Saturday, October 22, 2016



ው መሳይ በሽንጎ
አቶ አሉላና ወ/ሮ ገነት ከውጪ ሲያዩዋቸው እንከን የሌባቸው ባለትዳሮች ይመስላሉ፤የጋብቻ  ዘመናቸውም ከርም ያለ ነው፤  ወ/ሮ ገነት አስተዋይ ሴት ናቸው የተቸገረ አይተው አይጨክኑም  ለስው ያላቸው ፍቅር የለበጣ ሳይሆን እውነት ነው፤ የሆዳቸውን በሆዳቸው አድረገው በአፋቸው ስውን ያደልሉም፤ ግልጽ ሴት ናቸው ከዚህም የተነሳ በስዎች የተከበሩ ናቸው።
አቶ አሉላ ከባለቤታቸው ጋር የሚመሳስል ጠባይ አላቸው፤ ይሁን እንጂ  ከስው ፊት ሲሆኑና ከቤታቸው የሚያስተላለፉት መልዕክትና ጸባያቸው የተለያየ ነው፤ ከዚህ የተነሳ አቶ አሉላ ጸባያቸውን ወይም አመላቸውን መጨበጥ አይቻለም፤ ደግ  የሚስሩት ሁሉ ለይስሙላና ለመታወቅ ነው፤ እነዚህ ሁለት ባለና ሚስት በለታዊ ኑሮአቸው የሚያደርጉትን ምልልስ እንመልከት።
ከጠዋቱ ዘጠኝ ስዓት ነው፤ አንድ ግዋደኛቸው ወደቤት መጣና ከበር ላይ ቆም አለና ቤቶች እንድምን አደራችሁ ብሎ ስለማታ ጠየቀ፣
ማነው ብለው ወ/ሮ ገነት ወደበሩ ለመክፈት እየተራመዱ እያሉ፣ አቶ አሉላ ለባለቤታቸው
እጃቸውን በማወዛወዝ መልክት ስጠዋቸው፤ ሴትየዋም ወደ ባልተቤታቸው ዘውር ሲሉ፣
አቶ አሉላ ለባለቤታቸው “አሉላ የለም በዪው፣ ዝም ብሎ ነው፣ እንዴ ስው ቤት ዘው ብሎ ይመጣል?” በመጣበት እግሩ ይመለስ አሉ።
ወ/ሮ ገነትም ባላቸው የተናገሩት ነገር፣ ቢያስደንግጣቸውም ወደበሩ ቀርብ አሉና በሩን ገርብብ አድርገው ክፍተው አያሉ፣
እንግዳውም አቶ አሉላ አለ እንዴ? ብሎ ሲጠይቅ አቶ አሉላ የለሁም ብለሽ ንገሪው በሎኛል
አሉ ወይዘሮ ገነት ለንግዳው፤
እንግዳው ምንድነው? የሚሉት ወይዘሮ ገነት? አሁን እኮ ገና ጠዋት ነው ከመቼው ወጡ? አቶ አሉላ ከመቼ ወዲህ የጠዋት ስው ሆኑ? ቤተክርስቲያን ሄደው ማስቀደስ ጀመሩ እንዴ?
አዎን ለንፍሳቸው አድረዋል? አልስማህም እንዴ?
 አሁንም ደግሜ እነግርሃለሁ፤ አሉላ የለም ብይው ብሎ እንደነግረህ ነግሮኛል አሉት። እያለ ነው የለም ብሉት የሚልዎት?
እንግዳው በመድነቅ! ምን ማለቱ ነው አሉላ፣ ደህናም አይደል እንዴ?
ወይ ጎድ ብሎ እጁን ባፉ ላይ አደረገና ትንሽ ቆም ብሎ አስበ፤
ወ/ር ገነትም ከደጃፍ ላይ ያስቀመጡን እቃ ለማንሳት ዝውር ሲሉ፣
እንግዳው ወደቤት አዘናግቶ ገባ፤ ሲገባም አቶ አሉላ በአግዳሚ አልጋ ላይ ጋደም ብለዋል፤
አቶ አሉላ፤ ምን ነካዎት ከቤት እያሉ የለሁም የምታስብሉት  አለ እንግዳው
አቶ አሉላ ወደ እንግዳው ዘውር አሉና፣ ማን ነገረህ ብለው ሲጠይቁት ባለቤትዎ ናቸዋ አለ እንግዳው፤
አቶ አሉላ፤ እርስዋ ደግሞ ያልክዋትን በትክክል አልስማችም ተሳስታለች፤ አንተን ወዳጄን ከደጄ ድርስ መጥተህ እንዴት እያለሁ የለሁም እላለሁ?
አቶ አሉላ ነገሩን ለማረሳሳት ነገሩ ወዲህ ነው አሉት ለንግዳው፣
እንግዳው ወሬ አትለውጡ አቶ አሉላ ነገሩ ወዲህ ነው፣ ብለው ጀምረዋል ነገሩ ወዴት ነው?
ወ/ሮ ገነት ከውጪ ሲመጡ አንግዳውና አቶ አሉላ በአንድ ላይ ቁጭ ብለው አዩ፤ አሉላ የለም ብለሽ ሽኚው ያሉት ስው በየት አልፎ ከቤት እንደገባ ሳይወቁ ከባላቸው ጋር እንጅና ግዋንት ሆነው ሲነጋገሩ አዩ፤ ባላቸው ምን ያህል አስመሳይ እንደሆኑ አዩና በትዝብት ተሞልተው፤
አይ! የኔ ባለቤት፣ ይህ ጸባይህ መቼ ይሆን የሚለቅህ? የምትገርም ስው ነህ፤ እስቲ ቡና ላፍላ ብለው ወደ ግዋዳ ገቡ።

የሥነ ምግባር እሴቶች ለተሻለ ሕይወት
አንድ እህት ዓይኗን ማመን አልቻለችም! በጥቁር ፌስታል የተቀመጠ በጣም ብዙ ገንዘብ አግኝታለች፤ ያገኘችው ገንዘብ ከ20 ዓመት በላይ ሠርታ ከምታገኘው ደሞዝ የሚበልጥ ነው። ገንዘቡን የጣለው ማን እንደሆነ ታውቃለች። ታዲያ ምን ማድረግ ይኖርባታል? አንተ ብትሆን ኖሮ ምን ታደርግ ነበር? ለዚህ ጥያቄ የምትሰጠው መልስ ለሐቀኝነት ያለህን አመለካከትና ይህን የሥነ ምግባር እሴት ለመጠበቅ ያለህን ቁርጠኝነት የሚያንጸባርቅ ይሆናል።
እሴት ሲባል ምን ማለት ነው? ጥሩና አስፈላጊ እንደሆኑ አድርገን የምንመለከታቸው የሥነ ምግባር መመሪያዎች ወይም ደንቦች ማለት ነው። ከእነዚህ መካከል ይቅር ባይነት፣ ሐቀኝነት፣ የሌላውን ነፃነት ማክበር፣ ፍቅር፣ ለሕይወት አክብሮት ማሳየትና ራስን መግዛት ይገኙበታል። በመሆኑም የምንመራባቸው የሥነ ምግባር እሴቶች በባሕርያችን፣ ቅድሚያ በምንሰጣቸው ነገሮች፣ ከሰዎች ጋር ባለን ግንኙነት እንዲሁም ለልጆቻችን በምናስተላልፋቸው የሥነ ምግባር መመሪያዎች ላይ ተጽዕኖ ያሳድራሉ። እነዚህ እሴቶች በጣም አስፈላጊ ቢሆኑም ከጊዜ ወደ ጊዜ ግን የሰዎች ሥነ ምግባር እያዘቀጠ መጥቷል።
የሥነ ምግባር እሴቶች እየጠፉ መጥተዋል
በ2008 ተመራማሪዎች ለሥነ ምግባር እሴቶች ያላቸውን አመለካከት ለማወቅ በመቶዎች ለሚቆጠሩ ወጣቶች ቃለ መጠይቅ አድርገውላቸው ነበር።  ብሩክስ በኒው ዮርክ ታይምስ ላይ እንዲህ ብለዋል፦ “የእነዚህ ወጣቶች አስተሳሰብና አነጋገር ለሥነ ምግባር ያላቸው አመለካከት ምን ያህል የወረደ እንደሆነ ያሳያል፤ ይህ ደግሞ ልብ የሚሰብር ነው።” አብዛኞቹ አስገድዶ መድፈርና ነፍስ ግድያ መጥፎ እንደሆኑ ተሰምቷቸዋል፤ “ከእነዚህ የከፉ ድርጊቶች ውጭ ግን ሌላው ቀርቶ ሰክሮ እንደማሽከርከር፣ በትምህርት ቤት ውስጥ እንደማታለል ወይም ከጓደኛቸው ሌላ የፆታ ግንኙነት እንደመፈጸም ስላሉ ጉዳዮች ሲያስቡ የሥነ ምግባር እሴቶች ትዝ አይሏቸውም።” አንዲት ወጣት “አንድ ነገር ትክክል ነው ወይስ አይደለም ብዬ ለማሰብ ያን ያህል አልሞክርም” ብላለች። ብዙዎች “ትክክል መስሎ ከተሰማህ አድርገው። ልብህ የሚልህን አዳምጥ” የሚል አመለካከት አላቸው። እንዲህ ያለው አስተሳሰብ ጥበብ ነው?
የሰው ልብ ጥልቅ ፍቅርና ሐዘኔታ የማሳየት ችሎታ ቢኖረውም የዚያኑ ያህል ‘ተንኮለኛና አታላይም’ ሊሆን ይችላል። (ኤርምያስ 17፡9) የዓለም የሥነ ምግባር ገጽታ እየተለወጠ መምጣቱ ይህን አሳዛኝ እውነታ የሚያንጸባርቅ ነው። ይህ እንደሚሆን መጽሐፍ ቅዱስ ከረጅም ጊዜ በፊት እንደሚከተለው በማለት ትንቢት ተናግሯል፦ ‘በመጨረሻዎቹ ቀኖች ሰዎች ራሳቸውን የሚወዱ፣ ገንዘብ የሚወዱ፣ ጉረኞች፣ ትዕቢተኞች፣ ፍቅር የሌላቸው፣ ጨካኞች፣ ራሳቸውን የማይገዙ፣ ጥሩ ነገር የማይወዱና አምላክን ከመውደድ ይልቅ ሥጋዊ ደስታን የሚወዱ ይሆናሉ።’ 2 ጢሞቴዎስ 3:1-5
ይህን እውነታ መገንዘባችን የገዛ ልባችንን በጭፍን ከማመን ይልቅ እንድንጠረጥረው ሊያነሳሳን ይገባል! መጽሐፍ ቅዱስ “በራሱ የሚታመን ተላላ ነው” በማለት በግልጽ ይናገራል። (ምሳሌ 28:26) ልባችን በጥሩ ሁኔታ እንዲያገለግለን ከፈለግን ጠቃሚ በሆኑ የሥነ ምግባር እሴቶች መሠረት ልክ እንደ ኮምፓስ መስተካከል ይኖርበታል። እንዲህ ያሉ እሴቶችን ከየት ማግኘት እንችላለን? መጽሐፍ ቅዱስ ትክክለኛና ግልጽ በመሆኑ ብዙዎች እነዚህን እሴቶች ለማግኘት ወደ አምላክ ቃል ዘወር ይላሉ።
ልንተማመንባቸው የምንችል የሥነ ምግባር እሴቶች!
የመጽሐፍ ቅዱስ የሥነ ምግባር እሴቶች ለሰው ልጆች ተብለው የተዘጋጁ መሆናቸውን የሚያሳዩ ብዙ ማስረጃዎች አሉ። እስቲ ፍቅርን፣ ደግነትን፣ ልግስናንና ሐቀኝነትን እንደ ምሳሌ እንውሰድ።
ለሰዎች ፍቅር ማሳየት። ኢንጂኒየሪንግ ሃፒነስ—ኤ ኒው አፕሮች ፎር ቢልዲንግ ኤ ጆይፉል ላይፍ የተባለው መጽሐፍ “መውደድን ከተማርክ ደስታ በርህን ያንኳኳል” ብሏል። በእርግጥም ሰዎች እንደመሆናችን ፍቅር ያስፈልገናል። ያለ ፍቅር እውነተኛ ደስታ ልናገኝ አንችልም።
መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል? “ፍቅርን ልበሱ፤ ምክንያቱም ፍቅር ፍጹም የሆነ የአንድነት ማሰሪያ ነው።” (ቆላስይስ 3:14) ይኸው የመጽሐፍ ቅዱስ ጸሐፊ “ፍቅር ግን ከሌለኝ ከንቱ ነኝ” ብሏል።1 ቆሮንቶስ 13:2
እንዲህ ዓይነቱ ፍቅር ከፆታ ጋር የተያያዘ ወይም በስሜት ብቻ የሚመራ አይደለም፤ ከዚህ ይልቅ በመሠረታዊ ሥርዓት የሚመራ ነው። ችግር ውስጥ የወደቀን የማናውቀውን ሰው ብድር ይመልስልናል ብለን ተስፋ ሳናደርግ ግለሰቡን እንድንረዳው የሚገፋፋን የፍቅር ዓይነት ነው። አንደኛ ቆሮንቶስ 13:4-7 እንዲህ ይላል፦ “ፍቅር ታጋሽና ደግ ነው። ፍቅር አይቀናም፣ ጉራ አይነዛም፣ አይታበይም፣ ተገቢ ያልሆነ ምግባር አያሳይም፣ የራሱን ፍላጎት አያስቀድምም፣ አይበሳጭም። ፍቅር የበደል መዝገብ የለውም። ፍቅር በዓመፅ አይደሰትም፤ ከዚህ ይልቅ ከእውነት ጋር ደስ ይለዋል። ሁሉን ችሎ ያልፋል፣ . . . ሁሉን ነገር በጽናት ይቋቋማል።”
የፍቅር መሠሪ ጠላት ፍቅረ ንዋይ ነው፤ ፍቅረ ንዋይ ሲባል ለቁሳዊ ብልጽግናና ደስታ ከሁሉ የበለጠ ዋጋ መስጠት ማለት ነው። ዓለማዊ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት ግን ከመሠረታዊ ነገሮች ያለፈ ሀብት ማካበት ደስታ አያመጣም። እንዲያውም ለቁሳዊ ነገሮች ትልቅ ቦታ የሚሰጡ ሰዎች ደስታ በሚያሳጣቸው ነገር ላይ መዋዕለ ንዋያቸውን እያፈሰሱ ነው ሊባል ይችላል። መጽሐፍ ቅዱስም ይህ እውነት እንደሆነ ያረጋግጣል፤ መክብብ 5:10 “ገንዘብን የሚወድ፣ ገንዘብ አይበቃውም፤ ብልጽግናም የሚወድ፣ በትርፉ አይረካም፤ ይህም ከንቱ ነው” ይላል። በተጨማሪም መጽሐፍ ቅዱስ “አኗኗራችሁ ከገንዘብ ፍቅር ነፃ ይሁን” ይላል። ዕብራውያን 13:5
ደግነትና ልግስና።  ጽሑፍ ላይ “ወደ አንድ ሱቅ ገብተህ የዕድሜ ልክ ደስታ መሸመት ብትችል ኖሮ ጥሩ አይሆንም ነበር?” በማለት ጠይቋል። አክሎም “ይህ ሐሳብ ሊሆን የማይችል ነገር ቢመስልም የምትገዛው ነገር ለሌላ ሰው እስከሆነ ድረስ ግን በእርግጥ የሚሆን ነገር ነው” ይላል። ዋናው ነጥብ ምንድን ነው? መስጠት ከመቀበል የበለጠ ደስተኛ ያደርገናል። ቻርልስ ድ ዎርነር የተባሉ ጸሐፊ እንዲህ ብለዋል፦ “ማንም ሰው ሌላውን ከልቡ ሲረዳ ራሱንም የሚረዳ መሆኑ፣ ይህ በሕይወታችን ውስጥ ከምንካስባቸው አስደናቂ መንገዶች አንዱ ነው።” ይህ ሊሆን የቻለው አምላክ የሰው ልጆችን የፈጠረው ራስ ወዳዶች እንዲሆኑ ሳይሆን የእሱን ውድ ባሕርያት እንዲያንጸባርቁ አድርጎ በመሆኑ ነው። ዘፍጥረት 1:27
ሐቀኝነት። ይህ የሥነ ምግባር እሴት በማንኛውም የሠለጠነ ኅብረተሰብ ውስጥ አስፈላጊ ነገር ነው። ሐቀኛ አለመሆን ፍርሃትን፣ አለመተማመንንና ማኅበራዊ ዝቅጠትን ያስከትላል።
መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል? መዝሙረኛው “እግዚአብሔር ሆይ፤ በድንኳንህ ውስጥ ማን ያድራል?” በማለት ከጠየቀ በኋላ “አካሄዱ ንጹሕ የሆነ፣ . . . ከልቡ እውነትን የሚናገር” በማለት መልሱን ተናግሯል። (መዝሙር 15:1, 2) አዎ፣ በሁሉም መንገድ ሐቀኛ መሆን እስካሁን እንደተመለከትናቸው ሌሎች የሥነ ምግባር እሴቶች ሁሉ ሰዎች ሊኖሯቸው ከሚገቡ ባሕርያት አንዱ ነው። ይህ የሥነ ምግባር እሴት እንደሁኔታው የሚለዋወጥ ወይም የሚያዋጣ ሆኖ ሲገኝ ብቻ ተግባራዊ የሚደረግ አይደለም።
“ሕይወትን የሚወድና መልካም ቀኖችን ማየት የሚፈልግ ሰው . . . ከንፈሮቹንም የማታለያ ቃላት ከመናገር ይከልክል” የሚለው በ1 ጴጥሮስ 3:10 ላይ የሚገኘው ሐሳብ ምንኛ እውነት ነው!
‘በደጋግ ሰዎች ጐዳና ሂድ’
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኙት የሥነ ምግባር እሴቶች ፈጣሪያችን ለእኛ ያለውን ጥልቅ ፍቅር የሚያንጸባርቁ ናቸው፤ ምክንያቱም እነዚህ እሴቶች ‘በደጋግ ሰዎች ጎዳና እንድንሄድ’ ያስችሉናል። (ምሳሌ 2:20፤ ኢሳይያስ 48:17, 18) ይህን መመሪያ ስንከተል እኛም በተራችን ለአምላክ ያለንን ፍቅር እናሳያለን፤ ይህ ደግሞ ብዙ በረከት ያስገኝልናል። እንዲያውም መጽሐፍ ቅዱስ “እግዚአብሔርን ደጅ ጥና፤ መንገዱንም ጠብቅ፤ ምድሪቱን ትወርስ ዘንድ ከፍ ከፍ ያደርግሃል፤ ክፉዎችም ሲጠፉ ታያለህ” የሚል ተስፋ ይሰጠናል። መዝሙር 37:34
አዎ፣ የመጽሐፍ ቅዱስን መሥፈርቶች የሚከተሉ ሰዎች በጣም ግሩም የሆነ የወደፊት ተስፋ ይኸውም ከክፋት በጸዳች ሰላማዊ ምድር ላይ ለዘላለም የመኖር በረከት ይጠብቃቸዋል። በእርግጥም በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኙትን የሥነ ምግባር እሴቶች በደንብ ልንመረምራቸው ይገባል።
“ዓለም አቀፍ የሥነ ምግባር ደንብ” በአስቸኳይ ያስፈልጋል
ካውንስሊንግ ኤንድ ቫልዩስ የተባለው መጽሔት “የሰው ልጆች ሕልውና መቀጠል የተመካው ዓለም አቀፍ የሥነ ምግባር ደንብ ያስፈልጋል የሚለው ሐሳብ ተቀባይነት በማግኘቱ ላይ ሊሆን ይችላል” ብሏል። “አብዛኛዎቹ የሚስማሙበት ዓለም አቀፋዊ የሥነ ምግባር እሴት ወርቃማው ሕግ ሳይሆን አይቀርም።” ይህ ሕግ ምን ይላል? ኢየሱስ ክርስቶስ ያስተማረው ይህ ሕግ “ሰዎች እንዲያደርጉላችሁ የምትፈልጉትን ነገር ሁሉ እናንተም እንደዚሁ ልታደርጉላቸው ይገባል” ይላል። ማቴዎስ 7:12
የሚያስከብሩን የሥነ ምግባር እሴቶች
“ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ።”ማርቆስ 12:31
“ለማንም በክፉ ፋንታ ክፉ አትመልሱ።”ሮም 12:17
“አንዱ በሌላው ላይ ቅር የተሰኘበት ነገር ቢኖረው . . . እርስ በርስ በነፃ ይቅር መባባላችሁን ቀጥሉ።”—ቆላስይስ 3:13
“የገንዘብ ፍቅር የብዙ ዓይነት ጎጂ ነገሮች ሥር ነው።”1 ጢሞቴዎስ 6:10
ወቅታዊና ተግባራዊ 7 ትምህርቶች
ከታች የተዘረዘሩት ምሳሌዎች ወቅታዊና ተግባራዊ ሊሆኑ የሚችሉ በርካታ ምሳሌዎች ከሚገኙበት አንድ ጥንታዊ መጽሐፍ ላይ የተወሰዱ ናቸው። እነዚህ ምሳሌዎች በገንዘብ አያያዝህ ረገድ ሊጠቅሙህ የሚችሉት እንዴት እንደሆነ እስቲ እንመልከት።
1. ገንዘብን የሚወድ፣ ገንዘብ አይበቃውም፤ ብልጽግናም የሚወድ፣ በትርፉ አይረካም።” (መክብብ 5:10) ይህን ሐሳብ የተናገረው በሀብታሞች የሚቀና አንድ የተቸገረ ሰው አይደለም። ከዚህ ይልቅ በምድር ላይ ከኖሩት እጅግ ባለጠጋ ሰዎች መካከል አንዱ የሆነው የእስራኤሉ ንጉሥ ሰለሞን ነው፤ ይህ ንጉሥ ከራሱ ተሞክሮና ካያቸው ነገሮች በመነሳት እንዲህ ብሎ ሊጽፍ ችሏል። በዘመናችን ያሉ ሀብታም ሰዎችም ተመሳሳይ አስተያየት ሰጥተዋል።
2. “ምግብ እንዲሁም ልብስና መጠለያ ካለን በእነዚህ ነገሮች ረክተን መኖር ይገባናል። ይሁን እንጂ ሀብታም ለመሆን ቆርጠው የተነሱ ፈተናና ወጥመድ ውስጥ ይወድቃሉ።” (1 ጢሞቴዎስ 6:8, 9) ይህን ሐሳብ የጻፈው ከፍተኛ እውቅና ሊያስገኝለት የሚችለውን ሙያ ትቶ የኢየሱስ ክርስቶስ ተከታይ የሆነው ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ነው። ቅዱስ ጳውሎስ በዘመናችን ካሉ አንዳንድ ሃይማኖታዊ መሪዎች በተለየ መልኩ ከተማሪዎቹ ወይም ከእምነት አጋሮቹ ቁሳዊ ጥቅም ለማግኘት ፈጽሞ አልሞከረም። ከዚህ ይልቅ እንደሚከተለው ሲል በሐቀኝነት ተናግሯል፦የማንንም ብር ወይም ወርቅ ወይም ልብስ አልተመኘሁም። እነዚህ እጆቼ ለእኔም ሆነ ከእኔ ጋር ለነበሩት የሚያስፈልጉንን ነገሮች ለማሟላት እንዳገለገሉ እናንተ ራሳችሁ ታውቃላችሁ።የሐዋርያት ሥራ 20:33, 34
3. ከእናንተ መካከል፣ ግንብ ለመገንባት ፈልጎ ለመጨረስ የሚያስችል በቂ ገንዘብ እንዳለው ለማወቅ በመጀመሪያ ተቀምጦ ወጪውን የማያሰላ ማን ነው?” (ሉቃስ 14:28) የኢየሱስ ምሳሌ በዕለት ተዕለት በሚያጋጥምህ ሁኔታ ላይም ሊሠራ ይችላል፦ አንድን ነገር ከመግዛትህ በፊት (በተለይም ደግሞ በዱቤ) ቆም ብለህ ወጪህን ታሰላለህ? ወይስ በስሜት ተገፋፍተህ ትገዛለህ? ደግሞስ በእርግጥ ዕቃው ያስፈልግሃል? ዕቃውን ለመግዛትስ አቅምህ ይፈቅዳል?
4. ተበዳሪም የአበዳሪ ባሪያ ነው። (ምሳሌ 22:7) በቅርቡ በዓለም ላይ የደረሰው የገንዘብ ቀውስ ክሬዲት ካርድና ሌሎች የብድር ዓይነቶች ውድቀት ላይ እንደሚጥሉ በግልጽ አሳይቷል። ማይክል ዋግነር፣ 2009 ባሳተሙት ዩር መኒ፣ ደይ ዋን በተባለው መጽሐፋቸው ላይበዛሬው ጊዜ አንድ ሰው በአራትና ከአራት በሚበልጡ ክሬዲት ካርዶች ተጠቅሞ በአማካይ 9,000 ዶላር በላይ (151,200 ብር በላይ) ዕዳ ውስጥ መግባቱ የተለመደ ነገር ሆኗልብለዋል።
5. ኃጢአተኛ ይበደራል አይከፍልምም፤ ጻድቅ ግን ይራራል ይሰጣልም።” (መዝሙር 37:21) አንዳንድ ሰዎች ከስሬያለሁ ብሎ ማወጅ ከዕዳ የሚገላገሉበት ቀላል መንገድ እንደሆነ አድርገው ያስባሉ። ከእግዚአብሄር ጋር ያላቸውን ጥሩ የልጅና የአባት ቅርበት ከፍ አድርገው የሚመለከቱ ሰዎች ግን ዕዳቸውን በትጋት ለመክፈል ብቻ ሳይሆን ከቻሉ ያላቸውን ነገር ለሌሎች በልግስና ለማካፈል ይጥራሉ።
6. ጐልማሳ ነበርሁ፤ አሁን አርጅቻለሁ፤ ነገር ግን ጻድቅ ሲጣል፣ ዘሩም እንጀራ ሲለምን አላየሁም።” (መዝሙር 37:25) ይህን ሐሳብ የጻፈው ብዙ በደል የደረሰበት ሰው ነው። በርካታ ዓመታት በስደት ያሳለፈ ሲሆን በዋሻ ውስጥ ለመኖርና በባዕድ አገር ጥገኝነት ለመጠየቅ የተገደደበትም ጊዜ ነበር። ይህ ስደተኛ ማለትም ንጉሥ ዳዊት ውሎ አድሮ የጥንቷ እስራኤል ንጉሥ ለመሆን በቅቷል። ንጉሥ ዳዊት ከላይ የተናገረውን ሐሳብ እውነተኝነት ከራሱ የሕይወት ተሞክሮ ተገንዝቧል።
7. ከመቀበል ይልቅ መስጠት የበለጠ ደስታ ያስገኛል።” (የሐዋርያት ሥራ 20:35) ይህን የተናገረው በምድር ላይ ከኖሩት ሰዎች ሁሉ የሚበልጠው ታላቅ ሰው ነው። ኢየሱስከፊቱ ለሚጠብቀው ደስታ ሲልምድራዊ ሕይወቱን ሌሎችን ለማገልገል ተጠቅሞበታል። በአሁኑ ጊዜ ደግሞ በሰማይ የማይሞት መንፈሳዊ ሕይወት አግኝቶደስተኛ በሆነው አምላክበእግዚአብሄር ቀኝ ተቀምጧል። ዕብራውያን 12:2 1 ጢሞቴዎስ 1:11

እኛም አቅማችን በፈቀደልን መጠን ሌሎችን በማገልገል የኢየሱስን ምሳሌ መከተል እንችላለን፤ ደግሞም ሕይወታችን ትርጉም ያለው እንዲሆን የሚያደርግ ከዚህ የተሻለ ነገር የለም። እንግዲያውበራስ ወዳድነት ስሜት ገንዘብ ከማባከን ይልቅ ጠንቃቃ ቆጣቢ በመሆን ለሌሎች በልግስና መስጠት የተሻለ ነውበሚለው ሐሳብ እንደምትስማማ ምንም ጥርጥር የለውም።

በደመ ነፍስ ከሚገኝ ጥበብ የሚልቅ መመሪያ
“የግል የሥነ ምግባር አቋም የሚባለው፣ አንድ ሰው የሚያደርጋቸው ምርጫዎች ከሥነ ምግባር አንጻር ትክክል መሆን አለመሆናቸው የሚመዘንባቸው መሠረታዊ ሥርዓቶች ሳይኖሩ እንዲሁ በነጻነት የሚያደርገው ምርጫ ከሆነ በዚህ ሳቢያ የሚፈጠረውን የሥነ ምግባር ክፍተት ለመሙላትና ተገቢ ምግባር እንዲኖር ለማድረግ መንግሥታት የሚያወጡትን ሕግ መጠቀም የግድ ነው።” ዶክተር ዳንኤል ካለሃን
ሥነ ምግባር እያሽቆለቆለ ያለው ለምንድን ነው?
ሥነ ምግባር እያሽቆለቆለ እንዲሄድ ያደረጉት ነገሮች በርካታ ናቸው። ከእነዚህም አንዱ በባሕላዊ የሥነ ምግባር እሴቶች ላይ የማመጽ መንፈስ መስፋፋቱ ነው። ለምሳሌ ያህል፣ በዩናይትድ ስቴትስ ደቡባዊ ክፍል በተካሄደ አንድ የሕዝብ አስተያየት ጥናት መሠረት ጥያቄ ከቀረበላቸው የኮሌጅ ተማሪዎች መካከል አብዛኞቹ “ትክክልና ስህተት የሚባለው ነገር በግል አመለካከት ላይ የተመካ እንደሆነ” ይሰማቸዋል።
ለሥነ ምግባር እሴቶች ማሽቆልቆል ምክንያት የሆነውን  ነገር ጠቅሰዋል። በዛሬው ጊዜ የሚገኘው ኅብረተሰብ “የግል ፍላጎትን ወዲያውኑ በማርካት ላይ ያተኮረ ሲሆን የሰዎች ባሕርይ በዋነኝነት የተመሠረተው የሕይወት ትልቁ ዓላማ የግልና የጋራ ደስታ ማግኘት እንደሆነ በሚገልጽ መርሕ ላይ ነው” በማለት ጽፈዋል። ከሥነ ምግባር ጋር በተያያዙ ጉዳዮች ረገድ የግል ውሳኔ የማድረግ ነፃነት፣ ስግብግብነት እንዲሁም የራስን እርካታ መፈለግ ማራኪ መስለው ይቀርቡ ይሆናል፤ ይሁን እንጂ እነዚህ ነገሮች እውነተኛ ደስታና እርካታ ለማግኘት እንዲሁም ከሌሎች ጋር የተሻለ ዝምድና ለመመሥረት ያስችላሉ?
ኢየሱስ “ጥበብ . . . በሥራዋ ጸደቀች” ብሏል። (ማቴዎስ 11:19) ሰዎች የሥነ ምግባር እሴቶችን አሽቀንጥረው በመጣላቸው ከስጋት ተላቀው ይበልጥ ደስተኞች ሆነዋል? እንዲህ ዓይነቱ አኗኗር ካስገኛቸው ውጤቶች መካከል አንዳንዶቹ እያደር እየባሰ የመጣ አለመተማመን፣ ስጋት፣ የትዳር መፍረስ፣ ልጆች ያለ አባት ወይም ያለ እናት ማደጋቸው፣ በጾታ ግንኙነት የሚተላለፉ በሽታዎች መዛመት፣ ያልተፈለጉ እርግዝናዎች፣ የአደንዛዥ ዕፅ ሱሰኝነትና ዓመጽ ናቸው። እነዚህ እውነታዎች በግልጽ እንደሚያሳዩት ሰዎች በእርካታና በስኬት ፈንታ ሐዘንና ውድቀት እያጋጠማቸው ነው። ገላትያ 6:7, 8
የእግዚዝብሄር ነቢይ የነበረው ኤርምያስ በዘመኑ ከላይ የተጠቀሱትን ዓይነት ችግሮች ከተመለከተ በኋላ በአምላክ መንፈስ ተገፋፍቶ “እግዚአብሔር ሆይ፤ የሰው ሕይወት በራሱ እጅ እንዳልሆነች፣ አካሄዱንም በራሱ አቃንቶ ሊመራ እንደማይችል ዐውቃለሁ” በማለት ተናግሯል። (ኤርምያስ 10:23) በእርግጥም አምላክ፣ ከእሱ ተነጥለን ትክክልና ስህተት የሆነውን ራሳችን እንድንወስን አድርጎ አልፈጠረንም። ለእኛ ጠቃሚ የመሰለን ነገር ጎጂ ሊሆን ይችላል። መጽሐፍ ቅዱስ በምሳሌ 14:12 ላይ “ለሰው ቀና መስሎ የሚታይ መንገድ አለ፤ በመጨረሻ ግን ወደ ሞት ያደርሳል” በማለት ይናገራል።
በሥነ ምግባር ጉዳዮች ረገድ መመሪያ የሚያስፈልገን ለምንድን ነው? አንዱ ምክንያት ልባችን ሊያታልለን ስለሚችል ነው። መጽሐፍ ቅዱስ በኤርምያስ 17:9 ላይ “የሰው ልብ ከሁሉ ይልቅ ተንኰለኛ ነው፤ ፈውስም የለውም፤ ማንስ ሊረዳው ይችላል?” ይላል። አንድ ሰው ተንኮለኛ እንደሆነ እያወቅህ ታምነዋለህ? እንደማታምነው የታወቀ ነው! ሆኖም እያንዳንዳችን ተንኮለኛ የሆነ ልብ አለን። በመሆኑም አምላክ የሚከተለውን ቀጥተኛና ፍቅር የሚንጸባረቅበት ማስጠንቀቂያ ይሰጠናል:- “በገዛ ልቡ የሚታመን ሰው ሰነፍ ነው፤ በጥበብ የሚሄድ ግን ይድናል።”ምሳሌ 28:26 የ1954 ትርጉም
ይህ ጥቅስ ማድረግ የሚገባንን ቁልፍ ነገር ይገልጽልናል:- ፍጹም ባለመሆናችን ምክንያት በራሳችን ችሎታ ከመታመን ይልቅ በአምላካዊ ጥበብ መመላለስ ያስፈልገናል፤ በዚህም ራሳችንን ከብዙ ወጥመዶች እናድናለን። ከዚህም በላይ ውድ የሆነችው ጥበብ ከልብ ለሚፈልጓት ሁሉ በቀላሉ ትገኛለች። የአምላክ ቃል “ከእናንተ ማንም ጥበብ ቢጎድለው፣ ሳይነቅፍ በልግስና ለሁሉም የሚሰጠውን እግዚአብሔርን ይለምን፤ ለእርሱም ይሰጠዋል” ይላል።ያዕቆብ 1:5
በፍጹም ልብህ” በእግዚአብሔር ታመን
መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ፈጣሪያችን ሲገልጽ “እርሱ ዐለት፣ ሥራውም ፍጹም ነው፤ መንገዱም ሁሉ ትክክል ነው፤ የማይሳሳት ታማኝ አምላክ፣ ቀጥተኛና ጻድቅ አምላክም እርሱ ነው” ይላል። (ዘዳግም 32:4) በአካባቢያችን ምንም ዓይነት ለውጥ ቢከናወን እርሱ አስተማማኝ ሥነ ምግባራዊና መንፈሳዊ መመሪያ እንደሚሰጠን ሙሉ በሙሉ ልንተማመንበት እንችላለን። ምሳሌ 3:5, 6 “በፍጹም ልብህ በእግዚአብሔር ታመን፤ በራስህ ማስተዋል አትደገፍ፤ በመንገድህ ሁሉ እርሱን ዕወቅ፤ እርሱም ጐዳናህን ቀና ያደርገዋል” ይላል። በእርግጥም ‘የራሳችንን ጠጉር እንኳ ከሚቆጥረው’ ፈጣሪያችን የተሻለ መመሪያ ማን ሊሰጠን ይችላል? (ማቴዎስ 10:30) ከዚህም በላይ ይሖዋ በማንኛውም ወቅት፣ ሌላው ቀርቶ እውነታውን መቀበል በሚከብደን ጊዜም ጭምር ሐቁን እንዲነግረን የሚገፋፋው ፍቅር ያለው እውነተኛ ወዳጃችን መሆኑን አረጋግጧል። መዝሙር 141:5፤ ምሳሌ 27:6
በተጨማሪም እግዚአብሄር ለሚሰጠን መመሪያ እንድንገዛ እንደማያስገድደን ልብ በል። ከዚህ ይልቅ በፍቅር ተነሳስተን እንድንታዘዘው ይፈልጋል። “እኔ እግዚአብሔር አምላክህ፣ የሚበጅህ ምን እንደ ሆነ የማስተምርህ፣ መሄድ በሚገባህ መንገድ የምመራህ ነኝ። ትእዛዜን ሰምተህ ብቻ ቢሆን ኖሮ፣ ሰላምህ እንደ ወንዝ፣ ጽድቅህም እንደ ባሕር ሞገድ በሆነ ነበር” ይለናል። (ኢሳይያስ 48:17, 18) እንዲህ ዓይነት ባሕርይ ወዳለው አምላክ ለመቅረብ አትገፋፋም? ከዚህም ሌላ አምላክ፣ በዓለም ላይ በስፋት በተሰራጨውና በመንፈስ አነሳሽነት ባስጻፈው በቃሉ በመጽሐፍ ቅዱስ አማካኝነት ጥበቡን በቀላሉ እንድናገኘው አድርጓል! 2 ጢሞቴዎስ 3:16
የእግዚአብሄር ቃል መንገድህን እንዲያበራልህ ፍቀድ
መዝሙረኛው ቅዱሳን ጽሑፎችን አስመልክቶ “ሕግህ ለእግሬ መብራት፣ ለመንገዴም ብርሃን ነው” በማለት ጽፏል። (መዝሙር 119:105) ለእግራችን መብራት የሆነ ነገር፣ አጠገባችን የሚገኝን አደጋ እንድናይ የሚያስችለን ሲሆን የመንገድ ብርሃን ደግሞ ከፊት ለፊታችን ያለውን ጎዳና ያበራልናል። በአጭር አነጋገር የእግዚአብሄር ቃል በሁሉም ዘርፎች፣ ማለትም የአሁኑንም ሆነ የወደፊቱን ሕይወታችንን በሚነኩ ጉዳዮች ረገድ ጥበብ የሚንጸባረቅበትና ከሥነ ምግባር አንጻር ትክክለኛ የሆነ ውሳኔ እንድናደርግ በመርዳት ከአደጋ ተጠብቀን እንድንኖር ሊመራን ይችላል። ለምሳሌ ያህል የተራራውን ስብከት እንመልከት። ከማቴዎስ ምዕራፍ 5 እስከ 7 ላይ በተመዘገበው አጭር ንግግር ላይ ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ደስታ፣ ስለ ፍቅር፣ ስለ ጥላቻ፣ ስለ ምሕረት፣ ስለ ሥነ ምግባር፣ ስለ ጸሎት፣ ሀብትን ስለማሳደድና እንደዚያ ዘመን ሁሉ ዛሬም አስፈላጊ ስለሆኑ ሌሎች ብዙ ርዕሰ ጉዳዮች ተናግሯል። የተናገራቸው ነገሮች ጥልቅ ማስተዋል የተንጸባረቀባቸው ስለነበሩ “ሕዝቡ በትምህርቱ ተደነቁ።” (ማቴዎስ 7:28) አንተ ራስህ ጥቂት ጊዜ ወስደህ ያንን ስብከት ለምን አታነበውም? በትምህርቱ መደነቅህ አይቀርም።
እግዚአብሄርን እርዳታ መጠየቅ
እውነቱን ለመናገር በእግዚአብሄር ዓይን ትክክል የሆነውን ነገር ማድረግ ሁልጊዜ ቀላል አይደለም። እንዲያውም መጽሐፍ ቅዱስ ከኃጢአት ጋር በውስጣችን የምናደርገውን ትግል ከውጊያ ጋር ያመሳስለዋል። (ሮሜ 7:21-24) ይሁን እንጂ በአምላክ እርዳታ በዚህ ውጊያ ማሸነፍ ይቻላል። ኢየሱስ “ለምኑ ይሰጣችኋል፤ ፈልጉ ታገኛላችሁ፤ . . . ምክንያቱም የሚለምን ሁሉ ይቀበላል፤ የሚፈልግም ያገኛል” ብሏል። (ሉቃስ 11:9, 10) አዎን፣ እግዚአብሄር ወደ ዘላለማዊ ሕይወት በሚመራው ጠባብ መንገድ ላይ ለመጓዝ ልባዊ ጥረት የሚያደርግ ማንኛውንም ሰው ከመርዳት ወደኋላ አይልም። ማቴዎስ 7:13, 14።
የእግዚአብሄርን ውድ እውነቶች ተቀብለን ተግባራዊ ስናደርግ አእምሯዊ፣ ስሜታዊ፣ መንፈሳዊና አካላዊ ጥቅም እናገኛለን። መዝሙር 19:7, 8 እንዲህ ይላል:- “የእግዚአብሔር ሕግ ፍጹም ነው፤ ነፍስንም መልሶ ያለመልማል፤ . . . የእግዚአብሔር ሕግጋት ትክክል ናቸው፤ ልብን ደስ ያሰኛሉ። የእግዚአብሔር ትእዛዝ ብሩህ ነው፤ [ተስፋና ስለ እግዚአብሄር ዓላማ ግልጽ ግንዛቤ በመስጠት] ዐይንን ያበራል።”
እግዚአብሄር በቃሉ አማካኝነት የሚሰጠን እርዳታ በሥነ ምግባር ረገድ ትክክለኛ ኮምፓስ እንዲኖረንና በአሁኑ ጊዜ ሕይወታችን የተሻለ እንዲሆን በማስቻል ብቻ የተወሰነ አይደለም። ስለመጪው ጊዜም ጭምር ብርሃን ፈንጥቆልናል። (ኢሳይያስ 42:9)
የምትመራበት የሥነ ምግባር “ኮምፓስ”
ሰዎች ውድ የሆነ ስጦታ ይኸውም ሕሊና አላቸው። በመሆኑም በእያንዳንዱ ብሔርና ጎሣ ውስጥ ያሉ እንዲሁም በየዘመኑ የኖሩ ሰዎች ተመሳሳይነት ያለው የሥነ ምግባር መመሪያ አላቸው። (ሮሜ 2:14, 15) ይሁን እንጂ ሕሊና ሊሳሳት የማይችል መሪ አይደለም፤ የሐሰት ሃይማኖታዊ እምነቶች፣ ሰብዓዊ ፍልስፍናዎች፣ ጭፍን ጥላቻና የተሳሳቱ ምኞቶች ሕሊና በሚሰጠው መመሪያ ላይ ተጽዕኖ ሊያደርጉ ይችላሉ። (ኤርምያስ 17:9፤ ቈላስይስ 2:8) ስለዚህ አንድ አውሮፕላን አብራሪ አቅጣጫ የሚጠቁሙትን መሣሪያዎች ማስተካከል ሊያስፈልገው እንደሚችል ሁሉ እኛም ሥነ ምግባራዊና መንፈሳዊ ኮምፓሳችንን መፈተሽና አስፈላጊ በሚሆንበት ጊዜ “ሕግ ሰጪያችን”  እግዚአብሄር የጽድቅ መሥፈርቶች መሠረት ኮምፓሳችንን ማስተካከል ያስፈልገናል። (ኢሳይያስ 33:22) ከትውልድ ወደ ትውልድ ከሚለዋወጡት ሰብዓዊ የሥነ ምግባር መሥፈርቶች በተቃራኒ ፍጹም የሆኑት የአምላክ መሥፈርቶች ምንጊዜም አይለወጡም። “እኔ እግዚአብሔር አልለወጥም” ብሏል። ሚልክያስ 3:6
ስኬትና ደስታ ለማግኘት የሚረዳ መመሪያ
ደስታ ማግኘት
“መንፈሳዊ ነገሮችን የሚጠሙ ደስተኞች ናቸው።” ማቴዎስ 5:3
“ከሚቀበል ይልቅ የሚሰጥ ብፁዕ [“ደስተኛ፣” ነው።” የሐዋርያት ሥራ 20:35
“ብፁዓንስ [“ደስተኞችስ፣”] የእግዚአብሔርን ቃል ሰምተው የሚታዘዙት ናቸው።” ሉቃስ 11:28
መተማመን እንዲኖር ማድረግ
“እያንዳንዳችሁ ከባልንጀራችሁ ጋር እውነትን ተነጋገሩ።” ኤፌሶን 4:25
“ይሰርቅ የነበረ ከእንግዲህ አይስረቅ።” ኤፌሶን 4:28
“ጋብቻ በሁሉም ዘንድ ይከበር፤ መኝታውም ንጹሕ ይሁን።” ዕብራውያን 13:4
ጥሩ ግንኙነት መመሥረት
“ሌሎች እንዲያደርጉላችሁ የምትፈልጉትን ነገር እናንተም አድርጉላቸው።” ማቴዎስ 7:12
“[ባል] ሚስቱን እንደ ራሱ አድርጎ ይውደድ፤ ሚስትም ባሏን ታክብር።” ኤፌሶን 5:33
“እርስ በርሳችሁ . . . ይቅር ተባባሉ።” ቈላስይስ 3:13
አለመግባባትን ማስወገድና ልዩነቶችን መፍታት
“ለማንም ክፉን በክፉ አትመልሱ።” ሮሜ 12:17
“ፍቅር ታጋሽ ነው፤ ደግሞም ቸር ነው። . . . በደልን አይቈጥርም።” 1 ቆሮንቶስ 13:4, 5
“በቊጣችሁ ላይ ፀሓይ አይግባ።” ኤፌሶን 4:26
የሥነ ምግባር ደንቦች የሚለዋወጡበት ዓለም
አንድ በሰፊው የሚታወቅ አፈ ታሪክ፣ ታማኝ ሰው ፍለጋ በጠራራ ፀሐይ ፋኖስ ይዞ ይዞር ስለነበረ አንድ ሰው ይናገራል። ይህ ሰው በአራተኛው መቶ ዘመን ከክርስቶስ ልደት በፊት በአቴንስ ይኖር የነበረው ዳያጀኒዝ የተባለ ፈላስፋ ነው።
ይህ አፈ ታሪክ እውነት ይሁን አይሁን የሚታወቅ ነገር የለም። ይሁንና ዳያጀኒዝ ዛሬ በሕይወት ቢኖር ኖሮ ጥሩ ሥነ ምግባር ያላቸውን ሰዎች ለማግኘት የበለጠ መልፋቱ አይቀርም ነበር። ሰዎች ቋሚ የሥነ ምግባር ደንብ ሊኖራቸው ይገባል የሚለውን ሐሳብ ብዙዎች የሚቀበሉት አይመስልም። መገናኛ ብዙሃን በመንግሥት ደረጃ፣ በሰዎች የግል ሕይወት፣ በሥራውና በስፖርቱ ዓለም፣ በንግዱ ማኅበረሰብ እንዲሁም በተለያዩ ዘርፎች ስለሚታየው የሥነ ምግባር ውድቀት በተደጋጋሚ ይዘግባሉ። ያለፈው ትውልድ ከፍ አድርጎ ይመለከታቸው የነበሩት በርካታ የሥነ ምግባር እሴቶች በአሁኑ ጊዜ ቦታ የላቸውም። ባለፉት ጊዜያት ሲሠራባቸው የቆዩ መሥፈርቶች እንደገና የሚገመገሙ ሲሆን በአብዛኛው ውድቅ እንዲሆኑ ይደረጋል። ሌሎች የሥነ ምግባር ደንቦች ደግሞ በንድፈ ሐሳብ ደረጃ አድናቆት የሚቸራቸው ቢሆኑም በተግባር ላይ አይውሉም።
የሃይማኖት ሶሺዮሎጂስት የሆኑት  እንዲህ ብለዋል:- “ሰፊ ተቀባይነት የነበራቸው የሥነ ምግባር መሥፈርቶች ጊዜ ያለፈባቸው ሆነዋል። የሰዎች የሥነ ምግባር አቋም በባሕል እንዲሁም ተቋማት ባወጧቸው መሥፈርቶች ላይ የተመካ መሆን የለበትም የሚለው አስተሳሰብ ከመቼውም ጊዜ ይበልጥ ተቀባይነት አግኝቷል።” ሎስ አንጀለስ ታይምስ ያለፉትን 100 ዓመታት አስመልክቶ ጆናታን ግሎቨር የተባሉ ፈላስፋ የታዘቡትን በመጥቀስ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለዓመጽ መስፋፋት ትልቁን ሚና የተጫወተው፣ ሃይማኖትና ሰፊ ተቀባይነት የነበራቸው የሥነ ምግባር ደንቦች እየተዳከሙ መሄዳቸው መሆኑን ዘግቧል።
ሰፊ ተቀባይነት ያላቸውን የሥነ ምግባር እሴቶች በተመለከተ የተፈጠረው ግራ መጋባት፣ አንዳንድ ሰዎችን ቋሚ የሥነ ምግባር ደንብ ከመፈለግ አላገዳቸውም። የቀድሞው የዩኔስኮ ዋና ዳይሬክተር ፌዴሪኮ ማዮር ከጥቂት ዓመታት በፊት እንዲህ ብለው ነበር:- “ዓለማችንን ከመቼውም ጊዜ ይበልጥ የሚያሳስበው የሥነ ምግባር እሴቶች ጉዳይ ነው።” ይሁንና ዓለም መልካም የሆኑ የሥነ ምግባር ደንቦች ሊኖሩት አለመቻሉ ልንመራባቸው የሚገቡ ጤናማ የሥነ ምግባር ደንቦች ከናካቴው እንደሌሉ የሚያሳይ አይደለም።
ይሁን እንጂ ‘የትኛውን መሥፈርት እንከተል?’ ለሚለው ጥያቄ ሁሉም ሰው አንድ ዓይነት መልስ ይኖረዋል? እንደማይኖረው ግልጽ ነው። ታዲያ ትክክልና ስህተት ናቸው ለሚባሉት ነገሮች ተመሳሳይ አቋም ከሌለ፣ አንድ ሰው አንድ የሥነ ምግባር ደንብ ትክክል መሆንና አለመሆኑን እንዴት ማወቅ ይችላል? የሥነ ምግባር ደንብ እንደየሰዉ ይለያያል የሚለው አመለካከት በዛሬው ጊዜ ሰፊ ተቀባይነት አግኝቷል። ሆኖም ይህ አመለካከት ሰዎች የተሻለ የሥነ ምግባር አቋም እንዲኖራቸው እንዳላደረገ ማስተዋል ትችላለህ።
እንዲያውም እንግሊዛዊው ታሪክ ጸሐፊ ፖል ጆንሰን፣ ይህ ፍልስፍና ከ20ኛው መቶ ዘመን በፊት ጎልተው ይታዩ የነበሩት “የግል ኃላፊነትን የመወጣት ስሜት እንዲሁም ቋሚና ትክክለኛ የሆነ የሥነ ምግባር ደንብን የመከተል የሞራል ግዴታ ዝቅ ተደርገው እንዲታዩ ምክንያት አንደሆነ” አጥብቀው እንደሚያምኑ ገልጸዋል።
ታዲያ “ትክክለኛ የሆነ የሥነ ምግባር ደንብ” ማግኘት ወይም ‘ሰፊ ተቀባይነት ባገኙ የሥነ ምግባር ደንቦች’ መመራት ይቻል ይሆን? የተረጋጋ ሕይወት እንድንመራ የሚያስችሉንና ብሩሕ ተስፋ የሚፈነጥቁልን፣ ጊዜ የማይሽራቸው ቋሚ የሥነ ምግባር ደንቦች የማውጣት ሥልጣን ያለው አካል ይኖራል? የሚቀጥለው ርዕስ ለእነዚህ ጥያቄዎች መልስ ይሰጣል።
ጊዜ በማይሽራቸው የሥነ ምግባር ደንቦች መመራት
እያንዳንዱ ኅብረተሰብ የራሱ የሆኑ የሥነ ምግባር ደንቦች አሉት። ለምሳሌ ያህል፣ ሐቀኝነት፣ ደግነት፣ ርኅራኄና የራስን ጥቅም መሥዋዕት ማድረግ በሁሉም ሰዎች ዘንድ ከፍ ተደርገው የሚታዩና ብዙዎቻችንም የምንወዳቸው ባሕርያት ናቸው ቢባል አትስማማም?
የእነዚህ ባሕርያት ምንጭ ማን ነው?
የሥነ ምግባር መመሪያዎችን በዓለም ዙሪያ ከሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት እናገኛለን ብለን መጠበቅ አይኖርብንም። ምክንያቱም እነዚህ አብያተ ክርስቲያናት እንደ ኢየሱስና በመጀመሪያው መቶ ዘመን እንደነበሩት ተከታዮቹ የጽድቅ ሕግጋትን ከማስተማር ይልቅ ራሳቸውን የዚህ ዓለም ክፍል በማድረግ ወደ ክፋት አዘንብለዋል።
በመጀመሪያው መቶ ዘመን ከክርስቶስ ልደት በኋላ የኖረ ሳውል የተባለ አንድ ምሁር ነበር። ሳውል የኖረው የአይሁድ፣ የግሪክ እንዲሁም የሮም ባሕሎችና የሥነ ምግባር ደንቦች ከፍተኛ ተጽዕኖ በሚያሳድሩበት ማኅበረሰብ ውስጥ ነበር። ይህ ማኅበረሰብ ከነበሩት የተወሳሰቡ ወጎችና ሕጎች በተጨማሪ ሳውል የሰው ልጅ በተፈጥሮ ባገኘው የሥነ ምግባር ሕግ እንደሚመራ ተገንዝቧል። ይህ በተፈጥሮ ያገኘነው የሥነ ምግባር ሕግ ሕሊናችን ነው። ሳውል ክርስትናን ተቀብሎ ሐዋርያው ጳውሎስ ተብሎ መጠራት ከጀመረ በኋላ እንዲህ ሲል ጽፏል:- “ሕግ የሌላቸው አሕዛብ ሕግ የሚያዝዘውን ነገር በተፈጥሮ [“በደመ ነፍስ፣” ዘ ኒው ቴስታመንት ኢን ሞደርን ስፒች] ሲያደርጉ፣ ሕግ ባይኖራቸውም እነርሱ ለራሳቸው ሕግ ናቸው። ኅሊናቸው ስለሚመሰክር . . . የሕግ ትእዛዝ በልባቸው የተጻፈ መሆኑን ያሳያሉ።” ሮሜ 2:14, 15
ይሁን እንጂ ትክክልና ስህተት የሆነውን ለመለየት በደመ ነፍስ ወይም በተፈጥሮ ባገኘነው ሕሊና ብቻ መመራት በቂ ነው? የሰው ልጅ ታሪክ በግለሰብም ሆነ በቡድን ደረጃ በተፈጸሙ ስህተቶች የተሞላ መሆኑን ሳታስተውል አልቀረህም። ይህ ሁኔታ ብዙ ሰዎች፣ ሕይወታችንን የምንመራባቸው ከሁሉ የተሻሉ የሥነ ምግባር ደንቦች ለማግኘት ከእኛ የላቀ ችሎታ ካለው አካል እርዳታ ማግኘት ያስፈልገናል ብለው እንዲያስቡ አድርጓቸዋል። ብዙዎች፣ ጊዜ የማይሽራቸው የሥነ ምግባር መሥፈርቶችን በማውጣት ረገድ ከሰው ልጆች ፈጣሪ የተሻለ እንደማይገኝ ይስማማሉ። ዶክተር ካርል ጀንግ ዚ አንዲስከቨርድ ሰልፍ በተባለው መጽሐፋቸው ላይ “የአምላክን መመሪያ በጥብቅ የማይከተል ሰው በዚህ ዓለም የሚያጋጥሙትን ሥጋዊም ሆኑ ሥነ ምግባራዊ ፈተናዎች በራሱ ኃይል ሊቋቋም አይችልም” ሲሉ ተናግረዋል።
እኚህ ሰው የደረሱበት መደምደሚያ በጥንት ዘመን የኖረ አንድ ነቢይ ከጻፈው ሐሳብ ጋር ይስማማል:- “የሰው ሕይወት በራሱ እጅ እንዳልሆነች፣ አካሄዱንም በራሱ አቃንቶ ሊመራ እንደማይችል ዐውቃለሁ።” (ኤርምያስ 10:23) ፈጣሪያችን “የሚበጅህ ምን እንደ ሆነ የማስተምርህ፣ መሄድ በሚገባህ መንገድ የምመራህ ነኝ” ብሏል።ኢሳይያስ 48:17
እምነት የሚጣልባቸው የሥነ ምግባር ደንቦች የሚገኙበት አስተማማኝ ምንጭ
ከላይ የተጠቀሱት ሐሳቦች የሚገኙት በዓለም ዙሪያ በሰፊው በተሰራጨውና የሥነ ምግባር ደንቦች ምንጭ በሆነው በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ነው። በዓለም ዙሪያ የሚገኙ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች፣ ሌላው ቀርቶ ክርስቲያን ያልሆኑና ሃይማኖት የሌላቸው ሰዎች እንኳ ማስተዋልና ጥበብ ለማግኘት ቅዱሳን መጻሕፍትን ያነብባሉ። ጀርመናዊው ገጣሚ ዮሐን ቮን ጎት አንዲህ ብለዋል:- “እኔ በበኩሌ [መጽሐፍ ቅዱስን] እወደዋለሁ፣ እንዲሁም አከብረዋለሁ፤ ምክንያቱም በሕይወቴ የምመራባቸውን የሥነ ምግባር ደንቦች በሙሉ ያገኘሁት ከዚህ መጽሐፍ ነው ለማለት እችላለሁ።” የሂንዱ መሪ የነበሩት ሞሃንደስ ጋንዲ “በተራራ ስብከት [በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከሚገኙት የኢየሱስ ክርስቶስ ትምህርቶች መካከል አንዱ ነው] የተሰጣችሁን ጥልቅ እውቀት ቅሰሙ፤ . . . ምክንያቱም እነዚህ ትምህርቶች ለሁላችንም የሚጠቅሙ ናቸው” ማለታቸው ተዘግቧል።
ቀደም ሲል የተጠቀሰው ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ቅዱሳን መጻሕፍት እምነት የሚጣልባቸው የሥነ ምግባር ደንቦችን በመስጠት ረገድ የሚጫወቱትን ሚና አጉልቶ ሲገልጽ “ቅዱሳት መጻሕፍት ሁሉ የእግዚአብሔር መንፈስ ያለባቸው ናቸው፤ ለማስተማር . . . ይጠቅማሉ” ብሏል። (2 ጢሞቴዎስ 3:16) ይህ በእርግጥ እውነት ነው?
የተዘረዘሩት የሥነ ምግባር ደንቦች ቅዱሳን መጻሕፍት ከያዟቸው ጠቃሚ ምክሮች መካከል ጥቂቶቹ ብቻ ናቸው። ከእነዚህ በተጨማሪ የአምላክ ቃል በሕይወታችን ላይ መጥፎ ተጽዕኖ የሚያሳድሩ ጎጂ አስተሳሰቦችን፣ አነጋገሮችንና ድርጊቶችን እንድናስወግድ ያሳስበናል። ምሳሌ 6:16-19
አዎን፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርቶች ከሰው ልጅ ማኅበረሰብ ፈጽሞ ማግኘት የማንችለውን ምክር፣ ይኸውም ሰዎች ከሁሉ የተሻለውን የሥነ ምግባር እሴት እንዲያዳብሩ የሚያስችላቸውን መመሪያ ይሰጣል። እነዚህን ትምህርቶች ተቀብለው በተግባር ላይ የሚያውሉ ሁሉ በሕይወታቸው ላይ ጉልህ ለውጥ ያደርጋሉ። የተሻለ አስተሳሰብ ይኖራቸዋል። (ኤፌሶን 4:23, 24) ውስጣዊ ዝንባሌያቸው ይለወጣል። ብዙዎች በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኙትን የአምላክን የሥነ ምግባር ደንቦች መማራቸው ዘረኝነትንና ጭፍን ጥላቻን ከልባቸው ነቅለው እንዲያወጡ ረድቷቸዋል። (ዕብራውያን 4:12) መጽሐፍ ቅዱስና በውስጡ የሚገኙት የሥነ ምግባር እሴቶች ሰዎች ሁሉንም ዓይነት ዓመጽና ክፋት አስወግደው የተሻሉ ግለሰቦች እንዲሆኑ አነሳስተዋቸዋል።
አዎን፣ የመጽሐፍ ቅዱስ የሥነ ምግባር እሴቶች በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች፣ ሥር የሰደዱ ልማዶቻቸውንና በሌሎች ላይ ጉዳት የሚያስከትሉ ድርጊቶቻቸውን እንዲያስወግዱ ረድተዋቸዋል። (1 ቆሮንቶስ 6:9-11) የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርቶች፣ እነዚህ ሰዎች ልማዶቻቸውን ብቻ ሳይሆን ልባቸውን፣ ተስፋቸውንና የቤተሰባቸውን ሕይወት ጭምር እንዲለውጡ አድርገዋቸዋል። ይህ ዓለም የቱንም ያህል እየተበላሸ ቢሄድ በዓለም ዙሪያ የሚገኙ በርካታ ሰዎች ሕይወታቸው በመሻሻል ላይ ይገኛል። እንዲህ ያለው ለውጥ ለዘላለም የሚቀጥል ይሆናል። መጽሐፍ ቅዱስ “ሣሩ ይደርቃል፤ አበባውም ይረግፋል፤ የአምላካችን ቃል ግን ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል” ይላል። ኢሳይያስ 40:8
ይሁን እንጂ አንተስ “የአምላካችን ቃል” ከሚሰጠው ትምህርት ተጠቃሚ መሆን ትፈልጋለህ? የይሖዋ ምሥክሮች ሕይወትህን በመጽሐፍ ቅዱስ የሥነ ምግባር እሴቶች መምራት የምትችለው እንዴት እንደሆነ ሊያሳዩህ ፈቃደኞች ናቸው። ከእነዚህ የሥነ ምግባር እሴቶች ጋር ተስማምተህ መኖርህ በአሁኑ ጊዜ የአምላክን ሞገስ እንድታገኝ ይረዳሃል። ለወደፊቱ ደግሞ ጊዜ በማይሽራቸው መለኮታዊ ደንቦች እየተመራህ ለዘላለም እንድትኖር ያስችልሃል።
ጊዜ የማይሽራቸው የሥነ ምግባር ደንቦች
ወርቃማው ሕግ። “ሌሎች እንዲያደርጉላችሁ የምትፈልጉትን ነገር እናንተም አድርጉላቸው፤ ኦሪትም፣ ነቢያትም በዚህ ይጠቃለላሉና።” ማቴዎስ 7:12
ጎረቤትህን ውደድ። “ጎረቤትህን እንደ ራስህ ውደድ።” (ማቴዎስ 22:39) “ፍቅር በባልንጀራው ላይ ክፉ አያደርግም፤ ስለዚህ ፍቅር የሕግ መፈጸሚያ ነው።” ሮሜ 13:10
ሌሎችን አክብር። “እርስ በርሳችሁ በወንድማማች መዋደድ አጥብቃችሁ ተዋደዱ፤ አንዱ ሌላውን ከራሱ በማስበለጥ እርስ በርሳችሁ ተከባበሩ።” ሮሜ 12:10
ሰላምን እሻ። “እርስ በርሳችሁ ተስማምታችሁ በሰላም ኑሩ።” (ማርቆስ 9:50 የታረመው የ1980 ትርጉም) “ቢቻላችሁስ በበኩላችሁ ከሰው ሁሉ ጋር በሰላም ኑሩ።” (ሮሜ 12:18) “ሰላም የሚገኝበትን . . . ማንኛውንም ጥረት እናድርግ።” ሮሜ 14:19
ይቅር ባይ ሁን። “እኛም ደግሞ የበደሉንን ይቅር እንደምንል፣ በደላችንን ይቅር በለን።” (ማቴዎስ 6:12) “ይቅር ተባባሉ፤ እርስ በርሳችሁ ቸሮችና ርኅሩኆች ሁኑ።” ኤፌሶን 4:32
ታማኝ ሁን። ‘ለሚስትህ ታማኝ በመሆንና እርስዋን ብቻ በመውደድ እርካ። በወጣትነት ባገባሃት ሚስትህ ደስ ይበልህ። ውበትዋ ሁልጊዜ ያርካህ፤ በፍቅርዋም ዘወትር ደስ ይበልህ። በአመንዝራይቱ ሴት ለምን ትማረካለህ? ለምንስ ከሌላው ሰው ሚስት ጋር ትባልጋለህ?’ (ምሳሌ 5:15-20 “በትንሽ ነገር ታማኝ የሆነ በትልቁም ይታመናል፤ በትንሽ ነገር ያልታመነ በትልቁም አይታመንም።” (ሉቃስ 16:10) “ባለ ዐደራዎችም ታማኝ ሆነው መገኘት አለባቸው።” 1 ቆሮንቶስ 4:2
ሐቀኛ ሁን። “በአባይ ሚዛንና በከረጢት ባለ በተንኰል መመዘኛ ንጹሕ እሆናለሁን?” (ሚክያስ 6:11 የ1954 ትርጉም) “በሁሉም መንገድ በመልካም አኗኗር ለመኖር የሚናፍቅ ንጹሕ ኅሊና እንዳለን እርግጠኞች ነን።”ዕብራውያን 13:18
እውነተኛና ፍትሕ ወዳድ ሁን። “ክፉውን ጥሉ፤ መልካሙንም ውደዱ። በፍርድ አደባባይም ፍትሕን አታጓድሉ።” (አሞጽ 5:15) “እርስ በርሳችሁ እውነትን ተነጋገሩ፤ በአደባባያችሁም እውነትንና ትክክለኛ ፍርድን አስፍኑ።” (ዘካርያስ 8:16) “ውሸትን አስወግዳችሁ፣ እያንዳንዳችሁ ከባልንጀራችሁ ጋር እውነትን ተነጋገሩ።”ኤፌሶን 4:25
ታታሪና ትጉ ሠራተኛ ሁን። “በሙያው ሥልጡን የሆነውን ሰው አይተሃልን? በነገሥታት ዘንድ ባለሟል ይሆናል።” (ምሳሌ 22:29) “ለሥራ ከመትጋት አትለግሙ።” (ሮሜ 12:11) “የምታደርጉትን ሁሉ ለሰው ሳይሆን ለጌታ እንደምታደርጉት ቈጥራችሁ በሙሉ ልባችሁ አድርጉት።” ቈላስይስ 3:23
የዋህ፣ ርኅሩኅና ቸር ሁን። “ርኅራኄን፣ ቸርነትን፣ ትሕትናን፣ ጨዋነትንና ትዕግሥትን ልበሱ።” ቈላስይስ 3:12
ክፉን በመልካም አሸንፍ። “ጠላቶቻችሁን ውደዱ፤ ለሚያሳድዷችሁም ጸልዩ።” (ማቴዎስ 5:44) “ክፉን በመልካም አሸንፍ እንጂ በክፉ አትሸነፍ።” ሮሜ 12:21
ለእግዚአብሄር የከበረውን ወይም የተመረጠውን ምርጥህን ስጥ። “‘ጌታ አምላክህን በፍጹም ልብህ፣ በፍጹም ነፍስህ፣ በፍጹም ሐሳብህ ውደድ፤’ ይህ የመጀመሪያውና ከሁሉ የሚበልጠው ትእዛዝ ነው።”ማቴዎስ 22:37, 38
በመጽሐፍ ቅዱስ የሥነ ምግባር እሴቶች መመራት የተሳካ ትዳር፣ ደስተኛ የቤተሰብ ሕይወትና ጥሩ ወዳጆች እንድናገኝ ያስችለናል።






0 comments:

Post a Comment