በዶ/ር አመለወርቅ
እየሄድኩ ሳለ የወንጌል ጎዳና
እየሄድኩ ሳለ የሕይወት ጎዳና ፣
እያሄድኩ ሳለ የወንጌል ጎዳና፣
እየሄድኩ ሳለ የፍቅር ጎዳና፣
እየሄድኩ ሳለ የስላም ጎዳና፣
በሕይወቴ ስላም በመስፈኑ፣
ጠላቶቼ በቅናት ተቃጠሉ፣
እኔንም ወደ አዘቅት ለመጣል ወሰኑ፣
ምክር ተማከሩ፣ እንዲህም ተባባሉ፣
ኑ እንምክርበት ከአግልግሎት፣
እናስወግደው በምላስ ጅራፍ እንምታው አሉ፣
አንዳሉትም አደረጉብኝ፣
እኔም ስው በመሆኔ ልቤ አዘነባቸው፣
የውስጠኛው ልቤ አለቀስባቸው፣
በዚሁ ትካዜ ተውጬ እያለሁ፣
ልጄ ሆይ አይዞህ አትዘን ብሎ፣
ጌታዬ በቃሉ መጣና ልቤን ደገፈው፣
ቃሉንም ላከና ወስጤን ፈወስው፣
በአውሎ ነፋስ ውስጥ መንገድ አለኝ፣
እኔ የወጣትነት አምላክ ብቻ አይደለሁም፣
የርጅናም ግዜ አምላክህ ነኝ አለኝ፣
ልጄ ሆይ አትስጋ እኔ አኖርሃለሁ፣
ምድርና ሞላው የኔ አይደለምን?
ምን ገዶኝ መኖሪያህን እኔ አዘጋጀዋለሁ፣
ከዚህ በህዋላ ልቤ በሃሴት ተሞላ፣
እኔም ለአምላኬ ምላሼን ስጠሁ እንዲህም አልኩት፣
እየሄድኩ ሳለ በህይወት ጎዳና፣
እየሄድኩ ሳለ በጥበብ ጎዳና፣
እየሄድኩ ስለ በወንጌል ጎዳና፣
ጠላቶቼ መጥተው አሰናከሉኝ፣
አምላኬ አንተ! መጣህና ድል አቀዳጀኸኝ።
ተመስገን አምላኬ እስግድልሃለሁ፡
ጌታዬና አምላኬ አምባዬ እልሃለሁ።
0 comments:
Post a Comment