚአብሔርም እርሱ ራሱ ከእነርሱ ጋር ሆኖ አምላካቸው ይሆናል፤ እንባዎችንም ሁሉ ከዓይኖቻቸው ያብሳል፣ ሞትም ከእንግዲህ ወዲህ አይሆንም፣ ኀዘንም ቢሆን ወይም ጩኸት ወይም ሥቃይ ከእንግዲህ ወዲህ አይሆንም፣ የቀደመው ሥርዓት አልፎአልና ብሎ ሲናገር ሰማሁ።” ራእይ 21:3, 4
ይህ ዋስትና የተሰጠው ውድ መድኃኒቶችን የመግዛት አቅም ላላቸው ብቻ አይደለም። ኢሳይያስ 33:24 “በዚያም የሚቀመጥ:- ታምሜአለሁ አይልም” በማለት በራእይ ምዕራፍ 21 ላይ የተገለጸውን ትንቢታዊ ቃል ያጠናክርልናል። በዚያ ዘመን በምድር ላይ የሚኖሩ ሁሉ የአምላክን ሕግ የሚጠብቁ ከመሆናቸውም በላይ ፍጹም የሆነ ጤና ያገኛሉ። በዚህ መንገድ የብዙዎችን ሕይወት እየቀጠፈ ያለው ኤድስም ሆነ ሌሎች በሽታዎች በሙሉ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ይወገዳሉ።
የንግድ ምልክት የሌላቸው መድኃኒቶች በሌሎች የመድኃኒት አምራች ኩባንያዎች የተፈበረኩ መድኃኒቶችን በማስመሰል የሚሠሩ ናቸው። የዓለም የንግድ ድርጅት አባል የሆኑ አገሮች ድንገተኛና አጣዳፊ ሁኔታዎች በሚያጋጥሙበት ጊዜ የመድኃኒቶችን የባለቤትነት መብት ያለማክበር ህጋዊ ፈቃድ አላቸው።
ስፈልገው የነበረው እውነተኛ ፈውስ ይህ ነው
በኤች አይ ቪ መያዜን ያወቅኩበት ቀን አሁንም ድረስ ትዝ ይለኛል ትላለች አንድ ወጣት
በሕክምና ክፍሉ ውስጥ ከእናቴ ጋር ቁጭ ብዬ ሳለ ነበር ዶክተሩ መርዶዬን የነገረኝ። በሕይወቴ እንደዚያን ዕለት ያዘንኩበት ቀን አልነበረም። ሁሉ ነገር ተመሰቃቀለብኝ። ጆሮዬን ማመን አልቻልኩም። ምርመራው ላይ ስህተት ተሠርቶ ሊሆን ይችላል ብዬ አሰብኩ። የምናገረውና የማደርገው ነገር ሁሉ ጠፋኝ። አልቅሽ አልቅሽ ቢለኝም የማለቅስበት እንባ እንኳ አልነበረኝም። ዶክተሩ ስለ ዕድሜ ማራዘሚያ መድኃኒቶችና ስለ ሌሎች ጉዳዮች ከእናቴ ጋር እየተነጋገረ የነበረ ቢሆንም በጣም ከመደንገጤ የተነሳ ምን እንደሚል እንኳ ሊገባኝ አልቻለም ነበር።
እማርበት በነበረው ዩኒቨርሲቲ ውስጥ አንድ ሰው አስይዞኝ ሊሆን እንደሚችል ገመትኩ። ያለሁበትን ሁኔታ ሊረዳልኝ ለሚችል ሰው ስሜቴን ለማካፈል ብፈልግም ማንም ሰው ወደ አእምሮዬ ሊመጣልኝ አልቻለም። የከንቱነትና የዋጋቢስነት ስሜት ተሰማኝ። ቤተሰቦቼ አስፈላጊውን ድጋፍ ቢያደርጉልኝም የተስፋ መቁረጥና የፍርሃት ስሜት አደረብኝ። እንደ ሌላ ማንኛውም ወጣት እኔም ብዙ የምመኛቸው ነገሮች ነበሩ። በሳይንስ የመጀመሪያ ዲግሪዬን ለማግኘት ሁለት ዓመት ብቻ ቀርቶኝ የነበረ ቢሆንም ያ ሁሉ ተስፋ እንዳልነበረ ሆነ።
የታዘዙልኝን የዕድሜ ማራዘሚያ መድኃኒቶች መውሰድና ወደ ኤድስ ሕሙማን አማካሪዎች መሄድ ብጀምርም ያደረብኝ ጭንቀት ሊለቀኝ አልቻለም። ከመሞቴ በፊት እውነተኛውን ክርስትና እንዲያሳውቀኝ ወደ አምላክ ጸለይኩ። ሁለቱ ሴቶች በሬን አንኳኩ። ያን ቀን በጣም አሞኝ የነበረ ቢሆንም ሳሎን ውስጥ እንደ ምንም ብዬ ቁጭ አልኩ። ሁለቱ ሴቶች ራሳቸውን ካስተዋወቁኝ በኋላ ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስን እንዲያጠኑ በመርዳት ላይ መሆናቸውን ነገሩኝ። ጸሎቴ በመጨረሻ መልስ በማግኘቱ ትልቅ እፎይታ ተሰማኝ። ሆኖም አቅም አንሶኝ ስለነበር ረዘም ላለ ጊዜ ማንበብም ሆነ በትኩረት መከታተል አልቻልኩም። ሆኖም መጽሐፍ ቅዱስ ማጥናት እንደምፈልግ ነገርኳቸውና ቀጠሮ ይዘን ተለያየን። ይሁንና የቀጠሮው ጊዜ ከመድረሱ በፊት ባደረብኝ የመንፈስ ጭንቀት ሳቢያ የአእምሮ ሕሙማን ወደሚታከሙበት ሆስፒታል ገባሁ። ከሦስት ሳምንታት በኋላ ከሆስፒታል ስወጣ ሁለቱ ሴቶች እንዳልረሱኝ በማወቄ በጣም ደስ አለኝ። ሁለቱ ሴቶች አንዷ ዘወትር እየመጣች ትጠይቀኝ እንደነበር አስታውሳለሁ። በተወሰነ ደረጃ አገገምኩና ዓመቱ መገባደጃ ላይ መጽሐፍ ቅዱስ ማጥናት ጀመርኩ። ይሁን እንጂ የጤንነቴ ሁኔታ በየጊዜው ይለዋወጥ ስለነበረ ይህን ማድረጉ ቀላል አልነበረም። ሆኖም የምታስጠናኝ ሴት ችግሬን ትረዳልኝ የነበረ ከመሆኑም በላይ ታጋሽ ነበረች።
ስለ እግዚአብሔርና ስለ ባሕርያቱ ከመጽሐፍ ቅዱስ ስማርና እግዚአብሔርን ማወቅና የዘላለም ሕይወት ተስፋን መጠባበቅ ምን ማለት እንደሆነ ስገነዘብ ልቤ በጣም ተነካ። በተጨማሪም በሰው ልጆች ላይ መከራ የሚደርሰው ለምን እንደሆነ ለመጀመሪያ ጊዜ በግልጽ ተረዳሁ። በቅርቡ ሰብዓዊ መንግሥታትን ሁሉ ስለሚተካው የእግዚአብሔር መንግሥት ያገኘሁት እውቀትም እጅግ ያስደሰተኝ ከመሆኑም በላይ አኗኗሬን ሙሉ በሙሉ እንድለውጥ አነሳሳኝ።
ስፈልገው የነበረው እውነተኛ ፈውስ ይህ ነው። እግዚአብሔር አሁንም እንደሚወደኝና እንደሚያስብልኝ ማወቄ በጣም አጽናናኝ። ቀደም ሲል እግዚአብሔር እንደጠላኝና ይህ በሽታ የያዘኝም በዚሁ ምክንያት እንደሆነ አድርጌ አስብ ነበር። ይሁን እንጂ እግዚአብሔር በፍቅር ተነሳስቶ በኢየሱስ ክርስቶስ ቤዛዊ መሥዋዕት አማካኝነት የኃጢአት ይቅርታ ማግኘት የምንችልበትን ዝግጅት እንዳደረገ ሳውቅ “እርሱ ስለ እናንተ ያስባልና የሚያስጨንቃችሁን ሁሉ በእርሱ ላይ ጣሉት” የሚለው የ1
ጴጥሮስ 5:7 ጥቅስ በሚገልጸው መሠረት በእርግጥም እግዚአብሔር የሚያስብልን መሆኑን ተገነዘብኩ።
መጽሐፍ ቅዱስን በየዕለቱ በማጥናትና በሚካሄዱ ስብሰባዎች ላይ በመገኘት ወደ እግዚአብሔር ለመቅረብ የተቻለኝን ሁሉ እያደረግኩ ነው። ይህን ማድረጉ ሁልጊዜ ቀላል ባይሆንም እንኳ የሚያስጨንቀኝን ሁሉ ለእግዚአብሔር በጸሎት በመግለጽ ብርታትና ማጽናኛ እንዲሰጠኝ እለምነዋለሁ። በተጨማሪም የጉባኤያችን አባላት ምንጊዜም ከጎኔ ስለሆኑ በጣም ደስተኛ ነኝ።
ክፍል 3
ሁሉም ሰው አልፎ አልፎ ይታመማል። ሰዎች የሚታመሙት፣ የሚያረጁትና
የሚሞቱት ለምን እንደሆነ ታውቃለህ? አንድ ቀን ሰዎች መራመድ የማይችል ሰው ወደ ኢየሱስ አምጥተው ነበር፤
በዚህ ጊዜ ኢየሱስ ሰዎች የሚታመሙትና የሚሞቱት ለምን እንደሆነ ጠቁሞ ነበር። እስቲ በዚያ ወቅት የተፈጸመውን ነገር ልንገርህ።
ኢየሱስ በገሊላ ባሕር አቅራቢያ በሚገኝ አንድ ቤት ውስጥ ተቀምጦ
ነበር። በዚህ ጊዜ ብዙ ሰዎች ወደ እሱ መጡ። በጣም ብዙ ሰዎች መጥተው ስለነበር ሌሎች ተጨማሪ ሰዎች ወደ ቤት መግባት አልቻሉም።
ከሕዝቡ ብዛት የተነሳ ወደ በሩ ለመጠጋት የሚያስችል ቦታ እንኳ አልነበረም። ያም ሆኖ ሰዎቹ መምጣታቸውን አላቋረጡም ነበር። በዚህ
ጊዜ ሰዎች መራመድ የማይችል ሽባ የሆነ ሰው አመጡ። ሰውየውን በትንሽ አልጋ ወይም በቃሬዛ ላይ አድርገው የተሸከሙት አራት ሰዎች
ነበሩ።
ሰዎቹ ይህን የታመመ ሰው ወደ ኢየሱስ ማምጣት የፈለጉት ለምን እንደሆነ
ታውቃለህ? ኢየሱስ ሊረዳውና ከበሽታው ሊፈውሰው እንደሚችል እርግጠኞች ስለነበሩ ነው። ታዲያ ያ ሁሉ ሰው እያለ ሽባውን ሰው እንዴት
ኢየሱስ ፊት እንዳቀረቡት ታውቃለህ?
በመጀመሪያ ሰውየውን ተሸክመው ጣሪያው ላይ ወጡ። ጣሪያው ለጥ ያለ
ነበር። ከዚያም ጣሪያውን በስተው ሰውየውን ሊያሾልክ የሚችል ትልቅ ቀዳዳ ሠሩ። በመጨረሻም የታመመውን ሰው ከነአልጋው በቀዳዳው
በኩል አሾልከው ወደ ውስጥ አወረዱት። በእርግጥም ጠንካራ እምነት ነበራቸው!
በቤቱ ውስጥ ያሉት ሰዎች በሙሉ ይህን ሲያዩ ተገረሙ። ሽባውን ሰው
የተሸከሙት ሰዎች ከነአልጋው አውርደው በተሰበሰቡት ሰዎች መካከል አደረጉት። ኢየሱስ ሰዎቹ ያደረጉትን ሲያይ ተቆጣ? በጭራሽ! እንዲያውም
ሰዎቹ ባሳዩት እምነት ተደስቶ ነበር። ሽባውን “ኃጢአትህ ይቅር ተብሎልሃል” አለው።
በቦታው የነበሩት አንዳንድ ሰዎች ኢየሱስ እንዲህ ብሎ መናገሩ ትክክል
አይደለም ብለው አሰቡ። ኢየሱስ ኃጢአትን ይቅር ማለት የሚችል አልመሰላቸውም ነበር። ስለዚህ ኢየሱስ ኃጢአትን ይቅር ማለት እንደሚችል
ለማሳየት ሰውየውን “ተነስ፣ አልጋህን ተሸክመህ ወደ ቤትህ ሂድ” አለው።
ኢየሱስ ይህን ሲናገር ሰውየው ተፈወሰ። ሽባ መሆኑ ቀርቶ አሁን
ያለማንም ድጋፍ ራሱ ቆሞ መሄድ ቻለ። ይህን ተአምር ያዩት ሰዎች በጣም ተገረሙ። በሕይወታቸው በሙሉ እንደዚህ ያለ አስገራሚ ነገር
አይተው አያውቁም። ሰዎችን ከበሽታቸው መፈወስ የሚችል እንደዚህ ያለ ታላቅ አስተማሪ ስለሰጣቸው አምላክን አመሰገኑት።ማርቆስ 2:1-12
እኛ ከዚህ ተአምር ምን እንማራለን? ኢየሱስ ኃጢአትን ይቅር ለማለትና የታመሙ ሰዎችን ለማዳን የሚያስችል ኃይል እንዳለው እንማራለን። ይሁን እንጂ ሌላም የምንማረው
በጣም አስፈላጊ ነገር አለ። ሰዎች የሚታመሙት በኃጢአት ምክንያት እንደሆነ እንማራለን። ታዲያ ሁላችንም አንዳንድ ጊዜ የምንታመመው ኃጢአተኞች ስለሆንን
ነው ማለት ነው? አዎ፣ መጽሐፍ ቅዱስ ሁላችንም ኃጢአተኞች ሆነን እንደተወለድን ይናገራል። ኃጢአተኛ ሆኖ መወለድ ምን ማለት እንደሆነ
ታውቃለህ?ሁላችንም ፍጽምና የሌለን ወይም ጉድለት ያለብን ሆነን ተወልደናል ማለት ነው። አንዳንድ ጊዜ ሳንፈልግ ስህተት እንሠራለን።
ሁላችንም ኃጢአተኞች ልንሆን የቻልነው ለምን እንደሆነ ታውቃለህ?
ሁላችንም ኃጢአተኞች ልንሆን የቻልነው የመጀመሪያው ሰው አዳም አምላክን
ስላልታዘዘ ነው። አዳም የአምላክን ሕግ በጣሰ ጊዜ ኃጢአት ሠራ። እኛ ሁላችን ደግሞ ከአዳም ኃጢአትን ወረስን። ኃጢአት ከአዳም
የተጋባብን እንዴት እንደሆነ ታውቃለህ? እስቲ ይህን ነገር ሊገባህ በሚችል መንገድ ላስረዳህ።
ዳቦ ሲጋገር አይተህ ታውቃለህ? የዳቦ መጋገሪያ ዕቃው የተሰረጎደ
ከሆነ የሚጋገረው ዳቦ ሁሉ ምን እንደሚሆን ታውቃለህ? በዚህ ዕቃ የሚጋገረው ዳቦ ሁሉ ልክ እንደ ዕቃው የተሰረጎደ ይሆናል፣ አይደል?
አዳም እንደ ዳቦ መጋገሪያ ዕቃው ሲሆን እኛ ሁላችን ደግሞ እንደ
ዳቦው ነን። አዳም የአምላክን ሕግ ሲጥስ ፍጽምና የጎደለው ሆነ። ልክ እንደ ዕቃው የተሰረጎደ ወይም መጥፎ ምልክት የወጣበት ያህል
ነበር። ስለዚህ እሱ የሚወልዳቸው ልጆች እንዴት ያሉ ይሆናሉ?
ልጆቹ በሙሉ ያንኑ የአለፍጽምና
ምልክት ወይም ጉድለት ይዘው ይወለዳሉ።
አብዛኞቹ ልጆች ሲወለዱ በዓይን የሚታይ ትልቅ ጉድለት አይኖርባቸውም።
እጅ ወይም እግር የሌላቸው ሆነው አይወለዱም። ሆኖም ያለባቸው አለፍጽምና ወይም ጉድለት ከባድ በመሆኑ ይታመሙና ከጊዜ በኋላ ይሞታሉ።
እርግጥ ነው፣ አንዳንድ ሰዎች ከሌሎች ይበልጥ ቶሎ ቶሎ ይታመማሉ።
ይህ የሆነው ለምንድን ነው? ከሌሎች ሰዎች የበለጠ ኃጢአተኛ ሆነው ስለሚወለዱ ነው? አይደለም፤ ሁሉም ሰው ይዞት የሚወለደው ኃጢአት መጠን እኩል ነው። ሁላችንም ኃጢአተኞች ሆነን ተወልደናል። ስለዚህ ከጊዜ
በኋላ ሁሉም ሰው በሆነ ዓይነት በሽታ መታመሙ አይቀርም። የአምላክን ሕግ በሙሉ ለመታዘዝ የሚጥሩና ምንም ዓይነት ክፉ ነገር የማይሠሩ
ሰዎችም እንኳን ሊታመሙ ይችላሉ።
ታዲያ አንዳንዶቹ ሰዎች ከሌሎቹ ይበልጥ ቶሎ ቶሎ የሚታመሙት ለምንድን
ነው? ይህ
የሚሆንበት ብዙ ምክንያት አለ። ምናልባት የሚመገቡት በቂ ምግብ ላይኖራቸው ይችላል። ወይም ደግሞ ለጤንነታቸው ጠቃሚ የሆነ ምግብ
አይመገቡ ይሆናል። እንደ ኬክና ከረሜላ ያሉ ብዙ ጣፋጭ ነገሮች ይበሉ ይሆናል። ሌላው ምክንያት ደግሞ ማታ ቶሎ ስለማይተኙና በቂ
እንቅልፍ ስለማያገኙ ሊሆን ይችላል። ወይም ደግሞ በዝናብና በብርድ ሰዓት የሚሞቅ ልብስ አይለብሱ ይሆናል። አንዳንድ ሰዎች ደግሞ
ራሳቸውን ለመንከባከብ ቢጥሩም ሰውነታቸው ከሌሎቹ ይበልጥ ደካማና በሽታን መከላከል የማይችል ነው።
ታዲያ ፈጽሞ የማንታመምበት ጊዜ ይመጣ ይሆን? ከኃጢአት ነፃ መሆን
እንችል ይሆን? ኢየሱስ ለሽባው ሰው ያደረገለት ነገር ምን ነበር? ኢየሱስ ኃጢአቱን ይቅር ብሎታል፤ እንዲሁም ፈውሶታል። ኢየሱስ
ይህን መፈጸሙ ትክክል የሆነውን ነገር ለማድረግ ለሚጥሩ ሰዎች ሁሉ አንድ ቀን ምን እንደሚያደርግላቸው ያሳያል።
እኛም ኃጢአት መሥራት እንደማንፈልግና መጥፎ የሆነውን ነገር እንደምንጠላ
የምናሳይ ከሆነ ኢየሱስ ይፈውሰናል። ወደፊት አሁን ያለብንን አለፍጽምና ሁሉ ያስወግድልናል። ይህን የሚያደርገው የአምላክ መንግሥት
ንጉሥ ሆኖ በሚገዛበት ጊዜ ነው። ኃጢአታችን የሚወገድልን በአንድ ጊዜ ሳይሆን ቀስ በቀስ ነው። ከዚያም ኃጢአታችን ሙሉ በሙሉ ሲወገድ
ዳግመኛ አንታመምም። ሁላችንም ፍጹም ጤንነት ይኖረናል። ይህ በጣም የሚያስደስት ይሆናል!
ኃጢአት በሁላችንም ላይ ምን እንደሚያስከትል ይበልጥ ለመረዳት ኢዮብ
14:4፤ መዝሙር 51:5፤ ሮም 3:23፤ 5:12 እና 6:23ን አንብቡ።
መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?
መጽሐፍ ቅዱስ የሕክምና መጽሐፍ አይደለም፤ ደግሞም ሰዎች የሚያደርጉትን እያንዳንዱን ነገር የሚቆጣጠር
መመሪያ አልያዘም። ያም ቢሆን አምላክ፣ ጤንነትን ስለ መጠበቅ ያለውን አመለካከት የሚጠቁሙ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የሚገኙ ሐሳቦችን
ማወቅህ ይጠቅምሃል።
መጽሐፍ ቅዱስ ለሰውነታችን የምናደርገው እንክብካቤ አምላክን እንደሚያሳስበው የሚጠቁሙ በርካታ ሐሳቦች
ይዟል። ለምሳሌ ያህል፣ መጽሐፍ ቅዱስ ሆዳምነትንና ሰካራምነትን ጨምሮ ከልክ በላይ የሚደረጉ ጎጂ ነገሮችን ያወግዛል። (ምሳሌ
23:20) አምላክ ለጥንቶቹ እስራኤላውያን በሰጠው ሕግ ላይ በሽታዎች እንዳይስፋፉ ለመቆጣጠር ከተቻለም እንዳይከሰቱ ለመከላከል
መደረግ ያለባቸው ነገሮች ተካትተዋል። በተጨማሪም ሕጉ በሰው ላይ ጉዳት የሚያደርሱ አደጋዎችን ለማስወገድ የሚረዱ የደህንነት መመሪያዎችን
ይዟል። (ዘዳግም 22:8) ከዚህ በግልጽ ለማየት እንደሚቻለው መጽሐፍ ቅዱስ፣ ሰውነታችንን እንድንንከባከብና ጤንነታችንን ለመጠበቅ
አስፈላጊውን ነገር እንድናደርግ ያበረታታል።
የምንታመምበትን ምክንያት በተመለከተ መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?
“በአንድ ሰው አማካኝነት ኃጢአት ወደ ዓለም ገባ፤ በኃጢአትም ምክንያት ሞት መጣ።”ሮም 5:12
ሰዎች ምን ይላሉ?
ብዙዎች በሽታ ሰው በዝግመተ ለውጥ ሲገኝ በአጋጣሚ የተከሰተ ችግር እንደሆነ ያምናሉ። ሌሎች ደግሞ
እንደ ክፉ መናፍስት ያሉ ሚስጥራዊ ኃይሎች የጤና መቃወስ እንደሚያስከትሉብን አድርገው ያስባሉ።
መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?
መጽሐፍ ቅዱስ፣ የምንታመመው የመጀመሪያዎቹ ባልና ሚስት በአምላክ ላይ በማመፃቸው ምክንያት እንደሆነ
ይናገራል። (ሮም 5:12) የመጀመሪያዎቹ ወላጆቻችን አዳምና ሔዋን በአምላክ ላይ ከማመፃቸው በፊት ፍጹም ጤንነት ነበራቸው። አፍቃሪ
የሆነውን አምላክ እንክብካቤ ካጡ እንደሚሞቱ ያውቁ ነበር። (ዘፍጥረት 2:16, 17) ይሁንና ሆን ብለው ከአምላክ ጋር እንዲቆራረጡ
የሚያደርግ ነገር ፈጸሙ፤ በመሆኑም ፍጽምናቸውን አጡ።*
ፍጽምናቸውን ያጡት የመጀመሪያዎቹ ወላጆቻችን ለእኛም አለፍጽምናን አወረሱን። በመሆኑም የጤና እክሎችን
ለማስወገድ የቱንም ያህል ጥረት ቢደረግ መታመማችን አይቀርም።
ምን ማድረግ ትችላለህ?
አምላክ ያወጣቸውን ጥበብ
የሚንጸባረቅባቸው መመሪያዎች በመታዘዝ ከእሱ
ጋር እርቅ ከፈጠርክ ወደፊት ምድር
ገነት ስትሆን ፍጹም ጤንነት አግኝተህ መኖር
እንደምትችል መጽሐፍ ቅዱስ ያስተምራል። (ኢሳይያስ 33:24) አምላክ ሕመምን፣ በሽታንና ሞትን
ለማስወገድ ቃል ገብቷል። ራእይ
21:3, 4
መጽሐፍ ቅዱስ የሕክምና እርዳታ ማግኘትን ይቃወማል?
“ሐኪም
የሚያስፈልጋቸው ሕመምተኞች እንጂ ጤነኞች አይደሉም።” ማቴዎስ 9:12
ሰዎች ምን ይላሉ?
አንዳንዶች የሕክምና እርዳታ ከማግኘት ይልቅ
ሃይማኖታዊ ፈውስ (ወይም የእምነት ፈውስ)
ማግኘት የተሻለ እንደሆነ ይናገራሉ።
መጽሐፍ ቅዱስ ምን
ይላል?
በጥንት ዘመን በነበሩ የአምላክ ሕዝቦች መካከል የጤና
እርዳታ የሚሰጡ ሰዎች የነበሩ ሲሆን
አምላክ ይህን ሙያቸውን አልተቃወመም። (ዘፍጥረት 38:28፤
ቆላስይስ
4:14) እነዚህ ሰዎች ለመድኃኒትነት የሚውሉ ተክሎችንና ቅባቶችን በመጠቀም እንዲሁም ለሕመምተኞቹ አንድ
ዓይነት የአመጋገብ ሥርዓት በማዘዝ ወይም
በሌሎች የሕክምና ዘዴዎች ተጠቅመው ሕክምና በመስጠታቸው አምላክ እንዳልተደሰተ የሚገልጽ ሐሳብ
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አናገኝም። እንዲያውም ኢየሱስ “ሐኪም
የሚያስፈልጋቸው ሕመምተኞች እንጂ ጤነኞች አይደሉም” ሲል
ተናግሯል። ማቴዎስ 9:12
ይሁን እንጂ መጽሐፍ ቅዱስ
ጤነኛ ለመሆን ማንኛውም ዓይነት መሥዋዕት መከፈል አለበት የሚለውን አመለካከት አይደግፍም። ለምሳሌ ያህል
መጽሐፍ ቅዱስ፣ በዛሬው ጊዜ
በሚከናወነው የእምነት ፈውስ ከተፈወሱ መልካም ነው
ከዚህም ሌላ
በመናፍስታዊ ድርጊቶች አማካኝነት ፈውስ
ለማግኘት መሞከር በአምላክ ዘንድ
ተቀባይነት የለውም። (ገላትያ 5:19-21) የጤና እክል
በሚያጋጥመን ጊዜ መጽሐፍ ቅዱስ
በሚያወግዛቸው መንገዶች መጠቀም ተገቢ
ባይሆንም የሚቻል ከሆነ ወዲያውኑ ጥሩ
ሕክምና ለማግኘት መሞከር የጥበብ እርምጃ ነው።
በዚህ ርዕስ ውስጥ
“ፍጹም” እና “ፍጽምና” የሚሉትን ቃላት
የተጠቀምነው የመጀመሪያዎቹ ባልና ሚስት አምላክ ሲፈጥራቸው የነበራቸውን ጤንነት ለማመልከት ነው፤
የመጀመሪያዎቹ ወላጆቻችን በሕመም፣ በበሽታና በሞት
አይጠቁም ነበር።
“በአንድ ሰው በአዳም የተነሳ ኃጢአት ወደ ዓለም ገባ፤ በኃጢአትም ምክንያት ሞት መጣ” ሮም 5:12። ብዙዎች ስዎች በሽታ ሰው በዝግመተ ለውጥ ሲገኝ በአጋጣሚ የተከሰተ ችግር ነው ብለው ሲያምኑ፣ ሌሎች ደግሞ እንደ ክፉ መናፍስት ያሉ ሚስጥራዊ ኃይሎች የጤና መቃወስ እንደሚያስከትሉብን አድርገው ያስባሉ።
መጽሐፍ ቅዱስ፣ የምንታመመው የመጀመሪያዎቹ ባልና ሚስት አዳምና ሔዋን በእግዚአብሄር ላይ በማመፃቸው የተነሳ እንደሆነ ይናገራል (ሮም 5:12)። የመጀመሪያዎቹ ወላጆቻችን አዳምና ሔዋን በእግዚአብሄር ላይ ከማመፃቸው በፊት ፍጹም ጤንነት ነበራቸው። አፍቃሪ የሆነውን አምላክ እንክብካቤ ካጡ እንደሚሞቱ ያውቁ ነበር። (ዘፍጥረት 2:16, 17) ይሁንና ከእግዚአብሄር ጋር እንዲቆራረጡ የሚያደርጋቸው ሃጢያትን ፈጸሙ፤ በመሆኑም እግዚአብሄር ካስቀመጠላቸው ደረጃ ወይም መመሪያ ዝቅ አሉ ስለሆነም ችግር ውስጥ ገቡ ። ፍጽምናቸውን ያጡት የመጀመሪያዎቹ ወላጆቻችን ለእኛም ሃጢያትን አወረሱን። በመሆኑም የጤና እክሎችን ለማስወገድ የቱንም ያህል ጥረት ቢደረግ መታመማችን አይቀርም። እግዚአብሄር ያወጣቸውን ጥበብ የሚንጸባረቅባቸው መመሪያዎች በመታዘዝ ከእሱ ጋር እርቅ አንድ ስው ከመስረተ ወደፊት በኢሳይያስ 33:24፤ ራእይ 21:3- 4 እግዚአብሄር ሕመምን፣ በሽታንና ሞትን ለማስወገድ ቃል ገብቷል ጤንነትም ተገኝቶ መኖር እንደሚቻል መጽሐፍ ቅዱስ ያስተምራል።
ከላይ እንዳነሳሁት በሽታ ወደ አለም የገባው በሐጢያት የተነሳ ሲሆን እተባባስ የሄደው በሞራል ወድቀትና በድሎትና በምቾት የተነሳ ነው። የበሽታ ከተፈጥሮ መነሻዎቹ ደግሞ በእብራውያን መካከል በክፉ መናፍስት የተነሳ በሽታዎች በኢዮብ 2፡7 ማርቆ. 9፡17 ሉቃስ 13፡16 1 ቆር. 12፡7 ተጠቅስዋል። ሃይማኖተኛ የሆኑት አይሆዳውያን ደግሞ በሽታ በእግዚአብሔር እጅ የሚላክ መሆኑን በመዝ. 39፡9-11 መዝ. 90፡3-12 ተጽፎል በነርሱ አስተሳስብ በሁሉም ሁኔታ የተለዩ በሽታዎች ወደ ስው የሚላኩት ለቅጣት እንደሆነ በአቤሜሌክ ግያዝ እዮብ ኡዚያ ሚሪያም ሄሮድና ፍልስጤማያን ወዘተ ታሪካቸው ያመለክታል።
ከተባሉትም ሌላ ጥንትም ሆነ አሁን የሰውን ዘር የሚያጠቁ አብዛኞቹ በሽታዎች እንደ ፍርሃት፣ ሐዘን፣ ቅናት፣ ብስጭት፣ ጥላቻና የጥፋተኝነት ስሜት ከመሳሰሉ ስሜታዊ ውጥረቶች እንደሚመነጩ ይታመናል። ከዚህ አንፃር ‘እግዚአብሄርን መፍራት’ “ለሥጋህ ፈውስ ለአጥንትህም ጠገን” ነው የሚለው የመጽሐፍ ቅዱስ አነጋገር ያጽናናል ምሳሌ 3:7, 8። አጥንት የሰውነት ምሰሶ ነው። በመሆኑም መጽሐፍ ቅዱስ አንድን ሰው በተለይም ጥልቅ በሆኑ ስሜቶች የሚነካውን የአንድን ሰው ውስጣዊ ማንነት ለማመልከት “አጥንት” የሚለውን ቃል በምሳሌያዊ አነጋገር ይጠቀምበታል። ሆኖም እግዚአብሄርን መፍራት “ለስውነትህ ፈውስ” የሚሆነው እንዴት ነው? እግዚአብሄርን መፍራት የጥበብ መንገድ ነው። ከእግዚአብሄር የአቋም ደረጃዎች ጋር ተስማምቶ መኖር አሁንም ቢሆን በአካል ጤነኞች እንድንሆን ሊረዳን ይችላል። ከዚህም በላይ የእግዚአብሄር ሞገስ ያስገኝልናል። ይህ ደግሞ እግዚአብሄር በአካልም በስሜትም ፍጹም ጤንነት ወደምናገኝበት ፍጻሜ ወደሌለው ሕይወት ይመራናል ኢሳይያስ 33:24፤ ራእይ 21:4፤ 22:2።
አንዳንዶች የሕክምና እርዳታ ከማግኘት ይልቅ ሃይማኖታዊ ፈውስ (ወይም የእምነት ፈውስ) ማግኘት የተሻለ እንደሆነ ይናገራሉ።በጥንት ዘመን በነበሩ የእግዚአብሄር ሕዝቦች መካከል የጤና እርዳታ የሚሰጡ ሰዎች የነበሩ ሲሆን እግዚአብሄር ይህን ሙያቸውን አልተቃወመም። (ዘፍጥረት 38:28፤ ቆላስይስ 4:14) እነዚህ ሰዎች ለመድኃኒትነት የሚውሉ ተክሎችንና* ቅባቶችን በመጠቀም እንዲሁም ለሕመምተኞቹ አንድ ዓይነት የአመጋገብ ሥርዓት በማዘዝ ወይም በሌሎች የሕክምና ዘዴዎች ተጠቅመው ሕክምና በመስጠታቸው አምላክ እንዳልተደሰተ የሚገልጽ ሐሳብ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አናገኝም። ይሁን እንጂ መጽሐፍ ቅዱስ ጤነኛ ለመሆን ማንኛውም ዓይነት መሥዋዕት መከፈል አለበት የሚለውን አመለካከት አይደግፍም ማለትም በመናፍስታዊ ድርጊቶች አማካኝነት ፈውስ ለማግኘት መሞከር በእግዚአብሄር ዘንድ ተቀባይነት የለውም። (ገላትያ 5:19-21) የጤና እክል በሚያጋጥመን ጊዜ መጽሐፍ ቅዱስ በሚያወግዛቸው መንገዶች መጠቀም ተገቢ ያለመሆኑን የተረዳ ስው ለፈውስ መጸለይ ወይም የሚችል ከሆነ ወዲያውኑ ጥሩ ሕክምና ለማግኘት መሞከር የጥበብ እርምጃ ነው።
(med'-i-sin, med'-i-s'-n) የሐጢያት መድሐኒት ማለት ሲሆን (gehah, teruphah, rephu'ah) እነዚህ ቃላት በሥራ ላይ የዋሉት ለበሽታ በመድሐኒትነት ነው። በምሳሌ 17:22 በኪንግ ጄምስ ቨርሽን የተነሳው “ደስ የሚለው ልብ” እንደ ጥሩ መድሐኒት ነው ይለዋል።
በምሳሌአዊ አባባል ይሁዳንና እስራኤልን በተመለከተ ወደ ህዋላ ስለመመለስ (ኤርም. 30:13) የተመለከተ ነው። ነብዮ እንዳለው rephu'ah የሚፈውስ መድሐኒት (ኤር. 30:13) ነብዮ እንዳለው የሚፈውስ መድሐኒት የለም ነው። በመጨረሻም በኤር. 46:11 ኤርሚያስ ግብጽን ካልተፈውስች ሴት ወደ ገላአድ በለሳን ለመግዛት ከሄደችው ድንግልን ጋር ያወድድራታል። የነብዩ የህዝቅኤል ስለ ህይወት ዛፍና ቅጠሎቹ ያየው ራእይ (በኪንግ ጀምስ ቨርቪን) መድሐኒት የሚለውን ሲሆን ዘሪቫይዝድ ቨርቪን የብሪቲሽን የአሜሪካን የሚያሳየው “የሚፈውስ ወይም ፈውስ” ይለዋል አባባሉም ራዕ. 22:2 ላይ የተጠቀስውን “የዛፉ ቅጠሎች… ህዝቡን ሁሉ የሚፈውስ” ከሚለው ከህዝቅኤል 47:12 አወዳድር።
በጣም ጥቂት የተወሰኑ መፍትሄዎች በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጠቀሱ አሉ። እነዚህም (በኤርምያስ 8:22) "የገለዓድ በለሳን" አንድ anodyne እንደሆነ ይነገራል። "እንኮይ" (ዘፍጥረት 30:14) እና "caperberry" (መክብብ 12: 5 ከርቤ ከእንስላል ከአትክልትም ከከሙንም "ዘይትና የወይን ጠጅ" መልካም ሳምራዊ ሳሙና እና sodic ካርቦኔት (cleansers በስህተት "nitre") የተባለ በናትሮን" እና "የበለስ ጥፍጥፍ" ናቸው።
የግብጽ ፈርማኮፒያ ውስጥ ተለይተው ሊታወቁ የማይችሉ ብዙ ዕፅዋት ነበሩ ነገር ግን ጥቅም ላይ መድኃኒቶች አብዛኞቹ እንደ ማር ወተት ዱቄት ዘይት ኮምጣጤ, ወይን ጠጅ እንደ Dietetic ነበር። የባቢሎናውያን መድሃኒቶ ተመሳሳይ በ Mishna ውስጥ እሬት የዱር አበባ hemlock aconite እና ሌሎች መድኃኒቶች ነበሩ የኪንግ ጀምስ ቅጂ (ዘፀአት 30:25) በዚያን ጊዜ በአፓቲካሪ ጥበብ የተቀመመ የተቀደስ ዘይት እንደሆነ ነው የተጠቀሰው የሽቶዎችና የመድሃኒቶች ሽቶዎች ሠሪ እንደነበረ ያመለክታል።
በመጽሐፍ ቅዱስ ጊዜ የተለያዮ በሽታዎች የሚታከሙት በባለመድሐኒቶች ምናልባትም ከተክሎች በሚገኙ መድሐኒቶች ነው ተብሎ ይታመናል ለዚህም ምሳሌ ንጉስ አሳ 2 ዜና መዋዕል 16፡12 እንደተጠቀስው “በነገስ በስላሳ ዘጠነኛው አመት አሳ እግሩን ታመመ ደዌውም ጽናበት ነገር ግን በታመመ ጊዜ ባለ መድሐኒቶችን እንጂ እግዚአብሄርን አልፈለገም“ ፈውስንም አላገኘም። መድኃኒትነት ያላቸው እጽዋት ለሕክምና ተግባር ማገልገል ከጀመሩ በጣም ረጅም ዘመን አልፏል። በ16ኛው መቶ ዘመን ከክርስቶስ ልደት በፊት በግብጽ በተዘጋጀው ኤበርስ ፓፒረስ የተባለ ጽሑፍ ውስጥ ለተለያዩ በሽታዎች የሚያገለግሉ በመቶዎች የሚቆጠሩ የተፈጥሮ መድኃኒቶች ተመዝግበው ተገኝተዋል። ይሁን እንጂ አብዛኛውን ጊዜ መድኃኒትነት ያላቸው እጽዋት በጽሑፍ ሰፍረው የሚገኙ ሳይሆን በአፍ ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲተላለፉ የቆዩ ናቸው።
በጥንቱ የብሉይ ኪዳን ህብረተስብ የአይን ሕመምም ሌላው ችግራቸው ነበር ይህም በአያሌ ሥፍራዎች በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ተጠቅሷል የተጠቀስውም ከሌሎቹ በሽታዎች ጋር ሲሆን የበለጠ የተያያዘው በአይሁዶች ከግብጾችና ከፍልስፍጤም ስዎች ጋር ነበር። በዘፍጥረት 27፡1 የተጠቀስው “ይስሐቅም ሽምግሎ አይኖቹ ከማየት በፈዘዙ ጊዜ ችግሩ የካታራክት ወይም የሬቲና ዲጀነሬሽን ችግር ነው ያዕቆብ ደሞ ዘፍ. 48፡10 ዔሊ 1 ሳሙ. 4፡15 ተመሳሳይ የአይን ችግሮች አሏቸው። ሙሴና በዘዳግም 34፡7 ሙሴ በመቶ ጊዜ 120 አመቱ አይኑም አልፈዘዘም። ይህም በሽታ የሚይዘው በማንኛውም እድሜ ያሉትን ስዎች ሲሆን በከባድ ሁኔታ የሚተላለፍና በዚያን ጊዜ ከንጽሕና ጉድለትና ልጆች ላይ በዝንቦች ከታመሙ ስዎች አይን ወደ ሌሎች ስዎች በዝንብም ሆነ በንክኪ ይህ አይነት ተላላፊ የአይን በሽታ ያጠቃቸው ነበር።
በአሁድም ሕብረተስብ ውስጥ ይኸው የአይን በሽታ ተባብሶ እውርነትን ስለሚያስከተል በዚህ የአይነስውር የሆኑ ቀሳውስት ማገልገል አይመረጡም (ዘለዋ. 21፡16፥18) የአይን መሞጭሞችም እንኳ ለአገልግሎች እንዳይመረጥ ያደርገዋል (ዘለዋ. 21፡20)። በአዲስ ኪዳን ደሞ ከመወለዱ ጀመሮ እውር የነበር (ዮሐ. 9፡1) ይኸኛውም ሌላ የአይን መታወር ችግር ነው። በማርቆስ 8፡22 ላይ የተጠቀስውን ጌታ የፈውስው መታወሩ ከልጅነቱ ጀመሮ እንደሆነ ያመለክታል። ቅዱስ ጳውሎስም በደማስቆ መንገድ ላይ ከታላቅ ብርሃን የተነሳ አይኑ እንደታወረ ያመለክታል በዚህ ሥፍራ የቅዱስ ጳውሎስ አይን የታወረው በአይኑ ውስጥ ከገባው ከታላቅ ብርሃን የተነሳ ነበር በሐዋሪያት ሥራ 9፡18 ሐናንያ በጸለየለት ጊዜ ከአይኑ ላይ ቅርፊት ወደቀ ይሁን እንጂ የግራ አይኑ ምን ያህል ደካማ እንደሆነ አይታወቀም። በሮሜ 16፡22 የሮሜ መልክቱን የጻፈው እርሱ እራሱ ሳይሆን በቃል እየተናገረ የጻፈለት ሌላ እንደሆነ ያመለክታል ምናልባትም ቅዱስ ጳውሎስ የአይን ችግር ስለላው ነበር ተብሎ ይገመታል። በገላትያ 6፡11 እንዴት ባሉ ትላልቅ ፈደላት በእጄ እንደጻፉላችሁ እዩ ብሎ ለገላትያ ስዎች ይጽፍላቸዋል ምናልባትም ከዚህ አባባሉ የአይን ጤና ችግሮች አሉት ይህም 2 ቆሮ. 12፡7 የተጠቀስው ከዚህ የተነሳ ነው ተብሎ ይታመናል።
እግዚአብሄር አምላክ ሰብዓዊ ፍጡሮቹ ሲፈጥር እንዲታመሙና እንዲሞቱ ዓላማው አልነበረም። አዳምንና ሔዋንን በዔድን የአትክልት ቦታ ማለትም በደስታ ገነት ውስጥ ያስቀመጣቸው ለ70 ወይም ለ80 ዓመታት ብቻ ሳይሆን ለዘላለም ‘እንዲያለሟትና እየተንከባከቡ እንዲጠብቋት’ ነበር። (ዘፍ. 2:8, 15፤ መዝ. 90:10) እነዚህ የመጀመሪያዎቹ ባልና ሚስት ለእግዚአብሄር ታማኝ ሆነው ቢዘልቁና ለሉዓላዊነቱ በፍቅር ቢገዙ ኖሮ ጤና ማጣትንም ሆነ እርጅና የሚያስከትለውን ጉስቁልና እንዲሁም ሞትን ባላዩ ለኛም ባላስተላለፉት ነበር። መክብብ ምዕራፍ 12 ፍጹማን ባልሆኑ ሰዎች ላይ ከእርጅና ጋር ተያይዞ ስለሚመጣው “የጭንቀት ጊዜ” ቁልጭ አድርጎ ይገልጻል። (መክብብ 12:1-7) ሽበት ‘ከለውዝ ዛፍ’ አበባ ጋር ተመሳስሏል። እግሮች፣ እየጎበጡና እየተብረከረኩ ከመጡ ‘ብርቱ’ ሰዎች ጋር ተመሳስለዋል። የዓይን መዳከም፣ ብርሃን እናያለን ብለው ወደ መስኮት ሲመጡ ከጨለማ ሌላ ምንም ነገር ባላገኙ ወይዛዝርት መመሰሉ ትክክለኛ መግለጫ ነው። የረገፉ ጥርሶች ‘ጥቂት በመሆናቸው ምክንያት መፍጨት ባቆሙ’ ሴቶች ተመስለዋል። የሚብረከረኩ እግሮች፣ የደከሙ ዓይኖችና ጥርስ አልባ የሆኑ ድዶች አምላክ ለሰው ዘር የነበረው የመጀመሪያ ዓላማ ክፍል አይደሉም። ከዚህ በተጨማሪ ከአዳም የወረስነው ሞት ‘ከዲያብሎስ ሥራዎች’ አንዱ ሲሆን የእግዚአብሄር ልጅ በመስቀል ላይ በከፈለው ዋጋ አስወግዶታል ለዚህ ነው ሐዋርያው ዮሐንስ “የእግዚአብሔር ልጅ የተገለጠውም የዲያብሎስን ሥራ ያፈርስ ዘንድ ነው” ብሎ በድፍረት የጻፈው። 1 ዮሐ. 3:8::
መጽሐፍ ቅዱስ የሕክምና መጽሐፍ አይደለም፤ ደግሞም ሰዎች የሚያደርጉትን እያንዳንዱን ነገር የሚቆጣጠር መመሪያ አልያዘም። ያም ቢሆን እግዚአብሄር ጤንነትን ስለ መጠበቅ ያለውን አመለካከት የሚጠቁሙ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የሚገኙ ሐሳቦችን ያሳውቃል። መጽሐፍ ቅዱስ ለሰውነታችን የምናደርገው እንክብካቤ እግዚአብሄርን እንደሚያሳስበው የሚጠቁሙ በርካታ ሐሳቦች ይዟል። ለምሳሌ ያህል መጽሐፍ ቅዱስ ሆዳምነትንና ሰካራምነትን ጨምሮ ከልክ በላይ የሚደረጉ ጎጂ ነገሮችን ያወግዛል። (ምሳሌ 23:20) እግዚአብሄር ለጥንቶቹ እስራኤላውያን በሰጠው ሕግ ላይ በሽታዎች እንዳይስፋፉ ለመቆጣጠር ከተቻለም እንዳይከሰቱ ለመከላከል መደረግ ያለባቸው ነገሮች ተካትተዋል። በተጨማሪም ሕጉ በሰው ላይ ጉዳት የሚያደርሱ አደጋዎችን ለማስወገድ የሚረዱ የደህንነት መመሪያዎችን ይዟል። (ዘዳግም 22:8) ከዚህ በግልጽ ለማየት እንደሚቻለው መጽሐፍ ቅዱስ፣ ሰውነታችንን እንድንንከባከብና ጤንነታችንን ለመጠበቅ አስፈላጊውን ነገር እንድናደርግ ያበረታታል።
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ብዙ ተስፋዎች ለነፍስም ሆነ ሥጋ ፈውስ ማግኛ መንገድ ተስጥተዋል፤ ሆኖም በመጸሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጠቀሱትን ተስፋዎችና መመሪያዎችን አውቆ ከመጠቀም ይልቅ ባለማወቅ ብዙ ስዎች በአካልና በነፍስ በሽታ ይስቃያሉ። በአሁኑ ጊዜ ፈውስ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገለጸው በምን መንገድ ነው? ለሚለው መልሱ መጽሐፍ ቅዱስ በዚህ አስፈላጊ በሆነ ትምህርት ላይ በደፈናው አያልፈውም ይልቁንም እግዚአብሔር የፈውስን መንገዶች እንደተከናውኑ ለትምህርታችን ተጽፈው ይገኛሉ።
• እግዚአብሔር በሽታን እንደሚፈወስና ጤናን እንደሚያድስ (ዘዳግም 8፡4) ያመለክታል ይህም እውነት ለብዙዎች ያስፈልጋል።
• መጽሐፍ ቅዱስ ስለጤናማ ኒዩትሪሽን (ኦሪት ዘጽአት15፡16፤ ኦሪት ዘለዋውያን 11 ተጽፎ ይገኛል ጤናማ ያልሆኑ ምግቦች ለተለያዩ በሽታዎች ተመጋቢውን ያጋልጣሉ:: መጽሐፍ ቅዱስ ጤናማ አኗኗርን ማለትም ተከታታይ የስውነት እንቅስቃሴዎችንና ከተፈጥሮ ውጪ የሆኑ ጭናዎችን ማስወገድ (ኦሪት ዘለዋውያን 12-14) ተጽፎ ይገኛል ጫና የተለያዩ በሽታዎች መነሻ መሆኑን ያመለክታል እግዚአብሔር ደግሞ ለጤና ፈውስን በመድሐኒት አዘጋጅቷል (ያዕቆብ 5፡14)
ከሃጢያት የተነሳ የሚመጣውን በሽታ እግዚአብሔር በሽተኛውን ይቀርታ በመስጠትና በማንጻት ፈውስን ይስጣል (ኦሪት ዘሁልቁ 12፡13)
• እግዚአብሔር በእምነት በጽሎት በሽታን ይፈውሳል (ያዕቆብ 5፡15)
• እግዚአብሔር ፈውስን በተአምር (በእግዚአብሄር ምርጫ) ወይም በመድሕኒት ይፈውሳል የታመመው አማኝ እንዲፈወስ ምን ማድረግ አለበት? በሌላ ጊዜም ደግሞ ስዎች ታመው እንደሐዋሪያው ጳውሎስ 2 ቆሮ. 12፡7,10 ያልተፈውሱበት ጊዜ እንዳለ ማወቅ ይስፈልጋል አማኙ በአካል የታመመ እንደሆነ የበሽታው መነሻ ምን እንደሆነ ለይቶ ማወቅ ይኖርበታል፤ በሽታው መነሻው ከኒዩትሪሽን የተነሳ ከሆነ ኒዩትሪሽንን በማስተካከል እራስን መርዳት ነው። መታወስ ያለበት በሆስዔ 4፡6 ከውቀት ማጣት የተነሳ የሚመጣ ጉዳት እንዳለም ነው።
• በሽታው በሀጢያት የተነሳ ከመጣ (ያዕቆብ 5፡14,15) እንደተጠቀስው ፈውሱን መፈለግ ይኖርበታል ። የአማኙ መታመም ምናልባትም የእግዚአብሔር ፈቃድ ያለበት 2 ሳሙ. 4:4; እና 2 ቆሮ.12:7,10 ላይ እንደተጠቀስው አይነት ከሆነ ደግሞ ሌላ ገጽታ አለው።
• በጣም አስፈላጊ የሆነው የእምነት ጸሎት በሐዋሪያው ያዕቆብ የተጠቀስው የእምነት ጸሎት የተኮተኮተውና ጥንቃቄ የተደረገለት ትምህርቱ የሚያተኩረው በዮሐንስ ወንገል 16፡13 የተመስረተ የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያ ስለመሆን የተመለከተው ነው። የእምነት ጽሎት ያዕቆብ መንፈሳዊ መለየትንና መረዳትን በመለማመድ እምነት ጸሎት ውጤቱ ምንም ይሁን መጸለየና መቆምን ያመለክታል። ጸሎት እግዚአብሔር የሚፈውስበት መንገድ የቱንም ይምረጥ ታማኝነቱን ያረጋግጣል ስለሆነም የእምነት ጽሎት ጸላዮ የሚቀበለው እግዚአብሔር አማኙ የተያዘበትን በሽታ በመዝ 23፡4 ይቀበለዋል። የስውን ደካማነት የእግዚአብሔርን ጉልበት ይገልጣል (2 ቆሮ. 12፡7,10)። ኢየሱስ በሽተኞችን የፈወሰው በዘመናችን ፈውስ ከሚያከናውኑ ሰዎች ፍጹም በተለየ መንገድ ነበር። ለምሳሌ ያህል፣ ኢየሱስ እርዳታ ፈልገው ወደ እሱ የመጡትን ሕመምተኞች በሙሉ ፈውሷል። ከታመሙ ሰዎች መካከል የተወሰኑትን ፈውሶ የተቀሩትን እንዲሁ አልተዋቸውም። ከዚህም በተጨማሪ ሰዎችን የፈወሰው ሙሉ በሙሉ ከመሆኑም ሌላ ሁልጊዜ ማለት ይቻላል ሰዎቹ ከበሽታቸው የሚድኑት ወዲያውኑ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ “ኀይል ከእርሱ እየወጣ ሁሉንም ይፈውስ ስለ ነበር፣ ሰዎቹ ሁሉ እርሱን ለመንካት ይፈልጉ ነበር” በማለት ይናገራል ሉቃስ 6:19። ‘ኢየሱስ ሰዎችን የሚፈውሰው እምነታቸውን መሠረት አድርጎ ካልሆነ የፈወሳቸውን ሰዎች ብዙውን ጊዜ “እምነትህ አድኖሃል” ይላቸው የነበረው ለምንድን ነው?’ ተብሎ ቢጠየቅ (ሉቃስ 8:48፤ 17:19፤ 18:42) ኢየሱስ እንዲህ ብሎ ሲናገር እንደሚፈወሱ አምነው ወደ እሱ የመጡት ሰዎች እንደተፈወሱና ይህን ያላደረጉት ግን አጋጣሚውን ሳይጠቀሙበት እንደቀሩ መግለጹ ነበር። እምነት አያስፈልግም እያልኩ አይደለም:: ከበሽታቸው የዳኑት ሰዎችም ቢሆኑ የተፈወሱት በእምነታቸው ብቻ ሳይሆን በእግዚአብሄር ኃይል ነው። መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ኢየሱስ ሲናገር እንዲህ ይላል፦ “እግዚአብሔር . . . በመንፈስ ቅዱስና በኀይል ቀባው፤ እርሱም እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ስለ ነበረ በደረሰበት ሁሉ መልካም እያደረገ በዲያብሎስ ሥልጣን ሥር የነበሩትን ሁሉ ፈወሰ።” የሐዋርያት ሥራ 10:38።
"እግዚአብሔር ይፈውሳል ሐኪሙ ክፍያ ይጠይቃል"። (ቤንጃሚን ፍራንክሊን) ሁሉንም ዓይነት ሕመምና በመጨረሻም ሞትን ሊያስቀር የሚችል አንድም የሰው ልጅ ሕክምና የለም። ይህ የሆነበት ምክንያት እነዚህ ከመጀመሪያው አባታችን ከአዳም የተወረሱ በመሆናቸው ነው። (ኢዮብ 14:4፤ መዝሙር 51:5፤ ሮሜ 5:12) ብዙ የሕክምና ዓይነቶች ጠቃሚ ሆነው ሊገኙ ይችላሉ። ይሁንና ሕይወትን ከማራዘምና ለተወሰነ ጊዜ ብቻ ደህና ኑሮ እንዲኖር በማድረግ ለጊዜው እንደ ማስታገሻ ከማገልገል አያልፉም።
ክፍል 4
ክፍል 4
በዘመናችን ‘ተአምራዊ ፈውስ’ የሚከናወነው በአምላክ ኃይል ነው?
ሁላችንም ስንታመም ከሥቃያችን እፎይ የምንልበትን ጊዜ እንናፍቃለን። ኢየሱስ ክርስቶስ ሁሉንም ዓይነት በሽታዎች በመፈወስ ለብዙ ሕሙማን እፎይታ አስገኝቶላቸው እንደነበር የሚገልጹ በርካታ ታሪኮችን ከመጽሐፍ ቅዱስ ላይ አንብበህ ይሆናል። እነዚህ ሰዎች ሊፈወሱ የቻሉት እንዴት ነበር? መጽሐፍ ቅዱስ በአምላክ ኃይል እንደሆነ ይገልጽልናል። (ሉቃስ 9:42, 43፤ የሐዋርያት ሥራ 19:11, 12) ስለሆነም ሰዎቹን እንዲፈወሱ ያስቻላቸው እምነታቸው ብቻ ሳይሆን የአምላክ ቅዱስ መንፈስ ነበር። (የሐዋርያት ሥራ 28:7-9) ኢየሱስ የታመሙ ሰዎች ከሕመማቸው ለመፈወስ በእርሱ ማመናቸውን እንዲናገሩ የማይጠብቅባቸው ለዚህ ነበር።
‘ተአምራዊ ፈውስ ጊዜ ያለፈበት ነገር ነው? ወይስ ኢየሱስ ያከናወናቸው ዓይነት ፈውሶች ወደፊትም ይኖራሉ? በሕመም የሚሰቃዩ ወይም ሊድን በማይችል በሽታ የተያዙ ሰዎች ምን ተስፋ አላቸው?’ ብለህ ትጠይቅ ይሆናል።
አምላክ ጽድቅ በሚሰፍንበት አዲስ ዓለም ውስጥ ኢየሱስ ምድር ሳለ ያከናወናቸውን ዓይነት ተአምራዊ ፈውሶች እንደገና እንደሚፈጽም መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል። በአካባቢህ የሚኖሩ ክርስቲያኖች አምላክ ሁሉንም ዓይነት በሽታዎች አልፎ ተርፎም ሞትን በማስቀረት ማንኛውም የእምነት ፈዋሽ ማከናወን የማይችለውን ፈውስ የሚፈጽመው እንዴትና መቼ እንደሆነ እንድታውቅ ሊረዱህ ፈቃደኞች ናቸው። አዎን፣ አምላክ “ሞትንም ለዘላለም ሽሮአል።”ኢሳይያስ 25:8
በአንዳንድ አገሮች፣ ሃይማኖተኛ የሆኑ ሰዎች “በማይድን” በሽታ የተያዙ ብዙዎች ፈውስ እንዳገኙባቸው ወደሚታሰቡ ቅዱስ ስፍራዎች ሲጓዙ ማየት የተለመደ ነው። በሌሎች አገሮችም፣ መለኮታዊ ኃይል በመጠቀም በሽተኞችን እንደሚፈውሱ የሚናገሩ ሰዎች አሉ። በሌሎች አካባቢዎች ደግሞ በአንዳንድ መንፈሳዊ ፕሮግራሞች ላይ፣ የታመሙ ሰዎች ፈውስ እንዳገኙ በመናገር ከተሽከርካሪ ወንበራቸው ላይ ተነስተው ሲዘሉ አሊያም ምርኩዛቸውን ሲወረውሩ ይታያሉ።
እንዲህ ያሉትን ፈውሶች የሚያከናውኑት ሰዎች በአብዛኛው ሃይማኖታቸው የተለያየ ነው፤ ብዙውን ጊዜም አንዳቸው ሌላውን ከሃዲ፣ ሐሰተኛና አረማዊ እንደሆነ አድርገው ይመለከታሉ። በመሆኑም ‘አምላክ እርስ በርስ በሚቃረኑ ሃይማኖታዊ ድርጅቶች ተጠቅሞ ተአምር ይሠራል?’ የሚል ጥያቄ ይነሳ ይሆናል። ደግሞም መጽሐፍ ቅዱስ፣ “እግዚአብሔር የሰላም አምላክ እንጂ የሁከት አምላክ አይደለም” ይላል። (1 ቆሮንቶስ 14:33) ታዲያ እንዲህ ያሉት ‘ተአምራዊ ፈውሶች’ የሚከናወኑት በእርግጥ በአምላክ ኃይል ነው? ፈውስ የሚያከናውኑ አንዳንድ ሰዎች ይህን የሚያደርጉት በኢየሱስ ኃይል እንደሆነ ይናገራሉ። እስቲ ኢየሱስ ሰዎችን እንዴት እንደፈወሰ እንመልከት።
ኢየሱስ ሰዎችን የፈወሰው እንዴት ነበር?
ኢየሱስ በሽተኞችን የፈወሰው በዘመናችን ፈውስ ከሚያከናውኑ ሰዎች ፍጹም በተለየ መንገድ ነበር። ለምሳሌ ያህል፣ ኢየሱስ እርዳታ ፈልገው ወደ እሱ የመጡትን ሕመምተኞች በሙሉ ፈውሷል። ከታመሙ ሰዎች መካከል የተወሰኑትን ፈውሶ የተቀሩትን እንዲሁ አልተዋቸውም። ከዚህም በተጨማሪ ሰዎችን የፈወሰው ሙሉ በሙሉ ከመሆኑም ሌላ ሁልጊዜ ማለት ይቻላል ሰዎቹ ከበሽታቸው የሚድኑት ወዲያውኑ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ “ኀይል ከእርሱ እየወጣ ሁሉንም ይፈውስ ስለ ነበር፣ ሰዎቹ ሁሉ እርሱን ለመንካት ይፈልጉ ነበር” በማለት ይናገራል። ሉቃስ 6:19
አንድ የታመመ ሰው ካልተፈወሰ ይህ የሆነው ግለሰቡ እምነት ስለሌለው እንደሆነ በመናገር ሰበብ ከሚደረድሩት በዘመናችን የሚገኙ ፈዋሾች በተቃራኒ ኢየሱስ በእሱ ላይ እምነት የሌላቸውን አንዳንድ ሰዎችን እንኳ ፈውሷል። ለአብነት ያህል፣ ማየት የተሳነው አንድ ሰው እንዲፈውሰው ባይጠይቀውም ኢየሱስ ግን ፈውሶት ነበር። በኋላም ኢየሱስ “በሰው ልጅ ታምናለህን?” ሲል ጠየቀው። ሰውየውም መልሶ “ጌታዬ፤ አምንበት ዘንድ እርሱ ማን ነው?” አለው። በዚህ ጊዜ ኢየሱስ “ከአንተ ጋር የሚነጋገረው እርሱ ነው” በማለት መለሰለት። ዮሐንስ 9:1-7, 35-38
‘ኢየሱስ ሰዎችን የሚፈውሰው እምነታቸውን መሠረት አድርጎ ካልሆነ የፈወሳቸውን ሰዎች ብዙውን ጊዜ “እምነትህ አድኖሃል” ይላቸው የነበረው ለምንድን ነው?’ ብለህ ትጠይቅ ይሆናል። (ሉቃስ 8:48፤ 17:19፤ 18:42) ኢየሱስ እንዲህ ብሎ ሲናገር እንደሚፈወሱ አምነው ወደ እሱ የመጡት ሰዎች እንደተፈወሱና ይህን ያላደረጉት ግን አጋጣሚውን ሳይጠቀሙበት እንደቀሩ መግለጹ ነበር። ከበሽታቸው የዳኑት ሰዎችም ቢሆኑ የተፈወሱት በእምነታቸው ሳይሆን በአምላክ ኃይል ነው። መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ኢየሱስ ሲናገር እንዲህ ይላል፦ “እግዚአብሔር . . . በመንፈስ ቅዱስና በኀይል ቀባው፤ እርሱም እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ስለ ነበረ በደረሰበት ሁሉ መልካም እያደረገ በዲያብሎስ ሥልጣን ሥር የነበሩትን ሁሉ ፈወሰ።ሐዋርያት ሥራ 10:38
በዘመናችን፣ ያለ ገንዘብ ‘ፈውስ’ ማግኘት የሚቻል አይመስልም። ፈውስ የሚያከናውኑ ሰዎች ገንዘብ በመሰብሰብ ረገድ የተዋጣላቸው ናቸው። ከእነዚህ ፈዋሾች መካከል አንዱ በዓለም አቀፍ ደረጃ ባከናወነው ሥራ በአንድ ዓመት ውስጥ ከ850 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ እንዳገኘ ተገልጿል። አብያተ ክርስቲያናትም ፈውስ እንደሚያገኙ ተስፋ በማድረግ ቅዱስ ወደሆኑ ስፍራዎች ከሚመጡ ሃይማኖተኛ ሰዎች ከፍተኛ ትርፍ ያጋብሳሉ። በአንጻሩ ግን ኢየሱስ ከፈወሳቸው ሰዎች ፈጽሞ ገንዘብ አልጠየቀም። እንዲያውም በአንድ ወቅት የፈወሳቸውን ሰዎች መግቧቸው ነበር። (ማቴዎስ 15:30-38) ደቀ መዛሙርቱን ለስብከት ሲልካቸው እንዲህ ብሏቸው ነበር፦ “በሽተኞችን ፈውሱ፤ ሙታንን አስነሡ፤ ለምጻሞችን አንጹ፤ አጋንንትን አስወጡ፤ በነጻ የተቀበላችሁትንም በነጻ ስጡ።” (ማቴዎስ 10:8) ታዲያ በዘመናችን ፈውስ የሚያከናውኑ ሰዎች የሚያደርጉት ነገር ከኢየሱስ የተለየ የሆነው ለምንድን ነው?
“ፈውስ” የሚያከናውኑት በማን ኃይል ነው?
ባለፉት ዓመታት፣ በሕክምና መስክ የተሰማሩ አንዳንድ ሰዎች በአምላክ ኃይል ፈውስ እንዳከናወኑ የሚናገሩ ሰዎች አደረግን የሚሉት ነገር እውነት መሆኑን ለማረጋገጥ ሞክረዋል። ታዲያ ምን ውጤት አገኙ? በለንደን የሚታተም ዴይሊ ቴሌግራፍ የተባለ ጋዜጣ በዚህ ጉዳይ ላይ ለ20 ዓመታት ጥናት ያካሄዱ በእንግሊዝ የሚገኙ አንድ ሐኪም የሰጡትን ሐሳብ ጠቅሶ እንደዘገበው ከሆነ “ተአምራዊ ፈውስ እናከናውናለን የሚሉ ሰዎች የሚናገሩት ነገር እውነት መሆኑን የሚያረጋግጥ በሕክምናው መስክ የተገኘ አንድም ማስረጃ የለም።” ያም ሆኖ በርካታ ሰዎች እንደ ቅዱስ ተደርገው የሚታዩ ነገሮችን በመጠቀም፣ ቅዱስ ወደሆኑ ቦታዎች በመሄድ ወይም የአምላክ ኃይል እንዳላቸው በሚናገሩ ሰዎች አማካኝነት እንደተፈወሱ በቅንነት ያምናሉ። ታዲያ እነዚህ ሰዎች ተታልለው ይሆን?
ኢየሱስ ዝነኛ በሆነው የተራራ ስብከቱ ላይ፣ አስመሳይ የሆኑ የሃይማኖት ሰዎች “ጌታ ሆይ፤ ጌታ ሆይ፤ በስምህ . . . ብዙ ታምራት አላደረግንምን?” እንደሚሉት ተናግሯል። እሱ ግን መልሶ “ከቶ አላወቅኋችሁም፤ እናንት ክፉዎች፤ ከእኔ ራቁ!” ይላቸዋል። (ማቴዎስ 7:22, 23) ሐዋርያው ጳውሎስ ተአምር እንደሚፈጽሙ የሚናገሩ ሰዎች ኃይል የሚያገኙት ከማን እንደሆነ ሲገልጽ እንዲህ ብሏል፦ “የዐመፀኛው አመጣጥ በሰይጣን አሠራር ላይ የተመሠረተ ሲሆን፣ ይህም በሐሰተኛ ታምራት በምልክቶችና በድንቅ ነገሮች ሁሉ ይሆናል፤ እንዲሁም . . . በሚያታልል በተለያየ የክፋት ሥራ ይመጣል።”2 ተሰሎንቄ 2:9, 10
በተጨማሪም እንደ ቅዱስ ተደርገው በሚታዩ ነገሮች፣ በጣዖታትና በምስሎች አማካኝነት የሚከናወኑት “ፈውሶች” በአምላክ ዘንድ ተቀባይነት የላቸውም። እንደዚህ የሚባለው ለምንድን ነው? ምክንያቱም የአምላክ ቃል “ከጣዖት አምልኮ ሽሹ” እንዲሁም “ራሳችሁን ከጣዖቶች ጠብቁ” የሚል ግልጽ መመሪያ ይሰጣል። (1 ቆሮንቶስ 10:14፤ 1 ዮሐንስ 5:21) እንዲህ ያሉት “ፈውሶች” ዲያብሎስ ሰዎችን ከእውነተኛው አምልኮ ለማራቅ ከሚጠቀምባቸው መሠሪ ዘዴዎች መካከል የሚመደቡ ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ “ሰይጣን ራሱ የብርሃን መልአክ ለመምሰል ራሱን ይለዋውጣል” ይላል። 2 ቆሮንቶስ 11:14
ኢየሱስና ሐዋርያቱ ሰዎችን የፈወሱት ለምን ነበር?
በክርስቲያን ግሪክኛ ቅዱሳን መጻሕፍት ውስጥ ተመዝግበው የሚገኙ እውነተኛ ተአምራዊ ፈውሶች ኢየሱስና ሐዋርያቱ የአምላክ መልእክተኞች እንደሆኑ በግልጽ የሚያሳዩ ናቸው። (ዮሐንስ 3:2፤ ዕብራውያን 2:3, 4) ኢየሱስ ያከናወነው ተአምራዊ ፈውስ ሲሰብክ የነበረውን መልእክት የሚደግፍ ነበር፤ “በምኩራቦቻቸው እያስተማረ፣ የእግዚአብሔርን መንግሥት የምሥራች ቃል እየሰበከ፣ በሕዝቡ መካከል ማንኛውንም ደዌና ሕመም እየፈወሰ በመላው ገሊላ ይዘዋወር ነበር።” (ማቴዎስ 4:23) ኢየሱስ የታመሙትን መፈወስን ብቻ ሳይሆን በርካታ ሰዎችን መመገብን፣ የተፈጥሮ ኃይላትን መቆጣጠርንና ሙታንን ማስነሳትን ጨምሮ ያከናወናቸው ሌሎች ታላላቅ ነገሮች ታዛዥ ለሆኑ የሰው ልጆች በመንግሥቱ አገዛዝ ሥር ምን እንደሚያደርግላቸው የሚያሳዩ ናቸው። በእርግጥም ይህ የምሥራች ነው!
ኢየሱስ ያከናወናቸው ተአምራዊ ፈውሶች ለእኛ ትልቅ ትርጉም አላቸው። ኢየሱስ ስለ አምላክ መንግሥት ላስተማራቸው ትምህርቶች ትኩረት የምንሰጥና በትምህርቶቹ ላይ እምነት የምናሳድር ከሆነ ‘በዚያ ተቀምጦ “ታምሜአለሁ” የሚል አይኖርም’ የሚለው በመንፈስ መሪነት የተነገረ ተስፋ በመንፈሳዊም ሆነ በአካላዊ ፍጻሜውን የሚያገኝበትን ጊዜ በጉጉት መጠባበቅ እንችላለን። ኢሳይያስ 33:24፤ 35:5, 6፤ ራእይ 21:4
0 comments:
Post a Comment