የክፋት ጥግ[1]
እኔ አላምንም በክፋት ጥግ በስሌቱ፣
ስንቱ ወደቆ ከመንገድ ቀረ በከንቱ።
አላወኩ ክፋት ጥግ አለው ለካ፣
እጠነቀቅ ነበረ እንዳልነካካ። 
አወይ ሞኝነቴ እራሴ ስጥቼ ህዝቤን ማገልገሌ፣
ምን አገኘሁ አስቆጠረኝ እንጂ እደሞኙ ገሌ።
በስደት ምድር የህዝቤን ሽክሙን ተሽከሜ፣
ኑሮው እንዲቃና መልካም ህልም አልሜ፣
ህዝቤ በክፋቱ ከመንገድ አስቀረኝ ከተለምኩት ህልሜ። 
አምናለሁ ህልሜ ህልም ብቻ ሆኖ አይቀረም፣
የህዝቤ ክፋቱ ቢያይልም።
በሕይወቴ የኔ ቀን መጥቶ፣
የክፋት ስሌት በመልካም ተወጦ፣
ከክፋት ይልቅ ጽድቅ ተንስራፍቶ፣
የህዝቤ በክፋት የታወረው አይኑ በርቶ፣
ከክፋት ደግነት ማየሉን ተረድቶ፣
ከክፋቱ ከወጣ እራሱን መክሮና አበርትቶ፣
ያኔ ህልሜ ከግቡ ይደርሳል አይሆንም ቅረርቶ።
እኔ የምልህ!
ክፉ ለራሱ ደግ ለራሱ መሆኑን እያወክህ፣
የክፋት ስሌትን መንደፍ ለምን አስፈለገህ?






0 comments:
Post a Comment