በዶ/ር አመለወርቅ ሥዩም ከተጻፈው ገጽ 200 ላይ የተወስደ
ማሳስቢያ *አንባቢው ማወቅ ያለበት ይህ ከዚህ በታች የተጻፈ ለትምህርት እንጂ እራስን በራስ ለማከም የተጻፈ አይደለም። የጤና ችግር ያለው እርዳታ የሚፈልግ ስው ሁሉ ወደ ግል ሐኪሙ ሄዶ መታከም ይኖርበታል። በጽሑፉ ውስጥ የተጠቀሱትን
የተፈጥሮ መድሐኒቶች አንባቢው ተጠቅሞ ለሚደርስበ ማንኛውም ችግር ጽሐፊዋ ሃላፊንት እንደማትወስድ በቅድሚያ ይታወቅ።
የይስት ኢንፌክሽን መነሻው
Candida albicans ኢንፌክሽን
ወይም መመረዝ የሚፈጠረው በ fungi ማደግ የተነሳ ነው። ሴቶች በሕይወታቸው ውስጥ 75% ቢያምንስ ቢያንስ አንድ ጊዜ የቨጃይናል
ይስት ኢንፌክሽን ይይዛቸዋል። ሴቶች በሕይወታቸው ውስጥ 45% ሁልት ጊዜ ወይም ከዚያ በላይ ጊዜ በይስት ኢንፌክሽን ይመረዛሉ።
በሴቶቹ ብልቶች አካባቢ ማሳከክ ሕመም አልፎም ከብልቶቻቸው ውስጥ የሚወጣ ወፍራም ፈሳሽ ነገር መኖሩ በኢንፌክሽኑ እንደተመረዙ ያመለክታል።
በብልቶቻቸውም አካባቢ በተነካ ጊዜ ህመም በተለይም በግብረሥጋ ግንኙነት ጊዜና ሽንት በሚሽኑበት ጊዜ ሕመሙ ይጠነክራል።
የፈንገስ በስውነት ክፍሎች ላይ ማደግ ለአያሌ በሽታዎች መነሻ መሆን ይችላል። ከነዚህም መሃከል
ድካም የምግብ መፈጨትና የቆዳ ላይና የማስታወስ ችግሮች የስሜት መለዋወጥ የኢሚውን አስራር መድከምና በፈንጋል በባክቴሪያና በቫይራል
የመጠቃት ችግሮች የሳይነስ ኢንፌክሽን የዩሪናሪ ኢንፌክሽን የጥፍሮች
ኢንፌክሽን ለኬሚካል ሴንሲቲቭ መሆን ጆክ ኢች ካንዲዲያስ ከሚያስከትለው መሃከል ጥቂቶቹ ናቸው።
የአንቲባዮቲክ መጠቀም በስውነት ውስጥ የሚገኙትን መጥፎ ባክቴሪያዎችንና ጥሩዎቹንም አብሮ የማጥፋት
ጉልበት አለው። የአንቲባዮቲክ መጠቀም ስውነት ለይስት ኢንፌክሽን የተጋለጠ እንዲሆን ያደርገዋል። ሌሎችም መድሐኒቶች ለሆድ ውስጥ
ቁስል (የአልሰር) መድሐኒቶች (እንደ Zantac ና Tagamet) ያሉት መድሀኒቶች ካንዲዲያሲስን የሚያመጡት በሆድ ውስጥ ነው።
በሆድ ውስጥ ሃይድሮክሎሪክ አሲድ ካንዲዲያሲስን የሚከላክል አሲድ (HCL) ነው። በሆድ ውስጥ የሃይድሮ ክሎሪክ አሲድ መቀነስ እንፌክሽኑ
እንዲፈጠር ያደርጋል። በሆድ ውስጥ ሃይድሮክሎሪክ አሲድ ዝቅተኛ መሆኑ ከታወቀ ስዊዲሽ ቢተር የተባለውን መውስድ የሃድሮክሎሪክ
አሲዱን መጠን በሆድ ውስጥ ያስተካክላል። በስውነት የሚፈልጉት ነዋሪዎቹ ባክቴሪያዎች አንቲዮቲክ ከመጠቀም የተነሳ ቁጥራቸው የቀነሰ
እንደሆነና ወይም የበሽተኛው ተከላካይ ክፍሉ በበሽታ ምክንያት የደከመ እንደሆነ (በተለይም በዔድስ ወይም በስኳር በሽታ በኒዩትሪሽን
ማነስ በመድሐኒቶች ማለትም ለነቀርሳ የሚስጡ መድሐኒቶች ወይም corticosteroids የተጠቀመ እንደሆነ ካንዲዳ ፍንጋይ የመባዛትና
የበሽታ ምልክቶችን ማምጣች ይችላሉ።
ፈንገስ የሚያድግባቸው ሥፍራዎች በሴቶች ብልቶችና በአንጀቶች በቆዳ ላይ ወይም በአፍ ላይ በተጠቀሱት
የስውነት ክፍሎች ላይ እብጣትና መቆጣት ያመጣሉ። የቨጃይናል ይስት
ኢንፌክሽን አብዛኛውን ጊዜ የሚተላለፈው በግብረ-ሥጋ ግንኙነት አይደለም። Candida albicans fungus የሚያድገው በከንፈር
በጉንጮች ላይ በምላስና በትናጋ ውስጥ ነው። መመረዙ የሚያጠቃቸው የነቀርሳና የዔድስ በሽተኞችን (ኢሚውን ሲስተማቸው) የደከመውን
በሽተኞች ነው። Candida albicans fungus ኢሚውን ሲስተማቸው ጤናማ በሆኑትም ግለስቦች ላይ በተለይም በስኳር በሽተኞች
ላይና የጥርስ በሽታ ችግር ያለባቸው ሁሉ በዚህ መመረዝ ይጠቃሉ።
የጠነከረው ካንዲዲያሲስ ማለትም Candida fungi የደም ውስጥ ገብቶ ወደመላው ስውነት ከተስራጨ
በኋላ ስውነትን ይመርዛል። እንደዚህ አይነቱ ካንዲዳያሲስ ገና በተወለዱ ክብደታቸው እነስተኛ ጨቅላ ሕጻናትና ከጠነከረ የጤና ችግሮች
የተነሳ የኢሚውን ሲስተማቸው የደከመባቸው ላይ መባዛቱ ጎልቶ ይታያል። በተለይም የጠነከረ የጤና ችግሮች ከመኖሩ የተነሳ ለሕክምናቸው
የሚረዱበት እንደ catheters (ቀጭን ቲዮፕ በመጠቀም ወደ ስውነታቸው ውስጥ በማስገባት መድሐኒትም ሆነ ሌላ እርዳታ በሚያገኙት
በሽተኞች ላይና የመተንፈስ ችግር ላለባቸው በሽተኞች ደግሞ በአንገታቸው በኩል ተቀዶ እንዲተነፍሱ የተደርገበት ሥፍራ ላይ ቀዶ ጥገና
የተደርገበት የቁስል አካባቢ ላይ ኢንፌክሽኑ ይፈጠራል። በጤነኞቹ ግለስቦች ላይ ኢንፌክሽኑ የሚተላለፈው በደም ሥሮቻቸው በኩል የሚወስዱ
እጾችና መድሐኒቶች በመርፌ የተወጉበት ሥፍራዎች ላይ ይፈጠራሉ። በዚሁ ኢንፌክሽን የተያዘው ስው የተጠቀመበትን ሌላው ሲጠቀም ኢንፌክሽኑ
እንዲተላለፍ ዕድል ይኖረዋል።
አንድ ሴት ላይ ደጋግሞ የቨጃይናል ካንዲያሲስ ያጠቃት እንደሆነ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት ዔች አይቪ
የመኖሩ አመልካች ነው ተብሎ ተወስዷል። አንድ የጥናት ጽሑፍ ይህንኑ
በተመለከተ ከ 1992 ጀመሮ ኦቨር ዘ ካውንተር መድሀኒቶች ላይ የተጻፈው ምክር አንድ ሴት ደጋግሞ የቨጃይና ካንዲያሲስ ያጠቃት
እንደሆነ ምልክቶቹም አብረው ከታዩ የሚያመለክተው የጠነከረ የጤና ችግር ማለትም በዔች አይቪ መመረዝ እንዳለ ስለሆነ በአስችኳይ
በሃኪም መታየት እንዳለባቸው ነው። ከዚህም በተጨማሪ ሌላው በዔች አይቪ መመረዝ እንዳለ አመልካች የሚሆነው በሴቶች ላይ ፕልቪክ
ኢንፍላማቶሪ ስርቪካል ዳይስፕላሲያ (በሴት መሕጸን ውስጥ ነቀርሳ የተነሳ እንደሆነ በአፍና በጉሮሮ ውስጥ የይስት ኢንፌክሽንና ሌሎችም
በግብረ ሥጋ ግንኙነት የተነሳ የሚተላለፉ እንደጭብጥ (ሲፊሊስ) በብልቶች ላይ ቁስል የኽርፕስና የቫይረስ ኢንፌክሽን የተገኘ እንደሆነ
ነው። ለዚህም ኢንፌክሽን መርጃ በተፈጥሮ መድሐኒት ባለሙያዎች ተጠንቶ ውጤትን ስላሳየ ከብዙዎቹ ጥቂቶቹ ተጠቅስዋል ስለሆነም አንድ
ሴት በተባለው ኢንፌክሽን የሚትቸገር ከሆነ ከዚህ በታች የተጠቀሱትን የተፈጥሮ መድሐኒቶች በባለሙያው ምክር መውስድ ይረዳል።
Egg lecithin- የሴሎችን ጤንነት ለመጠበቅ ፡ 20 ግራም (ዔግ ሊችን) በየቀኑ ተከፋፍሎ የሚወስደው በባዶ ሆድ
ነጭ ሽንኩርት (ካዮ ግሪን) በተፈጥሮ እንቲባዮቲክነት ጠባይ አለው የኢሚውን ሲስተሙን ለማነቃቀትና
ለማጠንከር ለምግብ መፈጨት ለካንዲዳ ኢንፌክሽን ((በካዮሊክ ከዋኩናጋ) የተመረተው ቢሆን ይመረጣል። የአወሳስዱ መጠን 2 ካፕሱል
3 ጊዜ በቀን ከምግብ ጋር
Glutathione-በመያዣው ላይ በተጻፈው መመሪያ መስረት መውስድ የሚረዳውም ፍሪራዲካልስ በስውነት
ውስጥ እንዳይባዛ ለማስቆምና የኢሚውን ሲስተሙንና ቀይ የደም ሴሎችን ጤንነት ለመጠበቅ
Lycopene- በመያዣው ላይ ተስጠው መመሪያ መስረት ይወስዳል። በስውነት ውስጥ ነቀርሳ እንዳይፈጠር
ይከላከላል።
Natural carotenoid complex (Betatene) በመያዣው ላይ በተስጠው መመሪያ መስረት
ይወስዳል። የልብ በሽታዎችንም ሆነ ነቀርሳንና ፍሪራዲካልስን ከስውነት ውስጥ ለማስወገድና ለመዋጋትና የበሽተኛውን የኢሚውን ሲስተሙን
ለማጠናከር
Vitamin D3- አወሳስዱ 400 IU በየቀኑ
የበሽተኛውን የኢሚውን ክፍሉን ለማጠናከር
Vitamin C with Bioflavonoids አወሳስዱ ከ
10,000-20,000 ሚሊግራም በየቀኑ
በመከፋፈል ቢወስድ ይመረጣል
(buffered powdered ascorbic acid or Ester-C with minerals) ቢወስድ ይምረጣል።
Maitake extract ወይም reishi estract ወይም shiitake exctract- ከነዚህ
መሃከል አንዱን በሽተኛው በመያዣው ላይ በተስጠው መመሪያ መስረት ይወስዳል። የሚረዳው ለዔድስ በሽተኞች T- cell helper
ሴሎቻቸው ሥራቸውን በሚገባ እንዲስሩ ይረዳል። በላቦራቶሪ ጥናቶች ላይ እንደተገኘው የዔች አይቪ ቫይረሶችን የመግደል ወይም የማጥፋት
ጉልበት እንዳለው ነው።
Salmon oil with
Vitamin E (በካሪሶን ላቦራቶሪ የተመረተውን) መውስድ ይመረጣል።
አወሳስዱ በመያዣው ላይ በተስጠው መመሪያ መስረት ነው። የኢሴንሲያል
ፋቲ አሲድ ምንጭ ለጤና አስፈላጊ ዳይት ነው።
Alpha-Lipoic acid - በመያዣው ላይ በተስጠው መመሪያ መስረት ይወስዳል። በሽተኛውን የሚረዳው
የዔች አይቪ ቫይረሱ ሂደቱ እንዳይፋጠን ይከላከላል።
Bovine Colostrum-በዔድስ የተነስ የሚመጣውን ተቅማጥ ለመቆጣጠር ይረዳል አወሳስዱም በመያዣው
ላይ በተስጠው መመሪያ መስረት ነው
Raw Thymes glandular plus Multiglandular complex with raw
spleen glandular - በመያዣው ላይ በተስጠው መመሪያ መስረት ይወስዳል። የሚረዳው ለዔድስ በሽተኞች T- cell ለማጠናከር
(Glandular from lamb source are best)
ለፈናጋል ኢንፌክሽን የሚያስፈልጉ ንጥረ-ነገሮች
Vitamin B complex - 50 mg 3 ጊዜ በቀን ከምግብ ጋር
በተጨማሪም
Pantothenic acid (Vitamin B5) 50 mg 3 ጊዜ በቀን ከምግብ ጋር
ከተክሎች የሚገኙ መድሐኒቶች
Cat‘s Claw - ኢሚውን ሲስተምን
ያጠናክራል፤ ከዚህም ጠባዩ የተነሳ ለዔድስ በሽተኞችና ከዔድስ የተነሳ ለሚመጣው ነቀርሳ ይረዳበታል። በእርግዝና ጊዜ አይወስድም።
Black Radish, dandelion, Milk Thistle extracts, ጉበትን መገንባትና
መጠገን ሥራን ይስራሉ። አልፈውም ደምን ያጠራሉ መድሐኒቶች የሚወስዱት በመያዣቸው ላይ በተስጠው መመሪያ መስረት ነው።
Red Clover, Suma, Burdock Root, Goldenseal, Mullein - በስወነት
ውስጥ ደምንም ሆነ ሊፊቲክ ሲስተምን በቫይረስም ሆነ በባክቴሪያ የተመረዘ እንደሆነ የመጥራት ጉልበት አላቸው። ጎልደንሲል በየቀኑ
ካንድ ሳምንት በላይ አይወስደም በእርግዝና ጊዜም አይወስደም። የካርዲኦዮቫስኩላር በሽታ ካለ የስኳር ወይም ግሉኮማ ካለ በዶክተር
ቁጥጥር ሥር ሆኖ መውስድ አለበት።
0 comments:
Post a Comment