ክፍል 1
አቶ አሉላና ወ/ ሮ ገነት ከውጪ ሲያዩዋቸው እንከን የሌባቸው ባለትዳሮች ይመስላሉ፤የጋብቻ ዘመናቸውም ከርም ያለ ነው፤
ወሮ ገነት አስተዋይ ሴት ናቸው የተቸገረ አይተው አይጨክኑም ለስው ያላቸው ፍቅር የለበጣ ሳይሆን እውነት ነው፤ የሆዳቸውን
በሆዳቸው አድረገው በአፋቸው ስውን ያደልሉም፤ ግልጽ ሴት ናቸው ከዚህም የተነሳ በስዎች የተከበሩ ናቸው።
አቶ አሉላና ወ/ ሮ ገነት ከውጪ ሲያዩዋቸው እንከን የሌባቸው ባለትዳሮች ይመስላሉ፤የጋብቻ ዘመናቸውም ከርም ያለ ነው፤
ወሮ ገነት አስተዋይ ሴት ናቸው የተቸገረ አይተው አይጨክኑም ለስው ያላቸው ፍቅር የለበጣ ሳይሆን እውነት ነው፤ የሆዳቸውን
በሆዳቸው አድረገው በአፋቸው ስውን ያደልሉም፤ ግልጽ ሴት ናቸው ከዚህም የተነሳ በስዎች የተከበሩ ናቸው።
አቶ አሉላ ከባለቤታቸው ጋር የሚመሳስል ጠባይ አላቸው፤ ይሁን እንጂ ከስው ፊት ሲሆኑና ከቤታቸው የሚያስተላለፉት መልዕክትና ጸባያቸው የተለያየ ነው፤ ከዚህ የተነሳ አቶ አሉላ ጸባያቸውን ወይም አመላቸውን መጨበጥ አይቻለም፤ ደግ የሚስሩት ሁሉለይስሙላና ለመታወቅ ነው፤ እነዚህ ሁለት ባለና ሚስት በለታዊ ኑሮአቸው የሚያደርጉትን ምልልስ እንመልከት።
ከጠዋቱ ዘጠኝ ስዓት ነው፤ አንድ ግዋደኛቸው ወደቤት መጣና ከበር ላይ ቆም አለና ቤቶች እንድምን አደራችሁ ብሎ ስለማታ
ጠየቀ፣ ማነው ብለው ወ/ሮ ገነት ወደበሩ ለመክፈት እየተራመዱ እያሉ፣ አቶ አሉላ ለባለቤታቸው
ጠየቀ፣ ማነው ብለው ወ/ሮ ገነት ወደበሩ ለመክፈት እየተራመዱ እያሉ፣ አቶ አሉላ ለባለቤታቸው
እጃቸውን በማወዛወዝ መልክት ስጠዋቸው፤ ሴትየዋም ወደ ባልተቤታቸው ዘውር ሲሉ፣
አቶ አሉላ ለባለቤታቸው “አሉላ የለም በዪው፣ ዝም ብሎ ነው፣ እንዴ ስው ቤት ዘው ብሎ ይመጣል?” በመጣበት እግሩ
ይመለስ አሉ።
ይመለስ አሉ።
ወ/ ገነትም ባላቸው የተናገሩት ነገር፣ ቢያስደንግጣቸውም ወደበሩ ቀርብ አሉና በሩን ገርብብ አድርገው ክፍተው አያሉ፣ እንግዳውም አቶ አሉላ አለ እንዴ? ብሎ ሲጠይቅ አቶ አሉላ የለሁም ብለሽ ንገሪው በሎኛል አሉ ወይዘሮ ገነት ለንግዳው፤
እንግዳው ምንድነው? የሚሉት ወይዘሮ ገነት? አሁን እኮ ገና ጠዋት ነው ከመቼው ወጡ? አቶ አሉላ ከመቼ ወዲህ የጠዋት ስው ሆኑ? ቤተክርስቲያን ሄደው ማስቀደስ ጀመሩ እንዴ?
አዎን ለንፍሳቸው አድረዋል? አልስማህም እንዴ?
አሁንም ደግሜ እነግርሃለሁ፤ የለም ብዬ እንድነግርህ ነግሮኛል አሉት እንግዳውም የወ/ሮ ገነት አባባላቸው ገረመውና መቼም እያለ የለሁም አይልም፤ ወ/ሮ ገነትም ከት ብለው ሳቅይና ቆይተን እናየዋለን አሉት።
አሉላ የለም ብይው ብሎ እንደነግረህ ነግሮኛል አሉት። እያለ ነው የለም ብሉት የሚልዎት?
አሉላ የለም ብይው ብሎ እንደነግረህ ነግሮኛል አሉት። እያለ ነው የለም ብሉት የሚልዎት?
እንግዳው በመድነቅ! ምን ማለቱ ነው አሉላ፣ ደህናም አይደል እንዴ?
ወይ ጎድ ብሎ እጁን ባፉ ላይ አደረገና ትንሽ ቆም ብሎ አስበ፤ ወ/ ገነትም ከደጃፍ ላይ ያስቀመጡን እቃ ለማንሳት ዝውር ሲሉ፣
እንግዳው ወደቤት አዘናግቶ ገባ፤ ሲገባም አቶ አሉላ በአግዳሚ አልጋ ላይ ጋደም ብለዋል፤ አቶ አሉላ፤ ምን ነካዎት ከቤት እያሉ
የለሁም የምታስብሉት አለ እንግዳው አቶ አሉላ ወደ እንግዳው ዘውር አሉና፣ ማን ነገረህ ብለው ሲጠይቁት ባለቤትዎ ናቸዋ አለ እንግዳው፤አቶ አሉላ፤ እርስዋ ደግሞ ያልክዋትን በትክክል አልስማችም ተሳስታለች፤ አንተን ወዳጄን ከደጄ ድርስ መጥተህ እንዴት እያለሁ የለሁም እላለሁ?
እንግዳው ወደቤት አዘናግቶ ገባ፤ ሲገባም አቶ አሉላ በአግዳሚ አልጋ ላይ ጋደም ብለዋል፤ አቶ አሉላ፤ ምን ነካዎት ከቤት እያሉ
የለሁም የምታስብሉት አለ እንግዳው አቶ አሉላ ወደ እንግዳው ዘውር አሉና፣ ማን ነገረህ ብለው ሲጠይቁት ባለቤትዎ ናቸዋ አለ እንግዳው፤አቶ አሉላ፤ እርስዋ ደግሞ ያልክዋትን በትክክል አልስማችም ተሳስታለች፤ አንተን ወዳጄን ከደጄ ድርስ መጥተህ እንዴት እያለሁ የለሁም እላለሁ?
አቶ አሉላ ነገሩን ለማረሳሳት ነገሩ ወዲህ ነው አሉት ለንግዳው፣ እንግዳው ወሬ አትለውጡ አቶ አሉላ ነገሩ ወዲህ ነው፣ ብለው
ጀምረዋል ነገሩ ወዴት ነው?
ጀምረዋል ነገሩ ወዴት ነው?
ወ/ ገነት ከውጪ ሲመጡ አንግዳውና አቶ አሉላ በአንድ ላይ ቁጭ ብለው አዩ፤ አሉላ የለም ብለሽ ሽኚው ያሉት ስው በየት አልፎ ከቤት እንደገባ ሳይወቁ ከባላቸው ጋር እንጅና ግዋንት ሆነው ሲነጋገሩ አዩ፤ ባላቸው ምን ያህል አስመሳይ እንደሆኑ አዩና በትዝብት ተሞልተው፤ አይ! የኔ ባለቤት፣ ይህ ጸባይህ መቼ ይሆን የሚለቅህ? የምትገርም ስው ነህ፤ እስቲ ቡና ላፍላ ብለው ወደ
ግዋዳ ገቡ።
ግዋዳ ገቡ።
ባልና ሚስት ካንድ ወንዝ ይቀዳል እንዴ?
“ባልና ሚስት ካንድ ባህር ይቀዳል” እንደሚባለው አይነት አይደሉም ወ/ሮ ገነትና አቶ አሉላ። በተለያየ አቅጣጫ ሚጓዙ ባልና ሚስት ናቸው፣ ሆኖውም አብረው ይኖራሉ። አብሮ መኖር ሁሉ መኖር አይደለም ደባል ሆኖ መኖር እንጂ። የአላቻ ጋብቻ ቆይ ብቻ የሚለው ተረት ይገልጻቸው ይሆን? አቻም ባሆኑ አብረው ይኖራሉ ምን ችግር አላ ብቻ ፍቅር ይኑራቸው እንጂ፣ በትዳር ከነዋሪው ሌላ በዚህ ላይ ትችት የሚስጥ ያለ አይመለኝም በግምት ካለሆነ በተቀር።
እኔ የሚመስለኝ ሁሉቱም ባልና ሚስት አንድ አይነት ጠባይ ምርጫ ወዘተ. ተመሳሳይነት ያላቸው መሆን ይገባቸዋል ተስማምተው ለመኖር ፣ ያለበለዚያ ግን ባይስማሙ ምን ያስደንቃል ምክንያቱም ባልና ሚስቱ ካንድ ባህር አልተቀዱማ ሚስጢሩ እዚህ ላይ ይሆን ነዋ!
ወ/ሮ ገነት ባለቤታቸው ላሉት ነገር ይመኑበት አይመኑበት ይጉዳቸው ወይም አይጉዳቸው ግራና ቀኝ ሳይሉ ለጥ ስጥ ብለው ማድረግ ወይም መስማት አለባቸው፤ ይህንንም ሃሳባቸውን ባለቤታቸው ወ/ሮ ገነት ወልፊት እንዳይሉና ጥያቄ እንዳይነሱ የሚከላከሉበት መሳሪያቸው የነፍስ አባታቸው ያስተማሯቸውን ሴቶችን በተመለከተ በመጥቀስ መገዛት ለጥ ስጥ ማለት ማለት ይኖርባቸዋል የሚለውን ነው፤ የጠባይ ለውጥ ካሳዩ ግን ለነፍስ አባታቸው ሄደው እንደሚናገሩ በባለቤታቸው ጆሮ ውስጥ እንዲደውል ማደረግ የተለመደ ተግባራቸው ነው፤ ታዲያ አንድ ቀን እንደዚህ ሆነ።
አቶ አሉላና ባለቤታቸው ወ/ሮ ገነት ወደ ወዳጃቸው ቤት እንግድነት ሄዱ፤ መቼም አቶ አሉላ አስመሳይ ብቻ ሳይሆነ ተግደርዳሪም ናቸው፤ አንድ ነገር ለራሳቸው የሚጠቅም እንክዋን ቢሆን እንዲለመኑ ይፈልጋሉ፣ ከሳቸው በላይ አዋቂ ያለም አይመስላቸው። ይህ ባህሪያቸው ከምን እንዳደረሳቸው እንመልከት።
ባልና ሚስቱ እንግድነት የሄዱት ከተከበሩ ወዳጆቻቸው ቤት ነበር፤ እዚያ ቤት ደግሞ በአመጋገብ ሆነ በአለባበስና ባነጋገር የኢትዮጵያ ባህል የሚታይበት ቤተስብ ነው፤ ከትላልቁ ጀምሮ እስከ ልጆቹ ባህሉ የተጠበቀ ነው።
አቶ አሉና ወ/ሮ ገነት ከዚህ ቤተስብ ቤት እንደደረሱ የግቢውን በር አንክዋኩ፤ በበሩ ላይ ዘብ የቆመው ዘበኛ፣ የግቢውን በር ግርብብ አድርጎ ከፍቶ ማንነታቸውን ከለየ በኋላ በሩን ከፈተላቸው፣ ከዚህ ቀደም የሚያውቃቸው ስለነበረ፣ ወደ ግቢው ውስጥ ለማስገባት አላንገራገረም፤ እጅ ከነሳቸው በኋላ አስገባቸው።
ዘበኛው፤ ግቤው በጣም ስፊ ስለሆነ በሥርዓት ወዴት መግባት እንዳለባቸው ለማሳየት፣ ከፊት ከፊታቸው እየሄደ አቶ አሉናና ወ/ሮ ገነትን መመራት ቀጠለ፤
አቶ አሉላ ዘበኛው የሚያደርገው ነገር ደስ አላላቸውም፤ የዘበኛውን አገልግሎት የቆጠሩት እርሳቸው ሞኝ ሆነው ዘበኛው አዋቂ ሆኖ እንደመራቸው ነበር፤ ዘበኛውን ከላይ ወደታች ካዩት በኋላ፣ ወደ ዘበኛው ዘውር አሉና አንተ ደግሞ የምን ቤት ነህ? እኛ እኮ! ወዴት እንደምንሄድ የማናውቅ ስዎች ሆንን ነው እንዴ? እንደአይነስውር የምትመራን አሉት? ቀጥለውም አይናችን በግንባራችን ላይ አይደለም የተቀመጠው፣
ወ/ሮ ገነት እንደልማዳቸው የባለቸውን አመል ስለሚያውቁት፣ እርስዎ ደግሞ እንደው ለሁሉ ነገር አቃቂር አውጥተው ይችሉታል?
አቶ አሉላ፣ እኔ አሉላ አንቺን መስልኩሽ እንዴ ከመቼ ወዲህ ነው፣ እኔ በመሪ ወዲያና ወዲህ ሄጀ የማውቀው? እራሴን ችዬ የምኖር ስው፣ የስውን ድጋፍ የማልፍልግ እንደሆንኩ፣ አስረግጠሽ ታውቂ የለም እንዴ? ታዲያ መጠየቅ ይነስብኝ እንዴ? መጠየቅ መብቴ ነው አሉ አይናቸውን እያጉረጠረጡ።
ወ/ሮ ገንትም፣ ከቤት እንደተመለሱ አሁን አፋቸውን ካልጠበቁ አንድ ትችት ካፋቸው ከወጣ የሚደርስባቸውን ስለሚያውቁ፣ ነገሩን ለማለሳለስ ሙከራ አደረጉ እኔ እኮ ያልኩት ነገር ያስቆጣዎታል ብዬ አይደለም የተነገርኩት አሉ። ወ/ሮ ገነት ጠብ እንዳይጫር ጥረት ያደርጋሉ፤ ጥረታቸውም እንክዋን የማይስራላቸው ጊዜ አለ፤ የዛሬ የአቶ አሉላ የአይን ማግረጥረጥ የሚነግራቸው ነገር አለ፣ ይኸውም ጠብቂኝ እቤት ከተመለስን በኋላ የሚሉ ይመስላሉ።
ለምንድነው አቶ አሉላ ለባለቤታቸው የማይመች አመል የኖራቸው? የተባለ እንደሆነ መልሱ አንድ ነው። ምናልባትም አቶ አሉላ ባደጉበት ቤተስብ ውስጥ ሻካራ ንግግር የተለመደ ከነበረ፣ እሳቸውም እንዲህ ያለውን የአነጋገር ልምዳቸው ከሆነባቸው ምን ማድረግ ይችላሉ? በዚህ ረገድ እኝህ ስው ምን ማድረግ ይቻላሉ? በሕይወታቸው ውስጥ በተለየዩ መስኮች አንዳንድ ነገሮችን ላለማድረግ ቁርጥ ውሳኔ አድረገዋል። ታዲያ አነጋገራቸውን በተገመለከተ ገደብ የሚያበጁበት ምን ደረጃ ላይ ሲደርስ ይሆን?
አልሞት ባይ ተጋዳይ[1]
አልሞት ባይ ተጋዳይ ሆነና ነገሩ፣
ስንቶች በባላቸው ተስናክለው ቀሩ።
ባል ተብዬው በሃይማኖት ካባ ተሽፍኖ፣
የውስጥ ተንኮሉን በልቡ ስውሮ፣
ለማስመስል ያህል ጥቅሶችን ጠቃቅሶ፣
ጋብቻ ጠየቀኝ እንዲወጣ ከችግሩ ዳክሮ።
አወይ! ሞኝነቴ በቃላቱ ተታልዬ፣
ከወጥመዱ ገባሁና ቀረሁኝ ቀልዬ።
እርሱ የበላይ እኔ የበታች ሆኜ፣
በሃይማኖት ሽፋን ተሽፍኜ፣
ሀዘን ተፈራረቁብኝ ቀረሁኝ መንምኜ።
ሚስጢሩን ጠባቂ መሆኔን ተረድቶ፣
ጥቅስ መጥቀሱን ማስሪያው አድርቶ፣
ጭቆናውን ቀጠለ ክፋቱ አይሎ።
እየቆየሁ ስሄድ ውስጤ ተጎዳና፣
የስው ያልህ ብዬ ብጮህ ማን ተረዳኝና፣
ከችግሬ አወጣኝ ቶሎ ደረስና።
አወይ! የስው ልብ ክፋቱ፣
ጓደኛውን ለመጉዳት ቀን ከሌት ማስላቱ፣
በዳይ አላወክም እንዴ?
የተበዳዩ ፍርድ አይቀረም በከንቱ።
እኔ የምልህ?
ለክፋትህ መሽፈኛ የበግ ለምድ ለብስህ፣
ጥቅሶችን እየጠቀስክ የተንኮል ስሌትስ መሽፈኛ አድረገህ፣
የጊዜ ጉዳይ ነው እንጂ እወቀው አትቀርም በድለህ።
ጋብቻ መለኮታዊ ተቋም ነው
ይህ ጽሑፍ በጥንቱ ጋብቻ ውስጥ የነበረውንና አሁንም ያለውን የሞራልና/የሥነምግባር ማህበራዊነቱን ጨምሮ ያነሳል። ጋብቻ ህጋዊ እውቅና ያለው በክርስቲያኖችም ሆነ በሌሎች እምነቶችንም ጨምሮ በሲቪል ህግ በወጣው ሥርዓት የሚተዳደር ተቅዋም ነው። ጋብቻ በወንድና
በሴት መካከል ለይስሙላ ሳይሆን ዘላቂ ህብረትና አንድነት ላይ በውልና
በሥርዓት የተቋቋመ ተቅዋም ነው። በዚህ ጽሑፍ ብዙውን ጊዜ በባልና ሚስት መካከል ያለውን ህጋዊ ህብረትና ጋብቻ የሥነ ምግባር እና
ማኅበራዊ ገጽታዎች ይይዛል። "ባል እና ሚስት" ይህ
ጥንድ ቃላት የጋራ የፆታ ግንኙነት የሕይወት መብቶች እና ዘላቂ የሆነ አንድነት ብሎም "ሕጋዊ” የተፈጥሮ የእርስ በርስ
ስምምነት ይይዛል። የክርስቲያን ጋብቻ ህዋላ ቀር ከሆነው ባህል ቅምጥና እና ዝሙትን አያስተናግደም። ከአንድ በላይ እና polyandrous ማህበራት
እንደነዚህ ባለው ግንኙነት ውስጥ ብዛት ያላቸው ግለሰቦች ብዙ ትዳሮች በሚኖሩበት ህብረተስብ ነበሩ። በዚህ አይነት የጋብቻ አንዋንዋር ውስጥ ሴቶች ጋር በጅምላ ያለ ግንኙነት
ሆኖ ሳይጋቡ በተለምዶ ቅምጦች ነበሩ።
ጋብቻ አንድ ወንድና አንዲት ሴት በቅዱሳን መጻሕፍት ላይ በሰፈረው ሥርዓትና ደንብ መሠረት ባልና ሚስት
ሆነው በአንድነት ለመኖር የሚመሠርቱት ውህደት ነው። ጋብቻ መለኮታዊ ተቋም ነው። በትዳር ጓደኞች መካከል የፍቅር መንፈስ ስለሚኖርና
አንዱ የትዳር ጓደኛ ለሌላው አሳቢነት ለማሳየት ቃል የገባ ስለሆነ ጋብቻ በባልና በሚስት መካከል መተማመን ያለበትና የተቀራረበ
ግንኙነት እንዲኖር ያስችላል። እግዚአብሄር ጋብቻን ያቋቋመው የወንድ ማሟያ የምትሆን የቅርብ ጓደኛ ለማስገኘት ብቻ ሳይሆን በቤተሰብ ዝግጅት አማካኝነት
ሌሎች ተጨማሪ ሰዎች እንዲወለዱ ሲል ነው። በሚቻልበት ቦታ ሁሉ የክርስቲያን ጉባኤ የሚቀበለው ማንኛውም ጋብቻ በሕጋዊ መንገድ የተመዘገበ
እንዲሆን ይፈለጋል።
ከአገሩ ሕግ ጋር የሚስማማ ጋብቻ
መመሥረት አስፈላጊ ነውን?
ቲቶ 3:1:- “ለገዦችና ለባለ ሥልጣኖች የሚገዙና የሚታዘዙ . . . እንዲሆኑ አሳስባቸው።” (ሰዎች
እነዚህን መመሪያዎች ሲያከብሩ የተጋቢዎቹ ስም ከነቀፋ ይጠበቃል። የሚወለዱትም ልጆች ሕጋዊ ጋብቻ ከሌላቸው ወላጆች በሚወለዱ ልጆች
ላይ ከሚደርሰው ነቀፋ ይድናሉ። በተጨማሪም ጋብቻን ሕግ በሚጠይቀው መንገድ ማስመዝገብ ከትዳር ጓደኛሞች አንዱ በሞት በሚለይበት
ጊዜ የቤተሰቡን የንብረት ባለቤትነት መብት ለማስጠበቅ ይጠቅማል።)
ዕብ. 13:4:- “መጋባት በሁሉ ዘንድ ክቡር መኝታውም ንጹሕ ይሁን፤ ሴሰኞችንና አመንዝሮችን ግን
እግዚአብሔር ይፈርድባቸዋል።” (በሕጋዊ መንገድ መጋባቱ ጋብቻው “ክቡር” እንዲሆን በማድረግ ረገድ ትልቅ ድርሻ አለው። ለ“ሴሰኝነት”
እና ለ“ምንዝር” በምንሰጠው ትርጉም ላይ በቲቶ 3:1 ላይ የተጠቀሰውን ግንዛቤ ውስጥ ማስገባት ይኖርብናል።)
1 ጴጥ. 2:12–15:- “ስለሚመለከቱት ስለ መልካም ሥራችሁ፣ ክፉ እንደምታደርጉ በዚያ እናንተን
በሚያሙበት ነገር፣ በሚጐበኝበት ቀን እግዚአብሔርን ያከብሩት ዘንድ በአሕዛብ መካከል ኑሮአችሁ መልካም ይሁን። ስለ ጌታ ብላችሁ
ለሰው ሥርዓት ሁሉ ተገዙ፤ ለንጉሥም ቢሆን፣ ከሁሉ በላይ ነውና፤ ለመኳንንትም ቢሆን፣ ክፉ የሚያደርጉትን ለመቅጣት በጎም የሚያደርጉትን
ለማመስገን ከእርሱ ተልከዋልና ተገዙ። በጎ እያደረጋችሁ፣ የማያውቁትን ሞኞች ዝም ታሰኙ ዘንድ እንዲህ የእግዚአብሔር ፈቃድ ነውና።”
አዳምና ሔዋን አብረው መኖር
ሲጀምሩ “ሕጋዊ ሥርዓት” ተፈጽሞ ነበረን?
ዘፍ. 2:22–24:- “እግዚብሔር አምላክም ከአዳም የወሰዳትን አጥንት ሴት አድርጎ ሠራት፤ ወደ አዳምም
አመጣት። አዳምም አለ:- ይህች አጥንት ከአጥንቴ ናት፣ ሥጋም ከሥጋዬ ናት፤ እርስዋ ከወንድ ተገኝታለችና ሴት ትባል። ስለዚህም
ሰው አባቱንና እናቱን ይተዋል፣ በሚስቱም ይጣበቃል፤ ሁለቱም አንድ ሥጋ ይሆናሉ።” (አዳምንና ሔዋንን አንድ ላይ እንዲኖሩ ያደረገው
የጽንፈ ዓለሙ ሉዓላዊ ገዥ ይሖዋ አምላክ ራሱ እንደሆነ ልብ በል። አንድ ወንድና አንዲት ሴት ስለ ሕጋዊ ባለ ሥልጣን ሳይጨነቁ
አብረው ለመኖር አልወሰኑም። የጋብቻ አንድነት ዘላቂ መሆን እንዳለበት አምላክ ጠበቅ አድርጎ የተናገረውንም ልብ በል።)
ዘፍ. 1:28:- “እግዚአብሔርም [አዳምንና ሔዋንን] ባረካቸው፣ እንዲህም አላቸው:- ብዙ፣ ተባዙ፣
ምድርንም ሙሉአት፣ ግዙአትም፤ የባሕርን ዓሦችና የሰማይን ወፎች በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱትንም ሁሉ ግዙአቸው።” (እዚህ ላይ የመጨረሻው
ከፍተኛ ሕጋዊ ባለ ሥልጣን ጋብቻውን ባርኮታል። ሩካቤ ሥጋ እንዲፈጽሙ የተፈቀደላቸው ሲሆን ለሕይወታቸውም ትርጉም የሚሰጥ ሥራ ሰጣቸው።)
አንድ ሰው የአካባቢው ሕግ የሚፈቅድለት
ከሆነ ከአንድ ሚስት በላይ ሊኖረው ይችላልን?
1 ጢሞ. 3:2, 12:- “ኤጲስ ቆጶስ [“የበላይ ተመልካች” ] . . . የማይነቀፍ፣ የአንዲት ሚስት ባል [መሆን ይገባዋል።] . .
. ዲያቆናት እያንዳንዳቸው የአንዲት ሴት ባሎች ይሁኑ።” (እነዚህ ወንዶች ኃላፊነት የተሰጣቸው ብቻ ሳይሆኑ በክርስቲያን ጉባኤ
ውስጥ ያሉ ሰዎች እንደ መልካም ምሳሌ አድርገው የሚከተሏቸው ጭምር ናቸው።
1 ቆሮ. 7:2:- “ስለ ዝሙት ጠንቅ ለእያንዳንዱ ሚስት ትኑረው፣ እያንዳንዲቱም ደግሞ ለራሷ ባል
ይኑራት።” (ማንኛቸውም ቢሆኑ ከአንድ በላይ ማግባት አልተፈቀደላቸውም።)
አብርሃም፣ ያዕቆብ እና ሰሎሞን
እያንዳንዳቸው ከአንድ በላይ ሚስት እንዲኖራቸው አምላክ ለምን ፈቀደ?
ብዙ ሚስት የማግባትን ሥርዓት ያቋቋመው እግዚአብሄር አልነበረም። እግዚአብሄር ለአዳም የሰጠው አንዲት
ሚስት ብቻ ነበር። ከጊዜ በኋላ የቃየን ተወላጅ የነበረው ላሜህ ሁለት ሚስቶች አገባ። (ዘፍ. 4:19) ውሎ አድሮ ሌሎችም የእርሱን
ምሳሌ ተከተሉ፣ አንዳንዶችም ገረዶቻቸውን ቁባት አደረጉ። እግዚአብሄር ይህን አድራጎት ዝም ብሎ ተመልክቶታል። እንዲያውም እንዲህ
ባለ ግንኙነት ለተሳሰሩ ሴቶች ተገቢ አያያዝ እንዲደረግላቸው የሚያዙ ደንቦች በሙሴ ሕግ ውስጥ እንዲኖሩ አድርጓል። ይህን ያደረገው
ግን የክርስቲያን ጉባኤ እስከሚቋቋም ድረስ ነበር። ከዚያ በኋላ አገልጋዮቹ እርሱ ራሱ በኤደን ውስጥ አቋቁሞት ወደነበረው ሥርዓት
እንዲመለሱ አድርጓል።
አብርሃም ሦራን (ሣራን) ሚስት አድርጎ ወሰዳት። ሦራ ዕድሜዋ 75 ዓመት በሆነ ጊዜ ከዚያ በኋላ ልጅ
እንደማትወልድ አስባ በገረድዋ በኩል ሕጋዊ ልጅ ለማግኘት ባልዋ ከገረድዋ ጋር ግንኙነት እንዲያደርግ ራሷ ጠየቀችው። አብርሃምም
እንዳለችው አደረገ። ይሁን እንጂ በዚህ ሳቢያ በቤተሰቡ ላይ ከፍተኛ ግጭት ተፈጥሯል። (ዘፍ. 16:1–4) እግዚአብሄር ለአብርሃም
“ዘር” እንደሚሰጠው የገባውን ቃል ኪዳን ሣራ በተአምር እንድትፀንስ በማድረግ ፈጽሞአል። (ዘፍ. 18:9–14) ሣራ እስከሞተችበት
ጊዜ ድረስ አብርሃም ሌላ ሚስት አላገባም።ዘፍ. 23:2፤ 25:1
ያዕቆብ ከአንድ ሚስት በላይ ያገባው አማቱ ስላታለለው ነበር። ሚስት ለመፈለግ ወደ ፓዳንኤራም (ሜሶጶጣሚያ)
በሄደ ጊዜ ከአንድ በላይ የማግባት ፍላጎት በሐሳቡ ውስጥ አልነበረም። በያዕቆብ ሚስቶች መካከል ደስታቸውን የሚያጠፋ ምቀኝነት እንደነበረ
በመጽሐፍ ቅዱስ ተጽፎአል ። ዘፍ. 29:18–30:24
ሰሎሞን ብዙ ሚስቶችና ቁባቶች እንደነበሩት የታወቀ ነው። ነገር ግን ይህን በማድረጉ ንጉሡ “ልቡ እንዳይስት
ሚስቶችን ለእርሱ አያበዛም ” የሚለውን የእግዚአብሄርን ግልጽ ትእዛዝ እንደጣሰ ብዙ ሰዎች አይገነዘቡም። (ዘዳ. 17:17) ሰሎሞን
ከባዕድ አገሮች ባገባቸው ሚስቶቹ ተጽዕኖ ምክንያት የሐሰት አማልክትን አመለከ፣ “በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ነገርን አደረገ። .
. . እግዚአብሔር ሰሎሞንን ተቆጣ።”1 ነገ. 11:1–9
የትዳር ጓደኛሞች በሰላም አብረው
መኖር ካልቻሉ ተለያይተው እንዲኖሩ ይፈቀዳልን?
1 ቆሮ. 7:10–16:- “ሚስትም ከባልዋ አትለያይ፣ ብትለያይ ግን ሳታገባ ትኑር ወይም ከባልዋ ትታረቅ፣
ባልም ሚስቱን አይተዋት ብዬ የተጋቡትን አዛቸዋለሁ፣ እኔ ግን አላዝም ጌታ እንጂ። ሌሎችንም እኔ እላለሁ፣ ጌታም አይደለም፤ [ቁጥር
40 እንደሚያሳየው ቅዱስ ጳውሎስ ይህን የጻፈው በመንፈስ ቅዱስ ተመርቶ ነበር።] ከወንድሞች ወገን ያላመነች ሚስት ያለችው ቢኖር
እርስዋም ከእርሱ ጋር ልትቀመጥ ብትስማማ፣ አይተዋት፤ ያላመነ ባል ያላት ሚስትም ብትኖር ይህ ከእርስዋ ጋር ሊቀመጥ ቢስማማ፣ አትተወው።
ያላመነ ባል በሚስቱ ተቀድሶአልና፣ ያላመነችም ሚስት በባልዋ ተቀድሳለች፤ አለዚያ ልጆቻችሁ ርኩሳን ናቸው፤ አሁን ግን የተቀደሱ
ናቸው። የማያምን ግን ቢለይ ይለይ፤ ወንድም ወይም እኅት እንዲህ በሚመስል ነገር አይገዙም፤ እግዚአብሔር ግን በሰላም ጠርቶናል።
አንቺ ሴት፣ ባልሽን ታድኚ እንደ ሆንሽ ምን ታውቂአለሽ? ወይስ፣ አንተ ሰው ሚስትህን ታድን እንደ ሆንህ ምን ታውቃለህ?” (አማኙ
ወገን ችግሮችን በመታገሥ ጋብቻው ጸንቶ እንዲኖር ከልብ መጣር ያለበት ለምንድን ነው? ይህን የሚያደርገው የጋብቻን መለኮታዊ አመጣጥ
በማክበርና የማያምነው ወገን ከጊዜ በኋላ የእውነተኛው የእግዚአብሄር አገልጋይ ለመሆን ይችል ይሆናል በሚል ተስፋ ነው)።
ሌላ ለማግባት ሲባል ስለሚፈጸም
ፍቺ መጽሐፍ ቅዱስ ያለው አመለካከት ምንድን ነው?
ሚል. 2:15, 16:- “መንፈሳችሁን ጠብቁ፣ ማንም የልጅነት ሚስቱን አያታልል። መፋታትን እጠላለሁ፣
ይላል የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር።” ማቴ. 19:8, 9:-
“እርሱም [ኢየሱስ]:- ሙሴስ ስለ ልባችሁ ጥንካሬ ሚስቶቻችሁን ትፈቱ ዘንድ ፈቀደላችሁ ከጥንት ግን እንዲህ አልነበረም። እኔ ግን
እላችኋለሁ፣ ያለ ዝሙት ምክንያት [በጋብቻ ላይ የሚፈጸም የሩካቤ ሥጋ ውስልትና] ሚስቱን ፈትቶ ሌላዪቱን የሚያገባ ሁሉ ያመነዝራል
አላቸው።” (ንጹሕ የሆነው የትዳር ጓደኛ “ዝሙት” የፈጸመውን ወገን ለመፍታት ተፈቅዶለታል፣ ሆኖም ግን የግድ መፍታት አለበት ማለት
አይደለም)።
ሮሜ 7:2, 3:- “ያገባች ሴት ባልዋ በሕይወት ሲኖር ከእርሱ ጋር በሕግ ታስራለችና፤ ባልዋ ቢሞት
ግን ስለ ባል ከሆነው ሕግ ተፈትታለች። ስለዚህ ባልዋ በሕይወት ሳለ ለሌላ ወንድ ብትሆን አመንዝራ ትባላለች፤ ባልዋ ቢሞት ግን
ከሕጉ አርነት ወጥታለችና ለሌላ ወንድ ብትሆን አመንዝራ አይደለችም።”
1 ቆሮ. 6:9–11:- “አትሳቱ፤ ሴሰኞች ቢሆኑ ወይም ጣዖትን የሚያመልኩ ወይም አመንዝሮች ወይም
ቀላጮች ወይም ከወንድ ጋር ዝሙት የሚሠሩ [ወንዶች] . . . የእግዚአብሔርን መንግሥት አይወርሱም። ከእናንተም አንዳንዶቹ እንደ
እነዚህ ነበራችሁ፤ ነገር ግን በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም በአምላካችንም መንፈስ ታጥባችኋል፣ ተቀድሳችኋል፣ ጸድቃችኋል።” (ይህ
መግለጫ የጉዳዩን ክብደት ያጎላል። ንስሐ የማይገቡ አመንዝሮች በእግዚአብሄር መንግሥት ውስጥ ቦታ የላቸውም። ይሁን እንጂ ቀደም
ብለው ምንዝር የፈጸሙ፣ ምናልባትም ተገቢ ባልሆነ መንገድ ሁለተኛ ጋብቻ የፈጸሙ ሰዎች ከልብ ንስሐ ከገቡና ኃጢአት በሚያስተሠርየው
የኢየሱስ መሥዋዕታዊ ዋጋ ካመኑ የእግዚአብሄርን ይቅርታ ሊያገኙና በእግዚአብሄር ዘንድ ንጹሕ አቋም ሊይዙ ይችላሉ)።
በድሮ ጊዜ በወንድምና በእህት
መካከል ይደረግ የነበረውን ጋብቻ አምላክ ለምን ፈቀደ?
ቃየን ከእህቶቹ አንዷን (ዘፍ. 4:17፤ 5:4) (ወይም የወንድሙን ልጅ ሊሆን ይችላል) እንዳገባ
አብርሃም ደግሞ በግማሽ እህቱ የሆነችውን እንዳገባ (ዘፍ. 20:12) መጽሐፍ ቅዱስ ያሳያል። ነገር ግን ከጊዜ በኋላ በሙሴ በኩል
በተሰጠው ሕግ ላይ ይህን የመሰለው ጋብቻ በግልጽ ተጠቅሶ ተከልክሏል። (ዘሌ. 18:9, 11) ዛሬም በክርስቲያኖች መካከል አይፈቀድም።
በቅርብ ዘመዳሞች መካከል ከሚደረግ ጋብቻ በሚወለዱ ልጆች ላይ በዘር የሚተላለፉ ጐጂ ነገሮች የመድረሳቸው አጋጣሚ በጣም ከፍተኛ
ነው።
የሰው ልጅ ታሪክ በጀመረበት ጊዜ ላይ የወንድምና እህት ጋብቻ ስህተት ያልነበረው ለምን ነበር? እግዚአብሄር
አዳምንና ሔዋንን ፍጹም አድርጎ ከፈጠራቸው በኋላ የሰው ዘር በሙሉ ከእነርሱ እንዲገኝ አስቦ ነበር። (ዘፍ. 1:28፤ 3:20)
በዚህ መሠረት በመጀመሪያዎቹ ጥቂት ትውልዶች ውስጥ የቅርብ ዘመዳሞች ጋብቻ እንደሚኖር ግልጽ ነው። ሰብዓዊው ዘር አዳምና ሔዋን
ለነበራቸው ፍጽምና ቅርብ ስለነበር ኃጢአት ከመጣም በኋላ ቢሆን በመጀመሪያዎቹ ትውልዶች ላይ ይህ ዓይነቱ ጋብቻ አካለ ጐደሎነት
ለማድረስ የነበረው አደጋ እምብዛም አልነበረም። ይህም በዚያን ጊዜ ይኖሩ በነበሩት ሰዎች የዕድሜ ርዝማኔ ተረጋግጧል። (ዘፍጥረት
5:3–8፤ 25:7ን ተመልከት።) አዳም ኃጢአት ከሠራ ከ2,500 ዓመታት በኋላ ግን እግዚአብሄር የሥጋ ዘመዳሞች እንዳይጋቡ
ከለከለ። ይህም በሥጋ ዘመዳሞች መካከል የሚደረገው ጋብቻ በሚወለዱት ልጆች ላይ የሚያስከትለውን አካለ ጐደሎነት ለመከልከል ከማገልገሉም
በላይ የእግዚአብሄር አገልጋዮች የፆታ ሥነ ምግባር ንጽሕና በዚያን ጊዜ አስነዋሪ ድርጊቶችን ይፈጽሙ ከነበሩት በዙሪያቸው ከነበሩት
አሕዛብ የተሻለ አቋም እንዲኖራቸው አስችሏል።ዘሌዋውያን 18:2–18ን ተመልከት።
ትዳርን ለማሻሻል ምን ነገሮች
ሊረዱ ይችላሉ?
(1) አዘውትሮ የእግዚአብሄርን ቃል አንድ ላይ ማጥናትና ችግሮችን ለመፍታት እንዲረዳቸው ወደ እግዚአብሄር
መጸለይ።2 ጢሞ. 3:16, 17፤ ምሳሌ 3:5, 6፤ ፊልጵ. 4:6, 7
(2) የራስነትን ሥርዓት በደስታ መቀበል። ይህ በባል ላይ ከባድ ኃላፊነት ይጭናል። (1 ቆሮ. 11:3፤
ኤፌ. 5:25–33፤ ቆላ. 3:19) ሚስትም ከልብ ጥረት እንድታደርግ ይጠይቅባታል። ኤፌ. 5:22–24, 33፤ ቆላ. 3:18፤
1 ጴጥ. 3:1–6
(3) የፆታ ፍላጎትን ከትዳር ጓደኛ ጋር ብቻ ማርካት (ምሳሌ 5:15–21፤ ዕብ. 13:4) ለትዳር
ጓደኛ ችግር ከልብ ማሰብ መጥፎ ለመሥራት ከሚገፋፋ ፈተና ይጠብቃል።1 ቆሮ. 7:2–5
(4) በደግነትና በአሳቢነት እርስ በርስ መነጋገር፤ ከንዴትና ከጩኸት መራቅ፤ ንዝነዛንና የነቀፌታ
ንግግርን ማስወገድ።ኤፌ. 4:31, 32፤ ምሳሌ 15:1፤ 20:3፤ 21:9፤ 31:26, 28
(5) ታታሪ መሆን፤ ባልና ሚስት ለቤተሰቡ የሚያስፈልገውን መኖሪያና ልብስ እንዲሁም ለጤና የሚስማማ
ምግብ በማቅረብ በኩል እምነት የሚጣልባቸው ሆነው መገኘት። ቲቶ 2:4, 5፤ ምሳሌ 31:10–31
(6) ሌላው ወገን መሥራት የሚገባውን ሁሉ እንደሠራ ቢሰማችሁም ባይሰማችሁም የመጽሐፍ ቅዱስን ምክር
በትሕትና በተግባር ማዋል። ሮሜ 14:12፤ 1 ጴጥ. 3:1, 2
(7) ትኩረት ሰጥቶ የግል መንፈሳዊ ባሕርያትን ማዳበር።—1 ጴጥ. 3:3–6፤ ቆላ. 3:12–14፤
ገላ. 5:22, 23
(8) ልጆች ካሉ የሚያስፈልጋቸውን ፍቅር፣ ትምህርትና ማሰልጠኛ መስጠት።—ቲቶ 2:4፤ ኤፌ. 6:4፤
ምሳሌ 13:24፤ 29:15
ትዳራችሁ “በሦስት የተገመደ” ሆኖ እንዲቀጥል ጥረት ማድረግ፤‘በሦስት
የተገመደ ገመድ ቶሎ አይበጠስም።’መክ. 4:12
የመጀመሪያዎቹን ሰዎች በጋብቻ ያጣመራቸው ማን ነው?
እግዚአብሄር፣ ተክሎችንና እንስሳትን ከፈጠረ በኋላ የመጀመሪያ ሰው የሆነውን አዳምን ወደ ሕልውና አመጣው። ከዚያም
አዳም ኃይለኛ እንቅልፍ እንዲወስደው በማድረግ ከጎድን አጥንቶቹ አንዱን ወስዶ ፍጹም የሆነች ረዳት አበጀለት። አዳም፣እግዚአብሄር
የሰጠውን ረዳት ሲመለከት “እነሆ፤ ይህች ዐጥንት ከዐጥንቴ፣ ሥጋም ከሥጋዬ ናት” በማለት ተናገረ። (ዘፍ. 1:27፤ 2:18,
21-23) አምላክ የመጀመሪያዋን ሴት ከፈጠረ በኋላ በሥራው እንደተደሰተ አሳይቷል፤ እግዚአብሄር፣ ሔዋን ለአዳም ተስማሚ ረዳት
እንደሆነች ስላመነ እነዚህን ሰዎች በጋብቻ ካጣመራቸው በኋላ ባረካቸው። ዘፍ. 1:28፤ 2:24
አዳምና ሔዋን ግንኙነታቸው እንዲበላሽ ሰይጣን ምን አድርጓል?
የሚያሳዝነው ግን የእግዚአብሄር ዝግጅት የሆነው ጋብቻ ብዙም ሳይቆይ
ጥቃት ተሰነዘረበት። ይህ የሆነው እንዴት ነው? ከጊዜ በኋላ ሰይጣን ተብሎ የተጠራው አንድ ክፉ መንፈሳዊ ፍጡር ሔዋንን በማታለል
እግዚአብሄር እንዳይበሉ ከከለከላቸው ዛፍ እንድትበላ አደረጋት። አዳምም
ከሚስቱ ጋር በመተባበር የእግዚአብሄርን ትእዛዝ ጣሰ፤ እነዚህ ባልና ሚስት እንዲህ በማድረጋቸው ትክክለኛ በሆነው የእግዚአብሄር
አገዛዝና አመራር ላይ ዓምፀዋል። (ዘፍ. 3:1-7) እግዚአብሄር እነዚህን ባልና ሚስት ስለፈጸሙት ጥፋት ሲጠይቃቸው የሰጡት መልስ
ግንኙነታቸው እንደተበላሸ በግልጽ የሚያሳይ ነበር። አዳም “ይህች ከእኔ ጋር እንድትኖር የሰጠኸኝ ሴት፣ እርሷ ከዛፉ ፍሬ ሰጠችኝና
በላሁ” በማለት ጥፋቱ የሚስቱ እንደሆነ ገለጸ።ዘፍ. 3:11-13
አንዳንድ አይሁዳውያን ምን የተሳሳተ አመለካከት አዳብረው ነበር?
ከዚያ በኋላ ባሉት በርካታ መቶ ዘመናትም ሰይጣን በትዳር ጓደኛሞች
መካከል አለመግባባት እንዲፈጠር ለማድረግ የተለያዩ መሠሪ ዘዴዎችን ሲጠቀም ቆይቷል። ለምሳሌ ያህል፣ የሃይማኖት መሪዎች ጋብቻን
በተመለከተ ከቅዱሳን መጻሕፍት ጋር የሚጋጭ ትምህርት እንዲያስፋፉ ያደረገባቸው ወቅቶች አሉ። አንዳንድ የአይሁድ ሃይማኖታዊ መሪዎች፣
ባሎች ጥቃቅን በሆኑ ስህተቶች እንኳ ሚስቶቻቸውን መፍታት እንደሚችሉ በመግለጽ የእግዚአብሄርን መሥፈርቶች አቃልለዋል። ለምሳሌ አንድ
ባል፣ ሚስቱ ምግብ ላይ ጨው በማብዛቷ በጥቃቅን ምክንያቶች ብቻ ሊፈታት
እንደሚችል ይገልጹ ነበር። ይሁን እንጂ ኢየሱስ “በትዳሯ ላይ ዝሙት ፈጽማ እስካልተገኘች ድረስ ሚስቱን ፈትቶ ሌላ ሴት የሚያገባ
ሁሉ አመንዝራ ይሆናል” በማለት ተናግሯል። ማቴ. 19:9
በዛሬው ጊዜ የጋብቻ ዝግጅት ጥቃት እየተሰነዘረበት ያለው እንዴት ነው?
ሰይጣን
በዛሬው ጊዜም ቢሆን የጋብቻን ጥምረት ለማፍረስ የማይፈነቅለው ድንጋይ የለም። ተመሳሳይ ጾታ ባላቸው ሰዎች መካከል የሚፈጸመው ጥምረት፣
ያልተጋቡ ጥንዶች አብረው መኖራቸው እንዲሁም ትዳር በቀላሉ የሚፈርስ መሆኑ ሰይጣን የሚያደርገው ጥረት እንደተሳካለት የሚጠቁም ነው።
(ዕብራውያን 13:4ን አንብብ።) እኛስ ክርስቲያኖች እንደመሆናችን መጠን ትዳርን በተመለከተ በዓለም ላይ ተስፋፍቶ
የሚገኘው የተዛባ አመለካከት ተጽዕኖ እንዳያሳድርብን ምን ማድረግ ይኖርብናል? ትዳር ደስታ የሰፈነበትና የሰመረ እንዲሆን የሚረዱ
አንዳንድ ነጥቦችን እስቲ እንመልከት።
በትዳራችሁ ውስጥ እግዚአብሄር ቦታ እንዲኖረው አድርጉ
“በሦስት የተገመደ ገመድ” የሚለው አገላለጽ ከትዳር ጋር በተያያዘ ምን ትርጉም አለው?
ትዳር
የሰመረ እንዲሆን ከተፈለገ ባልና ሚስት በጋብቻቸው ውስጥ እግዚአብሄር ቦታ እንዲኖረው ሊያደርጉ ይገባል። የእግዚአብሄር ቃል ‘በሦስት
የተገመደ ገመድ ቶሎ አይበጠስም’ ይላል። (መክ. 4:12) “በሦስት የተገመደ ገመድ” የሚለው አገላለጽ ምሳሌያዊ ነው። ይህን አገላለጽ
ወደ ትዳር ስናመጣው በሁለት ክሮች የተወከሉት ባልና ሚስት፣ መሃል ላይ በሚገኝ ሌላ ክር ማለትም በእግዚአብሄር አምላክ አማካኝነት አንድ ላይ እንደተጣመሩ ወይም እንደተገመዱ ያሳያል። ባልና
ሚስት ከእግዚአብሄር ጋር መጣመራቸው ችግሮችን ለመቋቋም የሚያስችል መንፈሳዊ ጥንካሬ የሚሰጣቸው ከመሆኑም ሌላ ትዳራቸው ደስታ የሰፈነበት
እንዲሆን ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረክታል።
ክርስቲያኖች እግዚአብሄር በትዳራቸው ውስጥ ቦታ እንዲኖረው ማድረግ
የሚችሉት እንዴት ነው? አንዲት እህት፣ ከባለቤታቸው ጋር በተያያዘ
የትኞቹን ነገሮች ከፍ አድርገው እንደሚመለከቷቸው ገልጸዋል?
ታዲያ ባልና ሚስት ትዳራቸው በሦስት እንደተገመደ ገመድ እንዲሆን
ማድረግ የሚችሉት እንዴት ነው? መዝሙራዊው ዳዊት “አምላኬ ሆይ፤ ፈቃድህን ላደርግ እሻለሁ፤ ሕግህም በልቤ ውስጥ አለ” በማለት
ዘምሯል። (መዝ. 40:8) እኛም ለእግዚአብሄር ያለን ፍቅር በሙሉ ልባችን እንድናገለግለው ያነሳሳናል። ባልና ሚስት ከእግዚአብሄር
ጋር ጠንካራ የግል ጥምረት ሊመሠርቱ እንዲሁም የእሱን ፈቃድ ማድረግ ሊያስደስታቸው ይገባል። ከዚህም በተጨማሪ ባልም ሆነ ሚስት
የትዳር ጓደኛቸው ለእግዚአብሄር ያለው ፍቅር እንዲያድግ ለማድረግ መጣር ይኖርባቸዋል።ምሳሌ 27:17
የእግዚአብሄር ሕግ በውስጣችን ካለ እንደ እምነት፣ ተስፋና ፍቅር
የመሳሰሉ ባሕርያትን የምናዳብር ሲሆን እነዚህ ባሕርያት ደግሞ የጋብቻችንን ጥምረት ያጠናክሩታል። (1 ቆሮ. 13:13) በትዳር
ውስጥ 50 ዓመታት ያሳለፉ አንዲት እህት እንዲህ ብለዋል:- “ባለቤቴ የሚሰጠኝን መንፈሳዊ መመሪያና ምክር እንዲሁም ለእግዚአብሄር
ያለውን ፍቅር ከምንም ነገር በላይ ከፍ አድርጌ እመለከታቸዋለሁ፤ ባለቤቴ ከእኔ ይበልጥ እግዚአብሄርን ይወዳል።” እናንት ባሎች፣
ሚስቶቻችሁ ስለ እናንተ እንዲህ ብለው እንዲናገሩ የሚገፋፋ ባሕርይ አላችሁ?
በትዳር ውስጥ “መልካም ውጤት” ለማግኘት ምን ማድረግ ያስፈልጋል?
በትዳራችሁ ውስጥ ለመንፈሳዊ ጉዳዮችና ለክርስቲያናዊ እንቅስቃሴዎች
ቅድሚያ ትሰጣላችሁ? የትዳር ጓደኞቻችሁን እግዚአብሄርን አብረዋችሁ እንደሚያገለግሉ አጋሮቻችሁ አድርጋችሁ ትመለከቷቸዋላችሁ? (ዘፍ.
2:24) ጠቢቡ ንጉሥ ሰሎሞን “ለሥራቸው መልካም ውጤት ስለሚያገኙ፣ ከአንድ፣ ሁለት መሆን ይሻላል” በማለት ጽፏል። (መክ.
4:9) በእርግጥም ባልና ሚስት “መልካም ውጤት” እንዲያገኙ ማለትም ፍቅር የሰፈነበትና ዘላቂ የሆነ እንዲሁም ይሖዋ የባረከው ትዳር
እንዲኖራቸው ከፍተኛ ጥረት ማድረግ አለባቸው።
ባሎች ምን ኃላፊነት አለባቸው? በቈላስይስ 3:19 መሠረት አንድ ባል ሚስቱን እንዴት ሊይዛት ይገባል?
ባልና ሚስት ከእግዚአብሄር መሥፈርቶች ጋር ተስማምተው ለመኖር የሚያደርጉት
ጥረት በጋብቻቸው ውስጥ ለእግዚአብሄር ቦታ እንደሰጡት ወይም እንዳልሰጡት ይጠቁማል። ለቤተሰቡ የሚያስፈልገውን መንፈሳዊና ቁሳዊ
ነገር የማሟላት ኃላፊነት በዋነኝነት የተሰጠው ለባሎች ነው። (1 ጢሞ. 5:8) ከዚህም በላይ ባሎች ስለ ሚስቶቻቸው ስሜት እንዲያስቡ
ማበረታቻ ተሰጥቷቸዋል። ቈላስይስ 3:19 “ባሎች ሆይ፤ ሚስቶቻችሁን ውደዱ፤ መራራም አትሁኑባቸው” ይላል። አንድ የመጽሐፍ ቅዱስ
ምሑር ‘መራራ መሆን’ የሚለው ሐሳብ “አጥንት የሚሰብር ነገር መናገርንና መማታትን እንዲሁም ለሚስቶች ፍቅር አለማሳየትን፣ የሚያስፈልጋቸውን
አለማቅረብን ብሎም እንክብካቤ፣ ጥበቃና እገዛ አለማድረግን” እንደሚጨምር ገልጸዋል። በክርስቲያኖች ቤተሰብ ውስጥ እንዲህ ያሉ ባሕርያትን
ማሳየት ተገቢ እንዳልሆነ ምንም ጥርጥር የለውም። አንድ ባል የራስነት ሥልጣኑን ፍቅር በሚንጸባረቅበት መንገድ የሚጠቀምበት ከሆነ
ሚስቱ ለእሱ መገዛት ቀላል ይሆንላታል።
ክርስቲያን ሚስቶች ለራስነት ሥልጣን ምን አመለካከት ሊኖራቸው ይገባል?
በትዳራቸው ውስጥ እግዚአብሄር ቦታ እንዲኖረው ለማድረግ የሚፈልጉ
ክርስቲያን ሚስቶችም እግዚአብሄር ያወጣቸውን መሥፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል። ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ እንዲህ በማለት ጽፏል:-
‘ሚስቶች ሆይ፤ ለጌታ እንደምትገዙ ለባሎቻችሁም ተገዙ። ክርስቶስ፣ የቤተ ክርስቲያን ራስ እንደ ሆነ ሁሉ፣ ባልም የሚስቱ ራስ ነውና።’
(ኤፌ. 5:22, 23) ሰይጣን፣ ከእግዚአብሄር ርቆ በራስ መመራት ዘላቂ ደስታ እንደሚያስገኝ በመግለጽ ሔዋንን አታልሏታል። በዛሬው
ጊዜ በብዙ ትዳሮች ውስጥ በራስ የመመራት መንፈስ ይታያል። እግዚአብሄር ለትዳር ያለው ዓይነት አመለካከት ያላት ሴት ግን አፍቃሪ
ለሆነው ባሏ መገዛት የምትጠላው ነገር አይሆንም። እንዲህ ዓይነት አመለካከት ያላት ሴት እግዚአብሄር፣ ሔዋንን ለባሏ “ረዳት” ወይም
ማሟያ አድርጎ እንደሾማትና ይህንን ድርሻም የተከበረ አድርጎ እንደሚመለከተው ታስታውሳለች። (ዘፍ. 2:18) እግዚአብሄር የሰጣትን
ይህንን ድርሻ በፈቃደኝነት የምትቀበል ክርስቲያን ሚስት ለባሏ እውነተኛ “ዘውድ” ናት።ምሳሌ 12:4
አንድ ወንድም ትዳራቸው የሰመረ እንዲሆን የረዳቸውን ነገር ሲገልጹ ምን ብለዋል?
እግዚአብሄር በትዳር ውስጥ ቦታ እንዲኖረው የሚረዳው ሌላው ነገር
ደግሞ ባልና ሚስት የእግዚአብሄርን ቃል አብረው ማጥናታቸው ነው። በትዳር ዓለም 55 አስደሳች ዓመታት ያሳለፉት ወንድም “ጋብቻ
የሰመረ እንዲሆን የሚረዳው በጣም አስፈላጊ ነገር መጽሐፍ ቅዱስን አንድ ላይ ማንበብና ማጥናት ነው” ብለዋል። አክለውም እንዲህ
በማለት ተናግረዋል:- “የትዳር ጓደኛሞች አብረው መሥራታቸው በተለይም መንፈሳዊ ነገሮችን በአንድነት ማከናወናቸው እርስ በርሳቸው
ይበልጥ እንዲቀራረቡ እንዲሁም ከእግዚአብሄር ጋር የቀረበ ዝምድና እንዲኖራቸው ያደርጋል።” ባልና ሚስት አንድ ላይ ሆነው መጽሐፍ
ቅዱስን ማጥናታቸው የእግዚአብሄር መሥፈርቶች ምንጊዜም ከአእምሯቸው እንዳይጠፉ፣ ጠንካራ መንፈሳዊ አቋም እንዲኖራቸው እንዲሁም ቀጣይ
የሆነ መንፈሳዊ እድገት እንዲያደርጉ ይረዳቸዋል።
ባለትዳሮች አብረው መጸለያቸው በጣም አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው? ትዳር እንዲጠናከር አስተዋጽኦ የሚያደርጉት ሌሎች መንፈሳዊ እንቅስቃሴዎች የትኞቹ
ናቸው?
ከዚህም በተጨማሪ አስደሳች ትዳር እንዲኖራቸው የሚፈልጉ ባልና ሚስት
አብረው ይጸልያሉ። አንድ ባል በትዳሩ ውስጥ የተፈጠረውን ሁኔታ በመጥቀስ በእግዚአብሄር ፊት ‘ልቡን ማፍሰሱ’ የትዳሩን ጥምረት
እንደሚያጠናክረው ምንም ጥርጥር የለውም። (መዝ. 62:8) ለምሳሌ ያህል፣ ሁሉን ቻይ የሆነው አምላክ መመሪያ እንዲሰጣችሁ ከትዳር
ጓደኛችሁ ጋር ሆናችሁ በጸሎት ከለመናችሁት በኋላ በመካከላችሁ ተፈጥሮ የነበረውን አለመግባባት መፍታት ቀላል ይሆናል። (ማቴ.
6:14, 15) ባልም ሆነ ሚስት የትዳር ጓደኛቸውን ለመርዳት እንዲሁም ‘እርስ በርስ ለመቻቻልና አንዳቸው በሌላው ላይ ቅር የተሰኙበት
ነገር ካለ ይቅር ለመባባል’ ቁርጥ ውሳኔ በማድረግ ከጸሎታቸው ጋር የሚስማማ እርምጃ መውሰዳቸው ተገቢ ነው። (ቈላ. 3:13) ወደ
እግዚአብሄር መጸለያችሁ በእሱ የምትተማመኑ መሆናችሁን እንደሚያሳይ አስታውሱ። ንጉሥ ዳዊት “የሁሉ ዐይን አንተን በተስፋ ይጠብቃል”
ብሏል። (መዝ. 145:15) ወደ እግዚአብሄር በመጸለይ እሱን በተስፋ የምንጠብቅ ከሆነ ጭንቀታችን ይቀልልናል፤ ምክንያቱም እግዚአብሄር
‘ስለ እኛ እንደሚያስብ’ እናውቃለን።1 ጴጥ. 5:7
በጉባኤ ስብሰባዎች ላይ መገኘትና አብሮ ማገልገልም በትዳር ውስጥ
እግዚአብሄር ቦታ እንዲኖረው ለማድረግ ይረዳል። ባለትዳሮች ሰይጣን
ቤተሰብን ለመከፋፈል የሚጠቀምባቸውን ‘የተንኰል ሥራዎች’ እንዴት መዋጋት እንደሚችሉ በስብሰባዎች ላይ ይማራሉ። (ኤፌ.
6:11) አዘውትረው አንድ ላይ የሚያገለግሉ ባልና ሚስት ‘በምንም ነገር ሳይናወጡ ጸንተው መቆምን’ ይማራሉ።1 ቆሮ. 15:58
ችግሮች በሚፈጠሩበት ጊዜ
በትዳር ውስጥ ውጥረት እንዲሰፍን
ሊያደርጉ የሚችሉ አንዳንድ ነገሮች ምንድን ናቸው?
ቀደም ሲል የተጠቀሱት ሐሳቦች አዲስ እንዳልሆኑ ይሰማችሁ ይሆናል፤
ያም ቢሆን እነዚህን ሐሳቦች ከትዳር ጓደኞቻችሁ ጋር ለምን በግልጽ አትወያዩባቸውም? እነዚህን ነጥቦች በትዳራችሁ ውስጥ ተግባራዊ
በማድረግ አንዳንድ ነገሮችን ማስተካከል ይኖርባችሁ እንደሆነ ለማስተዋል ሞክሩ። መጽሐፍ ቅዱስ በትዳራቸው ውስጥ እግዚአብሄር ቦታ እንዲኖረው ያደረጉ ሰዎችም እንኳ ‘ብዙ ችግር እንደሚገጥማቸው’ በግልጽ
ይናገራል። (1 ቆሮ. 7:28) የሰው ልጆች ፍጹማን አለመሆናቸውና ይህ ክፉ ዓለም የሚያሳድረው መጥፎ ተጽዕኖ እንዲሁም የዲያብሎስ
ወጥመዶች፣ ታማኝ በሆኑ የእግዚአብሄር አገልጋዮች ትዳር ውስጥም እንኳ
ውጥረት እንዲሰፍን ሊያደርጉ ይችላሉ። (2 ቆሮ. 2:11) ያም ቢሆን እግዚአብሄር እንዲህ ያለውን ውጥረት እንድቋቋም ይረዳናል። አዎን፣ እነዚህን ሁኔታዎች መቋቋም
ይቻላል። ታማኙ ኢዮብ ከብቶቹን፣ አገልጋዮቹንና ልጆቹን ቢያጣም “በዚህ ሁሉ፣ . . . አልበደለም፤ በእግዚአብሔርም ላይ ክፉ አልተናገረም።”ኢዮብ
1:13-22
ሰዎች ውጥረት ሲያጋጥማቸው ምን ሊያደርጉ ይችላሉ? የትዳር ጓደኛችሁ ተገቢ ያልሆነ ነገር ቢናገራችሁ
ምን ማድረግ የተሻለ ነው?
በሌላ በኩል ግን የኢዮብ ሚስት “አሁንም ታማኝነትህን አልተውህምን?
ይልቁን እግዚአብሔርን ርገምና ሙት!” ብላው ነበር። (ኢዮብ 2:9) በእርግጥም አሳዛኝ ሁኔታዎች ወይም ሌሎች አስቸጋሪ ነገሮች
መከሰታቸው የሚፈጥረው ጭንቀት አንድ ሰው ማመዛዘን የጎደለው እርምጃ እንዲወስድ ሊያደርገው ይችላል። ጠቢቡ ሰሎሞን “ግፍ ጠቢቡን
ያሳብደዋል” በማለት ተናግሯል። (መክ. 7:7) የትዳር ጓደኛችሁ አንድ አስቸጋሪ ሁኔታ ስላጋጠመው ወይም “ግፍ” ስለደረሰበት በንዴት
ገንፍሎ የሚጎዳ ነገር ቢናገራችሁ ለመረጋጋት ሞክሩ። እሱ በተናገረበት መንገድ ምላሽ መስጠት ከሁለት አንዳችሁ ወይም ሁለታችሁም
ሁኔታውን የሚያባብስ ነገር እንድትናገሩ ሊያደርጋችሁ ይችላል። (መዝሙር 37:8ን አንብብ።) ስለዚህ የትዳር ጓደኛችሁ በመበሳጨቱ ወይም ተስፋ
በመቁረጡ የተነሳ ‘ኀይለ ቃል’ ቢናገራችሁ ነገሩን ለማለፍ ሞክሩ።ኢዮብ 6:3
ኢየሱስ በማቴዎስ 7:1-5 ላይ የሰጠው ሐሳብ በትዳር ውስጥ የሚሠራው እንዴት ነው? (ለ)
ሚዛናዊ መሆን በትዳር ውስጥ በጣም አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው?
ባለትዳሮች አንዳቸው ከሌላው በሚጠብቁት ነገር ምክንያታዊ መሆን
ያስፈልጋቸዋል። አንድ ባል ወይም አንዲት ሚስት፣ የትዳር ጓደኛቸው ጥሩ ያልሆነ ባሕርይ እንዳለው ይመለከቱና የትዳር ጓደኛቸውን
‘መለወጥ እንደሚችሉ’ ያስቡ ይሆናል። ፍቅርና ትዕግሥት በማሳየት የትዳር ጓደኞቻችሁ ቀስ በቀስ ማሻሻያ እንዲያደርጉ ልትረዷቸው
ትችሉ ይሆናል። ያም ቢሆን ግን አንድ ነገር አትዘንጉ፤ ኢየሱስ የሌሎችን ጥቃቅን ጉድለቶች የሚለቃቅምን ሰው፣ በራሱ ዓይን ውስጥ
ያለውን “ግንድ” ሳያይ በወንድሙ ዓይን ውስጥ ያለውን “ጉድፍ” ለማውጣት ከሚሞክር ሰው ጋር አመሳስሎታል። ኢየሱስ “እንዳይፈረድባችሁ
በማንም ሰው ላይ አትፍረዱ” በማለት አሳስቦናል። (ማቴዎስ 7:1-5ን አንብብ።) ይህ ሲባል ግን ከበድ ያሉ ችግሮች በቸልታ መታለፍ
ይኖርባቸዋል ማለት አይደለም። በትዳር ውስጥ ወደ 40 የሚጠጉ ዓመታትን ያሳለፉት አንድ ስው እንዲህ ብለዋል:- “የትዳር ጓደኛሞች
አንዳቸው ለሌላው ግልጽ መሆናቸውና ትክክለኛ የሆኑ አስተያየቶችን በፈቃደኝነት መቀበላቸው የአመለካከት ለውጥ እንዲያደርጉ ያነሳሳቸው
ይሆናል።” ስለዚህ ሚዛናዊ መሆን ያስፈልጋል። የትዳር ጓደኞቻችሁ እንዲኖሯቸው የምትፈልጓቸውን ባሕርያት እያሰባችሁ ከመበሳጨት ይልቅ
አሁን ያሏቸውን መልካም ባሕርያት ማድነቅንና በእነዚህ መደሰትን ተማሩ። መክ. 9:9
ችግሮች ሲፈጠሩ እርዳታ ከየት ማግኘት እንችላለን?
በሕይወታችሁ ውስጥ የሚያጋጥሟችሁ ለውጦች ፈተና ሊሆኑባችሁ ይችላሉ።
አንድ ባልና ሚስት ልጆች መውለዳቸው ሁኔታዎች ፈታኝ እንዲሆኑባቸው ሊያደርግ ይችላል። ባል ወይም ሚስት አሊያም ልጆች በጠና ይታመሙ
ይሆናል። ወይም ደግሞ በዕድሜ የገፉ ወላጆቻችሁ ለየት ያለ እንክብካቤ ያስፈልጋቸው ይሆናል። ልጆች ሲያድጉ ከቤተሰቡ ርቀው ሊሄዱ
ይችላሉ። ከቲኦክራሲያዊ መብቶችና ኃላፊነቶች ጋር በተያያዘም ሌሎች ለውጦች ሊመጡ ይችላሉ። እነዚህ ሁሉ ለውጦች በትዳር ጓደኛሞች
መካከል ውጥረት እንዲሰፍንና ጭንቀት እንዲፈጠር ሊያደርጉ ይችላሉ።
በትዳራችሁ ውስጥ በተፈጠረው ውጥረት የተነሳ ሁኔታዎች ከአቅማችሁ
በላይ እንደሆኑ ከተሰማችሁ ምን ማድረግ ትችላላችሁ? (ምሳሌ 24:10) ተስፋ አትቁረጡ! ሰይጣን ከእግዚአብሄር አገልጋዮች አንዱ ንጹሑን አምልኮ ሲተው ከማየት የበለጠ የሚያስደስተው ነገር
የለም። ባልና ሚስት እግዚአብሄር ን ቢተዉ ደግሞ በጣም ይደሰታል። እንግዲያው ትዳራችሁ በሦስት የተገመደ ሆኖ እንዲቀጥል የተቻላችሁን
ሁሉ አድርጉ። መጽሐፍ ቅዱስ ከባድ ፈተናዎች ቢያጋጥሟቸውም በታማኝነት ስለጸኑ ሰዎች የሚናገሩ በርካታ ታሪኮችን ይዟል። ለምሳሌ
ያህል፣ በአንድ ወቅት ዳዊት ‘አምላክ ሆይ፤ ሰዎች አስጨንቀውኛል’ በማለት ልቡን ለእግዚአብሄር አፍስሷል። (መዝ. 56:1) እናንተስ “ሰዎች” እንዳስጨነቋችሁ ተሰምቷችሁ
ያውቃል? ለጭንቀታችሁ ምክንያት የሆኑት ሌሎች ሰዎችም ይሁኑ የሚቀርባችሁ ሰው፣ እናንተም እንደ ዳዊት ለመጽናት የሚያስችል ብርታት
ማግኘት እንደምትችሉ አስታውሱ። ዳዊት “እግዚአብሔርን ፈለግሁት፤ እርሱም መለሰልኝ፤ ከፍርሀቴም ሁሉ አዳነኝ” ብሏል።መዝ.
34:4
የምናገኘው በረከት
የሰይጣንን ጥቃት መቋቋም የምንችለው እንዴት ነው?
በእነዚህ የመጨረሻ ቀናት የትዳር ጓደኛሞች “እርስ በርሳችሁ ተጽናኑ፤
አንዱም ሌላውን ያንጽ” የሚለውን ምክር ሁልጊዜ ተግባራዊ ማድረግ ይኖርባቸዋል። (1 ተሰ. 5:11) ሰይጣን፣ ‘ሰዎች ለእግዚአብሄር
ታማኝ የሚሆኑት በራስ ወዳድነት ተነሳስተው ነው’ የሚል አቋም እንዳለው
አትርሱ። ሰይጣን ለእግዚአብሄር ታማኝ እንዳንሆን ለማድረግ ሲል ትዳርን
ማፍረስን ጨምሮ ማንኛውንም ዘዴ ይጠቀማል። የሰይጣንን ጥቃት ለመቋቋም እንድንችል በእግዚአብሄር ሙሉ በሙሉ መታመን አለብን። (ምሳሌ 3:5, 6) ቅዱስ ጳውሎስ “ኀይልን በሚሰጠኝ
በእርሱ ሁሉን ማድረግ እችላለሁ” በማለት ጽፏል።ፊልጵ. 4:13
በትዳር ውስጥ እግዚአብሄር ቦታ እንዲኖረው ማድረግ ምን በረከት ያስገኛል?
በትዳር ውስጥ እግዚአብሄር ቦታ እንዲኖረው ማድረግ ብዙ በረከቶችን ያስገኛል። ሃምሳ አንድ ዓመታት በጋብቻ
ያሳለፉት አንድ ስው ባለቤታቸው ይህ እውነት እንደሆነ ይሰማቸዋል። እኚህ ወንድም እንዲህ ብለዋል:- “ባለቤቴን ስለሰጠኝ እንዲሁም በመካከላችን ስላለው አስደሳች
ወዳጅነት እግዚአብሄር ን ሁልጊዜ አመሰግነዋለሁ። ጥሩ አጋር ሆናልኛለች።” እነዚህ ባልና ሚስት ትዳራቸው ጠንካራ ሆኖ እንዲቀጥል
ማድረግ የቻሉት እንዴት ነው? “አንዳችን ለሌላው ደግነት፣ ትዕግሥትና ፍቅር ለማሳየት ምንጊዜም ጥረት እናደርጋለን” ብለዋል። ማንኛችንም
ብንሆን በዚህ ሥርዓት ውስጥ እስካለን ድረስ እነዚህን ባሕርያት ሙሉ በሙሉ ማንጸባረቅ አንችልም። ያም ቢሆን የመጽሐፍ ቅዱስን መሠረታዊ
ሥርዓቶች በተግባር ለማዋል እንዲሁም በትዳራችን ውስጥ እግዚአብሄር ቦታ እንዲኖረው ለማድረግ ከፍተኛ ጥረት ልናደርግ ይገባል። እንዲህ ካደረግን
ትዳራችን ‘በሦስት እንደተገመደ ገመድ ስለሆነ ቶሎ አይበጠስም።’መክ.
4:12
ክፍል 2
ክፍል 2
ጋብቻ እና ጤና
ጋብቻ እና ጤና በጣም የተዛመዱ ናቸው። ያገቡ ሰዎች እንደ ካንሰር፣ የልብ ድካምና ቀዶ ጥገናን የመሳሰሉ የተለያዩ
የጤና አደጋዎች ላይ የበሽታ መጎሳቆል እና ሞት ይጋጥማቸዋል። በእነዚህ ተጽእኖዎች ውስጥ በሴቶች እና በወንዶች አንጻራዊ ሁኔታ በከፊል
ሊከሰት የሚችሉት የፆታ ልዩነቶች አሉ።
ስለ ጋብቻ እና ጤና ብዙ ምርምር ላይ በተቃራኒ ጾታ ፍላጎት ላይ ያተኮሩ ሲሆን፤ ተመሳሳይ ፆታ ባላቸው
ጋብቻ ላይ የጤንነት ተጽእኖዎችን ለመግለፅ ተጨማሪ ሥራ ያስፈልጋል። ባለትዳር መሆናቸውና የጋብቻ ጥራቱ ከተለያዩ
የጤና መስኮች ጋር የተያያዙ ናቸው። ጥናቶች በእነዚህ አገናኞች ውስጥ የተካተቱትን የማህበራዊ ግንዛቤ፣ ስሜታዊ፣
ባህሪያዊ እና ባዮሎጂ ሂደቶችን መርምሯል።
ከጋብቻ ባሻገር ማኅበራዊ ግንኙነቶች በሰፊው በጤና ላይ ከፍተኛ ተፅእኖ አላቸው። የተለያዩ ጥናቶች ሜታ-ትንታኔዎች ጠንካራ ማህበራዊ ግንኙነቶች ያላቸው ሰዎች የሁሉምንም ምክንያቶች ሞት
የመቀነስ አጋጣሚያቸው 50% እንደሆነ ታውቋል። በተቃራኒው ብቸኝነት ከካንሰር በሽታ ጋር ተያይዞ የሚከሰተውን እና ሁሉንም
ምክንያቱን ለሞት ያጋልጣል። በቀጥታ ከጓደኞቻቸው ወይም ከሥራ ባልደረቦች ጋር ግንኙነት ከሌላቸው ጋር
ሲነፃፀር የጋብቻን ጤና ተጽእኖ በቀጥታ ያዛምዳል፤ ይሁን እንጂ ጋብቻ ከሌሎቹ ግንኙነቶች ይልቅ፣ ከፍተኛ ጠቀሜታ ሊያሳዩ የሚችሉ
በርካታ ምክንያቶች አሉት፤ ባለትዳሮች እንደ መብላት፣ መዝናኛ፣ የቤት አያያዝ፣ የልጅ እንክብካቤ እና እንቅልፍ የመሳሰሉ
የተለያዩ ሰፊ እንቅስቃሴዎች ሲያሳልፉ ጥንዶች አብረዋቸው ጊዜ አሳልፈዋል። ባለትዳሮችም እንደ የጋራ ፋይናንስ፣ ወይም የቤት ባለቤትነት የመሳሰሉ ሀብቶችን እና ኢንቨስትመንቶችን
ይጋራሉ፤ ሌላ ግንኙነት ዘመድ፣ ጋብቻ እየጨመረ ሊፈቷቸው የበለጠ ከፍተኛ ድጋፍ ምንጭ
ሆኖ ያገለግላል።
ተዋደው ደግሞ በጋብቻ የተሳሰሩ፣ ግን ያላገቡ ናቸው፤ በጋብቻ ውስጥ ነጠላ ሆነው ለሚያገኟቸው ሰዎች ጤናማ
የሆነ የመካከለኛ ቦታን ሊወክል ይችላል፤ ይሁን እንጂ ሰዎች በተለያዩ ምክንያቶች ሳይጋቡ አብረው ይኖራሉ። የጋብቻ መኖር ለትዳሩ መቅረብ ይሆናል። በዘር፣ በጎሳ፣ እና ማኅበራዊ-ኢኮኖሚያዊ ሁኔታ ውስጥ የምርጫ
ሁኔታዎች ያላገቡ ሳይጋቡ የተወሰኑ ቡድኖች ከሚያጋልጡ፤ እና እነዚህ ነገሮች ደግሞ ጋብቻ እና ሳይጋቡ ጤንነት ጥቅም
ላይ ተፅዕኖ ያደጋሉ።
የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻ
ይህ ጋብቻ በብዙ የማይደገፍ ቢሆንም ጋብቻው
ግን በተለይም በስሜኑ አሜሪካ እየተከናወነ ነው፤ ስለሆነም አጥኚዎች ይህንን ጋብቻ ደግፈውት ሳይሆን ጥናትቸው አጥንተው
ህብረተስብን ማስተማር ስላለባቸው አቅርበውታል እንዲህም ብለው፦ አብዛኛዎቹ ስለ ጋብቻና ጤና ጥናት የተቃራኒ ጾታዎች ጥንዶች
አጥንተዋል፤ ተመሳሳይ ፆታ ያላቸው እና ተቃራኒ ፆታ ያላቸው ጥንዶች ተመሳሳይነት አላቸው። ይኸኛው ጋብቻ ለጤንነት መግዋደል በተላያየ መልኩ ያጋልጣል ዝርዝር ውስጥ አልገባም።
በአንድ አይነት ጾታና በተቃራኒ ጾታ መካከል የተደርገው ጋብቾች ላይ የተደረጉት ጥናቶች የሚካፈሉት አንድ አይነት ነገሮች አሉ። ሁለቱም ጋብቻዎች የሚጀመሩት በጀመሩት ግዋደኝነት በከፍተኛ ደረጃ ተደስተው ነው ይሁን እንጂ ሁለቱም ጋብቻዎች ወደማሽቆልቆል ይደርሳሉ ማለትም ሁለቱም ወደማሽቆላቸው የሚያደርሳቸው ጉዳዮች አንድ አይነት ናቸው ይላሉ አጥኚዎቹ። ይሁን እንጂ ተመሳሳይ ፆታ ያላቸው ወንድማማቾች ግጭቶችን በተሻለ ሁኔታ ይፈታሉ፤ እና ከወላጆቻቸው ተቃራኒ ጾታ ጋር ሲነጻጸር የቤተሰብን ጉልበት በብዛት ያሰራጫሉ። የጋብቻ በበርካታ ሀገራት ውስጥ እና በብዙ የዩናይትድ ስቴትስ (ጋብቻ እና ጤና ላይ ብዙ ጥናቶች በተካሄዱበት) ሕገ-ወጥ ጋብቻ ሕገ-ወጥ ነው። በእነዚህ ክልሎች ጋብቻን ወይም ተያያዥ ህጋዊ ማዕቀቦችን ለጋብቻ መፍረስ አለመቻልን በተመለከተ ተመሳሳይ ፆታ ያላቸው ባልና ሚስቶች ጥበቃ አይደረግላቸውም። በተጨማሪም፤ ተመሳሳይ ፆታ ያላቸው ባልና ሚስቶች በጾታዊ ግንዛቤዎቻቸው ላይ የአዕምሮ ጤንነት እና የግንኙነት ችግርን የመጋለጥ አጋጣሚያቸው ከፍ ያለ ነው።
በአንድ አይነት ጾታና በተቃራኒ ጾታ መካከል የተደርገው ጋብቾች ላይ የተደረጉት ጥናቶች የሚካፈሉት አንድ አይነት ነገሮች አሉ። ሁለቱም ጋብቻዎች የሚጀመሩት በጀመሩት ግዋደኝነት በከፍተኛ ደረጃ ተደስተው ነው ይሁን እንጂ ሁለቱም ጋብቻዎች ወደማሽቆልቆል ይደርሳሉ ማለትም ሁለቱም ወደማሽቆላቸው የሚያደርሳቸው ጉዳዮች አንድ አይነት ናቸው ይላሉ አጥኚዎቹ። ይሁን እንጂ ተመሳሳይ ፆታ ያላቸው ወንድማማቾች ግጭቶችን በተሻለ ሁኔታ ይፈታሉ፤ እና ከወላጆቻቸው ተቃራኒ ጾታ ጋር ሲነጻጸር የቤተሰብን ጉልበት በብዛት ያሰራጫሉ። የጋብቻ በበርካታ ሀገራት ውስጥ እና በብዙ የዩናይትድ ስቴትስ (ጋብቻ እና ጤና ላይ ብዙ ጥናቶች በተካሄዱበት) ሕገ-ወጥ ጋብቻ ሕገ-ወጥ ነው። በእነዚህ ክልሎች ጋብቻን ወይም ተያያዥ ህጋዊ ማዕቀቦችን ለጋብቻ መፍረስ አለመቻልን በተመለከተ ተመሳሳይ ፆታ ያላቸው ባልና ሚስቶች ጥበቃ አይደረግላቸውም። በተጨማሪም፤ ተመሳሳይ ፆታ ያላቸው ባልና ሚስቶች በጾታዊ ግንዛቤዎቻቸው ላይ የአዕምሮ ጤንነት እና የግንኙነት ችግርን የመጋለጥ አጋጣሚያቸው ከፍ ያለ ነው።
ፆታ ልዩነቶች
ጋብቻ በጤና ላይ የሚያስከትለው ተፅዕኖ ከሴቶች ይልቅ ለወንዶች ጠንካራ ነው። የጋብቻ ሁኔታ - ማግባት ቀላል እውነታ ከሴቶች ይልቅ ለወንዶች ተጨማሪ የጤና ጠቀሜታ ይሰጣል። የሴቶች ጤና የጋብቻ ግጭት ወይም እርካታ ከሌለ በሴቶች ላይ በከፍተኛ ሁኔታ ተፅዕኖ ያደርግባቸዋል።
ለምሳሌ ባልተደሰቱ ያገቡ ሴቶች ከአንዲት ነጠላ ጓደኞቻቸው ጋር ጤናማ ካልሆኑ፤ የላቦራቶሪ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት ሴቶች ከጋብቻ ግጭቶች አንጻር ሴቶች ከወንዶች ይበልጥ የተጠናከረ
የስነ-መለኮታዊ ምላሾች አላቸው።
እነዚህ የሥርዓተ ፆታ ልዩነቶች በወንዶችና በሴቶች ግንኙነት መካከል ባለው ግንኙነት በከፊል ሊሆኑ
ይችላሉ፡፤ በሰዎችና በእንስሳት ምርምር ላይ የበታችነት ደረጃ ከማህበራዊ ውጥረት ጋር
ካለው ከፍተኛ የስነ-ልቦና ምልከታ ጋር የተቆራኘ ነው፤ በእርግጥም፣
ባለትዳሮች ከባልደረባዎቻቸው ጋር ክርክሮችን ይበልጥ ስነ-ምልልስ ማሳየት ይችላሉ፤ ባሎችም ሆኑ ሚስቶች ከትዳር ጓደኛቸው ለውጥ ለማምጣት በሚፈልጉበት ጊዜ ለክርክር ይጋለጣሉ። በትዳራቸው
ግጭት የሴቶች ከፍ ያለ የመጠቁ ምላሽ ምክንያት በትዳር ውስጥ ያላቸውን አንጻራዊ የበታች ቦታ ሊሆን
ይችላል።
የጤና መለካት
በጋብቻው እና በጤና መካከል ያለው ትስስር የተለያዩ ውጤቶችን ያካተተ ነው። እነዚህም በክሊኒካዊ የመጨረሻ
ደረጃዎች ምትክ የመጨረሻ ደረጃዎች፣ እና ባዮሎጂካል አማካሪዎች ሰፋ ያሉ ናቸው። ክሊኒካዊ የመጨረሻ ግምቶች ሰዎች እንዴት እንደሚሰማቸው፣ እንደሚሠሩ፣ እና እንደሚኖሩ የሚወስኑ ልዩነቶች
ናቸው፤ በጤና አጠባበቅ አቅራቢዎች እና ታካሚዎች እንደ ወሊድ ሆስፒታል ወይም የልብ
ድካም ሊኖራቸው ስለሚገባው አስፈላጊ ውጤት ይታወቃሉ።
ምትክ ኤንድፓይንተስ ና ባዮሎጂያዊ መካከለኛ መደበኛ ወይም ከተወሰደ የመጠቁ ሂደቶች ባዮማርከርስ-ተጨባጭ
አመልካቾች ዓይነቶች ናቸው። እነዚህ ሳይንሳዊ ማስረጃ ላይ የተመሠረተ ክሊኒካዊ ኤንድፓይንትስ፣
ለመተንበይ ይጠበቅባቸዋል። ለምሳሌ ያህል፣ ከፍ ያለ የደም ግፊት የልብ ሕመምና ለመተንበይ ተገኝቷል።
ባዮሎጂካል ሸምጋዮች በተደጋጋሚ በማንቀሳቀሱ ምክንያት የጤና ውጤትን የሚነኩ አጫጭርን የውጥረት ምንጮችን
ያንፀባርቃሉ። እነዚህ ሂደቶች ወደ ክሊኒካዊ የመጨረሻ ደረጃዎች ጋር የሚያገናኟቸው በቂ
ማስረጃዎች ስለሌሉ ወደ ምትክ የመቁጠሪያ ክፍሎችን ከፍ ለማድረግ ይረዷቸዋል። ምሳሌዎች የሆርሞን መጠን ለውጥ ወይም የበሽታ መከላከያ መለኪያዎች ለውጥን ያካትታሉ።
የጤና አገናኞች
ምርጫ እና ጥበቃ፦ የጋብቻ ጤና ጥቅሞች ከሁለቱም የመከላከያ ውጤቶች ውጤት ናቸው። የተሻሉ ጤንነት ያላቸው ሰዎች፣ ተጨማሪ ሀብቶች ያላቸው ሰዎች ለማግባት የበለጠ ዕድል አላቸው፤ እናም
ጋብቻ ሀብቶችን እና ማህበራዊ ድጋፍን ያመጣል። የጋብቻ ጥቅም ጤናን እንደሚጠብቅ ነው
ያገባ ስው ጤናው የተጠበቀ ነው።
የመሃበራዊ የሁለቱ ሞዴሎች ድጋፍ
ስለ ጋብቻ እና ጤና ጥናት ማሕበራዊ ግንኙነቶች ጥቅሞች ላይ ሰፊ ጥናት በማድረጉ
ሂደት ውስጥ አንዱ ነው። ማህበራዊ ትስስር ማንነት፣ ዓላማ የሌላው ድጋፍ ስሜት ጋር ሕዝቦች ይሰጣሉ። ሁለት
ዋና ዋና ሞዴሎች ምን ያህል የማህበራዊ ድጋፍ ተጽዕኖ ጤና ይገልጻሉ። በጋብቻ ላይ ጤናን በተመለከተ የተደረጉት ጥናቶች ከብዙዎቹ ጥናቶች
አንዱ ሲሆን የሚጠቅመውም ለማህበራዊ ግንኙነት ነው። በጋብቻ ውስጥ የመሃበራዊ ትስስር የማንነትን ስሜትና አላማን በማህብራዊ ህብረተስብ
ውስጥ ያለውን ትስስርና መታቀፍ ያካትታል። እነዚህም ሁለቱ ሞዴሎች ማህበራዊ ድጋፍ በጤና ላይ የሚያስከትለው አሉታዊ ተጽዕኖ ያሳድጋል።
ዋናውና አይነተኛው የሞዴሉ ተጽዕኖና አላማ ማህበራዊ ድጋፍ
ለተጋቢዎች ጤናቸውን በተመለከተ አስተዋጽኦ በማንኛውም መልኩ በስትሬስ ውስጥ የሚያደርገው ድጋፍ ነው። ሌላው ማህበራዊ ድጋፍ
ደግሞ ተጋቢዎች የደረስባቸውን አሉታዊ ተጽዕኖ ከጋብቻቸው ውጪ ለሚደርስባቸው የሚደረገው ማህበራዊ ድጋፍ ወይም እርዳታ ነው።
ውጥረት ላይ አሉታዊ ተጽእኖን ለመከላከል ማህበራዊ ድጋፍ ይሰጣል። ሁለቱ ሞዴሎች ማህበራዊ ድጋፍ እንዴት እንደሚቀየር እና
እንደሚለካው ይወሰናል። ሁለቱም ሞዴሎች
ማህበራዊ ትስስር በእውነታዊ ተጨባጭ እና በተገቢው ሁኔታ ላይ በመመስረት በእውነተኛ ድጋፍ ይደግፋሉ. ጋብቻ በሁለቱም ሞዴሎች ውስጥ የማህበራዊ ድጋፍ ምንጭ መሆን አለበት።