ጋኖች አለቁና ...[1]
ጋኖች አለቁና ምንቸቶች ጋን ሆኑ ብዬ ተነስቼ፤
የሚያመጣውን መዝዝ ሳላጤን ተግቼ ስርቼ፣
ተምሳሌቱን ለመረዳት መጣፍ አገላብጬ፣
ተረዳሁ እራሴን አንዳከረርኩ ከእውነቱ ወጥቼ።
ድውሮውኑ ልዩነቱን ሳልረዳ፣
በተምሳሌቱ መካከል ያለውን አረም ሳላጸዳ፣
ነገር ብከረክም ምን ዋጋ አለው ቀረሁ ሆኜ ባለዕዳ።
የመጣውን መዘዝ ማስታረቅ አቅቶኝ፤
ቀን ከሌት አወጣሁ አወረድኩ ሃሳቤን በቅቶኝ።
በጨረቃ ወጣሁ ከሃሳቤ ጋር ልደራደር፣
ምን ያደርጋል ክኡዝ ጋር ብነጋገር፣
መልስ አላገኘሁ እዲሁ ቀረሁ ስደናቆር።
ይበጀኛል ብዬ ከጠቢብ ጋር ልማከር ተነሳሁ፣
ጠቢብ ስው ከሀገሬ ስው መሃክል ማተርኩ፣
ምንም ቁም ነገር የሚያወራ አላገኘሁ፣
ይሄን ጊዜ ወደ ፈጣሪዬ ፊቴን መለስኩ፣
ለጥያቄዬ በድንገት በሃሳቤ መልስ አገኘሁ።
ጋኖች አልቀው ምንቸቶች ጋን ሆኑ የሚለውን ትችቴን ትቼ፣
በስው እኩልነት አመንኩ አስረግጬ።
እኔ ከልምዴ ልምከርህ!
በስው እኩልነት የምታምን ከሆነ፣
ወዲያ ወዲህ ስትል ጊዜህ ከባከነ፣
ወደ እውነት ተመለስ መግቢያው በር አልተከለከለ።
0 comments:
Post a Comment