Thursday, March 28, 2019


ሕሊናህን ጠብቅ


 ሥነ-ምግባር ( ቀጥተኛ ባህርይ-morale) ብዙ ምድብ የሆነ ቃል ነው።  ብዙውን ጊዜ የስነ-ጥበብ እና የሥነ-ጥበብ ሥራዎችን ባህሪይ ማስተማር እና ጠቃሚ ትምህርቶችን ለመግለፅ ያገለግላል. ስለ ባህላዊና ማህበራዊ ዓለምአቀፋዊ ገላጭ ስዕሎች፣ በተለይም ለየት ባለ ማህበረሰቦች በተለይም ትክክለኛና የተሳሳተ ምግባራትን የሚያስቀምጡ የባህሪዎችን ልማዶች እና ደንቦች ያመለክታል። በተለምዶ የሥነ-ምግባር  ስርዓተ-ዋልታ እና ተጨባጭ ነፀብራቅ ነው፤ ምን ዓይነት ባህሪያት እና መስፈርቶች ለተወሰኑ ኤጀንቶች እና ማህበረሰቦች እና እንዴት እነዚህ ደረጃዎች በህብረተሰብ አባላት እንዴት እንደሚባዛቱ መወሰን፣  ከዚህ አንጻር ሥነ ምግባራዊ ሁኔታ የግለሰብና የኅብረተሰብ ህይወት ትክክለኛውን ልምምድ የሚያመለክት ሲሆን "መልካም ህይወት" ምን ማለት እንደሆነ እና እንዴት ማግኘት መቻል እንዳለበት ያዛል።  ይህን በሚያደርጉበት ጊዜ የሞራል ስብዕና በተገቢው ደረጃ ላይ ያሉትን ባህላዊ  ሃይማኖታዊ እና የንድፈ ሀሳቦች ዓለም እሴቶች ላይ ያተኩራል።

 ሥነ-ምግባር ልክ እንደ ታሪኩ ምድብ

 ሥነ-ምግባር / morality ማለት ተቀባይነት ያለው የሰው ባህሪያትን ("የሰው ልጅ ባህሪያት") ለመግለፅ ጥቅም ላይ የዋለ የማህበራዊ ንድፈ ሐሳብ ማለት ነው፤ ከዚህ አንጻር የሥነ ምግባር አቋም በእንዲህ ዓይነቱ ማኅበረሰብ ውስጥ የተለመዱ ሕጎች ትክክል ወይም ስህተት የሆነውን ለመወሰን የሚጠቀሙባቸውን ባሕሎችና መሠረታዊ ሥርዓቶች ይገልፃል፤ ውጫዊ ደረጃ ላይ፣ ሥነ-ምግባር በኅብረተሰቡ ውስጥ ከሰዎች ጋር በሚኖረን ግንኙነት እና ማህበራዊ ሁኔታዎች ውስጥ እንዴት እርምጃ መወሰድ እንደሚቻል የሚናገሩ ልማዶችን እና የተለመዱ ልማዶችን ሊያመለክት ይችላል። እነዚህ ልምዶች  በአጠቃላይ በንድፈ-ሀሳብና በአዕምሮአዊ መሠረት ላይ ያርፋሉ፣ አንዳንድ ጊዜ የዓለም አተያይ ተብሎ የሚጠራ፣ እሱም የህብረተሰቡን ውስጣዊ እምነቶች እና እሴቶች ይገልጻል። ኤሚል ደኬምሄ (1858-1917) ይህንን " የጋራ ንቃተ-ህሊና" በማለት በመጥራት "በአማካይ የኅብረተሰብ ማህበረሰብ አባላት አጠቃላይ እምነቶች እና ስሜቶች በአጠቃላይ ህይወት ያለው የራሱ የሆነ ስርዓት ነው" ([1893 ] 1984 ገጽ 38-39)።  እንዲህ ዓይነቱ የዓለም እይታ ዘዴ ግለሰቦች እና ማህበራዊ ቡድኖች ሆን ተብሎ የተደረጉ እርምጃዎችን የሚወስዱባቸውን  እሴቶች ያኖራል፤ የግለሰብ እና የጋራ ድርጊቶች እነዚህን ተግባሮች ከሚፈጽሙባቸው ወይም ከሚፈለገው ሁኔታ ጋር የሚጣጣሙ ናቸው፣ የእምነቶች እና የአዕድሮቻቸው አመጣጥ ፍላጎትን ለማጠናከር ፣ ለሚመጡት ትውልዶች ደንቦችን እንደገና ማራመድ፣ እና በማጭበርበር ባህሪ ውስጥ ግልጽ እና ቀጥተኛ ዕዳዎች ላይ ጫና ይፈጥራል።

የተዛባ የኮምፒውተር ፕሮግራም እንዳለው በሚታወቅ አውሮፕላን ተሳፍሮ ለመሄድ የሚደፍር ሰው እንደማይኖር የታወቀ ነው። ይሁን እንጂ አንድ ሰው የአውሮፕላኑን የበረራ መቆጣጠሪያ ሥርዓት ቢያዛባ ወይም መረጃዎቹን ሆን ብሎ በሐሰት መረጃዎች ቢቀይርስ! ይህ ሁኔታ አንድ አካል በሕሊናህ ላይ ጥቃት ለመሰንዘር እያደረገ ካለው ሙከራ ጋር በእጅጉ ይመሳሰላል። የምትመራበትን የሥነ ምግባር ደንብ ለማበላሸት ቆርጦ ተነስቷል። ዓላማው ከአምላክ ጋር የሚያጋጭህን ጎዳና እንድትከተል ማድረግ ነው!—ኢዮብ 2:2-5፤ ዮሐንስ 8:44

ለመሆኑ ይህ ክፉ ጠላት ማን ነው? በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ “ዓለሙንም ሁሉ የሚያስተው፣ ዲያብሎስና ሰይጣን . . . እርሱም የቀደመው እባብ” ተብሎ ተጠርቷል። (ራእይ 12:9 ) በኤደን የአትክልት ሥፍራ የሐሰት ምክንያት በማቅረብ ሔዋን ትክክል እንደሆነ የምታውቀውን ነገር ችላ እንድትልና በአምላክ ላይ እንድታምፅ ባግባባት ጊዜ በድርጊት ታይቷል። (ዘፍጥረት 3:1-6፣ 16-19) ከዚያን ጊዜ ወዲህ ሰይጣን ሰዎች በጅምላ የአምላክ ጠላት እንዲሆኑ ለማድረግ የሚገለገልባቸውን የማሳሳቻ ድርጅቶች በሙሉ ሲያቋቁምና ሲመራ ቆይቷል። ከእነዚህ የማሳሳቻ ድርጅቶች መካከል በግንባር ቀደምትነት የሚጠቀሰው የሐሰት ሃይማኖት ነው።2 ቆሮንቶስ 11:14, 15



የተዛባ እምነትና  ሕሊና

የተዛባ እምነት የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል በሆነው በራእይ መጽሐፍ ውስጥ ታላቂቱ ባቢሎን ተብላ በምትጠራ ምሳሌያዊ ጋለሞታ ተመስላለች። ትምህርቶቿ የብዙ ሰዎችን የሥነ ምግባር ስሜት በማዛባት ከእነርሱ የተለየ እምነት ያላቸውን ሰዎች እንዲጠሉ አልፎ ተርፎም የጭካኔ ድርጊት እንዲፈጽሙባቸው አድርገዋል።

ኢየሱስ የተዛባ እምነት የአንዳንዶችን የሥነ ምግባር አቋም ምን ያህል ሊያዛባ እንደሚችል ለደቀ መዛሙርቱ ሲነግራቸው “የሚገድላችሁ ሁሉ እግዚአብሔርን እንደሚያገለግል የሚመስልበት ጊዜ ይመጣል” ብሏል። እንደነዚህ ያሉት ዓመፀኛ ግለሰቦች በሥነ ምግባር መበላሽትግ ምንኛ የታወሩ ናቸው! ኢየሱስ “አብንና እኔን ስላላወቁ ነው” ብሏል። (ዮሐንስ 16:2፣ 3) ኢየሱስ እነዚህን ቃላት ተናግሮ ብዙም ሳይቆይ ለሠሩት ወንጀል ሕሊናቸው እንዳይቆረቁራቸው ራሳቸውን ማሳመን በቻሉ አንዳንድ የሃይማኖት መሪዎች ገፋፊነት ተገደለ። (ዮሐንስ 11:47-50) ከዚህ በተቃራኒ ኢየሱስ እውነተኛ ተከታዮቹ በመካከላቸው ባለው ፍቅር ተለይተው እንደሚታወቁ ተናግሯል። ያም ሆኖ ፍቅራቸው ጠላቶቻቸውን ሳይቀር እስከመውደድ ሰፊ መሆን ነበረበት። ማቴዎስ 5:44-48፤ ዮሐንስ 13:35

የተዛባ እምነት የብዙዎችን ሕሊና ያበላሸበት ሌላው መንገድ ብዙሃኑ የሚፈልገውን ዓይነት ሥነ ምግባር በማስተማር ነው። ለዚያውም ሥነ ምግባር የሚባል ነገር ካላቸው ነው። ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ይህን በተመለከተ ትንቢት ሲናገር “ሕይወት የሚገኝበትን [“ጤናማ፣ ] ትምህርት የማይታገሡበት ዘመን ይመጣልና፤ ነገር ግን ጆሮቻቸውን የሚያሳክክ ስለ ሆነ፣ እንደ ገዛ ምኞታቸው ለራሳቸው አስተማሪዎችን ያከማቻሉ” ብሏል።2 ጢሞቴዎስ 4:3

በዛሬው ጊዜ የእምነት መሪዎች እግዚአብሄር ከጋብቻ ውጪ የሚደረግን የጾታ ግንኙነት አይቃወምም ብለው በማስተማር የሰዎችን ጆሮ ያክካሉ። የቤተ ክርስቲያን መሪዎች የመጽሐፍ ቅዱስን ሥነ ምግባር ችላ ካሉና ቤተ ክርስቲያናቸውም ከዚያ ያለፈ ነገር ካላደረገ ተከታዮቻቸው ምን ዓይነት የአቋም ደረጃ ይከተላሉ ብለን ልንጠብቅ እንችላለን? በሚልዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ጨርሶ ግራ ቢጋቡ ምንም አያስደንቅም።

በመብራት ምልክቶች በተመሰሉት የሥነ ምግባር ደንቦችና መጽሐፍ ቅዱስ በሚያስተምረው መንፈሳዊ እውነቶች መመራት ምንኛ የተሻለ ነው! (መዝሙር 43:3፤ ዮሐንስ 17:17) ለምሳሌ ያህል መጽሐፍ ቅዱስ አመንዝሮችም ሆኑ ዝሙት የሚሠሩ ሰዎች ‘የእግዚአብሄርን መንግሥት እንደማይወርሱ’ ያስተምራል። (1 ቆሮንቶስ 6:9፣ 10) ‘ለባሕርያቸው የሚገባውን ሥራ ለባሕርያቸው በማይገባው የለወጡ’ ወንዶችና ሴቶች ሥራቸው በእግዚአብሄር ፊት “ነውር” እንደሆነ ይነግረናል። (ሮሜ 1:26፣ 27፣ 32) ይህ ፍጹም ያልሆኑ ሰዎች የፈጠሩት የሥነ ምግባር እውነት አይደለም፤ እግዚአብሄር ፈጽሞ የማይሽረው በመንፈስ አነሳሽነት ያስጻፈው የአቋም ደረጃ ነው። (ገላትያ 1:8፤ 2 ጢሞቴዎስ 3:16) ሆኖም ሰይጣን ሕሊናን የሚያበላሽበት ሌሎች መንገዶችም አሉት።

በመዝናኛ ረገድ መራጮች ሁኑ

አንድ ሰው መጥፎ ድርጊት እንዲፈጽም ማስገደድ አንድ ነገር ነው፤ መጥፎ ድርጊት የመፈጸም ፍላጎት እንዲያድርበት ማድረግ ግን ከዚያ የከፋ ነው። “የዚህ ዓለም ገዥ” የሆነው የሰይጣን ግብም ይኸው ነው። የረከሰ አስተሳሰቡን ሞኞች በሆኑ ወይም ባልጠረጠሩ ሰዎች በተለይ ደግሞ ይበልጥ ለጥቃት በተጋለጡት ወጣቶች አእምሮና ልብ ውስጥ ለመቅረጽ አጠያያቂ የሆኑ ጽሑፎችን፣ ፊልሞችን፣ ሙዚቃዎችን፣ የኮምፒውተር ጨዋታዎችን እንዲሁም በኢንተርኔት የሚተላለፉ ወሲባዊ ሥዕሎችን በመሰሉ መንገዶች ይጠቀማል።ዮሐንስ 14:30፤ ኤፌሶን 2:1፣ 2

አንድ መጽሔት  ላይ የወጣ አንድ ሪፖርት “[በዩናይትድ ስቴትስ የሚኖሩ] ወጣቶች በየዓመቱ 10, 000 የሚያክሉ የዓመፅ ድርጊቶችን የሚመለከቱ ሲሆን ለልጆች የሚተላለፉ ፕሮግራሞች ደግሞ የበለጠ በጭከና ድርጊቶች የተሞሉ ናቸው” በማለት ይገልጻል። በተጨማሪም ሪፖርቱ “በአሥራዎቹ ዕድሜ የሚገኙ ወጣቶች በየዓመቱ 15, 000 የብልግና ፊልሞች፣ የሽሙጥ አነጋገሮችንና ቀልዶችን ይመለከታሉ” በማለት ገልጿል። ብዙ ተመልካች በሚኖርበት ምሽት ላይ የሚተላለፉ የቴሌቪዥን ፕሮግራሞች እንኳን “በአንድ ሰዓት ጊዜ ውስጥ ከ8 የሚበልጡ የጾታ ግንኙነት ድርጊቶችን የሚያሳዩ ሲሆን ይህም በ1976 ከነበረው በአራት እጥፍ ይበልጣል” በማለት ጠቅሷል። ጥናቱ የሚተላለፉት “ጸያፍ ንግግሮችም በሚያስደንቅ መጠን ጨምረዋል” ብሎ መናገሩ ብዙም የሚያስገርም አይደለም። ያም ሆኖ መጽሐፍ ቅዱስም ሆነ ብዛት ያላቸው ሳይንሳዊ ጥናቶች እነዚህን ፕሮግራሞች አዘውትሮ መመልከት ሰዎችን ይበልጥ እንደሚያበላሿቸው ያስጠነቅቃሉ። ስለዚህ አምላክን ማስደሰትና ራስህን መጥቀም የምትፈልግ ከሆነ “አጥብቀህ ልብህን ጠብቅ፣ የሕይወት መውጫ ከእርሱ ነውና” የሚለውን በምሳሌ 4:23 ላይ የሚገኘውን ምክር ተከተል።ኢሳይያስ 48:17

በብዙዎች ዘንድ ተወዳጅነትን ያተረፉ በርካታ ሙዚቃዎችም ሕሊናን ያበላሻሉ። በዚህ መንገድ የሚመላለሱ ሰዎች ሕሊናቸውን ስለሚያበላሹና ውሎ አድሮ የአምላክ ጠላቶች የሚያደርጋቸው ‘ክፉ ልብ’ በውስጣቸው እንዲፈጠር ስለሚፈቅዱ እንዲህ ማድረግ እንደማትፈልግ የታወቀ ነው። ዕብራውያን 3:12፤ ማቴዎስ 12:33-35። ስለዚህ መዝናኛን በመምረጥ ረገድ ጠንቃቃ ሁን። መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ በማለት በጥብቅ ያሳስበናል:- “በቀረውስ፣ ወንድሞች ሆይ፣ እውነተኛ የሆነውን ነገር ሁሉ፣ ጭምትነት ያለበትን ነገር ሁሉ፣ ጽድቅ የሆነውን ነገር ሁሉ፣ ንጹሕ የሆነውን ነገር ሁሉ፣ ፍቅር ያለበትን ነገር ሁሉ፣ መልካም ወሬ ያለበትን ነገር ሁሉ፣ በጎነት ቢሆን ምስጋናም ቢሆን፣ እነዚህን አስቡ።”ፊልጵስዩስ 4:8

ጤናማ ፍርሃትን ጨምሮ ለእግዚአብሄር ፍቅርና እምነት ስናዳብር ሕሊናችንን የመጠበቅ ፍላጎት እንዳለን እናሳያለን። (ምሳሌ 8:13፤ 1 ዮሐንስ 5:3) እነዚህ ባሕርያት የጎደሉት ሕሊና ሥነ ምግባራዊ ጥንካሬ እንደማይኖረው መጽሐፍ ቅዱስ ይገልጻል። ለምሳሌ ያህል መዝሙር 14:1 በልባቸው “እግዚአብሄር የለም” ስለሚሉ ሰዎች ይናገራል። እንዲህ ያለው የእምነት ማጣት ጠባያቸውን የሚነካው እንዴት ነው? ጥቅሱ በመቀጠል “በሥራቸው ረከሱ፣ ጎሰቈሉ፤ በጎ ነገርን የሚሠራ የለም” ይላል።

በእግዚአብሄር ላይ እውነተኛ እምነት የሌላቸው ሰዎች ወደፊት የተሻለ ጊዜ እንደሚመጣ የጸና ተስፋ አይኖራቸውም። ስለሆነም ሥጋዊ ምኞቶቻቸውን በማርካት ለዛሬ ብቻ መኖር ይፈልጋሉ። ፍልስፍናቸው “ነገ እንሞታለንና እንብላና እንጠጣ” የሚል ነው። (1 ቆሮንቶስ 15:32) በሌላ በኩል ግን ትኩረታቸውን በዘላለም ሕይወት ሽልማት ላይ ያደረጉ ሰዎች ብልጭ ብሎ በሚጠፋ የዓለም ደስታ አይዘናጉም። የሰለጠነው ሕሊናቸው በትክክል እንደሚሠራ የበረራ ኮምፒውተር ከአምላክ የታማኝነት ጎዳና ዝንፍ ሳይሉ መጓዛቸውን እንዲቀጥሉ ይረዳቸዋል። ፊልጵስዩስ 3:8

ሕሊናህ በሙሉ ኃይሉ በትክክል መሥራቱን እንዲቀጥል ከተፈለገ ከእግዚአብሄር ቃል ዘወትር መመሪያ ማግኘት ይኖርበታል። መጽሐፍ ቅዱስ ይህ መመሪያ የሚገኝበትን መንገድ “ወደ ቀኝም ወደ ግራም ፈቀቅ ብትል ጆሮችህ በኋላህ:- መንገዱ ይህች ናት በእርስዋም ሂድ የሚለውን ቃል ይሰማሉ” በማለት ይናገራል። (ኢሳይያስ 30:21) ስለሆነም መጽሐፍ ቅዱስን በየዕለቱ ለማንበብ ጊዜ መድብ። ይህም ትክክል የሆነውን ለማድረግ ትግል በምታደርግበት ወይም ስጋት በሚሰማህና በጭንቀት በምትዋጥበት ጊዜ ጥንካሬና ብርታት እንድታገኝ ይረዳሃል። ሙሉ በሙሉ በእግዚአብሄር ላይ የምትተማመን ከሆነ በሥነ ምግባርም ሆነ በመንፈሳዊ እንደሚመራህ እርግጠኛ ሁን። አዎን “ሁልጊዜ እግዚአብሔርን በፊቴ አየዋለሁ፤ በቀኜ ነውና አልታወክም” በማለት የጻፈውን መዝሙራዊ ምሳሌ ተማር። መዝሙር 16:8፤ 55:22።

የልጅ ፈቃድና ህሊና

በእግዚአብሄር ቃል ኪዳን ላይ በመቆም የልጅን ፈቃድ ማስልጠን ይችላሉ፤ ወላጆች ይህንን  ታላቅ የጥሪያቸውን ሥራ በሚያከናውኑበት ጊዜ በእግዚአብሄር መልኮታዊ ሃይል በመታመንና በመመካቱ ወደሙላቱ መድረስ የእምነታቸው መስረት አድርገው ከሆነ በልጆቻቸው ህይወት የልፋታቸውን ውጤት ያያሉ።

ወላጆች አንድን ድርጊት ከማድረጋቸው ወይም ከመወስናቸው በፊት አብረው ለምን ያንን እርምጃ እንደወስዱ ማስተማር ለልጆቻቸው ይጠቅማል። ይህም ማለት ልጆችን ለምን ክፉን እንቢ እንዲሉ ድግሞም ለመምረጥ እንዲችሉ ይረድዋቸዋል ማለት ነው።

እውነተኛ ትምህርት ውጤት ታየ የሚባለው በልጆች ህይወት ውስጥ ልጁ እራሱን ማስተማር ሲጀመር ነው፤ ስለዚህ የሥነምግባር ሥልጠናው ማቀናጀት ያለበት በልጁ ህይወት ውስጥ እራስን መግዛት (ጠማዩን መቆጣጠር) ሲችልና በውስጡ ተቆጣጣሪ የሆነው ህሊናውን መስማት ሲችል ነው። ህሊና ሁልጊዜ የሚያከናውነው ጥሩና መልካሙን የሆነውን ነገር በልጁ ሃሳብ ውስጥ ማስቀመጥ ነው፤ ግን ሁልጊዜ ትክክለኛ የሆነውን ብቻ አያስተምርም። አ ዕምሮ በአመለካከቱ ወይም ነገሮችን በማስተዋሉ በስህተት መልክ ሊሆን ይችላል፣እንዲያውም በህሊናው ልጁ መጥፎ መርጦ ጥሩን እንቢ የሚልበት ጊዜ አለ። 

የልጁ ሕሊና አንዳንድ ጊዜ ሊሳሳት ይችላል። ለምን? አንድ ኮምፓስ በብረት ከተሠራ ዕቃ አጠገብ ቢቀመጥ ወደ ሰሜን ሳይሆን ወደ ሌላ አቅጣጫ ሊያመለክት ይችላል። በተጨማሪም ኮምፓሱ ይበልጥ ጥቅም የሚኖረው ከትክክለኛ ካርታ ጋር ተቀናጅቶ ከተሠራበት ነው። በተመሳሳይም የልጁ ሕሊና የራስ ወዳድነት ምኞት ከተሸነፈ ወደተሳሳተ አቅጣጫ ይመራዋል። ከዚህም በላይ የልጅ ሕሊና በልጅነቱ በእግዚአብሄር ቃል ካልስልጠነ በእግዚአብሄር ቃል ውስጥ ከሚገኘው አስተማማኝ መመሪያ ጋር ተቀናጅቶ እንዲሠራ ካላደረገ አስፈላጊ በሆኑ በርካታ ጉዳዮች ረገድ ትክክል የሆነውን ነገር ከስህተቱ መለየት ሊያቅተው ይችላል። በእርግጥም ሕሊናችን በትክክል እንዲሠራ ከተፈለገ የእግዚአብሄርን ቅዱስ መንፈስ አመራር ማግኘት ያስፈልገናል። ጳውሎስ ‘ሕሊናዬ በመንፈስ ቅዱስ በመመራት ከእኔ ጋር ሆኖ ይመሠክርልኛል’ በማለት ጽፏል። (ሮም 9:1) ታዲያ ሕሊናችን ከእግዚአብሄር ቅዱስ መንፈስ ጋር ሙሉ በሙሉ እንዲስማማ ማድረግ የምንችለው እንዴት ነው?

ሕሊናችንን በማሠልጠን

ሕሊናችን ከተፈጥሮ ያገኘነው ስጦታ ቢሆንም እንኳ እክል አለበት። ፍጹም ጅምር የነበራቸው የሰው ልጆች የኋላ ኋላ “ኀጢአትን ሠርተዋል፤ የእግዚአብሔርም ክብር ጐድሎአቸዋል።” (ሮሜ 3:23) ሕሊናችን በኃጢአትና ባለፍጽምና የቆሸሸ በመሆኑ የተዛባና መጀመሪያ በታቀደለት መልኩ በትክክል የማይሠራ ሊሆን ይችላል። (ሮሜ 7:18-23) በተጨማሪም ውጫዊ ሁኔታዎች በሕሊናችን ላይ ተጽዕኖ ሊያደርጉ ይችላሉ። አስተዳደጋችን፣ ባሕላችን፣ እምነትና የምንኖርበት አካባቢ ሕሊናችንን ይቀርጹታል። እውነት ነው በዓለም ላይ የሚታየው ወራዳ የሥነ ምግባር ደንብና እያሽቆለቆለ የሄደው የአቋም ደረጃ የጥሩ ሕሊና መለኪያ ሊሆኑ አይችሉም። ስለሆነም ክርስቲያን ወላጅ የልጁን ሕሊናውን ለማሠልጠን የአምላክ ቃል በሆነው በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኘው የማይለዋወጥና ትክክለኛ መሥፈርት ተጨማሪ እርዳታ ያስፈልገዋል። እንዲህ ዓይነቱ መሥፈርት ሕሊናችን ሁኔታዎችን በትክክል እንዲያመዛዝንና ቀና የሆነ እርምጃ እንዲወስድ መመሪያ ይሆነዋል። (2 ጢሞቴዎስ 3:16) ሕሊናችን አምላክ ባወጣቸው መሥፈርቶች ሲመራ “መልካሙን ከክፉው ለመለየት” በማስቻል ከሥነ ምግባር ውጪ የሆኑ ጎጂ ድርጊቶችን ከመፈጸም ይጠብቀናል። (ዕብራውያን 5:14) ሕሊናችን አምላክ ባወጣቸው መሥፈርቶች እስካልሠለጠነ ድረስ ወደ መጥፎ ሁኔታዎች ስናመራ ማስጠንቀቂያ ላይሰጠን ይችላል። መጽሐፍ ቅዱስ “ለሰው ቀና መስሎ የሚታይ መንገድ አለ፤ በመጨረሻ ግን ወደ ሞት ይመራል” ሲል ይገልጻል። ምሳሌ 16:25፤ 17:20

ሕሊናችን እንዲረዳን ከፈለግን የሚሰጠንን ማስጠንቀቂያ ተቀብለን ተግባራዊ ማድረግ ይገባናል። በመጽሐፍ ቅዱስ ከሠለጠነው ሕሊናችን መጠቀም የምንችለው ማስጠንቀቂያውን ሰምተን አፋጣኝ ምላሽ ስንሰጥ ብቻ ነው። የሠለጠነ ሕሊና የአንድን መኪና ሁኔታ ከሚቆጣጠሩ ጠቋሚ መሣሪያዎች ጋር ሊመሳሰል ይችላል። ለምሳሌ ያህል፣ የዘይት ግፊት አመልካቹ የዘይቱ ግፊት መቀነሱን የሚጠቁም የማስጠንቀቂያ መብራት እያሳየን ነው እንበል። በዚህ ወቅት ለሁኔታው ትኩረት ከመስጠት ይልቅ መኪናውን ማሽከርከር ብንቀጥልስ? በሞተሩ ላይ ከባድ ጉዳት ሊደርስ ይችላል። በተመሳሳይም ሕሊናችን ወይም በውስጣችን ያለው ድምፅ አንድ የተሳሳተ እርምጃ እየወሰድን እንዳለ የሚጠቁም ማስጠንቀቂያ ይሰጠን ይሆናል። ሕሊናችን ያደረግነውን ወይም ልንወስደው ያሰብነውን እርምጃ ከቅዱስ ጽሑፋዊ መሥፈርቶችና የሥነ ምግባር ደረጃዎች ጋር በማወዳደር ልክ እንደ ጠቋሚ መሣሪያው የማስጠንቀቂያ መብራት ያሳየናል። ማስጠንቀቂያውን ሰምተን እርምጃ መውሰዳችን መጥፎ ድርጊት ከሚያስከትልብን መዘዝ የሚጠብቀን ከመሆኑም ባሻገር ሕሊናችን በተገቢው ሁኔታ መሥራቱን እንዲቀጥል ያደርገዋል።

ወላጆችም ሆኑ ልጆች በህሊናቸው የሚስጣቸውን ማስጠንቀቂያውን ችላ ቢሉትስ? ቀስ በቀስ ሕሊናቸው ይደነዝዛል። ሕሊናን በተደጋጋሚ ችላ ማለት ወይም አፍኖ መያዝ የሚያስከትለው ውጤት ሰውነትን በጋለ ብረት ከመጥበስ ጋር ይመሳሰላል። በተጠበሰው የሰውነት ክፍል ላይ ያሉት የነርቭ ሴሎች ስለሚሞቱ ሥፍራው ይደነዝዛል። (1 ጢሞቴዎስ 4:2) የደነዘዘ ሕሊናም ኀጢአት ስንሠራ አይወቅሰንም እንዲሁም ኀጢአቱን እንዳንደግም ማስጠንቀቂያ መስጠቱን ያቆማል። ጠባሳ ያለበት ሕሊና መጽሐፍ ቅዱስ ትክክልና ስህተት ስለሆኑ ነገሮች ያወጣውን የአቋም ደረጃ ችላ ስለሚል መጥፎ ሕሊና ይሆናል። በተጨማሪም ባለቤቱ ‘ደንዝዞ’ ከአምላክ ስለራቀ ሕሊናው የረከሰ ነው ሊባል ይችላል። (ኤፌሶን 4:17-19፤ ቲቶ 1:15) እንዴት ያለ አሳዛኝ ውጤት ነው!

በጎ ወይም ንጹሕ ሕሊና እንደያዙ መኖር ጥረት ማድረግ ይጠይቃል። ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ “በእግዚአብሔርና በሰው ፊት ንጹሕ ኅሊና እንዲኖረኝ ሁልጊዜ እጥራለሁ” በማለት ገልጿል። (የሐዋርያት ሥራ 24:16) ቅዱስ ጳውሎስ ክርስቲያን እንደመሆኑ መጠን እግዚአብሄርን ላለማሳዘን ሲል ያለመታከት ራሱን ይመረምርና አካሄዱን ያስተካክል ነበር። የምንሠራው ነገር ትክክል መሆንና አለመሆኑን የሚወስነው አምላክ እንደሆነም ያውቅ ነበር። (ሮሜ 14:10-12፤ 1 ቆሮንቶስ 4:4) በመሆኑም “ስለ ራሳችን መልስ መስጠት በሚገባን በእርሱ ፊት ሁሉም ነገር የተራቈተና የተገለጠ ነው” ብሏል። ዕብራውያን 4:13።  ቅዱስ ጳውሎስ ሰዎችን ቅር የሚያሰኝ ነገር ማድረግ እንደማይገባንም ተናግሯል። ለቆሮንቶስ ክርስቲያኖች “ለጣዖት የተሠዋ ሥጋ ስለ መብላት” የሰጣቸው ማሳሰቢያ ለዚህ ተስማሚ ምሳሌ ይሆናል። ጳውሎስ ለማስገንዘብ የፈለገው ነጥብ አንዳንድ ድርጊቶች ከአምላክ ቃል ጋር የማይቃረኑ ቢሆኑም እንኳ የሌሎችን ሕሊና ግምት ውስጥ ማስገባት ተገቢ መሆኑን ነው። ይህን አለማድረግ ‘ክርስቶስ የሞተለት ወንድማችን በመንፈሳዊ እንዲጠፋ’ ምክንያት ሊሆን ይችላል፤ በተጨማሪም ከአምላክ ጋር ያለንን ወዳጅነት ያበላሽብናል።1 ቆሮንቶስ 8:4, 11-13፤ 10:23, 24

ወላጅ የራሱንም ሆነ የልጁን ህሊና ማሠልጠንህን ማቅዋረጥ የለበትም ምንጊዜም ክርስቲያን ወላጅም ሆነ ልጁ በጎ ሕሊና ሊኖራቸው ይገባል፤ወላጅ ውሳኔ ሲያደርግ የእግዚአብሄርን መመሪያ ለማግኘት ጥረት ማድረግ ይኖርባቸዋል። (ያዕቆብ 1:5) የእግዚአብሄርን ቃል በቤተስብ ማጥናት፤ በተጨማሪም ወላጆች ልጆቻቸውን ያጠኑት የእግዚአብሄር ቃል መመሪያው አእምሮአቸውንና ልብባቸው እንዲቀርጽ እንደፈቅዱለት ክትትልና ማበረታቻ መስጠት ከሁሉም በላይ መጸለይ። (ምሳሌ 2:3-5) ልጆች ከበድ ያሉ ጉዳዮች  ሲገጥሟቸው ከሁኔታው ጋር ተዛማጅነት ያላቸውን የመጽሐፍ ቅዱስ መሠረታዊ ሥርዓቶች በተገቢው መንገድ መረዳታቸውን ለማረጋገጥ ወላጆች ምክር ቢስጥዋቸው ይረዳቸውል። የወላጅና የልጆች ግንኙነትና መተማመናቸው የስመረና ግልጽ ከሆነ ልጆች በወላጆቻቸው ምክርና የእንዲጠቀሙ ይሆናሉ (ምሳሌ 12:15፤ ሮሜ 14:1፤ ገላትያ 6:5) ልጁ ባደረገው ውሳኔ ሕሊናው ላይ ምን ተጽዕኖ እንደሚያሳድርና ከሌሎች ከሁሉም በላይ ደግሞ ከእግዚአብሄር ጋር ያለውን ግንኙነት እንዴት እንደሚነካው አብሮ ማየትም ያስፈልጋቸውል 1 ጢሞቴዎስ 1:5, 18, 19

የወላጆችም ሆነ የልጆች ሕሊናቸው ከአፍቃሪው ሰማያዊ አባታችን ከእግዚአብሄር ያገኘነው ድንቅ ስጦታ ነው። ይህን ስጦታ ከሰጪው ፈቃድ ጋር በሚስማማ መንገድ በመጠቀም ወደ ፈጣሪያችን ይበልጥ እንቅረብ። ልጆች በድርጊታቸው ሁሉ “በጎ ኅሊና” እንዲኖራቸው እንዲጥሩ በእግዚአብሄር አምሳል መፈጠራቸው በግልጽ እንዲያሳዩ ወላጆች ማስልጠንና ማበረታታት ያስፈልጋቸዋል።1 ጴጥሮስ 3:16፤ ቆላስይስ 3:10

ከላይ ያነሳሁት የልጆችን ህሊና የማስልጠኑ ተግባር ልጆችን በእግዚአብሄር ዙፋንና ወደ እግዚአብሄር ፈቃድ የሚያደርስዋቸው ይሆናሉ። ወላጅ የክፉና የደግ ነገር ትርጉሙ ሲገባው በልጁ ህይወት ሁለት የተለያዩ ሃያላት በህይወቱ ሥፍራ ለመያዝ  እንደሚታገሉ መረዳቱ ነው። በህይወት ጉዞ ውስጥ ክፉና ደጉን መመረጥ ለአጭር ወይም ለተወስነ ጊዜ ብቻ ሳይሆን ለረጅምና እስከኖርን ድረስ በዕየለቱ የሚገጥመን ነው። ወላጆች ይህንን በመረዳት በየእለቱ ከእግዚአብሄር የተስጣቸውን አደራ በመረዳት ልጆቻቸው በዚህ ሃሳብ ላይ እንዲነቃ መመሪያ በመስጠት በማበረታታት የልጁን ፈቃድ ማጎልበት ያስፈልጋቸዋል።

ወላጆች ይህ አነስተኛ ነው ብለው ስዎች የሚገምቱትን ተግባር ልጃቸው አድርጎት ሲያዩት ልጃቸው ከዚህ የበለጠ ነገር በህይወቱ እንደሚፈጽም ይገነዘባሉ። ይህ አውቆና ፈቅዶ ክፉን ትቶ ደጉን መምረጥ በልጆች ህይወት ውስጥ እግዚአብሄርንና ቅድስናውንና የዘላለም ህይወትን መምረጥ ማለት ነው።

ዉድ ወላጆች ሆይ! የእግዚአብሄር ታላቅ ስጦታ ለስው ልጆች የመምረጡ ነጻነት በፈቃደኛነቱ አምላኩን ለማምለክ የመምረጡ ነጻነት ነው። ስለዚህ እናንተ ወላጆች እግዚአብሄር ከስጣችሁ ከዚህ ታላቅ ሃላፊነት መካከል የልጆቻችሁን ፈቃድ ወደዚህ ለማድረስ እግዚአብሄር የልጆቻችሁ ፈቃድ አስልጣኞች አድርጎ ሾሞአችህዋል። የምታስለጥኑበትም በመምከርና በመምራት በመረዳት ልይ በተመስረተ መመሪያ ነው። ይህንን በምታደርጉበት ጊዜ ልጃችሁን ለእግዚአብሄር አግልግሎት አስለጠናችህዋቸው ማለት ነው። ይህንን ስታደርጉ የራሳችሁንም ብቁ አለመሆናችሁንም እየተመለከታችሁ ከድካማችሁ የተነሳ የራሳችሁ ደካማነት የልጁን ፈቃድ ማስልጠኛ ደካማ እንዳያደርገውም አብራችሁ ማወቅ የሚገባችሁ ጉዳይ አንዱ ከመሆኑም ሌላ ቅዱስ ጳውሎስ መፈስ ቅዱስ በድካማችን ያግዘናል የሚለውን ቃል መመሪያችሁ አድርጋችሁ በመውስድ የልጆቻችሁ መታደስ መለወጥ ከመንፈስ ቅዱስ ሥራ የተነሳ እንደሆነም አብሮ ማየቱ አስፈላጊ ነው። በመጨረሻው ስጦታችሁና ደስታችሁ ሊሆን የሚገባው ልጃችሁ ከራሳችሁ ፈቃድ የተነሳ ጥሩን ሲምርጡና እግዚአብሄርንም ሲመርጡ ነው።

ደካማ ሕሊና

ቅዱስ ጳውሎስ “አንድ ሰው አንዱን ቀን ከሌላው የተሻለ ቅዱስ አድርጎ ይቈጥራል፤ ሌላው ደግሞ ቀኖች ሁሉ እኩል እንደ ሆኑ ያስባል” በማለት ሌላም ሁኔታ ጠቅሷል። (ሮሜ 14:5ሀ) በሙሴ ሕግ መሠረት በሰንበት ሥራ መሥራት ክልክል ነበር። ሌላው ቀርቶ ወደ ሩቅ ቦታ መጓዝ ፈጽሞ የተከለከለ ነበር። (ዘፀአት 20:8-10፤ ማቴዎስ 24:20፤ የሐዋርያት ሥራ 1:12) ሕጉ ከተወገደ በኋላ ግን እነዚህ ደንቦች ተሻሩ። ይሁንና አንዳንድ አይሁዳውያን ክርስቲያኖች በፊት ቅዱስ አድርገው ይመለከቱት በነበረው ቀን ማንኛውንም ዓይነት ሥራ መሥራት ወይም ረጅም ርቀት መጓዝ ሳይከብዳቸው አልቀረም። በአምላክ ዓይን ሲታይ የሰንበት ሕግ የተሻረ ቢሆንም እንኳ እነዚህ ሰዎች ክርስትናን ከተቀበሉ በኋላም ሰባተኛውን ቀን ለመንፈሳዊ ጉዳዮች ብቻ ለማዋል ወስነው ሊሆን ይችላል። እንዲህ ማድረጋቸው ስህተት ነበር? ሰንበትን ማክበር መለኮታዊ ግዴታ ነው የሚል አቋም እስካልያዙ ድረስ ስህተት አልነበረም። ስለዚህ ቅዱስ ጳውሎስ ለክርስቲያን ወንድሞቹ ሕሊና ከነበረው አሳቢነት የተነሳ “እያንዳንዱ የራሱን ውሳኔ ልብ ብሎ ይወስን” ሲል ጽፏል። ሮሜ 14:5ለ ... 9፣ 10. ክርስቲያኖች ምን ከማድረግ መቆጠብ ይኖርባቸዋል?  ከላይ እንዳየነው ቅዱስ ጳውሎስ ክርስቲያናዊ መሠረታዊ ሥርዓት እስካልተጣሰ ድረስ የምርጫ ልዩነት መኖሩ ለአንድነት ስጋት መፍጠር እንደሌለበት ገልጿል። ስለዚህ ቅዱስ ጳውሎስ ደካማ ሕሊና ላላቸው ክርስቲያኖች “በወንድምህ ላይ ለምን ትፈርዳለህ?” የሚል ጥያቄ አቀረበላቸው። በእምነት የጎለመሱትን ደግሞ (ምናልባትም ሕጉ ይከለክላቸው የነበሩትን አንዳንድ ምግቦች ለመመገብ ወይም በሰንበት ሥራ ለመሥራት ሕሊናቸው የፈቀደላቸው ክርስቲያኖችን) “ለምንስ ወንድምህን ትንቃለህ?” ሲል ጠየቃቸው። (ሮሜ 14:10) ቅዱስ ጳውሎስ ደካማ ሕሊና ያላቸው ክርስቲያኖች ሰፋ ያለ አመለካከት ያላቸው ወንድሞቻቸውን ከመኰነን መቆጠብ ይገባቸዋል ማለቱ ነበር። በሌላ በኩል ደግሞ ጠንካራ የሆኑ ክርስቲያኖች በአንዳንድ ጉዳዮች ሕሊናቸው አሁንም ደካማ የሆነውን ክርስቲያኖች በንቀት መመልከት አይኖርባቸውም። ሁሉም የሌሎችን ትክክለኛ ውስጣዊ ዝንባሌ ማክበርና ‘ከሆኑት በላይ ራሳቸውን ከፍ አድርገው እንዳያስቡ’ መጠንቀቅ ይኖርባቸዋል።ሮሜ 12:3፣ 18

ይቀጥላል...

0 comments:

Post a Comment