ከመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ለመጠቀም የሚረዱ ሰባት ዘዴዎች
“መጽሐፍ ቅዱስ በታሪክ
ውስጥ ከፍተኛ ሽያጭ በማግኘት ረገድ ተወዳዳሪ የሌለው ከመሆኑም በላይ ከዓመት እስከ ዓመት በብዛት በመሸጥ ረገድ ቀዳሚውን ስፍራ
የያዘ መጽሐፍ ነው።”
ብዙዎች መጽሐፍ ቅዱስ በእጃቸው
ቢኖርም መጽሐፉን በማንበብ እምብዛም ጥቅም የማያገኙ መሆናቸው ያስገርማል። ሌሎች ሰዎች ግን በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚያነቡት ነገር
ከፍተኛ ጥቅም እንዳለው ይሰማቸዋል። ለምሳሌ ያህል፣ ናንሲ የተባለች ሴት እንደሚከተለው ትላለች፦ “በየቀኑ ማለዳ ላይ መጽሐፍ ቅዱስን
ማንበብና ባነበብኩት ላይ ማሰላሰል ከጀመርኩ ወዲህ በዕለቱ የሚያጋጥመኝን ማንኛውንም ችግር ለመጋፈጥ ዝግጁ እንደሆንኩ ይሰማኛል።
ይህ ልማዴ ያለብኝን የመንፈስ ጭንቀት ለማስታገስ ባለፉት 35 ዓመታት ውስጥ ከሞከርኩት ከማናቸውም ነገር የበለጠ ረድቶኛል።”
መጽሐፍ ቅዱስን አንብበህ
የማታውቅ ቢሆንም እንኳ አንዳንድ ሰዎች ይህን መጽሐፍ ማንበባቸው እንደጠቀማቸው ሲናገሩ መስማትህ የማወቅ ፍላጎትህን ይቀሰቅሰዋል?
መጽሐፍ ቅዱስን የማንበብ ልማድ ያለህ ሰው ከሆንክ ደግሞ ከንባብህ የበለጠ ጥቅም ማግኘት ብትችል ደስ ይልሃል? ከሆነ በዚህ ርዕስ
ውስጥ የተገለጹትን ሰባት ዘዴዎች ተግባራዊ ለማድረግ ሞክር።
ዘዴ 1 ትክክለኛ ዝንባሌ ይኑርህ
▪ መጽሐፍ ቅዱስን እንደ
አንድ ጥሩ ሥነ ጽሑፍ በመቁጠር ወይም የማንበብ ግዴታ እንዳለብህ ተሰምቶህ አለዚያም በዚህ በመከራ በተሞላ ዓለም ውስጥ መመሪያ
ለማግኘት በማሰብ ልታነበው ትችል ይሆናል። መጽሐፍ ቅዱስን በማንበብ የበለጠ ጥቅም የምታገኘው ግን ዓላማህ ስለ አምላክ እውነቱን
ማወቅ ሲሆን ነው። በተጨማሪም መጽሐፍ ቅዱስን የምታነበው መልእክቱ ሕይወትህን እንዲለውጠው በማሰብ ከሆነ ብዙ በረከት ታጭዳለህ።
መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሄርን
ቃል በትክክለኛ ዝንባሌ ተነሳስቶ የማንበብን አስፈላጊነት ያጎላል፤ ቃሉን ከመስታወት ጋር በማነጻጸር እንዲህ ይላል፦ “ማንም ቃሉን
የሚሰማ እንጂ የማያደርገው ከሆነ ይህ ሰው የተፈጥሮ ፊቱን በመስተዋት እያየ ካለ ሰው ጋር ይመሳሰላል። ይህ ሰው ራሱን ካየ በኋላ
ይሄዳል፤ ወዲያውም ምን እንደሚመስል ይረሳል። ሆኖም ነፃ የሚያወጣውን ፍጹም ሕግ በትኩረት የሚመለከትና በዚያም የሚጸና ሰው ሰምቶ
የሚረሳ ሳይሆን በሥራ ላይ የሚያውል ሰው ስለሆነ ይህን በማድረጉ ደስተኛ ይሆናል።” ያዕቆብ 1:23-25
በዚህ ምሳሌ ላይ የተጠቀሰው
ሰው ፊቱን በመስታወት ቢያይም በመልኩ ላይ ያለውን እንከን ሳያስተካክል ቀርቷል። ይህ ሰው ፊቱን የተመለከተው በችኮላ ሊሆን ይችላል፤
ወይም አስፈላጊውን ማስተካከያ ለማድረግ ፍላጎት አልነበረውም። በተመሳሳይ እኛም መጽሐፍ ቅዱስን የምናነበው እንደነገሩ ከሆነ ወይም
የምናነበውን በሥራ ላይ ካላዋልነው እምብዛም አይጠቅመንም። በተቃራኒው ቃሉን ‘በሥራ ላይ ለማዋል’ ብለን መጽሐፍ ቅዱስን የምንመረምር
ይኸውም የአምላክ ቃል አስተሳሰባችንን እንዲቀርጸውና በድርጊታችን ላይ ለውጥ ለማድረግ እንዲያነሳሳን የምንፈቅድ ከሆነ እውነተኛ
ደስታ ልናገኝ እንችላለን።
ዘዴ 2 እምነት የሚጣልበት የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም ምረጥ
በቋንቋህ የተዘጋጁ ብዙ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞች ይኖሩ ይሆናል። ማንኛውም
የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም ሊጠቅምህ ቢችልም አንዳንዶቹ ትርጉሞች በአሁኑ ጊዜ የማይዘወተሩ የድሮ ቃላትን ወይም የምሑራንን ቋንቋ ስለሚጠቀሙ
‘ተራው ሰው’ ለመረዳት አስቸጋሪ ሊሆንበት ይችላል። (የሐዋርያት ሥራ 4:13) የመጽሐፍ ቅዱስን መልእክት በትክክል የሚያስቀምጥ፣
ለመረዳት ቀላል የሆነና የማንበብ ፍላጎትን የሚቀሰቅስ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም ምረጥ።
ዘዴ 3 ጸልይ
“ከሕግህ ድንቅ ነገርን
እንዳይ፣ ዐይኖቼን ክፈት” ብሎ እንደጸለየው መዝሙራዊ አንተም የመጽሐፍ ቅዱስን ባለቤት እርዳታ የምትጠይቅ ከሆነ ስለ መጽሐፉ የበለጠ
ማስተዋል ማግኘት ትችላለህ። (መዝሙር 119:18) መጽሐፍ ቅዱስን ባነበብክ ቁጥር ቃሉን መረዳት እንድትችል እግዚአብሄር እንዲረዳህ
በጸሎት ጠይቀው። በተጨማሪም መጽሐፍ ቅዱስን ስለሰጠህ እግዚአብሄርን ልታመሰግነው ትችላለህ፤ ምክንያቱም ይህ መጽሐፍ ባይኖር ኖሮ
ስለ እሱ አናውቅም ነበር። መዝሙር 119:62
ዘዴ 4 በየቀኑ አንብብ
ብዙ ሰዎች ወደ እግዚአብሄር ቃል ፊታቸውን የሚያዞሩት ሲጨነቁ ብቻ ነው። ይሁን
እንጂ መጽሐፍ ቅዱስ በየዕለቱ እንድናነበው ሲያበረታታ እንዲህ ይላል፦ “ይህ የሕግ መጽሐፍ ከአፍህ አይለይ፤ በውስጡ የተጻፈውን
ሁሉ በጥንቃቄ እንድትፈጽመውም ቀንም ሆነ ሌት ከሐሳብህ አትለየው፤ ይህን ካደረግህ ያሰብኸው ይቃናል፤ ይሳካልም።” ኢያሱ 1:8
መጽሐፍ ቅዱስን አዘውትሮ
ማንበብ ያለውን ጠቀሜታ ለማስረዳት ልቡን የታመመ ሰውን እንደ ምሳሌ መውሰድ ይቻላል፤ ግለሰቡ ከወትሮው የበለጠ ለጤናው ተስማሚ
የሆኑ ምግቦችን ለመመገብ ወሰነ እንበል። ሰውየው እንዲህ ዓይነቱን አመጋገብ የሚከተለው ደረቱ አካባቢ ኃይለኛ ሕመም ሲሰማው ብቻ
ቢሆን ይጠቅመዋል? በጭራሽ። የበለጠ ጥቅም ለማግኘት ይህን ጤናማ የአመጋገብ ሥርዓት ያለማቋረጥ ሊከተለው ይገባል። በተመሳሳይም
መጽሐፍ ቅዱስን በየቀኑ ማንበብ ‘ያሰብኸው እንዲቃና’ ይረዳሃል።
ዘዴ 5 የተለያዩ መንገዶችን ተጠቀም
መጽሐፍ ቅዱስን ከዘፍጥረት
እስከ ራእይ ማንበብ ጥሩ ቢሆንም ሌሎች መንገዶችንም መጠቀምህ ንባብህ አስደሳች እንዲሆንልህ ሊረዳህ ይችላል። ከዚህ በታች አንዳንድ
ሐሳቦች ቀርበዋል።
በአንድ ግለሰብ ላይ ትኩረት
አድርገህ አንብብ። በአንድ የእግዚአብሄር አገልጋይ ላይ ትኩረት በማድረግ ስለ እሱ የሚገልጹትን ምዕራፎች ወይም የመጽሐፍ ቅዱስ
መጻሕፍት በሙሉ አንብባቸው፤ ለምሳሌ፦
• ዮሴፍ፦ ዘፍጥረት
37 እስከ 50
• ሩት፦ ሩት 1 እስከ
3
• ኢየሱስ፦ ማቴዎስ 1
እስከ 28፤ ማርቆስ 1 እስከ 16፤ ሉቃስ 1 እስከ 24፤ ዮሐንስ 1 እስከ 21።*
በአንድ ርዕሰ ጉዳይ ላይ
ትኩረት አድርገህ አንብብ። ከርዕሰ ጉዳዩ ጋር ግንኙነት ያላቸውን ጥቅሶች አንብባቸው። ለምሳሌ ያህል፣ ስለ ጸሎት ምርምር ማድረግ
ትችላለህ፤ ከዚያም መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ጸሎት የሚሰጠውን ምክርና በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከተመዘገቡት በርካታ ጸሎቶች መካከል አንዳንዶቹን
አንብብ።*
ጮክ ብለህ አንብብ። መጽሐፍ ቅዱስን ጮክ ብለህ በማንበብ በእጅጉ ልትጠቀም ትችላለህ።
(ራእይ 1:3) እንዲያውም በቤተሰብ ይህን ዘዴ መጠቀም ትችላላችሁ፤ አንቀጾቹን በመከፋፈል ወይም የተለያዩ የቤተሰብ አባላት በታሪኩ
ውስጥ የተጠቀሱትን ሰዎች ወክለው እንዲያነቡ በመመደብ መጽሐፍ ቅዱስን ጮክ ብላችሁ ልታነቡ ትችላላችሁ። አንዳንዶች በድምፅ የተቀረጸ
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ማዳመጥ ያስደስታቸዋል። አንዲት ሴት እንዲህ ብላለች፦ “የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ለመጀመር በጣም ከብዶኝ ስለነበር
በድምፅ የተቀረጸውን ማዳመጥ ጀመርኩ። አሁን መጽሐፍ ቅዱስ ከአንድ ጥሩ ልብ ወለድ የበለጠ ስሜት የሚመስጥ መጽሐፍ መሆኑን ተገንዝቤያለሁ።”
ዘዴ 6 አሰላስል
ያለንበት ዘመን ወከባ የበዛበትና ትኩረትን የሚከፋፍሉ ነገሮች የሞሉበት በመሆኑ
ለማሰላሰል የሚያስችል ጊዜ ማግኘት አስቸጋሪ ነው። ይሁን እንጂ የተመገብነው ነገር ጥቅም እንዲሰጠን ከሰውነታችን ጋር መዋሐድ እንዳለበት
ሁሉ ከመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ጥቅም ለማግኘትም በምናነበው ነገር ላይ ማሰላሰል አለብን። ይህን የምናደርገው ያነበብነውን ነገር በአእምሯችን
በመከለስና ራሳችንን እንደሚከተሉት ያሉ ጥያቄዎች በመጠየቅ ነው፦ ‘ያነበብኩት ነገር ስለ ይሖዋ አምላክ ምን ያስተምረኛል? በእኔ
ሕይወት ውስጥ የሚሠራው እንዴት ነው? ሌሎችን ለመርዳት ልጠቀምበት የምችለው እንዴት ነው?’
እንዲህ እያሉ ማሰብ የመጽሐፍ
ቅዱስ መልእክት ልባችንን እንዲነካው የሚረዳን ከመሆኑም ሌላ የእግዚአብሄርን ቃል በማንበብ የምናገኘውን ደስታ ከፍ ለማድረግ ያስችላል።
መዝሙር 119:97 “አቤቱ፤ ሕግህን ምንኛ ወደድሁ! ቀኑን ሙሉ አሰላስለዋለሁ” ይላል። መዝሙራዊው በቅዱሳን መጻሕፍት ላይ ቀኑን
ሙሉ ማሰላሰሉ ለተማረው ነገር ጥልቅ ፍቅር እንዲያዳብር ረድቶታል።
ዘዴ 7 መጽሐፍ ቅዱስን ለመረዳት እርዳታ ጠይቅ
እግዚአብሄር ቃሉን ያለ ማንም እርዳታ ሙሉ በሙሉ እንድንረዳ አይጠብቅብንም።
ራሱ መጽሐፍ ቅዱስ “ለመረዳት የሚከብዱ አንዳንድ ነገሮች” እንደያዘ ይገልጻል። (2 ጴጥሮስ 3:16) የሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ አንድ
ኢትዮጵያዊ ባለሥልጣን ያነበው የነበረውን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ለመረዳት ተቸግሮ እንደነበረ ይገልጻል። እግዚአብሄር ይህን ሰው
ለመርዳት ከአገልጋዮቹ አንዱን ፊሊጶስን ላከለት፤ በውጤቱም ኢትዮጵያዊው
ሰው “ደስ ብሎት ጉዞውን [ቀጥሏል]።”—የሐዋርያት ሥራ 8:26-39.
በዶ/ር አመለወርቅ ከተጻፈው ‘የቅዱስ ያዕቆብ የመልዕክቱ ሐተታዊ መግለጫ’ ከተባለው መጽሐፍ የተወስደ ሐተታዊ መግለጫ
የያዕቆብ መልክዕክት ምዕራፍ 1:17-18 ሐተታ
ጥቅስ 17 በጎ ስጦታ ሁሉ ፍጹምም በረከት ሁሉ ከላይ ናቸው፥ መለወጥም በርሱ ዘንድ ከሌለ በመዞርም የተደረገ ጥላ በእርሱ ዘንድ ከሌለ ከብርሃናት አባት ይወርዳሉ።
በጎ ስጦታና ፍጹም በረከት] ሁለቱ ስሞች
በግሪክ የተለያዩ
ናቸው የመጀመሪያው
የሚገልጸው በግልጽ
ሲስጥ የማይታይ
ስጦታን ሁለተኛው
ስጦታ ደግሞ
ላንድ ስው
ስጦታው ለማግኘት
የማይገባው ሆኖ
ሳለ የሚስጠውን
ስጦታ ነው።
ያንዱ ስጦታ
ወደ ሌላው
የመልካምነቱ መፍስስ
ስጦታውን ፍጹም
ያደርገዋል። ይህ “ፍጹም
በረከት“ ከጊዜያዊ
በረከቶች ያለፈ
በረከት ነው።
1 ቆሮ. 15፡33፤ ቲቶ
1፡12፤
እብ. 12፡13
ራዕ. 19፡12
እነዚህ ሁሉ
የሚያስታውሱት የተራራውን
ስብከት በማቴ.
7፡11 አብሮም
በሉቃ. 11፡13
የተስጠውን ተስፋ
ነው።
ከላይ ከስማይ] ፍጹም በረከት
የሚመጣው ወይም
የሚገኘው አንድ
ስው በመንፈስ
ከምድር ሳይሆን
ከስማይ የተወለደ
እንደሆነ ነው
(ዮሐ. 3፡3)
ከላይ ያለሆነው
ጥብብ ያዕ.
3፡15 ሲያመለክት
ከስማይ የሆነቸውን
ጥብብ ደግሞ
በያዕ 3፡17
ተመልክቷል። የቃሉ
ጎልህነት በመልዕክቱ
ወስጥ ያለው
ሃሳብ ከዮሐንስ
ወንጌል (ዮሐ. 3፡7፤ ዮሐ.
3፡31፤
ዮሐ. 19፡11)
ጋር ያይዘዋል።
ከብርሃናት አባት] ጸሐፈው የብዙ
ቁጥር የተጠቀመው
“ብርሃን“ ብዙ
አይነት አለው
የሚለውን ሃሳብ
ለመግለጽ ነው።
ይህም በተፈጥሮ
“ታላቅ ብርሃን“
ተብሎ በመዝ.
135፡7) የተመለከተውን አይነት ሲሆን እውቀት
የመንፈስ ቅዱስ
በርከት ከእግዚአብሄር የሚፈስውን “ብርሃን“ የሆነውን
ጨለማ የሌለበትን
በ1 ዮሐ.
1፡5 የተመለከተውን አይነት ነው። ይህ ተቀባይነት
ያለው እውነት
መለኮታዊ ተፈጥሮ
በተመለከተ ለሁለቱ
የቤተክርስቲያን የግዝረት
ታላቅ አስተማሪዎች
ቅዱስ ጳውሎስ
የአሕዛብ ወይም
የአረማውያን ሐዋሪያ
የእግዚአብሄርን ልጆች
ሲገልጻቸው “የብርሃን
ልጆች“ ሲል
በዔፊ. 5፡8
ጽፎአል። ቅዱስ
ጳውሎስ “ብርሃንን“
“ፍጹምንትን“ በተመለከተ
ሃሳቡን የወስደው
የእግዚአብሄርን የጥበብ
ስጦታውን በከፍተኛ
ደርጃ (በዘጽ.
28፡30፤
ዘለዋ. 8፡8፤ ዘዳግ.
33፡8፤
መዝ. 48፡3)
ከተመለከተው ነው።
በእርሱ ዘንድ መለዋወጥ] በቅድሚያ አባባሉ
የሥነ-ፍጥረት
አባባል ነው።
የሚያመለከተው የከዋክብትን
የሥፍራን መለዋወጥ
ወይም መቀያየር
ነው። “ብርሃን“
የሚለው ቃል
የሚያሳየው በቅድሚያ
በስማያት ያሉትን
የከዋክብት አካላት
ለአለም እንደ
ብርሃን ስጪዎች
አድርጎ ነው።
ከዚህም በማለፍ
እግዚአብሄር የጸሐይ
የጨረቃ የከዋክብት
ፈጣሪ መሆኑን
ጸሐፊው ያመለክታል።
ቅዱስ ያዕቆብ
ለማለት የፈለገው
እነዚህ ለአለም
ብርሃን ስጪ
የሆኑት የከዋክብት
አካላት ይለወጣሉ
የነርሱ ፈጣሪ
እግዚአብሄር አይለወጥም
ነው። መለዋወጥ
የእግዚአብሄር ባህሪ
አይደለም ቃሉም
የሚለው የእግዚአብሄር ተፈጥሮ ፈቃዱም እንደማይለዋወጥ ነው (ዘለዋ. 19፡2)
ይህ ማለት
እዚያው የተቀመጠ
የማይንቀሳቀስ ማለት
አይደለም። ጸሐፊው
በዚህ ጥቅስ
ውስጥ ያስቀመጣቸው
ንጽጽሮች የእግዚአብሄርን የማይለወጥ ባህሪ እንዳለው
ለአንባቢው ለማሳየት
ነው። እግዚአብሄር በድርጊት
የመግለጽ የማስብ
የመፍጠርና የመወስን
ችሎታ አለው፦
እግዚአብሄር የማይለወጥ
ስለሆነ ክርስቲያኖች
በፍቅሩና በሃይሉ
መመካት አለባቸው።
እግዚአብሄር እራሱ
ብርሃን ስለሆነ
ደግሞ የክርስቲያኑ
የመንፈሳዊ ሕይወቱ
እንዲያበራ የሚያደርገው
የበረከቱ ምንጭም
እንደሆም ያስረግጣል።
ከመዞር የተነሳ የሚያርፍ ጥላም የለም] ከመዞር ጥላ
ይገኛል። የመጨረሻው
ቃል አባባሉ
የተገኘውና በሥራ
ላይ የዋለው
ከኢዮብ 38፡33
“የስማያትን ሥርዓት
ታውቃለህ?ይህንን
በምድር ላይ
እንዲስለጥን ማድረግ
ትችላህ?” ዘዳግ.
33፡14 “ጸሐይ
በምታገኘው ምርጥ
ፍሬ፣ ጨረቃም
በምትስጠው መልካም
ነገር፤ በስማይት
ውስጥ የብርሃናትን
እንቅስቃሴ እንዳለም
እንደሚለዋወጥም ያመለክታል።
የቀድሞውም ቃል
የሥነ-ፍጥረት
ቃል ይመስላል
በሥራ ላይ
የዋለውም በመካከላቸው
በጨረቃ ስለሚሆነው
የጨለማ ግርዶሽ
ለመግለጽ ይመስላል።
ቅዱስ ያዕቆብ
እነዚህን ቃሎች
በማያዋላዳ ትክክለኛነት
አልተጠቀመባቸውም የቃሎቹም
አጠቃቀሙም በየትም
የአዲስ ኪዳን
ክፍሎች ወስጥ
አልታዩም እርሱ
ግን የተጠቀመባቸው ከጥብብን ጋር የሚመጣውን
ለመግለጽ ነው።
ቅዱስ ያዕቆብ
ሁለቱንም ቃላት
ተመሳሳይ ሃሳብን
ስለ ጸሐይ
መዞርና የጊዚያትን
መለዋወጥ ለመግለጽ
ተጠቅሞበታል። እምነትና
ጥበብ እግዚአብሄር
ስለማይለወጥ በርሱ
ላይ ይደገፋሉ።
ጥቅስ 16 እና 17 ማንኛውም እግዚአብሄር
ለአማኞች የስጣቸው
ስጦታ ለጥቅማቸው
ነው። እግዚአብሄር
በአማኞች ሕይወት
ፈተናን ሲፈቅድ
(1ቆሮ. 10፡13)
“ለሰው ሁሉ
ከሚሆነው በቀር
ምንም ፈተና
አልደረሰባችሁም፤ ነገር
ግን ከሚቻላችሁ
መጠን ይልቅ
ትፈተኑ ዘንድ
የማይፈቅድ እግዚአብሔር
የታመነ ነው፥
ትታገሡም ዘንድ
እንድትችሉ ከፈተናው
ጋር መውጫውን
ደግሞ ያደርግላችኋል”። ማንኛውም ክርስቲያን
በፈተናው ወቅት
ሊያስታውስው የሚገባው
ክፍል ነው።
አንድ አማኝ
ከዚህ በፊት
እንዳነሳሁት በፈተና
ማለፍም እንዳለ
መውደቅም አለ
በዚህ ሁሉ
አማኙ የእግዚአብሄርን እርዳታ እንዳማይለየው መረዳት
ይገባዋል።
በቅዱስ ያዕቆብ
የተፃፈው መልዕክት
የሚያስተምረው ስዎች
ሁሉ የራሳቸው
የሃጢያታቸው ፀሐፊዎች
ናቸው እራሳቸውን በራሳቸው
ከሃጢያት ስቃይ
ውስጥ የሚጨምሩት እራሳቸው እንደሆኑም ያነሳል።
በዚህ ሁሉ
መሃከል እግዚአብሄር የሕይወት
ምንጭ አንደሆነ
(ጥቅስ 16-17) ያመለክታል። ስለሆነም
የመልአክቱ ጸሐፊ
ከአይሁድ እምነት የመጡትን
ወንድሞቹን በእግዚኣብሄር ላይ ባላቸው አመለካከታቸውና አስተሳስባቸው ላይ ሊጠነቀቁ
አንደሚገባቸው ያስተምራቸዋል። ቅዱስ ያዕቆብ
ለአንንባቢዎቹ ይህንን
በሚልበት ጊዜ
ክርስቲያን ወንድሞቹ
በተሳሳተ አስተሳስብ
በመወስድ በክርስቶስ
ኢየሱስ በመንፈስ
ቅዱስ በኩል
ከተገለጠላቸው እውነት የኒቆላውያን
የመናፍቅ ትምህርት
በማስተናገድ እንዳይወስዱና እንዳያፈነግጡ ወይም እንዳይሽሹ በመረዳት
ሆኖ ወንድሞቹን
ያስጠነቅቃል። ጸሐፊው ለአንባቢዎቹ
አስረግጦ የሚናገረው
ወንድሞቹ የቱንም
ያህል በስህተት
ሃሳቦች የተሞሉም
ቢሆኑም አንኳ
በክርስቶስ ኢየሱስ
የተገለጠውን አውነት
ሊለውጡት አይችሉም።
እግዚኣብሄርንም ስህተት
ውስጥ ለመውደቃቸው
ምክንያት ማድረግም አይገባቸውም ምክንያቱም
መልካም ስጦታ
ሁሉ ከእግዚኣብሄር ከብርሃናት አባት በመሆኑና
የእግዚኣብሄር ባህሪው
የመልካም ሁሉ
ምንጭ አንጂ
የክፉ ባለመሆኑ
ነው (ጥቅስ
17) በዚህ በጥቅስ
17 ፀሐፊው የሚያተኩረው፦
(1) እግዚአብሄር
የብርሃናት አባት አንደሆነ
ነው። የሚታየው የፀሐይ
ብርሃን በስማያት
ያሉት ግኡዝ
አካላት ሁሉ
የተፈጠሩት በርሱ
አንደሆነ ያመለክታል።
ይህም በዘፍጥረት
በመጀመሪያዎቹ ምዕራፎች
ውስጥ አግዚኣብሄር
ብርሃን ይሁን
አለ ብርሃንም
ሆነ ወደሚለው
የፍጣሪነቱን ችሎታ
ፈጣሪነቱን ያስረግጣል።
አነዚህ የስራቸው
የአጁ ስራዎች
ይለወጣሉ አርሱ
ግን ፀንቶ
ይኖራል አይለወጥም።
2. መልካም ስጦታ
ሁሉ ከብርሃናት
አባት ከአግዚኣብሄአር ዘንድ ይመጣል ወይም
ይገኛል። ይህ
መልካም ስጦታ
በኢዮብ 32፡3
“ነገር ግን
በስው ውስጥ
መንፈስ አለ
ሁሉን የሚችል
ኣምላክ አስትንፋስ
ማስተዋልን ይስጣል
አርሱም ስው
አርሱን አንዲያውቅ
ጨለማውን በብርሃኑ
ይወጣል ስውንም
ወደ አውነቱ
ያመጣል። አልፎም
አግዚኣብሄር ለስለሞን እንደ ስጠው
ጥበብ መንግስትን የመምራት
ችሎትና ጥበብ
ከአግዚኣብሄር ለሚወዱት
ይስጣል መለኮታዊ
መገለጥ ሁሉ
ከላይ ከብርሃናት
አባት የተስጡ ናቸው።
(3) የሕይወት
መለወጥና የመልካምነቱ
መገለጫና ውጤቱንም
በሕይወታቸን ያየነው
ከርሱ የተነሳ
ነው (ጥቅስ
18)።
1፡18 “የፍጥረቱ በኩራት“ አንዲሆን በገዛ
ፈቃዱ በአውነት
ቃል ወለደን”። ቅዱስ ያዕቆብ
“የፍጥረቱ በኩራት” የሚለውን
አባባሉን ለምን
መረጠ? ቅዱስ
ያአቆብ “የፍጥረቱ
በኩራት” የሚለውን አባበሉን
የመረጠው በብሉይ
ኪዳን ጊዜ
አስራኤልን በሕዝብ
ደረጃ “የበኩር
ልጆቹ” ተብለው በአግዚኣብሄር አንደሚጠሩ ያውቃል ስለሆነም
ይህንን ቃል
ለወገኖቹ ለአይሁድ
አማኞች አግዚኣብሄር
ወደስጣቸው በቁልምጫ
ስማቸው መጥራት
ያስፈለገው ልባቸውን
ለማግኘት ብሎም
ከአግዚኣብሄር የራቁትም
ሆነ የደከሙትን ወደ ስፍራቸው
አንዲመለሱ ለማድረግ
በዚህ መረዳት
ውስጥ በመሆን
የተጠቀመበት አባባል ነው
ማለት ይቻላል።
ሁለተኛው “የፍጥረቱ በኩራት” የሚለው አባባል በጥቅም ላይ የዋለው የመጀመሪያውን የምድርን ፍሬ ስው በጉልበቱ ስርቶ የሚያገኘውን ለመግለጥ ነው። የፍጥረቱ በኩራት የሚያካትተው ስው በጉልበቱ ስርቶ ለፍቶ የሚያመጣው የስብሎች የመጀመሪያው ውጤቶች አንደሆኑ (ዘጽ. 34፡18-22 ዘለዋ. 23፡16-20) በተለይም ከምድር ላይ በቅለው የሚገኙትን የምግብ ውጤቶች ነው። ሶስተኛው በኩራት በጥቅም ላይ የዋለው የመጀመሪያውን መሃፀን ከፋች የሆነውን የሆድ ፍሬ (ልጅን) ለመግለጥ ነው። ስለ “ፍጥረቱ በኩራት” አግዚኣብሄርም ሙሴን አንዲህ ብሎ ተናገረው፡- በአስራኤል ልጆች ዘንድ ከስውም ከአንስሳትም መህፀን የሚከፍት በኩር ሁሉ ለኔ ይቀደስልኝ የኔ ነው። (ኦሪት ዘጽ. 13፡2፤ ኦሪት ዘጽ. 22፡29 አንደተፃፈው ለአግዚኣብሄር ይስጣል።
“ለዝምታ ጊዜ አለው”
“መናገር ብር ነው፤ ዝምታ ወርቅ ነው” የሚል አንድ የቆየ የምሥራቃውያን አባባል አለ። ብሪወርስ ዲክሽነሪ ኦቭ ፍሬዝ ኤንድ ፌብል የተሰኘው መጽሐፍ “ቃል አንድ ሰቅል ቢመዝን፣ ዝምታ ደግሞ ሁለት ሰቅል ይመዝናል” የሚል ከዚህ ጋር የሚመሳሰል የዕብራይስጥ አባባል እንዳለ ገልጿል። የጥንቱ እስራኤል ንጉሥ የነበረው ጠቢቡ ሰለሞንም እንዲህ ሲል ጽፏል፦ “ለሁሉም ነገር ጊዜ አለው፤ ከሰማይ በታች ለሚከናወነው ለማንኛውም ነገር ወቅት አለው፤ . . . ለዝምታ ጊዜ አለው፤ ለመናገርም ጊዜ አለው።” መክ. 3:1, 7
ታዲያ ከመናገር ይልቅ ዝም ማለት ተገቢ የሚሆነው መቼ ነው? “ጸጥ” እና “ዝም” ማለት የሚሉት ቃላት በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከመቶ ጊዜ በላይ ተጠቅሰዋል። እነዚህ ቃላት በተጠቀሱባቸው ቦታዎች ዙሪያ ያሉትን ሐሳቦች ስንመለከት፣ ዝም ማለት ተገቢ የሚሆኑባቸው ቢያንስ ሦስት ዘርፎች እንዳሉ እንገነዘባለን። ዝም ማለት የአክብሮት መግለጫና የአስተዋይነት ምልክት የሆነው እንዲሁም ጸጥታ ለማሰላሰል የሚረዳው እንዴት እንደሆነ አንድ በአንድ እንመልከት።
ዝምታ የአክብሮት መግለጫ ነው
ዝምታ፣ አክብሮት ማሳየት የሚቻልበት አንዱ መንገድ ነው። ነቢዩ ዕንባቆም “እግዚአብሔር ግን በተቀደሰ መቅደሱ አለ፣ ምድር ሁሉ በፊቱ ጸጥ ትበል” ብሏል። (ዕን. 2:20) በተጨማሪም እውነተኛ የአግዚኣብሄር አገልጋዮች ‘የአግዚኣብሄርን ማዳን፣ ዝም ብለው ተስፋ እንዲያደርጉ’ ማበረታቻ ተሰጥቷቸዋል። (ሰቆ. 3:26) መዝሙራዊው እንዲህ በማለት ዘምሯል፦ “በእግዚአብሔር ፊት ጸጥ በል፤ በትዕግሥትም ተጠባበቀው፤ መንገዱ በተቃናለት . . . ሰው ልብህ አይሸበር።” መዝ. 37:7
ታዲያ አንድም ቃል ሳንናገር አግዚኣብሄርን ማወደስ እንችላለን? አንዳንድ ጊዜ፣ በፍጥረት ላይ የሚታየውን ውበት ስንመለከት በአድናቆት ከመሞላታችን የተነሳ ስሜታችንን ለመግለጽ ቃላት ያጥረናል። በዚህ መልኩ ውብ ስለሆነው ተፈጥሮ ማሰባችን ፈጣሪን በልባችን የምናወድስበት አንድ መንገድ ነው። ዳዊት አንዱን መዝሙሩን የጀመረው “አግዚኣብሄር ሆይ፣ በጽዮን በአንተ ፊት ውዳሴና ዝምታ አለ፤ የተሳልነውን ለአንተ እንሰጣለን” በሚሉት ቃላት ነበር። መዝ. 65:1
ለአግዚኣብሄር አክብሮት ማሳየት እንዳለብን ሁሉ እሱ ለሚናገራቸው ነገሮችም አክብሮት ማሳየት ይኖርብናል። ለምሳሌ ያህል፣ የአግዚኣብሄር ነቢይ የነበረው ሙሴ በሕይወቱ ማብቂያ አካባቢ ለእስራኤል ብሔር ንግግር ባቀረበበት ወቅት እሱና ካህናቱ እንዲህ ብለው ነበር፦ “ጸጥ ብለህ አድምጥ! . . . አምላክህን እግዚአብሔርን ታዘዝ።” እስራኤላውያን የእግዚአብሔር ሕግ በሚነበብበት ቦታ ሲሰበሰቡ ልጆችም እንኳ ሳይቀሩ በትኩረት እንዲያዳምጡ ይጠበቅባቸው ነበር። ሙሴ “ይማሩ ዘንድ፣ . . . ወንዶችን፣ ሴቶችን፣ ልጆችን . . . ሰብስብ” በማለት ትእዛዝ ሰጥቶ ነበር። ዘዳ. 27:9, 10፤ 31:11, 12
በዘመናችን የሚገኙ የእግዚአብሔር አገልጋዮችም ጨምሮ በሁሉም ክርስቲያናዊ ስብሰባዎች ላይ የሚሰጡትን ትምህርቶች በአክብሮት ማዳመጣቸው ተገቢ ነው። ከመድረክ ጠቃሚ የሆነ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት በሚሰጥበት ጊዜ፣ ሳያስፈልግ ከሌሎች ጋር ማውራት ለእግዚአብሔር ቃል አክብሮት እንደጎደለን የሚያሳይ አይደለም? ስብሰባ በሚካሄድበት ጊዜ ዝም ብለን ማዳመጥ ይኖርብናል። ከአንድ ሰው ጋር በምንነጋገርበት ጊዜም ጥሩ አዳማጭ መሆናችን ለግለሰቡ አክብሮት እንዳለን ያሳያል። ለምሳሌ ያህል፣ ኢዮብ በሐሰት የወነጀሉትን ወዳጆቹን “አስተምሩኝ፤ እኔም ዝም እላለሁ” ብሏቸው ነበር። ኢዮብ እነሱ ሲናገሩ ዝም ብሎ ለማዳመጥ ፈቃደኛ ነበር። እሱ መናገር ሲፈልግ ደግሞ “ዝም በሉ፤ እኔ ልናገር” ብሏቸዋል። ኢዮብ 6:24፤ 13:13
ዝምታ የአስተዋይነት ምልክት ነው
መጽሐፍ ቅዱስ “አንደበቱን የሚገታ . . . ጠቢብ ነው” በማለት ይናገራል። በተጨማሪም “አስተዋይ . . . አንደበቱን ይገዛል” ይላል። (ምሳሌ 10:19፤ 11:12) ኢየሱስ ዝም በማለት ጠቢብና አስተዋይ መሆኑን ግሩም በሆነ መንገድ እንዴት እንዳሳየ ተመልከት። በአንድ ወቅት፣ ኢየሱስ በጣም ይጠሉት ለነበሩት ሰዎች መልስ መስጠት ምንም ፋይዳ እንደሌለው ስላስተዋለ ‘ዝም ማለትን’ መርጧል። (ማቴ. 26:63) በኋላም ተከሶ ጲላጦስ ፊት በቀረበበት ጊዜ “ምንም መልስ አልሰጠም።” እሱ ከሚናገር ይልቅ ተግባሩ ራሱ እንዲናገርለት በመምረጥ አስተዋይ መሆኑን አሳይቷል። ማቴ. 27:11-14
እኛም በተለይ የሚያበሳጭ ነገር ሲያጋጥመን አንደበታችንን መግታታችን አስተዋይነት ነው። የምሳሌ መጽሐፍ “ታጋሽ ሰው ትልቅ ማስተዋል አለው፤ ግልፍተኛ ሰው ግን ቂልነትን ይገልጣል” ይላል። (ምሳሌ 14:29) ፈታኝ ሁኔታ ሲያጋጥመን በችኮላ መልስ የምንሰጥ ከሆነ ‘ምነው ምላሴን በቆረጠው’ እንድንል የሚያደርገንን ያልታሰበበት ነገር ልንናገር እንችላለን። በዚህ ወቅት የተናገርነው ነገር ቂልነት የተንጸባረቀበትና በኋላ ላይ አእምሯችንን የሚረብሸን ሊሆን ይችላል።
ክፉ ሰዎች በሚያጋጥሙን ጊዜ አንደበታችንን መጠበቃችን አስተዋይነት ነው። በአገልግሎት ላይ ፌዘኛ ሰዎች ሲያጋጥሙን፣ የተሻለው መልስ ዝም ማለት ሊሆን ይችላል። በተጨማሪም አብረውን የሚማሩ ልጆች ወይም የሥራ ባልደረቦቻችን መጥፎ ቀልዶችንና የብልግና ቃላትን ሲናገሩ፣ በቀልዳቸው ወይም በንግግራቸው እንዳልተደሰትን ለማሳየት አንዳንድ ጊዜ ዝም ማለታችን አስተዋይነት ነው። (ኤፌ. 5:3) መዝሙራዊው “ክፉዎችም በእኔ ዘንድ እስካሉ ድረስ፣ ልጓም በአፌ አስገባለሁ” በማለት ጽፏል። መዝ. 39:1
“አስተዋይ” ሰው የሌሎችን ሚስጥር አያወጣም። (ምሳሌ 11:12) አንድ እውነተኛ ክርስቲያን በሚስጥር መያዝ ያለባቸውን ጉዳዮች ለሌሎች ላለመንገር ይጠነቀቃል። በተለይ ክርስቲያን ሽማግሌዎች ሚስጥር በመጠበቅ ረገድ ጠንቃቆች መሆን አለባቸው፤ ይህም የጉባኤው አባላት በእነሱ ላይ ያላቸውን እምነት እንዳያጡ ያደርጋቸዋል።
ዝምታ ጠቃሚ የሚሆንበት ጊዜ አለ። ሲድኒ ስሚዝ የተባለ በ19ኛው መቶ ዘመን የኖረ እንግሊዛዊ ጸሐፊ፣ በእሱ ዘመን ስለኖረ አንድ ሰው ሲጽፍ “ከሰው ጋር ሲጫወት አልፎ አልፎ ዝም ብሎ የሚያዳምጥ መሆኑ ከእሱ ጋር መጨዋወት አስደሳች እንዲሆን ያደርጋል” ብሏል። እርግጥ ነው፣ ሁለት ጓደኛሞች በየዕለቱ በሚያደርጉት ውይይት አንዱ ብቻ ተናጋሪ መሆን የለበትም፤ ሁለቱም ሐሳባቸውን መግለጽ አለባቸው። ይሁንና አንድ ሰው ከሌሎች ጋር በመጨዋወት ረገድ የተዋጣለት እንዲሆን ጥሩ አዳማጭ መሆን አለበት።
ሰለሞን “ከቃላት ብዛት ኀጢአት አይታጣም፤ አንደበቱን የሚገታ ግን ጠቢብ ነው” ሲል አስጠንቅቋል። (ምሳሌ 10:19) በመሆኑም አንድ ሰው የሚናገረው ነገር ባነሰ መጠን ማሰተዋል የጎደለው ነገር የመናገሩ አጋጣሚም የዚያኑ ያህል ይቀንሳል። እንዲያውም “አላዋቂ እንኳ ዝም ቢል ጠቢብ፣ አንደበቱንም ቢገዛ አስተዋይ ይመስላል።” (ምሳሌ 17:28) እንግዲያው እኛም ‘የከንፈሮቻችንን መዝጊያ እንዲጠብቅልን’ ይሖዋን በጸሎት እንጠይቀው። መዝ. 141:3
ለማሰላሰል ይረዳል
መጽሐፍ ቅዱስ በጽድቅ ጎዳና ስለሚጓዝ ሰው ሲናገር ‘[የእግዚአብሔርን] ሕግ በቀንና በሌሊት ያሰላስለዋል’ ይላል። (መዝ. 1:2) አንድ ሰው በዚህ መንገድ እንዲያሰላስል በጣም ምቹ የሚሆንለት እንዴት ያለ ሁኔታ ነው?
የአብርሃም ልጅ የሆነው ይስሐቅ ‘በመሸ ጊዜ ለማሰላሰል ወደ ሜዳ ወጥቶ ነበር።’ (ዘፍ. 24:63) ይስሐቅ ጸጥታ የሚሰፍንበትን ጊዜና ቦታ መርጦ ነበር። ንጉሥ ዳዊትም ያሰላስል የነበረው ሰው ሁሉ በሚተኛበትና ጸጥ ረጭ ባለው ሌሊት ነበር። (መዝ. 63:6) ኢየሱስ እንኳ ብቻውን የሚሆንበትና የሚያሰላስልበት ጊዜ ለማግኘት ከፍተኛ ጥረት አድርጓል፤ ግርግር ከሚበዛበት አካባቢ ርቆ ወደ ተራራ፣ ወደ ምድረ በዳ ወይም ወደ አንድ ገለልተኛ ስፍራ ይሄድ ነበር። ማቴ. 14:23፤ ሉቃስ 4:42፤ 5:16
ጸጥታ የሰፈነበት አካባቢ መንፈስን የሚያድስ መሆኑ አይካድም። እንዲህ ያለው አካባቢ ራሳችንን ለመመርመር የሚያስችል ምቹ ሁኔታ ይፈጥርልናል፤ ራሳችንን መመርመራችን ደግሞ በሕይወታችን ውስጥ ማሻሻያ ለማድረግ ከሚያስፈልጉን ወሳኝ ነገሮች መካከል አንዱ ነው። ጸጥታ የአእምሮ ሰላም ይሰጣል። ጸጥታ በሚሰፍንበት ጊዜ ማሰላሰል፣ ልካችንን የማወቅና የትሕትና ባሕርይ በውስጣችን እንዲተከል የሚያደርግ ከመሆኑም ሌላ በሕይወት ውስጥ ትልቅ ቦታ ሊሰጣቸው ለሚገቡ ነገሮች ያለንን አድናቆት ይጨምርልናል።
ዝምታ ጥሩ ነገር ቢሆንም “ለመናገርም ጊዜ አለው።” (መክ. 3:7) በዛሬው ጊዜ ያሉ እውነተኛ የእግዚአብሔር አገልጋዮች የእግዚአብሔርን መንግሥት ምሥራች “በመላው ምድር” ላይ በመስበኩ ሥራ በትጋት እየተካፈሉ ነው። (ማቴ. 24:14) ለምሥራቹ ምላሽ የሚሰጡ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ በመሄዱም የእግዚአብሔር አገልጋዮች የሚያሰሙት የደስታ ጩኸት ከምንጊዜውም ይበልጥ እያስተጋባ ነው። (ሚክ. 2:12 እንግዲያው የመንግሥቱን ምሥራች በቅንዓት ከሚያውጁትና ስለእግዚአብሔር ድንቅ ሥራዎች ከሚናገሩት ሰዎች መካከል ለመቆጠር የተቻለንን ሁሉ እናድርግ። በዚህ ጠቃሚ ሥራ እየተካፈልን አኗኗራችን ‘ዝምታ ወርቅ’ የሚሆንበት ጊዜ መኖሩን እንደምንገነዘብ የሚያሳይ ይሁን።
በደ/ር አመለወርቅ ሥዩም ከተጻፈው “የቅዱስ ጳውሎስ ወደ ሮሜ ስዎች የመልዕክቱ ሐተታ” መጽሐፍ ላይ የተወስደ የጥቅስ በጥቅስ ጥናት ከዚህ እንደሚከተለው ያትታል።
የሮሜ መልዕክት ምዕራፍ 11፡1-36 የመልዕክቱ ሐተታ
ቅዱስ ጳውሎስ በሮሜ ምዕራፍ 11 የሚያቀርበው መልዕክቱ እግዚአብሄር ከእስራዔል ሕዝብ ጋር ሥራውን እንዳልጨረስ በማረጋገጫ የጻፈው መልዕክቱ መሆኑ ነው።
በጥቅስ 1 ቅዱስ ጳውሎስ መልክቱን በጥያቄ ይጀምራል እንዲህም ሲል፦ እንግዲህ እግዚአብሄር ሕዝቡን ጣላቸውን? እላለሁ አይደለም። ቅዱስ ጳውሎስ ለጠየቀው ጥያቄ የሚገመተው አሉታዊ መልስ ሆኖ ሳለ ለጠየቀው ጥያቄ እራሱ “አይደለም ብሎ መልስ ስጥቶበታል። ቅዱስ ጳውሎስ እግዚአብሄር ሕዝቡን አለመጣሉን በማረገገጫነት እራሱን ያቀርባል። እርሱም ከእስራዔል ሕዝብ አንዱ መሆኑንና የአብረሃም ዘር ወገኑም ከቤንጃሚን መሆኑን ጨምሮ ገልጿል። ቅዱስ ጳውሎስ በአይሁድ መካከል ታማኝ የሆኑ ቅሬታዎች/ትሩፋን ምን ጊዜም ስለሚኖሩት እግዚአብሄር ሕዝቡን በጠቅላላ እንዳልጣላቸውም ያመለክታል።
በጥቅስ 2 እግዚአብሄር አስቀድሞ ያወቃቸውን ሕዝብ አልጣላቸውም። መጽሐፍ ስለ ዔልያስ በተጻፈው የሚለውን በእግዚአብሄር ፊት እስራዔልን እንዴት እንደሚከስ አታውቁምን?
እግዚአብሄር አስቀድሞ ያወቃቸውን የሚለውን ሐረግ በግለስብ ደርጃ ሳይሆን በሕዝብ ደርጃ እስራዔልን እንደሚያውቃቸው እንደለያቸው ያመለክታል። የእስራዔል ሕዝብ መታወቃቸውም የጀመረው ከአብረሃም ጥሪ ጀምሮ (ዘፍ. 12) እንደተጠቀስው እግዚአብሄር አብርሃም ሲጠራው ከወገኖቹ ከሃርንና ከኡር ተለይቶ በወጣ ጊዜ ነው። የእስራዔል ሕዝብ የታወቁት በእግዚአብሄር እቅድ ውስጥ ለእርሱ የተመረጡና የተለዩ ሕዝቦች የሆኑት በዚህ በአብረሃም ጥሪ አለም ሳይፈጠር መመረጣቸው እንደነበረ ያመለክታል።
ሕዝቡን ጣላቸውን? ይህ የጥያቄ አረፍተ ነገር ውስጥ “መጣል“ ማለት መተው ወይም መረሳት ማለት ነው። መጣል ወይም መተው የሚለው ቃል በእግዚአብሄር ከተመረጠ ሕዝብ ጋር የማይሄድ ቃል ነው። እግዚአብሄር የመረጠውን ሕዝብ ሊጥል ለምን መረጠ የሚለውን ጥያቄ ያስከትላል። ሌላው ደግሞ “መጣል ወይም መተው“ ከእግዚአብሄር ባህሪ ጋር የሚይሄድ ቃል ነው። እያሱ ምዕራፍ 1፡5-6 እግዚአብሄር የመረጠውን ሕዝብ ስለአለመጣሉ ያመለክታል። እግዚአብሄር ከመረጠ አይጥልም ምክንያቱም የእግዚአብሄር እቅድ ለእስራዔል ሕዝብ ዘላለማዊ ከመሆኑ የተነሳ የማያቋርጥ ወይም የሚቀጥል ስለሆነ ሕዝቡን እንደማይጥላቸው ያመለክታል።
ጥቅስ 3 እና 4 ጌታ ሆይ ነብያትህን ገደሉ መስዊያዎችህንም አፈረሱ እኔም ብቻዪን ቀረሁ ነፍሴንም ይሿታል።
ቅዱስ ጳውሎስ በጥቅስ 3 እና 4 ውስጥ የጠቀሳቸውን የጻፈው በዔልዛቤል አነሳሺነት ስለተገደሉት ነብያትና ስለፈረስው የእግዚአብሄር መስዊያዎች ነው ዔልያስም ብቻውን እንደቀረም እንደውም እርሱንም ለመግደል እንደሚፈልጉት ይናገራል። እግዚአብሄር ደግሞ ዔልያስን ባልጠበቀው ወይም ባላስበው መንገድ እርሱ ብቻ አንዳልቀረ ሌሎችም “ቅሬታዎች“ በአልን ያላመለኩ 7000 አሉኝ ብሎ ያሳውቀዋል። በዚህም የእግዚአብሄር ሁሉን አዋቂነቱና ሉአላዊ ሥልጣንና ጥበቃ በሚያስደንቅ መንገድ እንደተገለጠ ያመለክታል። ቅዱስ ጳውሎስ በነዚህ ጥቅሶች ያነሳው በእስራዔል ጉዳዮች ላይ በሮማ በሚኖሩት አማኞች/ክርስቲያኖች ብቻ ሳይሆን ለሚቀጥለውም የእስራዔል ሕዝብ ትውልድ ስለሚቀጥልም ነው። ቅዱስ ጳውሎስ የሚለው የመጀመሪያዎቹ በክርስቶስ ኢየሱስ ያመኑት አይሁዶች ናቸው እንጂ አሕዛብ ወይም አረማውያን አይደሉም። አሕዛብ ወይም አረማውያን እንደውም ከጥቂት ፈሪሳውያን ጋር በመተባበር ወደ መስቀል ሞት ያደርሱት ሮማውያን ናቸው።
በጥቅስ 5 ላይ እግዚአብሔር ለነብዩ ዔልያስ በብሉይ ኪዳን ዘመን ዔልያስ 7000 ቅሬታዎች ወይም ትሩፋን አሉኝ ብሎ እንደተናገረው በሐዲስም ኪዳንም የነዚህ ሕዝብ ቅሬታዎች ወይም ትሩፋን እንዳሉት ተመልክቷል። በጥቅስ 5 ትሩፋን ወይም ቅሬታዎች የሚባሉት 7000 ለበዓል ያልስገዱ እንደነበሩ ሁሉ በቅዱስ ጳውሎስም ዘመን ከተለያዩ ፈተናዎች ተፈትነው የነጠሩ ትሩፋን ወይም ቅሬታዎች ነበሩ። እነዚህ ቅሬታዎች ምን ጊዜም ክህደት በበዛበትም ጊዜ ነበሩ አሁንም አሉ የትሩፋኑ ወይም የቅሬታዎቹ የኖሩት ከሥራቸው ሳይሆን ከእግዚአብሄር ጸጋ እንደሆነ ቅዱስ ጳውሎስ ያመለክታል። እነዚህ ቅሬታዎች ወይም ትሩፋን በቅዱስ ጳውሎስ ዘመን የክርስቶስ አካል በመሆን በእብራውያን 3፡1 እንደተጠቀስው “ስለዚህ ከስማያዊ ጥሪ ተካፋዮች የሆናችሁ ቅዱሳን ወንድሞች ሆይ የሃይማኖታችንን ሐዋሪያትና ሊቀ ካህናት ኢየሱስ ክርስቶስ ተመልከቱ። ማንንኛውም ወደ ድነት የመጣ እስራዔላዊ የእስራዔል ተስፋዎች ማወራት ብቻ ሳይሆን እንደማንናውም ሃጢያተኛ ጌታን ተቀብለው ወደ ድነት መጥተዋል ቅዱስ ጳውሎስ ከነዚህ መካከል ነው።
ጥቅስ 6 እንደዚሁም በአሁኑ ዘመን ደግሞ በጸጋ የተመረጡ ቅሬታዎች አሉ። በጸጋ ከሆነ ከሥራ መሆኑ ቀርቷል ጸጋ ያለዚያ ጸጋ መሆኑ ቀርቷል።
በዚህ ጥቅስ ውስጥ ሥራ ማለት ያለጌታ እርዳታ ሕግን በመጠበቅ እግዚአብሄርን ደስ ለማስኘት መጣርና ለመጽደቅ መሞከር ነው። ስው በፍጥረቱ ሃጢያተኛ የሆነ እንዴት አድርጎ እግዚአብሄር የሚፈልገውን የቅድስና ሕይወት ሊኖር የሚችለው? ይህ ጥረት እግዚአብሄር የማይቀበለውና ፍሬ-ቢስ ነው።
ጸጋ ማለት ደግሞ እግዚአብሔር ብቻውን እራሱ የፈጸመው ሥራ ሲሆን ከጸጋ ተቀባዮ የሚፈልገው በእምነት ራሱን መስጠትና እግዚአብሄር ፈቃዱን እንዲገልጥበት መፍቀድ ብቻ ነው። በጸጋ ውስጥ ራሱን የሚገልጸው ጌታ ነው። በእግዚአብሄር ቃል ውስጥ ሁለቱ “ጸጋ“ ና “ሥራ“ የሚቃረኑ ናቸው።
ቅዱስ ጳውሎስ ከቅዱስ ጴጥሮስ ጋር ባለው ያለመግባባት በገላት. 2፡15 እና 21 የተመለከተው፦
እኛ በፍጥረት አይሁድ ነን ከሃጢያተኞችም ሆኑ አሕዛብ አይደለንም (ገላ. 2፡5)
ቁ. 21 የእግዚአብሄርን ጸጋ አልጥልም
ጽድቅስ በሕግ በኩል ከሆነ እንኪያስ ክርስቶስ በከንቱ ሞተ።
ቅዱስ ጳውሎስ ለመጀመሪያው የአባያተክርስቲያናት መማክርት በሐዋ. ሥራ. 15፡11 ነገር ግን በጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ እንደነርሱ ደግሞ እንድን ዘንድ እናምናለን። ቅዱስ ጳውሎስ በመልዕክቱ ውስጥ ከፍተተኛ ትኩረት ያደርገው ሥፍራ የስጠው “በጸጋ“ ላይ ነው።
ሮሜ 11፡7-10
ቅዱስ ጳውሎስ ለአንባቢው ለማሳየት የሚሞክረው የእግዚአብሄርን ሉአላዊ ከፍታውን በመጥቀም ያደርገውን ምርጫ ነው። እግዚአብሄር ሉአላዊ ከፍታውን በመጠቀም የመረጠው የእስራዔል ወገኖችን ብቻ ሳይሆን አሕዛብን እንደመረጠም ያመለክታል። በዚህ ምዕራፍ ቅዱስ ጳውሎስ በከፍተኛ ደረጃ የመለኮታዊ ሉአላዊነቱን በተመረጡት ህዝብ አመራሩና በአለም ታሪክና መድረክ ላይም መቼ መምጣት ወይም መታየት እንዳለባቸውም ውሳኔው የእግዚአብሄር መሆኑን ያመለክታል። ቅዱስ ጳውሎስ በ 7 እና 8 ጥቅሶች ውስጥ በግልጥ “ስለተመረጡት“ በተለይም በጥቅስ 7 ከአይሁዲነት ወደ ድነት የመጡ እንደቅዱስ ጳውሎስና ሌሎችም አምነው የዳኑት የእስራዔል ወገኖች ያመለክታል።
ጥቅስ 8 ሌሎችም ደነዘዙ እንዲሁም አይኖቻቸው እንዳያዩ ጂሮቻቸውም እንዳይስሙ እግዚአብሄር የእንቅልፍን መንፈስ እሰክዛሬ ደረስ ስጣቸው
በጥቅስ 8 እንደተመለከተው አብዛኛዎቹ የእስራዔል ሕዝቦች ልባቸውን አንዳጠነከሩ ያመለክታል:: የእስራዔል ልጆችን የያዛቸውን ልባቸውን ድንዳኔ ከፈርኦን የልብ መደንደን ጋር ይመሳስላል ይህም በሮሜ 9፡18 ተጽፎአል። በጥቅስ 8 የተጠቀስውን ከነብዮ ኢሳ. 29፡10 የተመለከተው ነው።
ተደነቁ ደነገጡም ተጨፈኑም እውሮችም ሆኑ
በወይን ጠጅ አይሁን እንጂ ስከሩ
በሚያስክር መጠጥ አይሁን እንጂ ተንገዳገዱ።
እግዚአብሄር የእቅንቅልፍ መንፈስን አፍስሶባቸዋል።
ቅደዱስ ጳውሎስ የሚለው ከላይ የተጠቀሱት በነብዮ በኢሳያስ እንደተነበየ ባላመኑት የእስራዔል ሕዝቦች ላይ እንደተፈጸመባቸው ያመለክታል። እግዚአብሄር ያዘጋጀውን የጽድቅ መንገድ ስላልተቀበሉ ልቦናቸው ጨለመ አይኖቻቸው ታወሩ የእንቅልፍ መንፈስም ወርደባቸው።
የእስራዔል ልጆች በብሄር ደረጃ ጽድቅን መፈለግ ሥራቸው ነው ጽድቅን ለማግኘት የሚጥሩትም የሙሴን ሕግ በመጠበቅ ወይም በሥራቸው ነው። በሥራ ጽድቅን ለማግኘት የሚስሩት ወይም ጻድቅ ለመሆን የሙሴን ሕግ በመጠበቅ በሌላ አባባል በእምነት ሳይሆን በሥራ የሚያደርጉት ጥረት ጽድቅን የሚያገኙበት መንገድ አለመሆኑን ቅዱስ ጳውሎስ በመልዕክቱ አስረግጦ ያመለክታል።
በጥቅስ 9 እና 10 የተመለከተውን ጥቅስ ቅዱስ ጳውሎስ ያጣቀስው ከዳዊት መዝሙር 69፡22፤23 ነው።
ዳዊትም፦
ማዕዳቸው ወጥመድና አሽክላ ማስናከያም
ፍዳም ይሁንባቸው አይኖቻቸው እንዳያዩ
ይጨልሙ ጀርባቸውም ዘወትር ይጉበጥ ብሏል።
ንጉስ ዳዊት ከላይ በተጠቀስው ሕይወት ያለፈ ነው። ዳዊት በገዛ ወገኖቹ ሲጠላና ሲነቅፍ የገዛ ሕዝቡ የሚሄድበት አስነዋሪ ድርጊት ሲያሳዝነው ብርቱ ጸሎት ጸለየ እንደጸለየውም እንቅፋትና ቅጣት ሆነባቸው እስካሁንም ድረስ መንቃት አልሆነላቸውም መዝ. 35፡8፤ 38፡4)።
የእስራዔል ሕዝቦች የልባቸው መደንደን ወይም ጥንካሬ ወደ ክፍተኛ ደርጃ የደረስው በመከራቸው ጊዜ ነው ስለሆነም መንፈሳዊ የልብ ጥንካሬያቸው በእስራዔል ሕዝቦች መካከል የሚታየው የትም አይታይም።
ጥቅስ 11-12
በጥቅስ 11 ቅዱስ ጳውሎስ የሚጠይቀው ጥያቄ እንግዲህ የተስናከሉ እስከሚወድቁ ድረስ ነውን? ብሎ ለጠየቀው ጥያቄ ደግሞ እራሱ “አይደለም“ ብሎ መልስ ይስጥበታል። ከዚህም በመቀጠል ነገር ግን እነርሱን ያስቀናቸው ዘንድ በእነርሱ በደል መዳን ለአሕዛብ ሆነ።
የቅዱስ ጳውሎስ አጠያየቅ የእስራዔል ሕዝብ መስናከላቸው የከበደ ከመሆኑ የተነሳ ከእግዚአብሄር እቅድ በፍጹም ወጡ ለሚለው መልስ ለማግኘት ነው። ለወደፊቱ ለእስራዔል ተስፋ የለም? ቅዱስ ጳውሎስ ላነሳው ጥያቄ መልስ ሲስጥ ለማሳየት የሞከረው የእስራዔል መስናከል ቋሚ አይደለም ምክንያቱም የእስራዔል ውድቀት ወደ ተሃድሶ ስለሚያደርሳቸው ነው። ቅዱስ ጳውሎስ በዚህ ጥቅስ አስገራሚ የሆነውን የእግዚአብሔርን ድንቅ አስራር ራሱን በራሱ በሚጠይቅ አይነት በማቅረብ መልስ በመስጠት አንባቢው እንዲያስተውል ያደርጋል። የእስራዔል መስናከል እስከ መጨረሻው ጸንቶ እስከሚጎዱ ድረስ የሚዘልቅ አይደለም። ቅዱስ ጳውሎስ በነዚህ ጥቅሶች ለአንባቢው የሚያመለክተው ሃጢያታቸው ጽናት የበረታ መሆኑን ለመግለጥ ነው። በጌታ ጸጋ ብቻ ሲታመኑ የሚነሱበት ጊዜ አለ ማለቱ ነው። የእስራዔል ሕዝቦች በእምነታቸው ከወደቁበት መነሳት አለም ሁሉ በጉጉት መጠበቅ እንዳለበት ለማሳየትና አሕዛብ ወይም አረማውያን ትሁታን እንዲሆኑ ለማድረግም የጻፈውን ገለጣ ቅዱስ ጳውሎስ ተጠቅሟል።
እግዚአብሄር የእስራዔል ጊዜያዊ ውድቀት ወይም መስናከል ለመልካም እንዳደረገውም ያነሳል። ቅዱስ ጳውሎስ እንደጠቀስው ከእነርሱ መውደቅ ወይም መስናከል የተነሳ ድነት ወደ አሕዛብ ወይም አረማውያን እንደመጣም መንገድም እንደከፈተ ያመለክታል። በፈንታው የአሕዛብ ወይም የአርማውያን ወደ ድነት መምጣታቸው አይሁዶች ቀንተውና ተቆጭተው ወደ ንስሃ እንደሚያመጣቸውም ተመልክቷል። አሕዛብ ወይም አረማውያን በእስራዔል ወድቀት ወይም መስናክል ወደ ጌታ ከመጡ ወደ ጌታ በመመለሳቸውማ የበለጠ ወደ እምነት የሚመለሱት አሕዛብ ወይም አረማውያን ቁጥር መብዛቱንም ያመለክታል በዚህም አስራር ውስጥ የእግዚአብሄር የድነት እቅድ ለአለም ሁሉ ይደርሳል።
ጥቅስ 13 እና 14
ለእናንተም ለአሕዛብ እናገራለሁ። እኔ የአሕዛብ ሐዋሪያ በሆንሁ መጠን ሥጋዪ የሆኑትን አስቀንቼ ምናልባትም ከእነርሱ አንዳንዱን አድን እንደሆነ አገልግሎቴን አከብራለሁ።
ከላይ በተመለከቱት ጥቅሶች ቅዱስ ጳውሎስ ለአሕዛብ ወይም አረማውያን በሐዋሪያት ሥራ ምዕራፍ 9 በተጠራው መስረት ሐዋሪያ ስለመሆኑና ለተጠራበትም ለአህዛብ ወይም አረማውያን ሐዋሪያነቱ ወቅት በመንፈስ ቅዱስ እንዳገዘው አገልግሎቱን በማክበር ጥቄቶቹን አይሁዶች ወደ ጌታ ለመመለስ እንዳስበ የሚያመለክት ነው። አይሁዶች ወገኖች በእርሱ አፍ በተስበከው ወንጌል የሚድኑትን አሕዛብ ወይም አረማውያንን አይተው በቅንዓት እንዲነሱና ወደ ጌታ ዘወር እንዲሉም ያደረገውን ጥረት ያመለክታል።
ጥቅስ 15
ቅዱስ ጳውሎስ በዚህ ጥቅስ ደግሞ የእስራዔልን ሕዝብ ለአሕዛብ ወይም ለአረማውያን በረከት ምክንያት አድርጎ እግዚአብሄር ተጠቀመባቸው የደህንነትን መንገድ ተቀብለው ወደ በረከቱ ሲገቡማ የጣምራ በረከቱ ከሞት የመነሳት ያህል እጥፍ ድርብ ደስታና በረከት ያመጣል የሚለውን የምስራች ያመለክታል።
ጥቅስ 11፡16
ቅዱስ ጳውሎስ በጥቅስ 16 የመጀመሪያው ክፍል ከዘሁልቁ 15፡17-21 ከተመለከተው ሃሳብ ጋር አያይዞ ጥቅሶታል። በዘሁልቁ 15፡17-21 የተመለከተው ከእርሻ የሚገኘው የመጀመሪያው ምርት ከሚያደርጉት ሊጥ አንድ እንጎቻ ለማንጻት ቁርባን እንደሚያቀርቡ ያመለክታል። በዚህ ክፍል “በኩር“ የተባሉት የእስርዔል ነገድ አባቶች ናቸው። እነዚህም የእስራዔል የነገድ አባቶች ከብሉይ ኪዳን የነበሩ አባቶች አብረሃም ይስሃቅና ያዕቆብ ናቸው የበለጠ ለመረዳት ዘዳ 23፡19፤ ዘጽ. 34፡22 ዘዳ. 26፡2, 10፤ ዘለዋ. 2፡12, 14, 23፡10 ዘሑ. 18፡12፤ 28፡26)። እግዚአብሄር የስጠውን ተስፋ የሚፈጽም መሆኑን ለማሳየት ወደ ተስጣቸው ተስፋ የሚመለሱም እንዳሉ ይመለክታል።
በቅዱስ ጳውሎስ ጊዜ ገና አዲስ ኪዳን ስላልተጻፈ እርሱ እራሱ በመልዕክቶቹ ውስጥ የሚጠቅስው ከብሉይ ኪዳን ነው። አብዛኛውን በአሁኑ ዘመን ያሉት አማኞች/ክርስቲያኖች የብሉይ ኪዳንን የክርስትና እምነት መስረት የሆነውን አያቁትም ስለሆነም የሚቆዮት በአዲስ ኪዳን ላይ ነው እንደዚህ መሆን የለበትም ይላሉ የሥነ-መለኮት ምሁራን። አዲስ ኪዳን ምንም እንኳ አዲስ ቃል ኪዳን የተሞላበትም ቢሆንም ቅዱስ ጳውሎስ በሮሜ መልዕክቶቹና በሌሎቹም እንደታየው የመልዕክቶቹ መስረት የብሉይ ኪዳን እንደሆነ ነው።
በአዲስ ኪዳን የተጻፈው አሮጌው (ብሉይ) የተስጠው ተስፋ ሙሉ የሆነበት ነው። አማኞች የብሉይ ኪዳንን የክርስትና እምነት ስረ-መስረቱን ካላጠኑ በአዲስ ኪዳን ውስጥ የተጻፈውን የእግዚአብሄርን ቃል ግልጽ ሊሆንላቸው አይችልም። አማኙ/ክርስቲያኑ ጥናት በሚያደርግበት ጊዜ ሙሉን መጽሐፍ ቅዱስን መሆን ይገባዋል።
በጥቅስ 17
የተመለከተው አንዳንድ የመጽሐፍ ቅዱስ አጥኚዎች እንደሚሉት ቅዱስ ጳውሎስ የወይራ ዛፍ የበለጠ እንዲያፈራ ምን መደረግ እንዳለበት ሙያው ነበረው ስለዚህም ትምህርቱን ለአንባቢው እንዲጨበጥ በዚህ ሥፍራ ተጠቅሞበታል ይላሉ። ቅዱስ ጳውሎስ በዚህ ጥቅስ ውስጥ ከቅርንጫፎቹ መልካሙን የወይራ ዛፍ የአስራዔል ተምሳሌት አድርጎ ሲጠቅምበት ግንዱ ደግሞ የእስራዔል አባቶች እነአብረሃም ይሳሕቅና ይዕቆብ ናቸው። እግዚአብሄር ቃል ኪዳን የገባው ለነዚህ አባቶች ነው (ሮሜ 11፡1፤ ዔርም. 11፡16)። በጥቅሱ ውስጥ የተመለከተው “አንዳንዱ ቢስበር“ የሚለው ሐረግ የወይራ ዛፍ የበለጠ እንዲያፈራ ቅርንጫፍ ተስብሮ ወደ እሳት ይጣላል (ማቴ. 21፡43 ኢሳ. 27፡11)።
ጥቅስ 16-24 ባሉት ጥቅሶች ቅዱስ ጳውሎስ ያነሳው አባባል ከተፈጥሮ ውጪ ነው። በጥቅስ 16 ውስጥ እስራዔልን በወይራ ተምሳሌት ያስቀምጣቸዋል። በጥቅስ 17 ደግሞ አሕዛብን ወይም አረማውያንን በወፍ ዘራሽ ተምሳሌት ያስቀምጣቸዋል። እስራዔል በመልካም በወይራ ዛፍ ተምሳሌት የተስጠው በአታክልት ውስጥ በሚገባ ጥንቃቄ ተደርጎለት የበቀለው የወይራ ዛፍ ነው። አሕዛብን ወይም አረማውያንን በወፍ ዘራሽ ተምሳሌት ሲያስቀምጠው በበረሃ ውስጥ እንደዚሁ ጥንቃቄ ወይም እንክብካቤ ሳይደረግለት የበቀለው መሆኑ ነው። ቅዱስ ጳውሎስ የአሕዛብን ወይም የአረማውያንን ወድ ድነት መምጣት በእንክብካቤ ያደገው መልካሙ የወይራ ዛፍ ላይ የወፍ ዘራሹ የወይራ ዛፍ ቅርንጫፍ እንደተጣበቀ አድርጎ ሥዕላዊ መግለጫ የስጠበት አገላለጽ በጥቅሱ ውስጥ ጎልቶ ይታያል። ቅዱስ ጳውሎስ በተምሳሌቱ ያቀረበው መግለጫው ከተፈጥሮ ተቃራኒ ነው የተባለው እንደዚህ አይነት የቅርንጫፎች ጥብቂያ ስለማይደርግ ነው ማለም ጥብቂያው የሚካሄደው ከሚመሳስለው የወይራ ቅርንጫፍ ጋር መሆን አለበት። በቅዱስ ጳውሎስ አባባል እግዚአብሔር ከተፈጥሮ ውጪ መስራት እንደሚችል አብሮ ለማመልከት የተጠቀመበት ተምሳሌት ነው። የቅዱስ ጳውሎስ ውይይት የሚያቀናው ወደ አይሁዶችና ወደ አሕዛብ ወይም አረማውያን በሮማ ለሚገኙ ብሎም ለአሁኑ ዘመን አማኞች ነው። ቅዱስ ጳውሎስ የሚስጠው ማጠንቀቂያ ከአሕዛብ ወይም አረማውያን ወደ ድነት የመጡት አይሁዶችንና እምነታቸውን በማሳነስ እራሳቸውን ክፍ ከፍ በማድረግ እንዳይታበዩ ነው። አሕዛብ ወይም አረማውያን ቅዱስ ጳውሎስ እንዳለው እንዳውም ወደ ድነት በአይሁዶች የተነሳ ስለመጡ ጌታን ማመስገን እንዳለባቸው ያመለክታል።
ጥቅስ 18-22
በቅዱስ ጳውሎስ አባባል በዚህ ክፍል አሕዛብ ወይም አረማውያንን እንደ በረሃ ወይራ ሲወስዳቸው እስራ ዔልን ደግሞ እንደመልካሙ ወይራ አስቀምጧቸዋል። ቅዱስ ጳውሎስ በዚህ ክፍል የወይራ ዛፎችን ማለትም መልካሙንና የበረሃውን የወይራ ዛፍን ተምሳሌት አድርጎ መውስድ ለአይሁዶችም ሆነ ለአሕዛብ ወይም አረማውያን የሚሆን እውነት ያስታውቃቸዋል በተለይም መልዕክቱ የሚጻፍላቸው በሮማ የሚኖሩ አማኞች/ክርስቲያኖች ከሁለቱም ወገኖች ወደ ድነት የመጡ በመሆናቸው ይህንን እውነት አስረግጦ እንደጻፈላቸው ያመለክታል። ቅዱስ ጳውሎስ የወይራ ዛፎችን ተምሳሌት በማስረጃነት ለማቅረብ የተጠቅመበት እንጂ አንዱን ከፍ ሌላውን ዝቅ ለማድረግ የተጠቅመበት ተምሳሌት አይደለም። ለሮማ አማኞች/ክርስቲያኖች የሚላቸው በእምነት የተቀበላቸውን የአሕዛብን ወይም የአረማውያንን ወገን በመዳናቸው ምክንያት በአይሁዶች ላይ እንዳይኮሩ ያስጠንቅቃል። በሮማ ያሉት እነዚህ ወገኖች የሚያዋጣቸው በግንዱ ውስጥ መኖር ብቻ ነው ይላቸዋል። ቅዱስ ጳውሎስ በመልዕክቱ ውስጥ የተጠቀመባቸው የተፈጥሮ እውነቶች የሚከተሉት ናቸው።
የበረሃ የወይራ ዘፍ ቅርንጫፎች የገቡት በእምነት ነው በእምነት የገቡት አሕዛብ ወይም አረማውያን በእምነታቸው ካልጸኑ የተስጣቸውን ጸጋ በጥንቃቄ ካልጠበቁ እነርሱም ልክ ያመጹት የእስራዔል ወገኖች የደረስባቸው ዕድል ይደርስባቸዋል። እንደ እውነቱ ከሆነ ቅዱስ ጳውሎስ እንደሚለው የበረሃ ወይራ ከመልካሙ ወይራ ጋር ከተቀየጠ ወይም ከተጣበቀ ወዲህ ጀምሮ ልዩነት የለም ልካም የወይራ ቅርንጫፎች ወይም የተፈጥሮ ቅርንጫፎች የወደቁት ባልማመናቸው የተነሳ ነው።
የበረሃ ቅርንጫፎች ወደ ድነት የመጡት በእምነት ነው ስለሆነም ቅርንጫፉ በራሱ መኖር አይችለም ጉልበትም ሆነ ጥንካሬ ያለው ከሥሩ እንጂ ከቅርንጫፉ አይደለም ቅርንጫፉ ምግቡን የሚያገነው ከሥሩ ነው።
ጥቅስ 19-24 ያሉት ጥቅሶች እግዚአብሄር ከአሕዛብ ወይም ከአረማውያን ከጨረስ በኋላ ወደ እእስራ ዔል እንደሚመለስ ያመላክታሉ። አይሁዶች ባለማመናቸው የተነሳ ከእምነት በስተ-ውጪ ተቀመጠዋል። አሕዛብ ወይም አረማውያን ደግሞ ከእምነታቸው የተነሳ በእምነት ውስጥ ገብተዋል ስሆነም በእግዚአብሄር ፊት ተቀባይነትና ተወዳጅነትን አግኝተዋል ስለሆነም አሕዛብ በአይሁዶች ላይ መኩራት የለባቸውም ከኮሩ ግን አሕዛብ ወይም አረማውያን በአይሁዶች ላይ የሆነባቸው ተመልሶ በነርሱም ላይ እንደሚሆን መገንዘብ አለባቸው።
ጥቅስ 25-32
ቅዱስ ጳውሎስ በተመለከቱት ጥቅሶች ውስጥ የሚያወዳድረው ማቴ. 13፡11 ሮሜ. 16፡1፤ 1 ቆሮ. 1፡7-10፤ ዔፌ. 1፡3 ሃሳቡን ለመግለጥና ለአንባቢው የመልዕክቱን ነጥብ ለማስጨበጥ ተጠቅሞበታል። የአሕዛብ ወይም የአረማውያን ሙላት የሚያመለክተው የመጨረሻው አሕዛብ ወይም አረማውያን ወደ ድነት መጥቶ በተክርስቲያን ከምድር ላይ የምትነጠቅበት ጊዜ ነው። በወቅቱ የአሕዛብ ዘመን በሉቃስ 21፡24 ከተጠቀስው ለየት ይላል በዚያን ጊዜ ለእርጉዞችና ለሚያጠቡ ወዮላቸው ታላቅ ችግር በምድር ላይ በዚህም ሕዝብ ላይ ይሆናልና በስይፍ ስለትም ይወድቃሉ ወደ አሕዛብ ሁሉም ይማረካሉ። የአሕዛብ ዘመን እስከሚፈጸም ድረስ እየሩሳሌም በአሕዛብ የተመረጠች ትሆናለች ይህም የሚያመለክተው የባቢሎን ምርኮኞች 587 ከክርስቶስ ልደት በፊት እስከ ቤተክርስቲያን መነጠቅ ድረስ ነው።
ጥቅስ 26-27
በነዚህ ጥቅሶች ውስጥ የእስራዔል ሕዝቦች እንደሚድኑ ያመለክታሉ። ለእስራዔል በሕዝብ ደርጃ ድነት በዔር. 31፡31-34) ባሉት ጥቅሶች እንደተመለከተው የአዲስ ቃል ኪዳን መፈጸም ይሆናል ጌታ ኢየሱስም ወደ ምድር ተመልሶ መንግስቱን ይመስረታል። ቅዱስ ጳውሎስ በነዚህ ጥቅሶች ውስጥ 26-32 ያሉትን በማገናኘት በማስማማት የጠቀሳቸው የዳዊት መዝ. 14፡7፤ ኢሳ. 59፡20, 21 ዔር. 31፡31 ናቸው። ቅዱስ ጳውሎስ ለማሳየት በግልጽ ስለብሉይ ኪዳንን ያለውን እውቀትና አብሮም ስለ እስራ ዔል ሕዝብ ከሃጢያት ነጻ ስለመውጣታቸው በትንቢት የተነገረውን ያነሳል።
ሮሜ 11፡ 33-36
ቅዱስ ጳውሎስ 33-36 ባሉት ጥቅሶች ውስጥ የሚያነሳው ስለውዳሴና ዝማሬ ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አያሌ ውዳሴዎች ተጽፈው ይገኛሉ ከነዚህም መሃከል ቅዱስ ጳውሎስ በሮሜ 16፡27 በዔፌ. 3፡21 ውስጥ የተጠቀሱት በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ተጽፈው ከሚገኙት ጥቂቶቹ ሲሆኑ በሮሜ መልዕክቶች ውስጥ 16 ውዳሴዎች ይገኛሉ።
በዶ/ር አመለወርቅ ሥዩም ከተጻፈው “የቅዱስ ጳውሎስ ወደ ሮሜ ስዎች የመልዕክቱ ሐተታ” መጽሐፍ የተወስደ የጥቅስ በጥቅስ ሐተታዊ መግለጫ
የቅዱስ ጳውሎስ መልዕክት ወደ ሮሜ ስዎች (ሮሜ. 13፡1-7)
የግሪኩ ቃል exousia የተመረጠ ባለሥልጣን የሚለውን ቃል ያመለክታል። ባለሥልጣኖች (የግሪኩ ቃል tasso የሚለው የሚያመለክተው በእግዚአብሄር የተመረጠ የተወስነ መሆኑን ነው። ይህም ማለት በእግዚአብሄር እቅድ ውስጥ የእግዚአብሄር የስው ወይም የምድር መንግሥት በምድር ላይ የፈቀደውና ያስቀመጠው በእርሱ ፈቃድ ውስጥ ሥነ-ምግባር የስፈነበትና የሞራል ሕግ በመንግሥቱ በፈጠረው የስው ልጆች መካከል በማንኛውም አለም ክፍል በሥራ እንዲውል ለማድረግ ነው።
1. የምድር መንግሥት ሃላፊነት (ሮሜ. 13፡1-7)
ምድራዊ መንግሥት በእግዚአብሄር የተቋቋሙ ናቸው የምድር መንግሥታት በእግዚአብሄር የተገኙና የተፈቀዱ ጊዜያዊ መንግሥታት ናቸው (ዘፍ. 9፡1-7፤ ሮሜ 13፡1-6፤ 1 ጴጥ. 2፡13-17)።
የምድር መንግሥት የተቋቋመው ለመግዛትና ለመቅጣት በሀገርም ሆነ ወይም በአለም አቀፍ ደረጃ ወንጀለኞችን ለመቅጣት ሲሆን የምድር መንግሥት በአለም አቀፍ ወይም በሕዝብ ደረጃ ሥራቸው የሚያካትተው ወንጀለኞች የሆኑትን ሕዝብ ወንጀላቸውን ያስቆማሉ። የስው (የምድር) መንግሥት ወንጀለኞች መቅጣት ብቻ ሳይሆን በምድር ላይ ሕግና ሥርዓትን ያሲዛሉ (ሮሜ. 13፡1-6፤ 1ጴጥ. 2፡13-17፤ ዘፍ. 9፡6፤ ኢሳ. 11፡4-9፤ ኢሳ. 65፡20፤ ዳን. 2፡21፤ 4፡17-25፤ 5፡21)።
የምድር መንግሥት የሚስራው ከክርስቲያኖች ከሌሎችም አማኝ ካልሆኑ ጋር አብሮ ሆነው ሕዝባቸውን መጠበቅና በከፍተኛ ደረጃ የሕዝቡ ደህንነትና አስተዳደር ማዋል ናቸው (ሮሜ. 13፡1፡ 1 ጴጥ. 2፡13-17)። ክርስቲያኖች የታወቁ የምድር መንግሥት አእሕዛብ መተው የለባቸውም። የምድር መንግሥት ሙሉ በሙሉ እግዚአብሄርን ለማያወቁ የተተው እንደሆነ ወንጌል አይሮጥም (1 ጢሞ. 1፡8-10)። ክርስቲያኖች በምድር መንግሥት ውስጥ ገብተው መመረጥ አለባቸው። የመንግሥት በምድር ላይ መኖር ለሁሉም ጠቅሜታ ስለሆነ እያንዳንዱ ክርስቲያን ጥሩ መንግሥት በምድር ላይ እንዲበዛ የራሱን አስተዋጽኦ ማድረግ ይኖርበታል።
2. የሕዝብ ወይም የዜጎች ሃላፊነታቸው (ሮሜ. 13፡1-7)
ባልሥልጣንን የሚቃወም የእግዚአብሄርን ሥርዓት ይቃወማል
የሲቪል መንግሥትን ታዘዙ (ሮሜ. 13፡1፤ ቲቶ. 3፡1፤ 1 ጴጥ. 2፡13-17)
የሲቪል መንግሥን መፍራት (ሮሜ. 13፡3፤ ምሳሌ 24፡21)
መልካም ሥሩ (ሮሜ. 13፡4፤ ቲቶ. 3፡1)
ለመንግሥት ቀረጥ ክፍሉ (ሮሜ. 13፡1-7፤ ማቴ. 22፡17-21)
ከስዎች የተበደራችሁትን መልሱ (ሮሜ. 13፡7)
የሲቪል ባለሥልጣናትን አክብሩ (ሮሜ. 13፡1-7፤ ኦሪት. ዘጽ. 22፡28፤ የሐዋ.ሥራ. 23፡5፤ 1 ጴጥ. 2፡13-17)
ለሲቪል ባለሥልጣናት ጸልዩ (1 ጢሞ. 2፡1-2)
የሲቪል ባለሥልጣን ያወጣውን ሕግ አክብሩ ወይም ጠብቁ (ሮሜ. 13፡1-7፤ እብራውያን 7፡26)
የሲቪል ባለሥልጣናትን አትሳደድቡ (መክብብ 10፡20)
ለስላም ሥሩ ወይም ቁሙ (ሮሜ. 12፡18)
የ ምድር ባለሥልጣኖች በምድር ላይ ያስቀመጣቸው በምድር ላይ የሥነ-ምግባርና የአስተዳደር ሥርዓትና በሥራቸው የሚገዛውን ሕዝብ ለደሕንነንቱ ጥበቃ ያደርጋሉ። ከዚህ ባለፈ ግን ሥልጣናቸውን ተጠቅመው ወይም ከጥበቃ ወይም ከአስተዳደር ድክመት የተነሳ የሚያስተዳድሯቸው ሕዝቦች ቢጎዱ በመንግሥታቸው ለሚያደርጉት ድርጊት ግን እግዚአብሄር ሃላፊነት የለውም እንደማንኛውም አገልጋይ እግዚአብሄር ይቀጣቸዋል።
ቅዱስ ጳውሎስ መልዕክቱን የጻፈው በሮማ ለሚኖሩት ከአይሁዲነትና ከአሕዛብ ወይም ከአርማውያን በቅድስት ህገር በዘመኑ ስለተነሳው የፓሊቲካ ነውጥና ሽብር እንዲቃወሙ ነበር። የአይሁድ ወገን የሆኑ አላማቸው በፍጹም ፓሊቲካዊ የሆነ ቀናተኞች ነበሩ እነዚህም ስዎች የሚንቀሳቀሱት በእግዚአብሄር ላይ ባለው እምነታቸው ወይም ስዎችን ከመውደዳቸው የተነሳ አልነበረም። እነዚህ የአይሁድ ወገን ቀናተኞች የሮማ ግዛት ወይም መንግሥት እንዲገለበጥ ይፈልጋሉ የሮማን መንግሥት ለመገልበጥ የሚጠቀሙበት መንገድ ግን የእግዚአብሄርን ፍቅር በሚቃወም መንገድ ነበር። ቅዱስ ጳውሎስ በሮማ በዚህ በቀውጢ ስዓት የአንባ ገነን አገዛዝ በሚገዛበት ጊዜ የኖረ ነበር በሮማ በኖረበትም ጊዜ የኖረው በእግዚአብሄር ባለው እምነት ነበር። በሮማ የሚሆነውንም ሆነ የሚካሄደውን ሁሉ አያምንበትም የሚያውቀው ግን አንድ ነገር ነበር ይኸውም ቅዱስ ጳውሎስ ሮማውያን በሚገዙበት ጊዜ ከአይሁድ ራባይነት (ቀናተኛ ፈሪሳዊ) የክርስቶስ ተከታዮቹን ከመጥላትና ከማሳደድ ወደ እውነተኛ ክርስትና እምነት መጥቶ በሐዋሪያነትና ለወንጌል ስባኪነት የተጠራበት ወቅት መሆኑን ነበር። ቅዱስ ጳውሎስ በሮማ ግዛት በነበረበት ወቅት በጥበቃው ሥር በነጻነቱ የተደስተበት ብሎም በዚውያን ወቅት ለወንጌል አገልግሎት በአቅራቢያው ባሉት በትላልቅ ከተሞችና የባህር በሮች የመጓዝ ዕድሎችንም ያገኘበት መሁኑን ያስታውሳል።
ቅዱስ ጳውሎስ ከላይ የተጠቀስውን ድጋፍ በርማ ዜግነቱ የተደረገለት ቢሆንም እንኳ ስለሮማ ግዛት ክፉውን ገጽታውን ደግሞ ሽሽጎ አላለፈም በመደጋገም ግዛት ውስጥ የነበረውን ክፉ ነገር ገልጦታል:: በክርስቲያኑ በአይሁዱ መካከል ያለውን እምነትም ሆነ አኗኗር ገልጦታል። አይሁዶች ለሮማ መንግሥት ቀረጥ መከፍል አይፈልጉም ለቄሳርም እጅ ስጥተው መግዛ አይፈልጉም። ቅዱስ ጳውሎስ ግን ከሮማ ክርስቲያኖች የሚፍልግባቸውን የመንግሥት ቀረጥ እንዲከፍሉ ይመክራቸዋል ለቄሳርም እንዲገዙም ይመክራል በክርስትና በአይሁዲነት መካከልም ልዩነቱን ያሳያቸዋል።
ሮሜ 13፡1-7
ጥቅስ 1 ነፍስ ሁሉ በበላይ ላሉት ባለ ሥልጣኖች ይገዛ።
ቅዱስ ጳውሎስ የሮማ አማኞች/ክርስቲያኖች ለምድራዊ መንግሥት ባለ ሥልጣናት (የሕዝብ ገዢዎች) አስተዳዳሪዎች የአሕዛብ ወይም አረማውያን ለሆኑ ሁሉ ተገዙ ብሎ ይመክራቸዋል። ክርስቲያኖች በአሕዛብ ወይም በአረማውያን ገዢዎች መገዛት የለብንም የሚለው ሃሳባቸው ተከትለው ላለመገዛት ተፈትነዋል። በሮማ ያሉት ክርስቲያኖች እኛ የሚገዛው ለክርስቶስ ነው ብሎው ያምኑ ነበር። በዚያን ጊዜ አሳዳጅ የሆነው ህገር እንኳን የቅዱስ ጳውሎስ ትምህርት የሲቪል አገዛዝ የተስጠው ከእግዚአብሄር ነው የሚለውን እምነቱን አላስቀረውም።
“መገዛት“ የሚለው ቃል በዋናነት ከጥቅስ 1-7 ተጠቅሷል። ነፍስ ሁሉ… የመጀመሪያው ጥቅስ “ነፍስ ሁሉ“ ሲል ክርስቲያኖች ብቻ ሳይሆኑ ማንኛውም የስው ዘር ለመንግሥት የመገዛት ግዴታ እንዳለባቸው ያመለክታል። ክርስቲያኖችም ሆኑ አሕዛብ ወይም አረማውያን አማራጭ የላቸውም ለበላይ መንግሥት መገዛታቸው በፍጹም አስፈላጊነት አለው። ለባለሥልጣናት ሥልጣን የስጠው ከእግዚአብሄር ነው ይህም በቲቶ 3፡1፤ 1 ጴጥ. 2፡13 እና የሐዋ.ሥራ. 5፡29) ተመልክቷል። ቅዱስ ጳውሎስ ለሲቪል መንግሥት መታዘዝን ማስቀረቱ አይደለም ይልቁንም የበለጠ ግልጽ አደረገው እንጂ ይህም 1ጴጥ. 2፡13-13፤ ሮሜ 13፡1-7 ተመልክቷል።
እንደ ቅዱስ ጳውሎስ ትምህርት የሮማ አማኞች/ክርስቲያኖች ለሲቪል መንግሥት መታዘዝ አለባቸው ይሁን እንጂ የሲቪሉ መንግሥት አስራሩ ከእግዚአብሄር መንገድ የወጣ ከሆነ አማኞቹ/ክርስቲያኖቹ የእግዚአብሄርን መንገድ ተከትለው የሚያስከተለውን ውጤት መቀበል ይጠበቅባቸዋል።
ጥቅስ 2 ቅዱስ ጳውሎስ በጥቅስ 2 ላይም በቁጥር 1 “ነፍስ ሁሉ“ ለባለሥልጣናት ከእግዚአብሄር የተስጡ ወይም የተመረጡ ስለሆነ ተገዙ ካለ በኋላ ባለሥልጣናቱ የሚቃወሙ የእግዚአብሄርን ሥርዓት ይቃወማል ካለ በኋላም ለሚቃወሙት ደግሞ በራሳቸው ላይ ፍርድን እንደሚቀበሉ ይናገራል።
በጥቅስ 3 ገዢዎች ለክፉ አድራጊዎች እንጂ መልካምን ለሚያደርጉ የሚያስረሩ አይደሉምና።
ቅዱስ ጳውሎስ በጥቅስ 3 ላይ ግልጽ በሆነ መንገድ ለበላይ በለሥልጣናት ወይም ገዢዎች መልካም ለሚያደርጉ ወይም በመንግሥት ባለሥልጣናት የተስጠው በማህበራዊ ኑሯቸው ምልልስ ውስጥ መልካም ሥነ-ምግባር የሚታይባቸው ዜጎች ገዢዎችን አይፈሩም። ክፉ አድራጊዎች ግን በማህበራዊ ኑሯቸው ምልልስ መጥፎ ሥነ-ምግባር ያላቸው በመንግሥት ባለሥልጣናት የተስጠውን መመሪያ የሚጥሱ ሁሉ በገዢዎች ዘንድ ክፉ ሥራቸው ይገለጣል ብለው ይፈራሉ። ቅዱስ ጳውሎስ በመቀጠል አንባቢውን ይጠይቃል “ባለሥልጣንን እንዳትፈራ ትወዳለህን? ብሎ ከጠየቀ በኋላ ደግሞ ከፍርሃት ለመዳን መልካም ማድረግ ምሥጋናም እንደሚያመጣለት ይመክራል።
ቅዱስ ጳውሎስ ለሮማ ክርስቲያኖች ለቄሳር ለመሳስሉት ነገስታት መገዛት የሚከብድ እንደሆነ እያወቀ ለምን ይህንን ይመክራል? የሚለውን ጥያቄ አንባቢው ቢያነሳ ቅዱስ ጳውሎስ አሁንም የሚመልስው ለማመንና ለመቀበል አስቸጋሪ ቢሆንም እንኳ ከእግዚአብሄር ሕዝብን ለማስተዳደር የተስጡ ስለሆኑ አሁንም ተገዙ የሚለውን መልስ ይስጣል። ቅዱስ ጳውሎስ እንደቄሳር ላሉት ተገዙ ሲል በምንም ዓይነት መንገድ በአማኞች/በክርስቲያኖች በውጪው አካላቸው ላይ ጉዳት ያስከትላል እንጂ የውስጥ ሕሊናቸውን መንካት እንደማይችል ነው። በሮማ አገዛዝ ብዙ ክርስቲያኖች ሕይወት እንደኔሮ አይነቱ በእሳት አቃጥለው እንደገደሏቸው ቅዱስ ጳውሎስ ያውቃል ይህ እንደዚህ አይነቱ ክፉ ደርጊት የተፈጸመው ከግዢዎች ስንፍናና ጨካኝነት የተነሳ ነበር። ጥቅስ 3 እና 4 ላይ ቅዱስ ጳውሎስ የስው መንግሥት አስፈላጊነትና አላማውን ይገልጻል። የስው መንግሥት የሚመስረተው ጥሩውን ለመደገፍ መጥፎውን ደግሞ ለመቅጣት ነው ጥሩውንና መጥፎው የትኛው እንደሆነ የሚወስነው መንግሥት ነው። ቅጹስ ጳውሎስ በነዚህም ጥቅሶች ክርስቲያኖች ሆነው የሮማ ዜግነት ያላቸው ሁሉ መንግሥቱን መታዘዝ ይጠበቅባቸዋል በመታዘዛቸው ታማኝነታቸውን የሚያሳዩት ግን መንግሥት የእግዚአብሔርን ቃል እስካልተቃወመ ድረስ ነው።
ጥቅስ 4 በከንቱ ግን ስይፍ አይታጠቅምና ክፉ ብታደርግ ቁጣውን ለማሳየት ክፉ አድራጊውን የሚበቀል የእግዚአብሄር አገልጋይ ነውና።
በጥቅስ 4 “መታጠቅ“ የሚለው ቃል በዚያን ጊዜ በክፍለ ህገር ውስጥ የሚያገለግሉት ሮማውያን መኮንኖች የሚታጠቁት ስይፍን ያመለክታል። ይህም ትጥቃቸው ምልክቱ ሕግ ተላላፊውን ወይም ክፉ አድራጊውን በሞት የመቅጣት ሥልጣን እንዳላቸውም ያመለክታል። ቅዱስ ጳውሎስ የጠቀስው “ስይፍ“ የሚወክለው መንግሥት ዜጎቹን ለመጠበቅ ወንጀለኞችን ለመቅጣት እንደሆነ ያሳያል። ክርስቲያኖች በመንግሥት ውስጥ ገብተው መሥራት ያለባቸው በመንግሥት በመንግሥቱ ሥርዓት ውስጥ የእግዚአብሄር ቃል የተጠበቀ በሥራ ላይ እንዲውል ለማጠናከር አይነተኛ መንገድ ስለሆነ ነው።
ጥቅስ 5 ስለዚህ ስለቁጣው ብቻ አይደለም ነገር ግን ስለሕሊና ደግሞ መገዛት ግድ ነው።
ቅዱስ ጳውሎስ በጥቅስ 5 ላይ ስለመገዛት ያነሳል። በሮማ ላሉት ቅዱሳን ቅዱስ ጳውሎስ ለመንግሥት እንዲገዙ ይመክራቸዋል። ክርስቲያኖቹ መገዛት ያለባቸው የባለሥልጣናቱ ቁጣ ወደኛ ይደርሳል ብለው ብቻ ሳይሆን መገዛታቸው እንደመታዘዝ ስለሚቆጠር ከሕሊና ወቀሳ ነጻ ስለሚያደርጋቸውና አልፎዖዖም ለመንግሥት ባለመገዛት የተነሳ ከሚመጣውም ችግር የተጠበቁ ስለሚያደርጋቸውም ጭምር ነው። ክርስቲያኖቹ መገዛታቸው ወዴታ ሳይሆን ግድም (ምርጫ የማይስጠበት) እንደሆነ ጥቅሱ ያመለክታል።
ጥቅስ 6 እና 7 ለሁሉ የሚገባውን አስረክቡ ግብር ለሚገባው ግብር ቀረጥ ለሚገባው ቀረጥን መፈራት ለሚገባው መፈራትን ከብር ለሚገባው ክብርን ስጡ።
ቅዱስ ጳውሎስ ግልጽ በሆነ መንገድ የሲቪል መንግሥትን ለመደገፍ እነዚህም ባለሥልጣኖች
በእግዚአብሄር ለሕዝብ አገልግሎት የተስጡ በመሆናቸው በእነዚህ በለሥልጣኖች ለተቋቋመው መንግሥት በሮማ ያሉት ክርስቲያኖች ቀረጣቸውን ለመንግሥት መክፍል እንዳለባቸው ይመክራል ይህም ቀረጥ በሥራ ላይ የሚወለው በጠቅላላው ለሕብረተስቡ ነው። ጥቅስ 7 ላይ ቅዱስ ጳውሎስ ጌታ ኢየሱስ በማርቆስ 12፡17 “የቄሳርን ለቄሳር የእግዚአብሄርንም ለእግዚአብሄር አስረክቡ ካለው ጋር በተመሳሳይ መልዕክት ለሮማ ክርስቲያኖች ይምክራል። ክርስቲያኖች ከሁሉም በላይ ክብር የሚስጡትና የሚፍሩት እግዚአብሄርን ነው ከዚያም እንደ አስፈላጊነቱ ለሁሉ የሚገባውን አስረክቡ በመቀጠልም ግብር ለሚገባው ግብርን ቀርጥ ለሚገባው ቀረጥን መፈራት ለሚገባው ደግሞ መፍራትን ከብር ለሚገባው ደግሞ ክብርን ስጡ ብሎ ይመክራል።
ሮሜ 13፡8-10
ቅዱስ ጳውሎስ በነዚህ ጥቅሶች ውስጥ ክርስቲያኖች የወንድሞቻቸው ባለዕዳዎች እንደሆኑ ያመለክታል። ያለመውደድ ባለ ዕዳ ያደርጋል። ወንድሙን ወይም ሌላውን ግን ሕግን እንደፈጸመ ያመለክታል።
በጥቅስ 8 ገለጻውን የሚጀምረው “ዕዳ አይኑርባቸሁ“ በማለት ነው። ዕዳ ማለት በብድር ከሚያበድር ስው የተገኘ ነው ተበዳሪው ስለ ዕዳው ባስበ ቁጥር ዕዳውን መክፈል የሚችልበትን መንገድ ይፈልጋል። በዚህ ክፍል የተጠቀስው ዕዳ በንብረት ወይም የቁሳቁስ ዕዳ ጋር የተያያዘ ሳይሆን ቅዱስ ጳውሎስ የሚለው በክርስቶስ ፍቅር የመውደድ ዕዳ እንዳለበት ነው። ፍቅር ዕዳ ነው ክርስቲያኖች በየቀኑ በየዕለቱ በየጊዜው እስከኖርን ድረስ የሚከፈል ነው። ክርስቲያኖች ባልንጀራቸውን እንደነፍሳቸው የወደዱ እንደሆነ ከሙሴ ሕግ እንዳለፉ ጥቅስ 9 ውስጥ ቅዱስ ጳውሎስ ያመለክታል።
በሮማ ያሉት አማኞች/ክርስቲያኖች እርስ በርሳቸው የመዋደድ ዕዳ እንዳለባቸው ያመለክታል። ሌላውን የሚወድ ሕግን እንደፈጸመም ያመለክታል። ቅዱስ ጳውሎስ የሚለው የተኛውን ሕግ ነው? የሙሴን ሕግ ማለቱ ነው? ቅዱስ ጳውሎስ ለሚስጠው ትምህርት እንደትራስ የሚጠቀመው የብሉይ ኪዳን እንደሆነ ባለፉት ምዕራፎች ተመልክቷል። በነዚህም ጥቅሶች አሥርቱን ትዕዛዛት አታመንዝር አትግደል አትስረቅ በውሽት አትመስክር አትመኝ ወዘተ. የሚለው ከላይኛይቱ ትዕዛዝ ሁሉ ጋር በዚህ ባልንጀራህን እንደነፍስህ ወደድ የሚለው ቃል ጠቅልሎታል። “ፍቅር“ በክርስቲያኑ የእምነት ጉዞ ውስጥ የያዘውን ከፍተኛ ሥፍራ ለማሳየት ቅዱስ ጳውሎስ ፍቅር የሕግ ፍጻሜ ነው ብሎ ምክሩን ይቋጫል።
በጥቅስ 8 ውስጥ ቅዱስ ጳውሎስ የሚጀምረው “የማንም ዕዳ አይኑርባችሁ“ በማለት ነው። በቅዱስ ጳውሎስ ዘመን የጌታ ጸሎት (አባታችን ሆይ) የሚለውን ጸሎት በተለይም “በደላችንን ይቅር በለን“ የሚለውን በትክክለኛው መንገድ ባለመረዳት ዕዳቸውን የማይከፍሉ ክርስቲያኖች ነበሩ። ይህም ሁኔታቸው በሚኖሩበት ሕብረተስብ ውስጥ መጥፎ ስም ያስጣቸው ነበር። ቅዱስ ጳውሎስ የሚለው ክርስቲያኖችን ዕዳቸሁን ክፍሉ በምትችሉት መንገድ የሚፈልግባችሁን ክፍሉ ብሎ ይመክራቸዋል። ወደ ትዕዛዝ ፍጻሜ የሚደረስው የተባሉትን ሁሉ ለመጠበቅ እውነተኛውን መንገድ “ባልንጀራህን እንደነፍስህ ወደድ“ የተባለውን በመፈጸም ነው ብሎ ቅዱስ ጳውሎስ ይመክራል። ቅዱስ ጳውሎስ በጥቅስ 7 ላይ ስለ ቀረጥ ወይም ግብር ከምድራዊ መንግሥት የሚያገንናኘውን ካነሳ በኋላ በጥቅስ 8 ላይ ከመንፈሳዊ ሕይወት ጋር “ዕዳን“ ያገናኘዋል ይኸውም ክርስቲያኑ የፍቅር ዕዳ እንዳለበት አብሮ ያመለክታል። ቅዱስ ጳውሎስ ፊስካል ፓሊሲ እያወጣ አይደለም በዚያን ዘመን የነበሩት ክርስቲያኖች ያለባቸውን ሕብረተስባዊ ሃላፊነት እንዲወጡ ለማሳወቅ ምክሩ የተስጠበት ነው።
ሮሜ 13፡11-14
ቅዱስ ጳውሎስ በነዚህ ጥቅሶች የሚገልጸው የዘመኑን መቃረብ ወይም የክርስቶስ ምጻት እንደቀረበ ነው። ከዚህም የተነሳ ክርስቲያኖችን ከእንቅልፍ ተነሱ ሲል ከመንፈሳዊ ድካም ወይም ማንቀላፋት ነቅታችሁ ተዘጋጁና መገለጡን ጠብቁ ማለቱ ነው። ካመንበት ጊዜ ይልቅ መዳናችን ዛሬ ወደኛ ቀርቧል ሲል የሚያመለክተው የክርስቶስን መገለጥ ወይም ምጻት መቃረቡን ነው። ሌሊቱ አልፎአል ቀኑም ቀርቧል ሌሊቱ አልፎል የሚለው ጥቅስ ውስጥ “ለሊት“ የሚለው ቃል ክርስቶስ በአለም ያልነበረበትን በዔፌ. 2፡2 እንደተጻፈው አለም ለጨለማው ገዢ ታልፎ የተስጠበትን ያመለክታል። ቀኑ ቀርቧል ከሚለው ጥቅስ ቀን የሚለው ቃል ደግሞ የክርስቶስን ምጻትና ከመጣም በኋላ የጽድቅ መንግሥቱን መስርቶ የሚገዛበትን ወቅት ያመለክታል። ቅዱስ ጳውሎስ የሮማ ክርስቲያኖች የክርስቶስ ምጻት ከመሆኑ በፊት 13፡12-13 የተመለከቱት ጥቅሶች ክርስቲያኖቹ በሕይወታቸው አካባቢ ክፍተት ታይቶ እንደሆነ ሕይወታቸውን እንዲያስተካክሉ ይመክራቸዋል።
ጥቅስ 14 ነገር ግን ጌታን ኢየሱስን ክርስቶስን ልበሱት ምኞቱንም እንደሚፈጽም ለሥጋ አታስቡ። በጥቅስ 14 ላይ ክርስቶስ የሚለው የግል ስም ማቴ. 1፡21 እርሱ ሕዝቡን ከሃጢያታቸው ያድናቸዋልና ስሙን “እየሱስ“ ትለዋለህ ይላል። “ክርስቶስ“ የሚለው ስም የተቅባ ስለሆነ ስለማዳን ሃይሉ ቅዱስ ጴጥሮስ በሐዋ.ሥራ. ምዕራፍ 3 በቤተመቅደስ የተቀመጠን ከሽባነቱ ከተፈወስ በኋላ የሐዋ.ሥራ 3፡13 የአብረሃም የይሳቅ የያዕቆብ አምላክ የአባቶቻችን አምላክ እናንተ አሳልፋቸሁ የስጣችሁትንና ሊፈታው ቆርጦ ስለ በጴላጦስ ፊት የካዳችሁትን ብላቴናውን ኢየሱስን አከበረው ይላል።
ቅዱስ ጳውሎስ በገላትያ 3፡27 ከክርስቶስ ጋር አንድ ትሆኑ ዘንድ የተጠመቃሁ ሁሉ ክርስቶስን ልብሳችሁታል። በሮማ ለሚኖሩ ክርስቲያኖች እንደዚሁ በሮሜ 13፡14 ላይ “ጌታ እየሱስ ክርስቶስን ልበሱት“ ብሎ ምክር ይስጣቸዋል። በቆሮንጦስ ለሚገኙ ክርስቲያኖች በ2 ቆሮ. 13፡5 እራሳቸውን እንዲመረምሩ ወይም እራሳቸውን እንዲፈትኑ ይመክራል በቆላሳያስ ለሚገኙ ክርስቲያኖች አሮጌውን ስው ስለማውለቅ ያነሳል። ቅዱስ ጳውሎስ ለሮማ ክርስቲያኖች ሌሎቹ አብያተክርስቲያናት የመክራቸውን ለነርሱም ይመክራል የሚላቸውም አዳማዊ (ሥጋዊ) ባህሪያትን አውልቃችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ በኩል የሚገኘውን አዲሱን ባህሪያት ልብሳችሁ ጌታ ምጻት በፊት ተዘጋጁ ተለማመዱ ወይም ኑሩት ነው።
በማጠቃለል የዚህ ምዕራፍ አላማ በሮማ ያሉት ክርስቲያኖች የጌታ ሁለተኛ ምጻት እየቀረበ ስለሆነ ከተለያዩ ሃጢያቶች ነጻ ወጥተው አሮጌውን ልብስ አውልቀው አዲሱን ልብስ ክርስቶስን ልብስው (የክርስቶስን ባህሪያት-የመንፈስ ቅዱስ ፍሬዎች ከክርስቶስ ዳግም ምጻት መዘጋጀት እንዳለባቸው ይመክራቸዋል።
ሚስተር ቤንጃሚን የኢሜል ዝርዝሮችን እነሆ ፣ Lfdsloans@outlook.com ፡፡ / ወይም ደግሞ ንግዴን ለመጀመር በ 90,000.00 ዩሮ ብድር የረዳኝ WhatsApp + 1-989-394-3740 እና እኔ በጣም አመስጋኝ ነኝ ፣ እዚህ አንድ ነጠላ እናት ነገሮች እንዳላደረጉ መንገድ ለመፍጠር እየሞከርኩ ነው ፡፡ ከእኔ ጋር ቀላል ይሁኑ ግን ንግዴ እየጠነከረ ሲመጣ እና እያሰፋ ሲሄድ እያየሁ በሚስተር ሚስተር እርዳታ ፊቴ ላይ ፈገግታ አሳየኝ ፡፡ የገንዘብ ድጋፍን መፈለግ ወይም በዚያ ንግድ ውስጥ መከራን ማለፍ ወይም የመነሻ የንግድ ሥራ ፕሮጀክት መጀመር መፈለግ ይህንን ማየት እና ከችግራቸው ለመውጣት ተስፋ ሊኖረው ይችላል ... እናመሰግናለን ፡፡
ReplyDelete