Tuesday, November 28, 2017

ሳራን ስማት
አብርሃም የእግዚአብሔር ሰው ነበር። እግዚአብሔርን ያነጋግረዋል። እግዚአብሔርም እርሱን በቀጥታ
ያነጋግረው ነበር። እግዚአብሔርም ወደ ኮከቦች እንዲመለከትና መቁጠር ይችል እንደሆነ ይጠይቀዋል።
ከአንተ የሚወጡት ዘር ማንዘሮችህም እንዲሁ አይቆጠሩም፣አለው። በዚያን ጊዜ አብራምና (ስሙ እንደዚያ ተብሎ ይጠራ ነበርና) ሳራይ ልጆች አልነበሯቸውም። በጣም እያረጁ ቢሄዱም ልጅ ግን አልነበራቸውም።
 ሳራ እግዚአብሔር ልጅ እንዳትወልድ ያደረጋት መሰላት።. ስለዚህ አገልጋይዋ አጋር የእርስዋን ቦታ ተክታ
ከአብርሃም ልጅ እንድትወልድ ወሰነች። በዚህ መንገድ የተወለደው ልጅም ስሙ እስማኤል ይባላል።
በአንድ ወቅት አብርሃም በሚኖርበት አካባቢ ከፍተኛ ድርቅ ስለነበር መላ ቤተሰቡን ይዞ ወደግብፅ ምድር
ተጓዘ። ወደ ግብፅ ምድር ሊደርሱ ሲሉ ሚስቱን ሳራን እህቱ እንደሆነች እንጂ ሚስቱ እንደሆነች እንዳትናገር መከራት። እጅግ በጣም ቆንጆ ስለነበረች ግብፃውያን በሚስቴ ምክንያት ይገድሉኛል ብሎ ፈራ። የግብፅ ንጉስ ፈርኦንም ሳራን አስጠራትና ወደቤቱ ወሰዳት። በዚህ ምክንያትም አሰቃቂ ነገሮች በፈርኦን ቤት ላይ መፈፀም ጀመሩ። ፈርኦንም ሳራና አብርሃም እንደዋሹትና ሳራ ሚሰቱ እንደሆነች ተረዳ። ፈርኦንም አብርሃምን ቤተሰቡን ይዞ እንዲሄድ ፈቀደለት። በተጨማሪም በጎችን በሬዎችንና ግመሎችን በስጦታ አበረከተለት።
አብርሃም እንደገና በተመሳሳይ መልኩ ንጉስ አቢሜሌክን ዋሸ። ንጉስ አቢሜሌክ ሳራ የአብርሃም እህት
እንደሆነች ስለተነገረው ሚስቱ ሊያደደርጋት አስቦ ነበር። እንደእውነቱ ከሆነ ሳራ ግማሽ እህቱ ናት። ቢሆንም ሚስቱ ናትና የተናገረው ነገር ውሸት ነው። እግዚአብሔር ለአቢሜሌክ በሕልም ተገልጦለት ሳራን የሚያገባት ከሆነ ሙት እንደሚሆን ነገረው። አቢሜሌክም አብርሃምን ለምን እንደዋሸ ከጠየቀውና ከወቀሰው በኋላ አሰናበተው። በተጨማሪም እንስሳትን አገልጋዮችንና በብዙ ሺህ የሚቆጠር ብር ሰጠው።
አብርሃም 99 ዓመት ሰው በሚሆንበት ጊዜም እግዚብሔር እንደገና ቃል ኪዳኑን አደሰ። ስሙንም ከአብራም ወደአብርሃም ቀየረለት። እንዲሁም የሚስቱ የሳራይ ስም ሳራ ሆነ።
አንድ ጊዜ ሶስት ሰዎች ወደ አብርሃም ድንኳን መጡ። ምግብ አቀረበላቸው። ከዚያም ከእርሱ ጋር ጨዋታ
ጀመሩ። ሳራ እንደምትወልድም ነገሩት። ከድንኳኑ ውስት ሆና ይህን የአብርሃምንና የሶስቱን ሰዎች ጨዋታ
ስታዳምጥ የነበረችው ሳራ ሳቀች። የሳቀችበት ምክንያትም እርሷ በዚያን ሰዓት 90 ዓመት ሲሆናት አብርሃም ደግሞ 100 ዓመት ሽማግሌ ነበር! ይህም ልጅ ለመውለድ የሚያስችል እድሜ አልነበረም። ከእግዚአብሔር ዘንድ የመጣው መልእክተኛም፣ለመሆኑ ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር አለ ወይ? ልክ በሚቀጥለው አመት በዚህን ሰዓት ሳራን እጎበኛታለሁ። ወንድ ልጅም ትወልዳለች፣አላቸው።  እንዳለውም አደረገ። 90 ዓመቷ ወንድ ልጅ ወለደች። ስሙንም ይስሐቅ ብላ ጠራችው። ትርጉሙምሳቅማለት ነው።
ሳራ ስትሞት እድሜዋ 127 ዓመት ነበር። ታዲያ ልጇ ይስሐቅ በዚያን ሰዓት 37 ዓመት ሰው ነበር። አብርሃም በሔብሮን አጠገብ የሚገኝ አንድ መሬት ገዛ። የመሬቱ ባለቤት በነፃ ሊሰጠው ፈልጎ ነበር። አብርሃም ግን የመሬቱን ዋጋ ካልከፈለ በስተቀር በነፃ እንደማይወስድ ነገረው። ሳራንም ከኤፍሮን በገዛው የእርሻ መሬት ላይ በሚገኘው ዋሻ ውስጥ ቀበራት።  በአዲስ ኪዳን 1ጴጥ.3:5 – 6 ስለ ሳራ እንዲህ እናነባለን፣እንዲህ በቀድሞ ዘመን በእግዚአብሔር ተስፋ ያደረጉት ቅዱሳት ሴቶች ደግሞ ለባሎቻቸው ሲገዙ ተሸልመው ነበርና፤ እንዲሁም ሣራ ለአብርሃም፦ ጌታ ብላ ተጠራዋለች።
እግዚአብሄር ባንድ ወቅት ሳራን ስማት ብሎት ነበር፤ ጊዜውም በጣም ለሁለቱም ለአብረሃምም ሆነ ለሳራ የከበደ ጊዜ ነበረ። በመካከላቸው ውዝግብ የተነሳው ሳራ የራስዋን እርጅና ተመልከታ ለመውለድ ተስፋ እንደሌላት አደርጋ ስለተቀበለች አገልጋይዋን አጋርን ወደ አብረሃም እንድተገባ አደረገች። ለሳራ ልጅ ለማግኘት ከዚህ የተሻላ አማራጭ በፊትዋ በርስዋ አስተሳስብ አልነበረም በመሆኑም ይህንን አርምጃ ወስደች አብረሃምም የሚስቱን ፍላጎት አይቶ ወደ አጋር ገባ አጋርም እስማኤልን ጸነስች። በአብረሃም ቤተስብ ውስጥ የልጅ ችግራቸው ተፈታ ብለው ሲጠብቁ ልጃቸው እስማኤል ከተወለደ በህዋላ ሌላ ችግር በቤታቸው አቆጠቆጠ ይኸውም የሳራና የአጋር ጉዳይ ነው። ነገሩም የተነሳው እንዲህ ነው ታናሽትዋ ታልቃዋን መናቅ ጀመረች ይህም ድርጊትዋ ሳራን አስቆጣት። ይህም ብቻ አይደለም  የሁለቱ ሴቶች ታሪካቸው የጀመረው ገና በግብጽ ሳሉ ነው። የሚገርመው ነገር ሁለቱ ባልና ሚስቶች (አብረሃምና ሳራ) የራሳቸውን ችግር ለማቃለል ወደ ግብጽ የሄዱት እነርሱ ናቸው።  አጋር በሀገርዋ ቁጭ ብላ የዕለት ሥራዋን ስትስራ የሄዱባት እነርሱ ናቸው እንጂ እርስዋ አይደለችም። የሳራና የአጋር ትውውቅ የጀመረው እዚያው ከፈርኦን ቤት ሳለች ነበር።  ፍርኦን ሳራን በቁንጅነዋ ተማርኮ የራሱ ሚስት ለማድረግ እየተዘጋጀ እያለ በቤተመንግሥት ውስጥ አጋር ለሳራ አገልጋይ ሆና በፈርኦን የተስጠቻት ነበረች። ሳራን ማገልገል የጀመረችው ገና በግብጽ ሳለች ነበር፤ በጣም የሚገርመው ነገር ፈርኦን የነብዩን ሚስት ተውለት ብሎ ከተናገረው በህዋላ አብረሃም ሚስቱን ሳርና ይዞ ወደ ተወለደበት ሲመለስ  የሳራን አገልጋይ አጋርን ሳይወስድባት አብራት እንዲትሄድ ፈቀደላት።
ከታሪካቸው እንደምንረዳው አጋር የገባቸው በነርሱ ችግር መካከል ነው የአብረሃም እራሱን ለማዳን ሲዋሽና እህቴ ናት ብሎ ለፈረኦን ሲናገር የመዋሽት ችግሩ የርሱ ነበር፤ ለአብረሃም መዋሽትና እራሱን ማዳን የለመደው ዘዴ ስለነበረ አሁንም ለአቤሜሊክም እንዲሁ አደረገ።  አሁን ደግሞ ልጅ ባላመውለዳቸው የተነሳ ባልና ሚስቱ አጋርን ተጠቅመው ደግሞ  እስማኤል ተወለደ።  የልጅ ችግራቸው ሲፈታ ደግሞ ሌላ ችግር ከመካከላቸው በቀለ? ለምን ይሆን?

ይቀጥላል...

0 comments:

Post a Comment