የቅናት ስሜት
ሰዎች ፍጹማን አለመሆናቸው በራሱ በውስጣቸው የመመቅኘት ወይም ‘የቅናት ዝንባሌ’ እንዲያድርባቸው ተጽዕኖ
ማድረጉ እንዳለ ሆኖ ይህን ዝንባሌ የሚያቀጣጥሉና የሚያባብሱ ሌሎች ምክንያቶችም አሉ። (ያዕ. 4:5) ሐዋርያው ጳውሎስ ከእነዚህ
ምክንያቶች አንዱን ሲጠቅስ እንዲህ ብሏል፦ “በመካከላችን የፉክክር መንፈስ በማነሳሳትና አንዳችን ሌላውን በመመቅኘት በከንቱ አንመካ።”
(ገላ. 5:26) በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ እንዲሉ የፉክክር መንፈስ፣ በአለፍጽምና ምክንያት የወረስነውን የምቀኝነት ዝንባሌ ጭራሹን
ሊያባብሰው ይችላል። ክሪስቲና እና ሆሴ* የሚባሉ ሁለት ክርስቲያኖች ይህ እውነት መሆኑን በራሳቸው ሕይወት ተመልክተዋል።
መጽሐፍ ቅዱስ ብዙ የማስጠንቀቂያ ምሳሌዎችን ይዟል። (1 ቆሮ. 10:11) ከእነዚህ መካከል አንዳንዶቹ፣
የምቀኝነት ስሜት እንዴት እንደሚያቆጠቁጥ ብቻ ሳይሆን እንዲቆጣጠራቸው የፈቀዱለትን ሰዎች እንዴት እንደሚመርዛቸው ጭምር የሚያሳዩ
ናቸው። ለምሳሌ ያህል፣ የአዳምና የሔዋን የበኩር ልጅ የሆነው ቃየን ወንድሙ አቤል ያቀረበው መሥዋዕት ዘንድ ተቀባይነት አግኝቶ የእሱ ሳያገኝ በመቅረቱ በጣም ተናድዶ ነበር። ቃየን
ስሜቱን መቆጣጠር ይችል የነበረ ቢሆንም ቅናት እንዲያሳውረው በመፍቀዱ ወንድሙን እስከ መግደል ደርሷል። (ዘፍ. 4:4-8) መጽሐፍ
ቅዱስ ቃየን “ከክፉው ወገን” ማለትም ከሰይጣን ወገን እንደሆነ መናገሩ ምንም አያስገርምም። 1 ዮሐ. 3:12
ዮሴፍ ከአባቱ ጋር ለየት ያለ ቅርርብ ያለው በመሆኑ አሥሩ ወንድሞቹ ይቀኑበት ነበር። ዮሴፍ ስላያቸው
ትንቢታዊ ሕልሞች ሲነግራቸው ጥላቻቸው እየጨመረ መጣ። እንዲያውም ሊገድሉት ፈልገው ነበር። በመጨረሻ ግን ለባርነት ሸጡት፤ ከዚያም
አባታቸው፣ ልጁ ዮሴፍ ሞቷል ብሎ እንዲያስብ በማድረግ የጭካኔ ተግባር ፈጸሙ። (ዘፍ. 37:4-11, 23-28, 31-33) እርግጥ
ነው፣ የዮሴፍ ወንድሞች ዓመታት ካለፉ በኋላ እርስ በርሳቸው “ይኸው በወንድማችን ላይ ባደረስነው በደል ምክንያት ቅጣታችንን እየተቀበልን
ነው። እርሱ እንደዚያ ተጨንቆ ስለ ሕይወቱ ሲማጠነን፣ እኛ አልሰማነውም ነበር” መባባላቸው በሠሩት በደል መጸጸታቸውን ያሳያል።
ዘፍ. 42:21፤ 50:15-19
ቆሬ፣ ዳታንና አቤሮንም ቢሆኑ የምቀኝነት ስሜት ያደረባቸው እነሱ ያገኙትን መብት ሙሴና አሮን ካገኙት
ጋር ማወዳደር ሲጀምሩ ነው። ሙሴ ‘ጌታ እንደሆነና’ ራሱን ከሌሎች በላይ ከፍ ከፍ እንዳደረገ በመናገር ከሰሱት። (ዘኍ.
16:13) ይሁንና ይህ ክስ ፈጽሞ ከእውነት የራቀ ነበር። (ዘኍ. 11:14, 15) ሙሴን የሾመው ራሱ እግዚአብሄር ነበር። እነዚህ ዓመፀኞች ግን ሙሴ ሥልጣን በማግኘቱ ተመቀኙት።
በመጨረሻም ምቀኝነት በእግዚአብሄር እጅ እንዲጠፉ አደረጋቸው። መዝ. 106:16, 17
ንጉሥ ሰለሞንም ምቀኝነት አንድን ሰው እስከ ምን ደረጃ ሊያደርሰው እንደሚችል ተመልክቷል። አንዲት
ሴት አራስ ልጇ ሲሞትባት የሞተውን ልጇን አብራት በምትኖረው ሴት እቅፍ ውስጥ ካለው ልጅ ጋር አቀያየረችው፤ ይህን ያደረገችው ሴትየዋ
የሞተው ልጅ የእኔ ነው ብላ እንድታስብ ለማድረግ ነበር። እነዚህ እናቶች ለፍርድ በቀረቡበት ወቅት፣ የሌላን ሰው ልጅ ለመውሰድ
የሞከረችው ሴት በሕይወት ያለው ልጅ ይገደል በሚለው ሐሳብ እስከ መስማማት ደርሳ ነበር። ይሁን እንጂ ሰለሞን ይህን ሲመለከት ሕፃኑ
ለእውነተኛዋ እናት እንዲሰጥ ፈረደ። 1 ነገ. 3:16-27
ምቀኝነት ከባድ መዘዞችን ሊያስከትል ይችላል። ከላይ የተጠቀሱት ቅዱስ ጽሑፋዊ ምሳሌዎች እንደሚያሳዩት
ምቀኝነት አንድን ሰው የጥላቻ ስሜት እንዲያድርበትና ኢፍትሐዊ እንዲሆን ሊያደርገው አልፎ ተርፎም ነፍስ እስከ ማጥፋት ሊያደርሰው
ይችላል። ከዚህም በላይ የጥቃት ዒላማ የሆኑት በምሳሌዎቹ ላይ የተጠቀሱት ሁሉም ግለሰቦች በደል የተፈጸመባቸው ባልሠሩት ጥፋት ነው።
ታዲያ ምቀኝነት ወይም ቅናት ሕይወታችንን እንዳይቆጣጠረው ምን ብናደርግ ይሻላል? ለምቀኝነት ማርከሻ የሚሆኑ ምን እርምጃዎችንስ
መውሰድ እንችላለን?
የምቀኝነት ፍቱን ማርከሻዎች!
ፍቅርንና የወንድማማች መዋደድን ማዳበር። ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ ክርስቲያኖችን እንዲህ በማለት መክሯቸዋል፦
“እንግዲህ ለእውነት በመታዘዝ ነፍሳችሁን ስላነጻችሁ ግብዝነት የሌለበት የወንድማማች መዋደድ ሊኖራችሁና እርስ በርሳችሁ አጥብቃችሁ
ከልብ ልትዋደዱ ይገባል።” (1 ጴጥ. 1:22) ታዲያ ፍቅር የሚገለጸው እንዴት ነው? ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ “ፍቅር ታጋሽና ደግ
ነው። ፍቅር አይቀናም፣ ጉራ አይነዛም፣ አይታበይም፣ ተገቢ ያልሆነ ምግባር አያሳይም፣ የራሱን ፍላጎት አያስቀድምም” በማለት ጽፏል።
(1 ቆሮ. 13:4, 5) በልባችን ውስጥ እንዲህ ዓይነቱን ፍቅር ማዳበራችን በውስጣችን ያለውን የምቀኝነት ዝንባሌ ለመቆጠር የሚረዳን
አይመስላችሁም? (1 ጴጥ. 2:1) የአምላክ ቃል እንደሚናገረው ዮናታን በዳዊት ከመመቅኘት ይልቅ “እንደራሱ አድርጎ ወደደው።”
1 ሳሙ. 18:1
ፈሪሃ አምላክ ካላቸው ሰዎች ጋር መወዳጀት። መዝሙር 73ን ያቀናበረው
ግለሰብ ከችግር ነፃ የሆነ የቅንጦት ሕይወት ይመሩ በነበሩ ክፉ ሰዎች ቀንቶ ነበር። ይሁን እንጂ “ወደ አምላክ መቅደስ” መሄዱ
የቅናት ስሜቱን እንዲቆጣጠር ረድቶታል። (መዝ. 73:3-5, 17) ንጉሥ ዳዊት ከእምነት ባልንጀሮቹ ጋር ኅብረት መፍጠሩ ‘ወደ
እግዚአብሄር በመቅረቡ’ ያገኛቸውን በረከቶች እንዲያስተውል ረድቶታል። (መዝ. 73:28) እኛም ዘወትር በክርስቲያናዊ ስብሰባዎች
ላይ በመገኘት ከእምነት ባልንጀሮቻችን ጋር ጊዜ የምናሳልፍ ከሆነ ተመሳሳይ ጥቅም እናገኛለን።
መልካም ለማድረግ መጣር። እግዚብሄር በቃየን ልብ ውስጥ የምቀኝነትና የጥላቻ ስሜት ማቆጥቆጡን ሲመለከት
‘መልካም እንዲያደርግ’ ነግሮት ነበር። (ዘፍ. 4:7) ታዲያ ክርስቲያኖች ‘መልካም ማድረግ’ የሚችሉት እንዴት ነው? ኢየሱስ
‘እግዚአብሄር አምላካችንን በሙሉ ልባችን፣ በሙሉ ነፍሳችንና በሙሉ ሐሳባችን መውደድ እንዳለብን እንዲሁም ባልንጀራችንን እንደራሳችን
አድርገን መውደድ እንዳለብን’ ተናግሯል። (ማቴ. 22:37-39) ሕይወታችን፣ እግዚአብሄርን በማገልገልና ሌሎችን በመርዳት ላይ
እንዲያተኩር ማድረግ ለቅናት ፍቱን ማርከሻ ነው። በስብከቱና ደቀ መዛሙርት በማድረጉ ሥራ ትርጉም ያለው ተሳትፎ ማድረጋችን አምላክንና
ባልንጀራችንን ለማገልገል ከሚያስችሉን ግሩም መንገዶች አንዱ ከመሆኑም በላይ ለእኛም የይሖዋን “በረከት” ያስገኝልናል።ምሳሌ
10:22
“ደስ ከተሰኙ ሰዎች ጋር ደስ” መሰኘት። (ሮሜ. 12:15) ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱ ባገኙት ስኬት ተደስቶ
ነበር፤ እንዲያውም በስብከቱ ሥራ እሱ ካከናወነው በላይ እንደሚሠሩም ገልጾ ነበር። (ሉቃስ 10:17, 21፤ ዮሐ. 14:12) የእግዚአብሄር
አገልጋዮች እንደመሆናችን መጠን አንድነት አለን፤ በመሆኑም የአንዱ ስኬት ለሁላችንም በረከት ነው። (1 ቆሮ. 12:25, 26)
ታዲያ ሌሎች ከእኛ የበለጠ ኃላፊነት ሲያገኙ ከመቅናት ይልቅ መደሰት አይገባንም?
ምቀኝነት “የሥጋ ሥራዎች” ከሚባሉት መካከል አንዱ በመሆኑ እያንዳንዱ ክርስቲያን ይህን ባሕርይ ለማስወገድ
ከፍተኛ ትግል ማድረግ ይኖርበታል። (ገላ. 5:19-21) የቅናት ወይም የምቀኝነት ዝንባሌ እንዳይቆጣጠረን ጥረት የምናደርግ ከሆነ
በሕይወታችን ይበልጥ ደስተኞች ልንሆንና በሰማይ ያለውን አባታችንን ልናስደስተው እንችላለን።
የቁጣኝነት መነሻው
ለቁጣ መንስኤ የሚሆኑት ነገሮች ውስብስብ ናቸው። የሳይንስ ሊቃውንትም
እንኳ ስለ ቁጣ ያላቸው ግንዛቤ አነስተኛ እንደሆነ አይሸሽጉም። ይሁን እንጂ ሁላችንም “የሚያስቆጣ ነገር” ሲያጋጥመን ልንበሳጭ
እንደምንችል በአእምሮ ጤንነት መስክ የተሰማሩ አብዛኞቹ ባለሙያዎች የሚስማሙበት ነገር ነው።
የሚያስቆጣ ነገር የሚባለው አንድን ሰው የሚያናድድ ወይም የሚያበሳጭ
ነገር ነው። ብዙውን ጊዜ የምንናደደው የፍትሕ መጓደል ወይም መድልዎ ሲፈጸም ስንመለከት ነው። አንዳንድ ጊዜ ደግሞ ሌሎች እንደናቁን
ሆኖ ሲሰማን ለምሳሌ ስንሰደብ ወይም ክብራችንን ዝቅ የሚያደርግ ነገር ሲያጋጥመን ልንቆጣ እንችላለን። ሥልጣናችን ወይም መልካም
ስማችን እንደተነካ ሲሰማንም በቁጣ ልንገነፍል እንችላለን።
እርግጥ ነው፣ ሰዎችን የሚያስቆጧቸው ነገሮች የተለያዩ ናቸው። ዕድሜና
ፆታ ሌላው ቀርቶ ባሕል እንኳ ሰዎችን የሚያስቆጧቸው ነገሮች እንዲለያዩ ሊያደርጉ ይችላሉ። ከዚህም በላይ ሰዎች የሚያስቆጡ ነገሮች
ሲያጋጥሟቸው ስሜታቸውን የሚገልጹበት መንገድም ይለያያል። አንዳንድ ሰዎች ብዙም የማይቆጡ ሲሆን ከተቆጡም ነገሩን ቶሎ ይረሱታል፤
ሌሎች ግን በቀላሉ የሚቆጡ ከመሆናቸውም በላይ ቁጣቸው እስኪበርድ ቀናት፣ ሳምንታት፣ ወራት ወይም ከዚያ የሚበልጥ ጊዜ ሊፈጅ ይችላል።
በዓለም ላይ ሊያስቆጡን የሚችሉ ብዙ ነገሮች አሉ። በዚህ ላይ ደግሞ
ሰዎች ከበፊቱ የበለጠ በቀላሉ የሚቆጡ እየሆኑ መጥተዋል። ለምን? አንዱ ምክንያት በዘመናችን የተስፋፋው ለሰዎች አሳቢነት አለማሳየትና
እኔ ልቅደም የሚል መንፈስ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ “በመጨረሻዎቹ ቀኖች . . . ሰዎች ራሳቸውን የሚወዱ፣ ገንዘብ የሚወዱ፣ ጉረኞች፣
ትዕቢተኞች፣ . . . ግትሮች፣ በኩራት የተወጠሩ” እንደሚሆኑ ይናገራል። (2 ጢሞቴዎስ 3:1-5) እነዚህ ቃላት በዛሬው ጊዜ ያሉትን
የአብዛኞቹን ሰዎች ዝንባሌ በትክክል የሚገልጹ አይደሉም? በእርግጥም
ራስ ወዳድ የሆኑ ሰዎች የፈለጉትን ነገር ማግኘት ካልቻሉ ብዙውን ጊዜ ውጤቱ ቁጣ ነው። ቁጣ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ የሚሄድ
ችግር እንዲሆን ያደረጉ ሌሎች በርካታ ምክንያቶችም አሉ።
የወላጆች ምሳሌነት
ወላጆች፣ ልጆቻቸው በልጅነትና በጉርምስና ዕድሜያቸው በሚያዳብሩት
ባሕርይ ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ያሳድራሉ። የሥነ ልቦና ተመራማሪ የሆኑት ሃሪ ሚልዝ “ሰዎች ቁጣቸውን መግለጽ የሚማሩት ገና ከትንሽነታቸው
ጀምሮ በአካባቢያቸው ሌሎች ቁጣቸውን የሚገልጹበትን መንገድ በመኮረጅ ነው” በማለት ተናግረዋል።
አንድ ሕፃን ብስጩ ሰዎች በበዙበት አካባቢ ካደገ በሌላ አባባል ሰዎች
በትንሽ በትልቁ በቁጣ ሲገነፍሉ የሚያይ ከሆነ በሕይወቱ ውስጥ ችግር ባጋጠመው ቁጥር በቁጣ ምላሽ እንዲሰጥ እየሠለጠነ ነው ሊባል
ይችላል። የልጁን ሁኔታ የተበከለ ውኃ ከሚጠጣ ተክል ጋር ልናመሳስለው እንችላለን። በዚህ ዓይነት ሁኔታ ውስጥ ያለ ተክል ቢያድግም
እድገቱ ሊቀጭጭና ምናልባትም ዘላቂ ጉዳት ሊደርስበት ይችላል። ቁጣም እንደተበከለ ውኃ ነው፤ እንዲህ ባለ አካባቢ ያደጉ ልጆች ትልልቅ
ሰዎች ሲሆኑ ቁጡ የመሆን አጋጣሚያቸው ሰፊ ነው።
በ1800 ከዓለም ሕዝብ መካከል በከተሞች ውስጥ የሚኖረው 3 በመቶ
ገደማ ነበር። በ2008 ግን ይህ ቁጥር አድጎ 50 በመቶ የደረሰ ሲሆን በ2050 ደግሞ 70 በመቶ እንደሚደርስ ይጠበቃል። ቁጥራቸው
እየጨመረ የሚሄድ ሰዎች በተጨናነቁ ከተሞች ውስጥ ተፋፍገው መኖር በቀጠሉ መጠን ቁጡና ብስጩ የሆኑ ሰዎች እየበዙ መሄዳቸው የማይቀር
ነው። ሜክሲኮ ሲቲን እንደ ምሳሌ እንውሰድ፤ በምድር ላይ ካሉት ትልቅና እጅግ የተጨናነቁ ከተሞች አንዷ በሆነችው በዚህች ከተማ
ዋነኛው የውጥረት መንስኤ የትራፊክ መጨናነቅ ነው። አንድ ጋዜጠኛ እንደዘገበው ሜክሲኮ ሲቲ 18 ሚሊዮን የሚያህል ሕዝብና ስድስት
ሚሊዮን መኪኖች ያሉባት ከተማ በመሆኗ “በዓለም ላይ ካሉት ዋና ከተሞች ሁሉ ይበልጥ ውጥረት የነገሠባት ሳትሆን አትቀርም።” ይኸው
ጋዜጠኛ አክሎም “ከፍተኛ የትራፊክ መጨናነቅ በመኖሩ ሰዎች በቁጣ የመገንፈላቸው አጋጣሚ በጣም ከፍ ያለ ነው” ብሏል።
በሕዝብ የተጨናነቁ ከተሞች በሌሎች መንገዶችም ውጥረት ያስከትላሉ፤
ከእነዚህም መካከል የአየር ብክለት፣ ከፍተኛ መጠን ያላቸውና የሚረብሹ ድምፆች መበራከት፣ የመኖሪያ ቤት እጦት፣ የባሕል ልዩነትና
የወንጀል ድርጊቶች መበራከት ይገኙበታል። ውጥረት የሚያስከትሉ ነገሮች በበዙ ቁጥር ሰዎች የመበሳጨት፣ የመቆጣትና ትዕግሥት የማጣት
አዝማሚያቸው እየጨመረ ይሄዳል።
ኢኮኖሚው የሚያስከትለው ውጥረት በዓለም ላይ የሚታየው የኢኮኖሚ ውድቀት
በየትኛውም ቦታ በሚኖሩ ሰዎች ላይ ውጥረትና ጭንቀት አስከትሏል። ዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም እና የተባበሩት መንግሥታት ዓለም
አቀፍ የሥራ ድርጅት (አይ ኤል ኦ) በ2010 በጋራ ያወጡት አንድ መግለጫ እንደሚያሳየው “በመላው ዓለም ከ210 ሚሊዮን የሚበልጡ
ሰዎች ሥራ አጥ እንደሆኑ ይገመታል።” የሚያሳዝነው ነገር፣ ከሥራ ከተቀነሱት ሰዎች መካከል አብዛኞቹ ተቀማጭ ገንዘብ የሌላቸው ሲሆን
ለሥራ አጦች የሚሰጥ እርዳታም አያገኙም።
ሥራ ያላቸው ሰዎችም ቢሆኑ መጨነቃቸው አይቀርም። አይ ኤል ኦ እንደገለጸው
ከሥራ ጋር ተያይዞ የሚመጣ ውጥረት “ዓለም አቀፍ ወረርሽኝ” ሆኗል። በኦንታሪዮ፣ ካናዳ የአስተዳደር አማካሪ የሆኑት ሎርን ከርቲስ
“ሰዎች ሥራቸውን እንዳያጡ የሚፈሩ ሲሆን የሚታያቸው መጥፎ መጥፎው ነገር ነው” በማለት ይናገራሉ፤ “እንዲህ ዓይነት ስጋት ስላላቸው
ከአለቆቻቸው ወይም ከሌሎች ሠራተኞች ጋር ሙግት መግጠም ይቀናቸዋል” በማለት አክለው ተናግረዋል።
የሩጫ ውድድር ላይ እንደሆንክና የምትሮጠው እግሮችህ በሰንሰለት ታስረው
እንደሆነ አድርገህ አስብ፤ ይሁንና በሰንሰለት የታሰርከው አንተ ብቻ መሆንህን ብታውቅ ምን ይሰማሃል? በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች
በዘራቸው ወይም በሌላ ምክንያት መድልዎ ሲደርስባቸው የሚሰማቸው ስሜት ከዚህ ጋር ተመሳሳይ ነው። ሰዎች ሥራ፣ ትምህርት፣ መኖሪያ
ቤትና ሌሎችም ለሕይወት አስፈላጊ የሆኑ ነገሮችን እንዳያገኙ መድልዎ ሲደረግባቸው ይበሳጫሉ።
ሌሎች ኢፍትሐዊ ድርጊቶችም የአንድን ሰው መንፈስ ሊደቁሱና ከፍተኛ
የስሜት ሥቃይ ሊያስከትሉበት ይችላሉ። የሚያሳዝነው ነገር አብዛኞቻችን በሕይወታችን ውስጥ በሆነ ወቅት ላይ የፍትሕ መጓደል ደርሶብን
ያውቃል። ከሦስት ሺህ ከሚበልጡ ዓመታት በፊት ጠቢቡ ንጉሥ ሰሎሞን “የተገፉትን ሰዎች እንባ ተመለከትሁ፤ የሚያጽናናቸውም አልነበረም”
በማለት ተናግሮ ነበር። (መክብብ 4:1) የፍትሕ መጓደል ሲስፋፋና የሚያጽናና ሲጠፋ አንድ ሰው ልቡ በቁጣ ሊሞላ ይችላል።
በቴሌቪዥንና በሌሎችም የመገናኛ ብዙኃን የሚታየው ዓመፅ በልጆች ላይ
ምን ተጽዕኖ እንዳለው ለማወቅ ከአንድ ሺህ በላይ የሚሆኑ ጥናቶች ተደርገዋል። በመገናኛ ብዙኃን የሚቀርቡትን ነገሮች በተመለከተ
ለሰዎች መረጃ የሚሰጥ አንድ ድርጅት መሥራች የሆኑት ጄምስ ስታየር እንዲህ ይላሉ፦ “እውነት የሚመስልና ዘግናኝ የሆነ የዓመፅ ድርጊት
[በመገናኛ ብዙኃን] በተደጋጋሚ የሚመለከት ትውልድ፣ ጠበኝነትን ተቀባይነት እንዳለው ነገር አድርጎ የሚያይ ከመሆኑም ሌላ የጭካኔ
ድርጊት እምብዛም የማይረብሸውና የርኅራኄ ስሜት የሌለው ይሆናል።”
እርግጥ ነው፣ በቴሌቪዥን አዘውትረው የዓመፅ ድርጊቶችን የሚያዩ አብዛኞቹ ወጣቶች ሲያድጉ ጨካኝ ወንጀለኞች ይሆናሉ ማለት
አይደለም። ይሁን እንጂ አስቸጋሪ ሁኔታዎች ሲያጋጥሙን በቁጣ መገንፈል ተቀባይነት ያለው ነገር እንደሆነ ተደርጎ ብዙውን ጊዜ በመዝናኛው
ዓለም ስለሚቀርብ የዓመፅ ድርጊቶች የማይዘገንኑት አዲስ ትውልድ ብቅ ብሏል።
ክፉ መናፍስት የሚያሳድሩት ተጽዕኖ
በዛሬው ጊዜ ሰዎች ጎጂ በሆነ መንገድ ቁጣቸውን እንዲገልጹ የሚያደርጋቸው
አንድ የማይታይ ኃይል ከበስተጀርባ እንዳለ መጽሐፍ ቅዱስ ይገልጻል። ይህ ኃይል ምንድን ነው? ገና በሰው ዘር ታሪክ መጀመሪያ ላይ
አንድ ዓመፀኛ መንፈሳዊ ፍጡር ሁሉን ቻይ የሆነውን አምላክ መቃወም ጀመረ። ይህ ክፉ መንፈሳዊ ፍጡር ሰይጣን ተብሎ የሚጠራ ሲሆን
ስሙም በዕብራይስጥ “ተቃዋሚ” ወይም “ጠላት” የሚል ትርጉም አለው። (ዘፍጥረት 3:1-13) ከጊዜ በኋላም ሰይጣን ሌሎች መላእክትን
አግባብቶ በዓመፁ እንዲተባበሩት አደረጋቸው።
አጋንንት ወይም ክፉ መናፍስት በመባል የሚታወቁት እነዚያ ዓመፀኛ
መላእክት የሚያሳድሩት ተጽዕኖ በምድር አካባቢ እንዲወሰን ተደርጓል። (ራእይ 12:9, 10, 12) በተጨማሪም አጭር ጊዜ እንደቀራቸው
ስለሚያውቁ “በታላቅ ቁጣ” ተሞልተዋል። እነዚህን ክፉ መናፍስት በዓይናችን ልናያቸው ባንችልም የሚያሳድሩትን ተጽዕኖ መመልከት እንችላለን።
እንዴት? ሰይጣንና አጋንንታዊ ጭፍሮቹ ኃጢአት የመሥራት ዝንባሌያችንን
ተጠቅመው እንደ “ጠላትነት፣ ጠብ፣ ቅናት፣ በቁጣ መገንፈል፣ የከረረ ጭቅጭቅ፣ መከፋፈል፣ . . . ምቀኝነት” ባሉትና እነዚህን
በመሳሰሉት ነገሮች እንድንካፈል ሊፈትኑን ይሞክራሉ። ገላትያ 5:19-21
በእርግጥም ከላይ ያየናቸውን ችግሮች፣ ተጽዕኖዎችና ውጥረት የሚፈጥሩ
ሁኔታዎች ከግምት ካስገባን ሰዎች የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴዎቻቸውን በሚያከናውኑበት ጊዜ ብስጩ የሚሆኑት ለምን እንደሆነ መረዳት
አያዳግተንም።
ጓደኛ ሊሆኑ
የሚችሉ ሰዎችን መፈለግ
አንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ምሳሌ “ከጠቢብ ጋር የሚሄድ ጠቢብ ይሆናል፤
የተላሎች ባልንጀራ ግን ጉዳት ያገኘዋል” በማለት ሐቁን አስቀምጦታል። (ምሳሌ 13:20) ብዙ ሰዎች ጓደኛ ሲመርጡ የሚያዩት መግባባታቸውን
ብቻ ነው። ከምንግባባቸው ሰዎች ጋር አብረን ስንሆን ደስ እንደሚለን የታወቀ ነው። ሆኖም ስለ እውነተኛ ማንነታቸው ብዙም ትኩረት
ሳንሰጥ ስለተግባባን ብቻ ሰዎችን ጓደኛ አድርገን የምንመርጥ ከሆነ ከባድ ችግር ላይ ልንወድቅ እንችላለን። አንድ ሰው ጥሩ ሥነ
ምግባር እንዳለውና እንደሌለው እንዴት ማወቅ ትችላለህ?
በቅድሚያ እኛ ራሳችን ጥሩ ሥነ ምግባር ያለን ሰዎች መሆን አለብን።
ትክክልና ስህተት የሆነውን፣ ጥሩውንና መጥፎውን ለይተን ማወቅና በማንኛውም ጊዜ ሥነ ምግባራዊ አቋማችንን ጠብቀን መኖር ያስፈልገናል።
ሌላ የመጽሐፍ ቅዱስ ምሳሌ “ብረት ብረትን እንደሚስል፣ ሰውም ሌላውን ሰው እንደዚሁ ይስለዋል” በማለት ይገልጻል። (ምሳሌ
27:17) እንደ ብረት የጠነከረ የሥነ ምግባር አቋም ያላቸው ሁለት ሰዎች ጓደኛሞች ከሆኑ መልካም ባሕርያትን በማዳበር ረገድ እርስ
በርስ የሚረዳዱ ከመሆኑም በላይ በመካከላቸው ያለው ወዳጅነት ይበልጥ ይጠናከራል።
“እኔ
እውነተኛ ጓደኛ የምለው በጥሞና የሚያዳምጠኝንና በደግነት የሚያነጋግረኝን እንዲሁም ሳጠፋ የሚገሥጸኝን ሰው ነው” በማለት አስተያየቱን
አንድ ስው ሰጥቷል። አዎ፣ የልብ ጓደኞቻችን ወጣትም ሆኑ አረጋዊ ትክክለኛውን አቅጣጫ ይዘን እንድንጓዝ የሚረዱንና ተገቢ ያልሆነ
ነገር ልናደርግ ስንል የሚያርሙን መሆን አለባቸው። መጽሐፍ ቅዱስ “የወዳጅ ማቁሰል ይታመናል” በማለት ይገልጻል። (ምሳሌ
27:6) ሥነ ምግባራዊም ሆነ መንፈሳዊ አቋማችንን ለማጠናከር ለአምላክና ለመሠረታዊ ሥርዓቶቹ ፍቅር ካላቸው ሰዎች ጋር ጓደኛ መሆን
ይኖርብናል። በፈረንሳይ የምትኖረው ሴሊን “በምማርበት ትምህርት ቤት እንደ እኔ ያለ ክርስቲያናዊ እምነትና ሥነ ምግባራዊ አቋም
ያላቸው ተማሪዎች ከሌሉ እውነተኛ ጓደኝነት መመሥረት ያለብኝ በጉባኤ ውስጥ ካሉ ክርስቲያኖች ጋር መሆን እንዳለበት ተገንዝቤያለሁ።
እነዚህ ጓደኞቼ ሚዛኔን እንድጠብቅ በእጅጉ ረድተውኛል” ስትል ተናግራለች።
ከአንድ ከተዋወቅከው ሰው ጋር ጓደኝነት መመሥረት ከፈለግህ ‘ጓደኞቹ
እነማን ናቸው?’ ብለህ መጠየቅህ ጠቃሚ ሊሆን ይችላል። የቅርብ ጓደኞቹ እነማን እንደሆኑ ማወቅህ ስለ እሱ ማንነት ጥሩ ግንዛቤ
እንድታገኝ ሊረዳህ ይችላል። በተጨማሪም በአካባቢው ያሉ የጎለመሱና የተከበሩ ሰዎች ለእርሱ ያላቸው አመለካከት ምንድን ነው? እንዲሁም
ጓደኛ ልናደርጋቸው ያሰብናቸው ሰዎች ከእኛ ጋር ያላቸው ግንኙነት ጥሩ ስለመሆኑ ብቻ ሳይሆን ከሌሎች ጋር ስላላቸው ግንኙነት ጭምር
ማሰብ ይኖርብናል። በተለይ ከጥቅም አንጻር ብዙም ሊያደርጉላቸው ለማይችሉ ሰዎች ያላቸው አመለካከት ምን ይመስላል? አንድ ሰው በማንኛውም
ጊዜ፣ ለሁሉም ሰው እንደ ሐቀኝነት፣ ታማኝነት፣ ትዕግሥትና አሳቢነት የመሳሰሉ ግሩም ባሕርያትን የማያሳይ ከሆነ ለአንተስ ወደፊት
ጥሩ ጓደኛ ሊሆንህ እንደሚችል ምን ዋስትና ይኖርሃል?
አንድ ሰው በዕለት ተዕለት ሕይወቱ የሚያንጸባርቀውን እውነተኛ ባሕርይ
በደንብ ለማወቅ ትዕግሥትና ብልሃት እንዲሁም ጊዜ ይጠይቃል። መጽሐፍ ቅዱስ “የሰው ልብ ሐሳብ እንደ ጥልቅ ውሃ ነው፤ አስተዋይ
ሰው ግን ከዚያ ቀድቶ ያወጣዋል” ይላል። (ምሳሌ 20:5) ጓደኛ ልናደርጋቸው ያሰብናቸውን ሰዎች እውነተኛ ባሕርይ፣ ዝንባሌ እንዲሁም
የሥነ ምግባር አቋም መገምገም እንዲያስችለን አንዳንድ ወሳኝ የሆኑ ርዕሰ ጉዳዮችን ማንሳቱ ጥሩ ሊሆን ይችላል። ምን ዓይነት አመለካከት
ያላቸው ሰዎች ናቸው? ደግ ናቸው ወይስ አይደሉም? እንዲያው በአብዛኛው ሲታዩ አዎንታዊና ብሩህ አመለካከት ያላቸው ናቸው ወይስ
አፍራሽ አመለካከት ያላቸውና ተጠራጣሪዎች? ለጋስ ናቸው ወይስ ራስ ወዳድ? እምነት የሚጣልባቸው ናቸው ወይስ የማይታመኑ? አንድ
ሰው ሌሎችን ለአንተ የሚያማ ከሆነ አንተንስ ለሌሎች እንዳያማ ምን ይከለክለዋል? ኢየሱስ “በልብ ውስጥ የሞላውን አንደበት ይናገረዋል”
ሲል ገልጿል። (ማቴዎስ 12:34) ሰዎች የሚናገሩት ነገር ማንነታቸውን ስለሚገልጽ ልብ ብለን ማዳመጥ ይኖርብናል።
አንዳንዶች ጓደኞቻቸው ልክ እንደ እነሱ ዓይነት ምርጫ ሊኖራቸው እንደሚገባ
አድርገው ያስባሉ። አንድ ትንሽ ልጅ “እኔ የምወደውን ዓይነት ኬክ የማይወድ ሰው በፍጹም ጓደኛዬ እንዲሆን አልፈልግም” ሲል ተናግሯል።
እርግጥ ነው፣ ጓደኛሞች እርስ በርስ ይበልጥ ሊግባቡ የሚችሉት በብዙ ነገር የሚመሳሰሉ ከሆነ ነው። በተለይ ደግሞ ተመሳሳይ የሆነ
ሥነ ምግባራዊና መንፈሳዊ አቋም ሊኖራቸው ይገባል። ይህ ሲባል ግን ባሕርያቸውም ሆነ አስተዳደጋቸው አንድ ዓይነት መሆን አለበት
ማለት አይደለም። እንዲያውም የተለያየ የሕይወት ተሞክሮ ያላቸው መሆኑ ሊጠቅማቸውና ጓደኝነታቸውን ሊያጠነክርላቸው ይችላል።
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ተመዝግቦ የሚገኘው በዮናታንና በዳዊት እንዲሁም
በሩትና በኑኃሚን መካከል የነበረው ግንኙነት ጓደኝነትን በተመለከተ ጊዜ የማይሽረው ምሳሌ ይሆነናል። እነዚህ ሰዎች የሚያመልኩት
አምላክም ሆነ የሚመሩበት መሠረታዊ ሥርዓት አንድ ነበር።* በዮናታንና በዳዊት እንዲሁም በሩትና በኑኃሚን መካከል በዕድሜም ሆነ
በአስተዳደግ ረገድ ትልቅ ልዩነት ነበር። በመሆኑም ጓደኝነትን በተመለከተ ከእነሱ አንድ ቁምነገር እንማራለን። ይኸውም ወጣቶችና
በዕድሜ ትልቅ የሆኑ ጓደኝነት ከመሠረቱ አንዳቸው ከሌላው ጥቅም ማግኘታቸው የማይቀር ነው።
በዕድሜ የተለያዩ
መሆን ያለው ጥቅም
ከእኛ በዕድሜ ከሚበልጡ ወይም ከሚያንሱ ጋር ጓደኝነት መመሥረታችን
ለሁለታችንም ከፍተኛ ጥቅም ይኖረዋል። በዚህ ረገድ ጥቅም ያገኙ ወጣቶች የተናገሩትን ተሞክሮ እስቲ እንመልከት።
“በዕድሜ ጠና ያሉ አንድ ባልና ሚስት ጓደኞች ነበሩኝ። እኔ የሚሰማኝን
ሁሉ እነግራቸዋለሁ፤ ደስ የሚለው ደግሞ እነሱም የሚሰማቸውን ሁሉ ይነግሩኛል። ልጅ ነች ብለው አይንቁኝም። ይህም ይበልጥ እንድወዳቸው
አደረገኝ። ከእነርሱ ጋር ጓደኛ መሆኔ በተለይ ችግር ሲገጥመኝ በእጅጉ ጠቅሞኛል። ችግሬን ለዕድሜ እኩዮቼ ሳጫውታቸው ብዙውን ጊዜ
የሚሰጡኝ ምክር ያልታሰበበት እንደሆነ አስተውያለሁ። እነዚህ በዕድሜ ጠና ያሉ ጓደኞቼ ግን እኛ ወጣቶች ገና ያልደረስንበት ተሞክሮ፣
ማስተዋልና ብስለት አላቸው። እነዚህ ጓደኞቼ በሕይወቴ ውስጥ ጥሩ ውሳኔዎችን እንዳደርግ ረድተውኛል።”
“ተሰባስበን
በምንጫወትበት ጊዜ ወጣቶችን ብቻ ሳይሆን በዕድሜ ጠና ያሉትንም እንጨምራለን። ወጣቶችና አዋቂዎች አንድ ላይ ተሰባስበን ስንጫወት
ውለን ማታ ስንለያይ ሁላችንም ተበረታተን ወደ ቤታችን እንደምንመለስ አስተውያለሁ። እንዲህ ያለ አስደሳች ጊዜ እንድናሳልፍ የሚረዳን
ሁላችንም በመጠኑም ቢሆን የተለያየ ዓይነት አመለካከት ያለን መሆኑ ነው።”
እናንተ ትልልቆችም ብትሆኑ ወጣቶችን ልትቀርቧቸው ይገባል። ከላይ
የተሰጡት አስተያየቶች እንደሚያሳዩት ወጣቶች የእናንተን የካበተ ተሞክሮ የሚያደንቁ ከመሆኑም በላይ አብረዋችሁ መሆን ያስደስታቸዋል። በሰማንያዎቹ ዕድሜ የሚገኙ አንዲት መበለት “ወጣቶችን ሆነ ብዬ እቀርባቸዋለሁ።
የእነሱን ብርታትና ጥንካሬ ሳይ እኔም መንፈሴ ይታደሳል!” በማለት ገልጸዋል። በዚህ መንገድ እርስ በርስ መበረታታት ይህ ነው የማይባል
ጥቅም አለው። ብዙ ጎልማሶች በሕይወታቸው ደስተኛና ስኬታማ ሊሆኑ የቻሉት ወጣት በነበሩበት ጊዜ በዕድሜ የሚበልጧቸውና ምሳሌ የሚሆኗቸው
ጓደኞቻቸው በሰጧቸው ጥሩ ምክር እንደሆነ ይናገራሉ።
ጓደኝነትን
ማጠናከር
ጥሩ ጓደኝነት ለመመሥረት አዲስ ጓደኞችን ማፍራት አለብህ ማለት አይደለም።
መልካም ባሕርይ ያላቸው ጓደኞች ካሉህ ጓደኝነታችሁ ይበልጥ የሚጠናከርበትን መንገድ ለምን አትፈልግም? የረጅም ጊዜ ጓደኞች ምንጊዜም
ውድ ስለሆኑ በአክብሮት ልንይዛቸው ይገባል። በጓደኝነት ያሳለፋችሁትን ጊዜ አቅልለህ ልትመለከተው አይገባም።
ከሁሉም በላይ ደግሞ እውነተኛ ደስታም ሆነ እውነተኛ ጓደኛ ማግኘት
የምትችለው ራስህን፣ ጊዜህንና ጥሪትህን በመስጠት መሆኑን አትዘንጋ። የምታገኘው በረከት ከምትከፍለው መሥዋዕትነት በእጅጉ የላቀ
ነው። ጓደኛ በምትመርጥበት ጊዜ ሁሌ የራስህን ጥቅም ብቻ የምታስብ ከሆነ መቼም ቢሆን ሊሳካልህ አይችልም። በመሆኑም ጓደኛ ለመምረጥ
ስታስብ በምታደንቃቸው ወይም ይጠቅሙኛል ብለህ በምታስባቸው ላይ ብቻ አታተኩር። ከዚህ ይልቅ ሌሎች ብዙ ትኩረት የማይሰጧቸውን ወይም
ጓደኛ በመመሥረት ረገድ ችግር ያለባቸውን መፈለግ ትችላለህ። ወጣት “እርስ በርስ ተገናኝተን ለመጫወት ስናስብ ብቸኝነት የሚሰማቸው
ወጣቶች እንዳሉ ስለምናውቅ እነሱንም እንጋብዛቸዋለን። ‘ብቻህን ቤት ቁጭ ከምትል ከእኛ ጋር መጫወት ትችላለህ፤ በዚያውም እርስ
በርስ እንተዋወቃለን’ እንላቸዋለን” በማለት ተናግራለች። ሉቃስ 14:12-14
በሌላ በኩል ደግሞ ጥሩ ሰዎች ጓደኛ ሊያደርጉህ ሲሞክሩ ቶሎ ብለህ
ፊት አትንሳቸው። “ከዚህ ቀደም ሰዎች እንዳገለሉህ ሲሰማህ በውስጥህ ትንሽ ቅሬታ ያድርብሃል። እንዲያውም ‘ጓደኛ ኖረኝ አልኖረኝ
ምንም ጥቅም የለውም’ ብለህ ማሰብ ትጀምራለህ። ከዚያም ዝምተኛ ወደመሆን፣ ራስህን ወደማግለልና ስለ ራስህ ብቻ ወደማሰብ ታዘነብላለህ።
ጓደኛ ከመፈለግ ይልቅ ሌሎች እንዳይቀርቡህ መንገዱን ሁሉ ትዘጋለህ” በማለት አስተያየቷን ሰጥታለች። አጉል ፍርሃት ወይም ራስ ወዳድነት
አዳዲስ ጓደኞች እንዳታፈራ እንቅፋት እንዲሆንብህ ከመፍቀድ ይልቅ ሌሎች እንዲቀርቡህ መንገዱን ክፍት አድርግ። ሌሎች ለአንተ አስበው
ጓደኛ ሊያደርጉህ ሲፈልጉ ከልብ ልታደንቃቸው ይገባል።
እውነተኛ
ጓደኞች ማፍራት
እውነተኛ ጓደኞችን ለማፍራት ምኞት፣ ሌሎች ለጓደኝነት እስኪጋብዙን
ድረስ መጠበቅና ጓደኛ ስለማፍራት ምክር የሚሰጡ ይህን የመሳሰሉ ርዕሶችን ማንበብ ብቻ አይበቃም። ጓደኛ ለማፍራት መሞከር ብስክሌት
ለመንዳት ከመለማመድ ጋር ይመሳሰላል። እንዲሁ በማንበብ ብቻ ጓደኛ የማፍራትም ሆነ ብስክሌት የመንዳት ችሎታ ማዳበር አይቻልም።
በተደጋጋሚ ልንወድቅ ብንችልም የግድ እየነዳን መለማመድ ያስፈልገናል። መጽሐፍ ቅዱስ ከሌሎች ጋር የጠበቀ ጓደኝነት መመሥረት የምንችለው
ከአምላክ ጋር የጸና ወዳጅነት መመሥረት ስንችል እንደሆነ ይናገራል። ሆኖም አምላክ ከእሱ ጋር ወዳጅነት ለመመሥረት ጥረት የማናደርግ
ከሆነ ከሌሎች ሰዎች ጋር ጓደኝነት ለመመሥረት የምናደርገውን ጥረት አይባርክልንም። በእርግጥ እውነተኛ ጓደኞችን ማፍራት ትፈልጋለህ?
ከሆነ ተስፋ አትቁረጥ! አምላክ እንዲረዳህ ጸልይ፣ ከራስ ወዳድነት ነፃ በሆነ ስሜት ሌሎችን ቅረብ እንዲሁም አንተ ራስህ ጓደኛ
ሁን። የእነዚህን ሰዎች ጓደኝነት በተመለከተ ሩት፣ አንደኛ ሳሙኤል እና ሁለተኛ ሳሙኤል የተባሉትን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ማንበብ
ትችላለህ።
ለወላጆች
የተሰጠ ማሳሰቢያ
ሌሎች
ብዙ ነገሮችን ከቤት እንደምንማር ሁሉ ስለ ጓደኝነትም መማር የምንጀምረው ከቤት ነው። በመሠረቱ የቤተሰብ ሕይወት ራሱ የአንድን
ትንሽ ልጅ የጓደኝነት ፍላጎት በሙሉ ያሟላል። በእንደዚህ ዓይነት ሁኔታ ሥር እያለም እንኳ አንድ ልጅ ከቤተሰቡ ውጭ የሚኖረው ግንኙነት
በአስተሳሰቡ፣ በስሜቱና በባሕርይው ላይ ተጽዕኖ ያሳድራል። ለምሳሌ ያህል፣ ከሌላ አገር ተሰደው የመጡ ሕፃናት ልጆች ከሌሎች ልጆች
ጋር ባላቸው ግንኙነት ብቻ አንድን አዲስ ቋንቋ ወዲያው የመናገር ችሎታ እንደሚያዳብሩ አስተውለህ ይሆናል።
ወላጅ
እንደመሆንህ መጠን ልጆችህ ጓደኞችን እንዴት በጥበብ መምረጥ እንዳለባቸው የመርዳት ጥሩ አጋጣሚ አለህ። ትንንሽ ልጆችና በጉርምስና
ዕድሜ ላይ የሚገኙ ወጣቶች ያለወላጅ እርዳታ ጓደኞቻቸውን በጥበብ ሊመርጡ አይችሉም። ሆኖም በዚህ ረገድ ችግር አለ። አብዛኞቹ ወጣቶች
ከወላጆቻቸው ወይም በዕድሜ ከሚበልጧቸው ጋር ከመወዳጀት ይልቅ ከእኩዮቻቸው ጋር መቀራረብን ይመርጣሉ።
ወጣቶች ምክር ለማግኘት ከወላጆቻቸው ይልቅ ወደ እኩዮቻቸው ዞር የሚሉበት
አንዱ ምክንያት ወላጆች የወላጅነት ግዴታቸውን በአግባቡ ስለማይወጡ መሆኑን አንዳንድ ባለሙያዎች ተናግረዋል። ወላጆች ለልጆቻቸው
መመሪያ ለመስጠት ጥረት በማድረግና ስለ ልጆቻቸው ከልብ የሚያስቡ በመሆን አምላክ የሰጣቸውን ኃላፊነት መወጣት ይጠበቅባቸዋል።
(ኤፌሶን 6:1-4) ግን እንዴት? ዶክተር ሮን ታፍል የተባሉ የቤተሰብ ኑሮ አማካሪ በጉርምስና ዕድሜ ላይ ከሚገኙ ልጆቻቸው ጋር
እንዴት መግባባት እንደሚችሉ ግራ የገባቸው ብዙ ወላጆች እንደሚያጋጥሟቸው ተናግረዋል። አብዛኞቹ ወላጆች የወላጅነት ግዴታቸውን ከመወጣት
ይልቅ “በመገናኛ ብዙኃን በስፋት በሚሰራጨው ዘመን አመጣሽ የልጅ አስተዳደግ ይሸነፋሉ” ብለው ጽፈዋል። ወላጆች ግን በዚህ አመለካከት
የሚሸነፉት ለምንድን ነው? “ልጆቻቸውን በደንብ ካለማወቃቸው የተነሳ የእነሱን ሐሳብ መረዳትም ሆነ ለጥያቄዎቻቸው መልስ መስጠት
ስለማይችሉ ነው።”
ሆኖም
ወላጆች ከወጣት ልጆቻቸው ጋር ጥሩ ግንኙነት እንዲኖራቸው ማድረግ ይችላሉ። ልጆች የሚፈልጉትን ነገር ከወላጅ ካላገኙ ወደ ጓደኞቻቸው
ዞር ማለታቸው እንደማይቀር ወላጆች ማወቅ አለባቸው። ታዲያ ልጆች የሚፈልጉት ነገር ምንድን ነው? “ማንኛውም ወጣት የሚፈልገውን ሁሉ ይፈልጋሉ፤ ይህም ማለት እንክብካቤ፣ አድናቆት፣
አይዞህ መባል፣ የማያሻማ መመሪያ፣ ከእነሱ ምን እንደሚጠበቅ ግልጽ የሆነ ማብራሪያና በቤተሰቡ ውስጥ ተፈላጊ እንደሆኑ የሚያረጋግጥ
ነገር ይፈልጋሉ” በማለት ተናግረዋል። አክለውም “የሚያሳዝነው ግን በዛሬው ጊዜ ያሉ አብዛኞቹ ወጣቶች ወላጆቻቸው ከላይ የተዘረዘሩትን
ፍላጎቶቻቸውን ሊያሟሉላቸው አልቻሉም፤ እንዲሁም ቤተሰባቸው ‘የራሳቸው ቤተሰብ እንደሆነ’ አይሰማቸውም” ብለዋል።
ልጆቻችሁ ጥሩ ጓደኞች እንዲያፈሩ እንዴት መርዳት ትችላላችሁ? በመጀመሪያ
ደረጃ አንተ ራስህ ሕይወትህን የምትመራበትን መንገድና የጓደኛ ምርጫህን በተመለከተ በጥሞና አስብ። የአንተም ሆነ የጓደኞችህ አኗኗርና
የሕይወት ግብ ከራስ ወዳድነት ነፃ የሆነና በምሳሌነት የሚጠቀስ ነው? መንፈሳዊ ነው ወይስ በቁሳዊ ነገሮች ላይ ያተኮረ? “ከቃልህ
ይልቅ ድርጊትህ ተጽዕኖ ስለሚያሳድር ልጆችህ የአንተንም ሆነ የጓደኞችህን እንዲሁም የጓደኞችህን ልጆች ጠባይና ድርጊት እንደሚያስተውሉ
መዘንጋት የለብህም”
እንስሳት
እንኳን በደመ ነፍስ በመመራት ልጆቻቸውን ከአደጋ ለመጠበቅ ከፍተኛ ጥረት ያደርጋሉ። ስለ ድብ የሚያጠኑ አንድ ባለሙያ እንዳሉት
“እናት ድቦች ግልገሎቻቸውን ሊያጠቃ ከሚችል ከማንኛውም ነገር በመከላከል ረገድ የታወቁ ናቸው” በማለት ተናግረዋል። ታዲያ ሰብዓዊ
ወላጆችስ ከዚህ ያነሰ ነገር ማድረግ ይጠበቅባቸዋል? ወጣት “ወላጆቼ
ከአጉል ጓደኛ ጋር ስገጥም ከመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ እያወጡ በማስረዳት ይመክሩኝ ነበር። በዚህ ጊዜ መጀመሪያ የሚሰማኝ ስሜት ‘ተመልከቱ
እንግዲህ! ጭራሽ ጓደኞች መያዝ አልችልም ማለት ነው እኮ’ የሚል ነበር። ጊዜ እያለፈ በሄደ ቁጥር ግን ወላጆቼ ትክክል መሆናቸውን
መገንዘብ ችያለሁ፤ ለትዕግሥታቸው አመሰግናቸዋለሁ፤ ከክፉ እንድጠበቅ ረድተውኛል” በማለት ተናግሯል።
በተጨማሪም ልጆቻችሁን ከሌሎች ማለትም መልካም ምሳሌ ከሚሆኑና ጥሩ ግቦችን ለማውጣት ከሚረዷቸው ጓደኞች ጋር እንዲተዋወቁ አድርጉ። ደስተኛና ጥሩ ደረጃ ላይ የሚገኝ ወጣት “እናታችን ወንዶቹ ልጆች ማንኛውንም ነገር የምናደርገው በአብዛኛው እርስ በርሳችን እንደሆነ ስላስተዋለች በሙሉ ጊዜ አገልግሎት ውስጥ ያሉ ወጣት ወንድሞችን ቤት ትጋብዝልን ነበር። ይህም ከእነሱ ጋር እንድንተዋወቅና ጓደኝነት እንድንመሠርት ረድቶናል” በማለት እናታቸው ያደረገችላቸውን በማስታወስ ይናገራል። በበኩልህ እንደዚህ የመሰለ ጥረት ካደረግክ ልጆችህ ጥሩ ጓደኝነት ሊመሠርቱ የሚችሉበት አጋጣሚ ልትፈጥርላቸው ትችላለህ።
የክፋት መነሻው
በተጨማሪም ልጆቻችሁን ከሌሎች ማለትም መልካም ምሳሌ ከሚሆኑና ጥሩ ግቦችን ለማውጣት ከሚረዷቸው ጓደኞች ጋር እንዲተዋወቁ አድርጉ። ደስተኛና ጥሩ ደረጃ ላይ የሚገኝ ወጣት “እናታችን ወንዶቹ ልጆች ማንኛውንም ነገር የምናደርገው በአብዛኛው እርስ በርሳችን እንደሆነ ስላስተዋለች በሙሉ ጊዜ አገልግሎት ውስጥ ያሉ ወጣት ወንድሞችን ቤት ትጋብዝልን ነበር። ይህም ከእነሱ ጋር እንድንተዋወቅና ጓደኝነት እንድንመሠርት ረድቶናል” በማለት እናታቸው ያደረገችላቸውን በማስታወስ ይናገራል። በበኩልህ እንደዚህ የመሰለ ጥረት ካደረግክ ልጆችህ ጥሩ ጓደኝነት ሊመሠርቱ የሚችሉበት አጋጣሚ ልትፈጥርላቸው ትችላለህ።
የክፋት መነሻው
የታሪክ መዝገብ ስለ ጥላቻና ደም መፋሰስ በሚገልጹ ዘገባዎች የተሞላ
ነው። እንደዚያም ሆኖ ብዙውን ጊዜ አሳዛኝ ክስተቶች በሚፈጠሩበት ወቅት ሰዎች ደግነትና ራስን መሥዋዕት የማድረግ መንፈስ የሚንጸባረቅባቸውን
አስደናቂ ነገሮች ሲያከናውኑ ይስተዋላል። ሆኖም አንደኛው ርኅራኄ የሌለው ነፍሰ ገዳይ የሚሆነውና ሌላኛው ከልብ በመራራት ሰዎችን
ለመርዳት የሚነሳሳው ለምንድን ነው? አንዳንድ ጊዜ ሰዎች እንስሳዊ የሆኑ ባሕርያትን የሚያንጸባርቁትስ ለምንድን ነው?
መጽሐፍ ቅዱስ “ሰው ገና ከልጅነቱ ጀምሮ ሐሳቡ ወደ ክፋት ያዘነበለ”
እንደሆነ በግልጽ ይናገራል። (ዘፍጥረት 8:21) በመሆኑም ልጆች ተንኮል መሥራት ይቀናቸዋል። (ምሳሌ 22:15) ሁላችንም ስንወለድ
ጀምሮ የሚቀናን ትክክል ያልሆነ ነገር ማድረግ ነው። (መዝሙር 51:5) የወንዝ ውኃ ከሚመጣበት አቅጣጫ በተቃራኒ መቅዘፍ ቀላል
እንዳልሆነ ሁሉ ጥሩ ነገር ማድረግም ብርቱ ጥረት ይጠይቃል። ያም ሆኖ ሁላችንም ሕሊና አለን። ይህ በተፈጥሮ ያገኘነው ትክክልና
ስህተት የሆነውን የመለየት ችሎታ በብዙዎች ዘንድ ተቀባይነት ባለው የሥነ ምግባር ደንብ መሠረት እንድንመራ ይገፋፋናል። በዚህም
ምክንያት በሥነ ምግባር ረገድ ምንም ሥልጠና ያላገኙ ሰዎችም እንኳ ደግነት በሚንጸባረቅበት ድርጊታቸው የሚታወቁ ሊሆኑ ይችላሉ።
(ሮም 2:14, 15) ይሁንና ከላይ እንደተገለጸው ልባችን ወደ ክፋት ያዘነበለ መሆኑ በውስጣችን ትግል እንዲፈጠር ሊያደርግ ይችላል።
ጥሩ በማድረግና ክፉ በማድረግ መካከል በውስጣችን ትግል እንዲፈጠር የሚያደርገው ሌላው ምክንያት ምንድን ነው?
እስስት አካባቢዋን ለመምሰል የቆዳዋን ቀለም እንደምትለዋውጥ ሁሉ
ዓመፀኛ የሆኑ ሰዎችን ወዳጆቻቸው የሚያደርጉ ግለሰቦችም የእነሱን እኩይ ምግባር ማንጸባረቃቸው አይቀርም። መጽሐፍ ቅዱስ “ክፉ በማድረግ
ብዙዎችን አትከተል” በማለት ያስጠነቅቃል። (ዘፀአት 23:2) በሌላ በኩል ደግሞ ሐቀኞችና ቅኖች ከሆኑ እንዲሁም ጥሩ ሥነ ምግባር
ካላቸው ሰዎች ጋር ዘወትር መቀራረብ ጥሩ የሆነውን ለማድረግ ያነሳሳል። ምሳሌ 13:20
ይሁን እንጂ ‘መጥፎ ድርጊት ከሚፈጽሙ ሰዎች ጋር ወዳጅነት እስካልመሠረትኩ
ድረስ ክፋት እንድፈጽም የሚያደርገኝ ምንም ነገር አይኖርም’ ብለን ማሰብ አንችልም። ፍጹማን ስላልሆን ክፋት በአእምሯችን ጓዳ ውስጥ
ተደብቆ ሊቆይ ይችላል፤ አጋጣሚውን ያገኘ ዕለት ግን ይፋ ይሆናል። (ዘፍጥረት 4:7) ከዚህም በላይ ክፋት በመገናኛ ብዙኃን አማካኝነት
ቤታችን ድረስ ሊመጣ ይችላል። የቪዲዮ ጨዋታዎች፣ የቴሌቪዥን ፕሮግራሞችና ፊልሞች ብዙውን ጊዜ ዓመፀኝነትንና በቀለኝነትን ያራግባሉ።
የውጭም ይሁን የአገር ውስጥ ዜናዎችን አዘውትረን መከታተላችን እንኳ ሰዎችን ለመከራና ሰቆቃ በሚዳርጉ የክፋት ድርጊቶች መዘግነናችንን
እንድናቆም ሊያደርገን ይችላል።
ለመሆኑ አካባቢያችን በመጥፎ ድርጊት እንዲበከል መንስኤ የሆነው
ነገር ምንድን ነው? መጽሐፍ ቅዱስ “መላው ዓለም ግን በክፉው ኃይል ሥር ነው” በማለት መልሱን ይሰጠናል። (1 ዮሐንስ
5:19) መጽሐፍ ቅዱስ “ክፉው” የተባለው ሰይጣን ዲያብሎስ ውሸታምና ነፍሰ ገዳይ እንደሆነ በግልጽ ይናገራል። (ዮሐንስ
8:44) ሰይጣን ዲያብሎስ ይህ ዓለም በሚያሳድረው ተጽዕኖ በመጠቀም ክፋትን ያስፋፋል።
‘በአመለካከታችንና በተግባራችን ላይ ተጽዕኖ የሚያሳድሩ እነዚህ
ሁሉ ምክንያቶች ስላሉ ለምናደርጋቸው ነገሮች ልንወቀስ አይገባም’ በማለት አንዳንዶች ለክፋት ድርጊታቸው ሰበብ ለማቅረብ ይሞክሩ
ይሆናል። እውነታው ግን ምንድን ነው? የመኪና ወይም የመርከብ መሪ አቅጣጫን እንደሚቆጣጠር ሁሉ አእምሮም ሰውነትን ይቆጣጠራል።
ጥሩ ወይም ክፉ ማድረግ—ምርጫው
ሰዎች ሆነ ብለው የሚፈጽሙት ነገር ጥሩም ይሁን ክፉ ከድርጊት በፊት
ሐሳብ ይቀድማል። አንድ ሰው መልካም ዘር ከዘራ ጥሩ ፍሬ እንደሚያጭድ ሁሉ እኛም የምናስበው ነገር አዎንታዊና ንጹሕ ከሆነ ጥሩ
ነገር ለመሥራት እንነሳሳለን። በተቃራኒው ደግሞ በአእምሯችን ውስጥ የራስ ወዳድነት ምኞት እንዲያቆጠቁጥ ከፈቀድን መጥፎ ፍሬ ማጨዳችን
ማለትም የተለያዩ የክፋት ድርጊቶችን መፈጸማችን አይቀርም። (ሉቃስ 6:43-45፤ ያዕቆብ 1:14, 15) በመሆኑም አንድ ሰው ጥሩ
ወይም ክፉ የሚሆነው በራሱ ምርጫ ነው ሊባል ይችላል።
ደስ የሚለው ነገር፣ መጽሐፍ ቅዱስ መልካም ማድረግን መማር እንደሚቻል
ይናገራል። (ኢሳይያስ 1:16, 17) ፍቅር ጥሩ የሆነውን ነገር ለማድረግ የሚገፋፋ ኃይል ነው፤ ምክንያቱም “ፍቅር በባልንጀራው
ላይ ክፉ አያደርግም።” (ሮም 13:10) ለሰዎች ፍቅር ካዳበርን በማንም ላይ ክፉ መሥራት የማይታሰብ ነገር ይሆናል።
ድብድብ ተምሮ ስላደገ ገና በልጅነቱ ፓንች (ቡጢኛው) የሚል ቅጽል
ስም አትርፎ ነበር። በተጨማሪም የግልፍተኝነት ባሕርይው ያስቸግረው ነበር። የመጽሐፍ ቅዱስን መሠረታዊ ሥርዓቶች በሥራ ላይ ሲያውል
ግን ቀስ በቀስ ለውጥ አደረገ። ይሁን እንጂ ይህን ማድረግ ለእሱ ሁልጊዜ ቀላል አልነበረም። የመጽሐፍ
ቅዱስ ጸሐፊ የሆነው ጳውሎስ “ትክክል የሆነውን ነገር ማድረግ ስፈልግ ከእኔ ጋር ያለው ግን መጥፎ ነገር ነው” በማለት የተናገረው
ዓይነት ስሜት የሚሰማው ጊዜ ነበር። (ሮም 7:21) ለዓመታት ከፍተኛ ጥረት ካደረገ በኋላ ግን ‘ክፉን በመልካም ማሸነፍ’ ችሏል። ሮም 12:21
ጥሩ ወይም ‘ደጋግ በሆኑ ሰዎች ጎዳና ለመሄድ’ ጥረት ማድረግ አስፈላጊ
ነው የምንለው ለምንድን ነው? (ምሳሌ 2:20-22) ምክንያቱም የኋላ ኋላ ጥሩነት በክፋት ላይ ድል ይቀዳጃል። መጽሐፍ ቅዱስ
“ክፉ ሰዎች ይጠፋሉ፤ . . . ለአፍታ እንጂ፣ ክፉ ሰው አይዘልቅም፤ . . . ገሮች ግን ምድርን ይወርሳሉ፤ በታላቅ ሰላምም ሐሤት
ያደርጋሉ” በማለት ይናገራል። (መዝሙር 37:9-11) አምላክ የክፋትን ርዝራዦች በሙሉ ያስወግዳል። ጥሩ የሆነውን ነገር ዘወትር
ለማድረግ ከልባቸው የሚጥሩ ሰዎች ከፊታቸው እንዴት ያለ ታላቅ ተስፋ ይጠብቃቸዋል!
ይህን አስተውለኸዋል?
● ለምናደርገው ነገር ኃላፊነቱን መውስድ ያለበት ማን ነው? ያዕቆብ 1:14
● አካሄዳችንን ማስተካከል እንችላለን? ኢሳይያስ 1:16, 17
● ክፋት ማብቂያ ይኖረው ይሆን? መዝሙር 37:9, 10፤ ምሳሌ 2:20-22
በዚህ ክፉ
ዓለም ውስጥ “ጊዜያዊ ነዋሪ” ሆኖ መኖር
“እነዚህ ሁሉ . . . በምድሩም ላይ እንግዶችና ጊዜያዊ ነዋሪዎች
መሆናቸውን በይፋ ተናገሩ።” ዕብ. 11:13
ኢየሱስ ስለ ደቀ መዛሙርቱ ሲናገር “በዓለም ውስጥ ናቸው” ብሏል።
ይሁን እንጂ አክሎ “እኔ የዓለም ክፍል እንዳልሆንኩ ሁሉ እነሱም የዓለም ክፍል [አይደሉም]” በማለት ተናግሯል። (ዮሐ.
17:11, 14) ኢየሱስ ይህን ሲል እውነተኛ ተከታዮቹ ሰይጣን አምላኩ ከሆነለት ‘ከዚህ ሥርዓት’ ጋር በተያያዘ ሊኖራቸው የሚገባውን
አቋም በግልጽ መናገሩ ነበር። (2 ቆሮ. 4:4) ምንም እንኳ የሚኖሩት በዚህ ክፉ ዓለም ውስጥ ቢሆንም የዚህ ዓለም ክፍል መሆን
የለባቸውም። በዚህ ሥርዓት ውስጥ ያሉበት ሁኔታ “መጻተኞችና ጊዜያዊ ነዋሪዎች” ከሆኑ ሰዎች ጋር ይመሳሰላል። 1 ጴጥ. 2:11
ከጥፋት ውኃ በፊት የነበሩት ሄኖክና ኖኅ ‘አካሄዳቸውን ከእግዚአብሔር
ጋር አድርገዋል።’ (ዘፍ. 5:22-24፤ 6:9) ሁለቱም ቢሆኑ እግዚአብሔር ክፉ በሆነው የሰይጣን ዓለም ላይ የሚያመጣውን ፍርድ
በድፍረት ሰብከዋል። (2 ጴጥሮስ 2:5ን እና ይሁዳ 14, 15ን አንብብ።) አምላካዊ ፍርሃት በሌለው ዓለም ውስጥ አካሄዳቸውን ከአምላክ ጋር በማድረጋቸው ሄኖክ
“አምላክን በሚገባ ደስ” እንዳሰኘ ሲነገርለት ኖኅ ደግሞ “ከበደል የራቀ ሰው” እንደነበር ተመሥክሮለታል። ዕብ. 11:5፤ ዘፍ.
6:9
አብርሃምና ሣራ፣ አምላክ ባቀረበላቸው ግብዣ መሠረት በከለዳውያን
ምድር በምትገኘው በዑር የነበራቸውን ምቾት ያለው ኑሮ ትተው በባዕድ አገር የዘላን ዓይነት ሕይወት ለመኖር ፈቃደኞች ሆነዋል።
(ዘፍ. 11:27, 28፤ 12:1) ሐዋርያው ጳውሎስ እነሱን በማስመልከት እንዲህ በማለት ጽፏል፦ “አብርሃም በተጠራ ጊዜ ወደፊት
ርስት አድርጎ እንዲወስደው ወደተወሰነለት ስፍራ ለመሄድ በመነሳት በእምነት ታዘዘ፤ ወዴት እንደሚሄድ ባያውቅም ይኖርበት የነበረውን
ስፍራ ለቆ ወጣ። በባዕድ አገር እንዳለ እንደ መጻተኛ በተስፋይቱ ምድር በእምነት ተቀመጠ፤ ከእሱ ጋር የዚሁ ተስፋ ቃል ወራሾች
ከሆኑት ከይስሐቅና ከያዕቆብ ጋርም በድንኳን ኖረ።” (ዕብ. 11:8, 9) ጳውሎስ እነዚህን ስለመሳሰሉ ታማኝ የእግዚአብሔር አገልጋዮች
አስመልክቶ እንዲህ ብሏል፦ “እነዚህ ሁሉ የተስፋውን ቃል ፍጻሜ ባያገኙም እምነታቸውን እንደጠበቁ ሞቱ፤ ሆኖም ከሩቅ አይተው በደስታ
ተቀበሉት፤ በምድሩም ላይ እንግዶችና ጊዜያዊ ነዋሪዎች መሆናቸውን በይፋ ተናገሩ።” ዕብ. 11:13
የአብርሃም ዝርያ የሆኑት እስራኤላውያን ቁጥራቸው እየበዛ ሄዶ የራሳቸው
የሆነ አገርና መተዳደሪያ ሕግ ያላቸው ብሔር ሆኑ። (ዘፍ. 48:4፤ ዘዳ. 6:1) ያም ሆኖ እስራኤላውያን፣ የሚኖሩባት ምድር ንብረትነቷ
የእግዚአብሔር መሆኑን ፈጽሞ መዘንጋት አልነበረባቸውም። (ዘሌ. 25:23) ምክንያቱም እስራኤላውያን የባለንብረቱን ፍላጎት የማክበር
ግዴታ እንዳለበት ተከራይ ነበሩ። ከዚህም በላይ ሰው “በእንጀራ ብቻ እንደማይኖር” ማስታወስ ይኖርባቸው ነበር፤ እንዲሁም ቁሳዊ
ብልጽግና እግዚአብሔርን እንዲረሱ ሊያደርጋቸው አይገባም ነበር። (ዘዳ. 8:1-3) እስራኤላውያን ወደ አገራቸው ከመግባታቸው በፊት
እንዲህ የሚል ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸው ነበር፦ “አምላክህ እግዚአብሔር ለአንተ ለመስጠት ለአባቶችህ ለአብርሃም፣ ለይስሐቅና ለያዕቆብ
ወደ ማለላቸው ምድር ሲያስገባህ፣ በዚያም ያልሠራሃቸውን ታላላቅና ያማሩ ከተሞችን፣ የራስህ ባልነበሩ መልካም ነገሮች ሁሉ የተሞሉ
ቤቶችን ያልቈፈርሃቸውን የውሃ ጕድጓዶች፣ ያልተከልሃቸውን የወይን ተክሎችና የወይራ ዛፎች ሲሰጥህና በልተህም ስትጠግብ፣ ከባርነት
ምድር ከግብፅ ያወጣህን እግዚአብሔርን እንዳትረሳ ተጠንቀቅ!”—ዘዳ. 6:10-12
ይህ ማስጠንቀቂያ መሰጠቱ ተገቢ ነበር። እስራኤላውያን ወደ ተስፋይቱ
ምድር ከገቡ በኋላ የፈጸሙት ነገር ምን ያህል አሳፋሪ እንደነበር በነህምያ ዘመን የነበሩ አንዳንድ ሌዋውያን ተናግረዋል። እስራኤላውያን
በተመቻቹ ቤቶች ውስጥ መኖር ሲጀምሩ እንዲሁም የተትረፈረፈ ምግብና ወይን ሲያገኙ “እስኪጠግቡ በሉ፤ ወፈሩም።” በኋላም በእግዚአብሔር
ላይ ያመፁ ሲሆን ይባስ ብሎም አምላክ እነሱን ለማስጠንቀቅ የላካቸውን ነቢያት ገደሉ። (ነህምያ 9:25-27ን አንብብ፤ ሆሴዕ 13:6-9) እምነት የለሾቹ አይሁዳውያን በሮም አገዛዝ ሥር በነበሩበት ወቅትም
ተስፋ የተደረገበትን መሲሕ እስከ መግደል ደርሰዋል! በመሆኑም እግዚአብሔር እነሱን በመተው አዲሱን ብሔር ማለትም መንፈሳዊ እስራኤላውያንን
እንደ ሕዝቡ አድርጎ ተቀበለ። ማቴ. 21:43፤ ሥራ 7:51, 52፤ ገላ. 6:16
‘የዓለም ክፍል አይደሉም’
የክርስቲያን ጉባኤ ራስ የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ፣ ተከታዮቹ የሰይጣን
ክፉ ሥርዓት ከሆነው ከዚህ ዓለም መለየት እንዳለባቸው በግልጽ ተናግሯል። ኢየሱስ ከመሞቱ ጥቂት ቀደም ብሎም ለደቀ መዛሙርቱ እንዲህ
ብሏቸው ነበር፦ “የዓለም ክፍል ብትሆኑ ኖሮ ዓለም የራሱ የሆነውን በወደደ ነበር። አሁን ግን እኔ ከዓለም መረጥኳችሁ እንጂ የዓለም
ክፍል ስላልሆናችሁ ከዚህ የተነሳ ዓለም ይጠላችኋል።” ዮሐ. 15:19
ክርስትና እየተስፋፋ ሲመጣ ክርስቲያኖች የዓለምን ልማዶች በመከተልና
የእሱ ክፍል በመሆን ከዓለም ጋር ተስማምተው መኖር ይጀምሩ ይሆን? የሚኖሩት የትም ይሁን የት ራሳቸውን ከሰይጣን ሥርዓት መለየት ነበረባቸው።
ሐዋርያው ጴጥሮስ፣ ክርስቶስ ከሞተ ከ30 ዓመታት ገደማ በኋላ በተለያዩ የሮም ግዛቶች ውስጥ ለሚኖሩ ክርስቲያኖች በጻፈው ደብዳቤ
ላይ እንዲህ ብሎ ነበር፦ “የተወደዳችሁ ወንድሞች፣ መጻተኞችና ጊዜያዊ ነዋሪዎች እንደመሆናችሁ መጠን ከነፍስ ጋር ከሚዋጉት ሥጋዊ
ምኞቶች ምንጊዜም እንድትርቁ አሳስባችኋለሁ። . . . በአሕዛብ መካከል መልካም ምግባር ይዛችሁ ኑሩ።”—1 ጴጥ. 1:1፤
2:11, 12
የጥንቶቹ ክርስቲያኖች፣ አኗኗራቸው እንደ “መጻተኞችና ጊዜያዊ ነዋሪዎች”
“በመጀመሪያዎቹ ሦስት መቶ ዘመናት ክርስቲያኖች ብዙውን ጊዜ ያለማቋረጥ ከባድ ስደት ይደርስባቸው እንደነበር ከማንም የተሰወረ አይደለም።
. . . የተለያየ የሐሰት ክስ ይሰነዘርባቸው ነበር። ክርስቲያኖች በአረማዊ በዓላት ላይ ባለመካፈላቸው ምክንያት አምላክ የለሾች
ተብለዋል። በአብዛኞቹ ማኅበራዊ ጉዳዮች ማለትም በአረማዊ ክብረ በዓላት ላይ እንዲሁም አረማዊ እምነቶች፣ ልማዶችና ሥነ ምግባር
የጎደላቸው ድርጊቶች የሞሉበት እንደሆነ አድርገው በሚያስቧቸው ሕዝባዊ የመዝናኛ ዝግጅቶች ላይ ባለመሳተፋቸው የሰውን ዘር እንደሚጠሉ
ተደርገው ይቆጠሩ ነበር።”
በዓለም ሙሉ በሙሉ አለመጠቀም
ይህ ሥርዓት በቅርቡ ከሕልውና ውጪ መሆኑ አይቀሬ ነው፤ በመሆኑም
እኛ የእግዚአብሔር አገልጋዮች ሊጠፋ በተቃረበው በዚህ ዓለም ውስጥ
የተደላደለ ኑሮ በመምራት ጊዜያችንን ማባከን እንደሌለብን እንረዳለን። ሐዋርያው ጳውሎስ እንዲህ በማለት የሰጠውን ማሳሰቢያ በሥራ
ላይ እናውላለን፦ “ወንድሞች፣ የቀረው ጊዜ አጭር መሆኑን ልነግራችሁ እወዳለሁ። ስለዚህ . . . የሚገዙም ምንም እንደሌላቸው እንዲሁም
በዓለም የሚጠቀሙ ሙሉ በሙሉ እንደማይጠቀሙበት ይሁኑ፤ ምክንያቱም የዚህ ዓለም ትእይንት እየተለዋወጠ ነው።” (1 ቆሮ.
7:29-31) በአሁኑ ጊዜ ያሉ ክርስቲያኖች በዓለም እየተጠቀሙ ያሉት እንዴት ነው? ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችንና የመገናኛ አውታሮችን
በመጠቀም የመጽሐፍ ቅዱስን መልእክት በመቶዎች በሚቆጠሩ ቋንቋዎች በዓለም ዙሪያ እንዲሰራጭ በማድረግ ነው። ለመኖር የሚያስፈልጓቸውን
ነገሮች ለማግኘት በተወሰነ መጠን በዓለም ይጠቀማሉ። ዓለም የሚያቀርባቸውን አንዳንድ አስፈላጊ የሆኑ ቁሳቁሶች ይገዛሉ፤ በሚሰጣቸው
አገልግሎቶችም ይጠቀማሉ። ያም ሆኖ ለቁሳዊ ነገሮችና ለሥራ ተገቢውን ቦታ በመስጠት በዓለም ሙሉ በሙሉ ከመጠቀም እንደሚርቁ ያሳያሉ።
1 ጢሞቴዎስ 6:9, 10ን አንብብ።
እኛ ክርስቲያኖች ጊዜያዊ ነዋሪዎች እንደመሆናችን መጠን ግባችን ከዚህ
የተለየ ነው። ‘ለራሳችን ታላቅ ነገር ከመሻት’ እንርቃለን። (ኤር. 45:5፤ ሮም 12:16) የኢየሱስ ተከታዮች በመሆናችን እንደሚከተለው
በማለት የሰጠንን ማስጠንቀቂያ ተግባራዊ ለማድረግ እንጥራለን፦ “አንድ ሰው ሀብታም ቢሆንም እንኳ ሕይወቱ በንብረቱ ላይ የተመካ
ስላልሆነ ተጠንቀቁ፤ ከመጎምጀትም ሁሉ ተጠበቁ።” (ሉቃስ 12:15) በዚህም የተነሳ ወጣት ክርስቲያኖች መንፈሳዊ ግቦችን እንዲያወጡ
በሌላ አባባል በአንድ በኩል እግዚአብሔርን ‘በሙሉ ልብ፣ በሙሉ ነፍስ፣ በሙሉ ኃይልና በሙሉ አእምሮ’ እያገለገሉ በሌላ በኩል ደግሞ
መሠረታዊ ፍላጎታቸውን ለማሟላት የሚያስችላቸውን ያህል ብቻ ሰብዓዊ ትምህርት እንዲከታተሉ ይበረታታሉ። (ሉቃስ 10:27) እንዲህ
የሚያደርጉ ከሆነ ‘በአምላክ ዘንድ ሀብታም’ መሆን ይችላሉ። ሉቃስ 12:21፤ ማቴዎስ 6:19-21ን አንብብ።
ስለ ኑሮ በመጨነቅ ሸክም እንዳይበዛባችሁ ተጠንቀቁ
የእግዚአብሔር አገልጋዮች ለቁሳዊ ነገር ያላቸው አመለካከት በዓለም
ላይ ከሚገኙ ሰዎች የተለየ ነው። በዚህ ረገድ ኢየሱስ ለተከታዮቹ እንዲህ ብሏቸው ነበር፦ “‘ምን እንበላለን?’ ወይም ‘ምን እንጠጣለን?’
ወይም ደግሞ ‘ምን እንለብሳለን?’ ብላችሁ ፈጽሞ አትጨነቁ። እነዚህ ነገሮች ሁሉ አሕዛብ አጥብቀው የሚፈልጓቸው ናቸው። በሰማይ
የሚኖረው አባታችሁ እነዚህ ሁሉ እንደሚያስፈልጓችሁ ያውቃል። እንግዲያው ከሁሉ አስቀድማችሁ የአምላክን መንግሥትና ጽድቅ መፈለጋችሁን
ቀጥሉ፤ እነዚህም ነገሮች ሁሉ ይሰጧችኋል።” (ማቴ. 6:31-33) በርካታ የእምነት ባልንጀሮቻችን በሰማይ የሚገኘው አባታችን የሚያስፈልጓቸውን
ነገሮች እንደሚያሟላላቸው በራሳቸው ሕይወት አይተዋል።
ኢየሱስ ስለ ዘሪው በተናገረው ምሳሌ ላይ “የዚህ ሥርዓት ጭንቀት
እንዲሁም ሀብት ያለው የማታለል ኃይል” በልባችን ውስጥ ያለውን የእግዚአብሔር ቃል ሊያንቀውና ፍሬ እንዳናፈራ ሊያደርገን እንደሚችል
ገልጿል። (ማቴ. 13:22) በዚህ ሥርዓት ውስጥ እንደ ጊዜያዊ ነዋሪ በመሆን ባለን ረክተን መኖራችን በዚህ ወጥመድ እንዳንወድቅ
ይጠብቀናል። እንዲሁም፣ ዓይናችን “አጥርቶ የሚያይ” ወይም “በአንድ ነገር ላይ ያተኮረ” እንዲሆን ይኸውም በሕይወታችን ውስጥ ለአምላክ
መንግሥትና ከመንግሥቱ ጋር ለተያያዙ ጉዳዮች ቅድሚያ እንድንሰጥ ያስችለናል። ማቴ. 6:22 የግርጌ ማስታወሻ
እኛ እውነተኛ ክርስቲያኖች ራሳችንን እንደ “መጻተኞችና ጊዜያዊ ነዋሪዎች”
አድርገን የምንቆጥርበት ዋነኛው ምክንያት ይህ ዓለም ሊጠፋ የቀረው ጊዜ አጭር እንደሆነ እርግጠኞች መሆናችን ነው። (1 ጴጥ.
2:11፤ 2 ጴጥ. 3:7) እንዲህ ዓይነት አመለካከት ያለን መሆኑ በሕይወታችን ውስጥ በምናደርገው ምርጫ እንዲሁም በምኞታችንና
በፍላጎታችን ላይ በጎ ተጽዕኖ ያሳድራል። ሐዋርያው ዮሐንስ የእምነት ባልንጀሮቹ ዓለምንም ሆነ በዓለም ውስጥ ያሉትን ነገሮች እንዳይወዱ
ምክር ሰጥቷቸዋል፤ ምክንያቱም “ዓለምም ሆነ ምኞቱ በማለፍ ላይ ናቸው፤ የአምላክን ፈቃድ የሚያደርግ ግን ለዘላለም ይኖራል።” 1
ዮሐ. 2:15-17
እስራኤላውያን፣ እግዚአብሔርን ቢታዘዙ ኖሮ ‘ከአሕዛብ ሁሉ የተወደደ
የእግዚአብሔር ርስት እንደሚሆኑ’ ቃል ተገብቶላቸው ነበር። (ዘፀ. 19:5) ታማኝ በነበሩበት ወቅት በአምልኳቸውም ሆነ በአኗኗራቸው
ከሌሎች ብሔራት ይለዩ ነበር። በተመሳሳይም በዛሬው ጊዜ እግዚአብሔር ከሰይጣን ዓለም ፍጹም የተለየ ሕዝብ ለራሱ መርጧል። ይህን
ሕዝብ አስመልክቶ መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል፦ “አምላካዊ ያልሆነ ምግባርንና ዓለማዊ ምኞቶችን ክደን አሁን ባለው በዚህ ሥርዓት
ውስጥ ጤናማ አስተሳሰብ በመያዝ፣ በጽድቅና ለአምላክ በማደር [እንኑር]፤ . . . በዚህ ሁኔታ አስደሳች የሆነውን ተስፋና የታላቁን
አምላክ እንዲሁም የአዳኛችንን የክርስቶስ ኢየሱስን መገለጥ እንጠባበቃለን፤
ክርስቶስ እኛን ከማንኛውም ዓይነት ዓመፅ ለማዳንና ለመልካም ሥራ የሚቀና የእሱ ብቻ የሆነ ሕዝብ ለራሱ ለማንጻት ራሱን ለእኛ ሰጥቷል።”
(ቲቶ 2:11-14)
0 comments:
Post a Comment