Tuesday, December 8, 2020

 

ጥበበኛና አስተዋይ ስለመሆን

ከእናንተ ጥበበኛና አስተዋይ ማን ነው? በመልካም አንዋ[]ዋሩ ሥራውን በጥበብ የዋህነት ያሳይ።ያዕ. 3:13

ጥበበኛ እንደሆነ አድርገህ የምትመለከተው ማንን ነው? ምናልባት ወላጆችህን፣ በዕድሜ የገፉ ሰዎችን አሊያም የኮሌጅ ፕሮፌሰሮችን ይሆን? አስተዳደግህና በአካባቢህ ያሉት ሁኔታዎች ጥበበኛ እንደሆነ ስለምታስበው ሰው ባለህ አመለካከት ላይ ተጽዕኖ ያሳድሩ ይሆናል። ይሁን እንጂ የአምላክን አገልጋዮች በዋነኝነት የሚያሳስባቸው አንድን ሰው በእግዚአብሄር ዓይን ጥበበኛ ነው እንዲባል የሚያደርገው ነገር ነው።

 ዓለም ጥበበኛ እንደሆኑ አድርጎ የሚቆጥራቸው ሰዎች ሁሉ በአምላክ ዘንድ ጥበበኛ ላይሆኑ ይችላሉ። ለምሳሌ ያህል፣ ኢዮብ ንግግራቸው ጥበብ የተሞላበት እንደሆነ አድርገው ከሚቆጥሩ ሰዎች ጋር የተወያየ ቢሆንምከመካከላቸው አንድም ጠቢብ እንዳላገኘተናግሯል። (ኢዮብ 17:10) ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ የአምላክን እውቀት ለመቀበል ፈቃደኛ ስላልሆኑ አንዳንድ ሰዎች ሲጽፍጥበበኞች ነን ቢሉም፣ ሞኞች ሆኑብሏል። (ሮሜ 1:22) በተጨማሪም ይሖዋ ራሱ በነቢዩ ኢሳይያስ አማካኝነትበራሳቸውም አመለካከት ጥበበኛ ለሆኑ ወዮላቸው!” በማለት ተናግሯል።ኢሳ. 5:21

 በግልጽ ለመረዳት እንደሚቻለው አንድን ሰው ጠቢብ የሚያሰኘውና የአምላክን ሞገስ የሚያስገኝለት ምን መሆኑን ማወቃችን አስፈላጊ ነው። ይህን በተመለከተ ምሳሌ 9:10 የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው፤ ቅዱሱንም ማወቅ ማስተዋል ነው ይላል። ጥበበኛ ሰው ለአምላክ ተገቢ የሆነ ፍርሃት ሊያድርበትና ላወጣቸው መሥፈርቶች አክብሮት ሊኖረው ይገባል። ይሁን እንጂ አምላክ መኖሩንና ያወጣቸው መሥፈርቶች እንዳሉ አምኖ መቀበል ብቻ በቂ አይደለም። ደቀ መዝሙሩ ያዕቆብ ይህን በተመለከተ ትኩረት የሚስብ ሐሳብ ተናግሯል። (ያዕቆብ 3:13  አንብብ።) ‘በመልካም አኗኗሩ ሥራውን ያሳይየሚለውን አገላለጽ ልብ በል። እውነተኛ ጥበብ በየዕለቱ በምታከናውናቸው ነገሮችና በንግግርህ መንጸባረቅ ይኖርበታል።

 እውነተኛ ጥበብ ጥሩ የማመዛዘን ችሎታ ማዳበርን እንዲሁም እውቀትንና ማስተዋልን ውጤታማ በሆነ መንገድ መጠቀምን ይጨምራል። እንዲህ ዓይነቱ ጥበብ እንዳለን ማሳየት የምንችለው እንዴት ነው? ያዕቆብ ጥበበኛ መሆናችንን ማሳየት የምንችልባቸውን የተለያዩ መንገዶች ዘርዝሯል።* ያዕቆብ ከእምነት አጋሮቻችንም ሆነ ከጉባኤ ውጪ ካሉ ሰዎች ጋር ጥሩ ግንኙነት እንዲኖረን የሚረዳ ምን ምክር ሰጥቶናል?

ድርጊታችን እውነተኛ ጥበብ እንዳለን ያሳያል

 ያዕቆብ ጥበብን ከመልካም አኗኗር ጋር አያይዞ መግለጹን ማስታወሳችን ጠቃሚ ነው። የጥበብ መጀመሪያ  እግዚአብሄርን መፍራት በመሆኑ ጥበበኛ የሆነ ሰው ከአምላክ መንገድና መሥፈርት ጋር ተስማምቶ ለመኖር ይጥራል። አምላካዊ ጥበብ በተፈጥሮ የምናገኘው ባሕርይ አይደለም። ይሁን እንጂ መጽሐፍ ቅዱስን አዘውትረን ማጥናታችንና ማሰላሰላችን ይህን ባሕርይ እንድናዳብር የሚያስችለን ከመሆኑም ሌላ በኤፌሶን 5:1 ላይ እንደተገለጸውአምላክን እንድንመስልይረዳናል። እግዚአብሄርን ይበልጥ እየመሰልነው በሄድን መጠን ድርጊታችን ጥበብ የሚንጸባረቅበት ይሆናል። የእግዚአብሄር መንገድ ከሰዎች መንገድ እጅግ የላቀ ነው። (ኢሳ. 55:8, 9) እግዚአብሄር ነገሮችን የሚያከናውንበትን መንገድ የምንኮርጅ ከሆነ ከክርስቲያን ጉባኤ ውጪ ያሉ ሰዎች ከሌሎች የተለየን መሆናችንን ያስተውላሉ።

ቅዱስ  ያዕቆብ እግዚአብሄርን የምንመስልበት አንዱ መንገድ ከጥበብ የመነጨ የዋህነት ማሳየት መሆኑን ገልጿል። የዋህነት ገር መሆንን የሚጠይቅ ቢሆንም አንድ ክርስቲያን አስፈላጊ በሚሆንበት ጊዜ ጥብቅና ጠንካራ የሥነ ምግባር አቋም ሊኖረው ይገባል። ይህ ደግሞ ሚዛናዊ እንዲሆን ይረዳዋል። እግዚአብሄር ገደብ የለሽ ኃይል ያለው ቢሆንም የዋህ ስለሆነ ወደ እሱ ለመቅረብ አንፈራም። የእግዚአብሄር ልጅ የአባቱን የየዋህነት ባሕርይ በሚገባ በማንጸባረቁ እንዲህ ለማለት ችሏል:- “እናንት ሸክም የከበዳችሁና የደከማችሁ ሁሉ ወደ እኔ ኑ፤ እኔም ዕረፍት እሰጣችኋለሁ። ቀንበሬን ተሸከሙ፤ ከእኔም ተማሩ፤ እኔ በልቤ የዋህና ትሑት ነኝና፤ ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ።ማቴ. 11:28, 29 ፊልጵ. 2:5-8

 መጽሐፍ ቅዱስ የዋህነትን ወይም ትሕትናን በማሳየት ረገድ ግሩም ምሳሌ ስለሆኑ ሰዎች ይናገራል። ከእነዚህ ሰዎች መካከል አንዱ ሙሴ ነው። ሙሴ ትልቅ ኃላፊነት የነበረው ሰው ቢሆንምበምድር ላይ ካሉት ሰዎች ሁሉ ይልቅ እጅግ ትሑትእንደሆነ ተገልጿል። (ዘኍ. 11:29 12:3) በተጨማሪም እግዚአብሄር ፈቃዱን መፈጸም እንዲችል ለሙሴ ታላቅ ኃይል ሰጥቶት እንደነበር አስታውስ። እግዚአብሄር ዓላማውን ለማስፈጸም የዋህ ወይም ትሑት በሆኑ ሰዎች ይጠቀማል። በግልጽ ለማየት እንደሚቻለው ፍጹማን ያልሆኑ ሰዎች ከጥበብ የመነጨ የዋህነት ማሳየት ይችላሉ። እኛስ ይህን ባሕርይ በማሳየት ረገድ ማሻሻያ ማድረግ የምንችለው እንዴት ነው? ገርነት ወይም የዋህነት የእግዚአብሄር ቅዱስ መንፈስ የሚያፈራው ፍሬ ክፍል ነው። (ገላ. 5:22, 23) እግዚአብሔር  የዋህነትን ይበልጥ ማንጸባረቅ እንድንችል እንደሚረዳን በመተማመን መንፈሱን እንዲሰጠን መጸለይና ይህን ባሕርይ ለማዳበር የታሰበበት ጥረት ማድረግ እንችላለን። ዘማሪው ‘[አምላክ] ለትሑታን መንገዱን ያስተምራቸዋልበማለት መናገሩ ይህን እንድናደርግ ያነሳሳናል። መዝ. 25:9   የሆነ ሆኖ የዋህነትን በማሳየት ረገድ ማሻሻያ ማድረግ ልባዊ ጥረት ሊጠይቅ ይችላል። አንዳንዶቻችን በአስተዳደጋችን የተነሳ ይህንን ባሕርይ ማሳየት ይከብደን ይሆናል። ከዚህም በላይ በአካባቢያችን ያሉት ሰዎች ለሚደርስብን ነገርእሾህን በእሾህእንድንመልስ በማበረታታት የዋሆች እንዳንሆን ይገፋፉናል። ይሁን እንጂ ይህ የጥበብ እርምጃ ነው? ቤትህ ውስጥ እሳት ቢነሳ እሳቱን የምታጠፋው በነዳጅ ነው ወይስ በውኃ? እሳቱ ላይ ነዳጅ መጨመር ቃጠሎውን ይበልጥ ያባብሰዋል፤ ውኃ ግን ሊያጠፋው ይችላል። በተመሳሳይም መጽሐፍ ቅዱስየለዘበ መልስ ቍጣን ያበርዳል፤ ክፉ ቃል ግን ቍጣን ይጭራልየሚል ምክር ይሰጠናል። (ምሳሌ 15:1, 18) በጉባኤ ውስጥም ሆነ ከጉባኤ ውጪ አለመግባባት ሲያጋጥመን ጉዳዩን በየዋህነት በመፍታት እውነተኛ ጥበብ እንዳለን ማሳየት እንችላለን።2 ጢሞ. 2:24  ቀደም ሲል እንደተጠቀሰው የዓለም መንፈስ ተጽዕኖ ያሳደረባቸው ብዙ ሰዎች ገር፣ ሰላማዊና የተረጋጉ አይደሉም። በዙሪያችን ያሉት አብዛኞቹ ሰዎች ቁጡና ዕብሪተኞች ናቸው። ያዕቆብ ይህን ያውቅ ስለነበር በጉባኤ ውስጥ የሚገኙ ሰዎች በዚህ ዓይነቱ መንፈስ እንዳይበከሉ አስጠንቅቋል።

ጥበበኛ ያልሆኑ ሰዎች የሚያሳዩት ባሕርይ

 ቅዱስ ያዕቆብ ከአምላካዊ ጥበብ ጋር የሚቃረኑ ባሕርያትን አስመልክቶ በግልጽ ጽፏል። (ያዕቆብ 3:14 አንብብ።) ቅንዓትና ጭቅጭቅ መንፈሳዊ አስተሳሰብ የሌላቸው ሰዎች የሚያንጸባርቋቸው ባሕርያት ናቸው። ሥጋዊ አስተሳሰብ እያየለ ሲሄድ ምን ሊከሰት እንደሚችል ተመልከት። ክርስቲያን ነን የሚሉ ስድስት ቡድኖች ኢየሱስ የተገደለበትና የተቀበረበት ሥፍራ ነው ተብሎ በሚታሰብ ቦታ ላይ የተገነባን አንድ ሕንፃ የተለያዩ ክፍሎች ይዘው ነበር። በእነዚህ ቡድኖች መካከል ለረጅም ጊዜ የዘለቀ አለመግባባት ነበር።  ይህን የመሰለው ያለመግባባት መንፈስ በእውነተኛ የክርስቲያን ጉባኤ ውስጥ መታየት የለበትም። ያም ሆኖ አንዳንዶች በአለፍጽምና ምክንያት እኔ ያልኩት ካልሆነ የሚል ስሜት ሊያንጸባርቁ ይታያሉ። ይህ ደግሞ ወደ ጠብና ግጭት ሊያመራ ይችላል። ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በቆሮንቶስ ጉባኤ ውስጥ እንዲህ ያለውን ሁኔታ ተመልክቶ ስለነበር እንዲህ ሲል ጽፏል:- “በመካከላችሁ ቅናትና ክርክር አለ፤ ታዲያ፣ ሥጋውያን መሆናችሁ አይደለምን? ተግባራችሁስ እንደ ማንኛውም ሰው ተግባር መሆኑ አይደለምን?” (1 ቆሮ. 3:3) በመጀመሪያው መቶ ዘመን በነበረው በዚህ ጉባኤ ውስጥ ይህ አሳዛኝ ሁኔታ ለተወሰነ ጊዜ ያህል ቆይቶ ነበር። በመሆኑም ዛሬም እንዲህ ያለው መንፈስ ወደ ጉባኤ እንዳይገባ ጥንቃቄ ማድረግ ይኖርብናል።  እንዲህ ያለው መንፈስ ወደ ክርስቲያን ጉባኤ ሰርጎ ሊገባ የሚችለው እንዴት ነው? ጥቃቅን በሚመስሉ ነገሮች ሊጀምር ይችላል። ለምሳሌ ያህል፣  የወንጌል አገልግሎትን ወይም  የቤተክርስቲያን የሽማአግሌዎች ምርጫን በተመለከተ እንዴት መካሄድ አለበት በሚለው ጉዳይ ላይ የአመለካከት ልዩነት ሊፈጠር ይችላል። አንድ ወንድም፣ ያቀረበው ሐሳብ ተቀባይነት ባለማግኘቱ ምክንያት ሊበሳጭና ምናልባትም የተደረጉትን ውሳኔዎች መተቸት ሊጀምር ይችላል። ከዚያም አልፎ ምንም ዓይነት ሥራ ላለመሥራት ይወስን ይሆናል! እንዲህ የሚያደርግ ሰው፣ ከጉባኤ ጋር የተያያዙ ሥራዎች ስኬታማ መሆናቸው የተመካው በጉባኤ ውስጥ በሚኖረው የሰላም መንፈስ እንጂ በአሠራር ዘዴው ላይ አለመሆኑን ዘንግቷል። የእግዚአብሄርን ሞገስ የሚያስገኘው ተጨቃጫቂ መሆን ሳይሆን የየዋህነት መንፈስ ማሳየት ነው።1 ጢሞ. 6:4, 5 በያዕቆብ 3:15, 16 ላይ ተመዝግቦ የሚገኘው በመንፈስ አነሳሽነት የተጻፈ ምክር አስፈላጊ እንደሆነ የሚሰማህ ለምንድን ነው?  አንድ ሰው እንዲህ ያለ ባሕርይ እንዲያሳይ ምክንያት የሚሆኑ ሌሎች ሁኔታዎችም ሊኖሩ እንደሚችሉ ግልጽ ነው። ይሁን እንጂ ሁኔታው ምንም ይሁን ምን እነዚህን ባሕርያት ላለማሳየት መጣር ይኖርብናል። (ያዕቆብ 3:15, 16 አንብብ።) ደቀ መዝሙሩ ቅዱስ ያዕቆብ እንዲህ ያሉት ባሕርያት ሥጋዊ አስተሳሰብ የሚንጸባረቅባቸውና ከሰማይ ከሆነችው ጥበብ የራቁ በመሆናቸውከምድርእንደሆኑ ተናግሯል። እንዲሁም የማሰብ ችሎታ የሌላቸው እንስሳት የሚያሳዩአቸውና ከሥጋዊ አስተሳሰብ የሚመነጩ ስለሆኑከሥጋእንደሆኑ ተገልጿል። ከዚህም በተጨማሪ የአምላክ ጠላት የሆኑትን መንፈሳዊ ፍጥረታት አስተሳሰብ የሚያንጸባርቁ ስለሆኑከአጋንንትናቸው። አንድ ክርስቲያን እንዲህ ያሉ ባሕርያትን ማንጸባረቁ ፈጽሞ ተገቢ አይደለም። እያንዳንዱ የጉባኤ አባል ራሱን መመርመርና እንዲህ ያሉ ባሕርያትን ለማስወገድ ጥረት ማድረግ ይኖርበታል። ፓስተሮች፣ ወንጌላውያን፣ ዲያቆናትና ሽማግሌዎች፣ በጉባኤ ውስጥ አስተማሪዎች እንደመሆናቸው መጠን ከአሉታዊ አመለካከቶች ራሳቸውን መጠበቃቸው እጅግ አስፈላጊ ነው። ባለብን አለፍጽምና እንዲሁም ዓለም በሚያሳድርብን ተጽዕኖ የተነሳ እነዚህን ባሕርያት ማስወገድ ብርቱ ጥረት ይጠይቃል። እንዲህ ማድረግ አንድን የሚያዳልጥ ዳገት ከመውጣት ጋር ሊመሳሰል ይችላል። ዳገቱን ስንወጣ አንድ የምንይዘው ነገር ከሌለ ወደኋላ ልንንሸራተት እንችላለን። ይሁንና በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኘውን ምክር በጥብቅ በመከተል የእግዚአብሄር ጉባኤ በሚሰጠን እርዳታ በመታገዝ ወደፊት መግፋት እንችላለን። መዝ. 73:23, 24

ጥበበኛ የሆነ ሰው ለማፍራት የሚጥራቸው ባሕርያት

 ያዕቆብ 3:1 አንብብ።ከሰማይ የሆነችው ጥበብከምታፈራቸው ባሕርያት መካከል አንዳንዶቹን በመመርመር ጥቅም ማግኘት እንችላለን። ንጹሕ መሆን ሲባል በድርጊታችንም ሆነ በአስተሳሰባችን ከመጥፎ ነገሮች መራቅን ይጨምራል። ከክፉ ነገሮች ለመራቅ ፈጣን መሆን ይኖርብናል። እንዲህ ማድረግ ቅጽበታዊ እርምጃ መውሰድ ይጠይቃል። አንድ ሰው ጣቱን ወደ ዓይንህ ቢሰነዝር ወዲያውኑ ፊትህን ታዞራለህ ወይም ዓይንህን በእጅህ ትከልላለህ። ይህ ቅጽበታዊ እርምጃ ነው። እንዲህ የምታደርገው አስበህ አይደለም። መጥፎ ነገሮች ሲያጋጥሙን የምንወስደው እርምጃም ተመሳሳይ መሆን ይኖርበታል። ንጽሕናችንን ጠብቀን ለመኖር ያለን ጠንካራ ፍላጎትና በመጽሐፍ ቅዱስ የሠለጠነው ሕሊናችን፣ ከመጥፎ ነገሮች ወዲያውኑ ዞር እንድንል ሊያደርጉን ይገባል። (ሮሜ 12:9) መጽሐፍ ቅዱስ ዮሴፍንና ኢየሱስን ጨምሮ ይህን የመሰለ እርምጃ ስለወሰዱ ሰዎች የሚገልጹ ምሳሌዎችን ይዟል። ዘፍ. 39:7-9 ማቴ. 4:8-10

 በተጨማሪም መለኮታዊ ጥበብ ሰላማዊ እንድንሆን ያደርገናል። ይህ ደግሞ እንደ ንዴትና ቁጣ ያሉትን ባሕርያት ማስወገድን እንዲሁም ሰላም የሚያደፈርሱ ድርጊቶችን ከመፈጸም መቆጠብን ይጨምራል። ቅዱስ ያዕቆብ በዚህ ረገድ ተጨማሪ ሐሳብ ሲሰጥየጽድቅም ፍሬ ሰላምን ለሚያደርጉ በሰላም ይዘራልብሏል። (ያዕ. 3:18) ‘ሰላም አድራጊዎችወይም ሰላም ፈጣሪዎች የሚለውን አገላለጽ ልብ በል። በጉባኤ ውስጥ የምንታወቀው ሰላም ፈጣሪ በመሆን ነው ወይስ ችግር ፈጣሪ? ብዙውን ጊዜ ከሌሎች ጋር እንጋጫለን? በቀላሉ  ሌሎችን የምናስከፋ ነን? ሌሎች የእኛን አመለካከት እንዲቀበሉ እናስገድዳለን ወይስ ሌሎችን ቅር የሚያሰኙ ባሕርያት ካሉን ለማስወገድ በትሕትና ጥረት እናደርጋለን? በሰዎች ዘንድ የምንታወቀው ከሌሎች ጋር ያለንን ሰላም ለመጠበቅ ጥረት የምናደርግ፣ ቂም የማንይዝና ይቅር ለማለት ፈጣኖች በመሆናችን ነው? ራሳችንን በሐቀኝነት መመርመራችን መለኮታዊ ጥበብ በማሳየት ረገድ ምን ማሻሻያ ማድረግ እንዳለብን እንድንገነዘብ ይረዳናል።

ቅዱስ  ያዕቆብ ከሰማይ የሆነችው ጥበብ ከምታንጸባርቃቸው ባሕርያት መካከል አንዱታጋሽነት’ ‘ምክንያታዊነትመሆኑን ገልጿል። ግልጽ የሆነ መጽሐፍ ቅዱሳዊና መሠረታዊ ሥርዓት በማይኖርበት ጊዜ ሌሎች የእኛን አቋም እንዲቀበሉ ከመጫን እንርቃለን? በሌሎች ዘንድ የምንታወቀው የዋህና በቀላሉ የምንቀረብ በመሆናችን ነው? እነዚህ ነገሮች ምክንያታዊ ሰዎች እንደሆንን የሚያሳዩ ናቸው።

 ክርስቲያኖች ቅዱስ ያዕቆብ የገለጻቸውን አምላካዊ ባሕርያት ለማንጸባረቅ ይበልጥ ሲጥሩ በጉባኤው ውስጥ እጅግ አስደሳች ሁኔታ ይኖራል! (መዝ. 133:1-3) የዋህ፣ ሰላማዊና ምክንያታዊ መሆናችን ከሌሎች ጋር ያለንን ግንኙነት የሚያሻሽለው ከመሆኑም ባሻገርከሰማይ በሆነችው ጥበብእንደምንመራ በግልጽ ያሳያል።  በጥቅሱ ዙሪያ ያለው ሐሳብ ያዕቆብ መልእክቱን በዋነኝነት የጻፈው ለጉባኤ ሽማግሌዎች ወይምአስተማሪዎችእንደሆነ ይጠቁማል። (ያዕ. 3:1) እነዚህ ሰዎች አምላካዊ ጥበብ በማሳየት ረገድ ምሳሌ መሆን ነበረባቸው። ይሁንና ሁላችንም ከዚህ ምክር ትምህርት ማግኘት እንችላለን።

 

0 comments:

Post a Comment