ስዎች አዋዊ እንደሆንኩ ነገሩኝ፣
የሚመጣብኝን መዘዝ አላወኩኝ።
አወኩ አወኩ ብዬ፣
በውቀቴ ሳይሆን በትዕቢት ተታልዬ፣
ምን ጠቀመኝ ቀረሁ ከስው ተገልዬ።
በእውቀት ማማ ላይ ቆሜ፣
የትዕቢትን ሽማ አገልድሜ፣
ነገሮችን ማየት ጀመርኩ ያላቅሜ።
በውቀት ትዕቢት ተነፍቼ፣
ማየት አቃተኝ አቋረጬ፣
ምን ያደርጋል በቅንነት አልስራሁ ተግቼ።
ያቀለምኩት እውቀቴ ሻግቶ፣
እውቀቴ መና ቀረ ተንከራቶ፣
ሊያድግ ሲገባው ትንስራፍቶ።
እኔ የምመክርህ!
በውቀት መታበይ ካላወጣ፣
ፈጥነህ ውጣ ከዚህ ጣጣ።
0 comments:
Post a Comment